ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ወቃጭ በዛ!!!!! ( ኢትዮጲያ 2)


ኢትዮጲያ የሚሏት፣ ምስኪን ሃገር አለች፣
እንደ ተዝካር ጌሾ፣
ሁሉ እየወቀጣት፣ ታሳዝነኛለች።
እንደ ጌሾ ወቅጠው፣ካላሟት በኹላ፣
ሁሉም ይግታታል፣
በቶፋ በምንቸት፣ ያጓሸውን ጠላ።
ሁሉም ሽንክናውን፣
በስካሩ ብዛት፣ እየከረከመ፣
እኔ ነኝ ኮማሪው፣
እኔ ነኝ ጠማቂው፣ ብሎ እየፎከረ፣
የአርባ ቀን እድሏ፣
መወቀጥ መወቀጥ፣ መላም ሆኖ ቀረ።:


((( ጃ ኖ )))💚💛❤️


@balmbaras
@getem
@getem
ሀገሬ ፍየል ናት፣ ያውም የታረደች፤ አምና
ለፋሲካ፣
አላፊና አግዳሚው፣ ግጦ የጨረሳት፣ የተዝካር
በረካ፣
ቆዳዋስ ወዴት ነው? ብዬ ሳፈላልግ፣ ስማስን
በልቤ፣
ይደበድቧታል፣ ታምቡር አድርገዋት፤ የባለዛር
ድቤ፡፡


((( ጃኖ )(💚💛❤️


@balmbaras
@getem
@getem
ቅድመ ፍልስፍና

( ኤፍሬም ስዩም )

ፈላስፋ ተነስቶ እግዜር የለም ካለ
አምላክ የለም ካለ
ፈላስፋው ልክ ነው
እግዜር ነው ፈላስፋው
ምክንያቱም…
እግዜር . . አንዱን አስነስቶ
አፉን በቃል ከፍቶ
እግዜር አለ ብሎ .. ሊያናግር ሲሻ ነው
ያን - የለም አስብሎ .. ቀድሞ ሚያናግረው


( ኑ፦ግድግዳ እናፍርስ ከተሰኘው መድብል የተወሰደ ገፅ፦24 )

ገፅ

@getem
@getem
@gebriel_19
~ምክር~

በ "ታላቅ ነኝ" ስሌት ስትታበይ ነፍስህ፣
ከቁብ ላልቆጠርከው ሲበዛ ንቄትህ፣
ቆም ብለህ ላንዴ ይሄን እውነት አውሳ፣
"ጠብታ ውሃ ናት ዓለት የምትበሳ።"

ሐሙስ ቀን 28/06/2011 ዓ•ል ጠዋት 2:20
©ሪሀቢቢ ዘ-ሐበሻ

@getem
@getem
@RiHabib
ትዝብት
"""""""""""

ከማዕዱ ከለከሉኝ
በዓይኔ አይቼው እየገፉኝ
ተገባብዘው በሉ እነሱ
ቁራሽዋን ግን ለኔ ነሱ
በልተው ጠግበው ከምግቡ
ያንን ሁሉ ሊያስተርፉ
ከኔ ትዝብት አተረፉ!!!

አብርሃም

@getem
@getem
@gebriel_19
ቀኖች እንዲህ ናቸው
*
አንዱ በሞተበት ~ሌላው ቆሞ ይሄዳል
አስተዋይ የሰራው~በሰንፍ ይናዳል
ሌላው በሰራው ግፍ ቀሪው ሰው ይጎዳል
*
እናም የኔ ቆንጆ
*
ከጾሙ ባሻገር
ስሚኝ ፩ ነገር
*
ፀሎትን ለማድረስ ~ከደጁ ስትሄጂ
ላንችም ብቻ ሳይሆን ~ቀኖችንም ዋጂ።
*
*
ደህና እደሩልኝ።
✍️እሱባለው ኢትዮጵያዊ (የቡዜ ልጅ)

@getem
@getem
@lula_al_greeko
*ከኛ መንደር*

አይተን ነበር ድሮ ወረቀት ወረቀት
አናት ላይ ተፅፎ
የጎደፈ ሲፀዳ ትወልድ
ለሀገር ተርፎ
ዛሬ ቀን ተገላብጦ ከኛ መንደር
ሀገር መሀፀኗ ሰንፎ
ልጅ ያቦከው አያወቅምና
ለራት አልፎ
የተማረ ገደላት
ሀገሬን በቁሟ ቆዳዋን ገፎ።


(ብሌን)

@getem
@getem
@gebriel_19
ወሊድና ወሲብ


ፍቅርና ወሲብ በድመቶች ዓለም
አለው አንዳች ነገር ፣ እጅግ የሚያስደምም።
ወሲብ የሠሩ እለት ፣ አይጣል ነው ምጣቸው
አገር ያዳርሳል ፣ ጩኸት እሪታቸው፦


የወሊድ ለታ ግን ፣ ምጥ የለባቸውም
አንዲት ጠብታ ድምጽ ፣ ቃል አትወጣቸውም።


የኛ ግን ሌላ ነው
ለፍቅርም ማማጥ ነው
ለ አንድነት ማማጥ ነዉ
ለወሊድ ማማጥ ነው
ለሞትም ማማጥ ነው
ጣር ነው ጅምራችን ፣ ጣር ነው መጨረሻው
<< ለምንድነው? >> አልኩኝ ፣ ከድመት ያነስነው!!!


((( ነብይ መኮንን )))💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
የምንሰፋው ጠፋ!!!!


ሁሉም በየቤቱ፤
እጁ እንደመራለት፤
ልቡ እንደፈቀደው፤
ቅዳጁን ሽንቁሩን፤
በድሪቶ ትብታብ፤
በቁጢት በወስፌ፤
እያጨማደደ፤
ይህ ቀዳዳ ሁላ፤
ቅድ አገኘሁ ብሎ፤
ስፍ በማያውቅ እጁ፤
እየተበተበ እየደራረተ፤ አጥብቦ እየሰፋ፤
"ሽንቁር "በበዛበት፤
"ቅዳጅ" በሞላበት፤
እኛ ሰፊዎቹ ፤የምንሰፋው ጠፋ።

((( ጃ ኖ ))💚💛

ሸጋ ጁምኣ!!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
እታለሜ ሙች!!!!!!!


እንደ ሙጀሌው ሸር፤ እንደ እሾሁ ክፋት፤
ደሞ እንደኔ ሩጫ፤ ደሞ እንደኔ ልፋት፤
ህልሜ ባዶ ነበር፤
አንች ባትኖሪ፤
ልዳብስህ እምትይ፤ እንደ ወላጅ እናት።


ይህ ጉደኛው እጅሽ፤
የህይወትን ቆንጥር፤
የኑሮን ሙጀሌ፤
እየመነገለ ባይጥለው አውጥቶ፤
እታለሜ ሙች!!!!!
እርሻው ሙቶ ነበር፤ ጎተራውም ጠፍቶ።


የጠላቴን ሰንኮፍ፤
በፍቅር እጆቿ፤
ፈንቅላ የምትጥል፤ ደማም ክንደ ብርቱ፤
እኔም በማጀቴ፤
እግሬን የምታበጅ፤
አለችኝ እቴጌ፤ አለችኝ ጣይቱ።

((( ጃ ኖ ))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
Nahu

አንቺ እውነትም ሴት ነሽ

ግላዊ ሂወትሽ ደስታሽ ሣያጓጓሽ
ለሰው የምትኖሪ የራስሽን ትተሽ
ዘመንሽን ምትገፊ ስለሰው እያሰብሽ
ለሰው እየለፋሽ
ስለሰው እየኖርሽ፡
ይሄን አወቄአለው
አንቺ እውነትም ሴት ነሽ፡፡

ሴት ነሽ ማለቴ ግን
አላዋቂ ሁሉ ደካማን ሲነቅፋ
አቅም የሌለውን ሴት ብሎ እንደሚያልፋ
ወይ ደሞ
ያቀለለ መስሎት ሴት ብሎ ሚሳደብ
ማክበሩን ሳያቀው የሚናገር ደደብ

የሴትነት ትርጉም ለኔ ይህ አደለም
ባዶ መረዳት ነው በሰነፎች አለም

እኔ ሴት የምላት
ለራስ ብቻደለም በዙርያዋ ላሉት
መናኖር እንደቻለች ምንም ቢታክታት
ደስታን ከፈጠረች የራሷም ቢያርባት
መስዋት ከከፈለች ልክ እንደ እናት
ሌላ ቃል የለኝም የኔ ሴት ይቺ ናት፡፡

አንቺም ለሰው የኖርሽ
ደስታን ልሰጥ ስትይ ደስታሽም ላጣሽ
ከራስሽም በላይ ስለ ምትወጂው ሠው መኖሩንም ከቻልሽ
አረጋግጫለው ዮሪ እውነትም ሴት ነሽ፡፡

28/06/2011

@getem
@getem
@gebriel_19
የተስፋ ፍሬ
****
ገበሬው በእርሻ ላይ
በአንድ እጁ ጭብጥ
እፍኝ ዘር ይዞ
ሁለት ምርጫ ቢመርጥ
(አንድም)
የጨበጠውን ዘር ወይ ጠብሶ ወይ ቆልቶ ወይ ቀቅሎ መብላት
(ወይም)...መሬትን ቆፍሮ ይችን እህል መዝራት
ሁለት ጥንፍ ይዞ ቢቸገር ማማረጥ
ይህን አይቶ ኖሮ
ፈጣሪ አስተማረ የሰውን ተስፋ ጥግ
ፍጥረት ዘርን ጥሎ ዘርን እንዲጠብቅ!

አብርሃም

@getem
@getem
@gebriel_19
ሰይ ብል!!!!!!!! ባነጣጥር!!!!!


ከጉዴዎቹ ዳር፣
ሰይ ብል!!!!!
ባነጣጥር!!!!
ባንከረባብት ፣ ሲል እየተኮሰ፣
ያገርን ብይ ሁላ፣
በላሁት እያለ፣ በእጁ እያፋፈሰ፣
የለመደው "ጀግና"፣
አሁንም ሰይ!!!!! ይላል፣
በየጉድጓዱ ዳር፣ እንዳምና ካቻምና
ምናምን ደግኖ፣
" ሰይ!!!! ማለቱን አይተው ፣ መገን የሱ ነገር፣
መች እንቅልፍ ይተኛል፣
" በላሁት!!!!" እያለ፣ ""ካላፈሰ"" በቀር።

((( ጃኖ )))💚💛❤️



@Balmbaras
@getem
@getem
👍1
ዕድለ-ዕድል(ልዑል ሀይሌ)
ሰው ይታመማል ወይ
ስለት አስገብቶ፤
እግሩን ይሰብራል ወይ
ምርኩዝ ዱላን አይቶ፤
.
ዓይኑን ያጠፋል ወይ
ጠላት ላለማየት፤
አይገናኝም ወይ
ላለመለያየት።
.
ያፍሳል ወይ ውሃውን
ከቁጭት ለመዳን፤
ከአውሬው ለመሸሽ
ያንሳል ወይ ከጉንዳን፤
.
ያነጥፋል ወይ እሾህ
ከገደል ሳር ፍርሃት ርቆ ሊገላገል፤
እጁን ይቆርጣል ወይ
አንበሣ ለመግደል፤
.
ቤቱን ያፈርሳል ወይ
ዛፍ ላይ የተሰራ
የወፍ ጎጆ እያየ፤
አይፈቀርም ወይ
የተፋቀረ ሰው ሲለያይ ስላየ።
.
ለዚህ ነው የምልሽ!..
ዓይንሽን አትመኝ
ጆሮሽን አትመኝ
ልብሽን አትመኝ፤
ልቤ ፈርሷልና
ጨረቃ ምድር ላይ ቆማ ስትገጥመኝ።
.
ለዚህ ነው የምልሽ!..
እንዳትታበዪ እንዳትኮሪበት፤
ምንም ትላንት ባይኖር
ለነገው ትንፋሼ
ትንፋሽሽ አለበት።
.
ስለዚህ!..
ክፈቺው ልብሽን
ክፈች ዓይኖችሽን ነገሽን አልሚ፤
ትላንት የወጋሽ ጦር
ነገ እንዳይገድልሽ ዛሬ አትታመሚ።
.
የምልሽን ስሚ!
ጆሮሽን ክፈቺ ኮርኩሪው ይሰማሽ፤
ያለፈው ሲቃ ድምፅ
ሊሽር ቆሞልሻል በፍቅር የተጠማሽ።
.
፳፱-፪-፳፻፲፩ ዓ.ም.

@getem
@getem
@lula_al_greeko
"የተዘጋ ሀሳብ"

( በኤፍሬም ሥዩም)


☞ እዚህ……
ሙዚቃ ከሌለው ስሜት ከማይሰጥ ቤት
ሀዘን ያልተለየው የከሰለን ህይወት
አዳፋ ለባሾች የቀን ሰራተኞች
ንቃቃታም ሴቶች ጉሊት ቸርቻሪዎች
አግዳሚ ወንበሩን ሚስኪኖች ከበውት
ማገር የሌለውን ጠባቡን ያፈር ቤት
በጠላ ባረቂ በጠጅ አጅበውት።
.
ከኑሯቸው በላይ ጫጫታቸው በዝቶ
ካዘናቸው ይልቅ ሳቃቸው ተሰምቶ
አንዱ ድሀ ዘፋኝ አንዱ አጨብጫቢ
አንድኛው ፎካሪ የጋባዥ አጃቢ
ባንድነት ተፋፍገው እየተማማሉ
ምግብ አልበላንም እየተባባሉ
ለድሃ እሚራራ ነፍስን ያደማሉ።
.
☞ እዚያ....
ጥቂት ሹማምንቶች የመተያያን ገንዘብ 'ሚጥሉበት
አጥተው
የግፍ ነጋዴዎች ንጋት ሳይቀድማቸው
ያልፈኩ አበቦች ከሚቆረጡበት
ለአይን የሚያሳሱ እንስቶች ካሉበት
ልክ በሌለው አፍ ዘፈኑ ተከፍቶ
የሚረግጠው ስፍራ እግራቸው ቦታ አጥቶ
በሬጌና በቫልስ፣ በቡጊ በቻቻ በሳንባና በራፕ፤
እንዲሁም በስክስታ ጭፈራቸው ደርቷል
የቀን ግፋቸውን ግድ የለሽ አይምሮን በውስኪ ያጥቡታል።
.
ከደጅ ከሀብታሞች ቡና ቤት፣ ድሆችም ባሉበት ካረቂ ቤቱ
በር
ከገንዳ ላይ ለቅሞ ሆዱን የሚሞላ አንድ ሚስኪን ነበር።
.
☞ እኔ .....
ሀብትን ከማይጠሉት ለድሆች ከሚያዝኑት መካከል ላይ
ቆሜ እሰቃይ ነበረ...
እውነት በሚሰፍር ቀን በሚታይ ህልሜ።
.
☞ ገንዳ ለቃሚው....
ኑሯቸው ነው ብለህ ስለነዚህ ድሆች ስለምን ታዝናለህ
እኒህ ትንሽ ድሆች ሀብት ቢሞላቻው ብር ቢተርፋቸው
ከባንኮኒ ቆመው ከመጠጣት ሌላ ምንድን ነው ትርፋቸው?
ምንድን ነው ተስፋቸው ገንዳው ላይ ለቆመው?
.
እኒህስ ሀብታሞች ከውስኪ ቤት አልፈው
ከመግባት ውስኪ ቤት
አንዷን ቆንጆ ትተው ከማቀፍ ሌላ ሴት
አይምሮአቸው ሂዶ ደርሶ የሚያርፍበት
አዲስ ኬላ የለም ሰርተው የሚፈጥሩት።
.
ስለዚህ ግጥምህን እንዲህ ብለህ ዝጋው
እንደዚህ አትማው
ሰካራም ድሃና መጠን አልባ ሀብታም
ፍፃሜው አንድ ነው
ከባንኮኒ ቆመው ከአግዳሚ ተነስተው ውስኪ ለማድረግ
ነው
አረቄውን ደፍተው።



(ከሶልያና የግጥም ሲዲ የተጻፈ)

ከ ገፅ

@getem
@getem
👍2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መስለውኝ ነበረ
የበቁ የነቁ
ያዉም የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች
ለካ እነሱ ናቸው
ጥሬ ጨው .... ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች
መፈጨት...መሰለቅ..መደለዝ..መወቀጥ...መታሸት...መቀየጥ
ገና ሚቀራቸው
እኔ የለሁበትም!>
ዘወትር ቋንቋቸዉ፡፡

(( ደበበ ሰይፉ ))

ነብስያህን አድምጥ ❤️❤️ ራስህን ሁን!!

ሁላችንም ምን አገባኝ የሚሉት....ፈሊጥ ተጠናውቶናል..

" የምናገባኝ ትውልድ ”


ወኔያችንን ምን እንደሰለበብን ባይታወቅም ብዙ ነገራቶች ላይ እጅግ ግድ የለሽ ሆነናል ። ለማንም ምንም የማይመስሉ ነገራቶች እንኳ ሳይቀር የሚቆረቁረን ዜጋዎች ነበርን ። ዛሬስ

እገሌ ሞተ ... ከሰውዬው ሞት ይልቅ የኛ ስሜት አልባ መሆን ይደንቃል

ረሃብ ሰውን ፈጀው ስንባል ... ዝም!!!

አረ ወጣቱ ተሰዶ ሀገር ያለ ተረካቢ ቀረች ... ዝምምም!!!

ከተማዋ ቆሸሸች .... ዝምምም

መንገድ ላይ የሚሸና ብናይም ... ዝምምም

የትራፊክ አደጋ በዛ ... ጉዳያችን ስላልሆነ ዝምምም

የእከሌ ቤት ፈረሰ .... የኛ እስካልፈረሰ አያገባንም

ጎዳና ተዳዳሪዎች ብርድ ፈጃቸው ... ልጆቻችን አይደሉምና አይመለከተንም

ስርቆት በዛ ... ዝምምም እኛ እስካልተሰረቅን


ሁሉም ጋቢና ከተቀምጠ መኪናው ከጭቃ አይወጣም!
ሰብሰብ ብላችሁ በመኪና ስትሄዱ በጭቃ ከተቀረቀረ የተወሰነው ሰው ወርዶ መግፋት
አለበት፡፡ ሁሉም "አይ እኔ ውስጥ ነው የምቀመጠው" "ታየኝ እኮ ጭቃ ሲነካኝ" ካለ
ተቀርቅራችሁ መቅረታችሁ ነው፡፡ ሌላው አማራጭ ሌላ መኪና መጥቶ ከጎተተ ብቻ ነው፡፡
አሁን የኢትዮጲያ ሁኔታ ጭቃ ውስጥ እንደተቀረቀረ መኪና ነው፡፡ የተወሰነው ያህል ዜጋ
ወርዶ ለመግፋት ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡ ተራ እየወሰድን ልንገፋ እንችላለን፡፡ ግን አንዱ
መጀመሪያ ላይ መጀመር አለበት፡፡ ሌላውም መቀጠል አለበት፡፡ በፉክክር ማንም
የመጀመሪያ አልሆንም ካለ ጭቃ ውስጥ መሰንበታችን ነው፡፡
---------------------------------------

ሁላችሁንም ለነበረኝ ሸጋ ጊዜዎች አመሰግናለሁ .....ብዙ አስተማሪዎች አሉኝ እዚህ ቻናል ውስጥ...አሁን ከራስ ጋር ስብሰባ የሚገባበት ሰዓት ነው.....አሁን ነብስያን እያደመጡ ራስን በመሆን ገንዳ ከመሆን የሚያመልጡበት ሰዓት ነው.......በመጨረሻም ቅዱስ ቁርኣን ምን ይላል መሰለህ...."ከችግር ቦኃላ ምቾት አለ"



በብቻነት ኑሮ ብቻ ይወደዳል በብቻነት ኑሮ ብቻ የሚለው ቃል...ብቻ ይወደዳል ...

የፀጥታ ዜማ ቅኝት ይወለዳል!!!
ሁላችንንም አመሰግናለሁ !!!🙏🙏
ለምን ይመስልሻል?
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ትናንት የጨቆኑት ፣ ጨቋኙን ለመጣል
"ሁላችን አንድ ነን ፣ አንድነት ይበልጣል
አንድነት ኋይል ነው ፣ አንድነት ያዋጣል
የኔ ደም ያንተ ነው ፣ ያንተም ነው የኔ ደም
ዘረኝነት ይውደም
ጎጠኝነት ይውደም
ፍሪደም ፍሪደም
ቅደም ቅደም ቅደም
ፍጠን ተባብሎ
አደባባይ ውሎ
ሰላም እንዲመጣ ፣ ሰላም ባስ አቃጥሎ
በከፋፈለው ፊት፣ ሀገር ህብረት ፈጥሮ
አንድ ነን እያለ ፣ ለአንድ ሀገር ዘምሮ
መንገድ እየዘጋ ፣ ድንጋዮች ደርድሮ
ጠብመንጃ ለማስጣል ፣ ድንጋይ ተወራውሮ
ጥይት ሲያዘንቡበት
ገዳይን ሲቃወም ፣ እጆቹን አጣምሮ
ጨቋኙን ለመጣል ፣ ተገርፎ ተወግሮ
አምስት ሊትር ውሃ ፣ ብልቱ ላይ ታስሮ
የተሰቃየ አምና
ፍርሃት በሚያጠፋ ፣ ወኔ ባለው ቃና
"ዘልአለም ከምትኖር ፣ በግፍ በጭቆና"
ለአንዲት ቀን ነፃነት ፣ መሞት ይሻላል ና
እያለ ሲጠራኝ ፣ ትግሉን እንዳስቀጥል
ፍቅርሽ አሸነፈኝ
መንገዶች ሳይዘጋ ፣ ባሶች ሳያቃጥል
ጭቆናሽ ፍትህ ነው ፣ ለጨቋኞች ማይጥል
ነፃነቴ አንቺ ነሽ ፣ ያገኘሁሽ በጥል
ቀንና ለሊቴ ባንቺ ነው የሚያልፈው
እያልኩ በስምሽ ፣ግጥም የምፅፈው
ለምን ይመስልሻል?
።።።
ተጨቆንን ብለው ፣ ትላንት ያለቀሱ
ጨቋኙን ለመጣል ፣ በህብረት የተነሱ
በአንድነት ኋይል ፣ ዛሬ ላይ ሲነግሱ
ህግ ለማስከበር ፣ ሰው እያፈረሱ
መብት ለመጠየቅ ፣ ሽመል እያነሱ
እኔ ብቻ ታገልኩ
የሚል ትምክህት ይዘው ፣ ሌላውን ሲረሱ
ሁሉም ነገር የኔ ፣ በሚል ክፉ አምልኮት
የተረኛ ስሜት ፣ ልባቸውን ማርኮት
ካለእኔ ፈቃድ ፣ እንዳትከፍቱ በር ፣ እንዳትዘጉ መስኮት
እንዳትለብሱ ኮት
እንዳታጨሱ እጣን
ቤት ንብረታችሁን ፣ ልቀቁና ውጡ ፣ እኛ ከተቆጣን
የእኛ ነው ፈጣሪ ፣ የእኛ ነው ሴይጣን
አዳኝም ገዳይም ፣ የእኛ ነው ስልጣን
ያለእኛ ፈቃድ ፣ አትዝሩ አትረሱ
መሬቱ የኛ ነው ፣ እግራችሁን አንሱ
የኛ ነው አየሩ
እኛ ካልፈቀድን እንዳትነፍሱ
ገለመሌ እያሉ
ጭቆናን የጠሉ
በተረኛ ስሜት ፣ ሲጨቁኑ በጣም
አዲስ ንጉስ እንጂ ፣ አዲስ ህዝብ አልመጣም
ነፃ አውጪ ነኝ ባዪ ፣ ራሱ ነፃ አልወጣም
ብሎ ሲተች ህዝቡ ፣ እየበላ ነገር
የባሰ አለና
ሀገርህን አትልቀቅ ፣ ሚል ተረት ሲናገር
ለኔ አንቺ ነሽና
የኔ ናት ቢሉኝም ፣ የማለቀው ሀገር
ለሌላ አልሰጥሽም ፣
ጊዜ ቢከዳኝም ፣ ቀኔ ቢጎድልብኝ
ሁለ ነገሬ ነሽ ፣ ፍቅርሽ ያደረብኝ
እኔ አንቺን ካገኘሁ
ቀረሁብት እንጂ፣ ከአለም ምን ቀረብኝ
ብዬ የማዜመው
የማንጎራጉረው የምደጋግመው
ለምን ይመስልሻል?
።።።።
በዚህ በጭንቅ ቀን
ለምን ባዮች ሁላ ለሞት ተሰልፈው
ሚዲያው ስለኳስ የሚለፈልፈው
እኔ ስላንቺ ጭን ፣ ግጥም የምፅፈው
ስለከንፈርሽ ጣም ቅኔ የምዘርፈው
ለምን ይመስልሻል?
።።።
በዚህ ጭንቅ ጊዜ
ድፍን ሀገር ታሞ ፣ ሀኪም ሲቸግረው
መድሀኒቴ አንቺ ነሽ ስል ማንጎራጉረው
አንዴ ላስነጠሰሽ
ይማርሽ እያልኩኝ ፣ ስጨነቅ የማድረው
ሀገር እያነባ
ለምን ይመስልሻል
ሰላሜ ነሽ እያልኩ ፣ ላንቺ ምዘምረው
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
"
ለውጡ እንዳይቀለበስ ነው

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1