አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
​​#ልጩህበት!!


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰትበ_ጥላሁን

ስንቶቹ ሳያውቋት አስበልታቸዋለች አንቺም ሳታውቂያት አብረሻት እንደመጣሽ ስለገባኝ ነው የነገርኩሽ
እኔ እንደነገርኩሽ እንዳትነግሪያት ዱርዬ ገዝታ ታስቀጠቅጠኛለች !!"
ብሎኝ ካጠገቤ እብስ አለ ።

እኔ ግን እዛው በቆምኩበት ዞረብኝ ጭውውውው አለብኝ ••••
•••
ለዚህ አብሯት ላለው ነው ማለት ነው እኔን ያጠመደችለት አልኩ እያየሁዋቸው
ሰውየውን እኮ ብታየው ምን እንደሚያህል! ማጅራቱ ላይ ያለው ስጋ ለብቻው ቢመዘን ከኔ ኪሎ እኩል ይሆናል!"
ስትለኝ ከመመሰጤ የተነሳ ሁለመናዬ እንቅስቃሴ አቁሞ ትንፋሼን አጥፍቼ ሳዳምጥ ከነበርኩበት ሁኔታ ውስጥ አውጥታ አሳቀችኝ።

አቦ እሄ ሁሉ ነገር ተፈጥሮ ትቀልጃለሽ አደል በይ አሁን ቀጥይ አልኳት
"ለመሆኑ ስምህ ማነው? " ድንገተኛ ጥያቄ ።
እስካሁን ስሜን አለማወቋ ሳይሆን የጠየቀችበት ሁኔታ እያሳቀኝ
ዳኒ እባላለሁ ዳንኤል አልኳት።
የሷን በወሬዋ መሀል ስለነገረችኝ መጠየቅ ሳያስፈልገኝ
በናትሽ ኤዱ ከዛ ቡሀላ ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ ቀጥያ አልኳት
ዘወር ብላ ወደ ግቢው ስትመለከት •••
አቦ ተይና እንግዲህ ድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ እንደሆነ አጥር የለው ምንድን ነው ወደዛ እምታይው
የማጅራቱ ስጋ ከኔ ክብደት ጋር እኩል ይሆናል እሚለው ጋር ነው የቆምሽው ስላት ፈገግ ብላ•••
"እውነቴን እኮ ነው በጣም ግዙፍ ሰው ነው!
እኔን ከዛ ሳሎን ቤት ከሚያህል ሱውዬ ጋር አንሶላ ልታጋፍፍ ማሰቧ የጭካኔዋን ልክ ያሳያል !
ብታየው ሲተነፍስ እራሱ ያስፈራል የታፈነ ነው እሚመስለው እኔን ደሞ እንደምታየኝ ቀጭን ነኝ ብብቱ ስር ደብቆኝ ወደ ፈለገበት ቢወስደኝ እራሱ ማን ያየዋል?"
አቦ እቺ ልጅ እኔ እንዴት እንዳመለጠች ለመስማት ጆሮዬ ቆሟል እሷ ትቀልዳለች ስል ሳቅ ብላ
"በገባንበት በር ቀጥ ብዬ ብወጣ ያዩኛል።
ግቢውን ካወከው የተወሰነ ቦታ ጭላንጭል ብርሀን የተወሰነ ቦታ ደግሞ ጭለማ ነው ስለሷ የነገረኝ ልጅ ጥግ ላይ ወዳለችው ጎጆ ቤት ውስጥ ነው የገባው ጎጆ ቤቷ ደግሞ እየጠጡ በሚጨፍሩ ሰዎች ጢም ብላለች ከመሀል ልጁን ማየት አልቻልኩም።
ሞባይል ረሳን ብለው የሄዱት ጓደኛቼ እስኪመለሱ ሽንት ቤት ገብቼ ከውስጥ ዘጋሁ።
ሽንት ቤት ሆኜ ልጁ ያለኝ ነገርና ቀን
እቺው መሰረት ቤት ሆነን ስልክ ሲደወልላት ምንም እንኳን እምታናግረው ከቤት እየወጣች ቢሆንም ከመራቋ በፊት ስታነሳው በንግግሯ መሀል አልፎ አልፎ ጆሮዬ ጥልቅ ሲሉ የነበሩ ቃላቶቿ አቃጨሉብኝ
በተለይ ደግሞ "እጄ ላይ አዲስ እቃ የለም " ያለችው ነገር
እቃዎቹ እኛ ነን ማለት ነው ።
እንደ እቃ ልትሸጠኝ እያመቻቸችኝ " እሄን ድርቅናሽን ተይና ፈጠን ያልሽ ሁኚ "
ማለቷን ሳስበው ነደድኩ መፍጠን እንደጓደኛቼ ከሆነ ዘላለሜን ላዝግም !
መፍጠን መበላሸት ፣ መፍጠን ያሳደጉኝን ወላጆቼን መርሳት እና ድካማቸውን መና ማስቀረት ከሆነ ባፍንጫዬ ይውጣ!
መፍጠን በተስፏ ደረሰች ደረሰች ተምራ ለሀገሯም ለኔም የምትጠቅም ዜጋ ሆነችልኝ እያለች በጉጉት የምትጠብቀኝን እናቴን እና ሀገሬን በማይሆን ተግባር ውስጥ ገብቶ ባጭሩ በመቀጨት ተስፋዋን ማጨለም ከሆነ •
በዚህ መልኩ ፈጥኜ ፈጣን ከምባል ፋራ፣ ፈዛዛ፣ ደንዛዛ፣ ገገማ ፣ሰገጤ ልባል !!
በሌሎቹ ተሳክቶልሻል በኔ ግን አይሳካልሽም መሲ ሀሳብሽ እሚሳካው ከገደልሽኝ ብቻ ነው እያልኩ እየፎከርኩ ከሽንት ቤት ስወጣ አሁንም ጋደኛቼ አልመጡም ። ሞባይል ጠፋ ብለው የሄዱት ሆን ብለው እኔን ለዛች አውሬ ጥለው ለመሄድ ሲሉ የፈጠሩት ምክንያት እንደሆነ የገባኝ ያኔ ነው።
ግራ ገብቶኝ ጥግ ይዤ እንደቆምኩ መሲ ምነው ቆየች ብላ ነው መሰለኝ ወደ ጀርባዋ ስትገላመጥ አየሁዋት ለሷ ግን አልታያትም ተነስታ ልትፈልገኝ ወደ ሽንት ቤት ብትሄድ እሄን ዝፍዝፍ ሸውጄ መውጣት አያቅተኝም በናትሽ ተነሽና ፈልጊኝ እያልኩ በመሀል ከጎጆ ቤቷ መሲና ሰውየው ወዳሉበት ሶስት ወጣቶች እየተጨቃጨቁና እየተጓተቱ መጡና አጠገባቸው እንደደረሱ ቅልጥ ያለ ፀብ ውስጥ ገቡ ደነገጥኩ ።
ትርምስምስ አለ በዚህ መሀል ልውጣ ?ታየኝ ይሆን?እያልኩ ስወዛገብ የቅዱሙ ልጅ ድንገት እጄን አፈፍ አርጎ
"ትፈዧለሽ እንዴ ፀቡ እኮ ድራማ ነው ውስጥ ሆኜ ስከታተልሽ ነበር ሆን ብዬ ነው ጀለሶቼ እዛጋ ሄደው ወከባ እንዲፈጥሩ ያመቻቸሁዋቸው
ከሷ ጋር ፊት ለፊት ተቃብቼ አንቺን ማስመለጥ ስላልፈለኩ ነው ልጅቷ ብዙ ኔት ወርክ ስላላት ሌላ ግዜ እንዳታስጠባኝ ብዬ ነው እንጂ እኛ አራት ሆነን ያንን አብሯት ያለውን ዘረጦ ፈርተነው እንዳይመስልሽ "
እያዋከበ ይዞኝ ከወጣ ቡሀላ
" እዛጋ ባጃጅ ታገኛለሽ ቆይ ትንሽ ላስጠጋሽ" እያለ ቁልቁል ወረድን ። እሱ እሄን ሁሉ ሲያወራ ስለደነገጥኩ ነው መሰለኝ ትንፍሽ አላልኩም በቃ ተመለስ ብዬው ቆም እንዳልን ከጀርባው ከሆቴሉ እየተምዘገዘገ የሚመጣውን ሰው ተመለከትኩና
በቆምኩበት በድን ሆንኩ ሁኔታዬ ግራ ገብቶት ሲያፈጥብኝ በጄ ወደሚመጣው ሰው እያመለከትኩ እንደምንም
ወይኔ ተከትለውን መጡ መሰለኝ አልኩት ደንግጦ ዞረ..

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1