አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
494 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ግን_አንድ_ቃል_አለ!

.እኔ በቅሎ አደለሁ

ይሄ ሁሉ ሸክም በላዬ ተጭኖ
እንደምን ልራመድ
የየለት ተግባሬ ብልጭ ብሎ መጥፋት
እሳት ሆኖ ማመድ

መኖር አለመኖር
አለመኖር መኖር

መሆን አለመሆን
አለመሆን መሆን

ጊዜ እነደሽልጦ እያገላበጠኝ
ወይ በደህና አልበስል
ዝም ብዬ እፀናለሁ እዮብን ይመስል

ዝም ብዬ
ዝም ብዬ
ይህም ያልፋል ብዬ

በጣር ያቆምኩት ቤት በንፋስ ይገፋል
በውኔ ያቀድኹት ህልም ሆኖብኝ ያልፋል

ወይ በርትቼ አልቆምም ወይ ወስኜ አሎድቅም
ዝም ብዬ እድሀለኹ እንደ ህፃን ልጅ አቅም

ዝም ብዬ
ዝም ብዬ
አንዲትን ቃል ብዬ

ላለመሞት መሞት ለመኖር መታገል
ብረት ነኝ ስል ኖሬ ሸክላ ሆንኩ እንደገል

ስብር ብር ..
. እንክት ክት
ጊዜ ሁን ያለኝን በምኔ ልመክት
ብቻ ግን ብቻ ግን አለሁ ለምልክት

ግን አንድ ቃል አለኝ
"አለት ሆኜ ወደኩ ጠጠር ሆኜ በዛው
የሚል ታሪክ አለኝ ነፍሴን የሚገዛው"
ተመስገን፡፡

🔘አስታውሰኝ ረጋሳ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍39🥰21