ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
🔆 የማርያም የዘር ሃረግ 🔆

(የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ- 3:)
...............

23፤ " ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር እንደመሰላቸው #የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ #የኤሊ ልጅ፥".......
.........................................

32፤ " የዳዊት ልጅ፥ የእሴይ ልጅ፥ የኢዮቤድ ልጅ፥ የቦዔዝ ልጅ፥ የሰልሞን ልጅ፥"....................
...........................................

36፤ የቃይንም ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜህ ልጅ፥

37፤ የማቱሳላ ልጅ፥ የሄኖክ ልጅ፥ የያሬድ ልጅ፥

38፤ የመላልኤል ልጅ፥ የቃይናን ልጅ፥ የሄኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ[10]።

▶️ የማቲዎስ የዘር ሃረግ ገለጻ
" #ከአብርሃም በመነሳት ወደ ፊት ወደ #ኢየሱስ ሲቀጥል " #የሉቃስ ግን #ከኢየሱስ ጀምሮ ወደ ኋላ ወደ #አዳም ይጓዛል።
#ማቲዎስ #የኢየሱስ ህጋዊ አሳዳጊ #አባት የነበረውን #የዮሴፍን #የዘር ሀረግ ሲሰጠን #ሉቃስ #የእናቱን #የማርያምን #የዘር #ሐረግ ይሰጠናል።

በሉቃስ 3-23
"ኢየሱስ አገልግሎቱን በጀመረበት ወቅት ዕድሜው 30 ዓመት ያክል ነበረ ይህም ኢየሱስ #የዮሴፍ ልጅ መሰላቸው እንጂ #የኤሊ...(የማርያም ዘር ማንዘር) ልጅ ነበር" ተብሎ ተገልጾአል።
ምንም እንኳ #ማቴዎስ 4 #ሴቶችን በዘር ሀረግ ዝርዝር ቢጠቅስም/ማቲ 1-3 ፣ 5 ፣ 16/ #ሴቶች #በህጋዊ #የዘር #ሐረግ ውስጥ ስለማይገቡ #ማርያም ራሷ ሳትጠቀስ #ከአባቷ #ከኤሊ ጀምሮ እስከ #ዘር #ማንዘሮቿ #አዳም ድረስ ተገልጾአል[11]።

ይህም #ኤሊ #የዮሴፍ #አባት መሆኑን እንደ ሉቃስ አጻጻፍ #ከተወሰደ ዮሴፍ #የያዕቆብ ልጅ እንደሆነ #ማቴዎስም በግልጽ #አስቀምጧልና #ዮሴፍ #የኤሊም #የያዕቆብም ልጅ ወይም #የሁለቱ #ውህድ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም 1 ሰው 2 #አባት የለውምና።
ይህ ከሆነ ደግሞ #በአዋልድ #መጽሀፍት
<< ጰጥሪቃና ቴክታ የማርያም ስምንተኛ ቅድመ አያት ዝርያዎች፤ ነጭ ጥጃ ከማህጸን ስትወጣ ያች ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲህ እያለ እስከ 7ኛ ትውልድ ድረስ 7ኛይቱም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃም ፀሐይን ስትወልድ አይቻለሁ ብትል ቴክታ ህልም ፈችዎችን ጠርቶ ጨረቃይቱ ማርያም ናት ፅሐይ ግን አልተገለጠልኝም ቢላቸውና ቴክታ ሄኤሜን፤ ሄሜን ዴርዴም ፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ #ሃናን#ሃናም #ማርያምን ወለደች፡ #ሃና በባሏ #በኢያቄም እጅ በትር እንደተያዘች ያች በትር አብባና አፍርታ እንዳየቻት #ኢያቄምም #በሀና እጅ ከፍሬው ሁሉ የሚመስለው የሌላ የሚጣፍጥ መልካም ፍሬ ተይዛ እንዳየች እርሷም ልጃቸው #ማርያም እንደነበረች የሚገልጸው አፈ ታሪክ #ከቁርዓን ተኮርጆ #በነገረ #ማርያም የተጻፈ #ተረት ሆኖ #ይቀራል ማለት ነው[12]።>>

ስለዚህም እንዲህ የሚያደርጉትን #ከተጻፈው #አትለፍ የሚለውን #መመሪያ #እንዲያነቡና #እንዲተገብሩ እናሳስባለን።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
____________
[1] 📚፤ ንቡር ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ፤ <ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት> (3ተኛ መጽሀፍ፥ ቼምበር ማተሚያ ቤት አ.አ፤ *ገጽ 264-267፤ 1998 ዓም።

📚፤ አማረ አፈለ ብሻው፤
<ኢትዮጽያ የሰው ዘር የተገኘባት የእምነትና የስልጣኔ ምንጭ ናት>
*ገጽ 116-122፥ አ.አ ጥር 1996 ዓ.ም

📚፤ አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ <ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው የተዋህዶ አንበሣም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው> (2ተኛ እትም ግንቦት 2001 ዓ.ም)

[2] 📚፤ በርሰ ሊቃነጳጳሳት ዩሐንስ ዳግማዊ ይፋ ካደረጉት ከዋናው የላቲን መጽሀፍ የተተረጎመ <የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ> *ገጽ 145፥ 1997 ዓ.ም።

[3] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ተአምረ ኢየሱስ፤ ምዕራፍ 3(፫)፤ 10(፲) ፤ *ገጽ 16(፲፮)፥ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1994 ዓ.ም።

[4] 📚፤ ድርሳነ ኪዳን ለማርያም ሳልስ፤ *ገጽ 48 1978 ዓ.ም።

[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም፤ የዘውትር መቅድም (*ገጽ 4(፬)፤ 16(፲፮) 1989 ዓ.ም።

[6] 📚፤ ደቀመዝሙር መልአኩ ዘድሜጥሮስ። <ስንዴውን ለመስዋት እንክርዳዱን ለእሳት> አ.አ. ሰኔ 1998፤ *ገጽ 21።

[7] 📚፤ <ድርሳነ ጽዮን ዘሐሙስ> 44-13 *ገጽ 158። አ.አ. ኅዳር 1998 ዓ.ም።

[8] 📚፤ ወንጌል ቅዱስ፤ ዘማቲዎስ ወንጌል፤ ንባቡና ትርጓሜው በግእዝና በአማርኛ፤ 1፡ 16። *ገጽ 52። 1997 ዓ.ም።
[9] 📚፤ ሃይማኖተ አበው፤ ቃል ግዝት ኤጲስቆጶስ፤ ክፍል 6 ፤ *ገጽ 577 1986 ዓ.ም።

[10] 📚፤ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ፤ <ለጌታ የተገዛህ ሁን> ፧ የማቴዎስ ወንጌል; ትርጉም ግርማዌ፤ *ገጽ 9፤ S.A.M፥ ኤስ ኤይ ኤም ማተሚያ ቤት አ.አ፤ 1995 ዓ.ም

[11] 📚፤ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ፤ <ሩህሩህ ሁን፥ የሉቃስ ወንጌል ትርጉም ፤ *ገጽ 31-32፤ S.A.M፥ ኤስ ኤይ ኤም ማተሚያ ቤት አ.አ፤ 1996 ዓ.ም

📚፤ ቄስ ኮሊን ማንሰል፤ <ትምህርተ እግዚአብሔር> ፩ኛ መጽሐፍ፤ *ገጽ 80፥ ንግድ ማተሚያ ድርጅት አ.አ፥ 1995።

[12] 📚፤ ተአምረ ማርያም 2፤ 8-9 3ተኛ እትም *ገጽ 17፥ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት። አ.አ 1989 ዓ.ም

📚፤ ያዕቆብ ሰንደቁ <እናታችን ጽዮን> 3ተኛ እትም *ገጽ 7-12። አ.አ፥ 1997 ዓ.ም።

📚፤ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ 5፥38። *ገጽ 111። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ 1983 ዓ.ም።

📚፤ ቅዱስ ቁርአን ሱረቱ አል-ኢምራ 3፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።

(1.2▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat