ግጥም ብቻ 📘
67.7K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
መንገደኛው ልቤ ቅጽበት'ዓት ከአንቺ ያደረ 
መሄድ አመል ሆኖበት ደሞ ሌላ አፈቀረ 
ደሞ ከሌላ አደረ አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ 
‧˚‧༘ 
ቀን ያሻገረኝ ዛጎሌን ጥዬ 
ሁሉም እንዳንቺ አይደለም ብዬ 
ነፍሴን ላጽናናት ወይ ልደልላት 
ናፍቆት ትዝታው ይበቃል ስላት   
༄ 
ተቀበለቺኝ 
❛❛ይሁና አለቺኝ❜❜ 
በል ሂድ እንግዲ... 
⸻ 
#ከአዲስ መስክ ላይ
ልዬ የሆነ ብስራት አይጠፋም 
ከንፎ መሰበር ሮጦ መውደቅ 
ህልምን ከመስበር ፍጹም አይከፋም 
 
ደሞ ወደ አዲስ ጠረን 
ደሞ ወደ አዲስ ገላ 
ይሁን ብላ ህይወት ስታባብለኝ 
⸻•⸻
ይኀው ደሞ ትዝ አለኝ 
ተሳሰረብኝ እግሬ 
በአንቺም ጊዜ አኮብኩቧል 
ክንፎቹን ልክ እንደ ዛሬ 
💧 
ትዝ አለሽ ያኔ? 
በሀዘን በእንባ የተማጸንኩሽ 
የበደሌ ስር ቅሉ ሳይገባኝ 
ይቅርታ ያልኩሽ 
🕯 
ገፍተሽ መሄድሽ 
ብቻዬን ስሆን ዛሬም ያመኛል 
አንዴ የቆሰለ ማደሪያስ
ቢያገኝ መች አምኖ ይተኛል? 
 
ግና ፍቅሬ... 
ቢሆንም ባይሆንም 
ክንፋም ህልሞች እንጂ 
ጨለማ አልለምንም 
ትሏ ህይወቴ
በጀንበር ብስራት ክንፍ ያበቀለ 
☾ 
ሁሉም እንዳንቺ አይደለም ያለ 
ደሞ ሌላ አፈቀረ 
አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ 
𓇢 
አንድ አይኑን ለመንገድ ገልጦ 
ከሌላ ልቡ ውስጥ አደረ...


የአብስራ ሳሙኤል

@getem
@getem
@getem
13👍11😱1