ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አንድ ሎሚ ግጥም
።።።።።።።።።።።።።።
አልገባኝም ነው ያልሽው?
"ሀምሳ ሎሚ ለመልቀም ሀምሳ ዛፍ አይተከልም
ሀምሳ እግር ወይን ተክሎ አንድ ሎሚ ማግኘት አይቀልም!"
ይኼ ምኑ ይከብዳል
"አንዴ የተከልሽው ሎሚ ዛፍ እልፍ ሎሚዎች ይወልዳል!"
ይኼ ምኑ ይከብዳል?

ሎሚ እኮ መድኃኒት ነው፣ ምንሽን ነበር ያመመሽ?
ሆምጣጤ ሻጩ በሙሉ ልጣጭ አብልቶ ያከመሽ?
የተከልሽው ሀምሳ እግር ወይን፣ ምኑ ላይ ምን አበቀለ?
ሀምሳ ዛፍ የያዘው መሬት፣ ለሎሚ ምነው ቀለለ?
ጥያቄ በዛብሽ መሰል¡
ከተከልሽው ሀምሳ እግር ወይን፣ ስንቱን እንደጠጣሽ ባላውቅም
(ቅርጫቱን ወደሻል አሉ)
የያዝሽው የሎሚ ቅርጫት፣ እመኚኝ ከሎሚ አይልቅም።
እንደው በራሳችን ሞት
በመቶ ሚቆጠር ሎሚ የሚይዝ ቅርጫት ታቅፎ
ተሸካሚውን ባፍጢሙ ድንጋይ ቢደፋው አንቅፎ
ከተሸከመው ቅርጫትና ቅርጫቱ ከያዘው ሎሚ
የቱ ነው ፈውስ የሚሆነው?
"..." ይበቃል መልስ አትድገሚ።

የሰማይን ደጃፍ አንኳኪ ያለምም ጫፍ ድረስ ሂጂ
ስለዋጋ ምንም አይከብርም ስለያዘው ዐላማ እንጂ።
ግጥም ርካሽ ነው አልሽ???
ጣትሽን ያንሻፈፉቱ ሙጃሌውና ሰንኮፉ
አልቅሰው ደም እየረጩ ተነቅለው የተራገፉ
ንገሪኝ በምን ነበረ
"በሰላሳ ሳንቲም መርፌ!"
ካንቺ ጋ ከምከራከር ግጥሜን ብጽፍስ አርፌ።
ቆይ አንዴ...

ሎሚውን ስለመርከሱ ስለዋጋው እያቃለሉ
በየማሳቸው መካከል አብዝተው ወይን የተከሉ
የሚሸከሙት ሸክማቸው ባዶ ቅርጫት ነው አሉ።
(መቼም አንቺም አታጪው
የሸክም ትርጉም ለጠፋው ሸክም ሸክምን ይወልዳል
በቃ ሀቁን አፍርጪው
ባዶነት ከባዶ ስም ጋር ይቀላል ወይስ ይከብዳል?)
ሺህ ጊዜ ወይን ቢወደድ ሺህ ጊዜ ቢናፈቅ ስካር
"ወይን ለልብ አይሆንም" የሚልሽ ታጫለሽ መካር?

ግጥም ርካሽ ነው አልሽ???
ዘመኑ የሚሉበት ነው ሁሉ ይባላል በቀላል
ከፍ የሚል ከክብሩ ወርዶ ዝቅ የሚል ላይ ይሰቀላል።
በሽታው ከቶ ላልገባው ፈልጎ ላልደረሰበት
ህመሙን ላራከሰ ነው መድኃኒት የሚረክስበት።
በቅድሚ ህመምሽን ለዪ!
ከዛ ግን አክብረሽ ያዢው እንደ ወይን እንደ አበባው
የመድኃኒቱ ዋጋ ላይ ያኔ ነው የምንግባባው።
አሁንስ አልገባሽም ወይ? ነው ወይስ ሽንፈት ያስፈራል?
አየሽው የግጥም አቅም
በስካር ሳይወላከፍ አደባባይ ላይ ይደፍራል።

ወይንሽን የተካፈለሽ ከስካር ጦስ ስላልዳነ
ማንም ሰው ደፍሮ አልነገረሽ ቅርጫትሽ ባዶ እንደሆነ።

@getem
@getem
@paappii


Yedil tizazu
Fight autism home teacher for autistic children በኦቲዝም ለታመሙ ልጆች ብቻ:

በኦቲዝም ለተጠቃ/ች ልጅ ድጋፍ፣ ክትትል እና የቤት ዉስጥ ትምህርት ይፈልጋሉ?
ኦቲዝም ምንድን ነው?
ኦቲዝም በህፃናት/ልጆች የነርቭና የእድገት ሂደት ላይ ውስንነትን በማስከተል ልጆቹ ከሰዉ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነትና የመግባባት ክህሎት እንዲሁም የመረዳት ችሎታ የሚጎዳ/የሚቀንስ ህመም ነዉ።
ኦቲዝም ለሁለንተናዊ የህፃናት/የልጆች እድገት አስፈላጊ የሆኑ ማህበራዊ ግንኙነቶችን እንዲሁም የልጆቹን ግለሰባዊ ባህሪያቶች ይጎዳል።
መፍትሄው ምንድን ነው?

ምንም እንኳ እስከ አሁን ድረስ ኦቲዝምን ፈፅሞ ሊያድን የሚችል ህክምና ባይኖርም ልጅዎ ላይ የሚታዩትን የህመም ምልክቶች በመቀነስ የልጅዎን እድገትና የትምህርት አቀባበል ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል።
ይህንንም የልጁ/ቷን ማህበረዊ፣ የመግባባት ክህሎትና ባህሪ ላይ አትኩረው በሚሰሩ ባለሙያዎች በሚተገበሩ ተከታታይ እና የተዋጣላቸዉ መርሃግብሮች ማሳካት ይቻላል።
ከምንሰጣቸው ድጋፍ፣ ክትትል እና ትምህርት መካከል፦
የመግባባት ክህሎት፦ የኦቲዝም ተጠቂ ልጅን የማህበራዊ እና የቋንቋ ችግሮች ላይ በመሥራት የመግባባት ክህሎትን ማጎልበት።
የባህሪ ለዉጥ፡- የኦቲዝም ተጠቂ ልጅ ሊኖሩት/ዋት የሚችሉትን አስቸጋሪ ባህሪያትን በመቀነስ እና መልካም ሥነምግባርን በማስረፅ ተፈላጊ የባህሪ ለዉጥ ማምጣት።

ትምህርት፡- ኦቲዝም ላለባቸዉ ህፃናት በጥናት በተቀረፀ የትምህርት መርኃግብር እና ለዚሁ አላማ በተዘጋጁ የትምህርት መርጃ መሳርያዎች በመታገዝ የቤት ውስጥ ተጨማሪ ትምህርት በመስጠት የልጆቹን የትምህርት አቀባበል ማሳደግ።

ቤተሰብ ተኮር ድጋፍ፡- ወላጆችና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት የኦቲዝም ተጠቂ ልጅን የመግባባት ክህሎት እና ችግሮችን የመፍታት ችሎታ ለማዳበር በምን መልኩ መቅረብ እና አብረዉ መጫወት እንዳላባቸው ማስተማር።

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ይደውሉ፦
0913011134
0910916602

@wegoch
@gebriel_19
Audio
ገጣሚ ፡- ታገል ሰይፋ
ስሙልኝ በሞቴ
#አስቂኝ

አዘጋጅ ፡-
@getem
@getem
Belay Bekele Weya
"እእፓ"(እኛው እንታረቅ ፓርቲ)
(በላይ በቀለ ወያ) # ሼር ይደረግ!
.
.
ከኛ ካልቀደሙ ፣ ምንከተላቸው
ለኛ ካላሰቡ ፣ ምሁር ምንላቸው
ከኛ የተሻለ
ማየትን ካልቻሉ ፣ እኛን የሚመሩን
ለእርቅ ያጨናቸው ፣ በፀብ ካቃቃሩን
አንድ አርጉን ያልናቸው
በብሔር ፣ በክልል ፣ ከፋፍለው ካጠሩን
ህልውናችንን
አምነን ምንሰጣቸው ፣ ለኛ ካለሰቡ
እኛን እንደማስፋት ፣ ቀድመው ከጠበቡ
ትውልድን ከትውልድ ፣ ካላቀራረቡ
አንድ ሀገር አፍርሰው ፣ መንደር ሳይገነቡ
በእኛ ላብ ሳይወዙ ፣ በኛ ደም ሳይሰቡ
እኛው እንታረቅ !
።።።
አክቲቪስቶቻችን ፣ አክቲቮች ካልሆኑ
የጎበጠን ትውልድ ፣ ጎብጠው ካላቀኑ
ለሀገር ካልቆሙ ፣
ሚከተላቸውን ፣ ወድቀው ካላፀኑ
እኛ አለንላቹ ፣ እሚሉን ከሌሉ
እንድንጠፋፋ ፣ ነገር ከፈተሉ
ቂም የቋጠረውን ፣ ማስታረቅ ካልቻሉ
ያለፈን ጠባሳ ፣ ነቅሰው ካልኳሉ
ለተቋሰልን እኛ ፣ ከኛ ካልተሻሉ
ቁስልን እንደማከም ፣ ቁስልን ከነካኩ
ሰላም እንደመስጠት ፣ በፀብ ከተመኩ
በኛ ላብ ሳይወዙ ፣ በኛ ደም ሳይረኩ
እኛው እንታረቅ።
።።።።
ነፃ አውጪ ነን ባዩ ፣ ጭቆናን ካመነ
ነፃነት ከነሳን ፣ በውሀ ቀጠነ
በታመሙ ህዝቦች
ለታመች ሀገር ፣ መድሐኒት ካልሆነ
ፈውስ መሆን ሲችል ፣ መርዝ ከቀመመ
ለመረዙት ትውልድ ፣ መርዝ ሆኖ ከቆመ
ስላም ለናፈቀው ፣ ሽብር ከሸለመ
ከኛ የተሻለው ፣ ለእኛ ካልጠቀመ
ለእኛ የታገለው ፣ ለእኛ ካልተገዛ
በሀገር ፍቅር ፈንታ
በሀገር ላይ ጥላቻ ፣ አትሞ ካባዛ
በእኛ ደም ሳይረካ ፣ በኛ ላብ ሳይወዛ
እኛው እንታረቅ።
።።።
የፖርቲዎች ብዛት ፣ ሀገር ካላፀና
ለሚነታረክ ህዝብ ፣ ካልሰጠ ፅሞና
ከኛ የተሻሉ ፣ ለእኛ ተደራጅተው
ከእኛ ቁጥር በላይ ፣ ፓርቲዎች መስርተው
ካላስተቃቀፉን ፣ በሀሳብ ተጣልተው
እኛን ሚወክሉ
ከእኛ ካልተሻሉ
ሸክም ሳይሆኑብን ፣ ሸክም የሚያቃልሉ
በእኛ ደም ሳይፈኩ ፣ በእኛ ደም ሳይጎሉ
እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች ፣ ያለ አንዳች ውከላ
"እእፓ" ሚል ፓርቲ ፣ መስርተን በመላ
እኛው እንታረቅ! ፣ እኛው ስንጣላ።

@getem
@getem
@getem
👍1
*ሰዎች ይገርመኛል*

ልቡን ከአባይ ማዶ በረሀ በልቶበት
ከቀዝቃዛው ከኛ መንደር ተቅበዘበዘት
በአርምሞ ብቃኘው ለኔ ያለው ፍቅር አናት
የበኩር ፍቅሩ ትዝታዋ አለበት
ወይ አለመታደል
ፀጉር በሌለበት ለሚዶ መጋደል፡፡



ብሌን አሰላ

@Getem
@getem
@gebriel_19
**** እኔ አንተን ስወድህ****
ልክ እንደ ጠዋት እንቅልፍ
ሰመመን የቃጣው
በአእዋፍ ዜማ የታጀበው
የካህናት ወረብ
ፅናፅል የሞላው
ልክ እንደ ሰማይ ጥግ
ፈክቶ እንደሚበራው
እንደ ምስራቅ
ሰማይ ጨረር የጋረደው
እንደ አዲስ ተስፋ
፣፣፣እኔ አንተን ስወድህ፣፣፣

እንደ ቀትር ፀሀይ
ውሎ እንደሚጣፍጥ
የማለዳ ጀምበር
ለመምሸት የሚያምጥ
እንደ ምሳ ሰአት
ደግሞም እንደ መቅሰስ
አንድ ላይ አጣምሮ
ጉራሽ እንደመቅመስ
ልክ እንደዛ ምሳ
ፍቅር እንደሞላው
የአብይ ፆም ውሎ
አስሮ እንዳሰቃየው

።።።እኔ አንተን ስወድህ።።።

አብረን እንደመሳቅ
ደግሞም እንደማልቀስ
የአንድነት ዋዜማን
አብረን እንደመቁረስ
ምሽት ላይ ተጋግዘን
ዘመን እንደመድረስ
በእሳት በውሀ
በባህር መዋኘት
በውህደት አለም
ባንድ መገናኘት
ምድር ስትሞሸር
ፅሀይ ስትዘቀዝቅ
ኮከቦችን ማየት
ጨረቃንም ማድነቅ
እኔ አንተን ስወድህ
ጠዋትና ማታ ሁሌ ማስታውስህ

ምሽት4:25 አ አ

Jerry dimple

@getem
@getem
@gebriel_19
ስትሻኝ ነይ በለኝ
ስትሻኝ ነይ በለኝ
ያንተው ከርታታ ነኝ
እዚህ ነይ እዚያ ነይ
ብትለኝ እኔ አለው
ሁሌም ካንተ ውጭ
ማን አለኝ እላለው፡፡
አገልጋይህ አርገኝ
ከእግርህ ስር አጎንባሽ
እህሉን ከአፍህ
እኔ ልሁን አጉራሽ፡፡
ውሀውን በተራ
በኔ እጅ ተጎንጨው፡፡
ያንተ እጅ አይንካ
ምንም አያምርበት ፡፡
ይልቅስ ባንተ እጅ እኔን እቀፍበት
ያንተ እጅ አይንካ
ምንም አትስራበት እኔን እቀፍበት፡፡

#ሄርሜላ_ውብሸት

@getem
@getem
@gebriel_19
ሦዕል ለማሳል
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 order ማድረግ ይቻላል።

ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ!
@seiloch
@seiloch
ይፍታ

መላ ያጣ ላጤ የላጤ ደንቆሮ
ውሉ የጠፋበት የመላ ቋጠሮ
ድመቱን አልጋው ላይ በገመድ ጠፍሮ
አይጥ ያሳድዳል ሊገላት አባሮ
ላ'ይጥ ዱላ ይዞ እቃ ከሚመታ
ስራዋን ትስራበት ድመቲቱን ይፍታ ፡፡

ከ የአገጭ ጢሞች መድብል
(በለው ገበየው)

@getem
@getem
@gebriel_19
ሃሎ የበግ አምላክ

ፋሲካ ደረሰ ፣
በግ ሁሉ አለቀሰ ፣
ሕዝቡ ይስለም ብሎ ፣
ለአንድ አላህ ከሰሰ ፡፡

አረፋ ደረሰ ፣
በግ ሁሉ አለቀሰ ፣
ሕዝብ ይጠመቅ ብሎ ፣
ለአንድ እግዜር ከሰሰ ፡፡

እንግዲህ ...
ፋሲካ እያለፈ ፣
አረፋ እየመጣ ፣
በደም ግብር ሰበብ ፣
በግ እሩሁን ካጣ ፣
ሠው እየታረደ ፣
በግ ነጣ እንዲወጣ ፣
ሃሎ የበግ አምላክ ...
የበግ በዓል አምጣ !!


ከ ዒሻራ መድብል
( ኑረዲን ኢሳ )

ማንኛውንም እንዲለቀቅላችሁ ምትፈልጉትን ግጥም ላኩልን!
@gebriel_19

@getem
@getem
ገንዘብ ግን የማነው??

ሁለት ሀሳብ ሆኜ ብዕሬን አነሳው
ጥያቄ ልጠይቅ እየተሰናዳው
ገንዘብ የእግዚአብሔር ወይስ የሴጣን ነው
የሚለው ጥያቄ ውስጤ ተመላልሶ
ሰላም እየነሳኝ ከአይምሮዬ ደርሶ
ብዙ ጊዜ አስቤ መፍትሄ መጣልኝ
መልሱን ላድማጭ ብዬ ይሄን ግጥም ፃፍኩኝ

          ገንዘብ ግን የማነው??
ገንዘብ የሴጣን ነው ብለው እያወሩኝ
ገንዘብ ስጠኝ ብዬ ፈጣሪን ለመንኩኝ
የሴጣን ነው እያሉ ፈጣሪን መለመን ስህተት ሆነብኝ
ግን ቆም ብዬ አሰብኩ እኔም ግራ ገብቶኝ
ገንዘብ ግን የሴጣን እንዴት ሆነ ብዬ አንድ ሰው ጠየኩኝ
   እሱም አንደዚህ አለኝ
ሠርተህ ያመጣኸው የልፋትህ ገንዘብ በላብህ የመጣ
አንተን ተገዢ አርጎ አይምሮህን ወርሶ ካመጣብህ ጣጣ
ለሰው ማሰብ ትተህ ለራስህም ሳትሆን
ጨካኝ ህሊና ቢስ አይምሮ የለሽ ስትሆን
ገንዘብ ሞልቶህ ሣለ ሰላም ካልተሰማህ
የሴጣን ገንዘብ ነው አይጠቅምህም ይቅርብህ
ብሎ መለሰልኝ የጠየኩት ሰው
ያለኝን ሰምቼ ሄድኩ አመስግኜው
ግን ከሄድኩበት መለስ አርጎ ጠራኝ
አንድ ነገር አለ ሳልነግርህ የቀረኝ
አለኝና ጠርቶ ወሬውን ቀጠለ
ገንዘብ የእግዚአብሔር የሚሆንበትም አንድ አጋጣሚ አለ
ሰርተህ ያመጣኸው የልፋትህ ገንዘብ በላብህ የመጣ
አንተን አለቃ አርጎ እሡ ባርያህ ሆኖ ከችግር ካወጣህ
ከራስህም አልፎ ለሰው ማሰብ ስትችል
አይቶ እንዳላየ ሰው ማለፍ ሳትችል
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ ካረከው
እሱን ነገር ለምን የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው
አለኝና ሄደ ምክሩን ጨርሶ
ግራ ያጋባኝን ጥያቄ መልሶ
ከዛም እኔ ብልጡ ያለኝን ሰምቼ
እግዜሩን እንዲ አልኩት እጆቼን ዘርግቼ
ያንተን ገንዘብ ስጠኝ መፍትሔ እንዲሆነኝ
ሰው ልርዳበትና ሰው ይደሰትብኝ::
                                      
                                               ★★★ F8 ★★★

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
Ethiopia: አርቲስት አለማየሁ ታደሰ ስለ ኢትዮጵያዊያን አንድነት እንባ እያነቀዉ ሲናገር 16k
Andafta
አርቲስት #አለማየሁ_ታደሰ ስለ ኢትዮጵያዊያን አንድነት እንባ እያነቀዉ ሲናገር

ግጥም ብቻ
🕥 10:36
💾 1.3 MB

@getem
@getem
@gebriel_19
//ማስተካከያ ፍርድ//

ባለ አንድ ጥፍር ንጉስ ፣ ግፍ እያዘነበ ፣ ሕዝብ ስላስነባ ፣
እግዜር ለንጉሱ ፣ ሲፎክት ይኖር ዘንድ ፣ እዥ እና እከክ ጀባ ፤
ሕዝቡም ለንጉሱ እጅግ ስላዘነ ፣
ፍርድ ሊያስተካክል እንዲህ ሲል በየነ ፦
" ከንቱ ነፍሱ ላትድን ፣ ባንድ ጥፍር ታካ ፣
አሁንም አሁንም ፣ ከንቱ እየነካካ ፣
እጁ መርዝ ሆኖበት ፣ ገላው እንዳይተላ ፣
አንድ ጥፍሩ ትጣል - ከጣቱ ተነቅላ ፡፡"

ከ ዒሻራ መድብል
( ኑረዲን ኢሳ )

@getem
@getem
@gebriel_19
#ድንቄም_ፃድቅ

ክብሩን ጥብያ ጥሎ ፤ በጎሳ ቀረርቶ
ከዘር ይማግጣል ፤ፍፁም ፍቅር ፈርቶ
ማ-መንዘር ሀገር ላይ ፤ ያ ሁሉ ተረስቶ
መ-መንዘር ፅድቅ ሆነ ፤በዝርዝር ተኮርቶ!

ውድነህ ተሾመ
16/06/2011

@getem
@getem
@Gebriel_19
Forwarded from SPACE COMPUTER
Forwarded from SPACE COMPUTER
🔥🔥ደረሰ🔥🔥 👍👍
በጉጉት የተጠበቀው አነጋጋሪ ቴአትር
የባህር ወጥ
አዲስ ቴአትር ለ እይታ የሚበቃበት ቀን መጋቢት 30/2011 ።
ድርሰትና ዝግጅት እሱባለው የኔነህ አልጣህ
በኤር ኦር የቴአትር ፕሮዳክሽን የቀረበ

መጋቢት 30/2011 ከ11:00 ሰአት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በታላቅ ድምቀት ይመረቃል !!!

ዘመን ተሻጋሪ ሀሳቦች በድንቅ የመድረክ ዝግጅት ተከሽነው
ፍቅርንና የሀገር አንድነትን ለማጽናት የሚከፈለውን ሀያል ተጋድሎ የሚያስቃኝ
ድንቅ የመድረክ ቴአትር

የባህር ወጥ
ጊዜ የገለጠው ክስተት
የማለዳ ኮኮቡ የትወናው ፈርጥ ካሳሁን ቦጋለ ድንቅ የትወና አሻራውን ያተመበት ዘመን ተሻጋሪ ቴአትር

ሺዎች ሊያዩት ጓጉተዋል እርስዎስ ?

ግሩም አስፋው(ኩሲ) ፣ አቤኔዜር አለማየሁ፣ ማቲዎስ ሽፈራው (ሉሉ) ፣ አሸናፊ ሀ/ማሪያም፣ኤልሻዳይ ሚፍታህ ፣ ብሩክ ሀብታሙ ተውነውበታል !!!
ኤር ኦር የቴአትር ፕሮዳክሽን

መጋቢት 30 ሰኞ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት
እንዳያመልጥዎ !!!!!

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ኡደት
""""""

ፈጣሪ ሸመነ
አንድ ሁለት እያለ ምድርን አሳመረ
ህይወትን አደለ ሁሉንም ፈጠረ
ነፍስን ከስጋ ጋር በፍቅር አቆራኘ
ለስጋ በምድር ምግብን አናኘ።
(ሰውም ይሄን ሲያገኝ)
ለእውነት መኖር ትቶ ለሆዱ አደረ
ጥጋብን ወደደ ስለ ሰው ችላ አለ
የከሲታዎች ሞት
በአንድ ቦርጭ ውስጥ ሆነ
(እንዲ ነዋ ቅሉ)
የሰው ልጅ ከእንስሳ በሀሳብ ቢልቅም
ሆዳም ሰው ሆድ እንጂ ፍቅርን አያቅም
ደፍ ደፏን ያስባል በሀሳብ አይመጥቅም
እሩቅ.... አያስብም!

*
ፈጣሪ ቀረፀ
ተፈጥሮ ላይ ጀጋኝ ሞትን አሰረፀ
በሞቱት መተኪያ ህይወትን አነፀ
በሞት ነፍስን አዛኝ ባደረጋት አፍታ
ሀዘንን አሳ'ጥቶ ሰጣት ለደስታ።
(ሰውም ይሄን ሲያገኝ)
ደስታው ቅጥ አጣና
ለስሜቱ ኖሮ ይሰፈር ጀመረ በፈጣሪ ቁና
ልኩን መያዝ ትቶ እግዜር አስከፋና
ይከተል ጀመረ የሲኦልን ዳና!

(እንዲ ነዋ ቅሉ)
የተደሰተ ሰው ልቡ ጮቤ ይረግጣል
የረጋችን ሰማይ
እግሩን አንፈራጦ አሻቅቦ ይመታል
በደስታው ሲሰክር ፈጣሪን ይረሳል
ፈጣሪን ሲረሳ
ከኔ በላይ ጌታ እያለ ይፎክራል።

*

ፈጣሪ ጠረበ
የሰውን ባህሪ ሁሉን አነበበ
ለሰው ነፍስ ማደሻ ተክልን ተከለ
በዚም አላበቃም አእዋፍን ፈጠረ
(ፈጣሪ ጠረበ)
የሰውን ባህሪ ሁሉን አነበበ
ትንሽ እንዲፈራ አውሬን አሰፈረ
ትንሽ እንዲጀግን ብልጠትን አደለ።
(ሰውም ይቺን ሲያገኝ)
በኖረው ብልጠት ላይ ጭካኔን ዘራበት
ፍቅርን ሰላም ትቶ ፀብ አበቀለበት
ብልጠቱ በዛና ግፍ ደራረበበት
ሚዛን ተዛባና ፍርድን አጓደላት

(እንዲህ ነዋ ቅሉ)
በግ በጅልነቱ ተገፍቶ እየኖረ
የፍየል ብልጥነት
ከግራ አዋላት ምንም አልጠቀመ
ምላሷም አልበጃት ጩኸት ብቻ ሆነ!

***
ፈጣሪ ጠረበ....አነፀ....ገነባ
የተፈጥሮን ኡደት ከነጋ ከጠባ
አንድ ሁለት ብሎ ፈካ እንደአበባ

(ግን ይቺን ሲያገኙ)
አንዳንድ ያልታደሉ
የፈጣሪ ፍጥረት ተፈጣሪ ሆኑ
በእግዜር ታለፉና በሰው ተፈጠሩ

(እንዲያ ነዋ ቅሉ)

በፈጣሪ ማሳ ሰው ክፉ ማብቀሉ
ረግጦ የገዛን ቆሞ መሸለሙ
ጭካኔ ያለው ሰው በሰው መታበሉ
አረም እና እህል አንድ ላይ መብቀሉ

(እንዲያ ነዋ ቅሉ...እንዲያ ነዋ ቅሉ)

አብርሃም

@getem
@getem
@gebriel_19
የተሠበረ የራቁት ፍቅር

#Johny_Debx
"""""""""፠"""""""""፠"""""""""
ስኖር የወለድኩት ሣልኖር ያልደረስኩት
ሳብ አድርጌ ጎተት መች ወጣው አየሁት
ሳምግ ስመግ ቢለኝ?
.......ኧረ ወደላይ ነው~
.......የራቁት ሩቅ ነው!

መውደድ የት መሀላው በጸሎት ለዋለ፣
በገዜ ዕርምታ ቆይ ልሂድ ና ልምጣ ዕየማለ
ደስታ ተራራ ነው ግን ደረስክ ከስሩ፣
ና ውጣ ይለኛል 'ስደርስ' ለሹሩሩ !

ፍቅር የደገሠው'
ለችግር የዳረው;
ሀሳብ ዕሷን ማየት፡
ረጅም አለንጋ የተረረ መሬት፡፡
ግና?
ግርፊያው መች ተጠላ ተኩሱ ወደታች
ጠመንጃ ወዳጅ.............. ተፈቃሪ ነች !
ታዲያ ~
ወዲያ~

ከዚህ በላይ ፍቅር
ከዚህ በላይ ችግር
ኧረ ዕንዴት ይረሳል ፣ ኧረ የት ይገኛል!
ራቅ ራቅ ስል ጅራፍ ይጠራኛል'
የራቁት ዕሩቅ ነው አጥብቀኝ ይለኛል!

@getem
@getem
@getem
****መንገደኛ******

በሀሳብ አገልግል ምኞቱን ሠንቆ
በተስፋ ጎዳና ተራውን ጠብቆ
የአለም መንገደኛ
አቀበት ይወጣል፤ቁልቁሉን ይወርዳል
ጀንበሯ ሳትጠልቅ ካሠበው ለመድረስ
ከህይወት ማዕድ ላይ ድርሻው ሊቋደስ
ሁሉም ሰው ይሄዳል ይጓዛል ይፈልሳል ........
ግና ከዚ ሁሉ የአለም መንገደኛ
ተግቶም የሚጓዘው ሌት ተቀን ሳይተኛ
ቀርፋፋውም ቢሆን ሌት ተቀን ሚተኛ
ከዚ ሁሉ ተጓዥ ደራሽ አንድም የለም
ከመጣበት አፈር ተመላሽ ነው ሁሉም።።።።፨
Zola

@getem
@getem
@gebriel_19