#ህይወት ተናገሩ !
.
ዘፈን ሀጥያት ነው ... አዝማሪ ነው ፈረስ
እሱን ሲሳፈሩ ... ገሀነም ነው የሚያደርስ
ሲሉሽ ሰባኪዎች...
የቃሉ አርበኞች ...
.
ህይወት ተናገሩ
ለፍቅር ዘምሩ ... ጥላቻን አርቁ
ከተኛችሁበት ... ነግቷልና ንቁ
የሚል ዘፈን አለ ...ደስ የሚል ሙዚቃ
እናም እኔና አንቺ
አርቲስቱ እንዳለው ጥላቻውን ሽረን
ለፍቅር እንንቃ!
.
ስሚ እስቲ ዜማውን
መርምሪው ግጥሙን
.
ዘፋኙ ምናለ?
ከምን ጥበብ ዋለ ?
.
"አንዳንዶች በእርድና ያወቁ መስሏቸው
ፀብን ይፈጥራሉ ንቃችሁ ተዋቸው
ፈተናና ናት ህይወት በሂደቷ ሁሉ
ስንቶች ነው ወድቀው ተሰናክለው ያሉ?
ህመም ክንዱ ሲያይል ሲበዛ ስቃዩ
ወደ ፈጣሪ ዘንድ ትጉና ፀልዩ !"
.
ብሎ አልተናገረም ?
ለስንቱ ሀኪም ሆኖ መንፈስ አላከመም ?
.
እስቲ ጠይቂያቸው
እንዴት ነው በያቸው ?
የሚመክር ትውልድ ለሀገር ዘምሮ
ፍቅርን የሚሰብክ ጥዑም ዜማ ፈጥሮ
ሞትን የሚያወርሱት ዘፋኝ ነው ብለው
ምን ባለ ስሌት ነው ሲኦል የሚዶለው?
.
ግድ የለም ጠይቂ
ግድ የለም መርምሪ
ቃሉን በደፈናው በግርድፉ ፈተሽ
ፅንፍ ይዘሽ አትቅሪ ።
.
ይመስጠር ይሄ ቃል ... ተገልጦ መጥሀፉ
አሜን አሜን ብለው
ስንቶች ነው ከእውነት ... ቀዬ ዘንድ የጠፉ?
.
እስቲ ቀርበሻቸው ...
እንዴት ነው በያቸው?
"ዘፈን ሀጥያት ነው ...
የዘፋኝ መንገዱ ... የሲኦል በራፍ ነው
መዳረሻው ሁሉ ...ፅልመት ጨለማ ነው"
ብለው ለሚተቹት የእምነት መምህራን
ፀልዩ የሚል አርቲስት
ምን ባለ መንገድ ነው ለሞት የሚመራን ?
ብለሽ ጠይቂያቸው...
👇
(በነገራችን ላይ ይሄ ሀሳብ ዘወትር በአዕምሮዬ ጓዳ ይመላለሳል። እናም የዴመን ማርሌን Speak life የተሰኘ ሙዚቃ ሳጣጥም ነው ይሄን ሀሳብ ለምን ወደ ግጥም ቀይሬ ሌሎችንስ አላማራምርም ? ስል የተነሳሁት ።
ስለዚህ ከሰፊው የግጥሟ መልዕክት ጭለፉና እናንተም ሀሳባችሁን ወዲህ በሉልኝ)
@getem
@getem
@paappii
#.......በሚካኤል አስጨናቂ ...
.
ዘፈን ሀጥያት ነው ... አዝማሪ ነው ፈረስ
እሱን ሲሳፈሩ ... ገሀነም ነው የሚያደርስ
ሲሉሽ ሰባኪዎች...
የቃሉ አርበኞች ...
.
ህይወት ተናገሩ
ለፍቅር ዘምሩ ... ጥላቻን አርቁ
ከተኛችሁበት ... ነግቷልና ንቁ
የሚል ዘፈን አለ ...ደስ የሚል ሙዚቃ
እናም እኔና አንቺ
አርቲስቱ እንዳለው ጥላቻውን ሽረን
ለፍቅር እንንቃ!
.
ስሚ እስቲ ዜማውን
መርምሪው ግጥሙን
.
ዘፋኙ ምናለ?
ከምን ጥበብ ዋለ ?
.
"አንዳንዶች በእርድና ያወቁ መስሏቸው
ፀብን ይፈጥራሉ ንቃችሁ ተዋቸው
ፈተናና ናት ህይወት በሂደቷ ሁሉ
ስንቶች ነው ወድቀው ተሰናክለው ያሉ?
ህመም ክንዱ ሲያይል ሲበዛ ስቃዩ
ወደ ፈጣሪ ዘንድ ትጉና ፀልዩ !"
.
ብሎ አልተናገረም ?
ለስንቱ ሀኪም ሆኖ መንፈስ አላከመም ?
.
እስቲ ጠይቂያቸው
እንዴት ነው በያቸው ?
የሚመክር ትውልድ ለሀገር ዘምሮ
ፍቅርን የሚሰብክ ጥዑም ዜማ ፈጥሮ
ሞትን የሚያወርሱት ዘፋኝ ነው ብለው
ምን ባለ ስሌት ነው ሲኦል የሚዶለው?
.
ግድ የለም ጠይቂ
ግድ የለም መርምሪ
ቃሉን በደፈናው በግርድፉ ፈተሽ
ፅንፍ ይዘሽ አትቅሪ ።
.
ይመስጠር ይሄ ቃል ... ተገልጦ መጥሀፉ
አሜን አሜን ብለው
ስንቶች ነው ከእውነት ... ቀዬ ዘንድ የጠፉ?
.
እስቲ ቀርበሻቸው ...
እንዴት ነው በያቸው?
"ዘፈን ሀጥያት ነው ...
የዘፋኝ መንገዱ ... የሲኦል በራፍ ነው
መዳረሻው ሁሉ ...ፅልመት ጨለማ ነው"
ብለው ለሚተቹት የእምነት መምህራን
ፀልዩ የሚል አርቲስት
ምን ባለ መንገድ ነው ለሞት የሚመራን ?
ብለሽ ጠይቂያቸው...
👇
(በነገራችን ላይ ይሄ ሀሳብ ዘወትር በአዕምሮዬ ጓዳ ይመላለሳል። እናም የዴመን ማርሌን Speak life የተሰኘ ሙዚቃ ሳጣጥም ነው ይሄን ሀሳብ ለምን ወደ ግጥም ቀይሬ ሌሎችንስ አላማራምርም ? ስል የተነሳሁት ።
ስለዚህ ከሰፊው የግጥሟ መልዕክት ጭለፉና እናንተም ሀሳባችሁን ወዲህ በሉልኝ)
@getem
@getem
@paappii
#.......በሚካኤል አስጨናቂ ...
#ህይወት ተናገሩ !
.
ዘፈን ሀጥያት ነው ... አዝማሪ ነው ፈረስ
እሱን ሲሳፈሩ ... ገሀነም ነው የሚያደርስ
ሲሉሽ ሰባኪዎች...
የቃሉ አርበኞች ...
.
ህይወት ተናገሩ
ለፍቅር ዘምሩ ... ጥላቻን አርቁ
ከተኛችሁበት ... ነግቷልና ንቁ
የሚል ዘፈን አለ ...ደስ የሚል ሙዚቃ
እናም እኔና አንቺ
አርቲስቱ እንዳለው ጥላቻውን ሽረን
ለፍቅር እንንቃ!
.
ስሚ እስቲ ዜማውን
መርምሪው ግጥሙን
.
ዘፋኙ ምናለ?
ከምን ጥበብ ዋለ ?
.
"አንዳንዶች በእርድና ያወቁ መስሏቸው
ፀብን ይፈጥራሉ ንቃችሁ ተዋቸው
ፈተናና ናት ህይወት በሂደቷ ሁሉ
ስንቶች ነው ወድቀው ተሰናክለው ያሉ?
ህመም ክንዱ ሲያይል ሲበዛ ስቃዩ
ወደ ፈጣሪ ዘንድ ትጉና ፀልዩ !"
.
ብሎ አልተናገረም ?
ለስንቱ ሀኪም ሆኖ መንፈስ አላከመም ?
.
እስቲ ጠይቂያቸው
እንዴት ነው በያቸው ?
የሚመክር ዘፋኝ ለሀገር ዘምሮ
ፍቅርን ለሚሰብክ ጥዑም ዜማ ፈጥሮ
ሞትን የሚያወርሱት አዝማሪ ነው ብለው
ምን ባለ ስሌት ነው
እንዲህ ያለው አፅናኝ ... ሲኦል የሚዶለው?
.
ግድ የለም ጠይቂ
ግድ የለም መርምሪ
ቃሉን በደፈናው በግርድፉ ፈተሽ
ፅንፍ ይዘሽ አትቅሪ ።
.
ይመስጠር ይሄ ቃል ... ተገልጦ መጥሀፉ
የሰሙትን ሁሉ ... አምነው እየፃፉ
አሜን አሜን ብለው
ስንቶች ነው ከእውነት ... ቀዬ ዘንድ የጠፉ?
.
እስቲ ቀርበሻቸው ...
እንዴት ነው በያቸው?
"ዘፈን ሀጥያት ነው ...
የዘፋኝ መንገዱ ... የሲኦል በራፍ ነው
መዳረሻው ሁሉ ...ፅልመት ጨለማ ነው"
ብለው ለሚተቹት የእምነት መምህራን
ፀልዩ የሚል አርቲስት
ምን ባለ መንገድ ነው ለሞት የሚመራን ? :)
ብለሽ ጠይቂያቸው...
///
.......ሚካኤል አስጨናቂ ...
@getem
@getem
@paappii
.
ዘፈን ሀጥያት ነው ... አዝማሪ ነው ፈረስ
እሱን ሲሳፈሩ ... ገሀነም ነው የሚያደርስ
ሲሉሽ ሰባኪዎች...
የቃሉ አርበኞች ...
.
ህይወት ተናገሩ
ለፍቅር ዘምሩ ... ጥላቻን አርቁ
ከተኛችሁበት ... ነግቷልና ንቁ
የሚል ዘፈን አለ ...ደስ የሚል ሙዚቃ
እናም እኔና አንቺ
አርቲስቱ እንዳለው ጥላቻውን ሽረን
ለፍቅር እንንቃ!
.
ስሚ እስቲ ዜማውን
መርምሪው ግጥሙን
.
ዘፋኙ ምናለ?
ከምን ጥበብ ዋለ ?
.
"አንዳንዶች በእርድና ያወቁ መስሏቸው
ፀብን ይፈጥራሉ ንቃችሁ ተዋቸው
ፈተናና ናት ህይወት በሂደቷ ሁሉ
ስንቶች ነው ወድቀው ተሰናክለው ያሉ?
ህመም ክንዱ ሲያይል ሲበዛ ስቃዩ
ወደ ፈጣሪ ዘንድ ትጉና ፀልዩ !"
.
ብሎ አልተናገረም ?
ለስንቱ ሀኪም ሆኖ መንፈስ አላከመም ?
.
እስቲ ጠይቂያቸው
እንዴት ነው በያቸው ?
የሚመክር ዘፋኝ ለሀገር ዘምሮ
ፍቅርን ለሚሰብክ ጥዑም ዜማ ፈጥሮ
ሞትን የሚያወርሱት አዝማሪ ነው ብለው
ምን ባለ ስሌት ነው
እንዲህ ያለው አፅናኝ ... ሲኦል የሚዶለው?
.
ግድ የለም ጠይቂ
ግድ የለም መርምሪ
ቃሉን በደፈናው በግርድፉ ፈተሽ
ፅንፍ ይዘሽ አትቅሪ ።
.
ይመስጠር ይሄ ቃል ... ተገልጦ መጥሀፉ
የሰሙትን ሁሉ ... አምነው እየፃፉ
አሜን አሜን ብለው
ስንቶች ነው ከእውነት ... ቀዬ ዘንድ የጠፉ?
.
እስቲ ቀርበሻቸው ...
እንዴት ነው በያቸው?
"ዘፈን ሀጥያት ነው ...
የዘፋኝ መንገዱ ... የሲኦል በራፍ ነው
መዳረሻው ሁሉ ...ፅልመት ጨለማ ነው"
ብለው ለሚተቹት የእምነት መምህራን
ፀልዩ የሚል አርቲስት
ምን ባለ መንገድ ነው ለሞት የሚመራን ? :)
ብለሽ ጠይቂያቸው...
///
.......ሚካኤል አስጨናቂ ...
@getem
@getem
@paappii
👍1
ኤሊና ጥንቸል ተቀጣጠሩ
ማራቶን ሩጫ ሊወዳደሩ።
የውድድሩ ሲያበቃ ሩጫ
እስቲ ገምቱ የማነው ዋንጫ?
— አዝማሪው —
በብላቴና ዕድሜዬ ስለ ህይወት ሲቀኙልኝ
ኤሊም ሆኜ እንድ'ቀድም
ጥንቸሎቼን አስተኙልኝ
መኖር መልካም ቀና ጥበብ የምትሻ
አሁን ባይገባንም
ትርጉም አይታጣም በስተ'መጨረሻ
፩
አየሽ በዚህ ተረት መኖር እንዲህ ይቀኛል
ሸክም ያልከው ዛጎል ጌጥህ ነው ይለኛል
አልችልም ካልክበት
አበቃ ካልክበት
ደሞ በአዲስ ፈና መንገድህን ቀጥል
የናቁት ጠጠር ነው ግዙፉን የሚጥል
ያቅተኛል ብለህ
ይከብደኛል ብለህ
በፍጹም አትፍራ።
ነበልባል ህልምህን
በእንቅልፋም ልቧች ላይ
ጎጆ አድርገህ ስራ።
ልቦናው የበራለት ከትልም ይማራል
ባሪያ ብለው የናቁት በጊዜው ይከብራል
አትፍራ! ግድየለም!
ሰጋር እግሩን አይተህ
❛❛አልቀድመውም አትበል❜❜
የኑሮን ውርርድ ሳትታክት ተቀበል
#ህይወት ጥበበኛው
መልካም ቅኔ አያጣም
ላሸነፈው ዋንጫ
ለደከመው ደሞ እንቅልፍ አይታጣም።
የአብስራ ሳሙኤል
@getem
@getem
@getem
ማራቶን ሩጫ ሊወዳደሩ።
የውድድሩ ሲያበቃ ሩጫ
እስቲ ገምቱ የማነው ዋንጫ?
— አዝማሪው —
በብላቴና ዕድሜዬ ስለ ህይወት ሲቀኙልኝ
ኤሊም ሆኜ እንድ'ቀድም
ጥንቸሎቼን አስተኙልኝ
መኖር መልካም ቀና ጥበብ የምትሻ
አሁን ባይገባንም
ትርጉም አይታጣም በስተ'መጨረሻ
፩
አየሽ በዚህ ተረት መኖር እንዲህ ይቀኛል
ሸክም ያልከው ዛጎል ጌጥህ ነው ይለኛል
አልችልም ካልክበት
አበቃ ካልክበት
ደሞ በአዲስ ፈና መንገድህን ቀጥል
የናቁት ጠጠር ነው ግዙፉን የሚጥል
ያቅተኛል ብለህ
ይከብደኛል ብለህ
በፍጹም አትፍራ።
ነበልባል ህልምህን
በእንቅልፋም ልቧች ላይ
ጎጆ አድርገህ ስራ።
ልቦናው የበራለት ከትልም ይማራል
ባሪያ ብለው የናቁት በጊዜው ይከብራል
አትፍራ! ግድየለም!
ሰጋር እግሩን አይተህ
❛❛አልቀድመውም አትበል❜❜
የኑሮን ውርርድ ሳትታክት ተቀበል
#ህይወት ጥበበኛው
መልካም ቅኔ አያጣም
ላሸነፈው ዋንጫ
ለደከመው ደሞ እንቅልፍ አይታጣም።
የአብስራ ሳሙኤል
@getem
@getem
@getem
❤35👍6🔥3