#ሁቱትሲ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች
፡
#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ
፡
፡
#የስደተኞች_መጠለያው_ምቾት
፡
፡
የፈረንሳዮቹ የስደተኞች መጠለያ የታጠቁ ወታደሮች የሚጠብቁት፣ ለቱትሲዎች ከለላ የሚሰጥና ሁቱዎችን የሚያገል ስፍራ ነው፡፡ ወታደሮቹ ስምንት ታንክ-መሰል ብረትለበስ ተሸከርካሪዎችን በግማሽ ክብ ቅርጽ ከትምህርት ቤቱ ሕንጻዎች ፊት ለፊት ያቆሙ ሲሆን የምሽጉን ውጨኛውን ክፍል ደግሞ ቀን ከሌት ቢያንስ መቶ የሚሆኑ ወታደሮች ይቃኙታል፡፡ እኛም ብረት-ለበስ ተሸከርካሪዎች ባሉበት ግማሽ ክብ ውስጥ ሙሉ ጊዜ ሰጥተው እንዲከላከሉንና መጸዳዳት ስንፈልግም ወደ ጫካ እንዲወስዱን ከተመደቡ ሰላሳ ወታደሮች ጋር እንኖራለን፡፡
የፈረንሳይ ወታደሮች በተደጋጋሚ ስለምንኖርበት ሁኔታ ይቅርታ ሲጠይቁን ያስቁኛል፡፡ ከመጣንበት ጋር ሲነጻጸር ፍጹም የምቾት ሕይወት በመኖር ላይ ነን፡፡ መጀመሪያ ላይ ከምንጭ ውሃ እናግዝና ገላችንንና ልብሳችንን በሳሙና እናጥብ ነበር!
ውጪ ላይ መተኛታችንን ፈረንሳውያኑ ወታደሮች እንደ ዋና መከራ ቢያዩትም እኛ ግን በደስታ ተቀብለነዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ በቆሻሻና በዛፍ ቅጠላ ቅጠል ተሸፍኜ በአለትና ድንጋይ ላይ በመተኛቴ የተነሳ እያመመኝ ብነሳም ክዋክብት ላይ አንጋጥጬ መተኛቱን ወድጄዋለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ፊት በቀኑ መጀመሪያ ላይ የማየት ያህል ነው፡፡
ምግብ እንድናዘጋጅ አይፈቀድልንም፡፡ ይህ የሆነው ትኩስ ምግብ ስላልነበራቸው ሲሆን አለማዘጋጀታችንም ለእኛ ምንም ችግር አያመጣም፡፡ ወታደሮቹ የታሸገ አይብ፣ ጣፋጭ ኮቸሮ፣ እሽግ የዱቄት ወተትና ፍራፍሬ ይመግቡናል፡፡ የምመገበው የተወሰነ ምግብ ቢሆንም ቀስ በቀስ ሰውነቴ እየጨመረ ሄደ፤ ወገቤም ወደ ውስጥ መግባቱን አቆመ፡፡
ፈረንሳውያን ሥራቸው እኛን መከላከል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ይህንን ተግባራቸውንም በሚገባ ተወጥተውታል፡፡ በምሽጉ ውስጥ በቆየሁበት ወቅት አንድም ጊዜ እንኳን በገዳዮቹ ማስፈራሪያ ደርሶብኝ አያውቅም፡፡ ሆኖም ግን ሁቱዎች ብዙውን ጊዜ በውጪው የምሽጉ ክፍል በመሰብሰብ በተደረደሩት ተሸከርካሪዎች መካከል እኛን ለማየት ይሞክራሉ፡፡ በእንስሳት መጠበቂያ ያለን እንስሶች እንደሆንን ሁሉ ያፈጡብናል … ከመጥፋት ጠርዝ ድረስ የታደነ ዘውግ ብቸኛ ቅሪቶች፡፡
‹‹እንስሳት እንደሆናችሁ ሁሉ ያዩዋችኋል፣ ግን እነርሱ ናቸው እንስሶቹ›› አለኝ የወታደሮቹ አበጋዝ አንድ ቀን ጠዋት ከደረስኩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፡፡ ፈረንሳይኛ በጥሩ ሁኔታ እንደምችል ስለተረዳ ብዙ አዋራኝ፡፡ ታሪኬን ነገርኩት፤ በጣም እንዳዘነልኝም ታየኝ፡፡ በሩዋንዳ ቱትሲዎች ያሳለፉትን፣ ታሪካችንንና የዘውግ ግጭቶችን ጣጣ ሁሉ ያውቃል፡፡
‹‹ባንቺና በኔ መካከል የሚቀር ነገር ልንገርሽ፤ የሀገሬ የርዕሰ-ብሔር ከራሱ ጋር አንዴት መታረቅ እንደሚችል አላውቅም - ጸጸቱ እንደማይገድለው›› አለኝ፡፡ ‹‹ብዙ ሁቱዎችን እንዴት ሰው እንደሚገድሉ ስላሠለጠነች ፈረንሳይ በእጆቿ ላይ ደም አለባት፡፡››
በሩዋንዳ ለተከሰተው ነገር የውጪ ዜጋ ወቀሳውን ሲቀበል ስሰማ ይህ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ለነፍሴ ጥሩ ነገር አደረገላት፡፡ ዓለም እየደረሰብን ያለውን ነገር አይቶ ለመርሳት መምረጡን በማወቄ የቄሱን ሬድዮ ስሰማ ብዙ ጊዜ ተስፋ እቆርጥ ነበር፡፡
‹‹ይህን ያህል ስለተረዳኸኝ አመሰግናለሁ›› ስል መለስኩለት፡፡ ‹‹ይህን እያደረጉ ያሉት ሰዎች በጣም መጥፎዎች ናቸው፡፡
‹‹መጥፎ? መጥፎ! ኢማኪዩሌ ከንቱ ግፈኞች ናቸው፡፡ ጭራቆች ናቸው! በደኅና ሁናቴ ላይ እንዳለሽ እንድታውቂ እፈልጋለሁ፡፡ እኔ እዚህ በሥራ ላይ እያለሁ አንዳች ጉዳት አይመጣብሽም›› አለኝ በወገቡ ላይ ያገነደረውን ጠመንጃ መታ መታ እያደረገ፡፡ ‹‹ላንቺ ከመከላከልም በላይ አደርግልሻለሁ፡፡ የተወሰነ ፍትሕም እለግስሻለሁ፡፡ አሁንም ይህ በኔና ባንቺ መካከል ይቅር እንጂ በቀል ከፈለግሽ ያንቺው ድርሻ ነው፡፡ ይፈልጉሽ የነበሩትን ወይንም ወላጆችሽንና ወንድሞችሽን የገደሉትን ሁቱዎች ስሞች ብትሰጭኝ አስገድልልሻለሁ፡፡
ያቀረበው ሐሳብ አስደነገጠኝ፡፡ በመታጠቢያ ቤቱ በነበርኩባቸው የመጀመሪያ ቀናት ሰሞን የተመኘሁት ይህንኑ ነበር፡፡ በኛ ሰዎች ላይ እየተፈጸሙ የነበሩትን ግድያዎች ቄሱ በነገሩን ጊዜ በቀልን በጽኑ በመፈለጌ ሁቱዎችን የምገድልበት ጠመንጃና መድፍ ቢኖረኝ ተመኝቼ ነበር፡፡ ያ ግን ልቤን ለእግዚአብሔር ምኅረት ከመክፈቴና ከገዳዮቹ ጋር ሰላም ከመፍጠሬ በፊት ነው፡፡
መኰንኑ ያቀረበልኝ ትክክለኛውን በቀል ነው - በኔ ትዕዛዝ የሚገድሉ የሠለጠኑና የታጠቁ ወታደሮችን፡፡ ማድረግ የሚጠበቅብኝ ብቸኛው ነገር አንድ ስም ሹክ ማለትና የቤተሰቤንና በሺዎች የሚቆጠሩትን በየጎዳናው እየበሰበሱ የነበሩትን ሰዎች ደም መበቀል ነው፡፡ በቀሉ ከልቡ የመጣ ቢሆንም በመኰንኑ ድምጽ ውስጥ ዲያብሎስ ይሰማኛል፡፡ በወቅቱ የምፈልገው ብቸኛ ነገር ሰላም ሆኖ ሳለ ይህ መኰንን በግድያ ቃል ኪዳኖች ይፈታተነኛል፡፡ እጄን ወደ ኪሴ አስገብቼ በአባቴ መቁጠሪያ
ጠቀለልኩት፡፡ ‹‹ይህን አደርግልሻለሁ በማለትህ አመሰግናለሁ -››
‹‹የምትፈልጊውን እገድልለሻለሁ!›› ለመግደል በጣም ከመጓጓቱ የተነሣ ንግግሬን እንኳን አላስጨርስ አለኝ፡፡ ‹‹በዚህ ምሽግ የምታውቂው ሁቱ ካለ ንገሪኝና እኔ ራሴ እገድለዋለሁ፡፡ ሁሉንም እጠላቸዋለሁ፡፡››
‹‹አዎን፣ እነዚህ ገዳዮች እንጂ ሁቱዎች ሁሉ ከንቱ አይደሉም መኰንን ሆይ፡፡ በዲያብሎስ ተታለዋል… ከአምላክ ርቀው ሄደዋል እና -››
‹‹ኢማኪዩሌ ሁቱዎች ከንቱ ናቸው›› እንደገና አቋረጠኝ፡፡ ‹‹ያደረጉት ከንቱ ነው፡፡ ይህ የጌታ ፈቃድ አሊያም የዲያብሎስ ሥራ እንደሆነ አትንገሪኝ - የሁቱዎች ሥራ ነው፡፡ እናም ብድራቸውን ያገኟታል፡፡ ሐሳብሽን ከቀየርሽ አሳውቂኝ፡፡ ለሌላ ሰው እኮ ልግደል አልልም፤ ታውቂያለሽ፡፡››
አምላክ የመኰንኑን ልብ በምህረቱ እንዲነካ ጸልዬ ለገዳዮቹም እንደገና ገጀራዎቻቸውን እንዲጥሉና የእግዚአብሔርን ምኅረት እንዲለምኑ ጸለይኩ፡፡ የመኰንኑ ንዴት በሩዋንዳ የጥላቻና ያለመተማመኑ ዑደት በቀላሉ እንደማይሰበር እንዳስብ አደረገኝ፡፡ እንዲያውም ግድያው ካቆመም በኋላ በእርግጠኝነት የባሰ መራር ሁኔታ ሊኖር ይችላል፤ ወደ ባሰ ሽብር የሚፈነዳ መራርነት፡፡ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ምኅረት ብቻ ያንን አሁን ከመከሰት ያቆመው ይሆናል፡፡ በምንም ዓይነት መንገድ አምላክ ቢያስቀምጠኝ ያንን ማየት እችላለሁ - ሌሎች እንዲኖሩ ማድረግም የሕይወቴ ሥራ ዋነኛ ክፍል ይሆናል፡፡
በቀጣዩ ቀን መኰንኑ ቃሉን መጠበቁን አሳየ - ሁቱዎችን በእውነት ይጠላ ኖሯል፡፡ አንድ እየደማ ያለና ‹‹የዘር ጭፍጨፋ ተራፊ ነኝ፤ የቆሰልኩትም ከቱትሲ አማጽያን ጎን ስዋጋ ነው›› የሚል ሰው ወደ ምሽጉ ገብቶ ይዘዋወራል፡፡ መኰንኑ ግን ስላላመነው ወታደሮቹ አንበርክከውና ጠመንጃዎቻቸውን ራሱ ላይ ደግነው እንዲጠይቁት አደረገ፡፡ መጀመሪያ ላይ ሲጠይቁት የኢንተርሃምዌ አባል መሆኑን ካደ፡፡ ከብዙ ምርመራ በኋላ ግን ተስፋ ቆረጠና ተናዘዘ፡፡ መኰንኑም ለወታደሮቹ ራሱን ሲነቀንቅላቸው ጎትተው ወሰዱት፤ ከዚያ በኋላም በጭራሽ አላየነውም፡፡ ከወታደሮቹ አንደኛው በሌላ ጊዜ ሰውዬው የኢንተርሃምዌ ሰላይ እንደሆነ ማመኑን ነገረኝ፡፡
‹‹ስለሱ አትጨነቂ - ከአሁን በኋላ አያስቸግርሽም›› አለኝ፡፡
ለአክስቶቼና ለልጆቻቸው