ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
.........አደዋ ዝም ብሎ ድል አይደለም💚
አድዋ የስነ-ልቦና ከፍታ ነው ;💛
አድዋ የእልህ ጥግ ነው ;❤️
አድዋ የነፃነት ዋጋ መለኪያ ነው ;💚
አድዋ የአገር ፍቅር ጫፍ ነው ; 💛
አድዋ የባርነት የሞት ጉድጓድ ነው ;💚
አድዋ ከመለያየታችን የለየን ድንበር ነው ;💛
አድዋ የእብሪተኞች ጥሩር ሀፍረት ነው ;❤️
አድዋ የሀበሻ የሞራል ከፍታ ነው ;💚
አድዋ የጥቁሮች አንገት ትራስ ሆኖ ቀና ያደረገ ነው ;💛
አድዋ የምኒልክ የመሪነት ጥበብ💚
የራስ መኮንን ራስነት ፣ የባልቻ ወኔ ፣ ያሉላ የድል ጮራ ❤️
ያያቶቼ የመንፈስ ከፍታ.ስጦታ ነው ።💛
አድዋ ከድል ባሻገር ሚሊዮን ርቀቶችን ከፍ ብሎ የተሰቀለው ለዚህ ነው።❤️
....... ያያቶቼ ደም መንፈሣዊ ፀበል ፣ አጥንታቸውም የፈውስ መናችን ነው ; ምልህ ለዚህ ነው።💚💛❤️

ይኸው ነው ለኔ.!!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
💚💛❤️
የአድዋ ሳምንት ላይ እኮ ነው ያለነው እንዴት ዝም ይባላል።

አሁን ልጅ ቢኖረንና "አደዋ ግን ምንድን ነው?" ቢለን ምን ልንለው ነው?

ለናንተ አድዋ ምንድነው...? አድዋን ስታስቡ ምን ይሰማቹሃል...?


#እየጠበቅናቹ ነው.......ዛሬ እስቲ ስለዚህ እናውጋ....አድዋ ሁለት ቀንም አይደል የቀረው.....

👇👇👇
@balmbaras
@Gebriel_19
@getem
@getem
Miki:👇👇

Adwa lene ye andinstachin masaya
Ethiopiawinet mn malet endehone yasayenbet nw

Yotod Michael:👇👇

Adwa ene negn .........

🇧🇰вĸ:👇👇👇

Adiwan sasib zare be hodachin ena be ayimorochin wist yizen yeminzorow Kim ket yemeta nw biye asibalew.........kimu yanem kenebere min yahil Hagerachewin be minim endemayideraderubet asayitewinal.....enam zare chigrachin le mefitat sinasib Ethiopia mitibal hager mederaderyachin mareg endelelbin yaseyegnal....
Melikam beal le hulachum
Bk...ke *NAZU/Adama/*
💚💛❤️💚💛❤️

@balmbaras
@Gebriel_19
@getem
@getem
💚💛💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ስንት አየሁ አለም አየሁ:👇👇👇👇

አድዋን ለመግለፅ አድዋን መሆን ያለብኝ ይመስለኛል.....ተኑሮ የተሞከረ የአፍሪካ ብርቅዬ አይደገሜ ታሪክ ይመስለኛል። መተባበር......ልዩነትን መዘንጋት ሰው መሆን ግድም ያለን ስብእና ብቻ በማሰብ የተሰራ ትልቅ ታሪክ......የመንጋት እና የመጣስ እሳቤን ስንቅ አድርጎ የተኬደ ጉዞ......ሰው በምድር ሳለ ሊከውነው የሚገባን የህይወት ስንክሳር አኳኋን በተሞክሮ ያስተማረ ብዙ ነገር ነው አድዋ ማለት።
አድዋ ዕለት ነው
ሰው የማርቀቅ ዶሴ የተሰነደበት
አድዋ ወቅት ነው
ነፃነት አሽቶ የተቀመሰበት
አድዋ ቦታ ነው
የመዳን ደም ፈልቆ ህዝብ ያጠመቀበት
አድዋ ጥበብ ነው
ህያው ፍልስፍና ምጥቀትን ያኖረ
አስገዳጅ መግነጢስ ግርምት የፈጠረ
አድዋ ፊደል ነው
ወደው የሚያጠኑት ፈቅደው የሚያነቡት
ህያው መፅሐፍ ነው።
.....💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

mnase tamrat:👇👇👇

አድዋ
የአንድነታችን ውጤት
የህብረታችን ማሳያ
የኢትዮጵያዊነታችን መሠረት
የመደመር ቀመር መጀመሪያ
የነፃነታችን ማብሰሪያ
ድልን ክብርን ማንነትን አብሮነትን
በአንድ ላይ የተጎናፀፍንበት ቀን
"የደመቅንበት ቀን"

Meklit:👇👇👇

Adwa lene..... ETHIOPIAWIT yemilew ma'erege yetetsafebet be'er new....

Feker abe Weeknd💞💓🥊🥊🥊🥊💖💕💘💝💕:👇👇👇

ዝክረ አድዋ
እስኪ ከአድዋ ድል ምን የተማርኩት ነገር አለ? ስል እርሴን ስጠይቅ ከተለያየ የተውጣጣ የመጣን ህብረተሰብ በአንድ ጥላ ስር ሰክን ባለ መልኩ ህብረተሰቡን አሰባስበው አንድ ሆነው ጠላትን እንዴት ድል ማድረግ እንዳለባቸው ወስነው በአንድነት በአጭሩ ድልን ተቀናጅተዋል ።

አሁን እኔ እንደሚመስለኝ ስትሰባሰብ አንድ ስንሆን ምን ያህል እማይቻል ነገር እንደሚቻል እንዴት አስፈሪም እንደምንሆን እንደምንከበርም ጭምር በማንኛውም ዘርፍ ላይ ህብረት አንድነት ምንያህል ሀይል እንዳለው እማይቻል እሚመስለውን ገድል ሊፈፀም አንደሚቻል የተማርኩበት ነው ።ስለዚህ ቅድም አያቶቻችን የራሳቸውን ታሪክ ሰርተው አልፈዋል ።በአጭሩ በተባበርን አንድ መሆይንን በጋራ መስራትን በጋራ ማደግን እንማር እላለው ከተሳሳትኩም አርሙኝ😍

@balmbaras
@Gebriel_19
@getem
@getem
👋ጄሪ ዲምፕል:👇👇👇

አድዋ ማለት ማንነታችን ነው
አድዋ ማለት ቋንቋችን ነው
አድዋ ማለት መሰረታችን ነው
ብቻ አድዋን ሀረግና ፊደላት ተደራርበው የማይገልፁት የማይተኩት የኛነታችን መሰረት ነው።
የትላንት ጀግኖቻችን ለዚህ አበቁን
ኢትዩጽያ ለዘላለም ትኑር።

አድዋ

Neba Ye abatua lj:👇👇👇

adwa malet lene yetkur hzbochi enba yetabesebet ye andnetachin masaya nechi keler enji mnm grma edelelew yasayubet Ethiopia jegna korat ena adegegna hager mehonuan yasayubet beka adwa malet lene lgeltsew yemalchlew yewst smet malet nw

jo jo:👇👇👇

adwa malet ye netsanetachen belen becha yemenasebew aydelem mekenyatum ashenafiwoch nen ena ye deel kenachen new be adwa mekenyat 14 ye africa hageratoch bandirachewen kegna amesaslewal yegna becha aydelem ye africa kurat new ena adwan basebku kuter yehone seweneten neezer yadergegnal,ahun ahun geen egna ahun yet nen abatochachen yet neberu

$ ï$ kîñg:👇👇👇

ሰላምታየን ሳቀረብ ከራሴ ዝቅ ከጉልበቴ በርከክ ብዬ ነው. ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ስለሆንክ በተለይ ሰው ሁሉ ስለ ራሱ ስለ ብሔሩ ስለ ክልሉ በሚያወራበት ሰአት አንተ ስለ አድዋ. ሁሉን አንድ ስለሚያረገው ስለ አድዋ እናውራ. እንወቅ ስላልክ ነው አድዋ !!!! አድዋ!!!! አድዋ. በአጠቃላይ አድዋን ስናስብ መሪውን. እምዬን ሚኒሊክን መርሳት የለብንም. አሊጫው መረቁ ወጡም ሰለቸኝ ሚኒሊክ ተነስቶ ሽሮ ባበላኝ መልካም አዳር ወዳጄ

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️


ሁላችሁንም እጅግ በጣም እናመሰግናለን🙏🙏ስለ አድዋ ስታስቡ የሚሰማቹን፣የምታስቡትን እና ስሜታቹን አጋርታችሁናልና ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏



*ሚኪ🙏
*ዮቶድ🙏
*b k ✔️bk tm🙏
* ስንት አየሁ አለም አየሁ🙏
*mnase tamrat
*meklit🙏
*feker abe weekend
*ገብርዬ🙏
*neba yeabatwa lij🙏
*jo jo🙏
*$i$ king🙏

@getem
@getem
@balmbaras

አድዋ መሬት ላይ እምቢልታ አታሞ ድምፀ ነጋሪት
ሰምቼ ነበረ ሲባረር ወራሪ ሲባረር ፍሺስት...

-ታምራት ጀምበሩ-

@getem
@getem
@gebriel_19
ነጩ ፈረስ ማን ነዉ?
ከአድዋ ጦር ማግስት
በቆሰለ አርበኛ የተማረከ ሰው
እልፍኝ ውስጥ ሆኖ እንደዚህ ጠየቀ…
"ሲወጋ፣ሲያዋጋ፣ሲያጠቃን የነበር
ነጩ ፈረስ የታል?"
ይሄ …ነጭ ወራሪ ይቀልዳል ልበል?
ነጩ ፈረስማ...
ጦርነት ስትለፍፍ ፣ ድንበር ስትገፋ
መሬት ስትቆፍር ፣ ዱካ ስታሰፋ
ይቅርብህ እያለ ምክር ያቀረበው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው
ነጩ ፈረስማ...
አይገባውም ብለህ ፣
አልተማረም ብለህ
እንደ ስፔን ፣ ፓርቹጋል እንግሊዝ ተመኝተህ
አፍሪቃ ምድር ላይ ግዛት ልያዝ ብለህ
ሰውነቱን ንቀህ
በጥቁረቱ ስቀህ
በብረት ካቴና አስረህ ያደማኸው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው!
ነጩ ፈረስማ...
ከኤርትራ ምድር መቀሌ አምባላጌ፣
ማን አለብኝ ብለህ ስትገፋ ስትወርረው
አይገባውም ብለህ
ውጫሌ ምድር ላይ
በቃላት ውስጥ መርዝ
ለውሰህ ሰጥተኸው
እውነቱን ተርጉሞ
"እምምቢ" ያለህ ሰው ነው!!
ነጩ ፈረስ የታል?
ነጩ ፈረስ የታል??
ይሄ ነጭ ወራሪ ይቀልዳል ልበል??
ነጩ ፈረስማ...
ያንተን ስልጡን ሀገር ፣
የሰለጠነን ሰው
የዘመነውን ጦር ፣
የታጠቀን አረር መትረየስ ሳይፈራ ፣ መድፉን ቁብ ሳይሰጠው
እምቢ ላገር ብሎ የተዋጋህ ሰው ነው!!
ነጩ ፈረስማ...
ነጩ ፈረስማ...
ተደፈርኩኝ ብሎ ከሰሜን፣ደቡብ ጫፍ
ምዕራብ ምስራቅ ነቅሎ
የከፋ ዘመኑን ፣ የሆድ ስሞታውን
ከመደፈር በታች አቅልሎ አሳንሶ
ግማሹ በጸሎት ጨፌውን ነስንሶ
ግማሹ በወኔ ጎፈሬውን ነቅሶ
እንደ አንበሳ አግስቶ ፣
እንደ ነብር ዝቶ
በምታ ነጋሪት ሁሉም በአንድ ከቶ
አድዋ ምድር ላይ
በጦር በጎራዴ የተጋፈጠህ ሰው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው!!
ነጩ ፈረስ የታል?
ነጩ ፈረስ የታል?
ይኼ… ነጭ ወራሪ ይቀልዳል ልበል?!
ነጩ ፈረስማ...
የጣይቱን ምክር ያባ መላን መላ
እሺ ብሎ ሰምቶ በልቡ እያብላላ
የእቴጌዋን ምክር ትዕዛዝ አክብሮ
የምትጠጣውን ምንጭ ከብቦ ተቆጣጥሮ
ውሃ ውሃ ያሰኘህ ደንቆሮ ነው ያልከው
አላወክም እንጂነጩ ፈረስ ያ ነው!!
ነጩ ፈረስማ…
ነጩ ፈረስማ...
እምነት በልቡ አስሮ
አንድነት አክብሮ
ፈጣሪውን ሰምቶ
ከራሱ ጋር ታርቆ
ጦርና ጎራዴ ባጭር ባጭር ታጥቆ
ሆ…ብሎ ሲመጣ ሆ…ብለህ ተኩሰህ
አገር ትኑር ባለ … አገር ትኑር ባለ
አገሩ ላይ ገድለህ
እሳት የሚተፋ ባሩዱ ሲያልቅብህ
በቀደመው ጥይት ቆስሎ የማረከህ
ደሙ እየፈሰሰ ውሃ ጠጣ ያለህ
አይገባውም ብለህ ንቀህ የደፈርከው
ንቀቱን ዋጥ አርጎ አንተን የማረከው
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያ ነው
ነጩ ፈረስማ…
መቀሌ አምባላጌ ዶግ አመድ አድርጎህ
በአድዋ ተራሮች እፍረት አከናንቦህ
ባቆሰልከዉ ጀግና እፍረት እጅ ሰጥተህ
ማተብ ባታከብርም ማተብ እያሳየህ
እልፍኝ አስገብቶ አብልቶ ያጠጣህ
ሮምን የጣለ አለም ያከበረዉ…
የጥቁር ህዝብ ኩራት መመኪያ የሆነው
ለማረከው ግብር ጥሎ ያጠገበው
የአድዋው ጀግና የቴዎድሮስ ልጁ
የዮሃንስ ወንድም የጣይቱ ባሏ
አላወክም እንጂ ነጩ ፈረስ ያልከው
የጥቁር ህዝብ ኩራት
ንጉሥ ምኒሊክ ነው!!!
ነጩ ፈረስ ማን ነው??
(በ ሰለሞን ሳህለ)
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍1
ምኒሊክ !!!!!!!!!!!!!!!!!!

ምኒሊክ ተወልዶ ፤
ባይተኩስ ናስማሰር ፤ ባያነሳ ሞይዘር ፤
ባንዳና ሰላቶ ፤
ፓስታ እያስቀቀለ፤ ተጫውቶብን ነበር ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባይባል ነፍጠኛ ፤
ተሸከም እያለ ፤
ተጫውቶብን ነበር ባንዳና ጎጠኛ ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባይባል እምዬ ፤
መይሳው ጃሎ ሲል ባይመጣ ገብርዬ ፤
አገር ሞታ ነበር ኧረ እናንተ ሆዬ ።
ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ዘገር ፤
ሹምባሻና ባንዳ፤
እንደዝክር ቂጣ፤
ቁርስርስ አድርጎ በጨረሰን ነበር ።
ምኒሊክ ተወልዶ ፤
ባድዋ ሰማይ ላይ ፤
ደመቅመቅ ብላ ፤ ባትወጣ ጠሃይ ፤
ጦቢያን ያህል ሃገር ፤ ይገኝ ነበር ወይ? ???

((( ጃ ኖ )))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
U°m P'rince':👇👇👇

"ታሪኩን የማያከብር ዜጋ ታሪክ ሊሰራ አይችልም " አድዋ ማለት ከታሪኮቻችን በላይ ነው ለ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የጥቁር ህዝቦች ኩራት ነን ስለዚህ እኛ ካልዘከርነው ጣሊያን አትዘክረውም

dan ab👇👇👇

አድዋ ለኛ ትልቅ ኩራት ነው......ጣልያን ያን ሁሉ መትረየስ ጠመንጃ ይዞ ለምን ተሸነፈ? ኢምንት የሀገር ፍቅር በልቡ ስላልነበረው ነው ነገር ግን አያቶቻችን የሀገር ፍቅር ስለነበራቸው መጀመሪያ ልባቸው ነው ያሸንፈው። ሌላው አያቶቻችን ጥበበኛ ነበሩ ብልህ....የሚገርመው አንድ ጥይት ለመቆጠብ ሁለት ሰው ሲደረብ አልመው በአንድ ጥይት ሁለት ሰው ያዳፍኑ ነበር........ሌላው አስገራሚ ነገር የጣልያን ወታደሮች ለሀገራቸው መሞቻ በድብቅ ጥይቶችን ይሸጡ ነበር። ስለዚህ ባጠቃላይ የአድዋ ጦርነት ልብ ባለው ሀገሩን በሚወድ እና ልብ በሌለው ሆዱን በሚወድ የተደረገ ጦርነት ነው........ልብ ያለው አሸንፏል፨

ክብር ደማቸውን አፍስሰው
አጥንታቸውን ከስክሰው
ላቆሙልን አባቶቻችን🙏

Heremela wubeshet👇👇👇

adwa yegeantachen meglecha ye nestantachen tergum legea le Ethiopiawiyan becha sayhon le Africawiyan kurat ye abat enatochache dem ena atent yetkeskesbet kebrebal adewa adewan saseb erfet yesmageal mekniyatum telatn yamiyabarer leb yetstege yezigeaw tewld tewkay nege tenant ensu yafesesut dem adera setogeal ena Ethiopian etadegat Zend atentachew yazgeal ena ewnt adwa ye adra kelbet nw selzi adera tekebay tewld enhun Ethiopia lezelalem tenur

@balmbaras
@Gebriel_19
@getem
@getem
አድዋ ኢትዮጵያ ነው።

አድዋ ነው ታሪክ
የኢ/ያ ጀግና የሚዘከርበት
ለኛ ለጥቁሮቹ መከታ የሆነበት
አድዋ ነው ቦታ ድል የተደረገበት
የሀገር ልዕልና ያልተደፈረበት
አድዋ ነዉ ጦርነት
<በነጭ አልገዛም
ጥቁር ነው ቀለሜ
ሀገሬ አትደፈር
እኔ እየኖርኩ ቆሜ>
ተብሎ የታወጀ ጦርነት ነበረ

አድዋ ነበር ድል
አድዋ ነፃነት
አድዋ ነዉ መኩሪያ
አድዋ ጀግንነት
አድዋ ኢትዮጵያ ነው
የአመት ታሪክ ነው
ትላንት የነበረ
የዛሬ ዝክር ነው

ኤደን

@getem
@getem
@getem
👍1
የአሉላ ኑዛዜ!!!!


ኣነ ወዲ ሰሜን፤
ኣነ ወዲ ጀግና፤
አነ ወዲ ጦቢያ፤
ድንበሬን ያፀናሁ፤
ቀይ ባህር ላይ ቆሜ፤ በጠባ በነጋ፤
ቃሌን ያከበርኩኝ፤
የምኒልክ ቀኝ እጅ፤
የጦቢያ ዘብ አደር፤
እኔ አይደለሁም ወይ፤
የሰሜኑ ሰንደቅ፤ አሉላ አባ ነጋ።


አይደለም የሞትኩት፤ ለሰፈር ለመንደር፤
አይደለም የሮጥኩት፤
በአጋም በኮርሽሙ፤
የወንድሜን ጎጆ ድካውን ለማጠር፤
ይልቅ፤
ምድሪቱን ጨርሼ፤
አፈሯን ቀልሸ፤
ያባቶቼን ድካ በደሜ ለክቼ፤
ደሜን ከውሃ ጋር፤
ቃሌን ከጦቢያ ጋር፤
በሞት እርሾ አቡክቼ፤
እኔ ነኝ አሉላ፤
እጣዋን የጋገርኩ፤ ቀይ ባህር ገብቼ።
ቼ!!!!
የምኒልክ ቀኝ፤ ያድዋ ገዳይ፤
አሉላ ጎራው አሉላ ሰማይ፤
ጎራዴው ታየ፤ አምባላጌ ላይ።


በክህደትህ ልክ ወርች አትሰረኝ፤
በሆድህ ቁንጣን አትቀፍረኝ፤
በመንደርህ ልክ አትደልድለኝ፤
ወደድክም ጠላህ፤
የአባ ነጋ ልጅ፤
የአባ ዳኘው ልጅ፤
ያድዋው ዘማች፤የምኒልክ ነኝ።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

@Balmbaras
@getem
@getem
የጠላሽ ይጠላ ያሳነሰሽ ይነስ
ከፍ በይ ኢትዮጵያ ስም ዝናሽ ይታደስ
ሱሴ ነሽ ኢትዮጵያ 💚💛❤️
ክብሬ ነሽ ኢትዮጵያ 💚💛❤️
ፍቅሬ ነሽ ኢትዮጵያ 💚💛❤️
አለሽ አለሽ አለሽ አለሽሽሽሽሽ💚💛❤️
አለሽ ልዩ ነገር ሌላውየማይገባው ከአምላክሽ በቀር💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

((( አለምፀሀይ ወዳጆ))

ሸጋ ጁምኣ!!!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
ሽኝት !!!!!!!

በፈራኡል እጆች፤
በዘንባላ ሚዛን ፤
በአስመሳዩች ችሎት ፤ ባሌን ብነጠቅም ፤
ለጭንጋፎች ብየ ፤
ለዱንያ ሰክሬ ለጃሂል አልወድቅም ።


እንኳን ለዲንና ለአለማቱ ጌታ ፤
ሰው እንኳን ይሞታል ባንድ አፍታ ትንታ ፤
ልቤ ተደናደን ጉልበቴ ሆይ በርታ ።


እምባ ያረገዙ የደከሙ አይኖቼ ፤
ፍቅር የለመዱት እርግብግብ እጆቼ ፤
ዛሬም መቃብር ዳር ፤ ደርሰው አልደከሙም ፤
ፍቅሬ የኔ አበባ ፤
ደህና ሁን ይሉሃል አሰለሙአለይኩም ።


አውቃለሁ ፤ አውቃለሁ ፣
ዳኛ ቢፈርድለት ፤ በችሎት ወንበር ስም ፤
ሰባብሮ ቢጥልም ፤ የወዳጅን ቅስም ፤
ጨካኙ ፈርኦን ፤
ዙፋኑን ነው እንጅ ፤ ጀነትን አይወርስም!!!!!

((( ጃ ኖ ))💚💛

ወንድሞቼ አላህ ጀነተል ፍርዶስን ይወፍቃቹ!!!!

@balmbaras
@getem
@getem
በጀግንነት አንባ ጀግኖች የሰሩተረን
ታሪኮንች ለቅሜ
ልፅፍ አስብና ግጥም እንዳ' ቅሜ
የፃፍኩለት ሁሉ ቃሉ ሳይመጥነው ነፃ
ማለት እሱ ዋጋው ምንያህል ነው?
ብዬ እጠይቃለሁ
በነፃ መተንፈስ
በነፃ መራመድ
በነፃ መናገር
ወይም ነፃ ሆኖ
በነፃ አለም እየዞሩ መብረር...ይህ የምልህ
በተግባር ሲተመን
የነፃው ሽልማት የማንነት ምግባር
ህሊና ብቻ ነው የድል ባለግንባር
እንደዚ በሆነው ንፁ አሸላለም
ከኢትዮጵያ ሌላ አንድም አርማ የለም
ብዬ እየተደመምኩ ባባቶቼ ስራ
ጀግንነት እንዲ ነው ልቤ ተነስ ኩራ
እያለ እሚያጀግን አንድ ስሜት አለኝ
እሱም ያንተ ፍቅር
በነፃ የተሰጠኝ
በድል ነፃ አርማ በቀለም ሸብርቄ
ሁሌም የማወራው
ላገኘሁት ሁሉ እምመሰክረው ታሪኬ ነው ብርቄ
እናልህ አለሜ
በነፃ ውል እስር እንደሀገሬ ክብር
ለፍቅርህ ወድቄ
የተረኩት ሁሉ ሰመመኑ ጭንቄ
ለኔ መዋቢያ ነው ማጌጫዬ ወርቄ
ፋኖ ልበል ዛሬም
ጀግንተነት ሲነሳ ጀግና ልብ ይቆማል
የጥላቻን መረብ ክንዱ ይበጣጥሳል
በአንድነት አርማ ነፃ ፍቅር አውጆ
ሊሰራ ይወስናል የመደመር ጎጆ...!!!
ክብር ለአባቶቻችን ....!!!
ፍቅር እንደ ሸማ ያላብሰን ...!!!
ተከተበ

በ ሮዚ የያቡ
A/D/F

@getem
@getem
@gebriel_19
ከያኒ ሚካኤልን ሚሊዮን ለክብረ አድዋ በተዘጋጀው ቡክሌት ላይ ቀጣዩን መልእክት አስተላልፏል። ዛሬ ምሽት በ12 ሰዓት ከ1700 በላይ ታዳሚ እንደሚገኝ የሚጠበቅበትን የዋዜማ ቴአትር በጣይቱ ሆቴል ተገኘተው.....ይካፈሉ።

መግቢያው 200 ብቻ ነው!

ክብረ ድግስ 💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
🇪🇹ከእምዬ ኢትዮጵያ ከታሪክ ማህደር
መች ተነግሮ ያውቃል የጀግኖቿ ነገር

💚💛❤️

ዘራፍ አካኪ ዘራፍ /
መች ይቀመጣል ዘራፍ ሲነሳ
ልቡ ድፍን ነው ልክ እንደ አንበሳ
አዋራው ጬሶ ደም ደም ሲመሥል
አባሮ ገዳይ ከዳመናው ስር
እኔ የዛ ሰው ነኝ የሀበሻ ምድር
ወኔን አስታጣቂ አሞቱ የሚመር
ከአንድ ወንዝ የምቀዳ ፡ የእሳት ልጅ ነኝ እሳት
የምኖር በክብር የምኖር በኩራት
ለሀገር መሞት ክብርን ያን ወኔውን ወሳጅ
እኔ የዛ ሰው ነኝ የጥቁር ደም ውላጅ
አደራ ጠባቂ የአካሉ ግማጅ
💚💛❤️

@getem
@getem
@sefisaosho
:::የደም ሐይቅ;;

ከአድዋ ማዶ ከተራራው ግርጌ
በሀሳብ ተጓዝኩኝ አንድ እውነት ፈልጌ
ሰው ለሰው አለቀ ሰው ለሰው ሞተለት
እማይሻር ታሪክ በደሙ ፃፈለት
አርበኛው አባቴ...
ይኸዉ አለውልህ ከሐይቁ ጠልቄ
ዘወትር እኖራለሁ በደም ተጥለቅልቄ
ቃሉም እውነት አለው ስቃዩ ይታያል
አጥንቱ ተሰብሯል
ውበቱ ረግፏል
የለበሰው ካባ በደም ተጨማልቋል
እኔ...
እባክህ አባቴ
ይኸው መሰላልህ
እኔ ላቀብልህ
ከዚያ ደም ውጣበት
በቢጫው ተራመድ ተስፋ በሞላበት
ከቆመው በአንድነት
ከሰማይ ሰማያት ፍንጣቂ አለበት
ከአርንጓዴው ግባ ዝናም ከወረደበት
ደምህን በሙሉ ጠርጎ ከሚያጥብበት
ከዚያ እኔን ትደርሳለህ
ልጅህ ከወዲያ ነኝ ትናፍቀኛለህ??
አባቴ...
ልጄ ተሳስተሀል
መሰላልህ ልክ አልቆመም
አስተካክለህ ከመሰልከው
ሠንሠለቱን ከወጠርከው
እኔ ወዳንተ አልመጣም አንተ ነህ ወደ እኔ በሀሳብ ምትደርሰው
እንደ ደራሽ ውሃ ቁልቁል የምትፈረው
ከአረንጓዴው ጀምር ከለመለመበት
ከአክሱም ፅዮን ፅላት
ከሳባ ንግስትነት
ከላሊበላ ቅርፅ ከጀጎል ግንብ ውበት
ከነተዋናይ ብዕር ከቅኔያቸው ልቀት
አንድ ነገር አድምጥ ከካሳም አንደበት
ከአርንጓዴው ጀምር ዝናም ከቆመበት
ዶፍ ከሚወርድበት
በቢጫው ተንበርከክ ስግደት ለስላሴ
ከአላህ ተማፀን ለነፍስህ ለነፍሴ
ዕርሱ በጥበቡ ኮኮብ ያደርግሀል
የተስፋው መቀነት በአንድነት ያስርሀል
ሠማያዊ ሠማይ ከሩቅ ይታይሀል
ያኔ ያኔ..
መንፈሴ ይረካል
ነፍሴ ይረጋጋል
ሞቴም እንቅልፍ ይሆናል
ሀውልቴም ይቆማል
ያኔ ከደሙ ሐይቅ ጠልቀህ ትገባለህ
እኔ ከወዲያ ነኝ ችለህ ትመጣለህ??

የካቲት 23 2009
ባታ አልሜ

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1