ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
1ኛ ጢሞቲዎስ 2፥5 "አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም #መካከል ያለው #መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው #የሆነ #ክርስቶስ #ኢየሱስ ነው፤" #የክርስቶስ ሰው የመሆን ምክንያት በዚህ መልእክት በሚገባ ሰፍሯል። በአዳም #በደል ምክንያት #ከእግዚአብሄር ፊት የራቀው #የአዳም ዘር ዳግመኛ #የእግዚአብሄርን #ፊት ለማየት የሚያስችል #ንጽህና ያልነበረው በመሆኑ፣…


ዕብራውያን 5፤ 7-10

<< እርሱም #በስጋው #ወራት #ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ #ጩኸትና #ከእንባ ጋር ጸሎትንና #ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።>>

አንዳንዶች ይህን #ጥቅስ አንስተው #ክርስቶስ #ከእኔ #ተማሩ ያለ #መምህር በመሆኑ #ለአብነት ብሎ ነው ቢሉም፣ #ሐዋርያው ግን #ምሳሌ ሆነ ሳይሆን <<እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት>> ነው የሚለው።

#ሐዋርያው #በሥጋው #ወራት የተቀበለው #መከራም #በሥጋ መሆኑ #ይታወቅ ዘንድ #ጌታችን #ጸሎትና #ምልጃን #ከእንባ ጋር አቀረበ አለ /1ኛ ጴጥ 4፥1/። ይህንን የተናገረው #ሐዋርያው #ጌታችን #መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሲል #መከራ መቀበሉን፣ የተቀበለው #መከራም #እውነት መሆኑን #ለማረጋገጥና #መከራው #መሪር(መራራ) መሆኑን ለማሳየት ይህንን ተናገረ። #ብርቱ #ጩኸት #ዕንባና #ጸሎት የሚለው ቃል #የመከራውን #ክብደት #ለማሳየት የተናገረው ቃል ነው። #ግኖስቲኮች እንደሚሉት #ሥቃዩ #የማስመሰል አካሉም ምትሐት አይደለም። #በእውነት #በሥጋ #ተሠቃይቶ ዐዘነ፣ ጸለየ።
📖/፤ ታደለ ፈንታው (ዲያቆን) (ትርጉም)፣ የዕብራውያን ትርጓሜ (2004) ገጽ 87።
ይህም #በሉቃስ #ወንጌል #ምዕራፍ 22፥44 ላይ ከሰፈረው ጋር ያላቸውን #ተግባቦት ለማስተዋል ይረዳል።
#እውነቱን ላለመቀበል (ለመቃወም) #መጽሐፍ #ቅዱስ ላይ ያሉትን ቃላት እስከ #መለወጥ ድረስ የተጓዙት አንዳንዶች ይህንንም #ጥቅስ #አሜን ብለው ለመቀበል #ዐመፀኛው #ልባቸው #ፈቃደኛ አልሆነምና << #ጌታችንና #መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ በሥጋው ወራት የፈጸመውን #ከቤዛነት (ከአስታራቂነት) ሥራው አንዱ የሆነውን #ምልጃን ይዘን አሁንም #በልዕልናው ያለውን #አምላክ #አማላጅ ማለት ተገቢ አይደለም>> ይላሉ።
📖/፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምእመናን የቅዱስ እስጢፋኖስ ጉባኤ፣ <ፍኖተ ብርሃን> (ጥቅምት 1990) ገጽ 16።

ይህ ሐሳብ ግን #ክርስቶስ #በሥጋው #ወራት ሳለ #በልዕልናው አልነበረም የሚል ይመስላል። እርሱ #ሰው #ከመሆኑም በፊት፣ #ሰው ሆኖም በአገልግሎት በነበረበት ጊዜም ሆነ ፣ #ከዕረገት #ቡኃላ #ከልዕልናው አልጎደለም። ስለዚህ #በአገልግሎት ዘመኑም #ፍጹም #ሰው #ፍጹም #አምላክ ሆኖ ከሆነ ሲያማልድ የነበረው አሁንም ያማልዳል ለማለት ምን ይከለክላል?? እርሱ ሰው ከመሆኑም በፊት #አምላክ ነበር ሰው በሆነም ጊዜ #አምላክ ነበር <አሁንም ፍጹም #ሰው ፍጹም #አምላክ> ነውና።

በአንድምታ ትርጓሜው ላይ፤
<<የሰውነት ሥራ በሠራበት ወራት ጸሎትን እንደ ላም፤ ስኢልን(ልመናን) እንደ በግ፤ አድርጎ አቀረበ። በፍጹም ኅዘን። በብዙ ዕንባ አቀረበ። የልቡና ነውና፤ ግዳጅ ይፈጽማልና፤ አንድ ጊዜ ነውና፤ በዐቢይ ገዐር ወአንብዕ(በብርቱ ጩኸትና እንባ) አለ። ከሞት ሊያድነው ወደሚቻለው ወደ አብ አቀረበ። የምእመናንን ድኅነት ለራሱ አድርጎ ኅበ ዘይክል አድኅኖቶ እሞት (ከሞት ሊያድነው ወደሚችል) አለ። አንድም ምእመናንን ከሞት ሊያድንለት ወደሚቻለው ወደ አብ አቀረበ። ቁርጥ ልመናውንም ሰማው።
📖/፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡና ትርጓሜው (አ.አ፣ ግንቦት 1988) ገጽ 425።
📖/፤ መሐሪ ትርፌ (ሊቀ ሊቃውንት)፣ የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነትርጓሜው (አ.አ፤ ጥቅምት 23 1948) ገጽ 632።

በሚል የሰፈረውን #ክርስቶስ #ስለ #ሰው ልጆች መከራ በተቀበለበት ሰዓት ወደ #አብ እንዴት #ይጸልይ እንደ ነበር መመልከት ይቻላል። ታዲያ በዚህ #ሰዓት #አምላክ አልነበረም ማለት ነው? እርሱስ #ፍጹም #አምላክ ነበር።

#እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል/ዩሀ 8፥32/

ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat @teeod
▶️ በኢትዮጽያ #የማርያም #ስዕል አመጣጥ #የረጅም ጊዜ #ታሪክ ባይኖረውም #በአጼ #ዳዊት #ዘመነ #መንግስት [በ1365-1395 ዓ.ም] <<ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጽያ ወንጌላዊ ሉቃስ የሳላት የማርያም ስዕል መጣች>> በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ #የሥዕል #በር ተከፈተ[8]።

▶️ በ14ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ #የአፄ ዘርዓ ያቆብ ቤተሰቦች #የፊተኛው ልጃቸው ስለሞተባቸው ገና #ሳይወለድ እያለ <<ተወልዶ በጤና ካደገ ለቅድስት ድንግል ማርያም እሰጠዋለው>> ብለው #በስእሉ ፊት ያልተለመደ #ጸሎትና #ስለት አቀረቡ[9]። ይህንንም #ስለት አይነት በተደጋጋሚ ሲሰማ ያደገው #ዘረዓ ያዕቆብ #ስልጣኑን {አፄነቱን} ሲረከብ #ስእሎችን #በከፍተኛ ሁኔታ #እንዲስፋፉና #እንዲሰገድላቸው #የማርያም #ስእልም [ስእለ አድህኖ] ተብሎ እንዲሰየም አደረገ። በዚህም 2ተኛው #ቆስጠንጢኖስ እንዲባል አስችሎታል[10]።

▶️ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ #በሙዚየም በኢትዮጵያ ስላሉ #ስነ ስዕላት አስመልክቶ የሚከተለውን አስፍሯል።

<<በሰሌዳ ላይ (በእንጨት በጨርቅ በብራናና በመሳሰሉት) የመሳል ጥበብ በኢትዮጵያ የተጀመረው በ15ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ እንደሆነ ይገመታል ከዚህ ዘመን በፊት የተሳሉ አንዳንድ የሰሌዳ ላይ ስዕሎች እስካሁን ድረስ አልተገኙም። የታሪክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት {ስዕላተ አስህኖ} ድንገት ብቅ ያሉት በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ [1434 እ.አ.አ] ዘመን እንደሆነና ይህም የሆነበት ምክንያት ንጉሱ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ከነበረው ልዩ እምነትና ፍቅር ጋር የተያያዘ ነው ይላሉ። ከዚህም የተነሳ በኢትዮጵያ ውስጥ "የስእላተ አድህኖ" ምስሎችን ማክበር በእርሱ መታመንና የስዕላቱ ተፈላጊነት እያደገ የመጣው ከእሱ ዘመነ መንግስት ወዲህ ነው። . . . የዘመኑ ዝነኛና ታዋቂ ሰዓሊ አባ ፍሬ ፅዮን የሚባል መነኩሴ ነበር። የእሱ ልዩና ፈር ቀዳጅ ስልት በዘመኑ የኢትዮጵያ የስነ ስዕል ጥበብ ላይ በእጅጉ ተጽኖ አድርጓል። በ15ኛው ክፍለ ዘመን 2ኛ አጋማሽ በአማራው ሃገር እና በሸዋ የተሳሉ ብዙ የሰሌዳ ስዕሎች ላይ እና በዚያ ዘመን በተሰሩ መስቀሎች ላይ የእሱ ስልት በእጅጉ ተንጻባርቆ ይገኛል።>>

▶️ ሥዕላት የተስፋፉት #ከውጪ ዓለም በተለይም #ከኢየሩሳሌምና #ከካይሮ እንዲሁም #በጣሊያን ሃገር ከምትገኘው #ከቪኒስ እና ከሌሎች #ከተሞች ጋር በተመሰረቱት ግንኙነቶች አማካኝነት ነው። ከእነዚህም በተጨማሪ #የኢትዮጽያ #ሰዓሊዎች #የቤዛንታይን #አሳሳል #ስልትንም በማጥናት የራሳቸውን #አዳዲስ #ስልቶች አዳበሩ።

<<ኢታሎ-ክሬታን>> የሚባለው #ስልተ አሳሳል ደግሞ #የእሬታ #ሰዓሊዎች #የቢዛንታይን #ስልት በመጠቀም #የኢጣልያንም #የስዕላተ #አድህኖ ይዘት #በስዕል የገለጹበት ነው። #ብራንካሎዮን የተባለው ታዋቂው #የቪኒስ #ሰዓሊ ኢትዮጵያ ውስጥ #ለ40 ዓመት በኖረበት ጊዜ #የ15ኛው ክፍለ ዘመን #የኢትዮጵያ አሳሳል #ሂደት እና #እድገት ላይ #ታላቅ #አስተዋጽኦ አድርጓል። በኢትዮጵያም ውስጥ #የጣሊያን #የአሳሳልን #ስልት ያስገባው ይኸው #ሰዓሊ ነው። በዚህ #ጣሊያናዊ #ሰዓሊ የተከናወኑት #ስዕሎች #የካትሮችንቶ አሳሳል ጥበቡን #ባህሪያት #ያንፀባርቃሉ

. . . በኢትዮጵያ #የስዕል ጥበብ ላይ ሌላኛው #የውጭ #አስተዋጽኦ የመጣው #በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ 30 #ዓመታት ወደ #ኢትዮጵያ ከገቡት #ኢየሱሳውያን {ጆስዊታስ}[11] አማካኝነት ነው።

▶️ በኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረው #ባህላዊ #የእመቤታችን #ስዕለ #አድህኖ አሳሳል በተጨማሪ <<የማጆ ወሬ ማርያም>> {በሮማ ከተማ ውስጥ የምትገኝ ቤተክርስቲያን} #አሳሳል #ስልት ገባ። ዋነኛው #የጣሊያን #ስዕል ለብዙ #ምዕተ አመታት #ሮማ #ከተማ ይቀመጥ ነበር። #በ1596 እ.ኤ.አ #ኢየሱሳውያን #የሮማውን #ሊቀጳጳሳት በማስፈቀድ #የዋንኛውን #ቅጅ #ስዕሎች በመላው #ዓለም ሊሰብኩ ወደሄዱባቸው #አገሮች ሁሉ ወሰዱ። በዚህ መሰረት #ኢትዮጵያ ውስጥ #ገባ። ከዚያን ጊዜ ወዲህ #የማጆሬዋ #ማርያም #ስዕል <<ምስለ ፍቅር ወልዳ>> ተሰኝቶና #በማርያም ተሰይሞ #በኢትዮጵያ #ጥናትና #ምርምር #ተቋም ከሚገኙት #ስዕላተ #አድህኖ ውስጥ አብዛኛውን ይኸው <<ምስለ ፍቅር ወልዳ>> የተባለው ነው።
@gedlatnadersanat