~~~ብርሀን ጨለማ ነው~~~(ሳሙኤል አዳነ )
*
ከፍ ብለህ ስትታይ ሂወትህ ሲበራ ፣
ስኬትን ስታገኝ ከእውቀትህ ጋራ ፣
አለሁ ባይ ይበዛል
ሰላም ነህ ይልሀል ሁሉም በየተራ።
*
ሂወት እጣ ሁና ቁልቁል ስታወርድህ ፣
ፀዳሏን ሰውራ ፅልመት ስትጋርድህ ፣
ውበትህ ረግፎ ፤ሰውነትህ ፈርሶ ፣
እጅና እግርህ ዝሎ፤ ፊትህ አፈር ለብሶ ፣
ያየህ ወዳጅ ሁሉ ትናንት ያከበረህ ፣
አበደ ይልሀል እንዲያ ተቸግረህ ።
*
ያጨበጨበልህ በደስታህ ባህር
አብሮህ እየዋኘ ፣
በቅቤ ምላሱ ሀብትህን ያገኘ ፣
እጂህ ባዶ ሲሆን
ሰለቸህውና ሞትህን ተመኘ ።
*
ይሄ ሁለት እግር ..
ሲኖርህ እያየ ስቆ ይሾምሀል ፣
እንቅፋት ሲመታህ እኔን ይልልሀል ፣
እንደ ፃድቁ እዮብ ሁሉን ያጣህለት
ርቆ ይሸሽሀል ፣
እሰይ የት አባቱ እያለ ያማሀል ፣
በሂወት እያለህ በቁም ይቀብርሀል ።
*
እናልህ ወዳጄ
ትናንት ዛሬ አይደለም ጊዜ ይለወጣል ፣
ምንም ያልኖረህ ለት
የቀለብከው ባሪያ ባንተ ላይ ይቆጣል ፣
የበራልህ ሻማ ጨርሶ ይቀልጣል ፣
ያኔ ስትጎሰቁል ድህነት ሲረግጥህ
አለሁ ባይ ይታጣል ፣
ከሌለህ የለህም ብርሀን ጨለማ ነው
እርሱም ተገልብጦ ጀርባውን ይሰጣል ።
በዚህ ሁሉ መሀል ..
ፈጣሪን መደገፍ ከሁሉ ይበልጣል ፣
አድስ ቀን ያመጣል ።
07/09/08
5፡30 pm
ወልዲያ ዩኒቨርስቲ
@getem
@getem
@gebriel_19
*
ከፍ ብለህ ስትታይ ሂወትህ ሲበራ ፣
ስኬትን ስታገኝ ከእውቀትህ ጋራ ፣
አለሁ ባይ ይበዛል
ሰላም ነህ ይልሀል ሁሉም በየተራ።
*
ሂወት እጣ ሁና ቁልቁል ስታወርድህ ፣
ፀዳሏን ሰውራ ፅልመት ስትጋርድህ ፣
ውበትህ ረግፎ ፤ሰውነትህ ፈርሶ ፣
እጅና እግርህ ዝሎ፤ ፊትህ አፈር ለብሶ ፣
ያየህ ወዳጅ ሁሉ ትናንት ያከበረህ ፣
አበደ ይልሀል እንዲያ ተቸግረህ ።
*
ያጨበጨበልህ በደስታህ ባህር
አብሮህ እየዋኘ ፣
በቅቤ ምላሱ ሀብትህን ያገኘ ፣
እጂህ ባዶ ሲሆን
ሰለቸህውና ሞትህን ተመኘ ።
*
ይሄ ሁለት እግር ..
ሲኖርህ እያየ ስቆ ይሾምሀል ፣
እንቅፋት ሲመታህ እኔን ይልልሀል ፣
እንደ ፃድቁ እዮብ ሁሉን ያጣህለት
ርቆ ይሸሽሀል ፣
እሰይ የት አባቱ እያለ ያማሀል ፣
በሂወት እያለህ በቁም ይቀብርሀል ።
*
እናልህ ወዳጄ
ትናንት ዛሬ አይደለም ጊዜ ይለወጣል ፣
ምንም ያልኖረህ ለት
የቀለብከው ባሪያ ባንተ ላይ ይቆጣል ፣
የበራልህ ሻማ ጨርሶ ይቀልጣል ፣
ያኔ ስትጎሰቁል ድህነት ሲረግጥህ
አለሁ ባይ ይታጣል ፣
ከሌለህ የለህም ብርሀን ጨለማ ነው
እርሱም ተገልብጦ ጀርባውን ይሰጣል ።
በዚህ ሁሉ መሀል ..
ፈጣሪን መደገፍ ከሁሉ ይበልጣል ፣
አድስ ቀን ያመጣል ።
07/09/08
5፡30 pm
ወልዲያ ዩኒቨርስቲ
@getem
@getem
@gebriel_19
ጠሀይ አትሞቅሞ አትነድም ስትሉ፤
ጎሞራው አይሞቅም ለብ ነው ስትሉ
አቃጥሎ ሚፈጀው ሰላቶና ባንዳን ከነ ግትልትሉ፤
እ(ኢ)ሳት ሊመጣ ነው እንግዲህ ምን ትሉ??
💚💛❤️ ሸጋ ቀን!!💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
ጎሞራው አይሞቅም ለብ ነው ስትሉ
አቃጥሎ ሚፈጀው ሰላቶና ባንዳን ከነ ግትልትሉ፤
እ(ኢ)ሳት ሊመጣ ነው እንግዲህ ምን ትሉ??
💚💛❤️ ሸጋ ቀን!!💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
እርሙን ተደፋፍሮ አንድ ቀን ቢዋጋ፣
አላስቀምጥ አለን ያንኑ እየወጋ።
(( የአንድ ባላገር ))💚💛❤
ግጥሙ ለሚመለከተው ሰውዬ ትሁንልን😜
@getem
@getem
@balmbaras
አላስቀምጥ አለን ያንኑ እየወጋ።
(( የአንድ ባላገር ))💚💛❤
ግጥሙ ለሚመለከተው ሰውዬ ትሁንልን😜
@getem
@getem
@balmbaras
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
✍✍ለጥቁር ጠቢባን✍✍
ምስጋና ለነሱ
ኢትዮጵያ ላነሱ
በጥበብ አጥምቀው ላቀኗት
ሀገሬን በዕውቀት ላደመቋት
ምስጋና ለጠቢባን አበው
ቀለምን ለፃፋ ፍቀው ብራና
ለዓለም ላበሩ የጥበብን ፋና
ላቀኑልን ዛሬ የኛንም ጎዳና
ለጥቁር ጠቢባን ለነሱ ምስጋና
ከጥበብ ከቅኔ
በፊደል ምጣኔ
የሰዋሰው ጅረት
ለኛ ላፈሰሱት
ከዕፅዋቱ ቀልመው
ቆጥረው ላስቆጠሩን
አዚህ ላደረሱ
የጥቁር ሙህራን
ምስጋና ለነሱ ለአርበኛ ጠቢባን
ዕውቀትን ላባሩ
ቀድመው ለበረሩ
ሊቃውንተ አበው የአቢሲኒያ ፋና
ስንቱን ላሸበሩ በዘመን ጎዳና
የጥበብን ምርኩዝ
የማይጠፋ ኩራዝ
ለኩሰው ለሰጡን
ምስጋና!!!ለነዛ ጠቢባን
ሊቃውንት
በጥበብ አብዝተው
ሀገሬነን ላቀኗት
✍✍ተፃፈ በጃህፈር
29/05/2011 ዓ.ም
ወለጋ መካነ አእምሮA
@getem
@getem
@gebriel_19
ምስጋና ለነሱ
ኢትዮጵያ ላነሱ
በጥበብ አጥምቀው ላቀኗት
ሀገሬን በዕውቀት ላደመቋት
ምስጋና ለጠቢባን አበው
ቀለምን ለፃፋ ፍቀው ብራና
ለዓለም ላበሩ የጥበብን ፋና
ላቀኑልን ዛሬ የኛንም ጎዳና
ለጥቁር ጠቢባን ለነሱ ምስጋና
ከጥበብ ከቅኔ
በፊደል ምጣኔ
የሰዋሰው ጅረት
ለኛ ላፈሰሱት
ከዕፅዋቱ ቀልመው
ቆጥረው ላስቆጠሩን
አዚህ ላደረሱ
የጥቁር ሙህራን
ምስጋና ለነሱ ለአርበኛ ጠቢባን
ዕውቀትን ላባሩ
ቀድመው ለበረሩ
ሊቃውንተ አበው የአቢሲኒያ ፋና
ስንቱን ላሸበሩ በዘመን ጎዳና
የጥበብን ምርኩዝ
የማይጠፋ ኩራዝ
ለኩሰው ለሰጡን
ምስጋና!!!ለነዛ ጠቢባን
ሊቃውንት
በጥበብ አብዝተው
ሀገሬነን ላቀኗት
✍✍ተፃፈ በጃህፈር
29/05/2011 ዓ.ም
ወለጋ መካነ አእምሮA
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
###ልጅ በእድሉ###
ይሄ ፀያፍ ብሂል፤
ከጥንት ጀሞሮ፤
ውስጤን ሲየሠሳክከኝ፤
አጥንቴን ሰርስሮ፤
ማወቅ እሻ ነበር፤
አንክሮ እና ንዴት፤
በደሜላይ ሰፍሮ።
በእቅፋችሁ ሆኖ፤
ላደገው ልጃችሁ፤
ልጅ በእድሉ ያድጋል፤
አይዞህ እያላችሁ፤
እንዲህ በማባበል፤
ምን ተጠቀማችሁ።
ያም ሆኖ
ያ የዋህ ልጃችሁ፤
ያላችሁትን ይዞ፤
በዚያ ክፉ ብሂል፤
ውስጡ ተመርዞ፤
እንዳላችሁት ወጣ፤
እድሉን ፍለጋ፤
ውቧ ጀንበር ጠልቃ፤
ምሽቱ እስኪነጋ።
ልቡም እጅግ ጏግቶ፤
ፍለጋ ጀመረ፤
እድሌን እንዳለ፤
እንደወጣ ቀረ።
ብላችሁት ነበረ፤
ልጅ በእድሉ ያድጋል፤
ይኸው ለእጣ ፈንታው፤
ሲሄድ እየመሸ፤
ሲሄድም ይነጋል።
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ከ ዩሐንስ ግርማሜ
@getem
@getem
@gebriel_19
ይሄ ፀያፍ ብሂል፤
ከጥንት ጀሞሮ፤
ውስጤን ሲየሠሳክከኝ፤
አጥንቴን ሰርስሮ፤
ማወቅ እሻ ነበር፤
አንክሮ እና ንዴት፤
በደሜላይ ሰፍሮ።
በእቅፋችሁ ሆኖ፤
ላደገው ልጃችሁ፤
ልጅ በእድሉ ያድጋል፤
አይዞህ እያላችሁ፤
እንዲህ በማባበል፤
ምን ተጠቀማችሁ።
ያም ሆኖ
ያ የዋህ ልጃችሁ፤
ያላችሁትን ይዞ፤
በዚያ ክፉ ብሂል፤
ውስጡ ተመርዞ፤
እንዳላችሁት ወጣ፤
እድሉን ፍለጋ፤
ውቧ ጀንበር ጠልቃ፤
ምሽቱ እስኪነጋ።
ልቡም እጅግ ጏግቶ፤
ፍለጋ ጀመረ፤
እድሌን እንዳለ፤
እንደወጣ ቀረ።
ብላችሁት ነበረ፤
ልጅ በእድሉ ያድጋል፤
ይኸው ለእጣ ፈንታው፤
ሲሄድ እየመሸ፤
ሲሄድም ይነጋል።
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ከ ዩሐንስ ግርማሜ
@getem
@getem
@gebriel_19
ቅዱስ ሌባቸው ነኝ
.
ሌባ ሳልሆን በፊት
ታማኝ ሰው ነበርሁ ÷ የሁሉም አገልጋይ
እምነትና አደራ
ተጣልተው ሲመጡ ÷ እኔ ነበርሁ ሸምጋይ
የሆነ ቀን ምሽት
ከድካሜ ሽሽት
እሳት ያለው እንቅልፍ ÷ ፍራሽ ላይ ሲያሞቀኝ
የሆነ ሰው መጥቶ
ታማኝነት ሐብቴን ÷ በሌሊት ሰረቀኝ
መቼም አያልፍ የለም ÷ ያ ሌሊት አለፈ
አላፊ አግዳሚው ግን ÷ እየተሰለፈ
ወደ እኔ ቤት መጣ
ንብረቴን በሙሉ
ሌባው በገባበት ÷ ተሸክሞ ወጣ ።
ታድያ ዛሬ ዛሬ
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ÷ በአይኑ ተጠቋቁሞ
ደጃፌ ላይ ቁሞ
እውነት ማወቅ ሲችል÷ ከትናንቴ ለቅሞ
ምን አይነት ፍርጃ ነው
ሌባ ነህ ለማለት ÷ ጣት የሚያስቀስረው
ሁሉንም ዘርፈውኝ
ሌብነትኮ ነው ÷ እጄ ላይ የቀረው !
…
እውነት ለመናገር
የዛሬ መፅዋቾች
የዛሬ ለጋሾች
ደግ እየተባሉ ÷ ሚጠራ ስማቸው
ድሮ አውቃቸዋለሁ
ሰፍሳፋነት ነበር ፥ ትልቁ ሀብታቸው
እኔ ቂመኛቸው ÷ አገሩ ሲዘርፈኝ
የበቀል ሰይጣኔ ÷ ወዳጅ አርጎ ሲያቅፈኝ
በሌሊት አድብቼ
የቤታቸውን በር ÷ ገንጥዬ ገብቼ
አንቀላፍተው ሳለ ÷ ከነስስታቸው
ቅዱስ ሌባቸው ነኝ
ጭካኔ እየሰረኩ ÷ ደግ ያደረኳቸው !!
…
☞ ናትናኤል ጌቱ
@getem
@getem
@kaleab_1888
.
ሌባ ሳልሆን በፊት
ታማኝ ሰው ነበርሁ ÷ የሁሉም አገልጋይ
እምነትና አደራ
ተጣልተው ሲመጡ ÷ እኔ ነበርሁ ሸምጋይ
የሆነ ቀን ምሽት
ከድካሜ ሽሽት
እሳት ያለው እንቅልፍ ÷ ፍራሽ ላይ ሲያሞቀኝ
የሆነ ሰው መጥቶ
ታማኝነት ሐብቴን ÷ በሌሊት ሰረቀኝ
መቼም አያልፍ የለም ÷ ያ ሌሊት አለፈ
አላፊ አግዳሚው ግን ÷ እየተሰለፈ
ወደ እኔ ቤት መጣ
ንብረቴን በሙሉ
ሌባው በገባበት ÷ ተሸክሞ ወጣ ።
ታድያ ዛሬ ዛሬ
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ÷ በአይኑ ተጠቋቁሞ
ደጃፌ ላይ ቁሞ
እውነት ማወቅ ሲችል÷ ከትናንቴ ለቅሞ
ምን አይነት ፍርጃ ነው
ሌባ ነህ ለማለት ÷ ጣት የሚያስቀስረው
ሁሉንም ዘርፈውኝ
ሌብነትኮ ነው ÷ እጄ ላይ የቀረው !
…
እውነት ለመናገር
የዛሬ መፅዋቾች
የዛሬ ለጋሾች
ደግ እየተባሉ ÷ ሚጠራ ስማቸው
ድሮ አውቃቸዋለሁ
ሰፍሳፋነት ነበር ፥ ትልቁ ሀብታቸው
እኔ ቂመኛቸው ÷ አገሩ ሲዘርፈኝ
የበቀል ሰይጣኔ ÷ ወዳጅ አርጎ ሲያቅፈኝ
በሌሊት አድብቼ
የቤታቸውን በር ÷ ገንጥዬ ገብቼ
አንቀላፍተው ሳለ ÷ ከነስስታቸው
ቅዱስ ሌባቸው ነኝ
ጭካኔ እየሰረኩ ÷ ደግ ያደረኳቸው !!
…
☞ ናትናኤል ጌቱ
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍1
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (👋ገብረዬ)
#Art_exhibition
Live music
Fashin show
Salsa dance
February 23
@ marriott excutive apartment
I care fund risinng event
@gebriel_19
@seiloch
@seiloch
Live music
Fashin show
Salsa dance
February 23
@ marriott excutive apartment
I care fund risinng event
@gebriel_19
@seiloch
@seiloch
@ድምቀትን ማክሰም@
* *
ትክክል እረስቶ ስርዝ መፈለጉ
ያ'በሻ ዲስኩሩ ያ'በሻ ስተቱ
ድልዝን አጉልቶ ትክክል ማፍዘዙ
ያ'በሻ ስተቱ ያ'በሻ ዲስኩሩ
ቁመት ቢረዝም በጣም ሎጋብቶን
ስም ይወጣልአል ለቁመት እሚሆን
እሱ ሰማይ ዳሱ - ጨረቃ አፖሉ
ደመና አስላዉ -ተራራ ትሪሱ
ክዋክብት ጠጠሩ-ምሰሶ ምርኩዙ
ያየር ነው ጓደኛ
የጉም ሚስጥረኛ
ፀሐይን የገጫት
ያ'ዋፋት እንቅፍት
ብለዉ ይጠሩአል
ብሉህም ያምሀል
በጣም አጭር ብቶን ቁመተ ስዝሮ
ላንተ ስም ይተጋል ሀበሻ አሳምሮ
ለበቁ እሳሩ - ሰረገላዉ ጓዳል
ቀይስሩ ትዋኑ- ዳይነሰሩ ቅማል
የልብ ሚስጥረኛው
ደሮ ናት ጓደኛው
እሱ መሬት ጠቀስ
ጓማ ፍንጣሪ ከሪሱ የሚደረስ
ብሉ ይስድብአል
ብሎህም ያምሀል
ትክክል ዘግቶ ስርዝ መፈለጉ
በቅጣት እንከን ዉስጥ ያ'በሻ ስተቱ
ድልዝን አጉልቶ ትክክል ማፍዘዙ
*****
✍ የተፃፈ ቢኒ እጠየ
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
@getem
@getem
@gebriel _19
* *
ትክክል እረስቶ ስርዝ መፈለጉ
ያ'በሻ ዲስኩሩ ያ'በሻ ስተቱ
ድልዝን አጉልቶ ትክክል ማፍዘዙ
ያ'በሻ ስተቱ ያ'በሻ ዲስኩሩ
ቁመት ቢረዝም በጣም ሎጋብቶን
ስም ይወጣልአል ለቁመት እሚሆን
እሱ ሰማይ ዳሱ - ጨረቃ አፖሉ
ደመና አስላዉ -ተራራ ትሪሱ
ክዋክብት ጠጠሩ-ምሰሶ ምርኩዙ
ያየር ነው ጓደኛ
የጉም ሚስጥረኛ
ፀሐይን የገጫት
ያ'ዋፋት እንቅፍት
ብለዉ ይጠሩአል
ብሉህም ያምሀል
በጣም አጭር ብቶን ቁመተ ስዝሮ
ላንተ ስም ይተጋል ሀበሻ አሳምሮ
ለበቁ እሳሩ - ሰረገላዉ ጓዳል
ቀይስሩ ትዋኑ- ዳይነሰሩ ቅማል
የልብ ሚስጥረኛው
ደሮ ናት ጓደኛው
እሱ መሬት ጠቀስ
ጓማ ፍንጣሪ ከሪሱ የሚደረስ
ብሉ ይስድብአል
ብሎህም ያምሀል
ትክክል ዘግቶ ስርዝ መፈለጉ
በቅጣት እንከን ዉስጥ ያ'በሻ ስተቱ
ድልዝን አጉልቶ ትክክል ማፍዘዙ
*****
✍ የተፃፈ ቢኒ እጠየ
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
@getem
@getem
@gebriel _19
<እንትናዬ 2>
አይኔ መከረኛው ከወዲያ ከወዲህ
ሲቀዣብር አይቶህ ፣
ተባባሪው ልቤ በሩን ከፍቶ አስገባህ
ከማንም ከምንም በላይ አነገሰህ፣
እንዳያውቁት የለም ተዋወኩህና ፣
ዘርግፌ ነገርኩህ የቤቴን ገመና ፣
እውነት እልሀለሁ እንዲህ አልነበርኩም፣
እንኳን ለወንድ ልጅ፤ለሴት ለሴቶቹም
እንዲህ ሆኜ አላውቅም፣
ሁሉንም አያለሁ፣
ሁሉንም አውቃለሁ ፣
ሁሌም እቀናለሁ ፣
አልነግርህም ብዬ ሁሉን ትቼው እንጂ
ሁሌ ማታ ማታ አለቅስ ነበረ ፣
ሀሞቴ ፈሶ አልቆ ቆሽቴ እያረረ ፣
አልነግርህም ብዬ ሁሉን ትቼው እንጂ ፣
እጇን ስትይዛት ፤ እጁን በቆረጠው፣
ስታያት ካየሁኝ ፤ አይኑን ባጨለመው ፣
ብየ ተመኝቼ ረግሜህ ነበር.....
ታዲያ ምን ያደርጋል...
ሲያምህ ያመኛል፤ስትስቅ እስቃለሁ ፣
የእጅህ ጣት ሲያርፍብኝ
እንቀጠቀጣለሁ፣
ይሔንን እያዩ 'አይኑን ባጨለመው'
ብሎ መመኘቱ ለምን ያስፈልጋል?
የኔ ጉድ አያልቅም! ለካ አንተን ሲያምህ
እኔንም ያመኛል!!!
ማኅሌት ሞላ
17/3/11
@getem
@getem
@gebriel_19
አይኔ መከረኛው ከወዲያ ከወዲህ
ሲቀዣብር አይቶህ ፣
ተባባሪው ልቤ በሩን ከፍቶ አስገባህ
ከማንም ከምንም በላይ አነገሰህ፣
እንዳያውቁት የለም ተዋወኩህና ፣
ዘርግፌ ነገርኩህ የቤቴን ገመና ፣
እውነት እልሀለሁ እንዲህ አልነበርኩም፣
እንኳን ለወንድ ልጅ፤ለሴት ለሴቶቹም
እንዲህ ሆኜ አላውቅም፣
ሁሉንም አያለሁ፣
ሁሉንም አውቃለሁ ፣
ሁሌም እቀናለሁ ፣
አልነግርህም ብዬ ሁሉን ትቼው እንጂ
ሁሌ ማታ ማታ አለቅስ ነበረ ፣
ሀሞቴ ፈሶ አልቆ ቆሽቴ እያረረ ፣
አልነግርህም ብዬ ሁሉን ትቼው እንጂ ፣
እጇን ስትይዛት ፤ እጁን በቆረጠው፣
ስታያት ካየሁኝ ፤ አይኑን ባጨለመው ፣
ብየ ተመኝቼ ረግሜህ ነበር.....
ታዲያ ምን ያደርጋል...
ሲያምህ ያመኛል፤ስትስቅ እስቃለሁ ፣
የእጅህ ጣት ሲያርፍብኝ
እንቀጠቀጣለሁ፣
ይሔንን እያዩ 'አይኑን ባጨለመው'
ብሎ መመኘቱ ለምን ያስፈልጋል?
የኔ ጉድ አያልቅም! ለካ አንተን ሲያምህ
እኔንም ያመኛል!!!
ማኅሌት ሞላ
17/3/11
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ይቅርታ የሚሉት ፤
እእፉታ የሚባል ፤
የቂም ማንቸፍቸፊያ ፤ እንዶድ ተሰጥቼ ፤
ካልጋየ እወድቃለሁ ፤
በይቅርታ እስትንፋስ ፤
የህሊና እገሬን ፤ እድፌን አንጽቼ ፤
የቂም ረመጤን ፤ ንዳዱን አጥፍቼ ፤
ጧ ብየ እተኛለሁ ፤
ከውብ ህሊና ጋር ፤ ተጋጥመው አይኖቼ፤
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
እእፉታ የሚባል ፤
የቂም ማንቸፍቸፊያ ፤ እንዶድ ተሰጥቼ ፤
ካልጋየ እወድቃለሁ ፤
በይቅርታ እስትንፋስ ፤
የህሊና እገሬን ፤ እድፌን አንጽቼ ፤
የቂም ረመጤን ፤ ንዳዱን አጥፍቼ ፤
ጧ ብየ እተኛለሁ ፤
ከውብ ህሊና ጋር ፤ ተጋጥመው አይኖቼ፤
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
<<በላይ በቀለ ወያ>>
ሥራ በሌለበት
ሥለ ሥራ ቋንቋ ፣ የሚነታረኩ
የትውልድ ልብ ላይ
ቂምን ለመጋገር ፣ ጥላቻ ሚያቦኩ
በነፃነት ምድር
ነፃ አውጪ ነን ብለው ፣ ባርነት ሚሰብኩ
ትውልዶችን ፈጥሮ ፣ ዝም ሲል ፈጣሪው
"ትናገር አደዋ"
እያልሽ በድፍረት ፣ ምታንጎራጉሪው
ምን ነክቶሽ ነው እቴ?
።።።
ከኔ ቋንቋ በቀር ፣ ለማይናገሩ
መግባባት አይኖርም ፣ መስማማት ኢንጅሩ
ገለመሌ እያለ
ቋንቋ ተከፋፍሎ ፣ ሲፎክር ሀገሩ
ሀገር መንደር ሲሆን ፣ ውቅያኖሱ ኩሬ
አንቺ ባለማወቅ
"ትናገር አደዋ ፣ ትናገር ሀገሬ"
ብለሽ የምትዘፍኚው
ወይ ደሞ በድፍረት ምታቀነቅኚው
ምን ነክቶሽ ነው እቴ?
።።።
አዋቂ ነኝ ባዮች
ፍቅርን አቀጭጨው ፣ ጥላቻን ሲያሰቡ
ተማሪ ነን ባዮች
"ቋንቋ መግባቢያ ነው "
በሚል አስተምሮት ፣ ብለው አልግባቡ
ትናገር አደዋ
ብለሽ የምትዘፍኚው ፣ መምህራቸውን ለሚደበደቡ
ምን ሆነሻል እቴ?
።።።
ለብዙ ሺህ ዘመን
እጇን ወደ አምላኳ ፣
ዘርግታ ስትኖር ፣ ሰርቀዋት ፀሎቷን
የቆጡን ለማውረድ ፣ ጥላ የብብቷን
የፉክክር ሀገር
የሚዘጋት አጥቶ ፣ እያደረች ክፍቷን
ሌባና ቀማኛ ፣ ለጉድ ተንሰራፍቶ
ዘረኛ መምህር
የቤት ስራ ሲሰጥ ፣ የሀገር ስራን ትቶ
ፍቅር ያግባባቸው
ያያት ቅድም አያቶች ፣ ታሪክን አንስቶ
ቋንቋ ላያግባባን
እውነት እየሰቀልን ፣ ለምንፈታ በርባን
ትናገር አደዋ
የሚል አጉል ቅኔ ፣ ከምትደረድሪ
አደዋ ዝም ብላ ፣ አንቺ ተናገሪ።
አለበለዚያ ግን
ብሔር ተከፋፍሎ ፣ ለሚጣላ ሀገር
ትናገር አደዋ
ትናገር ሀገሬ ፣ የምትይው ነገር
ለእሳት ልጅ አመዶች ፣ ነገር ነው ሚጭረው
ልናገር ብትልስ
ቆይ በማን ቋንቋ ነው ፣ የምትናገረው?
ራስሽ ተናገሪ።
@getem
@getem
@kaleab_1888
ሥራ በሌለበት
ሥለ ሥራ ቋንቋ ፣ የሚነታረኩ
የትውልድ ልብ ላይ
ቂምን ለመጋገር ፣ ጥላቻ ሚያቦኩ
በነፃነት ምድር
ነፃ አውጪ ነን ብለው ፣ ባርነት ሚሰብኩ
ትውልዶችን ፈጥሮ ፣ ዝም ሲል ፈጣሪው
"ትናገር አደዋ"
እያልሽ በድፍረት ፣ ምታንጎራጉሪው
ምን ነክቶሽ ነው እቴ?
።።።
ከኔ ቋንቋ በቀር ፣ ለማይናገሩ
መግባባት አይኖርም ፣ መስማማት ኢንጅሩ
ገለመሌ እያለ
ቋንቋ ተከፋፍሎ ፣ ሲፎክር ሀገሩ
ሀገር መንደር ሲሆን ፣ ውቅያኖሱ ኩሬ
አንቺ ባለማወቅ
"ትናገር አደዋ ፣ ትናገር ሀገሬ"
ብለሽ የምትዘፍኚው
ወይ ደሞ በድፍረት ምታቀነቅኚው
ምን ነክቶሽ ነው እቴ?
።።።
አዋቂ ነኝ ባዮች
ፍቅርን አቀጭጨው ፣ ጥላቻን ሲያሰቡ
ተማሪ ነን ባዮች
"ቋንቋ መግባቢያ ነው "
በሚል አስተምሮት ፣ ብለው አልግባቡ
ትናገር አደዋ
ብለሽ የምትዘፍኚው ፣ መምህራቸውን ለሚደበደቡ
ምን ሆነሻል እቴ?
።።።
ለብዙ ሺህ ዘመን
እጇን ወደ አምላኳ ፣
ዘርግታ ስትኖር ፣ ሰርቀዋት ፀሎቷን
የቆጡን ለማውረድ ፣ ጥላ የብብቷን
የፉክክር ሀገር
የሚዘጋት አጥቶ ፣ እያደረች ክፍቷን
ሌባና ቀማኛ ፣ ለጉድ ተንሰራፍቶ
ዘረኛ መምህር
የቤት ስራ ሲሰጥ ፣ የሀገር ስራን ትቶ
ፍቅር ያግባባቸው
ያያት ቅድም አያቶች ፣ ታሪክን አንስቶ
ቋንቋ ላያግባባን
እውነት እየሰቀልን ፣ ለምንፈታ በርባን
ትናገር አደዋ
የሚል አጉል ቅኔ ፣ ከምትደረድሪ
አደዋ ዝም ብላ ፣ አንቺ ተናገሪ።
አለበለዚያ ግን
ብሔር ተከፋፍሎ ፣ ለሚጣላ ሀገር
ትናገር አደዋ
ትናገር ሀገሬ ፣ የምትይው ነገር
ለእሳት ልጅ አመዶች ፣ ነገር ነው ሚጭረው
ልናገር ብትልስ
ቆይ በማን ቋንቋ ነው ፣ የምትናገረው?
ራስሽ ተናገሪ።
@getem
@getem
@kaleab_1888
👍1
በረቱ ፈረሰ ፤
ካንድ እናት ተወልደን ፤
ካንድ መስክ ግጠን ፤
ካንድ በረት አድረን ፤ አድገን ስናበቃ ፤
የፍቅራችን ብርሃን ፤
ምነው ድርግም አለ፤
ደመና እንደዋጠው ፤እንዳ'ምሌ ጨረቃ ???!!!
ምነው በስተማታ ፤
የገላችን ቀለም ፤
ጥቁር ነጭነቱ ፤ ታይቶን ልዩነቱ ፤
እንኳን አብሮ ማደር ፤
አብሮ መዋል ጠላን ፤ እኔና ጥጅቱ ፤
ነጮ ቀዮ በሚል ፤
ሌት ቀን ስንታገል ፤ አብረን የኖርንበት ፈረሰ በረቱ ።
በበረቱ ጋጣ ፤
አብሮ ሚያኗኑረን ፤ ላምነት እያለ ፤
ወይኖ ጥቁሮ በሚል፤
ቀለሙን ደክቶ ላም እየታገለ ፤
ያን ማደሪያ ጋጡን ፤
በእርግጫ በግፊያ ፤ አፍርሶ እየጣለ ፣
ያገሬ ላም ሁላ ፤
ማደሪያ ጠፍቶበት ፤
የጅብ ራት ሆኖ ፤ በየሜዳው ቀረ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
የኔዋ ቅዳሜ!! ሸጋዋ ቅዳሜ!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
ካንድ እናት ተወልደን ፤
ካንድ መስክ ግጠን ፤
ካንድ በረት አድረን ፤ አድገን ስናበቃ ፤
የፍቅራችን ብርሃን ፤
ምነው ድርግም አለ፤
ደመና እንደዋጠው ፤እንዳ'ምሌ ጨረቃ ???!!!
ምነው በስተማታ ፤
የገላችን ቀለም ፤
ጥቁር ነጭነቱ ፤ ታይቶን ልዩነቱ ፤
እንኳን አብሮ ማደር ፤
አብሮ መዋል ጠላን ፤ እኔና ጥጅቱ ፤
ነጮ ቀዮ በሚል ፤
ሌት ቀን ስንታገል ፤ አብረን የኖርንበት ፈረሰ በረቱ ።
በበረቱ ጋጣ ፤
አብሮ ሚያኗኑረን ፤ ላምነት እያለ ፤
ወይኖ ጥቁሮ በሚል፤
ቀለሙን ደክቶ ላም እየታገለ ፤
ያን ማደሪያ ጋጡን ፤
በእርግጫ በግፊያ ፤ አፍርሶ እየጣለ ፣
ያገሬ ላም ሁላ ፤
ማደሪያ ጠፍቶበት ፤
የጅብ ራት ሆኖ ፤ በየሜዳው ቀረ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
የኔዋ ቅዳሜ!! ሸጋዋ ቅዳሜ!!💚💛❤
@balmbaras
@getem
@getem
❤1
፡፡፡፡፡፡ፍካት ናፋቂዎች፡፡፡፡፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~
የዘመን እጣፋታ እኛን ባንቺ ላይ ጥሎ
የተስፋ ጽገሬዳ በከርስሽ ውስጥ አጎንቅሎ
ዘላለማዊ እንቡጥ በልቦናችን ሸብልሎ
አላበበ አልረገፈ
ፈክቶ አልተቀጠፈ
ቅጠል ብቻ ሰዶ ስሩን
ተስፋ ብቻ አንቡጦ እንቡጡን
ነቅለን አንወረውረው
ማንነት ከአስኳልሽ ቋጥሮን
ግብር ሆነን ጊዜ አቅምን ሰልቦን
እንቡጥ አምላኪ አደረገን የነገን ተስፋ ናፋቂ
ያልተቀደደ ጎህ ልጆች ሁሌ በተስፋ ታጣቂ፡፡
ምን ታረጊዋለሽ
©በድሉ ዋቅጅራ
#ቅኔ_አድባር
@getem
@getem
@gebriel_19
~~~~~~~~~~~~~~~
የዘመን እጣፋታ እኛን ባንቺ ላይ ጥሎ
የተስፋ ጽገሬዳ በከርስሽ ውስጥ አጎንቅሎ
ዘላለማዊ እንቡጥ በልቦናችን ሸብልሎ
አላበበ አልረገፈ
ፈክቶ አልተቀጠፈ
ቅጠል ብቻ ሰዶ ስሩን
ተስፋ ብቻ አንቡጦ እንቡጡን
ነቅለን አንወረውረው
ማንነት ከአስኳልሽ ቋጥሮን
ግብር ሆነን ጊዜ አቅምን ሰልቦን
እንቡጥ አምላኪ አደረገን የነገን ተስፋ ናፋቂ
ያልተቀደደ ጎህ ልጆች ሁሌ በተስፋ ታጣቂ፡፡
ምን ታረጊዋለሽ
©በድሉ ዋቅጅራ
#ቅኔ_አድባር
@getem
@getem
@gebriel_19
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ስሜ G እባላለሁ ስም መጥፎ ጎን ሊኖረው ይችላል በማለት ነው ግን በውስጥ መስመር ችግር የለውም የአፋልጉኝ ጥሪ ነው ።
ተወለድክ የተባልኩበት አገር መተማ ወይም ሸዲ ይባላል ስሙን እንጅ አገሩን በውን አላውቅም የኔ እናት ና አባቴ ለስራ የትውልድ አገራቸውን ለቀው ስራ ፍለጋ በተሰደዱበት ወቅት የእግዚአብሔር ፍቃድ ሆነና እኔን እድለቢሱን ልጃቸውን ወልዱ ግን ተስማምተው ተፋቅረው ትድረው ከወለዱኝ በሁላ ምክንያቱን ባልታወቀ ፀብ ተጣልተው ገና ቦርቄ ስልጨርስ እናቴ በሰው አስመጥታ ሰርቃ ወደ ጎንደር ይዛኝ ጠፋች 3 አመት ከሰው ቤት ተቀጥራ እዳሳደገችኝ ከዛም አሁን ወዳለሁበት አገር አመጣችኝ አባቴን ስላት ያኔ ልጅ እያለሁ ከአእምሮዬ በላይ የሆነ መልስ ትሰጠኝ ነበረች ከዛም አልፎ ብር ስትዚ። ስራ መስራት አለበህ ስትለኝ ያቅሜን እየሰራሁ ት.ት አቋረጥኩ ሀሳቤ ሁሉ ገንዘብ ለይ ሆነ ግን ሊሳካ አልቸለልኝም በዙ ለፋሁ የለ ወክቱ እዴት ይምጣ ገንዘብ እሷ አያደርገውም አያገኝም ዝም ይለኛል ይረሳዋል ትል ነበር ግን የናት ሞት ና የትን ድንጋይ እየቆየ ይቆረቁራል አይደል ሚባለው አሁን አባቴ በጣም ናፍቆኛል 19 አመት ያለ አባት ቆይቻለው እናቴ የተለያየ ምክንያት ታቀርባለች ግን የአባቴን ናፍቆት ግን አላስታገሰልኝም ይበልጥ ሳድግ ናፈቀኝ አሁን ክፉና ደጉን ለይቸ አወኩ አሁን ሶሻል ሚዲያም እደዚህ አይነትም በጎ ጎን አለው ብዬ ከስንት አመታት ደብቄ የያዝኩትን ሚስጢር በተዘበራረቀ ሀሳብ ሁኜ ትንሽ ለማለት ነው የመፃፉም ልምድ የለኝም ፍሬ ሀሳቡን ለማጋራት እንጅ ለማንኛውም እናቴ ፈንታ ጌታቸው ትባላለች እዚህ መጥታም አንድ ሰው አገባች አሁን 1ወንድም 1 እህት ወልዳለች 15 አመት ምናምን እየሆናቸው ነው ከተጋብ..................... የኔ ጉዳይ አንድም ቀን አስጨንቆት አያውቅም እጀራ አባቴ። አባቴ በለጠም የኔን እናት ከማግባቱ በፊት ከሌላ ወልዶ እደነበር ከውስጧ የልጠፋ እውነታ ነው ከዛ ውጭ አንድም ነገር የምታቀው ነገር የለም እናቴ እደ አባትም እናትም ሁና አሳድጋኛለች ቢሆንም እሷ ዘላለም አብራኝ እደማትሆን እና የፈጣሪ ነገር እሷን ይዞብኝ ከሄደ
ከዛ በሁላ ቤተሰብ ባገኝ ጣእም የለውም ለማንኛውም እናንተ በተቻላችሁ መጠን ቤተሰቤን እዳገኝ እርዱኝ
Call 0942329852
.
@getem
@getem
ስሜ G እባላለሁ ስም መጥፎ ጎን ሊኖረው ይችላል በማለት ነው ግን በውስጥ መስመር ችግር የለውም የአፋልጉኝ ጥሪ ነው ።
ተወለድክ የተባልኩበት አገር መተማ ወይም ሸዲ ይባላል ስሙን እንጅ አገሩን በውን አላውቅም የኔ እናት ና አባቴ ለስራ የትውልድ አገራቸውን ለቀው ስራ ፍለጋ በተሰደዱበት ወቅት የእግዚአብሔር ፍቃድ ሆነና እኔን እድለቢሱን ልጃቸውን ወልዱ ግን ተስማምተው ተፋቅረው ትድረው ከወለዱኝ በሁላ ምክንያቱን ባልታወቀ ፀብ ተጣልተው ገና ቦርቄ ስልጨርስ እናቴ በሰው አስመጥታ ሰርቃ ወደ ጎንደር ይዛኝ ጠፋች 3 አመት ከሰው ቤት ተቀጥራ እዳሳደገችኝ ከዛም አሁን ወዳለሁበት አገር አመጣችኝ አባቴን ስላት ያኔ ልጅ እያለሁ ከአእምሮዬ በላይ የሆነ መልስ ትሰጠኝ ነበረች ከዛም አልፎ ብር ስትዚ። ስራ መስራት አለበህ ስትለኝ ያቅሜን እየሰራሁ ት.ት አቋረጥኩ ሀሳቤ ሁሉ ገንዘብ ለይ ሆነ ግን ሊሳካ አልቸለልኝም በዙ ለፋሁ የለ ወክቱ እዴት ይምጣ ገንዘብ እሷ አያደርገውም አያገኝም ዝም ይለኛል ይረሳዋል ትል ነበር ግን የናት ሞት ና የትን ድንጋይ እየቆየ ይቆረቁራል አይደል ሚባለው አሁን አባቴ በጣም ናፍቆኛል 19 አመት ያለ አባት ቆይቻለው እናቴ የተለያየ ምክንያት ታቀርባለች ግን የአባቴን ናፍቆት ግን አላስታገሰልኝም ይበልጥ ሳድግ ናፈቀኝ አሁን ክፉና ደጉን ለይቸ አወኩ አሁን ሶሻል ሚዲያም እደዚህ አይነትም በጎ ጎን አለው ብዬ ከስንት አመታት ደብቄ የያዝኩትን ሚስጢር በተዘበራረቀ ሀሳብ ሁኜ ትንሽ ለማለት ነው የመፃፉም ልምድ የለኝም ፍሬ ሀሳቡን ለማጋራት እንጅ ለማንኛውም እናቴ ፈንታ ጌታቸው ትባላለች እዚህ መጥታም አንድ ሰው አገባች አሁን 1ወንድም 1 እህት ወልዳለች 15 አመት ምናምን እየሆናቸው ነው ከተጋብ..................... የኔ ጉዳይ አንድም ቀን አስጨንቆት አያውቅም እጀራ አባቴ። አባቴ በለጠም የኔን እናት ከማግባቱ በፊት ከሌላ ወልዶ እደነበር ከውስጧ የልጠፋ እውነታ ነው ከዛ ውጭ አንድም ነገር የምታቀው ነገር የለም እናቴ እደ አባትም እናትም ሁና አሳድጋኛለች ቢሆንም እሷ ዘላለም አብራኝ እደማትሆን እና የፈጣሪ ነገር እሷን ይዞብኝ ከሄደ
ከዛ በሁላ ቤተሰብ ባገኝ ጣእም የለውም ለማንኛውም እናንተ በተቻላችሁ መጠን ቤተሰቤን እዳገኝ እርዱኝ
Call 0942329852
.
@getem
@getem
✍✍✍ትላንት እና ዛሬ✍✍
ትላንት
በሰው ተሰብሬ ሁሉ ግራ ሆኖ
የልቤ መሰበር ከደስታዬ ገኖ
በባዶ ቢሰፈር የሰጠውት ፍቅር
ፍቅር የለም ብዬ ተሟገት ከእኔ ጋር
ዛሬ አንቺ ስትመጪ
የከዳውት ፍቅር ጥግኖ ቢረታኝ
መውደድ የለም ሙቷል
ያልኩት ቃል ተረሳኝ
የማልኩት መሀላ ቃላቱኳ ጠፋኝ
እንጀተናገሩት ሊቃውተ አበው
ለካስ እውነት አለው
ሰው ነው መድሀኒቱ ለተገፋ በሰው
ዛሬ አንቺ ስትመጪ
በፍቅር መአዛ
ሀሴቱ ሲበዛ
የነበረኝ ሁሉ እንደ አዲስ ቢበዛ
በፍቅር ማዕጠንትእንደገና ወዛ
ዛሬ አንቺ ስገቢ
የነበረኝ ፅልመት በሳቅሽ ተተካ
ብቸኝነት ቀርቶ በደስታ ተውካካ
ከየ ጉራንጉሩ የፈለኩት ዞሬ
እስኪቀጥን እግሬ
ዛሬ ከቤቴ ነው
አንቺ እመጣ ብለሽ ፋኖስ ሁናል ፍቅሬ
ተፃፈ በጃህፈር
27/05/2011ዓ.ም
ወለጋ መካነ አእምሮ
@getem
@getem
@gebriel_19
ትላንት
በሰው ተሰብሬ ሁሉ ግራ ሆኖ
የልቤ መሰበር ከደስታዬ ገኖ
በባዶ ቢሰፈር የሰጠውት ፍቅር
ፍቅር የለም ብዬ ተሟገት ከእኔ ጋር
ዛሬ አንቺ ስትመጪ
የከዳውት ፍቅር ጥግኖ ቢረታኝ
መውደድ የለም ሙቷል
ያልኩት ቃል ተረሳኝ
የማልኩት መሀላ ቃላቱኳ ጠፋኝ
እንጀተናገሩት ሊቃውተ አበው
ለካስ እውነት አለው
ሰው ነው መድሀኒቱ ለተገፋ በሰው
ዛሬ አንቺ ስትመጪ
በፍቅር መአዛ
ሀሴቱ ሲበዛ
የነበረኝ ሁሉ እንደ አዲስ ቢበዛ
በፍቅር ማዕጠንትእንደገና ወዛ
ዛሬ አንቺ ስገቢ
የነበረኝ ፅልመት በሳቅሽ ተተካ
ብቸኝነት ቀርቶ በደስታ ተውካካ
ከየ ጉራንጉሩ የፈለኩት ዞሬ
እስኪቀጥን እግሬ
ዛሬ ከቤቴ ነው
አንቺ እመጣ ብለሽ ፋኖስ ሁናል ፍቅሬ
ተፃፈ በጃህፈር
27/05/2011ዓ.ም
ወለጋ መካነ አእምሮ
@getem
@getem
@gebriel_19
~~የአዞ እንባ ~~(ሳሙኤል አዳነ)
ባልበሰለ አይምሮ
ሀገር ልናቆስል ፣
ከራስ ጋር ተጣልተን
ብሄር እንገምዳለን
አዋቂ ይመስል ።
.
እምነት አለኝ የሚል
መፆም ያላቃተው ፣
መነው ይችን ሀገር
ካለችበት ፍዳ
መታደግ አቃተዉ ።
.
ለካስ ውሸት ኖሯል
ያዞ ነው እንባችን ፣
ከይቅርታ ጀርባ
ከሳሽ ነው ልባችን ።
ፀሎት መፃፍ ይዘን
ጦር አለ በጃችን ።
የይምሰል ለቅሷችን
ግፍ እየቋጠረ ፣
ዞሮ እሚያቃጥለን
አሲድ ሆኖ ቀረ ።
.
እባክህ አምላኬ
ፅድቁም ይቅርና
በቅጡ ኮንነን ፣
የአንድናት ልጆች
ተባልተን እንዳናልቅ
አስታራቂ ሆነን ።
03/05/2011
3፡00am
አ.አ
@getem
@getem
@gebriel_19
ባልበሰለ አይምሮ
ሀገር ልናቆስል ፣
ከራስ ጋር ተጣልተን
ብሄር እንገምዳለን
አዋቂ ይመስል ።
.
እምነት አለኝ የሚል
መፆም ያላቃተው ፣
መነው ይችን ሀገር
ካለችበት ፍዳ
መታደግ አቃተዉ ።
.
ለካስ ውሸት ኖሯል
ያዞ ነው እንባችን ፣
ከይቅርታ ጀርባ
ከሳሽ ነው ልባችን ።
ፀሎት መፃፍ ይዘን
ጦር አለ በጃችን ።
የይምሰል ለቅሷችን
ግፍ እየቋጠረ ፣
ዞሮ እሚያቃጥለን
አሲድ ሆኖ ቀረ ።
.
እባክህ አምላኬ
ፅድቁም ይቅርና
በቅጡ ኮንነን ፣
የአንድናት ልጆች
ተባልተን እንዳናልቅ
አስታራቂ ሆነን ።
03/05/2011
3፡00am
አ.አ
@getem
@getem
@gebriel_19
ጋሽ አበራ ሞላ፤ ደሴን ሲያናግራት!!! እንዲህ ይመስለኛል!!!
((ምናባዊ የክራር ጨዋታ))
ገራዶ ከንፈርሽ፤
ጦሳ ተረከዝሽ፤
ሳላይሽ ቅንድብሽ፤
ዳውዶ መቀነትሽ፤
አረብ ገንዳ ባትሽ፤
አገር ግዛት አይንሽ፤
ቧ.........ን.........ቧ ውሃ ወገብሽ፤
ጀሜ ደም ግባትሽ፤
ሚጠሮ ግንባርሽ፤
በአደስና አርቲ፤
በወይባና ናትራ፤ እየተሞሸሩ፤
ለታመመ ጎበዝ፤
መድሃኒት ሆነሻል፤ ለድፍን ሃገሩ።
ደሴ ዙሪያው ገነት፤
ገራዶ ረግረጉ ፤ ቃሉና ጮሬሳ ፤
ሃየ በል እያለ ፤
እየተጫፈረ፤ ቀልቤ ከተደሳ፤
ያኔ ነው ያኔ ነው፤
ደሴ ሙጋድ ሰፈር፤
ባንተው መጀን ብዬ፤ ክራር የማነሳ።
አ፤፤፤፤፤፤፤አንች ጋር ነው እንጅ፤
ይ፤፤፤፤፤፤፤፤ ይህ ሁሉ ቁንጅና፤
ጠ፤፤፤፤፤ጠረንሽ ዝባድ ነው፤
የ፤፤፤፤፤፤ የስሂን መቀነት፤ የኢያሱ ጀበርና
ፍ፤፤፤፤፤፤ፍቅር የጦሳ ልጅ ፈርጥ ነሽ ናሙና፤
አይጠየፍ አሉሽ፤ እጅሽን አዩና።
ክርርም
ክርርም ፤
ስሜ አልወጣልኝም ያችንም ይችንም ።
ኪር ኪው ኪርካ፤
ልጅቱ ያለችው፤
ደሴ ሙጋድ ሰፈር፤ ሮቢት ነው ለካ።
እናቷ መነን ናት ፤ አባቷ ሸህ ሙሳ ፤
ከንፈሯ ሚመስለው ፤
የወሎ ሻሂ ቤት ፤ትኩስ አሳንቡሳ ፤
አንዴ ብትስመኝ ፤
ያ የተውኩት መውደድ ፤ መልሶ ተነሳ ።
ይልህና ፤ እንዲህ romantic የሆነ ትርክት ይጨምርልሃል። እንዲህ እያለ። አንዲት ውብ
የሆነች የንጉስ ሚካኤል ዘመድ ከተንታ ሚካኤል ተነስታ ደሴ በገባች ጊዜ ለካስ ቁንጅናዋ
ያማለላቸው የአይጠየፍ ባለሟሎች ተመኝተዋት ኖሮ ነይ ወደኔ ነይ ወደኔ እያሉ ቢሻሙባት
ጊዜ እርጎ ይመር የተባለች የሚካኤል ግብር ቤት ሰራተኛ እንዲህ አለቻቸው ይልህና፤
ክራሩን
ክር ኪር ኪር ኳ እያደረገ፤ እንዲህ ይልሃል.....
እቴ በሚካኤል፤
በመሃመድ አሊ ፤ በኢያሱ ስልሽ፤
ስንት ጊዜ ነበር፤
ያገር ግዛት ጎበዝ፤
ያገር ያለህ ብሎ፤ ያመላለሰሽሽሽሽሽ??
ሺ .........ሺ...........ብለው ነበር፤
የአይጠየፍ ዘቦች፤ ቁንጅናሽን አይተው፤
የኢያሱን ግልምጫ፤
ያንችን...
ማ...ማ....ር ፈርተው።
ብለው የአይጠየፍ ዘቦች ቢያሽሟጥጧት እንዲህ አለች አሉ።
ኢያሱ ቢጠራኝ፤የጌታ ወጉ ነው፤
ሚካኤልም ቢያዘኝ፤ የአባቴ ደብር ነው፤
እኔን ያስቸገረኝ፤
ጫንቃው ያጎፈረው፤ የሚካኤል ዘብ ነው።
ብላ ስትንቀባረር። አንድ ጀብራራ የአይጠየፍ እልፍኝ አስከልካይ እቃው አይሰራም እየተባለ
ይታማል። ምላሳም ነውና ዘቦቹ አይወዱትም። ያችን ሸጋ ልጅ ሲተናኮሏት ስላያቸው መቼም
ወሬ ማሳበቁ አይቀርም ብለው እንዲህ አድርገው አሸሞሩት ይልሃል አበራ ሞላ ክራሩን
ገረፍረፍ እያደረገ፤
የኛ ቤት ሹመኛ የኛ ቤት ውላጅ፤
ማቆም መች ይችላል፤ ማመላለስ እንጅ፤
ሃኪም የት ተገኝቶ ፤ ከኛ የታለና፤
ከላይ ከሰገነት፤ ከእልፍኙ ውጭና፤
ዳብሰው ያክሙሻል፤ ኢያሱ አባ ጤና።
የአሊ ቦራ ልጅ ነው፤
የሂመኖ ልጅ ነው፤
የሸዋረገድ ልጅ፤
አይጠየፍ ወጥተን እንየው እያሉ፤
ምነው ምን ነካቸው፤
የገራዶ ልጆች፤
መቼም ልጅ ነው ብለው፤
ያንን ልጅ ኢያሱ፤ ሲስሙት የዋሉ???
እያሉ ልጅ ኢያሱ በሸጋ ልጅ የሚጨክን አንጀት የሌላቸው መሆኑን ነገሯት።
ይህንን ነገር የተመለከተች ፀጉረ ብትን የስሂን ተማሪ ከት ብላ ስቃባቸው ስታልፍ ቆም
አሉና፤
ያስኮላ ተማሪ፤
ስሂን መቃኛው ላይ፤
እንግሊዝ ደብተርሽ፤ ወድቆ ተገኘ አሉ፤
ከጥሁፍሽ መሃል፤
yes yes ማለት ታበዣለሽ አሉ።
ሰኔ 30 ላይ፤
ካርድ ተቀብለሽ፤
ስሂን ቁልቁለት ላይ ስትወርጅ ባይሽ፤
ወሎ ሻሂ ቤት ነው፤
ጮርናቄ በሻሂ፤ የምጋብዝሽ፤
መቼም ዝም አይለኝ፤
ስኳር የቀመሰው፤ ስኳር ከንፈርሽ።
እያሉ ጣፍጭ romantic ስንኞችን እያፈሰሱ ቀዬውን አወዱት።
ጋሽ አበራ ክራሩን ገረፍረፍ እያደረገ፤
ይኸ ሁሉ ሲሆን፤
ሸጋና ደም ግባት፤
እንደ ቀለጠ ማር፤
እንደ ለጋ ብርዝ፤ የሚጎነጩባት፤
የኢያሱ ከተማ፤
የሚካኤል ድካ፤ ደሴ ናት ደሴ ናት።
የሚል ይመስለኛል።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
((ምናባዊ የክራር ጨዋታ))
ገራዶ ከንፈርሽ፤
ጦሳ ተረከዝሽ፤
ሳላይሽ ቅንድብሽ፤
ዳውዶ መቀነትሽ፤
አረብ ገንዳ ባትሽ፤
አገር ግዛት አይንሽ፤
ቧ.........ን.........ቧ ውሃ ወገብሽ፤
ጀሜ ደም ግባትሽ፤
ሚጠሮ ግንባርሽ፤
በአደስና አርቲ፤
በወይባና ናትራ፤ እየተሞሸሩ፤
ለታመመ ጎበዝ፤
መድሃኒት ሆነሻል፤ ለድፍን ሃገሩ።
ደሴ ዙሪያው ገነት፤
ገራዶ ረግረጉ ፤ ቃሉና ጮሬሳ ፤
ሃየ በል እያለ ፤
እየተጫፈረ፤ ቀልቤ ከተደሳ፤
ያኔ ነው ያኔ ነው፤
ደሴ ሙጋድ ሰፈር፤
ባንተው መጀን ብዬ፤ ክራር የማነሳ።
አ፤፤፤፤፤፤፤አንች ጋር ነው እንጅ፤
ይ፤፤፤፤፤፤፤፤ ይህ ሁሉ ቁንጅና፤
ጠ፤፤፤፤፤ጠረንሽ ዝባድ ነው፤
የ፤፤፤፤፤፤ የስሂን መቀነት፤ የኢያሱ ጀበርና
ፍ፤፤፤፤፤፤ፍቅር የጦሳ ልጅ ፈርጥ ነሽ ናሙና፤
አይጠየፍ አሉሽ፤ እጅሽን አዩና።
ክርርም
ክርርም ፤
ስሜ አልወጣልኝም ያችንም ይችንም ።
ኪር ኪው ኪርካ፤
ልጅቱ ያለችው፤
ደሴ ሙጋድ ሰፈር፤ ሮቢት ነው ለካ።
እናቷ መነን ናት ፤ አባቷ ሸህ ሙሳ ፤
ከንፈሯ ሚመስለው ፤
የወሎ ሻሂ ቤት ፤ትኩስ አሳንቡሳ ፤
አንዴ ብትስመኝ ፤
ያ የተውኩት መውደድ ፤ መልሶ ተነሳ ።
ይልህና ፤ እንዲህ romantic የሆነ ትርክት ይጨምርልሃል። እንዲህ እያለ። አንዲት ውብ
የሆነች የንጉስ ሚካኤል ዘመድ ከተንታ ሚካኤል ተነስታ ደሴ በገባች ጊዜ ለካስ ቁንጅናዋ
ያማለላቸው የአይጠየፍ ባለሟሎች ተመኝተዋት ኖሮ ነይ ወደኔ ነይ ወደኔ እያሉ ቢሻሙባት
ጊዜ እርጎ ይመር የተባለች የሚካኤል ግብር ቤት ሰራተኛ እንዲህ አለቻቸው ይልህና፤
ክራሩን
ክር ኪር ኪር ኳ እያደረገ፤ እንዲህ ይልሃል.....
እቴ በሚካኤል፤
በመሃመድ አሊ ፤ በኢያሱ ስልሽ፤
ስንት ጊዜ ነበር፤
ያገር ግዛት ጎበዝ፤
ያገር ያለህ ብሎ፤ ያመላለሰሽሽሽሽሽ??
ሺ .........ሺ...........ብለው ነበር፤
የአይጠየፍ ዘቦች፤ ቁንጅናሽን አይተው፤
የኢያሱን ግልምጫ፤
ያንችን...
ማ...ማ....ር ፈርተው።
ብለው የአይጠየፍ ዘቦች ቢያሽሟጥጧት እንዲህ አለች አሉ።
ኢያሱ ቢጠራኝ፤የጌታ ወጉ ነው፤
ሚካኤልም ቢያዘኝ፤ የአባቴ ደብር ነው፤
እኔን ያስቸገረኝ፤
ጫንቃው ያጎፈረው፤ የሚካኤል ዘብ ነው።
ብላ ስትንቀባረር። አንድ ጀብራራ የአይጠየፍ እልፍኝ አስከልካይ እቃው አይሰራም እየተባለ
ይታማል። ምላሳም ነውና ዘቦቹ አይወዱትም። ያችን ሸጋ ልጅ ሲተናኮሏት ስላያቸው መቼም
ወሬ ማሳበቁ አይቀርም ብለው እንዲህ አድርገው አሸሞሩት ይልሃል አበራ ሞላ ክራሩን
ገረፍረፍ እያደረገ፤
የኛ ቤት ሹመኛ የኛ ቤት ውላጅ፤
ማቆም መች ይችላል፤ ማመላለስ እንጅ፤
ሃኪም የት ተገኝቶ ፤ ከኛ የታለና፤
ከላይ ከሰገነት፤ ከእልፍኙ ውጭና፤
ዳብሰው ያክሙሻል፤ ኢያሱ አባ ጤና።
የአሊ ቦራ ልጅ ነው፤
የሂመኖ ልጅ ነው፤
የሸዋረገድ ልጅ፤
አይጠየፍ ወጥተን እንየው እያሉ፤
ምነው ምን ነካቸው፤
የገራዶ ልጆች፤
መቼም ልጅ ነው ብለው፤
ያንን ልጅ ኢያሱ፤ ሲስሙት የዋሉ???
እያሉ ልጅ ኢያሱ በሸጋ ልጅ የሚጨክን አንጀት የሌላቸው መሆኑን ነገሯት።
ይህንን ነገር የተመለከተች ፀጉረ ብትን የስሂን ተማሪ ከት ብላ ስቃባቸው ስታልፍ ቆም
አሉና፤
ያስኮላ ተማሪ፤
ስሂን መቃኛው ላይ፤
እንግሊዝ ደብተርሽ፤ ወድቆ ተገኘ አሉ፤
ከጥሁፍሽ መሃል፤
yes yes ማለት ታበዣለሽ አሉ።
ሰኔ 30 ላይ፤
ካርድ ተቀብለሽ፤
ስሂን ቁልቁለት ላይ ስትወርጅ ባይሽ፤
ወሎ ሻሂ ቤት ነው፤
ጮርናቄ በሻሂ፤ የምጋብዝሽ፤
መቼም ዝም አይለኝ፤
ስኳር የቀመሰው፤ ስኳር ከንፈርሽ።
እያሉ ጣፍጭ romantic ስንኞችን እያፈሰሱ ቀዬውን አወዱት።
ጋሽ አበራ ክራሩን ገረፍረፍ እያደረገ፤
ይኸ ሁሉ ሲሆን፤
ሸጋና ደም ግባት፤
እንደ ቀለጠ ማር፤
እንደ ለጋ ብርዝ፤ የሚጎነጩባት፤
የኢያሱ ከተማ፤
የሚካኤል ድካ፤ ደሴ ናት ደሴ ናት።
የሚል ይመስለኛል።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
❤1
//ላጣህ አቅም አጣሁ//
ዓለማዊ ልቤ ለበሰልህ ዳባ ምናኔ ተመኘ
በናቴ ቀብር ላይ የጠፋብኝ እንባ ፊቴ ላይ ተገኘ
ላጣህ አቅም አጣሁ፤
የሳምሶንን ገድል
ያላዛርን እድል
ያቡየን ተአምር
ተቀብዬ ነበር ቄስ እንዳስተማረኝ
አንተን አጣሁ ብየ ማመኑ ቸገረኝ
ክረምቱ ጨከነ
ጨላለመ ጋራው
በረዶና ጭፍራው
ከዋሻቸው ወጡ
ዛፎች ተመለጡ
ከምልአት ጎደሉ
ላባቸውን ያጡ
አሞሮች መሰሉ፤
ልረሳህ አልቻልኩም ልረሳህ እልና
ፊትህን አትመህ በየብስ በደመና
ከንፈርህ ያውና
ፈገግታህ ያውና
ውብ ዓይንህ ያውና ።
ገጣሚ:- በዕውቀቱ ሥዩም
@getem
@getem
@gebriel_19
ዓለማዊ ልቤ ለበሰልህ ዳባ ምናኔ ተመኘ
በናቴ ቀብር ላይ የጠፋብኝ እንባ ፊቴ ላይ ተገኘ
ላጣህ አቅም አጣሁ፤
የሳምሶንን ገድል
ያላዛርን እድል
ያቡየን ተአምር
ተቀብዬ ነበር ቄስ እንዳስተማረኝ
አንተን አጣሁ ብየ ማመኑ ቸገረኝ
ክረምቱ ጨከነ
ጨላለመ ጋራው
በረዶና ጭፍራው
ከዋሻቸው ወጡ
ዛፎች ተመለጡ
ከምልአት ጎደሉ
ላባቸውን ያጡ
አሞሮች መሰሉ፤
ልረሳህ አልቻልኩም ልረሳህ እልና
ፊትህን አትመህ በየብስ በደመና
ከንፈርህ ያውና
ፈገግታህ ያውና
ውብ ዓይንህ ያውና ።
ገጣሚ:- በዕውቀቱ ሥዩም
@getem
@getem
@gebriel_19