ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
“ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ"
#መዝ ፯ {፰} ፥፪
#ማቴ፳ ፩ ፥ ፲ ፮
ይህች ቀን #አባታችን_ቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት በተወለዱ በሦስተኛ ቀናቸው ከእናታቸው
ከእግዚኅረያ ዕቅፍ ወርደው ሥላሴን በአንድነት፤ በሦስትነት ያመሰገኑበት ቀን ነው። ቀኑ "
#ከሰተ_አፍሁ "በመባልም በኢቲሳ ተክለ ሃይማኖት በድምቀት ይከበራል። ቅዱሱ የገድል
መጻሕፋቸውም እንዲህ ተርኮልን እናነባለን።
#ይህውም_እግዚአብሔር የመረጠው ልጅ በተወለደ በሦስተኛው ቀን ይህችም
የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው መታሰቢያ በምትሆን በታወቀች ቀን በዕለተ
ሰንበት (እሁድ) ከመዓልቱ (ከቀኑ) በ፫ ሰዓት ይህ ብላቴና እጁን አንስቶ ወደ ሰማይ
ተመልክቶ ጮሆ ተናገረ።
#እግዚአብሔርንም እንዲህ ብሎ አመሰገነ።
#ከወልድ_ከመንፈስ_ቅዱስ_ጋር_በባህሪ_በሕልውና_አንድ_የሚሆን_አብ_በአካል_በስም_ልዮ_ነው
#ከአብ_ከመንፈስ_ቅዱስ_ጋር_በባህሪ_በሕልውና_አንድ_የሚሆን_ወልድ_በአካል_በስም_ልዮ_ነው
#ከአብ_ከወልድ_ጋር_በባህሪ_በሕልውና_አንድ_የሚሆ_መንፈስ_ቅዱስ_በአካል_በስም_ልዮ_ነው
በሦስት ሰዓት በቅዳሴ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወደ ወደደው ይወርዳልና ሕጻኑም መንፈስ
ቅዱስ ሲወርድ አይቶ ይህን ሦስት ምስጋና አቀረበ።
#እናቱም ከተመረጠ ልጇ ይህን ጽኑ ነገር ሰምታ በልቦናዋ አደነቀች "ልጄ ፍስሐ ጽዮን ምን
ትላለህ ?" አለችው። "........ ይህ ቃል የአባትህ ነው ላንተ ግን የሚገባህ ጡት መጥባት
ነው" ብላ ጡቷን አጎረሰችው።
ባሏ ጸጋ ዘአብ ቤተ መቅደስ የሚያጥንበትን ጊዜ ጨርሶ ሲመጣ ልጇ የተናገረውን ሁሉ
ነገረችሁ ጸጋ ዘአብም ነገሩን ሰምቶ አደነቀ ልጁንም ታቅፎ አንስቶ እየሳመ ልጄ
#እግዚአብሔር ያሳድግህ ብዙ ዘመን ያኑርህ እንዲህ እያልክ በቤተ እግዚአብሔር
ስትቀድስ ዓይህ ዘንድ እመኛለሁና"
#ገድለ ተክለ ሃይማኖት
ምዕራፍ ፲ ፭ ፥ ከቁጥር ፱ እስከ ፳፬
የ፲ ፱ ፻ ፹፱ ዓ.ም ፬ ተኛው ዕትም
ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ታኅሣሥ ፳ ፮ /፪ሺ፻-፲ ፫ዓ.ም
#ከሰተ አፍሁ !
_____
በሦስተኛውም ቀን በነ እግዚኅርያ ቤት ደስታ ነበር !
________
........ #ሁለቱም ፈሪያ እግዚአብሔር ያደረባቸው በጎ ሥራን የሚሠሩ ሰዎች ነበሩ የፀጋ ዘአብ ሚስት ሣራ ሃይማኖት ከምግባር መልክና ደም ግባት ከሙያ ጋር አሟልቷ የሰጣት ሴት ነበረች ። አማቷ የፀጋ ዘአብ አባት " ወረደ ምሕረት " የሥራዋን ደግነት አይተው " እግዚኀረያ " ብለው ስም አወጡላት ጌታ የመረጣት ማለታቸው ነው።

#በሊቀ_መላእክት_በቅዱስ_ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ፂዮን ።(የጽዮን ደስታዋ)ብለው ሰየሟቸው፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል። ይህን ጊዜ እናታቸው እግዚ ኀረያም በመገረም ሆና " ይህ ሥራ የአባት ነው ላንተ የሚገባህ ጡት መጥባት ነው" ብላ ጡቷን አጎረሰችሁ ፡፡

#ቅዱሳን_መላእክት ቀን ከሌት #ቅዱስ_ቅዱስ_ቅዱስ እያሉ ያመሰግናሉ ኢሳ 6፥÷6 ይህም የህጻኑ ሁኔታ መላእካዊ ግብሩን ገና በህጻንነት የገለጠ ሁኔታ ነበር። ካህኑ ፀጋ ዘአብ የወቅቱን የቤተ ክርሰቲያን አገልግሎታቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ሚስታቸው እግዚ ኀረያ በመገረም ሆና የሦስት ቀን ልጃቸው ፍስሐ ጽዮን እንዴት ባለ ምሥጋና ፈጣሪያቸውን እንዳመሰገነ ነገረቻቸው ጸጋ ዘአብም ሕጻኑን ተቀብለው ታቅፈው እየሳሙ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲ እያልክ በቤተ መቅደስ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለው አሉ።.....
ተክለ ኤል ከሚለው ድርሳኔ በከፊል | #የተወሰደ