ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ዝክረ_ቅዱሳን
°°°°°°_
#ቅዱስ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
-----------------------------------------
#አዘጋጅ ና አቅራቢ :- #ዲ/ን ሙሉ ዓለም አየለ
#የጊዜ ርዝማኔ 10 ደቂቃ 25 ሰከንድ
መጠን 11.9 mb ብቻ
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ!
“የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል"የተባለው ተፈፀመ
ት.ዘካ 9÷9

ይህ በነቢዩ ዘካሪያስ አስቀድሞ በትንቢት የተነገረ አማናዊ ቃል የተፈፀመው በኢየሩሳሌም ከተማ ደብረ ዘይት አቅራቢያ ቤተ ፋጌ በምትባል መንደር ነው::ጊዜው በግምት 2000ዓመት ገደማ ይሆናል::ከተማዋ በደስታ ታምሳለች የኢየሩሳሌም ከተማ በተለያዮ ጊዜያት ልዮ ልዮ ነገስታት በሰረገላ ተቀምጠው ጎብኝተዋታልች፣ገስተዋታል የዛሬው ግን ልዮ ንጉሥ ነው ስለ ፍቅር ሲል የእሳት ሰረገላውን ትቶ አህያን የመረጠ አበ ትህትና(የትህትና አባት)መድኃኒት የሆነ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::ሕዝቡም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው አስቀመጡት፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ማቴ 21÷1-17 ከፊትና በኋላ ያሉት ብዙ ሰዎችም “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
ሆሳዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው ሕዝቡም እንዲ ማለታቸው አቤቱ አሁን አድን ብሎ መዝሙረኛው ዳዊት የተናገረውን ንግግር ሲገልጡ ነው ።አህያይቱ ተሰርቃ ከነ ልጆ ከነ(ውርንጭላዋ) ታሰረች ነበር ያሰራት ሰው ሌባ ነወ የሌላ ሰው ንብረት እንደ ንብረቱ አድርጎ ከደጃፉ አስሯታልና ሌባው በቤቱ ያቆያት 5ቀን ተኩል ነው" የማታ የማታ እውነት ይረታ" እንዲሉ አበው እውተኛ ፈራጅ በወጣ ጊዜ አህያዋ ከእስራቷ እንድትፈታ አደረገ ::አህያዋ ና ውርንጫላዋ አዳምና ልጆቹ ሲሆኑ ሌባው ዲያቢሎስ ነው: በአሰት ንግግር እግዚአብሔርን ከመሰለ አምላክ ገነት ከምታክል ቦታ ለይቶ ለ5ቀን ተኩልያክል ጊዜ በሲዖል አስሮናል::
5500 ዘመን ሙሉ በእግረ አጋንንት ተይዘን ሰንጨነቅ መድኃኒት ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማንም አልደረሰልንም ነበርና ስለዚህ በደስታ ተሞልተው የሆሳዕና አሉ ::

ለምን በአህያና በአህያ ወርንጭላ ላይ ተቀመጠ ቢሉ?


እናቲቱ አህያ የብሎይ ውርንጭላይቱ የአዲስ ኪዳን ምሳሌ ናቸው በሁለቱ መቀመጡ ኦሪትን እንዳልሻረ ወንጌልንም እንደሰጠ ሲያጠይቅ አንድም እናቲቱ አህያ ሸክም የለመደች ነች አዲሲቱ ውርንጫይቱ ግን ሽክም ያለመደች የቤተ አሕዛብና የቤተ እስራኤል ምሳሌ ናቸው::ኦሪት ከባድ ወንጌል ግን ቀሊል ናትና አንድም ሕግ የለመዱና ሕግ ያለመዱ እዝቦች ናቸውና:: አንድም አህያ በወለደችሁ ታርፋለች እንዲሉ ኦሪትም በወንጌል ታግዛ ጸንታለችና ነው::ሌላው
👉ፋረስና በቅሎ ለጦርነት ይሁላሉ አህያ ግን አትውልም ጥንት ነቢያት ክፉ ትንቢትና ክፎ ወሬ ይዘው ሲመጡ ማቅ ለብሰው ትቢያ ነስንሰው በፈረስ ወይም በበቅሎ ተቀምጠው ወደ ከተማ ይባሉ መልካም ዜናና ትንቢት ይዘው የመጡ እንደሆነ ደግሞ በአህያ ላይ ተቀምጠው ይመጣሉ ሕዝቡም መቀመጫቸውን አይቶ መልካም ዜና እንዳመጡ ተረድቶ በደስታ ይበቀላቸው ነበርና ጌታችንም መልካም የድኅነት ዜና ሆኜ መጣው ሲል ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በአህያ ላይ ተቀመጠ::
👉በአህያ ተቀምጦ እንደሚመጣ በኦሪት የተነገሩ የኢሳይያስና የዘካሪያስን ትንቢት' ለመፈጸም ነው::(ትንቢቱን ለመፈጸም) ዘካ9÷9
👉ከእኔ ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና እንዳለ ትዕትናን ለማስተማር ማንንም አትናቁ ሲል ማቴ11÷29 ዮሐ13÷1
👉በፈረስና በበቅሎ ያለን ሰው ማንም አይደርስበትም በአህያ ያለን ሰው ግን በቶሎ ይደርሱበታል ስለዚህ እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የእሩቅ አምላክ አይደለሁም ከፈለጋችሁን በቅርብ ታገኙኛላችሁ ለማለት በአህያ ተቀመጠ ኤር 23÷23


🌴ሕዝቡ የዘንባባ ዝንጣፊ መያዛቸው🌴

🌿- ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔርን አመስግኖበታል (የደስታ መግለጫ በመሆኑ አንተ ደስታ የምትሰጥ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው)
🌿- ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው ይህንኑ አርአያ አድርገን እኛም እንዲሁ እናደርጋለን

"እነሆ ዛሬ እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር የሰራትን ቀን ይህች ነችና ሐሴትን እናድርግ " መዝ 117 (118) ÷ 24....ይቆየን
እንደ አህያይቱ እኛም ከእስራታችን ሁሉ ተፈተን የሰላም ባለቤት የሆነውን መዳኃኔ ዓለም ክርስቶስን በልባችን ከተማነት የምናሳድር እውነተኛ ክርስቲያኞች ያደርገን ዘንድ የእርሱ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን ለዘለዓለሙ አሜን❤️


ሀሳብ ጥቆማ ጥያቄና አስተያየታችሁን @YEAWEDIMERITE ላይ አድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ሰሞነ_ሕማማትን ምክንያት #በማድረግ ተደግሞ የተለቀቀ🙏

ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
#ምዕራፍ 3 ክፍል 1
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ደቂቃ :- #13 ደቂቃ 54 ሰከንድ
መጠን :- # 3.3 m.b ብቻ
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ደቂቃ :- #15 ደቂቃ 11 ሰከንድ
መጠን :- # 3.6 m.b ብቻ
#ረቡዕ #የምክር_ቀን
" #ምስጉን_ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ"
_______________________
#መዝ 1÷1

ይህ ዕለት የምክር ቀን ይባላል፣ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጻሕፋት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ወቅቱ አይሁድ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት በመሆኑና ብዙ ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረከ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለነበር ምናልባት ሁከት ይፈጠራል ብለው ሕዝብን እየፈሩ ሊይዙት ያመነቱ ነበር። ተሳክቶላቸው እንያዘው ቢሉ እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስን ከደቀ መዛሙርቱ ለይተው አያውቁትም ስለዚህ እርሱን በቅርብ የሚያውቅ ሰው ያስፈልጋቸዋልና በክፉ ምክራቸው እጅግ ተጨነቁ። ትንሽ ቆይቶ ግን ከደቀመዛሙርቱ መካከል አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ በክፉ ምክራቸው በመሳተፍ ጌታን በመሳም አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው ። ለምልክት ይሁናቸውም ዘንድም እኔ ሄጄ የምስመው ሰው እርሱ ክርስቶስ ነውና ያዙት ብሎ ተማከረ ጭንቀታቸው ተወገደ ለወረታውም ሰላሣ ብር መዘኑለት (ማቴ 26፡1-5 ፣ ማቴ26፡14-15 ፣ ማር 14፡1-2፣ ሉቃ 22፡1-6) 
#ዕለተ_ረቡዕ_መልካም_መዓዛ_ያለው_ቀንም_ይባላል፣ ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለ ሽቶዋ ማርያም) ከእንግዲህ ወዲህ በኅጢዓት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኀጢዓትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባሲጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ነው፡፡ የእንባ ቀን ይባላል ይህም ስያሜ የተሰጠበት ምክንያት ይህችው ማርያም እንተእፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢዓቷን ይቅር እንዲልላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ በጠጉሯም ማበሶ አክሊሌ ነክ ስትል ነው ። የማርያም እንተእፍረትን ኃጢዓት ይቅር ብሎ መባዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬ በመካከላችን አለና በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የራሳችንን ኃጢዓት በማሰብ በማልቀስና የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር በማቅረብ በመልካም ሥራዋ ልንመስላት ይገባል፡፡ (ማቴ 26፡6-13 ፣ ሉቃ 7፡36 ፣ ማር 14፡3-9 ፣ ዮሐ 12፡1-8)

...........ይቆየን…..........
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ
📢ዓውደ ምህረት 🎤


#ዕለተ_ሐሙስ

#ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል
__________________

በዚህ ዕለት መምህራቸው ሆኖ ሳለ ክርስቶስ በአጭር ታጥቆ አደግድጓ ወገቡን አስሮ የደቀመዛሙርቱን እግር ያጥብ ዘንድ በትህትና ዝቅ አለ:: ቅዱስ ጴጥሮስም እንዴት የእኛን እግር ታጥባለህ አንተኮ ጌታዬ ነኘ ብሎ ላላመታጠብ በትህትና እግሮቹን ሰበሰበ ጌታችንም በጥምቀት አክብሮ ልጅነትን ሊሰጣቸው ወዶ ነበርና ዛሬ ያልታጠበ ከእኔ ጋር ጽዋ ተርታ ዕድል ፍንታ የለውም አለው። ይህን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ደንግጦ እንደዛማ ከሆነ እንሬን ብቻ ሳይሆን ሰውነቴንም ጭምር እጠበኝ ብሎ ተናገረ ጌታችን ግን እግሩን የታጠበ ሰውነቱ ንፁዕ ነው ነገር ግን ሁላችሁ ንፁዕ አይደላቹሁም አላቸው አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳ በመካከላቸው ነበርና ዮሐ13÷10 ይህን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ታጠበ::
ይህም የሚያሳየው ከትህትናው ባሸገር የዓለምን ኃጢዓት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያአትት ኃጢዓተ ዓለም›› የዓለምን አጢኃት የሚስወግድ የእግዚአብሔር በግ ዮሐ 1÷29 እንዲል፡፡ ይህንን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳትና የደብር አስተዳዳሪዎች በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢዓት እጠብ ሲሉ በዕለቱ በአጸደ ቤተክርስቲያን የተገኙትን ምዕመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡያረፍዳሉ፡፡


#የምሥጢር_ቀንም_ይባላል
____________________

ለደቀ መዛሙርቱ ይህ ስለ እናንተ የሚፈሰው ደሜ ነው ይህ ደግሞ ስለ እናንተ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው ብሎ ዕብስቱን ባርኮ ወይኑንም ቀድሶ ለሐዋርያት የሰጠበት ቀን ነው ሐዋርያትም ከእጁ ተቀብለው በልተዋል ጠጥተዋል በዚህም ምስጢረ ቁርባንን ፈጽሞላችዋልና ዕለቲቱ የምስጢር ቀን ተብሎ ይጠራል ። #ማቴ 26÷ 26-28

#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል
__________________

በፍጥረታት የሚለመንና የሚመሰገን አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለምንና አላዋቂ የሆነውን ሥጋ የተዋሐደ አምላክ፣ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጥ አንድም የስጋ ሞት እጅግ አስፈሪ መሆኑን ለማጠየቅና በመከራቹ ጊዜ ወደ ሰማይ አባታችሁ ጸሎትን ጸልዮ ሲል ለአርያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴ ሰማኔ በአታክልቱ ሥፍራ ሲጸልይ አድሮል በዚህም ዓብይ ምክንያት ይህ ዕለት ጸሎተ ሐሙስ ተብሏል፡፡ (#ማቴ 26፡36-46 ፣ ዮሐ 17)


. ......ይቆየን.........

👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE

🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
📢 @AwediMeherit📢
📢 @AwediMeherit📢
📢📢📢📢📢📢📢📢
"ሰው ሆይ ከሰው ተጠበቅ"
#ማቴ 10÷17

#ዕለቱ_የዕሣዕና ዕለት ነው ! አህያ የያዙ የቤተክርስቲያን ወጣቶች ወደ አንድ ካህን አባት ቀረቡና አባታችን እርሶ እንደ ጌታ አምሳል በአህያዋ ላይ ይቀመጡና በዓለ ሆሣዕናን በምሳሌ ከሕዝቡ ጋር በድምቀት እናክብረው አሏቸው። አባም ዛሬስ እሺ ብዬ ብቀመጥላችሁ ችግር አልነበረውም ግን በሳምንቱ ማንን ስቀለው ስቀለው ልትሉ ነው አሏቸውና በአህያዋ መቀመጥን እንቢ አሏቸው ይባላል። #የዛሬን_ሳይሆን_የነገን አስብ !
#ሁለት ዓሣና አምስት የገብስ እንጀራ አበርክቶ ቢያበላቸው ካላነገስንክ አሉት በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ሲመጣም "ሆሣዕና በአርያም ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው" እያሉ ልብሳቸውን ጭምር በማንጠፍ አመሰገኑት። #ማቴ 21 ÷ 9 በሳምንቱ ጲላጦስ አስሮ ምን ላድርገው ቢላቸው ሕዝቡ ሁሉ " ስቀለው ስቀለው ስለቀው " እያሉ ጮሁ #ሉቃ 23÷21 የሐሰት ከሳሾች ጸሐፍት ፈሪሳዊያንን በጭፍን ተከትለው ሌባ ሌባ ሲባል ሰሙና ሌባ ሌባ ማለት አማራቸው ሳይመረምሩ ምን አጠፋ ሳይሉ ስቀለው ስቀለው እያሉ ጮኹ የኛ የሰው ልጆች መዋደዳችን የቀናት ነው መፋቀራችም ከአንድ ሳምንት አያልፍም ። እናም ሰው ሆይ ከሰው ተጠበቅ! “ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤” #ማቴ 10፥17 ዛሬ ያጨበጨበልን ነገ ያጨበጭብብናል ፣ ዛሬ የሳቀልን ነገ ይስቅብናል እርሱ ግን ሁሉን ያውቅ ነበረና አስቀደሞ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ ብሎ መክሮ ነበር #ማቴ 16÷6

#ከአንድ_ሳምንት_ፍቅርስ_ይሰውረን!

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ሚያዝያ ፳ ፪/ ፳ ፻ ፲ ፫ .ዓ.ም