ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
🤔🤔🤔 #የገባኝ 🤔🤔🤔

በኖሩኳቸው ትንሽ ዕድሜዎች
ባየዋቸው ጥቂት ሁነቶች
ሁሌም የሚገባኝ
ሁሌም የሚታየኝ
መድረሻዬ ነው ፍቅርሽ
ማብቂያዬ ነው ሴትነትሽ
አየሽ በትላንቴ ሸራ በብሩሼ ቀለም
መልክሽን እንጂ አንቺን መሣል አልችልም
ሠነፍ አትበዩኝ ሠንፌ እኮ አይደለም
የዕውቀቴ መጠን በአንቺ አይለካም
ይለካ እንኳን ቢባል መለኪያ የለውም
ብቻ ምን አለፋሽ ድፍረትን ደፍሬ
ፍቅሬን በትዝታሽ ሚዛን ሠፍሬ
ይሄን አስመሰልኩት ምኞቴን ቀምሬ
ነገን በዛሬ ላይ አዲስ ቀን ጀምሬ
የአዙሪቴ ጥጉ አንቺ ሆነሻል ፍቅሬ

ግን እኮ መድፈሩንስ ልድፈር
ስህተቱም ይሁን በኔ ይጀመር
እኔ የምፈራው እኔ የምሰጋው
በአንቺ እየታሰብኩ
በአንቺ እየታወኩ
የኔ የምለው እኔነቴ ጠፍቶ
አንቺ እንዳልባል ወንድነቴ ቀርቶ
ስር የሌለው ቅፅል መሰረት መስርቶ
አንቺ ላጲስ ሆነሽ እስራስ ሆኜ እኔ
እየሳልኩሽ ኖሬ በአላቂ ዘመኔ
እየሳልኩሽ ልሙት ለፍቅር ስህል ቅኔ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
የጨለማ ጥግ
(ልዑል ሀይሌ)

ተስፋ አትስጪኝ ንጋቴ
መጨለም መምሸቱ ካልቀረ
ውሰጂው የነገ ጥጋቴን
በልብሽ መደብ ያደረ
ዘመናት ባደረ ተስፋ
እንድቋደስሽም አልሻ
አንቅሬ ተፋሁሽ ንጋቴ
ዳግም ሄድኩኝ በጨለማ
ዳግመኛ ታመምኩ በግርሻ
..
ይመስገነው!
ካንቺ አርቆ ከጨለማ ላዛመደኝ
ይመስገነው!
ካንቺ ሽሽት ወደ ወህኒ ላወረደኝ
ላመስግነው ተንበርክኬ
ለዚህ ላበቃኝ ፈጣሪ
ጨለማውን ባይፈጥርልኝ
ምን ይሆን ነበር እጣዬ
ንጋቴ ክደሺኝ ስትቀሪ

፲፯-፪-፳፻፲፩

@getem
@getem
@lula_al_greeko
# # እርብትብት ከንፈርሽ ያንገትሽ ስር ሽታ፤
ከሞትም ያድናል እንኳን ከበሽታ ።


# # ምነው ባደረገኝ ፤ ሆርማት ውሃውን ፤
ሸጋ በከንፈሯ ፤ የምትጠጣውን ።


# # የሸግየን ከንፈር፤ ወልምጠህ ወልምጠህ ፤
ወዴት ትሮጣለህ ፤ደረትክን ገልብጠህ ።
# # ገልጨ እንዳላየው፤ የደረቷን ክሳት ፤
ባሏ ጉልቻ ነው ፤ አይለይም ከእሳት ።


# # መገን የወሎ ልጅከንፈረ ወለላ፤
ሸጋ ልጅ ዘለቀች ፤
የምወድህዋ ፤ አብሽር ይሁን ብላ ፤
እንደ በልጅግ ጥይት፤ አምራ ተወልውላ ።

የተባለላቸው የወሎ ሸግየዎች እነዚህ ናቸው!!!!! መገን ወሎ!!!!

((( ጃ ኖ ))💚💛

የኔዋ ቅዳሜ!!! ሽብርቅርቅ ያለ እንደነዚህ ሸጋ ሴቶች ያማረ የተዋበ ቅዳሜ ትሁንልን !!!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
👍1
****ባ4ቱ ስሌቶች ****(ሳሙኤል አዳነ)

ምንም ሳንለወጥ
ቀናት እያለፋ፣
መኖር እና መሞት
እየተጣደፋ ፣
በኛ ላይ ሲከንፋ፣
ሰው ሰራሸ አበባ
መስሎ ልቦናችን ፣
በተፈጥሮ ዑደት
ሲቆጠር እድሜያችን ፣
ሲገዝፍ አካላችን ፣
ሲለወጥ ፀጉራችን፣
ባሮጌ ማንነት
ልደትን ማክበሩ ፣
መጫወት ካልሆነ
ቀን እየቆጠሩ ፣
ዘመድ እየጠሩ ፣
የኖርንበት ዘመን፤ባ4ቱ ስሌቶች
ዜሮ ነው ቀመሩ ።

13/09/08
6፡15 pm
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ኑሮው የጎደለ

እንዳልከተልሽ
ዳናሽን ሳትተይ ÷ ተንነሽ እንደ ውሐ
ስትሰወሪብኝ
ብቻዬን ቀርቼ ÷ ከጦፈ በርሐ
ጣእም እያማረጡ
ወይን እየቆረጡ ÷ እፁብ ማለት ቀረ
ጣዝማው እንደ ኮሶ ÷ ይመረኝ ጀመረ

አዝኛለሁና ÷ ከእንግዲህ እንደ ሰው
የሌት አድናቂዎች ÷ ከልቅሶ ቀስቅሰው
ተመልከት አይበሉኝ
ምሽቱ ሲፈካ ÷ ምን እንደመሰለ
በሙሉ ጨረቃ
ሊገረም አይችልም ÷ ኑሮው የጎደለ!
...
☞ ናትናኤል ጌቱ
@getem
@getem
@kaleab_1888
ብዥታ ሕይወት
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ያልደረቀ እንባ
ያልደረቀ ቁስል
የፈጣሪን ቁጣ
ፍርዱን የሚመስል!
.
የባጀ ሕሊና
እረፍት አልባ ብክነት
የሟጠጠ ተስፋ
የማይነሱት ውድቀት!
.
የተረሳ ሕልም
የታቀፈ ረመጥ
እያሉ መገለል
በሰው ተስፋ መቁረጥ
.
የማስመሰል እውነት
የድመት ምናኔ
የተዛባ ሐሳብ
"ይኽ ዓለም ለምኔ?"

የመላዕከ ሞት ጥሪ
የገሃነም ጫፍ ጨዋታ
የገነት ማፈግፈግ
የኑሮ መተታ!
.
የመነጎልኩት ሁሉ፤የተጻፉት ሁሉ . . .
በሕይወቴ ውስጥ አሉ!
ውድቀቴም. . .
የቁም ሞቴም. . .
ድካሜና ብክነቴም. . .
ያንቺው መሄድ ነው. . .
የሄደ እግርሽን ዳና ተከትሎ
ካስለመድሺው አድባር አንቺ የለሽ ብሎ
መዓት ሰፈረብኝ መዓቱን ጠቅልሎ!
.
@huluezih
@getem
@getem
👍1
++ሰለሞን ሳህለ++

ትናንት...
እንደ ከሰረ ሰዉ
ወዘናዬ ጠፍቶ ጭዉ ብዬ ነጣሁ
በደበኞች ደባ
አንገቴን ደፍቼ ግፍ እንደ ዉሃ ጠጣሁ
ዝም ብዬ ተቀጣሁ...
ጮክ ብዬ ተቆጣሁ...
ልክ አንቺን ሳገኝሽ
ከሲኦል ሆድ ወጣሁ

ዛሬ...
የዛሬዉን ትርጉም የዛሬዉን ፍቺ
እንዲህ ነሽ ይልሻል ተቀበይዉ እንቺ
ዉስብስብ ቋጠሮን ስቀሽ የምትፈቺ
ቀና እምታደርጊ ቀና ሰዉ ነሽ አንቺ
ምንም እንዳይገርምሽ!!!

@getem
@getem
@gebriel_19
አሁን እያየሁሽ … ቁንጅናሽ አለቀ
እጅሽ ከረደደ ፥ ከንፈርሽ ደረቀ
ጡትሽ እያነባ ፥ ከደረትሽ ጎርባ
እንደ ቀንድ አውጣ አንገት ፥ ተጠቅሎ ገባ
የወደቀ አንሶላ ፥ ከአልጋው በታች ወርዶ
እንደዚያ መሰለ ፥ ቆዳሽ ተጨማዶ
ምነው እኔኮ ነኝ
ያየሁሽ ያን እለት ፥ ከማንም ቀድሜ
ወንበር ለቀቅሽለት
ከእኔ እና ከእርጅና ፥ ማን ይበልጣል በእድሜ?

☞ ካፒቴን ናትናኤል
@getem
@getem
@kaleab_1888
መንግስት ያሸንፋል"
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ተምሬ ያደግሁት - መንግስት ት/ቤት
ያለሁባት ምድር - የመንግስት መሬት
ተምሬ ምሠራው - መንግስት መሥሪያ ቤት
የኔ ምለው ያጣሁ....
የህይወቴን ክልል - መንግስት እያጠረው
"ያንተ ነኝ" ስትይኝ....
የመንግስት እንዳልሆንሽ - የምጠራጠረው
ለምን ይመስልሻል........ ?
የኔ ነሽ ብል እንኳ...
መንግስት "የኔ " ካለሽ....
የኔ ብትሆኚም ፣ የመንግስት ሆነሻል።
...... ...... ..............................
እንጂማ እንዳይመስልሽ...
የግሌ ብትሆኚ ፣ አይደለም ጠልቼ
የምጠራጠርሽ...
እንዳይጋራኝ ነው ፣ መንግስትን ፈርቼ ።
ለዛ ነው የኔ ውብ
ያንተ ነኝ ስትይኝ ፣ የሚነሳኝ ጤና
ከህዝብ መሀከል ፣ እኔ አንዱ ነኝና
እንዳላጣሽ ብዬ
የመንግስት ማለት
የህዝብ ማለት ነው ፣ የምለው ስፅናና፡፡
መሄድም መምጣት ነው!
መንግስት ያስተማረኝ ፣ ህዝበ ፍልስፍና፡፡
.................. ........... ..........
ይልቅ እሱን ተይው....
"የኔ ነሽ ያንቺ ነኝ" - መባባል አይበጅም
የኔ ያንቺ መሆን፣
ያንቺ የኔ መሆን፣
በመንግስት እንጂ - በኛ አይፈረጅም።
*
*
እንደዚህ ነውና...
"የኔ" ሚለው ያጣ - ቀኑን የተቀማ
በኔና ባንቺ ዘንድ...
ባይኖርም ብርሀን - ባይኖርም ጨለማ
ቀን እስኪወጣልን ....
ቀን የወጣላቸው ፣ ሰዎችን እንማ ።
ይኸውልሽማ...
ፍቅሩን ለመጋበዝ ፣
በቸገረኝ ሰበብ ፣እየተበደረ
ውዱን ለማግኘት ሲል...
በታመምኩኝ ሰበብ ፣ ከስራ እየቀረ
ህዝብን የሚያጉላላ ፣ አንድ ሰው ነበረ ።
ነበረ የምልሽ ...
ያ ነበር እኔ ኘኝ ፣ የጠፋብኝ መላ
በየ መስሪያ ቤቱ...
እንደኔ ብዙ አለ ፣
ህዝብን እያስራበ ፣ ውዱን የሚያበላ
ፍቅሩን ለማግኘት ሲል ፣ ህዝብን የሚያጉላላ ።
............................................ ..
ይኸውልሽማ...
እዛ እኛ መስሪያ ቤት ፣
"ፀሀፊ" ምትባል ፣ የማታውቅ ፅፋ
ጭኗን እየናጠች...
የአለቃዋን አይን ፣ ተግታ ምታለፋ
አንዲት ሴት ነበረች ፣ የጠፋባት መላ
አለቃዋ ቢሮ ...
ከገባች አትወጣም ፣ ህዝብን "ችላ" ብላ፡፡
በየ መስሪያ ቤቱ...
እንደሷ ብዙ አሉ!
"ፀሀፊ" ተብለው ፣ ምንም የማይፅፉ
ባለቃ ተማርከው ፣ ህዝብ የሚፀየፉ፡፡
.............................................
ይኸውልሽማ....
የ"መንግስት' ማለት ፣
ትርጉሙ ያልገባው ፣ የህዝብ እንደሆነ
ዘብ ሆኖ ተቀጥሮ...
ህዝብን ይፈትሻል ፣ መንግስት እያመነ፡፡
በየ መስሪያ ቤቱ...
በር ላይ ተተክለው ፣ ዘብ ሆነው የቆሙ
ብዙ ሰዎች አሉ!
መንግሥት አሳልፈው ...
በፍተሻ ሰበብ ፣ህዝብን የሚያቆሙ፡፡
ይልቅ እንተወው...
"መንግሥት ህዝብ ነው
ህዝብ መንግስት ነው" ፣ መባባል አይበጅም
"የሱ" የኛ መሆን
"የኛ" የሱ መሆን
በመንግሥት እንጂ ፣ በኛ አይፈረጅም፡፡
@getem
@getem
@kaleab_1888
የቅዳሜ ማስታወሻ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ልባቸውን አይቶ
እግር የነሳቸው ፣ ቀርፋፋ ቀናቶች
ዘልዛላ ለሊቶች
እንደ ማቱ ሳላ ፣ እድሜ የሚያዘግሙ
ከሰኞ ተነስተው ፣ አርብ እስከሚያከትሙ
በስራ በትምህርት
በስብሰባ ብዛት
በሰበብ ባስባቡ ፣ ሲያቀጥኑኝ አክርረው
እንደ ጠቦት ቆዳ ፣ ሲሰቅሉኝ ወጥረው
በአማራሪ ቀኖች ፣ የማልማረረው
እራሴን ለማጥፋት
ብዙ ጊዜ አስቤ ፣ ሀሳብ ምቀይረው
ለቅዳሜ ስል ነው።
።።።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው ፣
አደረች አራዳ ፣ ዘፈን ይለቀቃል
አሳዳሪ አራዳ ፣አልጋቤቱ ያልቃል
እንደጉድ ይጠጣል ፣ ይሰከራል በጣም
ነይና ላሳይሽ
ቅዳሜ የቀረ ፣ ዘላለም አይመጣም።
።።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው
በየመጠጡ ቤት ፣ ገርበብ ያሉ ጭኖች
በየ ጎዳናው ላይ
ቆንጆ ሴት የጫኑ ፣ ጢኒኒጥ መኪኖች
በየ ፋርማሲው ቤት
ፅንስን የሚያመክኑ ፣ እንክብል ኪኒኖች
የሚያዘዋውረው
የሚመነዝረው
የሚያመነዝረው ፣ እንደጉድ ይበዛል
ፌስቡክ ላይ ምታውቂው ፣
በስካር ጠንብዞ
ፖስት የሚያደርገውን ፣ ሚሪንዳ ይገዛል
"ይህች ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው? " ፣ ብሎ ላይኩን ያባዛል።
።።።
ነይና ላሳይሽ
ጨዋ የሚባል ህዝብ ፣ ጠፍቶት ትርጓሜ
ቀሚስ የሚባለው
የት እንደሰረሰ ፣ አጥሮ እንደጷግሜ
የዝች ሀገር ጉዞ
ወዴት እንደሆነ ፣ መልስ አለው ቅዳሜ።
።።።
ነይና ላሳይሽ
የአልኮል ባህር ላይ ፣ የመረብ አጣጣል
መንግስት አልወርድ ያለው
ውስኪ እያወረደ ፣ ሴት ከቦት ይጠጣል
የቢራ ያጣ ሰው
ስለውስኪ አጠጣጥ ፣ አቃቂር ያወጣል
ጭፈራው ለጉድ ነው ፣
ጨፋሪው ብዙ ነው ፣ አያስጥልም ጠጠር
ዝቅ ቢሉ ጭን ነው
ጎንበስ ቢሉ ጡት ፣ ቀና ሲሉ ከንፈር
ነፃ ይታደላል
አንድ የሰከረ ሰው
እቺ ሀገር ወዴት ነው ፣ የምትሔደው ይላል።
።።።
ሁሉ እየተነሳ
ይቺ ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው ብሎ ፣ መጠየቅ ቢወድም
ነይ መልሱን ላሳይሽ
ወደ አልጋ ቤት እንጂ ፣ ወዴትም አትሔድም።
ዛሬ "ቅዳ" ሜ ነው
@getem
@getem
@kaleab_1888
~~~ውሰጂው~~~(ሳሙኤል አዳነ)

ካንች ስለይ ቀን
እሳቱ ቀዝቅዞ ውሀው አቃጠለ ፣
ሌሊቱም ቀረና ቀን ሁኖ ቀጠለ ።
*
አንችን ስለይሽ ቀን
ምድርና ሰማይ ቦታቸውን አጡ ፣
ጨረቃ ከዋክብት ድንጋይ አቀለጡ ።
*
አንችን ስለይሽ ቀን
መንፈሴ ተነክቶ ልቤ ተላወሰ ፣
ይጠላኛል ያልኩት ሰይጣን አለቀሰ።
*
እኔ አንችን ስለይሽ
ዛሬ የነበረው ትናንት እየሄደ ፣
ነገ የምንለው ዛሬ እየወለደ ፣
ቀን ቆጠራው ሁሉ ዝብርቅርቁ ወጣ ፣
ካላንደሩ ቀርቶ ጊዜው ቀመር አጣ ።
*
አንችን ስለይሽ ቀን
ስአታት ቀን ወልደው
ሳምንት አረገዙ ፣
አምና እና ዘንድሮ ሞተው ተገነዙ ።
*
የተለየሽኝ ቀን
አለኝ ያልኩት ሁሉ
እንደጉም በነነ ፣
ተፈጥሮው ጠፍቶበት
ጣቴ መዳፍ ሆነ ።
*
አየሽ
አንችን በማጣት ውስጥ
የተፈጥሮ ኡደት ስርአቱ ፈረሰ ፣
የጽሀዩ ብርሀን መጠኑ ቀነሰ፣
ጊዜ እንደፍቃዱ
ነገር እንደልኩ ተሰፋ አልተሰፋ ፣
ፍቅርሸ ቢሰውረኝ
ልክ የምለው ጠፋ ።
በዚህ ሁሉ መሀል
ልቤ እየተጓዘ፣
አለ እንደነቀዘ ።
*
እና ምን ልልሽ ነው
ያልሆነውን ሰጥተሸ
ልቤን ከምትጎጂው ፣
ብቸኝነት ሞልተሽ
ዉስጤን ከምታርጅው፣
እኔም ልቅርና
ዘመኔን ውሰጂው ።

21/07/ 2010
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ

@getem
@getem
@gebriel_19
...ስሜት ተጋሪዎች...

ከድንክ አልጋዬ ላይ ህልም አይቸ ማታ
የባ'ል ገበያ ውስጥ የትዳር ገበታ
ወይዛዝርት መበልት ስሜት ተጋሪዎች
ፍቅርን በድቃቂ ሳንቲም መንዛሪዎች
ምን አልባት ወደ ፊት ሴተኛ አዳሪዎች

ይህ አይመጥንሽም ይህም አይሆንሽም
ቅቅል አይጋብዝም ክለብ አያመሽም
ያኛው ዝምተኛ ዝጋታም ኮስታራ
ሁል ጊዜ ቁምነገር ቀልድ የማያወራ
ቀብራራ ገጠሬ ቪላ ቤት የሌለው
ገና በማህፀን አምላክ የበደለው

እያሉ በህብረት በማበር ሲዞሩ
በትዕቢት በጉራ እንደተወጠሩ
ከደራው ገበያ ጥሪት ሳይሸምቱ
በጠራራው ፀሐይ እንዲያ እነደዋተቱ
አንዳቸው ሳይዘግኑ ብፌው ባዶ ሆነ
ሰዓቱ መረሸ ገቢያው ተበተነ
ምሱ ፆም ማደር ነው
መውደድን በወረት በብር ለተመነ

©ዶ/ር ጌታነህ ካሴ ከዝቋላ(ፅፅቃ)

@getem
@getem
@gebriel_19
(ሚ)መ(ስ)ዶ(ማ)ሻ(ር)
(ልዑል ሀይሌ)

በእልፍ መዶሻ የተቀጠቀጠ
የጠበቀ ሚስማር፤
ከግድግዳ ታግሎ
መሸሸጊያ ሊያበጅ ተገፍቶ የሚማር፤
.
'ፍሬሙን' ለመስቀል
እየደበደቡት ለአካሉ ማይሳሳ፤
እኔ'ኮ ሚስማር ነኝ
መዶሻ ማልፈራ እየተደበደብኹ ይዤሽ የምነሳ፤
.
አትፍረጅ ባናፂ
ምስልሽን ሊሰቅል ለሚደበድበኝ፤
መዶሻውን ተይው
ከግድግዳው ጥጋት መ'ቶ ሚያላትመኝ፤
ብቻ ነይ ይስቀልሽ
ግድግዳው ላይ ኑሪ፤
ሕመሜን 'ረሳለሁ
ከነውብ ፀዳልሽ ከጎኔ ስታድሪ፤
.
እወድሻለሁ!!..
፳፮-፭-፳፻፲፩ ዓ.ም.
@getem
@getem
@gebriel_19
ቻው ማለት ምንድር ነው???


በሰው ጫካ መሃል፤
በሰው ጎርፍ መሃል፤ አዳም በሞላበት፤
ወንድም ጋሸ የሚል፤
የደግ ሰው ትንፋሽ፤
ያንጀት ባልንጀራ፤ ጓድ በጠፋበት፤
እንደምን ይገዳል፤
መሄድን እያዩ፤ ቻው ወንድሜ ማለት።


እንግዳማ፤
በዚህ በኛ ቀዬ፤
ሰው እንዳሸዋ ነው፤
እንደ ሰማይ ኮከብ፤
በየራሱ ዛቢያ የተመረገደ፤
ሩጫውን ይዟል፤
የራሱን ማድጋ፤
የራሱን ጎተራ ፤ ጎታ እየለበደ፤
እኛም ሰው መርግጎን፤
በብቻነት ሲቃ፤
ሽብሽብ ገላችን ላይ፤
ሲቃ እየቀደመን፤ እምባ እየወረደ፤
በዚያው በቆምንበት፤
ዘመንና ወዳጅ፤
እዝነትና ፍቅር፤
እሱም ወረት ጠልፎት፤ ቻው እያለን ሄደ።

((( ጃኖ ()

ሸጋ ምሽት !!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
++ምክር8+++(ሳሙኤል አዳነ)

አባት
ስማኝማ ልጄ..
በዚች ምድር ላይ ደስታን ስትፈልግ ፣
እህ በለኝና እምልህን አድርግ ።
*
ምክር 1
እድሜህ እንዲባረክ
ጉዞህ እንዲሰምር ፣
ታልቅህን አክብር
አባትህን ሰማ ፣
እናትህን ስማ ፣
ለታናሽህ ብስለት ሁንለት ዋዜማ
+
ምክር 2
በንባብ በእውቀት ራስህን ገንባ፣
የሰው ድንበር ዘለህ ባልገባህ አትግባ ።
አምሮ አለህና ጥንትም ስትፈጠር ፣
በጎውን ተመልከት ክፈትን አትቁጠር ።
+
ምክር 3
ለጓደኛህ ታመን እንደራስህ ውደድ ፣
ይጎዳሀልና በሱስ አትጠመድ ፣
ስርቆት ይቅርብህ ውሸትም አትልመድ፣
በአይንህ ያየህው ፤
የሰማሀው ሁሉ ልክ አይሆንም እና ፣
በምልካም ስራ እንጅ በክፋት አትቅና ።
+
ምክር4
መብላትን ከወደደህ መስራትን አትጥላ ፣
ማንንም ለመርዳት አትበል ወደኋላ፣
ፌስቡክ ላይ ተጥደህ
ሀገር አታባላ ፣
ነገር አታብላላ ።
+
ምክር 5
ግልፍተኛ አትሁን ስከን ተረጋጋ ፣
ከውሳኔህ በፊት ማስተዋል አትዘንጋ ፣
ጥርስህን አሳይተህ ልብህን አትዝጋ።
ልክ አይሆንም እና አፍ ከልብ ሲልቅ ፣
ካልሲህን ለመስጠት ጫማህን አታውልቅ ።
+
ምክር 6
ሁሉን ለኔ አትብል ልክህን እወቀው ፣
ያለህን አክብረህ ኑሮህን አድምቀው ።
በራስህ ተማመን በሁሉም አትንፈስ ፣
እንደመስኖ ውሀ በመሩህ አትፍሰስ ።
+
ምክር 7
ሰላም እንዳይርቅህ ክብር አንዳያሳጣህ ፣
በህይወት እስካለህ ክፉ ቃል አይውጣህ ።
ሰማህ ልጄ...

ልጅ
እየስማሁህ ነው ፣
ቀጣዩስ ምንድን ነው ?
+
7ቱን ምክሮቸን አጥብቀህ ያዛቸው ፣
ከማዳመጥ አልፈህ
ሰርተህ ኑርባቸው ።
=
ምክር8
ሰው ሁን !!!

13/05/2011
5:00pm
አ.አ

@gebriel_19
@getem
@getem
ጋሻውን ተዪና.....
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አንቺ ወዲያ ማዶ ፣ እኔ ወዲህ ማዶ
ናፍቆት ሲያሰቃየን
ልባችን ተጣምሮ ፣ ነፍሳችን ተዋዶ
ባያገናኘንም ፣ ተራራው ተንዶ
መጥቼ እንዳላይች
መጥተሽ እንዳታዪኝ ፣
መንገዱ ርቆብን ፣ጉልበታችን ርዶ
ድምፄ ሲናፍቅሽ
ድምፅሽ ሲናፍቅሽ
ከስልጡን ሀገራት ፣ ስልጣኔን ወስዶ
ጋሻውን ተዪና
ስልክ ባያነሳ ፣ ምኒሊክ ተወልዶ
እንገናኝበት ፣ መሥመር ሲቸግረን
በቀጭኑ ሽቦ ፣ ባያነጋግረን
እንኳንስ ሀበሻ
እኔናንቺ ራሱ
እንቁላል ነበርን ፣ ናፍቆት የሚሰብረን፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንዲ እንደዛሬው
እንደ እጅ አሻራ
በየሰዉ መዳፍ ፣ ሳይገባ ካሜራ
ምስሌን ማየት ሲምርሽ ፣ ምስልሽ ሲናፍቀኝ
መጥቼ እንዳላይሽ ፣ መንገዱ ሲርቀኝ
መጥተሽ እንዳታዪኝ ፣ ርቆሽ መንገዴ
ምኞት ብቻ ሲሆን ፣ መውደድሽ መውደዴ
እንተያይበት
መፍትሔ ስናጣ ፣ ሚጋርደን በዝቶ
ጋሻውን ተዪና
ሚኒሊክ ተወልዶ ፣ ባያነሳ ፎቶ
ባይጨብጥ ካሜራ ፣ መተያየት ሲያምረን
እንኳንስ ሀበሻ
እኔናንቺ ራሱ
እንቁላል ነበርን ፣ አምሮት የሚሰብረን፡፡
፡፡፡፡፡፡
እንደው ሌላው ቀርቶ
አንቺም ሴት ነሽ እና
ሴት አክባሪ ልቤ ፣ ለሴቶች ሲባባ
በኩሬ በምንጩ
እንስራዋ ከብዷት ፣ሴት ልጅ ስታነባ
ጋሻውን ተይና
ሚኒሊክ ተወልዶ ፣ ቧንቧ ባያስገባ
ሸክም የሚሰብረው
እንቁላል ነበረ ፣ የስንቷ ሴት ጀርባ፡፡
፡፡፡
እናም እልሻለሁ
ለብዙዎች ችግር ፣
መፍትሔ የሚሆን ፣ ሚኒሊክ ተወልዶ
እያሱ የሚሉት
ፀሐይን ሲያቆማት
ሚኒሊክ ከሰማይ ፣ ፀሐይን አውርዶ
ለሀገር ምስራቅ ሆኖ ፣ ስልጣኔን ማልዶ
በሀገር ምድር ነጋ
ሌላው ሌላው ቀርቶ
መንገድሽ መንገዴ ፣ በርቀት ሲዘጋ
ጋሻውን ተዪና
ምኑሊክ ተወልዶ
ባቡር ባያነሳ ፣ ሀዲድ ባይዘረጋ
እንገናኝበት ፣ መንገድ ሲቸግረን
ባካል መገናኘት ፣ መተቃቀፍ ሲያምረን
እንኳንስ ሀበሻ
እኔናንቺ ራሱ
እንቁላል ነበርን ፣ መንገድ የሚሰብረን፡፡
።።።።።
ብቻ ምን አለፋሽ
ብቻ ስንቱን ላውራሽ
በያንዳንዱ ሰው ውስጥ ፣ ተፅፏል ታሪኩ
ሚኒሊክ ነው ወዙ
የነፃነት ሳይሆን
የድል ቀን የሚያከብር ፣ የኢትዮጵያዊ መልኩ፡፡
።።።።።።
ብቻ ምን አለፋሽ
ብቻ ስንቱን ላውራሽ
እንኳን ለኔና አንቺ
እንኳን ለሀበሻ
እንኳን ለሀገሩ
ለአህጉሩ የተረፈ ፣ ነው የብርሃን ታሪክ
እምዬም አብዬም ፣ አንዱ ሰው ሚኒሊክ፡፡
።።።።።።።።።።
"ሚኒሊክ ተወልዶ ፣ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ፣ ይህን ጊዜ ሐበሻ"
@getem
@getem
@kaleab_1888
የናፍቆት መድሀኒት
~~~~~~~~~~~
ናፍቆት ልቤን ሰልቦ ... ሲገዘግዘኝ==
ፓራስታሞል ሆኖ ... ድምፅሽ ፈወሰኝ
ደጋግመሽ ደውይ
ከስልኬ ጫፍ ላይ መድሀኒት እንዳገኝ

© ዳንኤል ከበደ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

@getem
@getem
@gebriel_19
ቀና ብዬ ቀረሁ
.
.
ለሊቱ ረዘመ...
በኮከብ ቦግ እልም፥ ሰማዩ ሲሞላ
ፍጥረት ፀዳልሽን
ብርሃንሽን ረስቶ
ጠባቂ የለሽም ..ከኔ አይኖች ሌላ።
.
.
ቀና ብዬ ቀረሁ
.
.
የጊዜን ሰሌዳ፥
ዓለሜው ሸምድዶ፥
ከየኮከቡ ጋር፥ እጣውን ገመደ
የጨለመ መርሳት፥
ለፈካ መዘመር፥
የጠፋን መዘንጋት፥
የበራን ማወደስ፥ ህዝበ አዳም ለመደ
ከኔ ልብ በቀር፥
በምድር ደረት ላይ ፥
አንድም ፍጡር የለም፥
በቦግሽ ትዝታ፥
ክሱም እውነታሽ ላይ፥ ነፍሱን የጠመደ።
.
.
ቀና ብዬ ቀረሁ
.
.
በመንጋጠጥ ብዛት፥
የተወጣጠሩ፥
ያንገቴ ጅማቶች፥ ረግበው መሬት ላሱ
ተሳቢ ተራማጅ፥
ተጎታች ነፍሳቶች፥
ከማይንቀሳቀስ፥
ሀውልት አካሌ ላይ፥ መኖሪያ ቀለሱ
ከኮከብ አንብበው፥
በእጣ ፋንታቸው፥
ተስፋ እየቆረጡ፥
ሀገር የቀየሩት፥
ዓለምን አስሰው፥ ደክመው ተመለሱ
የኔ አይኖች ብቻ
ከየማቀፊያቸው
ከየስርጉዳቸው
ናፍቀው ተፈልቅቀው፥ ወደውጭ ፈለሱ።
.
ቀና ብዬ ቀረሁ
ቀ'ና ሁኜ ቀረሁ
ከበድን ትዝታሽ፥
ካስከሬን ትውስታሽ፥ ማር እየናፈኩኝ ማርጀት ምድረ በዳ፥
ማጣት በረሃ ላይ፥
ከቢሆን ዐለትሽ ፥ ውሃ እያፈለቅሁኝ ጎረምሳ ተስፋሽን፥
ከጃጀ ካረጠ፥
ከተጎሳቆለ
ሞት ከተዋደደ፥ ተስፋዬ አዳብዬ
.
መምጣትሽ ላይበጀኝ፥ ቀረሁ ቀና ብዬ።

@getem
@getem
@paappii

By Rediet Aseffa!
👍2
Forwarded from SPACE COMPUTER
👍1