Audio
መንፈሳዊ ውይይት
እንኳን #አደረሳችሁ አደረሰን!
ርዕስ:- #ኪዳነ ምህረት
#በቡሩክ መልሳቸው እና
#በተርቢኖስ ሰብስቤ
#ዓውደምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ነሐሴ 16/2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
እንኳን #አደረሳችሁ አደረሰን!
ርዕስ:- #ኪዳነ ምህረት
#በቡሩክ መልሳቸው እና
#በተርቢኖስ ሰብስቤ
#ዓውደምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ነሐሴ 16/2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Forwarded from Deleted Account
አመሰግናለሁ ጥያቄ ጳጳሳት የሚይዙት መቋሚያ ለየት ያለ ነዉ ለምን እንደሆነ ምሳሌነቱስ ከመፅሃፉ ቅዱስ ጋር ምን ያገናኘዋል ???
Forwarded from Tt
ሰላም ለናንተ ይሁን። መላእክት ስጋ የለበሱ ካልሆኑ መልክአ መልክ ለምን እንደግማለን?
Forwarded from Tt
ተዝካር/ፍትሀት ጥቅሙ ምንድን ነው? ሰው እሚፀድቀውም አሚኮነነውም በስራው ከሆነ ምን ይጠቅመዋል?
ሠላም እንደምን አመሻችሁ ሳምንት የትዕማርን ታሪክ ዳሰን ነበር:: ሀሳባችሁን ላጋራችሁን ሁሉ በትዕማርና በመሰል እህቶቿ ስም እናመሰግናለን ቃለ ሕይወት ያሰማልን !
#ግን መጨረሻዋ ምን ሆነ? ካልን
👉እግዚአብሔር ፈርዷል የትዕማር ደም እና እንባ ፈሶ አልቀረም አምኖን የገዛ እህቱን እንዳረከሳት በገዛ ወንድሙ በአቤሴሎም በሰይፍ ተገሏል::
አቤሴሎም በአምኖን ላይ ቂም ይዞ ኖሮ አባታቸው ንጉሱ ዳዊት እንደማይገኝ እያወቀ ድግስ ደገሰ አባቱ ዳዊትንም አውቆ እንዲመጣ ጋበዘው ንጉሱም እንበዛብሃለን እንከብድሃለን እኔ አልመጣም አለው አቤሴሎምም የልቡን በልቡ ይዞ አንተ ካልመጣህ ታላቅ ወንድም እንደ አባት ነውና ወንድሜ አምኖንን ላከው አለው ላከለትም :: አቤሴሎምም ለአሽከሮቹ በሉ አብሉት አጠጡት በኃላ ሲሰክር በሰይፍ ውደቁበት ብሎ ትዕዛዝ ሰጠ የንጉስ ልጅ ነው ብላችሁ እንዳትፈሩ እኔም የንጉስ ልጅ ነኝ ሲልም እንዳይዘናጉ አሳሰባቸው :: እንዳለውም አደረጉ አምኖንም በዛ ሞተ
✋በወቅቱ ትዕማር ከወንድሞ ከአምኖን ለማምለጥ የራሷን ጥረት አድርጋለች:: እንዴት ቢሉ አባትህ ዳዊትን ጠይቅ እርሱ እኔን አይነሳህም ስትል ተሰምታለች ትዕማር ይህን ማለቷ አባታቸው ንጉሥ ዳዊትን የሚያክል ሰው ሴት ልጁን ለወንድ ልጁ የሚድር ሆኖ አይደለም ። ለጊዜው ቢተወኝ ብላ የፈጠረቻት ዘዴ ነበረች ። ነገር ግን ከእሷ ይልቅ ብርቱ ነበርና በግድ አስነወራት ይለናል :: ይህም አገላለጽ በራሱ የትዕማርን የማምለጥ ግብግብ የሚያሳይ ነው ::
.....ይቆየን .....
🤝የዛሬው ታሪካችን ደግሞ ቀጥሎ ይቀርባል
#ለበለጠ መረጃ
2ሳሙ13፥1 ጀምሮ ሙሉን ያንብቡት
“አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤”
— ገላትያ 6፥7
ዓውደ ምህረት የናንተ
👇👇👇👇👇👇

እንዲህ ተብሎ ይጻፍ
በዘመነ ብልፅግና ስርዎመንግስት 7512 ዓመተ ዓለም ፡በሰኔ 23/2012 ዓ/ም አበቅቴው 6 መጥቅዕ 24 በ293ኛው ቀን በሰኔ 23/2012 አብይ በሚባለው መሪ የኢትዮጵያ ገበዝ በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ሰለቀናች ሃይማኖታቸው 67 ክርስቲያኖች ሰማዕትነት በአክራሪ ኢስላሞች ታረዱ ተቃጠሉ አካላቸው ጎደለ ንብረታቸውም ወደመ ብዙ አባቶች አለቀሱ ወንዶቹም ሴቶችም አዘኑ በዚህ ጊዜ ታማኙ አገልጋይ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀኑ የተሰውትን ከትንሽ እስከ ትልቅ ከደቂቅ እስከ ሊቅ ወንድ ሴት ሳይለይ የሁሉንም መከራ አየ በአምላኩ ፊትም አቤቱ የሰራዊት ጌታ እግዚብሔር ሆይ የእነዚህን የኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ደም እስከመቼ ነው የማትቀበለው እያለ በየቀኑ ማለደ ጌታ እግዚአብሔርም የምስክሮቼን ደም ከገዳዮች እጅ እቀበላለሁ ሞትም ጥላቸው ይሆናል አለ፡፡ ሕዝቡም ሁሉ በሰማዕቱ ምልጃ ተፅናና በረከቱ ምልጃው አይለየን አሜን፡፡
በአባቶቼ መግለጫ በቁጭት በብግነት እነደነበረ እንደ አንድ ምዕመን ጊዚያዊ ማስታገሻ መገኘቱ አባቶችም ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ መጀመራቸው ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሰጠው አደራ የእነርሱም መሆኑን የተነፈሱበት መሆኑ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ያስብላል ፡፡ ፍራቻዬ ግን የብልፄግና ፓርቲ ትዕቢት የወጠረው በመሆኑ በፕሮቴስታንታዊ ንግርት አስተምህሮ እና አቋም ላይ እንደ መመስረቱ መንግስት እርምት ላይወስድ ስለሚችል የኦርቶዶክስ ወጣት በጥበብ በብልሃት እና ነገን በማሰብ ቤተክርስቲያኗን ለትውልድ ማትረፍ ከዚህ ከእኔ ትውልድ ይጠበቃል ስለዚህ ምን ማድረግ እንዳለብን በየደብራችን በመምክር ለአገር ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ ስለሆነ የአባቶች ውሳኔ የእኛም ውሳኔ መሆኑን መመስከር ይጠበቅብናል፡፡
👉 @AwediMeherit

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
‹‹ የጻድቅ ሰዉ ጸሎት በስራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች›› ያዕቆብ 5÷16
+++ ጸሎት ከ እግዚአብሔር ጋር የምንነጋግርበት መንገድ ነው። በቅዱስ ወንጌል ላይ ጌታችን በምሳሌ ሲያስተምር እንዲህ አለ ‹‹ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛው ቀራጭ ፈሪሳዊው ቆሞ በልቡ ይህን ጸለየ ‹እግዚአብሔር ሆይ እንደ ሌላው ሰው ሁሉ ቀማኞችና አመጸኞች አመንዝሮች ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንኩ አመሰግናልሁ ፥ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ አስራት አወጣለሁ › አለ ፤ ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሳ እንኳ አልወደደም ነገርግን‹ አምላክ ሆይ እኔን ኃጢያተኛውን ማረኝ› እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር ። እኔ ግን እላቹሃለው ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ ÷ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል ብሎ ጌታችን ስለ ጸሎት አስተምርዋል። መጽሐፍ ቅዱስም እኛ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን በሉ ብሎ ነው የሚያዘን…..ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበር ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ በምድርም ላይ ሶስት አመት ከስድስት ወር አልዘነበም ሁለተኛም ጸለየ ሰማዩም ዝናብ ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች ፤ ይስሐቅም ስለ ሚስቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ መካን ነበርችና እግዚአብሔር ተለመነው ርብቃም ሚስቱ ጸነሰች፤ ሊቀ ነቢያት ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ስለ ሕዝበ እስራኤል ጸለየ መና ከሰማይ አውርዶ ውሃ ከጭንጫ አፍልቆ መገባቸው፤ ኤልሳዕም የሶሪያው ንጉስ ወልደ አዴር ሠራዊቱን አሰልፎ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ በፍርሃት የደነገጠውን ሎሌውን ‹‹ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ ››ብሎት ወደ እግዚአብሔር እጆቹን ዘርግቶ‹ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን እባክህ ግለጥ› ብሎ ከጸለየ ብኋላ እግዚአብሔር የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ አየም፤ እነሆም በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈርሶች እና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር ዳግመኛም ኤልሳዕም ‹አቤቱ እነዚህን ሰዎች አሳውራቸው› ብሎ ጸለየ እግዚአብሔርም እንደ ፈቀደው አደርገለት አሳውሮ ግን አልትዋቸውም ወደ ሰማሪያ በገቡ ጊዜ ዓይኖቻቸው እንዲገለጥ አድርጓዋል።
+++ከክርስቶስ ልደት በኋላም በአዲስ ኪዳን ብዙዎች የተመረጡ ቅዱሳን ቅድስት በሆነች ጸሎታቸው ብዙ ተአምራትን አድርገዋል እግዚአብሔርንም አስደስተዋል ። በ1197 በታሕሳስ 24 ዕለት በቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ክልል ከአባታቸው ከቅዱስ ጸጋዘአብ ከ እናታቸው ከቅድስት እግዚእኀሪያ የተወለዱት ቅዱስ እግዚአብሔር ገና ከእናታቸው ማህጸን የመረጣቸው የወንጌል ገበሬ ትሁት ጻድቅ አባት የሁላችን ጠባቂ ብጹህ ወቅዱስ አቡነ ተክለሐይማኖት በቅድስት ጸሎታቸው ብዙ ተአምራትን አድርግዋል ።ከጓደኞቻቸው ጋር ወደ አደን ሄደው ሳለ ጌታቸን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ ከዚህ በፊት በደማስቆ ቅዱስ ጳውሎስን ለሐዋርያነት እንደመረጠው እሳቸውንም ለኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ሐዋርያ እንዲሆኑ መርጦ ከአውሬ አዳኝነት ሰውን በትምህርተ ወንጌል እያደኑ ለመንግስተ ሰማያት እንዲያበቁ ጠራቸው የሐዋርያነት ስማቸውንም ተክለሐይማኖት ብሎ ሠየመው ይህም ትርጉሙ የአብ ተክል የወልድ ተክል የመንፈስ ቅዱስ ተክል ማለት ነው።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ተክለሐይማኖት ተብለው መጠራት ጀመሩ ሳኦል ጳውሎስ ተብሎ እንደተጠራ ሁሉ ።የምድር ቤቴን ከፍቼ እንደውጣው አንተም የሰማይ ቤትህን ክፈትልኝ ብለው ለማስትማር በምናኔ በሐዋርያነት ተልእኮ ለኢትዮጵያውያን ሐዲስ ሐዋርያ በመሆን እንደ በግ በተኩላዎች መካከል የማስተማር ስራቸውን ቀጥለዋል።ጣኦታትን መዝብረው አሳፍረዋል የዲያቢሎስን ክፉ ምክሩን አክሽፈዋል ፤ ጽኑ ተጋድሎን ፈጽመዋል ህይወታቸውን እስከማጣት ድረስ በቃልና በኑሮ ሰብከዋል ተጋድለዋል ። ከ 1267 ዓ.ም እስከ 1289 ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ ካላው ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባት ስምንት(8) ጦሮችን ሁለቱን በፊት ሁለቱን በኋላ ሁለቱን በቀኝ ሁለቱን በግራ አስተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል አምሳል በመዘርጋት የክረስቶስን ሕማምና ሞት ነገረ መስቀሉን በማሰብ በተመስጦ ሌትና ቀን ያለማቋረጥ በጾም በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋድሉ ከቁመጥ ብዛት የተነሳ ጥር 4 ዕለት በ1282 ዓ.ም የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች።ደቀመዛሙርቱም የመንፈሳዊው አባታቸውን ስባሪ አጽም አክብረው በስርዐት አኑረውታል እግራቸው እስኪሰበር የቆዩባቸው ዓመታት በቁጥር ሃያ ሁለት(22) ናቸው ‹‹በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአል ››ብሎ ሐዋርያው እንደተናግረው/1ኛ ጴጥ 4፥1-2/ ብጹዕ አባታችን ከኃጢአት ርቀው መከራ መስቀሉን በመሸከም ራስን በመካድ በመስዋዕትነት ሕይወት ፈጣሪያቸውን አገልግልዋል።ከ 1289 ዓ.ም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ብቻ በመቆም ያለምግብ በትኀርምት ሌትም ቀንም ለዓይኖቼም መኝታ ለሽፋሽፍቶቼም እንቅልፍ÷ለጉንጮቼም ዕረፍትን አልሰጥም ብለው እንደምሶሶ ጸንተው በትጋት ለሰው ዘር በሙሉ ድኅነትን ሲለምኑ ኖርዋል።በዚህን ጊዜ ውስጥ ጌታችን ተገልጾ ወዳጄ ተክለሐይማኖት መታሰቢያህን ለሚያደግ ስምህን ለሚጠራ ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ፍጹም ዋጋ ፍጹም ክብርን እሰጠዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል ‹ በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው ከተፈተነ በኃላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና› እንደተባለው በመጨረሻም በ ነሐሴ 24 ዕለት በ 1296 ዓ.ም ጌታችን የገባላቸውን ቃለ ኪዳን ለመንፈሳዊ ልጆቻቸው እና ለደቀመዝሙሮቻቸው ከነገሩ በኃላ በክበር ዐርፈዋል ‹‹ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብጹዓን ናቸው፥ አዎ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ብልዋል ከድካማቸው እንዲያርፉ ሥራቸው ይከተላቸዋል ወደ ሕይወት ምንጭም ይወስዳቸዋል ››ነውና የሚለው ቃሉ በአካለ ነፍስ ወደ ፈጣሪያቸው ሄደዋል በዚያም እንደ ፀሐይ እያበሩ ይኖራሉ፤ በቃል ኪዳናቸው ስለኛ ስለ ኃጥአን የሚለምኑ ገድለኛ ደገኛ አባታችን ጻድቁ ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ ተክለሐይማኖት ናቸው።
‹‹ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታድረጋለች››……….የጻድቁ አባት የአቡን ተክለሐይማኖት ረድኤት በረከት አማላጅነት ጣዕም ፍቅራቸው በእኛ በ ልጆቻቸው ላይ በእውነት ይደርብን! …አሜን!
……..እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው ፥ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል እግዚአብሔር ይመስገን…….መዝ 67፥35
አዘጋጅ ፦ቡሩክ መልሳቸው
ቀን 23/12/2012

“#እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ።”
መዝ 4፥3
ብዙዎች እግዚአብሔር በጻድቃን እንደሚገለጥ ባለማወቅ የቅዱሳኑ ነገር የእግዚአብሔርን ነገር በልጦ የሸፈነው ይመስላቸዋል :: ግን ነገሩ እንዲህ አይደለም ውኃን ከጥሩ (ከጠራው) ነገርን ከሥሩ እንዲሉ የጻድቅን ትርጉም በመጀመሪያ በአጭሩ እንመልከት::
ጻድቅ የሚለው ግሥ እውነተኛ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ለብዙ ቁጥር ስንጠቀመው ጻድቃን ብለን ማናበብ እንችላለን እውነተኞች ማለታችን ነው!::
በእውነቱ "ጻድቅ" የሚለውን መቀጽል በመጀመሪያ በተገባ የሚገባው ለልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው :: እግዚአብሔር አምላክ እቀደስ አይል ቅዱስ እጸድቅም አይል ነገር ጻድቅ ነው ጽድቁም እንደ ቅዱሳን የጸጋ (የስጦታ) እንደ ሰይጣንም የሐሰት ሳይሆን ማንም ያልሰጠው ማንም የማይቀማው በባህሪው ጻድቅ እውነተኛ ቅዱስም አምላክ ነው ::“እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ #አምላካችንም_ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።” እንዲል መጽሐፍ 1ኛ ሳሙ 2፥2
ጻድቅ ወይም እውነተኛ ለመሆን በእውነት ማመን ፣ ስለ እውነት መናገር፣ ስለ እውነት ማስተማር፣ ስለ እውነት መኖር ይጠይቃል :: ታዲያ ይህ እውነት ማነው ካልን እግዚአብሔር ነው:: “እኔ መንገድና #እውነት ሕይወትም ነኝ፤ ” ዮሐ14፥6
ከእነዚህ እውነተኞቹ ጻድቃን መካከል የጽላሎሹ ኮከብ የእግዚ አርያ ዐይን ማረፊያ የፀጋ ዘአብ አብራክ የምመናን እረኛ የወንጌል አርበኛ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ግምባር ቀደም ናቸው:: ድካምን በማብዛት እንደ ነቢያት ወንጌልን በማስተማር እንደ ሐዋርያት በመገረፍ እንደ ሰማዕታት መሰለ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር በጻም በድካም ሌት ተቀን ተጉ 22ዓመት በሁለት እግራቸው ከቆሙ በኃላ ከመቆም ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራ ወደቀች በዚህም ለአፍታ ሳይዘናጉ ለ7ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው በትዕግሥት 29 ዓመት በጸሎት ተጋደሉ :: መጻሕፍ “እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን” ያዕ5፥11 ብሏልና " #ብፁህ " አልናቸው :: የሥራዬን ጽናት የሃይማኖቴን ደግነት ግለጥ እያሉ በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ ክርስቶስን ሲሰብኩ ቆይተዋል እንዲያውም በከተታ አውራጃ በዚህ በታመኑለት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲያስተምሩ ሀገሪው ሰምቶ ለዛፍ መስገድን ሊያስቆሙን ነው ከፈጣሪያችን ሊያጣሉን ነው ብለው እንደ አንበሳ ሊውጧቸው ተነሱ አባታችን ግን በልበ ሰፊነት በነገር አሳላፊነት እያለዛዘበ አስተማሯቸው ወደ ቀናች ሃይማኖትም መለሷቸው:: ይህ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ምን ያክል ድንቅ እንደሆነ የሚያመላክት ነው እንጂ የቅዱሳኑ ሕይወት የእግዚአብሔር ነገር ነገረ እግዚአብሔርን የሸፈነ አይደለም ጻድቃን ቅዱሳን “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፥” የሚሉ ናቸውና 1ኛ ቆሮ1፥23
እንደ ልቤ የተባለውም ቅዱስ ዳዊትም “እግዚአብሔር #በቅዱሳኑ_ላይ_ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።”መዝ 67(68)፥35 ሲል የጻድቃን ሕይወት ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር የተገለጠበት ድንቅም የሚያደርግበት ለሕዝብም ኃይልን የሚያድልበት መሆኑን መስክሮልናል በዚህም ነገር እግዚአብሔር ይመሰገንበታል :: “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” ብሎ ያዘዛቸውም በእነርሱ መልካም ሕይወት የሰማይ አባታቸው እግዚአብሔር ስለሚገለጥበት ነው። ማቴ 5፥16
አንዳንድ አካላት ግን ይህን ባለ መገንዘብ ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ ይልቅ ቅዱስ ጳውሎስን ከነገረ እግዚአብሔር ይልቅም ነገረ ቅዱሳንን አስበልጣ ትሰብካለች ይላሉ:: ነገሩ ከፈረሱ ጋሪውን እንደማስቀደም ያለ ነገር ነውና የትም አያደርስም :: ይህ ዓይነቱ አካሄድ የዋልዮሽ አካሄድ በመሆኑ መጨረሻው ገደል ነው:: የዚህ ትምህርት ምንጭም ክርስቶስ ብቻ በቂዬ ነው የምትለው የመናፍቁ ዓለም ጨዋታ ነች :: ለክርስቶስ የተቆረቆሩ በማስመሰል ምርጦቹ ቅዱሳኑን ለማራቅ አያስፈልጉም ለማለት የሚደረግ ዳርዳርታ ነች :: ቅዱሳን ማሰብ በስማቸው ዝክር ማዘከር ስማቸውን መጥራት ገድላቸውን መስማት ማሰማት የተገባ ደገኛ ሥርዓት ነው ሙሽራው ክርስቶስ ብቻ ሳይሆን ሚዜዎቹ ቅዱሳንንም መቀበል ይገባል::
እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማቴ 10፥40-41 መቀበል ከነ ሚዜዎቹ ነው ማነው? እስቲ ከውጪ የመጣ ወዳጁን አንተ ና ወደ ቤቴ ግባ የያዝከው የሻንጣ ገንዘብ ግን ከቤቴ አይገባም ብሎ ወዳጁን ስለ ገንዘቡ አልቀበልም የሚለው? ቅዱሳን የክርስቶስ ገንዘቡ ናቸው :: ያለ እነርሱ ልንቀበለው አንችልም::
“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን #ዋኖቻችሁን_አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”ዕብ 13፥7 እንግዚህ እግዚአብሔር ያከበረውን ማን ያቀለዋል ?
“በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ በቤቱና በቅጥሩ የማይጠፋ የዘላለም የመታሰቢያ ስም የሰጣቸው እራሱ ባለቤቱ ነው ኢሳይ56፥5
እግዚአብሔር ለጻድቃን የሰጣቸው ወይም የሚሰጣቸው ክብር በሕይወተ ሥጋ ብቻ ሳሉ አይደለም ለሞታቸውና ለአጸደ ነፍሳቸውም ጭምር የሚሆን ከብረው የሚያከብሩበት ዘላለማዊ ሥጦታ ጭምር ነው እንጂ:: “የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።” መዝ116፥15
ጻድቁም ወደ ሰማዕታት አደባባይ ሄጄ በስምህ ሰማዕትነትን እቀበል ዘንድ አውዳለውና ያን እንዳደርግ እዘዝ አሉት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መቀዳደምክን ጨረስክ ከሞት በቀር የቀረህ የለም ሁሉን ፈጽመሃል ሞትህንም እንደ ሰማዕታት ሙት አድርጌ እቀበለዋለው አላቸው :: ብዙ ቃል ኪዳንም ከሰጣቸው በኃላ አባታችን ነሐሴ 24 ቀን በ99 ዓመት ከ10ወር 10ቀናቸው ቅዱስት ነፍሳቸው ከቅዱስ ሥጋቸው ተለየች::
#የአባታችን የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት እረድኤት በረከታቸው ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትሁን !::አሜን!
“#የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።” ዘኍልቁ 23፥10
.............#ይቆየን..........
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ነሐሴ 24 ቀን 2012ዓም

በዓለ #ወልድ በዓለ #እግዚአብሔር
#የፈጣኑ_ሰው መልስ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።
እነርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።
#ምሥጢረ ተዋሕዶ የአምላክ ልጅ የሰው ልጅ የሰው ልጅ የአምላክ ልጅ ብሎ ያለ መነጣጠል ማመን ነው:: #ለዚህ ነው ስለ ሰው ልጅ ተጠይቆ ስለ አምላክ ልጅ መልሶ ትክክል የሆነው ::
#ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብም የድንግል ማርያምም የበኩር ልጅ ነው::
ነሐሴ 29/2012ዓ.ም
ኃ/ማርያም