ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
መጽሀፈ ሰአታት

💠 "ሰዓሊ ለነ ሰንበት ክርስቲያን ቅድስት፣ ለውለደ ሰብእ መድኃኒት፣ ወእስከ ለዓለም ሰፋኒት"
💠 " ለሰው ልጆች መድኃኒት የሆንሽ እስከ ዘላለም ገዢ የሆንሽ የክርስቲያን ሰንበት ሆይ ለምኝልን (አማልጅን)
/ሰዓሊ ለነ ከሚባል ክፍል -- ገጽ 30/

▶️ የመጽሀፉ ደራሲ #ሰንበተ #ክርስቲያን የሚለው #ዕለተ #እሁድን እንደሆነ ከተለመደው አባባል ማወቅ ይቻላል። #እሑድን በተመለከተ በግእዙ ሐዲስ ኪዳን <<ወበእሑድ ሰንበት መጽአት ማርያም መግደላዊት>> የሚባል ንባብ ይገኛል(ዩሐ 20፥1)። በአማርኛው ግን <<ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን ማርያም መግደላዊት ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች>> ይላል። ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን የሚለው በግሪኩ <<μιᾷτῶν σαββάτων/ሚያ ቶን ሳባቶን/>> የሚለው ቃል ሲሆን ትርጉሙም ያው <ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን> የሚል ነው። በግእዙ <<ወበእሑድ ሰንበት>> የሚለው ንባብ ግን በግሪኩ ስለሌለ #የትርጉም #ስህተት መሆኑ ግልጽ ነው። እንዲሁም በሌላ ቦታ <<ወበዕለተ እሑድ እንዘ ጉቡኣን ንሕነ ከመ ንባርክ ማዕደ>>/ሐዋ 20፥7/ ይላል፤ ይህም በአማርኛው << #ከሳምንቱ #በመጀመሪያው ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን..>> ተብሎ #የተተረጎመ ሲሆን በዚህኛውም ሆነ በፊተኛው ምንባብ ያለው #የግሪኩ ቃል እሁድ ሰንበት እንደሆነች የማያሳይ በመሆኑ "እለተ እሑድ" <<ሰንበት>> እንደሆነች የማያሳይ በመሆኑ "እለተ እሁድ" <<ሰንበት>> እንደሆነች የሚናገረው የግእዝ ንባብ #የትርጉም #ስህተት የወለደው መሆኑን እንገነዘባለን። ለብሉይ ኪዳን #ህዝብ #እግዚአብሔር #ዕረፍተ #ስጋ እንድትሆናቸው #ዕለተ #ሰንበትን ሰጥቷቸው ነበር፤ ይሁንና #ሰንበት #በጥላነት #ክርስቶስን ታመለክት ነበር፤ ይህንንም መጽሀፍ ቅዱስ ሲያስረዳ <<እንግዲህ #በመብል ወይም #በመጠጥ ወይም ስለ #በዓል ወይም ስለ #ወር መባቻ ወይም ስለ #ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ፤ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች #ጥላ ናቸውና #አካሉ ግን #የክርስቶስ ነው>> ይላል/ቆላ 2፤ 16-17/። ስለሆነም <በአዲስ ኪዳን> #ሰንበተ #ክርስቲያን #ኢየሱስ #ክርስቶስ ነው እንጂ #ዕለተ #እሑድ አይደለችም።
ከዚህም ጋር ደግሞ << ንዑ ኅቤየ ኲልክሙ ስሩሐን ወጽዑራን ወአነ አአርፈክሙ ማለትም እናንተ ደካሞች #ሸክማችሁ #የከበደ ሁሉ ወደኔ ኑ እኔም #አሳርፋችኋለሁ>>/ማቴ 11፥29/ የሚለውን ማስተዋል ያስፈልጋል፤ ይህንን በመረዳት አንዲት #የማትሰማና #ሕያዊት ያልሆነች #የጊዜ #ክፍልፋይ ዕለተ #እሁድን #ሰንበት ብሎ ማክበርን ትቶ <አማናዊውን ሰንበት> #ክርስቶስን ማክበርና #በእርሱም #ማረፍ ይገባል።
እጅግ #የሚያሳዝነው ደግሞ ዕለቷ <<ለውሉደ ሰብእ መድኃኒት ወእስከ ለዓለም ሰፋኒት>> <<ለሰው ልጆች #መድኃኒት ለዘላለዓም #ገዥ የሆንሽ>> መባሏ ነው። #የኑፋቄውን ክፋት ለመረዳት ለዚህች #ዕለት የተሰጡትንና #መድኃኒት#ገዥ የሚሉትን #ቃላት እንመርምር።