አትሮኖስ
268K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
432 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

#ያሬድ

ሁሉም ተሳካለት፡፡ ከዚያው አካባቢ አበበች የምትባል ልጅ አገባ፡፡ ኑሮውን ለማሻሻል ከግብርና ስራው በተጨማሪ የንግድ ስራ ለመስራት አቀደ፡፡ ለባለቤቱ ማማከር እንዳለበት ወሰነ፡፡

አንድ ቀን ከባለቤቱ ጋር እራት እየበሉ ነው፡፡ "እንዴው ይሔ የግብርና ስራ ከእጅ ወደ አፍ ብቻ ሆነ፡፡ በትርፍ ሰዓቴ እንኳን ንግድ ብሞክር ፤ ሳይሻል አይቀርም" አላት ያሬድ ለባለቤቱ አበበች፡፡ በእጁ የተቀለለውን እንጀራ እየጎረሰ፡፡

"ሃሳብህ ጥሩ ነው፡፡ ግን ምን ዓይነት ንግድ ነው የምነግደው? አለች አበበች፡፡

ጥያቄን በጥያቄ እንዲሉ መልሶ "ቡና ይሻላል ወይስ አልባሳት?'' አላት፡፡

ሁለቱም አማራጮች ጥሩ ናቸው፡፡ ግን ከየት አምጥተህ ነው የምትነግደው ?፡፡

ያሬድ ተጨማሪ የንግድ ስራ ለመስራት እንጅ ከየት አምቶ እና ምን እንደሚነግድ እንኳን በደንብ አላሰበበትም፡፡

አልባሳት በቅርብ ባይገኝም ወደ ድሬደዋ በመሔድ ማግኘት እንደሚቻል ግን ያውቃል፡፡

"ድሬደዋ በውሎ ገባ መድረስ ይቻላል እንዴ"? አለችው፡፡

ያሬድ ድሬደዋ ሔዶባት አያውቅም፡፡ "ሰዎች ሲያወሩ ሰምቻለሁ፡፡ ውሎ ገባ አይደረስም፡፡ መኪና ከተገኘ ሁለት ቀን ቢወስድ ነው"፡፡

ያሬድ ከባለቤቱ ተስማምቶ ፤ ማምጫ ገንዘብ ለሰው አበድሮት የነበረውን ሰበሰበ፡፡ ከቤትም ትንሽ ስንዴ ሸጦ ለመነገጃ የሚሆን ገንዘብ አጠራቀመ፡፡

ታዲያ ወደ ድሬደዋ ሲሔድ ቤቱን ፣ ከብቶቹንና ባለቤቱን ብቻዋን ጥሏት እንዳይሄድ ስጋት አደረበት፡፡

ተመስገን ለቤተሰቦቹ ውሃ ሊቀዳ አህያ ላይ ጀሪካን እየጫነ ነው፡፡

"ደህና አደርህ ተመስገን" አለ፡፡ ቤቱን እና ከብቶቹን እስከሚመለስ እንዲያይለት ሊጠይቀው በጥዋት የመጣው

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደርህ ያሬድ" አለ፡፡ ጀርካን መጫኑን ተወት አድርጎ ወደ ያሬድ እየተጠጋ፡፡ የእጅ ሰላምታ ሰጥቶት ወደ ቤት ግባ አለው ተመስገን፡

"አልገባም ይሁን" ብሎ "አንተጋር ነበር የመጣሁት" አለ

"ምነው በሰላም" ?

"አይ! በሰላም ነው፡፡ አንድ ነገር ላስቸግርህ ብየ ነው የመጣሁት"፡፡

"ምን ችግር አለው የምችል ከሆነ"፡፡

"አይ! ቀላል ነው"፡፡ እኔ ወደ ድሬደዋ ለመሄድ ስለፈለግሁ ቤቴን እንድትከታተልልኝ ፈልጌ ነበር፡፡

"ምነው በሰላም ነው፡፡ ወደ ድሬደዋ የምትሄደው ?

"ለራሴ ጉዳይ ነው፡፡ ትንሽ አልባሳት ለመነገድ ስላሰብኩ ለማምጣት ነው የምሔደው ፡፡

"አይ! ደህና ነው፡፡ እከታተልልሃለሁ ግን ለምን አብረን ብቻህን እዛ ድረስ ከምትሄድ ለኔም ታስተዋውቀኝ ነበር አለ ተመስገን፡፡

"ሐሳብህ ጥሩ ነው፡፡ ግን እኔም ገና አዲስ ስለሆንኩ መጀመሪያ ልየውና የሚያዋጣ ከሆነ አብረን እንሔዳልን እስከዛ ገንዘብ አጠራቅም፡፡ ብሎት ተሰነባብተው ተለያያዩ።

እድላዊት

ሲሻለኝ ውለታቸውን በጉልበቴም ቢሆን አግዠ እከፍላቸዋለሁ ብላ አሰበች፡፡ ግን ያሰበችው ቶሎ አልሆነም፡፡

ከህመሟ ሳይሻላት እየባሰባትና እየጠናባት ሄደ፡፡ ሁለት ወር ከ18 ቀን የአልጋ ቁራኛ ሆና አሳለፈች፡፡ ምነው እዛው ጫካ ሞቼ በቀረሁ ኖሮ፡፡ እንደዚህ የአልጋ ቁራኛ ሆኘ ሰው ከማስቸገር ምን አለ ፈጣሪየ መከራና ስቃየን ከምታበዛብኝ ብትገላግለኝ?፡፡ ፈጣሪዋን እየተማፀነች እና እያማረረች ውላ በተራው ጨለማውን ተገን አድርጎ ሌሊቱ ይተካል፡፡

እድላዊት ሌሊትም ሆነ ቀን የምትተኛበት የእንቅልፍ ሰዓት በሃሳብና በጭንቀት ሳይታወቃት ቀን መሽቶ ይነጋል፡፡ በብርድልብስ ውስጥ ተሸፍና የምታለቅሰው እንባ ቢጠራቀም ዘመዶቿንና ቤተሰቦቿን ይቀብርላት ነበር፡፡

አንዳንዴ ሲጨንቃት የተሻላት ይመስላታል፡፡ ለመሄድ አስባ ትነሳለች፡፡ አሁን ልሂድ በቃ ተሸሎኛል፡፡ እናንተንም
አስቸገርኳችሁ፡፡ ተነስታ ለመሄድ ስታስብ አቅም ያንሳታል ፤ እራሷን ያዞራታል፡፡ ተመልሳ መቀመጥ አትችልም፡፡

የእድላዊት ቶሎ አለመዳንና የአልጋ ቁራኛ መሆኗ አሳስቧቸዋል ፤ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡ ምነው ፈጣሪዬ ይህችን አንድ ፍሬ ህፃን የአልጋ ቁራኛ ከምታደርግብኝ ለኔ ብሰጠኝ፡፡ እያሉ ፈጣሪያቸውን እየተማፀኑ ውለው ማደራቸው ሳያንሳቸው እድላዊት ደግሞ በሽታዋን ሳታስብ አስቸገርኳችሁ ስትላቸው የባሰ ያስጨንቃቸዋል፡፡

እባክሽን ልጄ ተለመኝኝ ; እባክሽ ስለፈጠረሽ አምላክ ; በደንብ ሲሻልሽ ትሔጃለሽ፡፡ ልጄ እባክሽ ለኔ ምንም አታስቢ፡፡ አንቺ ብቻ ዳኝልኝ፡፡ ለሁሉም ይደረሳል፡፡ ብለው ምንም እንዳታስብና እንዳትጨነቅ ይማፀኗታል ፡፡

እድላዊት በትንሹም ቢሆን እየተሸላት መጣ፡፡ መጀመሪያ ውለታቸውን ከፍየ እሄዳለሁ ብላ ያሰበችውን አረሳችም፡፡

ገና በደንብ ሳይሻላት ለመርዳት ተቻኮለች፡፡ ቡና ሲያፈሉ እኔ አፈላለሁ እያለች ወ/ሮ በሰልፏን ታስቸግራቸውም ጀመር፡፡ ቆይ በደንብ አልተሻለሽም፡፡ በደንብ ሲሻልሽ ታፈያለሽ፡፡ ቢከለክሏትም እሽ አትላቸውም ነበር፡፡

እድላዊት በቤቱ ውስጥ ያለውን ስራ በመስራት መርዳትና ማገዝ ጀመረች፡፡ ትንሽ ሲሻለኝ እሄዳለሁ ያለችውን ሰረዘች፡፡ ውለታቸውን በደንብ ለመክፈል ህሊናዋ አስገደዳት፡፡

የተባረከች ልጅ የእግዚአብሔር ቸርነት ያደረባት፡፡ የትንሽ አዋቂ በማለት ያመሰግኗትም ነበር ፤ ወሮ በሰልፏ፡፡

ከባለቤታቸው አንድ ወንድ ልጅና ሁለት ሴት ልጆችን ወልደዋል፡፡ያለመታደል ሆኖ ግን ሁለቱን ሴት ልጆቻቸውን በአንድ ወቅት በተከሰተው የኩፍኝ ወረርሽኝ በሞት ተነጥቀዋል፡፡

የሴትን ልጅ ጥቅም በደንብ ያወቁት በእድላዊት እንጅ በልጆቻቸውም አልነበረም፡፡ እርጅናቸው ገፋ ባይባልም በባለቤታቸውና በልጆቻቸው ሞት በመከራ ላይ መከራ አሳልፈዋል፡፡ አቅማቸው እየደከመ ፤ ጤንነታቸው ከቀን ቀን እየባሰባቸው ሄደ፡፡ የጤና ማጣታቸው ታዲያ አልጋ እንዲይዙ አስገድዷቸዋል፡፡

እድላዊት ከቤተሰቦቿ የተፈጠረችበትን ቀን ስታስታውስ አምርራ ትረግማለች፡፡ ቤተሰቦቿ እንደ ወ/ሮ በሰልፏ ቅን ፤ የሰውን ሃሳብ የሚረዱ ቢሆኑ ኖሮ ዛሬ ትምህርቷን ጨርሳ እሩቅ የመድረስ ፤ አላማዋና ተስፋዋ በተሳካላት ነበር፡፡

አንዴ ለመከራ የታደለች አድርጎ የፈጠራት እድላዊት፡፡ ከአልጋ ቁራኛ ተነስታ ውለታቸውን በጥቂቱም ቢሆን በጉልበቷ ከፍላ ለመሔድ ተነሳች፡፡ ግን አልተሳካላትም፡፡ ያስታመሟት ወሮ በሰልፏ ተረኛ የአልጋ ቁራኛ ሆኑባት፡፡

ጥላቸው እንዳትሄድ በእጃቸው በልታ ፣ ጠጥታ ያደረጉላት ውለታ ፤ መቼም የማይረሳ ሆነባት፡፡ ብትሔድ እንኳን  የማይቀናትና የማይሳካላት መስሎ ታያት፡፡ ከስራቸው ሆና ለማስታመም ተገደደች፡፡

ወላጅ እናቷን እንደምጠራው እማዬ ምን ላምጣሎት ? ምን ላድርግሎት ? ምን ይሻላል ? እያለች አቅሟ የፈቀደውን ሁሉ እያደረገች አስታመቻቸው፡፡

ታዲያ ስትወጣና ስትገባ አይን አይናቸውን ስትመለከት ህመማቸው ፤ ህመሟ ይሆንባታል፡፡ ሁለት ወር ከ18 ቀን የአልጋ ቁራኛ እያለች

ያደረጉላት ሁሉ በሃሳቧ ይመጣ፡፡

አይኖቿ በእንባ ይሞላሉ፡፡ ስታለቅስ እንዳያዩዋት ወደ ውጭ ወጥታ ልውጣ ልውጣ እያለ በሃይል የሚያስቸግራትን ፤ የእንባ ጎርፍ ፊቷንና አይኖቿ እስከሚቀሉ ድረስ ታዘንበዋለች፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ የራሳቸው በሽታና ስቃይ ሳያንሳቸው በእድላዊት ማሰብና መጨነቅ አንጀታቸው አልችል አለ፡፡