ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Forwarded from እኔም ትውልድ ነኝ ብፅይት እልሻለው
ሮማዊው ወታደር።እኔ ብሆን ብሎ ማሰብ ይከብዳል ።ምክንያቱም ሮዊው ወታደር ክርስቶስ ንፁህ ሰው መሆኑን እንጂ አምላክ መሆኑን
አያውቅም።አምላክ መሆኑን ቢያውቅና ወንጌል የገባው ሰው ቢሆን ለሱ በአይሁዶች መተቸትና መጠላት ከምንም አይቆጥረውም ነበር።ስለዚ ይህ ሮማዊ ወታደር።ክርስቶስ እንደ ሰው ስላየው ነው በጦር የወጋው።እኔ ብሆን እንክዋን የሰውን ጎን በጦር ልወጋ ቀርቶ በረሮም መግደል እፈራው።ስለዚህ ይህ ወታደር እኔ ብሆን ይህንን አይሁድ በግፍ የሚሰቅሉት ሰው ንፁህ እንደሆነ ካወቅሁና ከነሱ ጋር መተባበር ካልፈለኩ ከዛ አከባቢ ለተወሰነ ቀናት እርቅ ነበር
Audio
ወቅታዊ መንፈሳዊ ውይይት
ርዕስ #ነገረ መስቀል

በወንድሞቻችን
#ቡሩክ መልሳቸው
#ተርቢኖስ ሰብስቤ
#ይዘት
👉የመስቀል ትርጉም
👉ታሪካዊ ድኃራው በብሉይና በአዲስ
👉 ለመስቀል ሊደረግ የሚገባ አክብሮት
የሴቶችን መንፈሳዊ አገልግሎት በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ያላቸውን ልዩ ክብር እና ቦታ ምን እንደሆነ ያውቃሉ?

https://youtu.be/6G_kwNz0k44
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (1ኛ ሳሙ 7:12 αβεпεζεя)
የሴቶችን መንፈሳዊ አገልግሎት በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ያላቸውን ልዩ ክብር እና ቦታ ምን እንደሆነ ያውቃሉ?

https://youtu.be/6G_kwNz0k44
" #መስቀለኛዋ አንባ "
ግሸን ማርያም ደብር በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ደብር ናት፤ ይህች ደብር በሐይቅና በመቅደላ፤በደላንታ፤ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ የሆች ስትሆን። በርዋ አንድ ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ናት፡፡ በበርዋ ከተገባ በኋላ ግቢዋ ከላይ ሜዳና መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡ በትግራይ እንደ ደብረ ዳሞ በበጌምድር እንደዙር አምባ በመንዝ እንደ አፍቅራ ናት ፡፡ ወደዚህች ደብር ለመሔድ በረሐ አቋርጦ በሸሎን በመሻገር ፫ ሰዓት መንገድ አቀበት በመውጣት አንድ ቀን ሙሉ ተጉዞ ማታ ፲፪ ሰዓት ይገባል ፡፡ግሸን ማርያም በፊት #ደብረ_እግዚአብሔር ትባል ነበር ፡፡ ይህ ደብረ እግዚአብሔር የሚለው ስያሜም በጻድቁ ንጉሥ ላሊበላ እጅ ከቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ #በእግዚአብሔር_አብ ስም ስለነበረ #ደብረ_እግዚአብሔር ተብሎ ተጠራ፡፡ ከዚያም በዓጼ ድግናዣን ዘመን መንግሥት የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት ሐይቅ ደብር ነጎድጓድ ተብሎ ሲሰየም ግሸን የሐይቅ ግዛት ስለሆነች #ከደብረ_እግዚአብሔር ደብረ ነጎድጓድ ተብላለች ፡፡
ከዚያም በ ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በዓጼ ዘርአ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የክርስቶስ ግማደ መስቀሉ ግሸን ገብቶ ሲቀመጥ ከደብረ ነጎድጓድ ደብረ ከርቤ ተብላለች የደብሩ አስተዳዳሪም መምህረ እሥራኤል ዘደብረ ከርቤ ይባል ነበር ፡፡ ከደብረ ከርቤ ተመልሳ ግሸን ማርያም ተብላለች፡፡ ይህች ግሽን የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀልኛ ቦታ ነቸና ለግማደ መስቀሉ ማረፊያ ትሆን ዘንድ ተመረጠች ፡፡
በዚያም ዘመን የነበሩት የኢትዮጵያ ጳጳሳት የነበሩት አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የተባሉ ከንጉሡ ከዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ጋር ሆነው የምህረት ቃል ኪዳን ለመቀበል በዚህች በግሸን ደብር ሱባዔገቡ ። በሱባዔአቸውም በመጨረሻ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ " ይህች ቦታ እኔ ተወልጄ ያደኩባትን ኢየሩሳሌምን ትሁን፣ የተሰቀልኩባትንም ቀራንዮን ትሁን ፣ የተቀበርኩባትንም ጎልጎታን ትሁን ። በዚች ቦታ እየመጣ የሚማፀነውን ሁሉ ቸርነቴ ትጎበኘዋለች ጠለ ምህረቴንም አይለይባትም ፤ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ መጥቶ የተቀበረ ኢየሩሳሌም እንደተቀበረ ይሆንለታል "። የሚል የምህረት ቃል ኪዳን ተገለጸላቸው። ስለዚህም ግሸን ደብረ ከርቤ ዳግሚት ኢየሩሳሌም (ሁለተኛይቱ ኢየሩሳሌም )ተብላ ትጠራለች ። አፄ ዘርያቆብም ከአባታቸው ከአፄ ዳዊት በተቀበሉ አደራ መሠረት በዚያች አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀመጧቸው ዘመኑም በ፲፬ ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው::

#ምንጭ:- መጻሕፈ ጤፉት፣
ዲ/ን መልአኩ እዘዘው ጽሁፍ

"ሰብ ይቀድስ ለመካን መካን ይቀድስ ለሰብ"
"ሰው ቦታን ይቀድሳል ቦታም ሰውን ይቀድሳል"
#መስከረም ፩ ፭/ ፳ ፻-፩ ፫ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
#ዓውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
" #አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል"
" #መስቀሌን በመስቀልያ ቦታ አስቀምጥ"
መጽሐፈ #ጤፉት

መስቀሌን በመስቀልያ ቦታ አስቀምጥ የሚለው ትዕዛዝ ለአፄ ዘር ያዕቆብ የተነገረ ቢሆንም ቅሉ ለኛ ለክርስቲያኖችም የታዘዘ ኃይለ ቃል ነው። የሰው ልጅ ቃጥ ብሎ ቆሞ እጆቹን ወደ ግራና ወደ ቀኝ ቢዘረጋ ሁነኛ የመስቀል ቅርጽ ያለው መስቀልያ ቦታ መሆኑን ይረዳ ነበር። ብዙዎች ግን በprotocol ሰበብ ለቀረጻ አይመችም !፣ ለሰርግ አይሆንም ፣ ውበት ይደብቃል እያሉ መስቀሉን ከመስቀልያ ቦታ አውርደው ጥለውታል። ቅዱስ መስቀሉ ግን "እንወደው ዘንድ ደም ግባት የለውም" ኢሳ53÷1-12 እስኪባልለት ድረስ መዳኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ደም ግባት ያለን ያደርገን ዘንድ ወዝና ደሙን ያንጠፈጠፈበት ውበታችን ነበር ። #ስለዚህ_ዛሬም "አንብሩ መስቀልየ በዲበ መስቀል" እየተባልን ነው። #መድኃኔዓለም በዕለተ ዓርብ ከቀኔ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በገዛ ሥልጣኑ ከለየ በኋላ በኋላ ከመስቀሉ አውርደው ቀበሩት ፡፡ በ፫ኛው ቀን ሲነሣ ተሰቅሎ የነበረው የእንጨት መስቀል ሌት ተቀን በሙሉ ሳያቋርጥ እንደፀሐይ ሲያበራ በተጨማሪም አጋንንት ሲያባርር ድውይ ሲፈውስ ሙት ሲያነሣ ቤተ እሥራኤል አይሁድ ቀንተው በዓዋጅ ትልቅ ጉድጓድ ቆፍረው በመቅበር የቤት ጥራጊና አመድ ጠቅላላ የቆሻሻ መከማቻ እንዲሆን ወሰኑ፡፡

ከዚያ ዘመን ጀመሮ እስከ ሦስት መቶ ዘመን ድረስ የተከማቸው ቆሻሻ እንደተራራ ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ የታላቁ ቆስጠንጢኖስ እናት እሌኒ ንግሥት የተባለች ደግ ሴት የክርስቶስን መስቀል መስከረም ፲፯ ቀን ፫፻፳ ዓ.ም. ላይ በዕጣን ጢስ ምልክት ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት ፲ ቀን አግኝታ በማውጣት ታላቅ ቤተ መቅደስ ጎልጎታ ላይ ሠርታ በክብር አስቀመጠችው ። ይህ መስቀልም ከዚያ ዘመን ጀምሮ እንደ ፀሐይ እያበራ ድውይ እየፈወሰ አጋንንት እያባረረ ልዩ ልዩ ተአምራትን እየሠራ ሙት እያነሳ ዕውር እያበራ ተአምራቱን ቀጠለ፡፡ ይህንንም ከኃያላን ነገሥታት መካከል የፋርስ ንጉሥ መስቀሉን ማርኮ ፋርስ ወስዶ አስቀመጠው። በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም ምዕመናን የሮማውን ንጉሥ ሕርቃልን ዕርዳታ በመጠየቅ እንዲመለስ አድርገው በኢየሩሳሌም ብዙ ዘመን ሲኖር እንደገና ኃያላን ነገሥታት ይህን መስቀል እኔ እወስድ እኔእወስድ እያሉ ጠብ ፈጠሩ። በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም፤የቁስጥንጥንያ፤የአንጾኪያ፤የኤፌሶን፤የአርማንያ ፤ የግሪክ ፤ የእስክንድርያ የመሳሰሉት የሃይማኖት መሪዎች ጠቡን አበረዱት ከዚህም አያይዘው በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የክርስቶስ መስቀል ከ፬ ከፍለው በዕጣ አድርገው በስምምነት ተካፍለው ከሌሎቹ ታሪካዊ ንዋያት ጋር በየሀገራቸው ወስደው በክብር አስቀመጡት፡፡ የቀኝ ክንፉ የደረሰው ለአፍሪቃ ስለነበር ከታሪካዊ ንዋያተ ቅድሳት ጋር በግብጽ የሚገኘው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጠው፡፡ ይህ ግማደ መስቀልም ለብዙ ዘመን በእስክንድርያ ሲኖር በግብጽ ያሉ እስላሞች እየበዙ ኃይላቸው እየጠነከረ ሄደ። በእስክንድርያ የሚኖሩትን ክርስቲያኖች ሥቃይ ያጸኑባቸው ጀመር ክርስቲያኖቹም አንድ ሆነው መክረው ለኢትዮጵያዊ ዓፄ ዳዊት እንዲህ የሚል መልዕክት ላኩ “ንጉሥ ሆይ! በዚህ በግብጽ ያሉ እስላሞች መከራ አጽንተውብናልና ኃይልህን አንሥተህ አስታግሥልን ብለው ጠየቁት” ። ዳግማዊ ዓፄ ዳዊትም ለመንፈሳዊ ኃይማኖት ቀንተው የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶአቸው ፳ ሽህ ሠራዊት አስከትለው ወደ ግብፅ ዘመቱ በዚህ ጊዜ በግብፅ ያሉ ኃያላን ፈሩ ተሸበሩ ንጉሡ ዳግማዊ ዳዊትም እንዲህ የሚል መልዕክት ለእስላሞች ላኩ። በተፈጥሮ ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ክርስቲያኖች ጋር ካልታረቃችሁ ሀገራችሁን መጥቼ አጠፋዋለሁ የሕይወታችሁ መሠረት የሆነውንም የዓባይን ወንዝ ገድቤ በርሃብ ነው የምፈጃችሁ የሚል ማስጠንቀቂያ ላኩ ፡፡

የንጉሡ መልዕክት ለእስላሞች እንደደረሳቸው ፈርተው እንደጥንቱ በየሃይማኖታቸው ፀንተው በሰላም እንዲኖሩ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ታረቁ፡፡መታረቃቸውን ዳግማዊ ዳዊት ሰሙ በዚህም ጉዳይ ንጉሡ በጣም ደስ አላቸው እግዚአብሔርንም አመሰገኑ የዓባይንም ወንዝ እንደ ቀድሞ ለቀቁላቸው በግብፅ የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ከ፲፪ ሺህ ወቄት ወርቅ ጋር ደስታቸውን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለዳግማዊ ዳዊት በደብዳቤ አድርገው ላኩላቸው ንጉሡም የደስታውን ደብዳቤ ተመልከተው ደስ ኣላቸው። ወርቁን ግን መልሰው በመላክ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፉ በግብፅ የምትኖሩ የክርስቶስ ተከታዮች ሆይ እንኳን ደስ አላችሁ የላካችሁልኝን ፲፪ ሺህ ወቄት ወርቅ መልሼ ልኬላችኋለሁ የእኔ ዓላማ ወርቅ ፍለጋ አይደለም። የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ በተቻለኝ ችግራችሁን ሁሉ አስወገድኩላችሁ አሁንም የምለምናችሁ በሀገሬ በኢትዮጵያ ረሀብና ቸነፈር ድርቅ ስለወረደብኝ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎበት የነበረውን መስቀልና የቅዱሳንን አፅም ከሌሎች ክቡራን ዕቃዎች ጋር እንድትልኩልኝ ነው የሚል ነበር፡፡ በእስክንድርያም ያሉ ምእመናን ይህ መልዕክት እንደደረሳቸው ከሊቃነ ጳጳሳቱና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ጋር ውይይት በማድረግ ይህ ንጉሥ ታላቅ ክርስቲያን ነው፡፡ ስለዚህ ልቡን ደስ እንዲለው የፈለገውን የጌታችንን ግማደ መስቀል ከቅዱሳን አጽምና ንዋየ ቅድሳት ጋር አሁን በመለሰው ፲፪ ወቄት ወርቅ የብርና የንሐስ የመዳብና የወርቅ ሣጥን አዘጋጅተን እንላክለት ብለው ተስማምተው በክብር በሥነ ሥርዓት በሠረገላና በግመል አስጭነው ስናር ድረስ አምጥተው አስረከቧቸው። በጊዜውም በእጃቸው እያጨበጨቡ በእግራቸው እያሸበሸቡ በግንባራቸው እየሰገዱ በክብር በደስታ ተቀበሉት ይህም የሆነው መስከረም ፳፩ ቀን ነው፡፡ በኢትዮጵያም ታለቅ ብርሃን ሌት ተቀን ፫ ቀን ሙሉ ሲበራ ሰነበተ፡፡ ነገር ግን ግማደ መስቀሉ ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ ሳይደርስ በድንገት ዓፄ ዳዊት ስናር ላይ አረፉ፡፡ ግማደ መስቀሉም የግድ በዚያው በስናር መቆየት አስፈለገው፡፡

ከዚህ በኋላ የሟቹ የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዘርአ ያዕቆብ እንደነገሡ ወደ ሥናር ሔደው ግማደ መስቀሉን ከሌሎቹ ንዋያተ ቅድሳት ጋር አምጥተው በመናገሻ ከተማቸው በደብረ ብርሃን ላይ ቤተ መቅደስ ሠርተው ለማስቀመጥ ሲደክሙ ።በሕልማቸው አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል ወዳጄ ዘርአ ያዕቆብ ሆይ መስቀሌን በመስቀልኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ የሚል ሕልም አዩ ፡፡ ንጉሡም መስቀለኛ ቦታ እየፈለጉ በኢትዮጵያ አውራጃዎች ሁሉ መስቀለኛ ቦታ በመፈለግ ከብዙ ቦታ ላይ አስቀምጠውት ነበር ። ለምሳሌ በሸዋ በደርሄ ማርያም ፤ በመናገሻ ማርያም ፤ በወጨጫ መስቀሉን አሳርፈውት ነበር፡፡ ነገር ግን የመጨረሻውን ቦታ ያላገኙ በመሆኑ በራዕይ እየደጋገገመ መስቀሌን በመስቀልኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ እያለ ይነግራቸው ነበር፡፡ዓፄ ዘርአያዕቆብም ለ፯ ቀናት ያህል ሱባዔ ገቡ በዚያም የተገለፀላቸው መስቀልኛውን ቦታ የሚመራህ ዓምድ ብርሃን ይመጣል አላቸው እርሳቸው ከዚያ እንደወጡ መስቀለኛውን ቦታ የሚመራ ዓምደ ብርሃን ከፊታቸው መጥቶ ቆመ በዚያ መሪነት ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ ውስጥ ግሸን ከምትባል መርቶ አደረሳቸው ፡፡ ይህች ግሽን የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀልኛ ቦታ ሁና ስለአገኟት የልባቸው ስለደረሰ ደስ አላቸው ፡፡ በዚያችም አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀመጧቸው ዘመኑም በ፲፬ ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ በመጀመሪያም ይህ ግማደ መስቀል ከእስክንድርያ ስናር የገባው መ
ስከረም ፲ ቀን ነው ወደ ኢትዮጵያም የገባው በመስከረም ፳፩ ቀን ነው፡፡ አሁንም በመጨረሻ ግሸን አምባ የገባው መስከረም ፳፩ ቀን ሲሆን ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ቅዳሴ ቤቱ አከበሩ። አፄ ዘርዓያዕቆብ ከግማደ መስቀሉ በተጨማሪ በተቆለፈ ሳጥን የተቀበሉትን ቅዱሳን ነዋያት በፅሑፍ በመዘርዘር ለመላው ኢትዮጵያዊያን መስከረም ፳፩ ቀን ገለጡላቸው፡፡

በነቢዮ በዳዊት ቃል“ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።” ተብሎ የተነገረው ትንቢት ዳግም በኛ በኢትዮጵያውያን ስለተፈጸመ ሁል ጊዜ በመስቀሉ ደስ ይለናል ከጠላት ቀስት ሁሉ እናመልጥበታለንእና መዝ60፥4።
............ ይቆየን ..........
ከእፀ መሰቀሉ እረድኤትና በረከት ያድለን ......አሜን!

#መስከረም ፩፭/ ፳፻-፩፫ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE

#ዓውደ ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Watch "ሌላ ትምክህት ከኔ ይራቅ ሳምንታዊ የቀጥታ መርኃ ግብር" on YouTube
https://youtu.be/68GpUB5EQ_o
የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ.mp3
7.2 MB
#ስብከተ ወንጌል

አስተማሪ :- #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ :- #ወንድማችን ቡሩክ መልሳቸው!

ርዕስ:- #የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
" #መስቀለኛዋ አንባ "
ግሸን ማርያም ደብር በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ደብር ናት፤ ይህች ደብር በሐይቅና በመቅደላ፤በደላንታ፤ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ የሆች ስትሆን። በርዋ አንድ ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ናት፡፡ በበርዋ ከተገባ በኋላ ግቢዋ ከላይ ሜዳና መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡ በትግራይ እንደ ደብረ ዳሞ በበጌምድር እንደዙር አምባ በመንዝ እንደ አፍቅራ ናት ፡፡ ወደዚህች ደብር ለመሔድ በረሐ አቋርጦ በሸሎን በመሻገር ፫ ሰዓት መንገድ አቀበት በመውጣት አንድ ቀን ሙሉ ተጉዞ ማታ ፲፪ ሰዓት ይገባል ፡፡ግሸን ማርያም በፊት #ደብረ_እግዚአብሔር ትባል ነበር ፡፡ ይህ ደብረ እግዚአብሔር የሚለው ስያሜም በጻድቁ ንጉሥ ላሊበላ እጅ ከቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ #በእግዚአብሔር_አብ ስም ስለነበረ #ደብረ_እግዚአብሔር ተብሎ ተጠራ፡፡ ከዚያም በዓጼ ድግናዣን ዘመን መንግሥት የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት ሐይቅ ደብር ነጎድጓድ ተብሎ ሲሰየም ግሸን የሐይቅ ግዛት ስለሆነች #ከደብረ_እግዚአብሔር ደብረ ነጎድጓድ ተብላለች ፡፡
ከዚያም በ ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በዓጼ ዘርአ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የክርስቶስ ግማደ መስቀሉ ግሸን ገብቶ ሲቀመጥ ከደብረ ነጎድጓድ ደብረ ከርቤ ተብላለች የደብሩ አስተዳዳሪም መምህረ እሥራኤል ዘደብረ ከርቤ ይባል ነበር ፡፡ ከደብረ ከርቤ ተመልሳ ግሸን ማርያም ተብላለች፡፡ ይህች ግሽን የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀልኛ ቦታ ነቸና ለግማደ መስቀሉ ማረፊያ ትሆን ዘንድ ተመረጠች ፡፡
በዚያም ዘመን የነበሩት የኢትዮጵያ ጳጳሳት የነበሩት አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የተባሉ ከንጉሡ ከዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ጋር ሆነው የምህረት ቃል ኪዳን ለመቀበል በዚህች በግሸን ደብር ሱባዔገቡ ። በሱባዔአቸውም በመጨረሻ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ " ይህች ቦታ እኔ ተወልጄ ያደኩባትን ኢየሩሳሌምን ትሁን፣ የተሰቀልኩባትንም ቀራንዮን ትሁን ፣ የተቀበርኩባትንም ጎልጎታን ትሁን ። በዚች ቦታ እየመጣ የሚማፀነውን ሁሉ ቸርነቴ ትጎበኘዋለች ጠለ ምህረቴንም አይለይባትም ፤ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ መጥቶ የተቀበረ ኢየሩሳሌም እንደተቀበረ ይሆንለታል "። የሚል የምህረት ቃል ኪዳን ተገለጸላቸው። ስለዚህም ግሸን ደብረ ከርቤ ዳግሚት ኢየሩሳሌም (ሁለተኛይቱ ኢየሩሳሌም )ተብላ ትጠራለች ። አፄ ዘርያቆብም ከአባታቸው ከአፄ ዳዊት በተቀበሉ አደራ መሠረት በዚያች አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀመጧቸው ዘመኑም በ፲፬ ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው::

#ምንጭ:- መጻሕፈ ጤፉት፣
ዲ/ን መልአኩ እዘዘው ጽሁፍ

"ሰብ ይቀድስ ለመካን መካን ይቀድስ ለሰብ"
"ሰው ቦታን ይቀድሳል ቦታም ሰውን ይቀድሳል"
#መስከረም ፩ ፭/ ፳ ፻-፩ ፫ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
#ዓውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ዐውደ ምሕረት
የመስቀሉ ላይ ስጦታዎች.mp3
#ስብከተ_ወንጌል
አስተማሪ:- #ልዑል_እግዚአብሔር
ተናጋሪ :- ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም

ርዕስ :- #የመስቀሉ_ላይ ስጦታዎች

በውስጡ የተዳሰሱ ነገሮች
- በመስቀል ላይ የተሰጡ ስጦታዎች አለ እንዴ?
-ምን ምን ናቸው?
-እንዴት ሰጡ?
-መቼ ተሰጡ?
-ለምን ተሰጡ? ወዘተ
#ዓውደ ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
መስከረም ፳ ፪\፪ ፳ ፻ ፲፫ ዓ.ም
Watch "መዓዛሽ ሸተተኝ ከግሸን ልዩ ያሬዳዊ ዝማሬ በዘማሪ ክብሮም ግደይ እና ዘማሪት ሳራ ተፈራ Meazash Shetetegn Kegishen EOTC Mezmur" on YouTube
https://youtu.be/31QylaSZOSA
https://www.youtube.com/channel/UCFypMaWT51ciqhSkERztUdg

ሰብስክራይብ በማድረግ ካዘጋጀነው መንፈሳዊ ማዕድ ይቋደሱ።