#ከወደቁ_አይቀር_ለጽዮን !
አንዳንድ ውድቀቶች ካለ አስፍላጊ አቋቋሞች በእጅጉ የተሻሉ ናቸው ። ለምሳሌ ከሐውልቱ
እንደምናየው ለጽዮን መውደቅ በእውነቱ ዋጋ ያለውና የተሻለ አወዳደቅ ነው::
# ይህ በመጠኑና በውበቱ ከፍ ያለው ሃውልት አሁን ሳይወድቅ ቆሞ ካለውና በቅርቡ ከሮም
ከመጣው ዕድሜ ይሁን በሰው ሀገር ያለ ቦታው መቆሙ የሞራል መላሸቅ ያስከተለበት
የሚመስለሁ እንደ አዛውንት ጎብጦ በመደገፊያ በግድ ከቆመው ሐውልት በተለየ መልኩ
በፊት ለፊቱ ወድቆ ይታያል::
ይህ የአክሱም ሐውልት ከመሐመድ ግራኝ ወራራ በወላ የተነሳችው ሴቷ ግራኝ ዮዲት
ጉዲት ካስከተለችው ጥፋቶች መካከል የጥፉቷን ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የሆነ ታሪካዊ
የሀገር ቅርስ ነው :: ዮዲት በክርስቲያንኖችና በቤተክርስቲያን ላይ ባደረባት የተሳሳት ጥላቻ
ኃያሌ የጭካኔ ተግባራትን በክርስቲያኖችና በቤተክርስቲያን ላይ ያስከተለች የታሪክ ጠባሳ
ነች ::
# ከበዙ ጥፉቶች በኃላ ወደ እዚህ ወደ አክሱም ሐውልት መቆሚያ አካባቢ ስትደርስም
ጭፍሮቿ እንደለመዱት የእክሱምን ሐውልቶች ይጥሏቸውና ይሰባብሯቸው ዘንድ ተራኮቱ
ዮዲትም ሁሉንም ሐውልቶች አትጣሏቸው አንዱንና ትልቁን ለዐይንም የሚማርከውን
ሐውልት ብቻ ጣሉት ሌሎቹን ግን እንዳትነኩ ስትል ትዕዛዝ አስተላለፈች ጭፍሮቿም
ለምን? ሲሉ ጠየቁ
በሌሎች ቦታዎች እዳደረግን ሁሉንም ብንሰባብርና ብናወድማቸው መጪው ትውልድ
ሲያቸው አንድ ጊዜ ተበሳጭቶ ብስጭቱን ይተወዋል የሚያምረውን ና ተለቅ የሚለውን
ሐውልት ብቻ ብንጥለውና ሌላው ብንተውለት ግን ባየውና በሰማው ቁጥር ይህ ትልቁኮ
ባይወድቅ ከነዚኞቹ በላይ ውብ የሀገር ቅርስ ሆኖ ይታይ ነበር እያለ ዘላለም ዓለሙን
እየተቃጠለ ሲብሰለሰል ይኖራል ገባችሁ! ስትልም አምቧረቀችባቸው:: እነርሱም የክፋት
ጥግ መሆኗን በሆዳቸው እየታዘቡ፣ እየተገረሙም ሐውልቱን ጣሉት።
# ሐውልቱ ግን ለትውልዱ ቁጭት ሳይሆን ትምህር ይሆን ዘንድ ወደ ጽዮን ወደቀ
ተንበርከኮም ሰገደላት ። የጌታዬ እናት በፊትሽ እቆም ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እያለም
ተሳለማት ። ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ ልብ ያለውም ልብ ያድርግ "በፈሊጥ ካልገባው
በፍልጥ " እንዲሉ ሰው ሁለት ጊዜ ይማራል ይላሉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን አንድ በሣር
" ሀ " ብሎ ካልሆነም በአሳር " ዋ "ብሎ ። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ብራና ዳምጠው
ቀለም በጥብጠው በሣር ስግደት እንደሚገባት ሲያስተምሩን ካልገባን በአሳር ጎንበስ
ማለታችን አይቀርምና ከአሳሩ በፊት በሳሩ ተማሩ እንላለን።
“ # የአስጨናቂዎችሽም_ልጆች_አንገታቸውን_ደፍተው_ወደ_አንቺ_ይመጣሉ ፥ የናቁሽም
ሁሉ # ወደ_እግርሽ_ጫማ ይሰግዳሉ፤ # የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል
# ቅዱስ_የሆንሽ_ጽዮን ይሉሻል።”
# ኢሳ 60፥14
ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ኅዳር 21/2013ዓ.ም
የተከተበ

" #ደስታ_ተክለ_ሃይማኖት ተወለደ"
#የሚገቡት
እንኳን ማርያም ማረችሽ ፣
አሜን!
እንኳን ማርያም ሁለት አረገችሽ
አሜን!
#የሚወጡት
ማርያም ጭንሽን ታሙቀው
አሜን!
ማርያም በሽልም ታውጣሽ.......ይሏታል
የእመጫቷ መልስ አሜን !አሜን! የሚል ብቻ ነው። ይህ የእግዚእኃረያ ቤት ነው። ባሏ ፀጋ ዘአብ ደስታውን መቋቋም አቅቶታል ቤቷ በወዳጆቻቸው እና በጠያቂዎቻቸው እንዲሁም ባለ መውለዳቸው እንደ ኃጢያተኛ ቆጥሮ ይጠቋቆሙባቸው በነበሩ ሰዎች ተጨናንቃለች መካን ሚስቱ ወንድ ልጅን ወልዳለችና ። ለሁሉም እንደ ማዕረጋቸው ምሳ አደረጉላቸው ማጋረጃ ገልጠው እናቲቱንና ልጇን ቅቤ እስኪቀቡ የቸኮሉ ሳይኖሩ አይቀሩም ሌላው ግን ስለ አወላለዷ ለመረዳት ሰሀናቸውን ይዘው የወላዲቱ አልጋ አጠገብ ጠጋ ብለው የተቀመጡም አልጠፋም ።
#እርሷም_የእግዚአብሔርን ቸርነት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት እየመሰከረች ከሞተለሚ ምርኮ እንዴት ባለ ተአምር እደዳነች እያወራች ከባሏ ከፀጋ ዘአብም ጋርም ወንድ ልጅ ስለ መውለዷ አስቀድመው ዕራይን እንዳዮ እየነገረቻቸው ቀኑን በደስታ አሳለፈች ደስታ የሆነ ልጅ ወልዳለችና ።
*ስሙንስ ማን አላችሁት ?
ፍስሐ ጽዮን ( የጽዮን ደስታዋ) ብለነዋል ። ነገር ግን መላእኩ እንደነገረን ስሙ ሌላ ነው ከእናንተም የተሰወረ በልበ ሥላሴ የተጻፈ አዲስ ስም ይወጣለታል ብሎናል። "ተክለ ሃይማኖት"! ሕጻናት እንደሚያለቅሱም አያለቅስም ነበር "ቅኖች ሰዎች ሁል ጊዜ ደስ ይላቸዋል" እንደሚል
"ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለእራስህ አዘጋጀህ " አንደተባለም ሕጻኑ ፍስሐ ጽዮን በተወለደ ገና በሦስተኛው ቀን ከእናቱ እቅፍ ወርዶ "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ ሥላሴን በአንድነት በሦስትነት አመስግነ:: መዝ 9÷2
#ልጆች_የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው የእግዚአብሔር ስጦታ ሁሉ ደግሞ ደስ ያሰኛል ። ይልቁኑ እግዚአብሔር በእነርሱ አድሮ ድንቅ ሥራውን ይሰራባቸው ዘንድ ያዘጋጃቸው የቅዱሳን ሰዎች ልደታቸው ብቻ ሳይሆን እነርሱ እራሳቸው ደስታ ናቸው :: " በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ተድላና ደስታም ይሆንልሃል" ዮሐ1፥14 ተብሎ እንደተጻፈ እውነት ነው በመወለዱ ብዙዎች ደስ ብሎናል በሉቃስ ወንጌል ላይ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል በመጥምቀ መለኮት በቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ እንደሚሰኙ አስረግጦ ነግሮናል።
እነሆ ዛሬ ደግሞ እንደ ዮሐንስ በድንግልና የኖረ እንደ መጥምቁ ካህን ያውም ሰማያዊ የሆነ እንደ አዋጅ ነጋሪው በምድረ ኢትየጵያን ሁሉ እየዞረ ወንጌልን የሰበከ ለእናትና ለአባቱ እንዲሁም ለብዝዎቻችን የደስታ ምንጭ የሆነ የጽዮን ደስታዋ የተባለ ፍስሐ ጽዮን ተወለደ እነሆ እኛም እንደ ተስፋው ቃል ዳግማዊው ዮሐንስ ተወልዶልናልና ደስ አለን::
#መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰለሞን" ጻድቃን በበዙ ቁጥር ሕዝብ ደስ ይለዋል" እንዳለ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በተወለዱ ሰዓት ክርስቲያኖች ደስ ብሏቸዋል ምክንያቱም ጻድቁ ሕሙማነ ነፍስን በትምህርታቸው ሕሙማነ ሥጋን በተአምራታቸው እያዳኑና እየፈወሱ ለሕዝብ ደስታ ምንጭ ሆነዋል ያን ጊዜ ብቻም ሳይሆን ዛሬም በአፀደ ነፍስ ሳሉ ለኛ ለክርስቲያኖች የደስታችን ምንጭ ናቸው " የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለችና " ስለኛ የጽድቅ ሕይወት የሰላም እጦት የሃይማኖት ጉለት የምግባር ዝቅጠት ዕለት ዕለት ወደ ፈጣሪ እየጸለዮ ያማልዱናልና ነው #ያዕቆ 5÷16
በጻድቃን መወለድ ሕዝብ ደስ የሚለው በተወለዱበት ዘመን እና ወር ብቻ አይደለም አንዴ ጻድቃን ከተወለዱ በኃላ ሕዝብ ለዘለአለሙ ደስ ይለዋል ጻድቃን በአፀደ ሥጋም በአፀደ ነፍስም በምልጃቸው ደስ ያሰኛሉና ..... .. ልክ እንደዛሬው......
" #እኔ ግን ለዘለዓለሙ ደስ ይለኛል
ለያዕቆብ( #ለተክለ_ሃይማኖት )
አምላክም ዝማሬን አቀርባለው" #መዝ76÷9
...........ይቆየን........
የጻድቁ አባታችን የተክለ ሃይማኖት እረድኤትና በረከት በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በሕዝበ ክርስቲያኖች ላይ ሁሉ ለዘለዓለሙ ቀንቶ ይኑር ....!!!
ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ታህሳስ 22/2013ዓ/ም

“ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ"
#መዝ ፯ {፰} ፥፪
#ማቴ፳ ፩ ፥ ፲ ፮
ይህች ቀን #አባታችን_ቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት በተወለዱ በሦስተኛ ቀናቸው ከእናታቸው
ከእግዚኅረያ ዕቅፍ ወርደው ሥላሴን በአንድነት፤ በሦስትነት ያመሰገኑበት ቀን ነው። ቀኑ "
#ከሰተ_አፍሁ "በመባልም በኢቲሳ ተክለ ሃይማኖት በድምቀት ይከበራል። ቅዱሱ የገድል
መጻሕፋቸውም እንዲህ ተርኮልን እናነባለን።
#ይህውም_እግዚአብሔር የመረጠው ልጅ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ይህችም
የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው መታሰቢያ በምትሆን በታወቀች ቀን በዕለተ
ሰንበት (እሁድ) ከመዓልቱ (ከቀኑ) በ፫ ሰዓት ይህ ብላቴና እጁን አንስቶ ወደ ሰማይ
ተመልክቶ ጮሆ ተናገረ።
#እግዚአብሔርንም እንዲህ ብሎ አመሰገነ።
#ከወልድ_ከመንፈስ_ቅዱስ_ጋር_በባህሪ_በሕልውና_አንድ_የሚሆን_አብ_በአካል_በስም_ልዮ_ነው ፤
#ከአብ_ከመንፈስ_ቅዱስ_ጋር_በባህሪ_በሕልውና_አንድ_የሚሆን_ወልድ_በአካል_በስም_ልዮ_ነው፤
#ከአብ_ከወልድ_ጋር_በባህሪ_በሕልውና_አንድ_የሚሆ_መንፈስ_ቅዱስ_በአካል_በስም_ልዮ_ነው ።
በሦስት ሰዓት በቅዳሴ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወደ ወደደው ይወርዳልና ሕጻኑም መንፈስ
ቅዱስ ሲወርድ አይቶ ይህን ሦስት ምስጋና አቀረበ።
#እናቱም ከተመረጠ ልጇ ይህን ጽኑ ነገር ሰምታ በልቦናዋ አደነቀች "ልጄ ፍስሐ ጽዮን ምን
ትላለህ ?" አለችው። "........ ይህ ቃል የአባትህ ነው ላንተ ግን የሚገባህ ጡት መጥባት
ነው" ብላ ጡቷን አጎረሰችው።
ባሏ ጸጋ ዘአብ ቤተ መቅደስ የሚያጥንበትን ጊዜ ጨርሶ ሲመጣ ልጇ የተናገረውን ሁሉ
ነገረችሁ ጸጋ ዘአብም ነገሩን ሰምቶ አደነቀ ልጁንም ታቅፎ አንስቶ እየሳመ ልጄ
#እግዚአብሔር ያሳድግህ ብዙ ዘመን ያኑርህ እንዲህ እያልክ በቤተ እግዚአብሔር
ስትቀድስ ዓይህ ዘንድ እመኛለሁና"
#ገድለ ተክለ ሃይማኖት
ምዕራፍ ፲ ፭ ፥ ከቁጥር ፱ እስከ ፳፬
የ፲ ፱ ፻ ፹፱ ዓ.ም ፬ ተኛው ዕትም
ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ታኅሣሥ ፳ ፮ /፪ሺ፻-፲ ፫ዓ.ም

"የባሕርይ ገዥ ክርስቶስ ከዕለት ከሰዓት አስቀድሞ የነበረ ሲሆን የሰዎችን ልደት ዛሬ ተወለደ።" ሃይማኖተ አበው
የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የሐዋርያት ደቀ መዝሙር የነበረ አጢፎስ በሃይማኖተ አበው ላይ የልደትን ነገር በተናገረበት ድርሳኑ ይህን መሰከረ።
ክርስቶስን የባሕርይ ገዥ ጌታ አለው። ሌሎች ገዥ ቢባሉ በጸጋ በስጦታ፤ ሌሎች ጌታ ቢባሉ የምድር፤ ሌሎች ገዥ ቢባሉ በጊዜ የሚገደብ፤ በዘመን የሚወሰን ነው። ለእርሱ ግን ጌትነትን የሚሰጠው ሰጪ አልያም የሚወስድበት ወሳጅ የሌለበት የባሕርይ ገንዘቡ ነውና የባሕርይ ገዢ አለው። ዮሐ 13:13
ከዕለትና ከሰዓት አስቀድሞ ነበርም አለው። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመናት የማያረጅ እንዲሁም በጊዜ የማይወሰን ከ ብሎ መጀመርያ እስከ ብሎ መጨረሻ የሌለው ቀዳማዊ ድኃራዊ ነውና ከዕለት ከሰዓት አስቀድሞ የነበረ ብሎ መሰከረ። ዮሐ 1:1 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቱ ቀዳማዊነቱን ሲናገር "በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት አስቀድሞ #በኩር ነው። ሁሉ በእርሱ ለእርሱ ተፈጥረዋል።" ብሎ የዘመናት ፈጣሪ ከዘመን አስቀድሞ የነበረ አምላክ መሆኑን መሰከረ። ቆላ 1:15 ጌታ በወንጌል ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር የነበረ መሆኑን ሲናገር እንዲህ አለ። "አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።" ዮሐ 17:5
ይህ የባሕርይ ገዥ ከዕለት ከዓመት ከዘመናት አስቀድሞ የነበረ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የሰዎችን ልደት ዛሬ ተወለደ ተባለ። እንዴት የሚደንቅ እንዴትስ የሚረቅ ምሥጢር ነው???
ሥጋ ያልነበረ በመለኮቱ ጥንት ያልነበረው እርሱ ጥንት ያለውን ሥጋ ስለምን ተዋሐደ? አይታይ የነበረው አምላክ የሚታይ ሥጋን ተዋሕዶ ስለምን ታየ? ስለምንስ ተዳሰሰ? በባሕርይው የማይወሰንና ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነ አምላክ ስለምን በድንግል ማኅጸን አደረ? የማይሰጡት ቸር የማያበድሩት ባለጠጋ ሲሆን ስለምን በከብቶች በረት ተጣለ? ሰማይን በደመና የሚሸፍን በከዋክብት የሚያስጌጥ እርሱ ስለምን በጨርቅ ተጠቀለለ? ለዚህ ሁሉ መልሱ ሰው ወዳጅ የሆነ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ፍጹም ቢያፈቅረው አይደለምን? ሰው ሰውን ቢወድ ነቅ ፈልጎ ምክንያት አበጅቶ ነው። እግዚአብሔር ግን ሰውን የወደደው እንዴት ነው ቢሉ እንዲሁ ያለምክንያት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነው። እንደውም መወደድ የሚገባን ሆነን ሳለን እንኳን አይደለም። ስንጠላው ወደደን ስናምጽና ስንርቀው ቀረበን ስንበትን ሰበሰን ጠላቶቹ ሳለን ነፍሱን ስለኛ ቤዛ ሰጥቶ ታረቀን። ዮሐ 3:16 ሮሜ 5:10 የነገሥታት ንጉስ በትሕትና ከሰማይ ከመንበሩ ወርዶ ፍቅሩን ከገለጸልን እኛማ ምን ያህል ልንዋረድ ምን ያህልስ ልንዋደድ ይገባል?
ይቆየን።
መልካም የልደት በዓል ይሁንልን።
ወልደ ተክለሃይማኖት ታኅሳስ 29 2013 ዓ.ም
👉 @AwediMeherit

❝ወይከውነከ ትፍሥሕተ ወኃሴተ ወብዙኃን ይትፌሥሑ ... በልደቱ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።❞
—ሉቃስ 1: 14
ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው ማን ነው ቢሉ ? መጋቢ ሐዲስ የተባለ ቅዱስ ገብርኤል ነው ። ለማን ተናገረው ቢሉ ስለ ዮሐንስ መወለድ ለካህኑ ዘካርያስ ባበሰረበት ሰዓት ተናግሮታል።
በእውነት ጥምቀቱ መንግስተ ሰማያት የማታስገባ ከዕዳ ደብዳቤ ነጻ የማታወጣ መጥምቀ መለኮት በመወለዱ ብዙዎችን ደስ ካሳኘ በመወለዱ ብዙዎች
መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለበት ቅዱሱ አምላክ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን የሚያድል እርሱ መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክ በዳዊት ከተማ በመወለዱ እንዴት ደስ ይሰኙ ይሆን!
በክርስቶስ ልደት በብሉይ ኪዳን ብዙ ሊሆኑ የማይታሰቡ ነገሮች ሆነዋል ። ሰው እና መላዕክት በአንድነት ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማይ ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብ ብለው በአንድነት አመሰግነዋል።
ተጣልተው የነበሩ ሰው እና መላዕክት ፣ ሰማይ እና ምድር ፣ ብርሃን እና ጨለማ ከዋክብት እና ፀሃይ በአንድነት ታርቀው ለፈጣሪያቸው ምስጋናን አቅርበዋል። ምክንያቱም በፈጣርያቸው በክርስቶስ ልደት የጥል ግርግዳ ፈርሷል እና! ማንነታቸው ታድሶ አዲስ ፍጥረት ሆነዋል እና። ❝ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።❞
—2ኛ ቆሮ 5: 17
የአምላክ ሰው መሆን እንዴት ያለ ትዕትና ነው ! ሰማይ ዙፋኑ ምድርም የእግር መረገጫው የሆነው ፈጣሬ ዓለማት በምድር በቤተልሔም ግርግም መወሰኑ እንዴት ያለ ልዕልናን በትዕትና መግለጥ ነው። እንዴት ያለ በሰው አእምሮ መርምረው ሊደርሱበት የማይችሉት ጥልቅ ነው ። በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል !
የፈጠረውን ሥጋ ካንዲት ከአስራ አምስት ዓመት ብላቴና መንሳት እንዴት ያለ ድንቅ ነው ። እኔስ አበው እንዳመሰገኑህ እንዲህ እያልኩ አመሰግንሃለው። ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻልህ መጠን አድርገህላት ነው ፤ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማ ያልተቃጠለችው ኃይልህን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው።
❝ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።❞
—ኢሳይያስ 9: 6
ጌታችን ሆይ በአንተ መወለድ ዓለም አጥቶት የነበረውን ሰላም አግኝቷል ።
የአገራችንን መከፍፈል ... ፍቅር የጠፋበትን የሰዎችን ልቡና ፍቅርህን እና አንድነትህን ላክልን ።
መልካም የልደት በዓል !
አዘጋጅ :-ዲያቆን ኢንጅነር እስጢፋኖስ ደሳለኝ
👇👇👇👇
@Yotor24
@Yotor24
ታህሳስ 2013
አዲስ አበባ - ኢትዮጲያ
#ዓውደ_ምሕረት_የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇

ፆመ ገሃድ ምንድነው?
ጾመ ገሃድ
ይህ ጾም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ
የጥምቀት ዋዜማ የሚፆም ፆም ነው፡፡ ይህም ማለት በጥምቀት ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው፡፡ የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነም የጥምቀትን ድራር መጾም ነው፡፡ ሐዋርያት
«ልደት ጥምቀት ዓርብ ረቡዕ ቢውል በሌሊት ቀድሰው ሥጋውን ደሙን ይቀበሉ፤ ከሌሊቱ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጹሙ ብለው አይፍረዱ» ብለዋል /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/፡፡ የልደትና
የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ሃምሳ የሚበላውን የጥሉላት ምግብ በጠዋት በመብላት ምእመናን በዓሉን እንዲያከብሩ ታዟል፡፡
ይህም እነዚህ ሁለቱ ታላላቅ የእግዚአብሔር በዓላት
በመሆናቸው ነው፡፡ የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማክሰኞንና ሐሙስን
በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል፡፡ በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ሥራ ይከናወናል፡፡ የጥምቀትን ዋዜማ ጥሉላት መባልዕትን መተው ነው፡፡ ይህንንም እንደ ዘይቤው ገሀድ ይለዋል፣ መገለጫ፣ ግልጥ፣ ይፋ መሆን ማለት ነው፡፡
እንዲሁም ጋድ ይለዋል፣ ለውጥ፣ ልዋጭ ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ረቡዕ ዓርብ ሲውል በዚያ ለውጥ ማክሰኞ ሐሙስ ይጾማልና ጋድ አለው፡፡ እንዲሁም አንድ ጊዜ ሲጾም አንድ ጊዜ ሲቀር
እንዳይረሳና ቅዳሜ ወይም እሑድ በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ አይቻልም፣ ነገር ግን እህል ውኃ እንጂ ጥሉላት ከመብላት መጠበቅ ይገባል፡፡
ልደት የሚውልባቸው ረቡዕና ዓርብ ቢሆኑ የፍሥክ /
የሚበላባቸው/ ቀናት ሆነው እንዲከበሩ ሐዋርያት ያዘዙ ቢሆንም በዋዜማው የሚገኙት ማክሰኞና ሐሙስ ከጾመ ነቢያት ጋር የተያያዙ ስለሆኑ መጾማቸው ግድ ነው፡፡ ሆኖም የነቢያትን ጾም
የማይጾሙ ሰዎች በመላው የጾሙ ቀናት ሲበሉ ቆይተው
በዋዜማው ብቻ ገሀድ ነው ብለው ይጾማሉ፡፡ ነገር ግን ይሄ ትክክል አይደለም። ጾሙ የጥምቀት ብቻ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ አባቶቻችን በፆም በጸሎት በረከት እንዳገኙ እኛም ከእግዚአብሔር በረከት እናገኛለን እና መፆምን ቸል አንበል ለዚህም አምላካችን ይርዳን አሜን፡
ነገ 10/05/2013 ገሀድ ነው እንዳንረሳ .. መልካም በዓል
@AwediMeherit

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሰን።
ነገረ ጥምቀት
ወአሜሃ መጽአ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ እም ገሊላ ውስተ ዮርዳኖስ ከመ ይጠመቅ እም ዮሐንስ ... ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።
ለጌታ ሠላሳ ሲሞላው ለዮሐንስ መንፈቅ ሲተርፈው (ሠላሳ ዓመት ከስድስት ወር በኃላ) ያን ጊዜ ጌታ በዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።
እስቲ እንጠይቅ?
ማን ወደ ማን ነበር መሔድ የነበረበት? ዮሐንስ ወደ ጌታ ወይስ ጌታ ወደ ዮሐንስ? እርግጥ ፈጣሪ ወደ ፍጡሩ መሔዱ የመጣው ለትዕትና እንጂ ለልዕልና አለመሆኑን ሲያጠይቅ ነው። እንዴት ያለ ትዕትና ነው!
አንድም ስርዓትን ሲሰራ ነው። እንዴት ያለ ስርዓት ቢሉ ማንም ተጠማቂ ወደ ካህናት መሔድ እንዳለበት ሲያጠይቅ ወደ ዮሐንስ ሄዶ ተጠመቀ።
ለምን በዮርዳኖስ ተጠመቀ ቢሉ?
1. ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ
• ❝ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።❞ መዝሙር 114: 3
• ❝አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ፥ምን ሆናችኋል?❞ መዝሙር 114: 5
2. ምሳሌነቱ ይፈጸም ዘንድ
• ዮርዳኖስ ነቁ አንድ ነው በኃላም በደሴቱ ይከፈላል መልሶ ከታች መልሶ ይገናኛል ።
ምሳሌነቱ ፡- ከላይ ነቁ (መነሻው) አንድ መሆኑ የሰው ዘር ሁሉ በአዳም አንድ መሆኑን ሲሆን በኃላም በደሴት መለያየቱ አንድ የነበረው የሰው ልጅ ደሴት በተባለ ኃጥያት መከፋፈሉ አንድም ህዝበ እስራኤል እና አህዛብ ተብሎ መለያየቱ ፣ ወርዶ አንድ መሆኑ በጥምቀተ ክርስቶስ ህዝብ እና አህዛብ አንድ መሆናቸውን ያሳየናል።
ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።
እናቱ ኤልሳቤጥ ድንግል ወደ እርሷ በመጣች ጊዜ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል ያለው በማዕጸን እያለ ሰምቶ ነበር እና እርሱም አምላኩን ወደ እርሱ መምጣቱ ተመልክቶ ይህ ነገር እንዴት ይሆንልኛል ብሎ የጌታውን አምላክነት መሰከረ !
ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት። ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።
ማቴ 3 ፡ 13-17
ጌታ ለምን ተጠመቀ?
1. በጥምቀቱ ድኅነተ ሰጋ ድኅነተ ነብስን ሊሰጠን
• ማርቆስ 16: 16 ❝ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።❞
2. ዳግም ልደትን ለእኛ ሊሰጠን
• ዮሐንስ 3: 3 ❝ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።❞
• ቲቶ 3፡4 ❞ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም❞
3. ለኃጥያታችን የስርየት መንገድ ሲሰራልን
• ሐዋርያት ስራ 22: 16 ❝አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ።❞
በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ እንደሆንን እንዲሁ መለያየታችንን ክርስቶስ በፍቅር አንድ ያድርገን ።
መምህር ዲ/ን ኢ/ር እስጢፋኖስ ደሳለኝ
👇👇👇👇
👉@Yotor24
@Yotor24
ጥር 11 2013 ዓ.ም
አ.አ / ኢትዮጲያ
#ዓውደ_ምህረት_የእናንተ
👇👇👇👇👇👇

✞ቻይ ሆይ ታገስ✞
ስትታገስ የምታተርፈው እንጂ የምታጣው አንዳችም ነገር አይኖርም ለጊዜው በጽኑ ብትፈተንም በለሷን በመታገስ ጠብቀሃታልና ፍሬዋን ትበላለህ ይህች ፍሬ ግን እንደዘበት አትገኝም ታለፋለች ታደክማለች ካወቅባት ለምትሄደው መንገድ ርስት ብሎም ስንቅ ትሆንሃለች ካሰብክበት ካለምክበት ቦታ ታደርስሃለች ቻይ ሆይ ታገስ ! በምትሰማው ነገር በምታየው ድርጊት እንዳትሸበር ትዕግስትክ እየተሸረሸረ ተመናምኖ ይቀራልና ክርስቶስ ይህችን ግራ ይምታጋባ ዓለም በምን ያሸነፋት ይመስልሃል? በትዕግስት እኮ ነው! ሀሜቱን፣ ስድቡን፣ ዱላውን ፣መከራውን፣ረሃብ ጥሙን ታግሶ አልፎ " በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ፤ ነገር ግን አይዟችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ" ብሎ ዓለም ለምታቀርብልን ፈተና ዝግጁ እንድንሆን እርሱን ይዘን እንደምናሸንፋት ተስፋ ሰጥቶ ልበ ሙሉ እንድንሆን በር የከፈተልን። አድምጠኝማ ወዳጄ ክርስትያን በዓላማው የሚጸና ጽኑ ታጋሽ አስተውሎ ነገሮችን መርምሮ የሚናገር ሁሌም አዛኝቷ ድንግል ማርያምን ከመንገዱ አስቀድሞ የሚጓዝ ተስፈኛ .. ኸረ ምኑን ጠቅሼ ልጨርስልህ! በቃ ጠቅለል ሳደርግልሀህ አምላኩን መድኅን ዓለም ክርስቶስን በቃልም በህይወቱም የመሰለ ማለት ነው ። ስለዚህ ወዳጄ ቶሎ እንደ ጀበና የምትገነፍል ከሆነ ልምድ በልምድ ይሻራልና ትዕግስትን ተለማመዳት ከዛ ሳታውቀው እንደ ቀሚስ ከአካልህ አጥልቀሃት እንደ መቀነት ትታጠቃታለህ ያኔ ትሁት ትሆናለህ ክርስቶስን ትመስላለህ በእምነት ጠንክረው እንደጸኑት አባቶች ትመስላለህ ይህን ታደርግ ዘንድ ቸሩ መድኃኔዓለም ከእናቱ ከቸሪቱ ከአማላጂቱ ከድንግል ማርያም ጋር አብሮህ ይሁን።!!!አሜን!!!
ቡሩክ መልሳቸው
ጥር 13 2013 ዓ.ም
አ.አ/ኢትዮጵያ