ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
< ኑዛዜ>

ከትዝታሽ ጋራ ለሚባዝት ልቤ
ኩታ ላሠራለት ንድፍ አሰባስቤ
አንችን የሚመስል የጥርስሽን ድርድር
አንችን የሚመስል የፀጎርሽን ብጥር
አንችን የሚመስል የአይንሽን ስር ኩል
አንችኑ የሚያክል ከቁመትሽ እኩል
አሠራለው ኩታ አሰራው ጥለት
ለብሼው እንድኖር የአካልሽን ውበት
በዛው ቢገንዙኝ ደክሞኝ የሞትኩ እለት፡፡

.....አብርሀም(ልጅ ኤቢ)

@getem
@getem
@komeb
#አልልሽም
:
:
ከፍጥረት ለይቶ እንደሰራሽ በማር
የውበትሽና የፀባይሽ ማማር
ባንድ ተሰባጥሮ አቅሌን አስቶኛል
አንደኛዬ ነሽ ግን ማለት ይከብደኛል።
:
:
ጡት እንዳጣ ዕፃን ልጅ ስነፋረቅ ውዬ
ልክ ዐይንሽን ሳየው በደስታ ዘልዬ
ማልቀሴን ረስቼ ሰላም አድሬያለው
አንደኛዬ እኮ ነሽ ማለት ግን ፈራለው።
:
:
የህይወቴ ግማድ የመኖሬ ጉዳይ
የደስታዬ ወሰን የአንድ ልቤ ሙዳይ
አንቺ እንደሆንሽ ባውቅም
የኔ አንደኛ ብዬሽ አልመፃደቅም።
:
:
ተንጠራርተሽ ደርሰሽ አቅፈሽ በሹክሹክታ
ዐይን ዐይኔን እያየሽ ስትዪኝ የኔ ጌታ
ሀሴት ይወረኛል ከእግር እስከ ፀጉሬ
አንደኛዬ ነሽ ግን አልልም ደፍሬ።
:
:
እውነት ነው የኔ ውድ እንዴትስ ደፍራለው
አንቺን እንዲ ማለት በጣሙን አፍራለው።
:
:
አንቺን አቅፎ ኖሮ አንቺን አቅፎ መሞት ምን ልቤ ቢመኝም
ተቀየሚኝ እንጂ አፈር እስክገባ አንደኛዬ አትሆኚም።
እንደው ቢሆን እንኳን አንደኛዬ እንድልሽ እውን ፈልገሽም
ሲያምርሽ ይቅር እንጂ መቼም አልልሽም።
:
:
ምክንያቱም ውዴ ...
አንደኛ ነው ሲባል አንድ ነገር ደርሶ
ሁለተኛ ሆኖ ከእርሱ ትንሽ አንሶ
የሚፎካከረው ሌላ አካል እንዳለ
መረዳት ቀላል ነው በደንብ ላስተዋለ።
:
:
ስለዚም እንቁዬ ...
በውበት በፀባይ ሁለተኛ ሆኖ ካንቺ ሚወዳደር
ቢፈለግ አንዳች ሰው በሌለበት ሀገር
አንደኛዬ እኮ ነሽ እንዴትስ እላለው
ብቸኛዬ ሆነሽ ብቻሽ ሆኜ ሳለው።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu

@getem
@getem
👍2
#የልደትሽ_መርዶ

ለራሱ ሲል...
ይመጣል ልደትሽ፣
ዘመናትን ቆጥሮ
እርጅናን ሊያበስርሽ፣
ምን አስቸኮለሽ
ይዘግይ ምን አለበት፣
የምትኖሪው እድሜ
ያልፋል...እንደ ዘበት !!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ባለ ሚዛን ሲመዘን(ልዑል ሀይሌ)

መለኪያ እያበጀ
እንደምን ነው ሚያንሰው?፤
ሚዛን እየሰራ በገዛ ቀመሩ
እንዴት ይጎ'ላል ሰው፤
.
ምነው የቀለለው
ያ የሚዛን ሰሪ፤
ምነው ያልተማረ
ትምህርት የጀመረ ቀለም አስተማሪ፤
መጫማት ያቃተው
ምነው ጫማ የሰራ፤
ምነው ሰፊ ይቀዳል የተሰፋ ሸራ፤
እግሩን ይቆርጥ ጀመር
በጫማ ሊራመድ መንገዱን ሊጓዘው፤
አዋቂነት ሽሽት
አላዋቂነትን ስለምን'ነው የያዘው?።
.
እንዴት ነው ምጠይቅ
ጥያቄ ምልክት የፈጠርኩ ይመስል፤
እንዴት እወቅሳለሁ
አርቄ እያየሁት ከመርገምቱ ተራ
የራሴንም ምስል፤
.
እንዴት በሚዛኔ
በኔ ስፍር ቀመር በቆመ መስፈሪያ፤
ቀልዬ ተገኘሁ በስጋዬ ጣሪያ፤
.
ምን ይሉታል የኔን!?...
በሰራሁት ሚዛን ዞሮ መለካካት፤
በሚበልጠኝ ማዘን
በምበልጠው መርካት፤
.
ምን ይሉታል የኔን?!...
.
በቀሰምኩት ቀለም
ጠቅሼ ባኖርኩት በውጥር ብራና፤
እንዴት ማንበብ ይጥፋኝ
የቀረፅኩትን ቃል መልሼ እንደገና?፤
.
ለምን ነው ዕውቀቴ
ለምን ነው ዕምነቴ ምስጥ የሸረሸረው?፤
ካ'ፈር ሳልተኛለት እንዴትስ ደፈረው?
.
እንዴት ነው የኖርኩት
ልብስ ሰፊ ሆኜ መራቆቴ የበዛ?፤
ለብሶ ሞቆት ሲሄድ
ስፌቴን ያዋስኩት ጥበቤን የገዛ?፤
ምነው ተራቆትሁኝ
እርቃን ቀረሁ በዓለም፤
ከጥጥ የፈተልኩት
ጥበቤ የት ሄደ
ካኖርኩበት የለም፤
.
ማረሱም ሳይጠፋኝ
መፍጨቱም ሳይጠፋኝ
ማቡካት መጋገሩ ሳይጠፋኝ ይህ ሁሉ፤
ምን ይሉታል የኔን
ሌላ እጅ መለመን አጉራሽ መማጠኑ፤
.
ምን ይሉታል የኔን ምንም ሆኖ መቅረት፤
አስባለሁ ብለው ማያሳስብ ነገር
ሲያስቡ መገኘት፤
ለማያውቁት ገላ የሚያውቁትን ገላ
ሸጠው ቸረው ማደር፤
የራስን ኑሮ ህልም ለቅዠት መገበር፤
.
ምን ይሉት ኑሮዬን?
ለማስጫ ባሰሩት ረዥም ቃጫ ገመድ፤
ጨዋታን አስበው ለመዝለል መላመድ፤
በከፍታ ዝላይ እጅ እግርን ማድከም፤
ሸክምን አራግፈው ሌላ ህመም መሸከም፤
.
ምን ይሉት ጥያቄ?
ጥያቄ ምልክት የሚለውን ምስል ፤
ራስን እያዩት
ከመርገምቱ ተራ በተጠየቁልኝ ያነፁት ይመስል?።
በጥያቄ ማሸሽ የራስን ዕውነታ
ሐሰትን ለማንገስ
እውነት ለባርነት ማሰገድ በተርታ?፤
ምን ይሉት ፅድቅ ነው
ምን ይሉት መቀደስ?፤
በጨው ማስቀመጫ
በርበሬን ማወደስ?፤
ምን ይሉት ምንነት
ሰውነትን ማርከስ?፤
በሳቅ አስመስለው የሰው ገላ መንከስ።
.
ምን ይሉታል የኔን!?...
በሰራሁት ሚዛን ዞሮ መለካካት፤
በሚበልጠኝ ማዘን
በምበልጠው መርካት፤
.
ምን ይሉታል????
፲፬-፭-፳፻፲፩ ዓ.ም.

@getem
@getem
@lula_al_greeko
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
((ሰለሞን ሳህለ))
ሰው ሲኮን ሰው አለ

ትናንት …
ተሰብሮ የጠፋ የትራስጌ መብራት
ከሆቴል የመጣ ያልተጨረሰ ራት
ዝናብ ያጠቆረው የኮርኒስ ላይ ሥዕል
በጤነኛ መንደር የታመመ ክፍል
የደረቀ ካልሲ የሸበተ ዳቦ
የሲጋራ ቁራጭ
የገልባጭ ግልባጭ
የጅን ውስኪ ቢራ ትልቅ ትንሽ ጠርሙስ
ወንበር ላይ ያደረ
የተጨማተረ የተቀደደ ልብስ
(ሰው አይሆንም ብለሽ
ሄደሻል ግድ የለም)

ትናንት …
ቁርስ ባይቀመስ ራት ባይበላ
የደሞዝ ቀን ጠዋት ዱቤያችን ቢሰላ
ሰኞ ራስ ፈለጣ ሰኞ ቀን አንጎበር
ኪራዩ ደርሶበት የተቆለፈ በር
በእንዲህ አይነት አለም
እኔን እንዳትፈሪ ባንች አልቀየምም
(ሰው አይሆንም ብለሽ
ሂደሻል ግድ የለም)

ትናንት …
የሰው ልጅ የሰው ነው የሰው ባዳ የለም
ሰው አድርጊኝ አንቺ ሰው ከሰው አያንስም
ሰውነት ሰው መሆን ሰውነት ትርጉሙ
ሰውን ሰው ማድረግ ነው
ሃሳብና ትልሙ ድካምና ህልሙ
ብየ በልመና ላንች ብናገርም
ወዳንቺ ብጮህም
ሰውነትን ፈርተሽ
ሰውነትን ንቀሽ
ከማይልቀው እድል መመጽወትን ጠልተሸ
በጤነኛ መንደር በታመመ ክፍል
ብቻየን እንድኖር በብቻነት ዓለም
ሰው አይሆንም ብለሽ
ሂደሻል ግድ የለም

ዛሬ …
ህእ …
ዛሬ …
የተቆለፈዉ በር በቁልፉ ተከፍቶ
የኮርኒስ ላይ ሥዕል በትርጉሙ ኮርቶ
ሌላ ሊሳልበት ቀለም ተቀብቶ
የትራስጌ መብራት አሸብርቆ አብርቶ
የታመመ ክፍል ተሽሎት ታክሞ
ጤነኛ መንደሩ ካንቺ ጋራ ታሞ
በድቤ ዝየራ ውቃቢውን ስሞ
ቤትሽ ጭስ አፍኖት ደንቁሮ ባታሞ
ቁርስ ራት ተዘሎ
ምሳ ሊያውም ቆሎ
የናፈቀው ህጻን በጀርባሽ ላይ ታዝሎ
በልመና ቃና በሬን ያንኳኳሽው
ሰው አትሆንም ስትይ ሰው ሆንኩኝ ማለት ነው?

ሰው ሲኮን ሰው አለ
ከማያልቀው እድል ይኸው ልመጽውትሽ
ነይ ግቢ ግድ የለም ከነ ህጻን ልጅሽ !!!

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
#ሰሞነኛ_ወሬ

በኛ አገር...
ያንዱ ስም 'ሚወሳ፣
አንድም...
ሲወድቅ ነው...
አለዚያም....ሲነሳ፣
የእስሩም ወሬ
ሳምንትን አይዘልቅም፣
ባ'ንዱ መፈታት ነው
ወሬው...የሚያከትም🤔 !!!

#ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@kaleab_1888
ድምፅሽ ከጆሮየ ÷ ዉብ ምስልሽም ከአይኔ
ድጋሚ ላይመጡ ÷ እንዲጠፉ ከኔ
.
.
በኮረብታዉ አናት ÷ ዲንጋይ ላይ ወጥቼ
ላንቃየ እስኪበጠስ ÷ ሞኝ አፌን ከፍቼ
.
.
ስምሽን እጣራለዉ ÷ እደጋግማለዉ
በጩሀቴ ጉልበት ÷ ላርቅሽ ተጋለዉ
.
.
ዳሩ ምን ያደርጋል ÷ ተፈጥሮም አድልቶ
መልሶ ያመጣሻል ÷ የገደል ማሚቶ

ቃኤል

@getem
@getem
@gebriel_19
👍2
የጃገማ ፀሃይ!!!!!!!


ጠየቀችው ልጅት፣
ይህንን ሳተና፣ይህንን ጅግሳ፣
ሲራመድ የኖረ፣
ሲጨፍር የኖረ፣
በባንዳ መቃብር፣በሰላቶ ሬሳ።


ደግማ ጠየቀችው፣
ጃገማ ግን ማነው????
የኬሎ ልጅ ማነው????
እንደ አደይ አበባ፣
እንደ መስቀሏ ወፍ፣ የተሽሞነሞነው፣
በአበሻ ጦር ሜዳ፣
በዲሞፍተር ቃንቄ፤ ሜዳይ ያሸገነው?


ኧረ ይህ ሰው ማነው?????
እየገራረማት፣
እየደናነቃት፣
ዘመን በማይሽረው፣
በአባቷ ወላፈን፣ በቃንቄው ተገርማ፣
ጠየቀች አባቷን፣
በጨዋ ልጅ ወገብ፣ ጎንበስ ቀለስ ብላ፣
ጃገማ አባ ዳማ፣
የበረሃው ግለት፣ የናዳው ስባሪ፣
የጠላትን ምሽግ፣
የሰላቶን ክምር ደርምሶ ፎካሪ።


ጀግና ልብ እንጅ የለውም ምላስ፤
እንኳንስ ስሙ ጥላው የሚዋስ።
ብሎ ጃገማ፤
አልጋውን ንቆ ድንገት ቀጥ አለ፤
በሃሳብ ጥሻ፤
በትዝታ ጦር እየሸለለ።


""" ዘራፍ!!!!!!!
ዘራፍ!!!!!!
ዘራፍ ፣አካኪ ዘራፍ!!!!!!!!
ጃገማ ኬሎ፣
የጦቢያ ዶቃ፣ የዳማ ፈረስ፣
ጎራው ላይ ሲዘልቅ፣ ምሽግ እሚያፈርስ።
ሃይ ዘራፍ ብሎ፣ ዘሎ ሲገባ፣
ይዝረጠረጣል ባንዳና ሌባ።
ዘራፍ ጃገማ ባለውጅግራ፣
ጎጆ መስርቷል፣
ቃል ኪዳን አስሯል፣ ከጦቢያ ጋራ።
ስማ ንገረው፣ ያን የባንዳ ዘር፣
እንጫጫዋለሁ፣ እንደ ጎመንዘር!!!!
የበጋው መብረቅ፣ የእሳቱ ጉማጅ፣
እንደ እርጥብ ቃሪያ፣
የሚለበልብ፣ ስሙ የሚፋጅ፣
የአባ ዳማ ልጅ፣
ከዘር ማንዘሩ፣ ጠላት አዋራጅ።""

"""
ብሎ ሲፎክር
እንደ ፈላ መጅ፣ እንደጀበና፣
ፊቱ ለበሰ ፣
ኢትዮጲያ የሚል፤ ቀስተ ደመና።


ይች ልጅ ጠየቀች፣
አባቷን ደጋግማ፣ ደጋግማ ጠየቀች፣
በአበሻ ልጅ ማእረግ፣
የዚህን ጃውሳ፣ አይን አይኑን እያዬች።
ጅግሳው ጃገማ፣
በሸገነው ቃሉ፣ ባጭሩ ነገራት፣
መቼስ የጀግና ልጅ፣የአባት ወግ አይጠፋት።
ትክዝክዝ እንዳለ፣
እንባ እንዳቀረረ፣
ይኸው ይኸ ጀግና፣ እንዲህ ተናገረ፣


አየሽ የትምወርቄ፤
አርበኛ በደሙ፤
ጀግና በድምድሙ፤
በአጥንቱ መግሮ ፤በተሰራች ሃገር፤
ከሞት ይቆጠራል፤
ለሠላቶ ውላጅ፤
የሚቆራርሱት ጣቢታ መጋገር።


ባንዳ ቀኑ ገጥሞት፤
ወንበር የሰጡት ቀን፤ ሃገር ይወገሻል፤
አርበኛም ዱር ወዶ፤
ካገር ሞት የኔ ሞት፤
ይቅደምና ልሙት፤
እያለ ከቤቱ ከደጁ ይሸሻል።


ግን እንዲህም ሆኖ፤
በአርበኞቹ ጥላ፤
በደም የተዋጀ፤
በአጥንት የታጠረ፤
የነፃነት ቅኔ፤
በትውልዱ ቀለም፤
እየተማገረ ቅኔው እስኪፈታ፤
አይፈርስም ሰንደቁ፤
በአልብላቢት ከንፈር፤ በምላስ ሩምታ፤
ያኔ ይፈወሳል፤
ምን አገባኝ ይሉት፤ የዘመን በሽታ።


እየውልሽ ልጄ፤
የጃገማን ድንበር፤
የጃገማን ሰንደቅ፤
ቀስተ ደመናውን፤
ብጣሽ ጨርቅ እያሉ፤
በርኩሰት አፋቸው፤ ንቀው ያዋረዱ፤
በየመሸታው ቤት፤
ቂጡን ገልቦ ሚሄድ፤
ችው ችው የሚባል፤ ቡችላ ወለዱ።


እናምልሽ ልጄ፤
ሞተን የሰራናት፤
ወድቀን ያነሳናት፤
ኢትዮጲያ እምትባል፣
ገራሚ አገር አለች፣
እድሜዋን ፈጀችው፣
አርበኛን አዋርዳ፣ ባንዳ እየሰቀለች።
ዘመን ቡቱቶዋን፤
እከክዋን አራግፋ፤
ባንዳ ቤቱ ሲፈርስ፣
ሰላቶ ሲረክስ፣ ፊቱ ሲገረጣ፣
ያኔ ነው የኔ ልጅ፣
የጃገማ ፀሃይ፣
በአበሾቹ ሰማይ፣ ቀድማ የምትወጣ።
ኧረ ትውጣ!!!!!!!!!"
"""

( ብወደው፣ብወደው ለማልጠግበው፣ ለጄኔራል ጃገማ
ኬሎና ለልጁ የትም ወርቅ ጃገማ)

መልካም ልደት!!!💚💛❤️

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
👍1
---ከወደቅሽ እኩል ነን ---
።።ረድኤት አሰፋ ።።።

@getem
@getem
@gebriel_19
የማርያም ንግስ ዕለት
(ኤፍሬም ስዩም)
የማርያም ንግስ ዕለት...
አዳፋ ነጠላ
የቀጠነ ገላ ፥ ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ...
ጥቁር ያዘን ቀሚስ ፣ ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች...
ከቤተስኪያን አጸድ ፥ ቆማ ከዋርካ ስር
አንዲት ሚስኪን ባልቴት ...ትለማመን ነበር
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም ፣ መሶቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ፣ ጀርባዬ ተራቁቷል፡፡
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ፣ ትለምናት ነበር
ከቤተስኪያን ጎሮ ፣ ቆማ ከዋርካው ስር፡፡
የደብሩ አለቃ
ካባ ላንቃ ለብሶ ፣ ምጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጩ ፣ ወደፊት ተስቦ
የንግሱን ምእመን ፣ ወደፊቱ ስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክ ብሎ ያስተምራል

የመቅደሱ ቀለም ፣ ሊታደስ ይገባል

የካህናት ደሞዝ ፣ ሊጨመር ግድ ይላል

ደጀሰላም ወንበር ፣ እጅጉን ያንሰናል
እናም...
ከዚህ ታላቅ ደብር ፣ ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን ፣ እጃችሁ የታለ?
እያለ፡፡
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል፡፡
ለንግሱ የመጡ...
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች...
ጥለት የለበሱ ፣ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ ...እፊት ከመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ ፣ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሰላሙ ፣ ደሞም ለወንበሩ
በሺ..."የሚቆጠሩ
ብሮች ወረወሩ"
የደብሩ አለቃ ፣ ግንባር በጣም ወዛ
የሚወረወረው ፣ ብሩም በጣም በዛ፡፡
.
የዛች የምስኪን ነፍስ
ያች ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካው ስር
ተስፋዋ ማርያምን ፣ ትለማመን ነበር
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም ፣ መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኝም ፣ ማድጋዬ ጎድሏል
እለብሰው የለኝም ፣ ጀርባዬን በርዶታል
አንቺ ነሽ 'ተስፋዬ' ፣ የኔ 'ተስፋ 'ሞቷል
ወድቃ እየተነሳች
እንባ እያፈሰሰች፡፡
ግና -ግን ለዛሬ ፣ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ፣ ውሰጂ እንባዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ ፣ የአንገት ሀብሌን፡፡

@getem
@paappii
ለእግዜር የተፃፈ

እንዴት ነህ አግዜር ሆይ
ሰላም ሰላም ለከ
ይሁን ለስምከ
እኛማ ደህና ነን
ከምድረ ፋይድ ሁነን
መከራን አምጥተን
መከራ እየበላን
እኛማ ደህና ነን
አንዱን አየሻርን
አንዱን እየሾምን
በጎጥ ተከፋፍለን
በዘር ተበታትነን
የወለዱ እነሱ
እዥ እያለቀሱ
ከአንድ አፈር ተሰርተን
አንዲት ነፍስ ተላብሰን
ውስጥ ውስጡን ተባላን
ነፃነት ነው ያልነው
ነፃነት አሳጣን
ይገርማህ እዚህ ከምድረ ፋይድ ስር
እውነትን ተናገር ከመሸበት ማደር
አሁን አዚህ ቀርቷል
በሆድ ተተክቷል
አንዱ እየተራበ አንዱ እየጎረሰ
ቀዳዳው በርክቶ በዛ እየፈሰሰ
ላንቃችን ተዘግቶ እንባችን ይፈሳል
ከሰው ከፍ ብሎ ወንበር እና ነዋይ
አቤላችን ጠፍቶ ቃየል ሁኖ የበላይ
ፍቅር ቤቱን ለቆ አንድነት ርቋል
ከምድር አንጋጦ አንተን ይጠብቃል
አግዜሩ ፈጣሪ
የዓለም ሁሉ ሰሪ
አትበለን ችላ ፍቅርህን አደራ
እኛ እንዳንጠፋ እንደነ ገሞራ
ወይ ወርደህ አንተና
ወይ ሙሴን ላክና
ከፍለን እንሻገር እንለኩስ ፋና
አንተ ከሀሊ ነህ ትችላለህ ሁሉን
መቀነቷን ሰጠህ በአንድነት ቀምረን
ፍቅራችን ይመለስ ሰላማቻን ይገስ
ከምድር እስከ ሰማይ
ካንተ መንበር ድረስ
ተፃፈ በጃህፈር

21/05/2011
ወለጋ መካነ ሙህራን

@getem
@getem
@gebriel_19
የሰማይ ቤት ግሮሰሪ
(አሱ እንደፃፈዉ)
.
.
"ጨረቃ" ምንላት
ግሮሰሪ ቤት ናት!!!
"ሰማይ" ለምንለው ፣ ቀውጢ ከተማ
ሥራ ምትጀምረው ፣ሲሆን ነው ጨለማ!!!
..................................................
በር እንደከፈተች ፣ አብረው የሚወጡ
ከዋክብት ደሞ...
ሰካራሞች ናቸው ፣ እሷ ጋ ሚጠጡ!!!
*********************
በጣም የሰከረው...
ከሰማይ ፈጥፍጦ ፣ ራሱን ሲገድል
"ተወርዋሪ ኮከብ" ..
ማለት ነው የኛ እድል!!!
********************
ተወርዋሪ ጠርሙስ ሊሆንም ይችላል!
ማን ያውቃል?

@getem
ባይገጥምም ይገጥማል
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሚታገላት ልቤ ፣ የሚጥላት እሱ
የፍቅር ጥያቄ
ያቀረብኩት እኔ ፣ ምትመልሰው ለሱ
አለመገጣጠም ፣ ግጥም ነው በራሱ።

@getem
@getem
@genbiel_19
👍1
#ነፃ_አውጪ

ሰደድ እሳት ሆኖ
ነገር ባገር ላይ ከመጣ፣
ያፈገፈገው ነው
ሌላውን ነፃ የሚያወጣ !!!



#ሀብታሙ_ወዳጅ

@getem
@getem
@gebriel_19
የባለ ዛር ድቤ!!!!!!!!


እንደ ፊዳ ፍየል ፤
ቆዳዋ ተገፎ ፤
በገዛ አንጋሬዋ ፤ ስበው የወጠሯት፤
ያም ልምታሽ፤
ያም ልምታሽ ፣
ያም ልምታሽ እያለ ፤ የሚቀባበላት ፤
መታረዷ ሳያንስ ፤
ቆዳዋም ተገፎ ፤ እረፍት ያላደላት ፤
ሁሉም በየተራ ፤
በአይበሉብሽ ቡጢ፤ የሚደበድባት፤
እምየ ኢትዮጲያ ፤
የባለዛር ድቤ፤ የጉድ ከበሮ ናት ።

((( ጃ ኖ )))💚💛

ሸጋ ጁምኣ!!!!

@balmbaras
@getem
@getem
/// ድምፅ_ወይስ_ብርሃን///
ካወራሽው ሁሉ ፤ አንዱንም አልያዝኩት
እንዳይከፋሽ ነበር ፤ ጆሮዬን የጣልኩት
ከአንደበትሽ ላይ ፤ ቃላት ሲዳክሩ
ሁሉንም ነግሮኛል ፤ የአይንሽ ጨረሩ!
-
በኔ እና አንቺ ሰማይ …
በዶፍ ዝናብ መሃል ….
ከነጎድጓድ ቀድሞ ፤ መብረቁን አየነው
ለካስ ከድምፅ ይልቅ ፤ ብርሃን ነው ‘ሚፈጥነው፡፡
----//-----
@getem

.