ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ሐዲስ_ሱራፊ_ተክለ_ሃይማኖት

#ሱራፊ ማለት መልአክ፣ ከካህናተ ሰማይ አንዱ ማለት ነው፡፡ ሱራፌን፣ ሱራፌል፣ ሱራፌም (በፅርዕ ሴራፊም፣ በዕብራይስጥ ስራፊም) ማለት የነገድ ስም፣ ልዑላን መላእክት፣ ሊቃናት፣ የሚያጥኑ፣ ካህናት፣ ቀሳውስት፣ ቀዳሾች ማለት ነው /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ/ ከዚህ ላይ ሱራፊ ነጠላ ቍጥርን ሲያመለክት፤ ሱራፌል ደግሞ ብዙ ቍጥርን ያመለክታል፡፡ ሱራፌል ለቅዱሳን በሰው አምሳል በመገለጣቸው ሽማግሌዎች ተብለው ተጠርተዋል /ኢሳ.24፥23፤ መሳ.13፥2-25፤ /፡፡ በግእዝ ቋንቋ ደግሞ ካህናተ ሰማይ ይባላሉ፡፡ ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ቁጥራቸው 24 እንደሆነ ባለ እራዮ ዮሐን ጽፎልናል ይህ ግን 24ሰዓት ያለ እረፍት የሚያመሰግኑ መሆናቸውን ለማመልከት የተጠቀመበት አገላለጽ ነው እንጂ ቁጥራቸውስ 24ብቻ ሆኖ አይደለም ።


ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ስማቸውን ጭምር በመጥቀስ ለኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ሰላምታ አቅሮቦላቸዋል። በአብ መንበር ዙሪያ ላሉ ለ24ቱ ሰማያውያን ካህናት ሰላምታ ይገባል፤ በእጆቻቸው ውስጥ ላለ ማዕጠንትም ሰላምታ ይገባል፤ በራሶቻቸው ላይ ላሉ አክሊላትም ሰላምታ ይገባል፤ አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል፣ ታድኤል፣ እፍድኤል፣ ዘራኤል፣ ኤልኤል፣ ተዳኤል፣ ዮካኤል፣ ገርድኤል፣ ልፍድኤል፣ መርዋኤል፣ ኑራኤል፣ ክስልቱኤል፣ ኡራኤል፣ ባቱኤል፣ ሩአኤል፣ ሰላትኤል፣ ጣውርኤል፣ እምኑኤል፣ ፔላልኤል፣ታልዲኤል፣ ፐስልዱኤል፣ አሌቲኤል ለተባሉ ስሞቻቸውም ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው / መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ እንደተረጎመው)

ዛሬ በዚህች መጠነኛ ጽሁፍ ኅዳር 24ቀን ከነዚህ ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ጋር ተደምሮ የሥላሴን መንበር ያጠነ አዲሱን ምድራዊ ሱራፊን ተክለ ሃይማኖት /ተክለ ኤልን /እናስተዋውቃችዋለን። ካህናተ ሰማይ ሱራፌል ከዘር የተገኙ ምድራዊያን አይደለም ተክለ ኤል ተክለ ሃይማኖት ግን ከሕግ ዘር የተገኘ ምድራዊ ሰው የሆነ ሐዲስ ሱራፊ ነው።
‹ተክል› ማለት ፍሬያማ ዕንጨት፣ ዛፍ፣ ቅመም፣ ቅጠላ ቅጠል፣፣ የሚሸተት፣ቢበሉት ጥጋብ ፣ቢያርፉበት ጥላ የሚሆን ገነታዊ ዕፅ፣ እንዲሁም ሕግ ሥርዓት ማለት ነው /ማቴ.15፥13/፡፡

"ኤል" ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ማለት ነው :: ስመ መላእክት ስመ እግዚአብሔርን ያዘሉ በመሆናቸው የሁሉም ቅዱሳን መላእክ ስም "ኤል" የሚል መቀጽል አለው ለምሳሌ ከላይ የጠቀስናቸው የሃያራቱን ካህናተ ሰማይ የሱራፌልን ስም መመልከት ይቻላል :- አካኤል፣ ፋኑኤል፣ ጋኑኤል ወ.ዘ.ተ ስለዚህ "ተክለ ኤል " ማለታችንም ይህ ሐዲስ ሱራፊ ስሙ ከስማቸው ጭምር የሚገጥም መሆኑን ለመግለጥ ነው። የእግዚአብሔር ተክል ተክለ እግዚአብሔር ማለታችን ነው :: ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ባስልዮስ ዘ ቄሳሪያ እኔስ እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው ብሎ እንደተናገረ " ተክለ ኤል" ተክለ እግዚአብሔር ሲባልም የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተክል የሚል ትርጉም ይሰጣል ።


#አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የተወለዱት በሸዋ ክፍለ ሀገር ዛሬ ኢቲሳ በመባል በሚታወቀው ከከሰም ጅረት አካባቢ ባለ ቦታ በጥንቱ ፈጠጋር ቡልጋ በደብረ ጽላልሽ አውራጃ ዞረሬ በተባለው ሥፍራ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብ (የአብ ሥጦታ) ከሚባል ካህን እና ሣራ ወይም እግዚእ ኅረያ(እግዚአብሔር የመረጣት)በመባል ከምትታወቅ ደጋግ ከሆኑ ባልና ሚስቶች በመላእክ አብሳሪነት መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ገደማ ነው።
ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጺዮን ።(የፂዮን ደስታዋ)ብለው ሰየሟቸው፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል። ይህን ጊዜ እናታቸው እግዚ ኀረያም በመገረም ሆና " ይህ ሥራ የአባት ነው ላንተ የሚገባህ ጡት መጥባት ነው" ብላ ለህጻኑ ጡቷን አጎረሰችሁ ፡፡ ይህም የህጻኑ ሁኔታ መላእካዊ ግብሩን ገና በህጻንነት የገለጠ ነበር ቀን ከለሊት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ማመስገን የመላእክት መገለጫ ነውና ኢሳ 6÷6 ። ካህኑ ፀጋ ዘአብ የወቅቱን የቤተ ክርሰቲያን አገልግሎታቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ሚስታቸው እግዚእ ኀረያ በመገረም ሆና የሦስት ቀን ልጃቸው ፍስሐ ፂዮን እንዴት ባለ ምስጋና ፈጣሪያቸውን እንዳመሰገነ ነገረቻቸው ጸጋ ዘአብም ህጻኑን ተቀብለው ታቅፈው እየሳሙ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲ እያልክ በቤተ መቅደስ ስትቀድስ ዐይህ ዘንድ እመኛለው አሉ።

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከአብሮ አደግ ጓደኞቹ ጋር በዱር ፈረስ ሲጋልብ ጦር ሲሰብቅ ተገናኝቶት ፍስሐ ጺዮን የሚለውን ስሙን በፈጣሪው ትዛዝ መሠረት ለውጦ ከእንግዲህ ወዲህ "ተክለሃይማኖት" እየተባልክ ተጠራ እንጂ ስም ፍስሐ ጺዮን አይሁን አላቸው አበው ስምን መላእክ ያወጣዋል እንዲሉ ፡፡ አያይዞም ፈረስ መጋለብ ጦር መስበቅ ቀስት መወርወር እንሰሳት ማደንን ተው ከእንግዲህ ወዲህ መስቀል ጨብጥ በወንጌል ስበክ ከአፍህ በሚወረወር በቃለ እግዚአብሔር መረብነት ሰው አድን አለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመላእኩ ክንፍ ላይ ተገልጦ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጌሃለሁ ብሎ በሐዋርያት ሾመት ሐዋርያ አድርጎ ሾመው። ጓደኞቹም ከያሉበት ተሰብስበው ወደ ተክለ ሃይማኖት ቀረቡ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ግን አላስተያይ አላቸው ስለዚህ ፊትህን ማየት አቃተን ተሸፋፈንልን ሲሉ ተማጠኑት። ሙሴ ከሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ በወረደ ጊዜ አሮንና የእስራኤል ልጆች ሁሉ ሙሴ ሆይ ከፊትህ የሚወጣው ብርሃን አላስተያይ ብሎናልና እባክህ ፊትህን ሸፍንልኝ እንዳሉት ዘጽ 34÷29_35

#ጻድቁ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው ዲቊናን፤ በ22 ዓመታቸው ደግሞ ቅስናን ከግብፃዊው ጳጳስ ከአባ ጌርሎስ ወይም (ከአባ ቄርሎስ) ዘንድ ተቀብለዋል፡፡ ሐዋርያዊ ተግባርንም በከተታ እና በፈጠጋር (በጽላልሽና በአካባቢዋ፣በዳሞት በምድረ ወላይታ፣በአምሓራና በሸዋ በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ በኣድያማተ ትግራይ፣በገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ፣በገነተ ማርያም ላስታ በደብረ ዘመዶ ማርያም ገዳም፣ በኤርትራ ገዳማት ፣በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም ወዘተ በአገሪቱ ወንጌል ባልተዳረሰበት ቦታ ሁሉ እየተዘዋወሩ በመላዋ ኢትዮጵያ ወንጌልን አስፍተዋል።
ጻድቁ አባታችን ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው፣ ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና በመኖራቸው፤ እርሳቸው በአሚነ ሥላሴ ጸንተው ሌሎችንም እንዲጸኑና እንዲያምኑ በማድረጋቸው፤ እንደዚሁም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ በመስበክ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ዛሬም በአጸደ ነፍስ ሆነው የሚፈውሱ ሐዲስ ሐዋርያ ሐዲስ ሱራፊ ናቸው።


በየ ደረሱበት ሥፍራ ሁሉ ከሥራቸው ጽናት ከተአምራታቸው ብዛት የተነሳ አንተ ሰውነህን ወይስ መላእክ ነህን ንገረን ይሏቸው ነበር። እርሳቸውም ከንቱ ውዳሴን ነፍሳቸው አጥብቃ ትጸየፈው ነበርና አባቶቼ እንደ

#ቀጣዮይ ይመልከቱ
👇👇👇👇
“ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ"
#መዝ ፯ {፰} ፥፪
#ማቴ፳ ፩ ፥ ፲ ፮
ይህች ቀን #አባታችን_ቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት በተወለዱ በሦስተኛ ቀናቸው ከእናታቸው
ከእግዚኅረያ ዕቅፍ ወርደው ሥላሴን በአንድነት፤ በሦስትነት ያመሰገኑበት ቀን ነው። ቀኑ "
#ከሰተ_አፍሁ "በመባልም በኢቲሳ ተክለ ሃይማኖት በድምቀት ይከበራል። ቅዱሱ የገድል
መጻሕፋቸውም እንዲህ ተርኮልን እናነባለን።
#ይህውም_እግዚአብሔር የመረጠው ልጅ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ይህችም
የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው መታሰቢያ በምትሆን በታወቀች ቀን በዕለተ
ሰንበት (እሁድ) ከመዓልቱ (ከቀኑ) በ፫ ሰዓት ይህ ብላቴና እጁን አንስቶ ወደ ሰማይ
ተመልክቶ ጮሆ ተናገረ።
#እግዚአብሔርንም እንዲህ ብሎ አመሰገነ።
#ከወልድ_ከመንፈስ_ቅዱስ_ጋር_በባህሪ_በሕልውና_አንድ_የሚሆን_አብ_በአካል_በስም_ልዮ_ነው
#ከአብ_ከመንፈስ_ቅዱስ_ጋር_በባህሪ_በሕልውና_አንድ_የሚሆን_ወልድ_በአካል_በስም_ልዮ_ነው
#ከአብ_ከወልድ_ጋር_በባህሪ_በሕልውና_አንድ_የሚሆ_መንፈስ_ቅዱስ_በአካል_በስም_ልዮ_ነው
በሦስት ሰዓት በቅዳሴ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወደ ወደደው ይወርዳልና ሕጻኑም መንፈስ
ቅዱስ ሲወርድ አይቶ ይህን ሦስት ምስጋና አቀረበ።
#እናቱም ከተመረጠ ልጇ ይህን ጽኑ ነገር ሰምታ በልቦናዋ አደነቀች "ልጄ ፍስሐ ጽዮን ምን
ትላለህ ?" አለችው። "........ ይህ ቃል የአባትህ ነው ላንተ ግን የሚገባህ ጡት መጥባት
ነው" ብላ ጡቷን አጎረሰችው።
ባሏ ጸጋ ዘአብ ቤተ መቅደስ የሚያጥንበትን ጊዜ ጨርሶ ሲመጣ ልጇ የተናገረውን ሁሉ
ነገረችሁ ጸጋ ዘአብም ነገሩን ሰምቶ አደነቀ ልጁንም ታቅፎ አንስቶ እየሳመ ልጄ
#እግዚአብሔር ያሳድግህ ብዙ ዘመን ያኑርህ እንዲህ እያልክ በቤተ እግዚአብሔር
ስትቀድስ ዓይህ ዘንድ እመኛለሁና"
#ገድለ ተክለ ሃይማኖት
ምዕራፍ ፲ ፭ ፥ ከቁጥር ፱ እስከ ፳፬
የ፲ ፱ ፻ ፹፱ ዓ.ም ፬ ተኛው ዕትም
ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ታኅሣሥ ፳ ፮ /፪ሺ፻-፲ ፫ዓ.ም