ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አለሜ ናፈከኝ

በኖርንበት ጊዜ በነዛ ዘመናት
በደስታ በሀዘን  ያለፍት አመታት
ለካ ይናፍቃል
                 ጭቅጭቅ ሁካታ
                   ኩርፊያና ፀጥታ
                   ማልቀስ ነበር ፌሽታ
ሁሉም ይናፍቃል የራከኝ ለታ
          
                By     @Hanipia



@getem
@getem
@getem
29😢9👍6🔥6
አንተ ማለት እኮ......
.
.
የአይኖችህ ማማር፤
ዉስጥ የሚሰረስር፤

የጥርሶችህ ፀዳል ልብ የሚሰነጥቅ፤
ፈገግታህ ሚወደድ መንፈስን የሚሰርቅ፤

አንተ ማለት እኮ......
የሹማምንት አብራክ የመኳንንት ዘር፤
ነቅዕ ያልተገኘብህ የዉቦች ሀሉ ዳር፤

ልቡ 'ሚደነግጥ ያየ የሚመኝህ፤
በነጋ በጠባ ሁሉ የሚያልምህ፤

አንተ ማለት እኮ........
በፈራሽ ዉበትህ ሠርክ የምትመካ፤
በለበስከዉ አልባስ ሰዉን የምትለካ፤

ከራስህ ተጣልተህ ሰላምህን ያጣህ፤
መደሰት የራቀህ አንተ ማለት ይህ ነህ።
...............................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
38👍5🔥5
ጥቂት አዋጥተን ፥ ለሌሎች ደስታ
ብንኖር መልካም፤ ብንሞት እፎይታ

ጊዜ ገበሬው፥ ላያጭድ አይዘራም፤
ፈክቶ የኖረ ፥መክሰም አይፈራም።

by Bewuketu seyum
መልካም ልደት በዉቄ

@getem
@getem
@paappii
🎉3320👍4
የአብስራ ሳሙኤል

ማንበብ ቢሳነን እንጂ
ቅንጣት እውነት መች ይጠፋል?
ህይወት በምድር ገጽ ላይ
ገጸ ሰቡን ማልዶ ይጽፋል.
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔


አሁን አሁን ያለፈችው
ቆንጅዬ ወጣት —
የእንባ ካፍያ፣ ያ'ረጠበው
ጉንጯ መንጣት.

ንስንስ ጸጉሯ ያዘለው
የግንጥል አበባ ገላ፣
ዝም ብላን ያለፈች
እንዲያው እንዲሁ... ዝም ብላ!

ልቡሰ ህሊናው ለመራው
ስውር እውነት እዚህ ይገኛል!

እንዲህ እንዲህ ይለኛል —
❛❛አለመንኩም ብዙ ነገር
አልማለድኩም ምቾት ድሎት፣

መገፋት ላሳሳት ነፍሴ
ለ'ልቧ ልቤን ልሰጣት፣
የልጅነት ትኩስ ህልሜን
ተይ ስላሉኝ መች ቀጨሁት?
ሰው አይደለሁ ተመኘሁት.

እንዲህ እንዲህ በቃል ቢሉት
አይገባውም ያልቀመሰ፣
ለፍቅር ጎኑን ብጠጋው
የፍትወት ፍሙን ለበሰ።

ወንድ እንዲህ ነው አልልህም፣
እሱ ግን እንዲህ ነበረ —
ወድጄ ክብሬን ብሰጠው
የማፍቀር ቅስሜን ሰበረ.

የአበባ ጉንጉን አንጥፎ
በመባው ማሳ ደፈረኝ...
ፈቅጄ ከተኛ'ሁለት;
ከእንግዲህ እውነት ምን ቀረኝ❜❜?



ደሞ ከሷ፣ አሁን አሁን
ካለፈችው ወጣት እግር ስር፣
የነበረች የኔ ቢጤ
ምስኪን ለማኝ፣

ነጠላዋን ለጎዳናው ያነጠፈች፣
እንደ ጤዛ በማለዳው የረገፈች።

ምኞት ህልሟን ምስጥ
የበላው የእግሮቿን ስር፣
ልቡሰ ልቦናህን አንቃው፣
እዚህም እውነት አይጠፋም!

ክብርን በዲናር ከመቸርቸር
መለመን እንዴት አይከፋም?
እንዲህ እንዲህ ትለኛለች
❛❛ይጸድቃሉ በመስጠት፣
ውስጥ ማግኘት አለ!"

ሰው በደለኝ አልልህም፤
የጊዜ እንጂ የሰው ጌታ
ወዴት አለ?

የማውቀው ሰው፦
የሚሰጥም፣ የሚነሳም፣
የሚጥልም፣ የሚያነሳም❜❜።



ደሞ ደሞ
ከሚስኪኗ የኔ ቢጤ ከአይኗ ሳያርቅ
ለጋ እድሜውን በጎዳና የሚቦርቅ፣

አፍ ሲፈታ "የዳቦ አለህ?"
የሚል ቃላት የቀመሰ፣
ለእግሩ ጠጠር ..
ለሌሊቱ ቁር ንፋስ ያንተራሰ።

አዲስ ትውልድ! አዲስ ሀገር!
አዲስ ታሪክ የሚናገር፣
❛❛በዚህ በጎዳና፦
ከሚያልፍ፣ ከሚመጣው፣
ከሚመላለሰው፣
ከመንገደኛው ሰው —

ሁሉም የግሉ ድብቅ እውነት አለው!
የሚያነጣጥለው፣
የሚያመሳሰለው።

ከመልኩ ገጽ ላይ
ተመልከት ሀዘኑን አስተውል ደስታውን፤
ቢተራመስ እንጂ
ማንም አያውቀውም
መድረሻ ቦታውን።

አልፎ፣ ሂያጅ መንገደኛ ነው
የሰው ልጅ በዚች ምድር —
ከልቦናው መቅረዝ በእኩል
ተስፋ ምኞት የሚያሳድር!

እናም እኔ፦
የማውቀው ሰው፦
**የሚሰጥም፣ የሚነሳም፣
የሚጥልም፣ የሚያነሳም❜❜።


@getem
@getem
@getem
36👍5
ኡስስስስ
አትረብሹኝ

ዝምታን ነው ምሻ
በስተመጨረሻ

እራሴን ላናግር
አታብዙብኝ እግር

አታንጋጉ ወሬ ማበል
ትንሽ ዝም ልበል።

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
50👍7🔥7
ይህ ቀዥቃዣ ዝናብ - ገላሽን ይንካና
ወዮለት ሰማዩ - ወዮለት ደመና !

ወፍ አይዘምርልሽ - ዛፍ አያስጠልልሽ
በቃ እኔ አለሁልሽ !

ደግሞ ይሄን እወቂ !
ሆዴ እንደሚበላኝ ፥ ካለኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ ፥ በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር ፥ በእግዜር ስትመኪ !

እኔ ነኝ ጠባቂሽ !
እኔ ደስታሽ !
እኔ ፈገግታሽ !

ሁሉንም የምሆን ... !

እግዜር ፥ አላህ ፥ ሰማይ
ንፋስ ፥ ውሃ ፥ ድንጋይ

ያንቺ ብቻ አገልጋይ !
ያንቺ ብቻ ታጋይ !

"ክነፍ !" በዪኝ - ልክነፍ
"እረፍ !" በዪኝ - ልረፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ ፥ በእኔ በኩል ይለፍ !!!

by Habtamu hadera

@getem
@getem
@paappii
65👎12🤩11👍9😁6🔥5😱5🎉2
የአብስራ ሳሙኤል

ኖሮ ማለፍ ብቻ አይደለም የህይወቴ ጥግጋቱ
በሀብት በዕቁባት አይለካም የዐላማዬ ጽናቱ
ቁና ባይሞላ ከቁብ፣ ከእፍኝ ባይቆጠር 
የድርሻዬን ልጣል ጠጠር... 
የድርሻዬን ላዋጣላት 
ሀገሬኮ ማንም የላት!
***
እንዲህ እንዲህ፣ በዚህ በዚህ
በየጎዳናው ላይ
ደም እንደ ወራጅ ውሀ በሚገበርበት 
ሀዘን እሮሮ'ችን
እንባችን በዝናብ በሚታበስበት
ሰቂቃና ሰቆቃ ባደቀቃት ሀገር
መኖር ብቻ አይበቃም 
***
በዘመን ድልድይ ላይ ኦናነት ማሻገር
የድርሻዬን መንገድ ልያዝ
የድርሻዬን ፋና ልቅደድ
ቀጣይ ትውልድ ተተክቶኝ
ወደሚሻው እንዲራመድ ...
***
ስብከት መሰል አይደል?
ድሮም እውነት ይሰለቻል
ያልገነቡት ሀገር ማውረስ
ለቀብር መች ይመቻል? 
ብቻ ብቻ፣ እንዲሁ ማለፍ እፈራለሁ! 
"ምን ሰራህ?" ይለኛል ነፍሴ 
ከጥገትሽ ጠብቶ ባይጸናም 
"አለሁሽ!" ይላል መንፈሴ
"አልደላሺኝም ለኔም !
ሳር ቅጠልሽ መቼ ጣመኝ? 
እንዴት ትቼ ልተውሽ?
ህመምሽ ሰርክ እያመመኝ!" 
***
እማ እማ እናት አለም... 
ኖሮ ማለፍ ጀብድ አይደለም! 
ጀንበርን በስካር እየተደበቁ
ከየጎዳናው ላይ ቢነሱ፣ ቢወድቁ... 
***
ታሪክ አያድስም፣ ዘመን አያቀናም 
ወዝ ያልፈሰሰበት በምኞት አይጸናም
ጥቂት ጠጠር እናዋጣ እፍኝ መባ እንገብራት 
ከእኛ ሌላ፣..ሀገሬኮ ማንም የላት!


@getem
@getem
@getem
24🔥3
ጥያቄ??

አሁን በእኛ ዘመን ፍቅር የምንለዉ፤
በቅዱስ መፅሐፍ ሠርክ የምናነበዉ፤

ካፋችን ማይጠፋ ቀን በቀን ምንጠራዉ፤
ፍቺዉ የጠፋብን ፍቅር ግን ምንድነዉ??
..................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
37👍7🔥4👎2
ዜማ ከምፈጥር
ቅኔ ከምቋጥር
ምስልሽን ለመሳል ፥ ሸራ ከምወጥር
ቃል ከማፈላልግ ፥ የሚመጥን ላንቺ
ምናለ ብትመጪ ?

ነይ እንተቃቀፍ
ነይ ዝም እንባባል
ደሞ ለፍቅር ቃል
የሚጽፍ ሰው ሞልቷል
የሚቀኝም አለ
ከእኔ የተሻለ
ልብ ላይ የሚደርስ
የቀረበ ለነፍስ

አንቺ ብቻ ድረሽ
ሌላውን ታያለሽ

እሩቅ ለሩቅ ሆነው
የተነፋፈቁ
አንዴ ተገናኝተው
በአንድ ጥላ ሲያርፉ
ይዘምራል ወፉ
ይደንሳል ዛፉ ።
ብቻ አንቺ ነይልኝ !

By Hab HD

@getem
@getem
@paappii
49🤩3👍2🔥2😱1🎉1
መንገደኛው ልቤ ቅጽበት'ዓት ከአንቺ ያደረ 
መሄድ አመል ሆኖበት ደሞ ሌላ አፈቀረ 
ደሞ ከሌላ አደረ አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ 
‧˚‧༘ 
ቀን ያሻገረኝ ዛጎሌን ጥዬ 
ሁሉም እንዳንቺ አይደለም ብዬ 
ነፍሴን ላጽናናት ወይ ልደልላት 
ናፍቆት ትዝታው ይበቃል ስላት   
༄ 
ተቀበለቺኝ 
❛❛ይሁና አለቺኝ❜❜ 
በል ሂድ እንግዲ... 
⸻ 
#ከአዲስ መስክ ላይ
ልዬ የሆነ ብስራት አይጠፋም 
ከንፎ መሰበር ሮጦ መውደቅ 
ህልምን ከመስበር ፍጹም አይከፋም 
 
ደሞ ወደ አዲስ ጠረን 
ደሞ ወደ አዲስ ገላ 
ይሁን ብላ ህይወት ስታባብለኝ 
⸻•⸻
ይኀው ደሞ ትዝ አለኝ 
ተሳሰረብኝ እግሬ 
በአንቺም ጊዜ አኮብኩቧል 
ክንፎቹን ልክ እንደ ዛሬ 
💧 
ትዝ አለሽ ያኔ? 
በሀዘን በእንባ የተማጸንኩሽ 
የበደሌ ስር ቅሉ ሳይገባኝ 
ይቅርታ ያልኩሽ 
🕯 
ገፍተሽ መሄድሽ 
ብቻዬን ስሆን ዛሬም ያመኛል 
አንዴ የቆሰለ ማደሪያስ
ቢያገኝ መች አምኖ ይተኛል? 
 
ግና ፍቅሬ... 
ቢሆንም ባይሆንም 
ክንፋም ህልሞች እንጂ 
ጨለማ አልለምንም 
ትሏ ህይወቴ
በጀንበር ብስራት ክንፍ ያበቀለ 
☾ 
ሁሉም እንዳንቺ አይደለም ያለ 
ደሞ ሌላ አፈቀረ 
አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ 
𓇢 
አንድ አይኑን ለመንገድ ገልጦ 
ከሌላ ልቡ ውስጥ አደረ...


የአብስራ ሳሙኤል

@getem
@getem
@getem
21👍15😱2
ደግሞም አንዳንዴ
መልካም ነው ብለህ
የተከልከው ዛፍ ፤
እሾህ ያፈራል ፤

ልብ አለው ብለህ
የቀረብከው ሰው ፤
እባብ ይኾናል ፤

ጨበጥኩት ያልከው
ድንገት ይወድቃል ፤

ቀረብኩት ያልከው
ድንገት ይርቃል ፤

ግን ከዚህ ሁሉ
ፈገግ እያሉ
መኖር ይደንቃል ፤

ትንሽ
ተዋርደህ ፤

ደስታ'ና ተድላ
ይቅርብኝ ብለህ ፤

ውበቷ እንዳያድፍ
ሕጓ እንዳይሻር
ሚዛኗ እንዳይጎድል ብታዝንላትም ፤

ሕይወት ጨካኝ ናት
ለሚሳሳላት
ምሕረት የላትም ።

By Tewodros kasa

@getem
@getem
@paappii
68😱8👍5🔥4🤩4
‎ አስር ጊዜ ውድቀት
‎ አስር ጊዜ ጭንቀት
‎ በጭቃ ውስጥ ሲያልፉ

‎ ማይወዱትን መውደድ
‎ ማይለምዱት መልመድ
‎ ስቃይ ብቻ ትርፉ



‎ ብዙ አመት ለመኖር ብልም ደፋ ቀና
‎ ሞቴን ተመኘሁኝ አፈቀርኩሽና።

‎ ኤዲያ!

‎ ዮኒ
‎      ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
44👍11🔥11😢4👎2😱2🤩2
(በዕምዓዕላፍ)

         ወደ ውስጥ ፈሶ
         ወደ ውስጥ አልቅሶ
         መሬት ሳትረሰርስ
         እምባውን ጨርሶ
ይሆናል እያልኩኝ  በመላምት ተስፋ
ምኞት ላያፀናኝ   ነፍሴ ተቀስፋ
        የልቤ መናወዝ
        የኔ መንጠራወዝ
                        ስለ አንቺ ነበረ
ፍቅርሽ መስቀል ሆኖ   የተቸነከረ

በጠባብ ማነቆ  ቀንበር ተሸክሜ
የፍቅርን መቀነት  በተስፋ አገልድሜ

             ከእድሜ
                       ቀድሜ
እንሆ  አሰስኩሽ.......
               ለዘመናት ባጀሁ
               አመታትን ፈጀሁ
አንጋጥጬ እያዬሁ  የማይወርድ መና
ሰማዩን ከልሎት  የማይዘንብ ደመና
       እያዬሁ ሳላምን
       እግዜርን ስለምን
       እኔ ወበከንቱ
       የትም ቀረሁ እቱ

@getem
@getem
@getem
👍3832🔥2😢2🎉1
የማርያም መንገድ
.
.
መንፈሴ ሲዝል ሰላሜ ጠፍቶ፤
ልቤ ሲታወክ ዉስጤ ተረትቶ፤

ቢጨንቀኝ ጊዜ........

አጥብቄ ለመንኩ የማርያም መንገድ፤
ካለሁበት ማጥ ያሻግረኝ ዘንድ።

በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
57🔥7👍4
ኤሊና ጥንቸል ተቀጣጠሩ
ማራቶን ሩጫ ሊወዳደሩ።
የውድድሩ ሲያበቃ ሩጫ
እስቲ ገምቱ የማነው ዋንጫ?
                
                — አዝማሪው —

በብላቴና ዕድሜዬ ስለ ህይወት ሲቀኙልኝ
ኤሊም ሆኜ እንድ'ቀድም
ጥንቸሎቼን አስተኙልኝ

መኖር መልካም ቀና ጥበብ የምትሻ
አሁን ባይገባንም
ትርጉም አይታጣም በስተ'መጨረሻ



አየሽ በዚህ ተረት መኖር እንዲህ ይቀኛል
ሸክም ያልከው ዛጎል ጌጥህ ነው ይለኛል

አልችልም ካልክበት
አበቃ ካልክበት
ደሞ በአዲስ ፈና መንገድህን ቀጥል
የናቁት ጠጠር ነው ግዙፉን የሚጥል
ያቅተኛል ብለህ
ይከብደኛል ብለህ
በፍጹም አትፍራ።

ነበልባል ህልምህን
በእንቅልፋም ልቧች ላይ
ጎጆ አድርገህ ስራ።

ልቦናው የበራለት ከትልም ይማራል
ባሪያ ብለው የናቁት በጊዜው ይከብራል

አትፍራ! ግድየለም!
ሰጋር እግሩን አይተህ
❛❛አልቀድመውም አትበል❜❜
የኑሮን ውርርድ ሳትታክት ተቀበል

#ህይወት ጥበበኛው
መልካም ቅኔ አያጣም
ላሸነፈው ዋንጫ
ለደከመው ደሞ እንቅልፍ አይታጣም።

የአብስራ ሳሙኤል

@getem
@getem
@getem
52👍11🔥3
( ልመለስ ነበር )
============

ከእናቴን ማህጸን ልክ ስወጣ
ያቀፉኝ እጆች ሚሞቀው ፎጣ
ገና ሳለቅስ የጎረስኩት ጡት
እኒያ ደግ አይኖች የማይቆጡት
የእሹሩሩ ድምጽ አባባይ ዜማ
የምቾት ዓለም የህልም ከተማ

ዘልቀው ላይዘልቁ ላይቆዩ ነገር
የውሸት ደልለው በማደናገር
አስቀሩኝ እንጂ .. ከዚህ ሞት መንደር
      አመጣጤ እኮ
ጥቂት ቆይቼ ልመለስ ነበር  !!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
100🔥6👍5😱5🤩3😢2😁1
አብሮ መጥፋት

በፍቅር ሰንሰለት እኔን ላንቺ ድሮ፣
ያለፈ ታሪክሽን
የኀጢአቴን ግርሻት ሊያጠፋ ቀን ቀጥሮ፤
"ወደ ኋላ መዞር ላ'ፍታ ሳትመኙ፣
ወደ ፊት ተጓዙ ነጋችሁን ቃኙ!
ለፍቅር ታመኑ ለፍቅር ተቀኙ!"
የሚል ትእዛዝ ሰጥቶን
ትናንትናችን ላይ እቶን እሳት ቢለቅ፣
ወላዋይ መንፈስሽ
ልክ እንደ ሎጥ ሚስት ታየ ሲፍረከረክ፡፡

የቀድሞ ፍቅረኛሽ…
ያ ሁሉ ትዝታ
መጥፋት አብከንክኖሽ በድንገት ስትዞሪ፣
የጨው ሐውልት ግግር
አድርጎ ቢያስቀርሽ የፍጥረት ፈጣሪ፤
ሎጥን ልምሰል ብዬ…
የፍቅርሽ እርምጃ
ከኋላዬ ሲቀር ወደ ፊት አልሄድም፣
አይቼሽ ለማልቀስ
አይቼሽ ለመድረቅ
ያ'ምላኬን ቃል ሽሬ መዞሬ አይቀርም፡፡

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
40🔥5👍2🤩2
አዝማሪ ቤት አፍሮ ፥
ፀሎት ሥቆም የሚያንጎራጉረኝ ፤
ግራ -ገብ ነብሴ ነው
ከሠው ፣ ከአምላክ የለያየኝ ።

by leul Zewelde

@getem
@getem
@paappii
32😢7😁6🤩1
(የሞገሴ ልጅ)
ከእኔ ካልመጣ
ሂጂልኝ ማለትን - አፌ ካልተማረ፣
ካልሄድኩ ካለ ልብሽ፣
ብከለክለውስ - መቼ ትቶት ቀረ?

ኁሌ አትሂጂ ባይ
ኁሌ ልሂድ በሚል ረባሽ ከተገፋ፣
ሰይጣንን ያስቀናል፣
እንኳንስ በሌላው በራሱ ሲከፋ!

By @eyadermoges

@getem
@getem
@getem
29🔥5👍1🤩1
‎ እጠራጠራለሁ
‎ ተቃርበሽ  ተቃርበሽ ስጠፊ ስላየሁ
‎ ደግሞም እቀናለሁ
‎ እንደኔ ምትወጂው ይኖር ወይ እላለሁ

‎ አልመስል አለኝ እውነት-የምትስሚኝ የምታቅፊኝ
‎  ተቃርበሽ ልጠፊኝ?
‎ ፍቅር ጣዕም አስለምደሽ ከአይን ልደበዝሽ
‎ ለምንድነው የምትስሚኝ?
‎ ለምንድነው የምስምሽ?

‎ እጠራጠራለሁ
‎ ስትርቂኝ ስላየሁ
‎ ስትስሚኝ ስላየሁ
‎ 
‎ ካንቺ ፍቅር ውጥን ብርቅም ብሸሽም
‎ እወድሻለሁኝ ግን ልቤ አያምንሽም
‎ አፈቅርሻለሁኝ ግን ልቤ አያምንሽም።

‎ ብቻ
‎ አለሁ እንዳለነው
‎ ስትቀርቢኝ እያየው
‎ ስትርቂኝ እያየው
‎ አለሁኝ እንዳለሁ

ዮኒ
‎      ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
22👍19😢2