ከነ ገበየሁ ጎን!!!!!
ለምንድን አልተክዝ፣
ለምንድን አልቆዝም፣ እኔ አርበኛይቱ፣
የሚኒሊክ በልጅግ፤
የአድዋ ነበልባል ፣ የጧት ጠሃይቱ፣
የአሉላ ምንሽር፣
የጣይቱ ግንባር፤ የባልቻ ጉልበቱ።
ለምንድር አይከፋኝ፤
ለምን አልቀየም፤ ለምን አልቆጣ፤
"አድዋ ምኔ ነው???
ምኒሊክ ምኔ ነው????
ባፍንጫየ ይውጣ!!!!!!
ተውን አትጨቅጭቁን፤
ኳሱን እንይበት፤ ድራፍቱን እንጠጣ፤
የሚል የጉድ ጅራት፤
ጀምበር መሸኛው ላይ፤ ከኋላ ሲመጣ።
በላየ ላይ ሰፍሮ፤
በወሬ መቀነት፤
በምላስ ተከቦ፤
ታሪክ የሚሸፍጥ፤
ዘመን የሚያሳብቅ፤የዘመን ቡትቶ፤
ዙሪያየን ከቦኛል፤
ዝንጋኤ የበላው፤
እንዴት እንደቆመ፤
ማሰብ ያደከመው፤
ሃገርና ሰንደቅ፤ በደም ግብር ፀንቶ።
ምነው የጦቢያ አምላክ፤
በእድሜየ ጀምበር ላይ፤
ሃገርና ሰንደቅ፤
አፈርና ድካ፤
ቃልና መታመን፤
ሞትና ነፃነት፤
እንዴት እንደቆመ
በማይገባው ትውልድ፤
መሃል ተቀምጬ፤
መንፈሴ እየራደ፤
ወኔየ እየከዳኝ፤
በሰላቶ ምላስ፤
በባንዳዎች ሽሙጥ፤
በረከሰ ከንፈር፤
ምኒሊክ ተሰድቦ፤
ባንዳ እየገነነ፤
በጎጋ መፈክር፤
ቅስሜ ተፈርክሶ፤ አንገቴን ከመስበር፣
ሞት ይሻላል ብየ፤
ምነው አድዋ ላይ፣
ከነ ገበየሁ ጎን፣ ወድቄ በነበር።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
የዛሬ አመት እንዲህ ብለን ነበር.....የዘንድሮ አድዋ ግን ይለያል......ብዙ ሰው ላይ አድዋን ለማክበር መነቃቃት ተፈጥሯል ብዬ አስባለው....በመንግስት ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ፣ አዲስ አበባ ላይ ባሉ የተለያዩ ሰፈሮች እና በየመስሪያ ቤት እንዲሁም ከሀገር ውጪም የነገውን አድዋን ለማክበር ሁሉም ዝግጅቱን ጨርሶ ነገን በጉጉት ይጠብቃል.......ቢያንስ እስከ ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ሰው ይጠበቃል.......የሚቀጥለው አመት ፈጣሪ ካደረሰን ከዚህኛው አመት በተሻለ እንደሚደምቅ ደሞ እርግጠኛ ነኝ.......በመጨረሻም ለረጅም ጊዜ እውቅና ተነፍጎት የተነበረው የአድዋ በዓል ዘንድሮ ለድሉ በዓል እንደሚገባው ባይሆን.....ባለፋት አመታት ከነበረው ....አንፃር ሲታይ ግን እጅግ በጣም አስደሳች ነው !!!!!!!
ነገ በጥዋቱ ሚኒልክ ሃውልት ስር እንገናኝ!!!💚💛❤️
ሰላም እደሩልኝ💚💛❤️
ያስከበሩኝን አያቶቼን ሳከብር እኖራለሁ!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
ለምንድን አልተክዝ፣
ለምንድን አልቆዝም፣ እኔ አርበኛይቱ፣
የሚኒሊክ በልጅግ፤
የአድዋ ነበልባል ፣ የጧት ጠሃይቱ፣
የአሉላ ምንሽር፣
የጣይቱ ግንባር፤ የባልቻ ጉልበቱ።
ለምንድር አይከፋኝ፤
ለምን አልቀየም፤ ለምን አልቆጣ፤
"አድዋ ምኔ ነው???
ምኒሊክ ምኔ ነው????
ባፍንጫየ ይውጣ!!!!!!
ተውን አትጨቅጭቁን፤
ኳሱን እንይበት፤ ድራፍቱን እንጠጣ፤
የሚል የጉድ ጅራት፤
ጀምበር መሸኛው ላይ፤ ከኋላ ሲመጣ።
በላየ ላይ ሰፍሮ፤
በወሬ መቀነት፤
በምላስ ተከቦ፤
ታሪክ የሚሸፍጥ፤
ዘመን የሚያሳብቅ፤የዘመን ቡትቶ፤
ዙሪያየን ከቦኛል፤
ዝንጋኤ የበላው፤
እንዴት እንደቆመ፤
ማሰብ ያደከመው፤
ሃገርና ሰንደቅ፤ በደም ግብር ፀንቶ።
ምነው የጦቢያ አምላክ፤
በእድሜየ ጀምበር ላይ፤
ሃገርና ሰንደቅ፤
አፈርና ድካ፤
ቃልና መታመን፤
ሞትና ነፃነት፤
እንዴት እንደቆመ
በማይገባው ትውልድ፤
መሃል ተቀምጬ፤
መንፈሴ እየራደ፤
ወኔየ እየከዳኝ፤
በሰላቶ ምላስ፤
በባንዳዎች ሽሙጥ፤
በረከሰ ከንፈር፤
ምኒሊክ ተሰድቦ፤
ባንዳ እየገነነ፤
በጎጋ መፈክር፤
ቅስሜ ተፈርክሶ፤ አንገቴን ከመስበር፣
ሞት ይሻላል ብየ፤
ምነው አድዋ ላይ፣
ከነ ገበየሁ ጎን፣ ወድቄ በነበር።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
የዛሬ አመት እንዲህ ብለን ነበር.....የዘንድሮ አድዋ ግን ይለያል......ብዙ ሰው ላይ አድዋን ለማክበር መነቃቃት ተፈጥሯል ብዬ አስባለው....በመንግስት ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ፣ አዲስ አበባ ላይ ባሉ የተለያዩ ሰፈሮች እና በየመስሪያ ቤት እንዲሁም ከሀገር ውጪም የነገውን አድዋን ለማክበር ሁሉም ዝግጅቱን ጨርሶ ነገን በጉጉት ይጠብቃል.......ቢያንስ እስከ ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ሰው ይጠበቃል.......የሚቀጥለው አመት ፈጣሪ ካደረሰን ከዚህኛው አመት በተሻለ እንደሚደምቅ ደሞ እርግጠኛ ነኝ.......በመጨረሻም ለረጅም ጊዜ እውቅና ተነፍጎት የተነበረው የአድዋ በዓል ዘንድሮ ለድሉ በዓል እንደሚገባው ባይሆን.....ባለፋት አመታት ከነበረው ....አንፃር ሲታይ ግን እጅግ በጣም አስደሳች ነው !!!!!!!
ነገ በጥዋቱ ሚኒልክ ሃውልት ስር እንገናኝ!!!💚💛❤️
ሰላም እደሩልኝ💚💛❤️
ያስከበሩኝን አያቶቼን ሳከብር እኖራለሁ!!!!
@balmbaras
@getem
@getem
÷+÷+÷÷+አድዋ ኬኛ÷+÷+÷++÷
ውጫሌ ኬኛ ብለህ በፊርማ
ያንን ጥቁር ሰው ብታታልልም
በፍቅር እንጂ በገዛ ሜዳ
ያውም በጠላት ነጥብ አንጥልም።
ክተት የጠራን አዋጅ ያወጅነው
ልብ ሰ'ተንህ ስትመኝ ድንበር
የሀገር ፍቅር እይ ብለን እንጂ ላንተ መግርፊያ ያንተው ቀበቶ ትበቃ ነበር።
÷+÷+÷+አድዋ ኬኛ÷+÷+÷+÷+
@ሰሙ (ጠይም ሰው)
#አድዋ (የሰው ድል)
#ምኒልክ (ጥቁር ሠው)
#ጣይቱ (እመቤት)
Picture credit #BrandYard
ተጻፈ 22-06-2011
#Dire
@getem
@getem
@gebriel_19
ውጫሌ ኬኛ ብለህ በፊርማ
ያንን ጥቁር ሰው ብታታልልም
በፍቅር እንጂ በገዛ ሜዳ
ያውም በጠላት ነጥብ አንጥልም።
ክተት የጠራን አዋጅ ያወጅነው
ልብ ሰ'ተንህ ስትመኝ ድንበር
የሀገር ፍቅር እይ ብለን እንጂ ላንተ መግርፊያ ያንተው ቀበቶ ትበቃ ነበር።
÷+÷+÷+አድዋ ኬኛ÷+÷+÷+÷+
@ሰሙ (ጠይም ሰው)
#አድዋ (የሰው ድል)
#ምኒልክ (ጥቁር ሠው)
#ጣይቱ (እመቤት)
Picture credit #BrandYard
ተጻፈ 22-06-2011
#Dire
@getem
@getem
@gebriel_19
ድግስ ደግሻለው
እምዬ ኢትዮጵያ
ድግስ ደግሻለው
አንቺን ላውድስሽ
እንግዳዬ አድርጌ
በክብር ላኖርሽ
እንደ ጥንት ወገኔ
እግርሽን አጥቤ
ከመደብ ላኖርሽ
የድሮ ክብርሽን
ልመሰክርልሽ
ድግስ ደግሻለዉ
አንቺን ላወድስሽ
ለነጋሪት መቺው ሹክ ብዬዋለው
ወገንሽ እንዲጋበዝ አስጠንቅቄዋለው
ለጡሩንባም ነፊ
እንዲሁ ብዬዋለው
አንድ ሰዉ እንዳይቀር
አጥብቄ ብያለው
ሰንጋም አርጃለው
ከዳቢት ከሻኛው
በደንብ ሰድሪያለው
የጠጁንም ነገር
ለእማማ አስካለ
እንዲያው ጥዬዋለው
የጎደለኝ የለም ተዘጋጅቻለው
ክብርሽን ልመልስ
ድግስ ደግሻለው
እንድትመጪ እምዬ
አደራ ልሻለው።
ቀኑ እኮ ዛሬ ነው
ዘገየሽስ ምነው ?
የጎደለ ኖረ ያልተስተካከለ
ምነው ቆየሽብኝ ?
የዛሬው ድግሴ ለየት ያለ እኮ ነው
ክብርሽ እንዲመለስ የተዘጋጀ ነው
ለጥንቱ ከፍታሽ ምስክርነትነው
ፈራሽ እንዴ እምዬ ?
ዘገየሽስ ምነው
አጥንት ተከስክሶ
ደም ፈሶ ሜዳ ላይ
ክብርሽ ሳይነካ
ለኛ እንደደረሽን
የአደራ ሀገር የደም ዋጋነትሽን
ባደባባይ ቆሜ
ልናገርልሽ ነው
የ ዛሬዉ ድግሴ ለየት ያለ እኮ ነው
ክብርሽ እንዲመለስ የተዘጋጀ ነው
የጥንት ስልጣኔሽ
ሉአላዊነትሽ የሚታይበት ነው ።
አትስጊ እምዬ እኔ አለሁልሽ
በዚኛው ድግስ ላይ
ልጆችሽ አይሞቱም
አንቺም አታለቅሺም
ደቦ መስራት እንጂ
ደባ ሴራ የለም
የፍቅር ቦንብ እንጂ
የፈንጂዉ ቦንብ የለም
የጥንቱ ታሪክሽ
ቀዳማዊነትሽ
ዛሬ ይመለሳል አትስጊ እምዬ
ልጆችሽ ቆመናል
ይልቅስ ቶሎ ነይ
ያንቺ መምጣት እኮ ያጠናክረናል
ጥርጥር አይባሽ
የጥንቱ ታሪክሽ
ቀዳማዊነትሽ ዛሬ ይመለሳል
የአደራ ሀገር የደም ዋጋነትሽ
ባደባባይ ቆሜ ልናገርልሽ ነው
እሰይ እልል እልል ልበል ቆሜ
አውቅ ነበር እምዬ እንደማትቀሪ
በኛ በልጆችሽ እንደማጨክኝ
ድግሱ ላንቺ ነው
ክብርሽ ይገለጥ ዘንድ
የተዘጋጀ ነዉ ።
እንግዲህ እምዬ
ቃል ኪዳን ልግባልሽ
በቀይ ቢጫ አረንጓዴው
ይሀው ልማልልሽ
ሞት እንግዲህ የለም
ደም አይፈስ ሜዳ ላይ
ወገን ወገኑ ላይ
ክፋት አንዳያስብ
እጁን ላያነሳ በጎሪጥ ላያየው
ጀርባ እንዳይሰጠው
የፍቅር አርበኛ እኔ ሆንሻለው
ብዙ አርበኞችን ላንቺ አሰልፋለው
እንደ እብድ እየጮሁኩ
ፍቅርን እሰብካለው
በአረንጓዴው በቢጫው በቀዩ
ሰንደቅሽ እምልልሻለው
ሀገሬ ኢትዮጵያ
እምዬ ኢትዮጵያ
የቀድሞ ክብርሽን
እመልዋለው
እንመልሰዋለን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@getem
@getem
@getem
እምዬ ኢትዮጵያ
ድግስ ደግሻለው
አንቺን ላውድስሽ
እንግዳዬ አድርጌ
በክብር ላኖርሽ
እንደ ጥንት ወገኔ
እግርሽን አጥቤ
ከመደብ ላኖርሽ
የድሮ ክብርሽን
ልመሰክርልሽ
ድግስ ደግሻለዉ
አንቺን ላወድስሽ
ለነጋሪት መቺው ሹክ ብዬዋለው
ወገንሽ እንዲጋበዝ አስጠንቅቄዋለው
ለጡሩንባም ነፊ
እንዲሁ ብዬዋለው
አንድ ሰዉ እንዳይቀር
አጥብቄ ብያለው
ሰንጋም አርጃለው
ከዳቢት ከሻኛው
በደንብ ሰድሪያለው
የጠጁንም ነገር
ለእማማ አስካለ
እንዲያው ጥዬዋለው
የጎደለኝ የለም ተዘጋጅቻለው
ክብርሽን ልመልስ
ድግስ ደግሻለው
እንድትመጪ እምዬ
አደራ ልሻለው።
ቀኑ እኮ ዛሬ ነው
ዘገየሽስ ምነው ?
የጎደለ ኖረ ያልተስተካከለ
ምነው ቆየሽብኝ ?
የዛሬው ድግሴ ለየት ያለ እኮ ነው
ክብርሽ እንዲመለስ የተዘጋጀ ነው
ለጥንቱ ከፍታሽ ምስክርነትነው
ፈራሽ እንዴ እምዬ ?
ዘገየሽስ ምነው
አጥንት ተከስክሶ
ደም ፈሶ ሜዳ ላይ
ክብርሽ ሳይነካ
ለኛ እንደደረሽን
የአደራ ሀገር የደም ዋጋነትሽን
ባደባባይ ቆሜ
ልናገርልሽ ነው
የ ዛሬዉ ድግሴ ለየት ያለ እኮ ነው
ክብርሽ እንዲመለስ የተዘጋጀ ነው
የጥንት ስልጣኔሽ
ሉአላዊነትሽ የሚታይበት ነው ።
አትስጊ እምዬ እኔ አለሁልሽ
በዚኛው ድግስ ላይ
ልጆችሽ አይሞቱም
አንቺም አታለቅሺም
ደቦ መስራት እንጂ
ደባ ሴራ የለም
የፍቅር ቦንብ እንጂ
የፈንጂዉ ቦንብ የለም
የጥንቱ ታሪክሽ
ቀዳማዊነትሽ
ዛሬ ይመለሳል አትስጊ እምዬ
ልጆችሽ ቆመናል
ይልቅስ ቶሎ ነይ
ያንቺ መምጣት እኮ ያጠናክረናል
ጥርጥር አይባሽ
የጥንቱ ታሪክሽ
ቀዳማዊነትሽ ዛሬ ይመለሳል
የአደራ ሀገር የደም ዋጋነትሽ
ባደባባይ ቆሜ ልናገርልሽ ነው
እሰይ እልል እልል ልበል ቆሜ
አውቅ ነበር እምዬ እንደማትቀሪ
በኛ በልጆችሽ እንደማጨክኝ
ድግሱ ላንቺ ነው
ክብርሽ ይገለጥ ዘንድ
የተዘጋጀ ነዉ ።
እንግዲህ እምዬ
ቃል ኪዳን ልግባልሽ
በቀይ ቢጫ አረንጓዴው
ይሀው ልማልልሽ
ሞት እንግዲህ የለም
ደም አይፈስ ሜዳ ላይ
ወገን ወገኑ ላይ
ክፋት አንዳያስብ
እጁን ላያነሳ በጎሪጥ ላያየው
ጀርባ እንዳይሰጠው
የፍቅር አርበኛ እኔ ሆንሻለው
ብዙ አርበኞችን ላንቺ አሰልፋለው
እንደ እብድ እየጮሁኩ
ፍቅርን እሰብካለው
በአረንጓዴው በቢጫው በቀዩ
ሰንደቅሽ እምልልሻለው
ሀገሬ ኢትዮጵያ
እምዬ ኢትዮጵያ
የቀድሞ ክብርሽን
እመልዋለው
እንመልሰዋለን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@getem
@getem
@getem
ስም!!!!!!
ማን ነው የወደቀው ፤
የማነው ይኸ እግር ፤ አትበሉኝ ዛሬ ፤
አድዋ በሞተው ፤
ስሙ ባልተጣፈ ፤ ከርታታ ገበሬ ፤
ስሟን ተክላ ኖረች ፤ ኢትዮጲያ ሃገሬ ።
የኔ ዘመን ግብዝ ፤
ሲወዘወዝ ያድራል ፤ ስም ጥሩኝ እያለ በየጉራንጉሩ ፤
አልሰማም መሠለኝ ፤
አርበኛው አያቱ ፤
ስሙ እንደተረሳ ስም ተክሎ ላገሩ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
እንኳን 123 የአድዋ የድል በዓል💚💛❤️
ሸጋዋ የኔዋ ቅዳሜ......መተሽ መተሽልኝ ዛሬ ጭራሽ በአድዋ ቀን ላይ አረፍሽልኝ....ተገጣጠማቹልኝ እንዲህ ነው እንጂ...ከተገጣጠሙ አይቀር❤️
@balmbaras
@getem
@getem
ማን ነው የወደቀው ፤
የማነው ይኸ እግር ፤ አትበሉኝ ዛሬ ፤
አድዋ በሞተው ፤
ስሙ ባልተጣፈ ፤ ከርታታ ገበሬ ፤
ስሟን ተክላ ኖረች ፤ ኢትዮጲያ ሃገሬ ።
የኔ ዘመን ግብዝ ፤
ሲወዘወዝ ያድራል ፤ ስም ጥሩኝ እያለ በየጉራንጉሩ ፤
አልሰማም መሠለኝ ፤
አርበኛው አያቱ ፤
ስሙ እንደተረሳ ስም ተክሎ ላገሩ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
እንኳን 123 የአድዋ የድል በዓል💚💛❤️
ሸጋዋ የኔዋ ቅዳሜ......መተሽ መተሽልኝ ዛሬ ጭራሽ በአድዋ ቀን ላይ አረፍሽልኝ....ተገጣጠማቹልኝ እንዲህ ነው እንጂ...ከተገጣጠሙ አይቀር❤️
@balmbaras
@getem
@getem
እንዴት! ያውም አድዋን!?
(በድሉ ዋቅጅራ)
.
ምነው!?
አድዋን ያህል ታቦት!
ነጻነትን ያህል ጽዋ!
ምነው አጣ፣ አንጋሽ - ደጋሽ፣
የጀግና አባቱን፣ ድል ወራሽ?
ምነው?
.
ምነው?
ምነው! ጭር አለ ቀዬው፣ ዳዋ ዋጠው ደብሩ፤
ፎካሪ ናፈቀ ፈፋው፣ ሸላይ ጠፋ ባገሩ፡፡
ምነው?
.
ምነው?
በደም ቀለም፣ በአጥንት ብእር የተጻፈ ገድል፤
የጥቁር ህዝቦች፣ የነጻነት ውል፤
አድዋን ያህል ድል?
ምነው!?
.
ምነው!?
እንደመጥበትን ልቦና፣ እንናገርበትን ልሳን፣
አንከበርበትን ግርማ፣ እንከብድበት ሚዛን፣
ምነው! . . . . ያውም አድዋን!?
.
ምነው!?
በጎሰኝነት ችካል፣ በየጎጡ ጋጥ ታስረን፤
‹‹አድዋ!›› ማለት ከበደን፤
‹‹ኢትዮጵያ!›› ማለት ሸከከን፡፡
ባንባረክ ልንባርከው፣ ቅርጫ ʽናረገው አማረን፡፡
የአባቶቻችን ድል አሳከከን፤
ለትርክት አንደበት አጠረን!
ጀግንነትን አንውረስ - እንፍራ፣ እዳ አለው፣
ስንቀል ይከብዳል፤
ጀግንነት ጣር አለው ይቅር፣
እንዴት ድል መውረስ ያቅታል!?
.
ምንስ ድንቁርና ቢጎራበተን፤
ጎሰኝነት ቢያባትተን፤
እንዴት ድል መውረስ ያቅተን!
ያውም አድዋን! ከሀገር፣ ከሰንደቅ፣ ከነጻነትም በላይ፤
የሰው መሆንን ማተብ፣ የ‹‹ሳቬጅ›› ተረት ተርትን ስራይ፤
የአፍሪካን የነጻነት አዋይ፤
እንዴት!
.
ኧረ ወገኔ ውሉን ስቷል፤
አድዋ ተራራ መስሎታል!
ሸንሽኖ ሊከፋፈለው፣ ኮረብታ ሊያደርገው አምሮታል፡፡
አድዋ የአንድ ቀን ውሎ፣ አድዋ ተራራ መስሎታል፡፡
.
መንፈስ እኮ ነው አድዋ፣ . . . .
ፈለግ - ለመንገዳችን፣ ለታሪካችን - ልሳን፤
ዙፋን - የነጻነታችን፣ የአብሮነታችን ቁርባን፤
የመረዳዳት ፍሬ፣ የኢትዮጵያዊነት መልህቅ፤
የደገፈን - እንዳንወድቅ፤
ያጸናን - እንዳንዋዥቅ፡፡
እንዳንፈርስ ያጠነከረን፣ . . .
እንዳንጎድል - ቀድሞ የሰፈረን፡፡
. . . . . ምነው ዘመን አወረን!?
.
አድዋ እንደሁ መንፈስ ነው!
እንኳን ጎጥ - ሀገር ያልቻለው፤
ጽናት - አህጉር የጠበበው፤
አይገድቡት - ይፈሳል፤
አያቅቡት - ይዳረሳል፡፡
.
ታዲያ ምነው!?
ምንስ ድንቁርና ቢጎራበተን፤
ጎሰኝነት ቢያባትተን፤
እንዴት ድል መውረስ ያቅተን!
ያውም አድዋን!
-------------💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
የካቲት 23፣ 2009፤ አዲስ አበባ፡፡
@getem
@getem
@balmbaras
(በድሉ ዋቅጅራ)
.
ምነው!?
አድዋን ያህል ታቦት!
ነጻነትን ያህል ጽዋ!
ምነው አጣ፣ አንጋሽ - ደጋሽ፣
የጀግና አባቱን፣ ድል ወራሽ?
ምነው?
.
ምነው?
ምነው! ጭር አለ ቀዬው፣ ዳዋ ዋጠው ደብሩ፤
ፎካሪ ናፈቀ ፈፋው፣ ሸላይ ጠፋ ባገሩ፡፡
ምነው?
.
ምነው?
በደም ቀለም፣ በአጥንት ብእር የተጻፈ ገድል፤
የጥቁር ህዝቦች፣ የነጻነት ውል፤
አድዋን ያህል ድል?
ምነው!?
.
ምነው!?
እንደመጥበትን ልቦና፣ እንናገርበትን ልሳን፣
አንከበርበትን ግርማ፣ እንከብድበት ሚዛን፣
ምነው! . . . . ያውም አድዋን!?
.
ምነው!?
በጎሰኝነት ችካል፣ በየጎጡ ጋጥ ታስረን፤
‹‹አድዋ!›› ማለት ከበደን፤
‹‹ኢትዮጵያ!›› ማለት ሸከከን፡፡
ባንባረክ ልንባርከው፣ ቅርጫ ʽናረገው አማረን፡፡
የአባቶቻችን ድል አሳከከን፤
ለትርክት አንደበት አጠረን!
ጀግንነትን አንውረስ - እንፍራ፣ እዳ አለው፣
ስንቀል ይከብዳል፤
ጀግንነት ጣር አለው ይቅር፣
እንዴት ድል መውረስ ያቅታል!?
.
ምንስ ድንቁርና ቢጎራበተን፤
ጎሰኝነት ቢያባትተን፤
እንዴት ድል መውረስ ያቅተን!
ያውም አድዋን! ከሀገር፣ ከሰንደቅ፣ ከነጻነትም በላይ፤
የሰው መሆንን ማተብ፣ የ‹‹ሳቬጅ›› ተረት ተርትን ስራይ፤
የአፍሪካን የነጻነት አዋይ፤
እንዴት!
.
ኧረ ወገኔ ውሉን ስቷል፤
አድዋ ተራራ መስሎታል!
ሸንሽኖ ሊከፋፈለው፣ ኮረብታ ሊያደርገው አምሮታል፡፡
አድዋ የአንድ ቀን ውሎ፣ አድዋ ተራራ መስሎታል፡፡
.
መንፈስ እኮ ነው አድዋ፣ . . . .
ፈለግ - ለመንገዳችን፣ ለታሪካችን - ልሳን፤
ዙፋን - የነጻነታችን፣ የአብሮነታችን ቁርባን፤
የመረዳዳት ፍሬ፣ የኢትዮጵያዊነት መልህቅ፤
የደገፈን - እንዳንወድቅ፤
ያጸናን - እንዳንዋዥቅ፡፡
እንዳንፈርስ ያጠነከረን፣ . . .
እንዳንጎድል - ቀድሞ የሰፈረን፡፡
. . . . . ምነው ዘመን አወረን!?
.
አድዋ እንደሁ መንፈስ ነው!
እንኳን ጎጥ - ሀገር ያልቻለው፤
ጽናት - አህጉር የጠበበው፤
አይገድቡት - ይፈሳል፤
አያቅቡት - ይዳረሳል፡፡
.
ታዲያ ምነው!?
ምንስ ድንቁርና ቢጎራበተን፤
ጎሰኝነት ቢያባትተን፤
እንዴት ድል መውረስ ያቅተን!
ያውም አድዋን!
-------------💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
የካቲት 23፣ 2009፤ አዲስ አበባ፡፡
@getem
@getem
@balmbaras
እነርሱ ወደቁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!
እኔም ከጣይቱ ፤
ሳይወድቁ መነሳት ፤ መራመድ ተምሬ ፤
በሩጫው ሜዳ ላይ ፤
ሰብሮ የሚራመድ ፤
አቦ ሸማኔ ነው ፤ ልማደኛው እግሬ ።
ቀልቤን ለመዘወር ፤
ግር እያሉ መጥተው ፤ ከፊት ከሃላየ ፤ እየተንጃረሩ ፤
አሁንም አሁንም ፤
ቅደሚያት ቅደሚ በሚል ፈረንጅኛ እየተማማሉ ፤
ታዲያ ምን ዋጋ አለው ፤
አሯሯጬ ሁሉ ፤
መሯሯጥ ነው እንጅ ፤ መድረስ መች ተማሩ ።
እኔም በሜዳየ ፤
የጣይቱ ልጅ ነኝ ፤
መሙን የምረገጥ፤ አሻፈረኝ ብየ ፥
ከመዳረሻው ላይ ፤
ቁሜ የማገሳ ፤ አሯሯጬን ጥየ ።
አዎ ዛሬም ዛሬ ፤
በሩጫው ትራክ ላይ ፤
በይ ድረሽ እያለ ፤
በይ ስገሪ እያለ ፤
ሽምጥ የሚነዳኝ ፤ ልብ እያበረታ ፤
አሯሯጬ ሁሉ እየተዋከለ ፤ ጉልበቱ ሲረታ ፤
በወዳቂዎች ፊት ፤
እኔን ያቆመኛል ፤ የምኒሊክ አምላክ የጣይቱ ጌታ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
እንኳን አደረሳችሁ !!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
እኔም ከጣይቱ ፤
ሳይወድቁ መነሳት ፤ መራመድ ተምሬ ፤
በሩጫው ሜዳ ላይ ፤
ሰብሮ የሚራመድ ፤
አቦ ሸማኔ ነው ፤ ልማደኛው እግሬ ።
ቀልቤን ለመዘወር ፤
ግር እያሉ መጥተው ፤ ከፊት ከሃላየ ፤ እየተንጃረሩ ፤
አሁንም አሁንም ፤
ቅደሚያት ቅደሚ በሚል ፈረንጅኛ እየተማማሉ ፤
ታዲያ ምን ዋጋ አለው ፤
አሯሯጬ ሁሉ ፤
መሯሯጥ ነው እንጅ ፤ መድረስ መች ተማሩ ።
እኔም በሜዳየ ፤
የጣይቱ ልጅ ነኝ ፤
መሙን የምረገጥ፤ አሻፈረኝ ብየ ፥
ከመዳረሻው ላይ ፤
ቁሜ የማገሳ ፤ አሯሯጬን ጥየ ።
አዎ ዛሬም ዛሬ ፤
በሩጫው ትራክ ላይ ፤
በይ ድረሽ እያለ ፤
በይ ስገሪ እያለ ፤
ሽምጥ የሚነዳኝ ፤ ልብ እያበረታ ፤
አሯሯጬ ሁሉ እየተዋከለ ፤ ጉልበቱ ሲረታ ፤
በወዳቂዎች ፊት ፤
እኔን ያቆመኛል ፤ የምኒሊክ አምላክ የጣይቱ ጌታ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
እንኳን አደረሳችሁ !!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
እንኳን ለመላው የጥቁር ነፃነት ቀን ለ አድዋ በአል በሰላም አደረሳችሁ !!
.
(ይታይ ሀብቴ)
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ማንም አይደፍርም የእምዬን ደጃፍ
ተጠርቷል አሉ በነጋሪት
ጠላት ቢደፍረው የእምዬን ቤት
ሆ ብሎ ወጣ ንብ ሰራዊት
ጥቁር ሀበሻ ደመ ኮስታሬ
ደሙን የሰዋ ላንዲት ሀገሬ
አንገቱን ሰቶ ሆኖኛል ክብሬ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ማንም አይደፍርም የእምዬን ደጃፍ
ጥቁር አንበሳ እጀ ብረቱ
አያመነታ ላንዲት እናቱ
40 ሰው ጥሎ ድል ነው እራቱ
ዘራፍ
ሽምጥ ጋላቢ ከነፈረሱ
በዱር አዳሪ ድንጋይ ትራሱ
ለናት ሀገሩ አትሳሳ ነብሱ
ሞትን ያስመኛል ግርማሞገሱ
ዘራፍ ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ማንም አይደፍርም የእምዬን ደጃፍ
ሄደህ ንገረው ለዛ ለፈሪ
ዘንዶ ያወጣል አሳ ጎርጓሪ
እጄን አልሰጥም ላንተ ሰፋሪ
ዘራፍ
እህል አልቀምስ እንቅልፍም የለኝ
ጀግና የወለደው የጀግና ልጅ ነኝ
ክብሬን አልሰጥም ሞት ካሎሰደኝ
እከ ከ ከ ከ ከ ከ
ዘራፍ ዘራፍ ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ማንም አይደፍርም የእምዬን ደጃፍ።
.
#The_Real_One <3
@getem
@getem
.
(ይታይ ሀብቴ)
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ማንም አይደፍርም የእምዬን ደጃፍ
ተጠርቷል አሉ በነጋሪት
ጠላት ቢደፍረው የእምዬን ቤት
ሆ ብሎ ወጣ ንብ ሰራዊት
ጥቁር ሀበሻ ደመ ኮስታሬ
ደሙን የሰዋ ላንዲት ሀገሬ
አንገቱን ሰቶ ሆኖኛል ክብሬ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ማንም አይደፍርም የእምዬን ደጃፍ
ጥቁር አንበሳ እጀ ብረቱ
አያመነታ ላንዲት እናቱ
40 ሰው ጥሎ ድል ነው እራቱ
ዘራፍ
ሽምጥ ጋላቢ ከነፈረሱ
በዱር አዳሪ ድንጋይ ትራሱ
ለናት ሀገሩ አትሳሳ ነብሱ
ሞትን ያስመኛል ግርማሞገሱ
ዘራፍ ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ማንም አይደፍርም የእምዬን ደጃፍ
ሄደህ ንገረው ለዛ ለፈሪ
ዘንዶ ያወጣል አሳ ጎርጓሪ
እጄን አልሰጥም ላንተ ሰፋሪ
ዘራፍ
እህል አልቀምስ እንቅልፍም የለኝ
ጀግና የወለደው የጀግና ልጅ ነኝ
ክብሬን አልሰጥም ሞት ካሎሰደኝ
እከ ከ ከ ከ ከ ከ
ዘራፍ ዘራፍ ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ማንም አይደፍርም የእምዬን ደጃፍ።
.
#The_Real_One <3
@getem
@getem
አሰለማለይኩም፤
የሃበሾቹ ሙፍቲ፤ የወሎው ደረሳ ፤
እንባዎት ሲረግፍ ፤
እኔንም ጃሂሉን ፤ አስለቀሱኝሳ???
እሱ ለደገፈው ፤
ቅዋ ላበደረው ፤ ለተባረከ ሰው ፤
የእዝነት እምባ መስሎኝ ፤
ገና በአሻጋሪ ፤ በልኣ ሚመልሰው ።
የሃበሻ ክዋክብት ፤
ሃገሩን ያቀኑት ከጧት እስከ ማታ ፤
ነቅለው የጨረሱት፤
የወንዙን ሙሲባ ፤ ያገሩን በሽታ ፤
አልነበረም እኮ ፤
ሃራም ነህ ሃራም ነህ ፤ እየተባባሉ እየተካሰሱ ፤
በአፉታ ቀልባቸው ፤
ለረቢል አለሚን ፤ እንባባ እያፈሰሱ ፤
የስንቱን ልዩነት ፤
የገነባውን ግንብ ካቡን አፈረሱ ።
አባባ ሸህ ኡመር ፤
እንባቸው ከአይናቸው፤ የተወረወረው ድንገት አፈትልኮ ፤
በኡማው መሃከል ፥
ለቆመው ግድግዳ ፤ ግንቡን መደርመሻ መዶሻ ነው እኮ ።
እኮ!!!!!
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ የረፍት ቀን!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
የሃበሾቹ ሙፍቲ፤ የወሎው ደረሳ ፤
እንባዎት ሲረግፍ ፤
እኔንም ጃሂሉን ፤ አስለቀሱኝሳ???
እሱ ለደገፈው ፤
ቅዋ ላበደረው ፤ ለተባረከ ሰው ፤
የእዝነት እምባ መስሎኝ ፤
ገና በአሻጋሪ ፤ በልኣ ሚመልሰው ።
የሃበሻ ክዋክብት ፤
ሃገሩን ያቀኑት ከጧት እስከ ማታ ፤
ነቅለው የጨረሱት፤
የወንዙን ሙሲባ ፤ ያገሩን በሽታ ፤
አልነበረም እኮ ፤
ሃራም ነህ ሃራም ነህ ፤ እየተባባሉ እየተካሰሱ ፤
በአፉታ ቀልባቸው ፤
ለረቢል አለሚን ፤ እንባባ እያፈሰሱ ፤
የስንቱን ልዩነት ፤
የገነባውን ግንብ ካቡን አፈረሱ ።
አባባ ሸህ ኡመር ፤
እንባቸው ከአይናቸው፤ የተወረወረው ድንገት አፈትልኮ ፤
በኡማው መሃከል ፥
ለቆመው ግድግዳ ፤ ግንቡን መደርመሻ መዶሻ ነው እኮ ።
እኮ!!!!!
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ የረፍት ቀን!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
የማይነድ እሳት !!!!!
የማይነድ ቁስቋስ ፤ ማገዶ አምጥታችሁ ፤
ማለዳ ጀምሬ ፤
እፍ ብል እፍ ብል ፤
አልሰማም ጀበናው ፤አልፈላም ቡናችሁ ።
የለመደባችሁ ፤
ደረቅ ትእዛዛችሁ ፤
ቆስቁሺው ነው አንጅ፤
አንድጅው ነው እንጅ፤ አጭሺ እንደገና ፤
እኔም እርም አያርመኝ ፤
ደግሞ እንደ በቀደም እንደ ትናንትና ፤
ዛሬም እፍ....... እላለሁ
እንዳይፈላ እያወቅኩ ፤ የእናንተ ጀበና ።
ቆስቁሽበት ብለው ፤
ጤዛ የጠገበ ፤
የለዘዘ ቁስቋስ ፤ ይዘው እየመጡ ፤
ዛሬም እንደገና ፤
እሳቱ አልነደደም ፤ እነርሱም አልጠጡ ።
ምድጃ ዳር ቆሞ ፤
የማይነድን ቁስቋስ ፤
አቃጥሉ ቆስቁሱ ፤
አንድዱበት ብሎ ፤ በእፍ ባይ መከበብ ከጧት እስከ ማታ ፤
አየዋ ልንገርህ ፤
ያበሻ ግብር ነው ፤ የጦቢያ በሽታ ።
(((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
የማይነድ ቁስቋስ ፤ ማገዶ አምጥታችሁ ፤
ማለዳ ጀምሬ ፤
እፍ ብል እፍ ብል ፤
አልሰማም ጀበናው ፤አልፈላም ቡናችሁ ።
የለመደባችሁ ፤
ደረቅ ትእዛዛችሁ ፤
ቆስቁሺው ነው አንጅ፤
አንድጅው ነው እንጅ፤ አጭሺ እንደገና ፤
እኔም እርም አያርመኝ ፤
ደግሞ እንደ በቀደም እንደ ትናንትና ፤
ዛሬም እፍ....... እላለሁ
እንዳይፈላ እያወቅኩ ፤ የእናንተ ጀበና ።
ቆስቁሽበት ብለው ፤
ጤዛ የጠገበ ፤
የለዘዘ ቁስቋስ ፤ ይዘው እየመጡ ፤
ዛሬም እንደገና ፤
እሳቱ አልነደደም ፤ እነርሱም አልጠጡ ።
ምድጃ ዳር ቆሞ ፤
የማይነድን ቁስቋስ ፤
አቃጥሉ ቆስቁሱ ፤
አንድዱበት ብሎ ፤ በእፍ ባይ መከበብ ከጧት እስከ ማታ ፤
አየዋ ልንገርህ ፤
ያበሻ ግብር ነው ፤ የጦቢያ በሽታ ።
(((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
ዝም በሉ!!!!!!!!!!!!!!!!
እስኪ ዝም በሉ ፤
በህያው መውደድ ፊት ፤ ብሶት አትጻፉ ፤
በሰባራ ፊደል ፤
ኑሮ የሳለውን ፤ ህይወት አትግደፉ ።
አንዳንድ ቀን አለ ፤
የፊደል ገበታ ፣ ገልጦ የማይገልጠው የናፍቆት ጋጋታ ፤
ቢጭኑት የማይሞቅ ፤
እንደ ደብተራ ሻሽ ፤ እንዳለቀ ኩታ ፤
እናም ዝም በሉ ፤
በናፍቆት ተድጦ ፤
ፊደል የሞተ ቀን ፤ ጉልበቱ ሲረታ ፤
ምን ሊረባ ፊደል ፤ ምን ሊሆን ጫጫታ ፤
ህይወት ያጎበጠው ፤ የናፍቆት በሽታ ፤
ስሙኝማ ጓዶች፤
መዳኛው ገላ ነው ፤ ያንገት ጠረን ሽታ ።
እናም እህት አለም ፤
ተናገሪ አትበይኝ ፤
በይ ልስማው አትበይኝ ፤
ያንጀቴን ሰው መራብ ፤ የናፍቆቴን ጣጣ ፤
አለ እኮ በኛ ቤት፤
በዝምታ መሃል ፤
አንገት ተጠምጥሞ ፤ በናፈቀ ትንፋሽ ተስሞ ሚወጣ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
እስኪ ዝም በሉ ፤
በህያው መውደድ ፊት ፤ ብሶት አትጻፉ ፤
በሰባራ ፊደል ፤
ኑሮ የሳለውን ፤ ህይወት አትግደፉ ።
አንዳንድ ቀን አለ ፤
የፊደል ገበታ ፣ ገልጦ የማይገልጠው የናፍቆት ጋጋታ ፤
ቢጭኑት የማይሞቅ ፤
እንደ ደብተራ ሻሽ ፤ እንዳለቀ ኩታ ፤
እናም ዝም በሉ ፤
በናፍቆት ተድጦ ፤
ፊደል የሞተ ቀን ፤ ጉልበቱ ሲረታ ፤
ምን ሊረባ ፊደል ፤ ምን ሊሆን ጫጫታ ፤
ህይወት ያጎበጠው ፤ የናፍቆት በሽታ ፤
ስሙኝማ ጓዶች፤
መዳኛው ገላ ነው ፤ ያንገት ጠረን ሽታ ።
እናም እህት አለም ፤
ተናገሪ አትበይኝ ፤
በይ ልስማው አትበይኝ ፤
ያንጀቴን ሰው መራብ ፤ የናፍቆቴን ጣጣ ፤
አለ እኮ በኛ ቤት፤
በዝምታ መሃል ፤
አንገት ተጠምጥሞ ፤ በናፈቀ ትንፋሽ ተስሞ ሚወጣ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
❤1
አላሳዝንሽም?
እኔ አንቺን አፍቅሬ
ከሰውነት ተርታ ወዲያ ተሸቀንጥሬ
የምኖርበትን እይወቴን ረስቼ
እስከማልታወቅ ጠቍሬ ከስቼ
አንቺ የኔ ካልሆንሽ ህይወቴ ይረሳ መኖሬ አይታወስ
እያልኩ እስካነባ ከጸባሆት ድረስ
ከጸባሆት ደርሶ መልሶ እስኪዘንብ
ድንገት ክረምትሆኖ ልብስሽ ልብሴ ሲረጥብ
ዝናብ ይመስልሻል ይኀው አሁን እንዄን ከላይ የሚዘንበው የኔው እምባኮ ነው
አላሳዝንሸም?
በኔ ፍቅር ጉዳይ እግዜር ጣልቃ ገብቶ
ዶፉን የሚያወርደዉ መብረቁን አብርቶ
ደግሞም ሳያባራ ጨረቃ በግርጌ ፀሀይ በቀኝ በኩል ድንገት የምትወጣው
ጠብ ጠብ እያለ ኮከቡ እሚረገፈው ለምን ይመስልሻል የሀዘኔን ጥልቀት አይተው ተመልክተው
የእምባኤን ብዛት መላዕክት ለክተው ቢነግሩት እኮነው
አላሳዝንሽም?
አለሽበት ካሉት አለሸ ካልኩት ቦታ ይኀው ቁጭ ብያለው
አንቺን በመጠበቅ አንቺን መስያለው
የአይኖችሽ ጥላ አይኔላይ ስላሉ
አይኖቼን ብታዪ ያንቺን ይመስላሉ
በሩ በተነካ ሰዉ ባለፈ ቁጥር
መጣች ቅረች የሚል ጎዶሎ ስቆጥር
አመሸው እንደዚ ቆየሁኝ እንደዛ ዝቅ አልኩ ወደምድር አሻቀብኩ ወደዚያ
ከፍብዬ አየሁት ተንሳፈፍኩ ወደላይ እንደማያይ ገባኝ ሰው ከራሱ በላይ
አላሳዝንሽም?
ምድር ተፈርክሷል ሰማይ ተሰንጥቋል
በስንጥቁ መሃል እግዚሃር ይታያል
በስንጥቁ መሃል አግዚሃር እንዲ ይላል
አያሳዝንሽም?
ጨረቃንም እንኪ ፀሀይን ውሰጃት ብቻ አንድ ሂጂለት
ይልሻል እግዜሩ ገብቶታል ነገሩ
አላሳዝንሽም?አሳዝንሻለዉ ጨካኝ አይደለሽም አዛኝ ነሽ አዉቃለዉ
ይህ ሁሉ ሲሆን ይህ ሁሉ ሲፈጠር ባትሰሚ ባታይ ነዉ !!!
(ትልቅ ይቅርታ ለምዕልቲ ኪሮስ🙏🙏🙏)
@getem
@getem
@gebriel_19
እኔ አንቺን አፍቅሬ
ከሰውነት ተርታ ወዲያ ተሸቀንጥሬ
የምኖርበትን እይወቴን ረስቼ
እስከማልታወቅ ጠቍሬ ከስቼ
አንቺ የኔ ካልሆንሽ ህይወቴ ይረሳ መኖሬ አይታወስ
እያልኩ እስካነባ ከጸባሆት ድረስ
ከጸባሆት ደርሶ መልሶ እስኪዘንብ
ድንገት ክረምትሆኖ ልብስሽ ልብሴ ሲረጥብ
ዝናብ ይመስልሻል ይኀው አሁን እንዄን ከላይ የሚዘንበው የኔው እምባኮ ነው
አላሳዝንሸም?
በኔ ፍቅር ጉዳይ እግዜር ጣልቃ ገብቶ
ዶፉን የሚያወርደዉ መብረቁን አብርቶ
ደግሞም ሳያባራ ጨረቃ በግርጌ ፀሀይ በቀኝ በኩል ድንገት የምትወጣው
ጠብ ጠብ እያለ ኮከቡ እሚረገፈው ለምን ይመስልሻል የሀዘኔን ጥልቀት አይተው ተመልክተው
የእምባኤን ብዛት መላዕክት ለክተው ቢነግሩት እኮነው
አላሳዝንሽም?
አለሽበት ካሉት አለሸ ካልኩት ቦታ ይኀው ቁጭ ብያለው
አንቺን በመጠበቅ አንቺን መስያለው
የአይኖችሽ ጥላ አይኔላይ ስላሉ
አይኖቼን ብታዪ ያንቺን ይመስላሉ
በሩ በተነካ ሰዉ ባለፈ ቁጥር
መጣች ቅረች የሚል ጎዶሎ ስቆጥር
አመሸው እንደዚ ቆየሁኝ እንደዛ ዝቅ አልኩ ወደምድር አሻቀብኩ ወደዚያ
ከፍብዬ አየሁት ተንሳፈፍኩ ወደላይ እንደማያይ ገባኝ ሰው ከራሱ በላይ
አላሳዝንሽም?
ምድር ተፈርክሷል ሰማይ ተሰንጥቋል
በስንጥቁ መሃል እግዚሃር ይታያል
በስንጥቁ መሃል አግዚሃር እንዲ ይላል
አያሳዝንሽም?
ጨረቃንም እንኪ ፀሀይን ውሰጃት ብቻ አንድ ሂጂለት
ይልሻል እግዜሩ ገብቶታል ነገሩ
አላሳዝንሽም?አሳዝንሻለዉ ጨካኝ አይደለሽም አዛኝ ነሽ አዉቃለዉ
ይህ ሁሉ ሲሆን ይህ ሁሉ ሲፈጠር ባትሰሚ ባታይ ነዉ !!!
(ትልቅ ይቅርታ ለምዕልቲ ኪሮስ🙏🙏🙏)
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1