ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አተላው ይደፋ !

የዘረኝነት ጉሽ ፣
. . . . . . ያሰከረው ትውልድ ፤
አንጎሉ እንደዞረ ፤
አንጀቱ እንዳረረ ፤
. . . . . . ቀኑን ከሚገፋ ፤
ጋኑን አለቅልቆ ፣ አተላውን ይድፋ ፡፡

ዶ / ር በድሉ ዋቅጅራ
@getem
@getem
@Yeaseratfere
" ከስዕሉ ጀርባ "
( በአምባዬ ጌታነህ )
ለመክሊቱ መቅድም አይኑ እያማተረ፣
አንዴ መምህሩን አንዴ ተማሪውን እየቀያየረ ፣
በምትሀት እጆቹ ቁጭ አርጎ እያኖረ፣
ክፍል ውስጥ ተቀምጦ ፦
ስዕል ብቻ ሚስል አንድ ልጅ ነበረ።
ከእለታት ባንድ ቀን መምህሩ ሲዞር "ደብተርህን "ሲለው፤
ደብተሩን አሳየው።
የስዕል ደብተሩን የሰጠኝ ነው መስሎት፣
መምህሩ ደንግጦ
"ሌላ ደብተር" አለው፣
ሌላ ደብተር ሰጠው፣
ይህንም ቢገልጠው፣
ስዕል ብቻ ሆኖ እሱ ያፃፈውን ኖት ማየት ናፈቀው።
....
ወደ በሩ በኩል እጁን እየጠቆመ "ውጣ ከዚህ "አለው።
ልጁን አስወጥቶ ደብተሩ ላይ ባሉ ስዕል አፈጠጠ፤

<ስዕል ፩>

ሀገር የሚረከብ ሀገርን የሚቀርፅ
ትውልድን ለማነፅ
ደፋ ቀና የሚል ከጠመኔው ጋራ የተመሳሰለ፣
ኑሮ ያንገላታው ትጉህ መምህር አለ።

<ስዕል፪>

የመምህሩን መኖር
ከመጤፍ ሳይቆጥር
ስልክ ሚጎረጉር
ፀጉሩን በጣቶቹ እያፍተለተለ፣
አልፎ አልፎ መምህሩን ቀና ብሎ እያየ ከሱ ጋራ መስሎ ከእሱ ጋ የሌለ፣
የአርሴናልን ማሊያ የለበሰ ወጣት አንድ ተማሪ አለ።

<ስዕል ፫>

በተደፋ ኩሏ የተንሸዋረረች፣
ያለ እረፍት ከንፈሯን እያሸራመጠች፣
ተገላልጣ ለብሳ ሳትታይ የቀረች፣
በስተመጨረሻ ተስፋ የቆረጠች፣
የምትቁነጠነጥ አንዲት ሴት ልጅ አለች።

<ስዕል፬>

መምህሩ ሚለውን ከአፉ እየነጠቀ እየተከተለ፣
በደብተሩ ሚያስቀር ትጉህ ተማሪ አለ።

<ስዕል ፭>

የመምህሩን መውጫ ስአት የናፈቁ፣
ቁራጭ ወረቀት ላይ በተፃፃፏቸው ቃላት የሚስቁ፤
በወንበሩ አሻግረው እግርና እግራቸውን እያነባበሩ፣
ፍቅር ሚጀምሩ፣
በብርድ የሞቃቸው እሳት ልጅ ነበሩ።

<ስዕል ፮>

በዛ በኩል ደግሞ፣
ሁሉንም ተማሪ እያየ በአርምሞ፣
በድርጊቶቻቸው ከልቡ ተገርሞ፣
" ልሳላቸው ብሎ እየሳለ ሳለ "
ድንገት መምህሩ አይቶት ወደ እሱ መጣና፣
" ስዕል ከምትስል ለምን አትማርም
በኋላ ሳትማር ለወላጅ ለሀገር ከምትሆን ሸክም?
ብትከታተለኝ ሳይሻል አይቀርም፣"
የሚል መምህርና የተማሪው ምስል
በስዕሉ ይታያል።

ከዛም መምህሩ
ይህን ሁሉ ስዕል ተመለከተና፣
"ያለ መክሊቱ ነው የሚማረው?" ብሎ ከልቡ አዘነና፣
የስዕል ስድስትን- መምህር ተግባር ወስዶ፣
" ና ግባ" አለው ልጁን የጥል ግምቡን ንዶ።
ይህን ሁሉ ምናብ በስዕል መስሎ በስንኝ ሚሰድር፣
ከስዕሉ ጀርባ ሳይ ገጣሚ ነበር።

09/06/2011ለሊት 10:24

@getem
@getem
@gebriel_19
ነገ ቅዳሜ 6 ሰአት በመዘጋጃ ቴያትር ቤት "ሰው መሆን "የፊልምና የቴያትር ብሮዳክሽን የሚያቀርበውን የኪነ-ጥበብ ዝግጂት ትታደሙ ዘንድ በአክብሮት ጠርተነወታል

!!!በእለቱ የሚቀርብት ስራወች!!! ---------------------------------------
ቴያትር በሰው መሆን
ድስኩር በመጋቢ ሀድስ እሽት አለማየሁ
ግጥም በገጣሚ በሀብታሙ ያለው
ወግ በተዋናይና ደራሲ ፍቃዱ ከበደ
ወግ በሰው መሆን በረድኤት ተስፋየ
እድሁም በተጋባዥ እንግዳ ደራሲና ገጣሚ አያልነህ ሙላት ሌሎችም ስራወች ተውበን ለመቅረብ ዝግጂታችንን ጨርሰናል። እናተስ???

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
አባት´ማ

እነሱ ካንተ እኩል ወንድ መባላቸው
እነሱ ካንተ እኩል ስም መሰጠታቸው
ለኔ ከዚያም በላይ ለእኔ ከአባት በላይ
አሁንም ላውራልህ ወጥቼ አደባባይ
ባይበላም ባይጠጣም ባይገባ ከቤት
ከደጃፍ ቁጭ ሲል ደስ ይላል አባት
አሁን ነው የገባኝ እንዲያ የሚሉት ተረት
እረ ለመሆኑ .. ለእነሱ ወንድ ብሎ ስም ያወጣላቸው
ከአንተ ከአባቴ እኩል ያረጋቸው

እናም የኔ ቆንጆ እናማ የእኔ ክብር
ሞተሀል ተብሎ ስገኝ በአንተ ቀብር
አላመንኩም ነበር
ግን ....ግን....
አሳመነኝ ጊዜ አሳመነኝ አመት
ካንተ ተለይቼ ብቻዬን ኖርኩበት
ካንተ መለየቱ አንድንም ትልቅ ቅዠት
አንድም ትልቅ እውነት
አባት ማለት ስሙ ለአንተ ቢያንስብም
የወንድነት ልኩ አባት ስለሆነ
አባዬ ስላልኩህ አንተም አልከፋህም

ላላገኝህ ሄደህ ዘመናት አለፉ
ቀናትና ሰከንድ በፍጥነት ከነ ፉ
ከህልሜ ባንኜ ህልም ባደረኩት
ቅዠቴንም ትቼ እውነት ባስመሰልኩት
ያንተን አለመኖር መኖር ከተባለ
እንደው በለወጥኩት

እኔ ግን ያመኛል
ወንዶች የተባሉት ካንተ እኩል ሲጠሩ
በለምለም ሜዳ ላይ ገለባ እየዘሩ
እናማ
ወልዶ ማሳደጉ ወንድ ሆኖ መፈጠር
የአባን አባትነት አያክልም ነበር

እናም የኔ አባት እናም የኔ ቀለም
በስጋ ባትኖር ብትርቅ ከዚህ አለም
ከትዝታችን ላይ የረ ሳሁት የለም

አባት ማለት ለእኔ ስኖር በዘመኔ
፻(100)አለቃው ይትቤ
የአንገት ማህተቤ
የ የ ቀን ክታቤ
ለዛሬው ማንነት መ ሰረት የሰጠኝ
ለእኔ እሱ ነው አባት በዚህ ምድር ስገኝ።

(ነፃነት ይትባረክ)

@getem
@getem
@gebriel_19
​አትላስ የግሪኩ፣ አትላስ መለኮቱ፣ ምድርን ስላዘለ
ሲዘከር ጉብዝናው፣ ሲወደስ መጠሪየው፣ ፅኑ እየተባለ።
የኔ ስስ ትከሻ ምን ተብሎ ይጠራ
ተሸክሞ ሚኖር ምድርን፣ ከአትላስ ጋራ ?

(በእውቀቱ ሰዩም )

@getem
@getem
@paappii
ሃሎ የበግ አምላክ

ፋሲካ ደረሰ ፣
በግ ሁሉ አለቀሰ ፣
ሕዝቡ ይስለም ብሎ ፣
ለአንድ አላህ ከሰሰ ፡፡

አረፋ ደረሰ ፣
በግ ሁሉ አለቀሰ ፣
ሕዝብ ይጠመቅ ብሎ ፣
ለአንድ እግዜር ከሰሰ ፡፡

እንግዲህ ...
ፋሲካ እያለፈ ፣
አረፋ እየመጣ ፣
በደም ግብር ሰበብ ፣
በግ እሩሁን ካጣ ፣
ሠው እየታረደ ፣
በግ ነጣ እንዲወጣ ፣
ሃሎ የበግ አምላክ ...
የበግ በዓል አምጣ !!


ከ ዒሻራ መድብል
( ኑረዲን ኢሳ )

@getem
@getem
🔥1
አትሄድም ብዬ

አትኤድም ብዬ ፣
ጎጆዬን ላሰፋ ፤
ግርግዳ ስገፋ ፤
ጥሪት ላጠራቅም ፤
ጥሬ ስቆረጥም ፤

አትሄድም ብዬ ፣
የብቻ ጎጆዬን ሰው ልመጂ ስላት ፤
ቡናው ሳያከትም ፤
ካፊያው ሳያባራ ፤
... ከአጠገቤ አጣኃት ፤

በል ተከተል ልቤ ፦
ማግኘት ነበር ጣሩ ፣ ማጣት መች ይደንቃል ፤
እንኳን በጅ ያልያዙት ፣ ጥሬ ካፍ ይወድቃል ፡፡

የወይራ ስር ፀሎት
( ዶ / ር በድሉ ዋቅጅራ )

@getem
@getem
@getem
ተፈላሰፍ አለኝ

📝📝📝

ተመሰጥ ተደመም ተመልከት ተፈጥሮ
እይታህን አጥራ አስተውል በአንክሮ
ተገንጠል ተለየው ናቀው ይህን ዓለም
ቆሞ አንቀላፍቷል በቁሙ በማለም
ጠይቅ ተመራመር ግለጠው መጽሐፉን
አራግፈው መርምረው እየው ብራናውን
የአባቶችን እውቀት ባሕረ ሃሳቡን
ግባና ፈትሸው ቅኔ ማህሌቱን
ጥበብን ፈልጋት እውቀትን አስሳት
ግባ ከመድራሳው እውነትን ፈልጋት


ተነስ ተመራመር ተፈላሰፍ አለኝ
ጥልቅ ብለህ ስመጥ ግባበት አሰኘኝ
የኋላውን እውቀት የዛሬን መነሻ
የነገን አብነት መንገድ መቀየሻ
አንሳው አሞግሰው አይረሳ ከቶ
የፀና ዛፍ የለም ስሩ ተበላሽቶ
አለኝ አስታወሰኝ የህሊናው ደውል
ሊያባንነ ኝ ቢሻ ካንቀላፉ መሃል
ይህንንም ነግረውኝ ጠፉ ተሰወሩ
አነቃነው ብለው ርቀው በረሩ
መች ተረዱኝና....
አውቆ የተኛን ሰው...መሆኑን ነገሩ

🗒🗒🗒

ኪነ ዳን

@getem
@getem
@gebriel_19
ይመስለኛል ልቤ
ያመልክሽ ነበረ
ድንገት"ሰው" ስትሆኚ
ቅያሜው መረረ።
አንቺም ትክክል ነሽ....
ባልተፃፈ ራእይ
ባልተባለ ንግርት
በሚቆጠር ነገ
እፍኝ እድል ዘግኖ
እሷኑ መንዝሮ
መኖር ከተቻለ
ከመላእክት ይልቅ
ሰው መሆን ተሻለ።
(በዚ አላዝንብሽም)
ልቤም እውነት አለው.......
አፍቃሪ ልብና
የፈጣሪ ሚዛን
ይመሳሰላሉ
ከፍጡራን መሀል
ከላባ የቀለለ
ልብ ይፈልጋሉ።
(በዚ አትዘኝብኝ)

ዳኒ.B.

@getem
@getem
@gebriel_19
"ትርጉም የለሽ ፍቅር "
( አምባዬ ጌታነህ )

ሰርክ ትዝ የሚለኝ አንቺን ባሰብኩ ቁጥር፣
በሰው መጣ ፍርሀት የሳምኩሽ ቀን ነበር።
ሰይጣን የኔን እምነት ሊፈታተነው ሲል፣
አንቺን ውብ አድርጎ ፊቴ አመጣሽ ልበል!
መች ጠፋኝ ቀድሞውን አንቺ ነሽ ድክመቴ፣
በአንቺ የምትሀት ውበት፦
ስንቱን የእግዜርን ህግ ያለ ምርጫ ሻርኩት።
አንቺን በልቤ ላይ ያለ ጫና አንግሼ፣
ከነ በድን አካሌ ቤተሰኪያን ደርሼ፣
እስከ ዘጠኝ ፆሜ በዛው አስቀድሼ፣
ወደ ቤት ስመለስ፦
ድንገት በመንገድ ላይ አንቺን ካገኘሁሽ፣
"አንተቃቀፍም"የተባባልነውን በአንዴ ረሳውና ስበር እመጣለሁ በእቅፌ ላስገባሽ።
አንቺን መመኘት ነው ትልቅ ሀጢያት ህመም፣
እውነቱን ልንገርሽ በአሁኑ ሁዳዴ መራብ ነው የኔ ፆም።

▥ 10/07/2011 ▥

@getem
@getem
@gebriel_19
ተላለፉ ሲለን
**

ከመረዋው ውግረት
ከቃጭሉ ዋይታ እኩል ብንሰማም
በአንድ ደውል ድምፅ
ግለ ህሊናችን አንድ ላይ ቢደቃም
ተላለፉ ሲለን
ፊትና ኃላ እንጂ እኩል አንነቃም።

ይስማዕከ ወርቁ
ከ "የወንድ ምጥ" የግጥም መድብል

@getem
@getem
@gebriel_19
ወዳጄ ቤት አከራይን የሚያህል ገጣሚ የለም ስልህ?...ይኸው እትዬ
ሰርጓጇ ቤት እየመቱ ነው..ኳኳኳ!.."ስማ!...ትከፍል እንደሁ
ክፈል...አሻፈረኝ ያልክ እንደሁ ቤቴን ለቀህ ውጣ!!.."...(ርዕስ ነው)
(ልዑል ሀይሌ)
.................................................
ስላንቺ ልገጥም
ሐሳብ ይዤ ነበር ከልቤ ውስጥ ወጥቶ፤
ግን ቤት አከራዬ ኪራይ ሲጠይቁኝ
የቤት ኪራይ በሚል ርዕስ ተተክቶ፤
ጉዞ ጀምሬያለሁ ወደ ሌላ ግጥም፤
ላንቺ ፍቅር ብዬ
የቤት አከራዬን አሳልፌ አልሰጥም፤
.
ይኸውልሽ ዓለሜ!...
የተከራይ ዕዳ የተከራይ ጣጣ፤
በአከራይ ፍቃድ ነው
እንኳንስ ጎጆውን ፍቅረኛ የሚያጣ፤
ስለዚህ አትምጪ
ተይ ልጣሽ ግድየለም፤
አንቺ አትታወቂም
በአከራዬ ዓለም፤
.
በአከራዬ ዓለም!..
ክፈል የሚለው ነው
ረዥም ስንኛቸው፤
ተይ ራቂኝ ዓለሜ
ይምሩኝ እንደሆን አንቺን ልክፈላቸው፤
.
አውቃለሁ ውድ ነሽ..
እንኳን በወር ኪራይ በነፍስ ማትሸጪ፤
ግን እያንኳኩ ነው
የማደርገው ጠፋኝ በቃ ቤቴ አትምጪ፤
.
በቃ ቤቴ አትምጪ!
በቃ ቤቴ አትምጪ!..
ልቤን እሰጥሻለሁ
ከማይደርሱበት ላይ
አርፈሽ ተቀመጪ፤
.
ይኸውልሽ ዓለሜ!!...
እሮሮ ነው መቼም
የሚሰማው ሁሉ የፈጣሪን ጸጋ ሰው ሲያሳድረው፤
ይኸው አከራዬም
አኖርኩህ ይሉኛል በተሠጠኝ አፈር ሌላ አፈር ጭነው፤
መቼም ታውቂዋለሽ
አፈር ነው ኑሯችን አፈር ነው ልብሳችን፤
ግን መች ይረዱናል
ቤት አከራያችን፤
.
የሚያነበንቡት
ክፈል ነው ክፈል ነው ሰርክ እየተነሡ፤
በአከራዬ ድርሰት
ሰው ያንሣል ከኪሡ፤
.
እናም እኔም አለሁ
እያደር እያደር ኪሴ እየበለጠኝ፤
አንቺን ልሸጥሽ ነው
ኑሮ ይሁዳ ነው አሳልፎ ሰጠኝ፤
.
እናም!...
ስላንቺ ልገጥም
ሐሳብ ይዤ ነበር ከልቤ ውስጥ ወጥቶ፤
ግን ቤት አከራዬ ኪራይ ሲጠይቁኝ
የቤት ኪራይ በሚል ርዕስ ተተክቶ፤
ጉዞ ጀምሬያለሁ ወደ ሌላ ግጥም፤
ላንቺ ፍቅር ብዬ
የቤት አከራዬን አሳልፌ አልሰጥም፤

፳፯-፯-፳፻፲፩ ዓ.ም.
ከለሊቱ ፭:፴ ሰዓት

@getem
@getem
@getem
#የኔ ዓለም
(ማዶ)

ሰማዩ አለቅጥ - አጎንብሼም ቀርቦኝ
ምድሩም ላ'ሳቤ - ተሰብስቤም ጠቦኝ
እንደዚህ አንሼ
እንዲህ አጎንብሼ
ከ'ርጅናዬም ብሼ
ቀና ማለት ከብዶኝ - መሬት ፥ መሬት ስቃኝ
የማስተዋል ልምሻ - ዘውትር እየደቃኝ
በነበርኩኝ ጊዜ - አንቺ ብቅ ብለሽ
ሰ...ፊ መሬት ሆነሽ - ጥልቅ ሰማይ ሰቅለሽ
አዲስ ዓለም ሰርተሽ - ስላ'ረግሽኝ ቀና
( ያው ብዙ አይደለሽ-)
ግራና ቀኝ ቁሜ - አንዴ ሹመት ላፅና ...
( በእቅፍሽ ስሆን -- )
እስትንፋስሽ ንፋስ - ውበትሽ ዳመና !

ፍርድ እና እርድ
( አበረ አያሌው )

@getem
@getem
@getem
#ሽር---ሸረሪቷ

አንጀቷን ---
የተቋጨውን ከእትብቷ
ወተቷን ---
የተሾመውን ከግቷ
ወለላዋን ---
የተሰራውን በደሟ
ቅርሷን ---
ያኖረችውን በስሟ
አወጣችው ! - እያማጠች
እንደ ፈትል - እያደራች
እንደ ጅማት - እየላገች
እሷ ---
ቤተሰሪዋ ...
ብቸኛዋ ...
ኗሪዋ ...
ድምፅ የላትም ---
አትሰማም
ኮቴዋ እንኳን ---
አይጣራም
ዝም - ሽው
ሽክርክርክር ...
አቅታዋን ገትታ
መዞር
በዝምታ በጸትታ ---
መሽከርከር
ያለ ተራዳ ---
ድንኳን ማቆም
ያለ ካስማ ---
ቱሻ ማገም
ትንፋሽ የለ ---
ወይ ኮሽታ
ጣሪያ ማድራት ---
በዝምታ በጸትታ
ወራጀ የለ ---
ባለ ማገር
በጸጥታ ---
ትንፋሽ መስበር ...
ጣሪያ ሠርታ ---
መሽከርከር
ግድግዳ ሠርታ ---
ሳትወጥር
ሽር - ሸረሪቷ ---
ኃያል ጥበቧን ሰጥታ
አጀብ ዘመኗን ፈጅታ ---
ሽር --- ሸረሪቷ
ላንዲት መዓልት ቆይታ
አዲስ ቤቷን ሰርታ
ሽር --- ሸረሪቷ ---
ሁሉን ነገር ረስታ ...

ሚያዚያ ---- 1977
የማለዳ ስንቅ
(አበራ ለማ)

@getem
@getem
ይድረስ......
ንጉሱም እንዳይከሰስ
ከሀሳብ እጅጉን ርቆ
ሰማዩም እንዳይታረስ
ከጠፈር ባንድ ሸምቆ።
* * * * * *
ይህ ምስኪን
ሆድ የባሰው ህዝብ
የሚላስ ሚቀመስ ያጣው
ስምክን በየአድባሩ ጥግ
ሰርክ ከሚያሳቅለው
አቤቱ ፈጣሪያችን ሆይ
ንጉሱን ባትችል እንኳ
ሰማዩን ትንሽ ዝቅ አርገው።
ዳኒ.B

@getem
@getem
# የመሸባት……..
ትላንት ዛሬን ወልዶ
ዛሬም ነገን ናፍቆ
እየተያያዙ ሲጉአዙ ሲጉአዙ
ሲሄዱ ሲነጉዱ
ቆሜ አሳልፌአቸው
…………………………….
ቁጭ ብዬ ሳያቸው
ይተባበራሉ ይከባበራሉ
ሰኞ ከማክሰኞ
አሮብም ካሙስ ጋር
አብረው ይሄዳሉ
ይፍጣጠራሉ ይወላለዳሉ
እነሱም እንደ ሰው
ያድጋሉ ይሞታሉ
###################
ይህንን የምልህ ምለፈልፍብህ
ልሰብክህ አይደለም ጊዜን ላስተምርህ
እኔው ተገርሜ ተደንቄ እኮ ነው
አንተን ላማክርህ ያኔን ላስታውስህ
*
*
*
አስታወስከው አይደል ያኔ ያልኩትን ጊዜ
ያበዛው ስህተቴን ያስቃኘኝ ትካዜን
የፍቅሬን መግለጫ ፊደል ምመርጥልህ
ኢሜል ምልክልህ
በ ቀን አስር ጊዜ በ ስልክ ማወራህ
ላግኝህ እያልኩኝ የምጨቀጭቅህ
አስታወስከው አይደል…….
የረፍትህን ጊዜ
ያቺን ቅድስት ሀሙስ ብዬ የሰየምኳትን
በናፍቆት በጉጉት ሁሌ ምቆጥራትን
ነገ እኮ ሀሙስ ነው እያልኩኝ ለሁሉም የማወራላትን
###############################
ታድያ…………………………………………………..
###############################
ለማንስ ላካፍለው ይህንን ስህተቴን
ለማንስ ላውርሰው ይህን ነጩን ጸጉሬን
የተጨማደደው ያረጀውን ፊቴን
ሸካራውን እጄን
ፍለጋ ያደከመው የጠቆረው እግሬን

ላንተ!
ለልጆችህ !
ወይንስ ለራሴው!
በ ቤዛዊት ከበደ

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
የፋኖ ፍቅር

ሰይፍ ከሰይፍ እየተፋጨ ፣
ሕይወት ባረር እጅ እየተዳጨ ፣
ሞት በጥይት አፍ ሰክሮ እያፏጨ ፣
ጨበጣ ውጊያ ቀውጢ ሲጀመር ፣
ጉንፋን ይዞኛል ያልሽኝን ነገር
ላንቺ እየሰጋው ሳስበው ነበር ፡፡


ኑረዲን ኢሳ

@getem
@getem
@getem
አተላው ይደፋ !

የዘረኝነት ጉሽ ፣
. . . . . . ያሰከረው ትውልድ ፤
አንጎሉ እንደዞረ ፤
አንጀቱ እንዳረረ ፤
. . . . . . ቀኑን ከሚገፋ ፤
ጋኑን አለቅልቆ ፣ አተላውን ይድፋ ፡፡

ዶ / ር በድሉ ዋቅጅራ

@getem
@getem
@getem