#ሮዛ
፡
፡
#ክፍል_አራት (🔞)
፡
፡
#ከጋዳፊ_ጋር_ድንኳን
ጥር 24/2001
እሁድ ጥዋት 2፡25 ላይ ሞባይሌ አቃጨሰች፤ በስስ ፒጃማ አልጋዬ ላይ እንደተጋደምኩ፣ ፍሩት ፓንቼን
እየጠጣሁ፣ አል ጀዚራ እየተመለከትኩ ነበር፡፡እሁድ ጠዋት ሀልጊዜም እንዲሁ ነኝ፡፡ ከራሴ ጋር ጓደኛ የምሆንባት የተባረከች ማለዳ ናት እሁድ፡፡ የተጋደምኩበት አልጋ ሲነዝረኝ ስልኬ ቫይብሬት እያደረገች እንደሆነ ተረዳሁ፡፡ አይኔን ከቴሌቪዥኑ ሳልነቅል ስልኬን በዳበሳ ለማግኘት ሞከርኩ፡፡ እውነቱን ለመናገር በዚህ ሰዓት ማንኛውንም የስልክ ጥሪ ባላስተናግድ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም እሁድ ጠዋት ነው፡፡
እሁድ ጠዋት ለምን ከመንግስተ ሰማይ አይደወልም ስልኬን ለማንሳት ፍላጎት የለኝም፡፡ እሁድ ጥዋት የኔ ናታ፣ የብቻዬ፡፡
ሌሎች ሰዎች ቤተክርስቲያን ለመሳለም ሲሄዱ እኔ ሳምንቱን ሙሉ ወንድ ከሚባል ቀፋፊ ፍጡር ጋር የሰራሁትን ሀጥያት ለማሰርየት እተጣጠባለሁ፤ ከዚያም ለብቻዬ አልጋዬ ላይ ተጋድሜ ሂሳብ
አወራርዳለሁ፤ ጌታን እማጸናለሁ፡፡ ቅልል ይለኛል፡፡ ጌታዬ “ኦልሬዲ” የልቤን ስለሚያውቅ የሀጥያቴን
ጥልቀት ለማሳየት የግድ ማልቀስ ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ ማልቀስ ግብዝነት ነው፡፡ እሁድ ጠዋት ለምን እንደሆነ አላውቅም መቅደስ የገባሁ ያህል ሰላም ይሰማኛል፡፡ እሁድ ጠዋትን የማጣጥማት አልጋዬ ላይ ሆኜ ሳሳልፍ ብቻ ነው፡፡ ወትሮ ስልኬን እንኳን አላበራም ነበር፡፡ ዛሬ ሳላጠፋው ረስቼው ነው የሸቀብኝ
ጥሪውን ችላ ብለውም ስልኬ አንሶላዬን እየነዘረች ረበሸችኝ፡፡ በስንት መከራ በዳበሳ ፈልጌ አገኘኃት፡፡
ጥሎብኝ ሪሞት ኮንትሮል፣ የቤት ቁልፍና ስልክ ሁልጊዜ ይሰወሩብኛል፡፡ እበሽቃለሁ፡፡ ሶስቱ ነገሮች ከኔ
ጋር በግድ አኩኩሉ በመጫወት እኔን ሊያበሽቁ የተፈጠሩ ቁሳቁሶች አድርጌ ነው የማያቸው፡፡
ማንም ይሁን ማን በደዋዩ እናደድበታለሁ ብዬ ነበር፡፡ ደዋዩ"ኡስማን ዘ ፒምፕ መሆኑን ሳውቅ ብሽቀቴ ተነነ፡፡ኡስማን boss ነው፡፡ ኡስማን kingነው፡፡ ኡስማን የጉሮሮ ገመድ ነው፡፡ደፍረን የማንበጥሰው የጉሮሮ ገመድ ሰሞኑን እረፍት አልባ አድርጎኛል፡፡የአፍሪካ ህብረት ጉባኤው ከመጀመሩ አንድ ሳምንት አስቀድሞ ነው የኡስማን ወፎች የሆንን ሁላ ጠብ እርግፍ ስንል የከረምነው፡፡ እስካሁን ከአልጄርያ
ዲፕሎማት ጋር በሀርመኒ ሆቴል(ለሁለት ቀናት)፣ከቤኒኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ባልደረባ ጋር ለአንድ ሌሊት በሂልተን ሆቴል፣ከፈርጣማው እና የመቶ ሜትር ሯጭ ከሚመስለው የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ባልደረባ ጋር ለሁለት ቀናት በጁፒተር ሆቴል፣ እንዲሁም በጉባኤው ላይ በታዛቢነት ለመታደም ከመጣ ሬኮስ
ዶልፊኖ ከሚባል የአውሮፓ ህብረት የዲፕሎማቲክ አታሼ ጋር አንድ ሌሊት በኢንተር ኮንተነታል ሆቴል አድሬያለሁ፡፡
እድሜ ለኡስማን ዐስር ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 4200 ዶላር አካባቢ ቦርሳዬ ውስጥ ገብቷል ይህ ብር እንዴት እንደገባ
ብቻ ነው የማውቀው እንጂ እንዴት እንደጠፋ አላውቅም። ከነ ማኪ ጋር ስንገባበዝ ሸራተን ኦፊስ ባር ስንጫጫስ፣ ምን ስንል፣ ድምጥማጡን አጠፉነው፡፡ሁላችንም እንዲህ ነን።ገንዘብ በርከቶልን አያውቅም፡፡ ዶላር ካልበረከተልን ምን ሊበረክትልን እንደሚችል አላውቅም።
ጥሩ እንግሊዝኛ ስለምናገር ፣አረብኛና ፈረንሳይኛን ደግሞ እንደነገሩ ስለምሞክር ኡስማን ከሌሎች ወፎች
በተሻለ እኔን ለዲፕሎማት ከላይንቶቹ ማቅረብ ይመርጣል። ክላይንቶቹ በአመዛኙ በኔ ደስተኞች ናቸው ያንን የምረዳው ከሚሰጡኝ ጉርሻ ነው ለምሳሌ ናይጄርያዊው የፕሬዘዳንቱ ረዳት "ወደ አቡጃ አብረን እንሂድና አፓርታማ ገዝቼ ላኑርሽ" ብሎኛል።
ሶስት ሚስቶች እና 15 ልጆች እንዳሉት ግን አልደበቀኝም፡፡ለጊዜው “አስብበታለሁ” ብዬው ተለየሁትና
ትላንት ምሽት ደጋግሞ ሲደውልልኝ ስልኬን አላነሳሁለትም፡፡ለምን እንደሆነ አላውቅም ሰውየው ቀፈፈኝ፡፡ ለነገሩ ከበፊትም ለናይጄሪያውያን ጥሩ አመለካከት የለኝም፤ከልጅነቴ ጀምሮ ድግምታም እንደሆኑ ስሰማ ነው የኖርኩት፡፡
የአልጄሪያው ሰውዬ ደግሞ የሚያምር የእጅ አምባር ሰጠኝ፡፡ በቅድሚያ ለኔ ሳይሆን ለሚስቱ ሊወስድላት ገዝቶት እንደነበረና ስላስደሰትኩት ግን ለኔ ሊሰጠኝ እንደወሰነ ሲነግረኝ በሆዴ «አይ የአረብ ነገር!» አልኩኝ፡፡ ላልቀበለው ሁሉ ፈልጌ ነበር፡፡ በኋላ ሳስበው ብልጥ መሆን እንዳለብኝ ገባኝ፡፡ አረብ
እስከሆነ ድረስ ለሚስቱ ሌላ ገዝቶ ይሰጣታል በሚል ተቀበልኩት፡፡
የምትነዝረዋን ሞባይሌን ሳነሳት እረፍት አገኘሁ ፤ ኡስማን ራሱ ገና ከአልጋው የተነሳ አልመሰለኝም፤ ድምጹ እንቅልፍ ተጭኖታል፡፡
ሮዝ እንዴት አደርሽ?በጥዋት ስለቀሰቀስኩሽ ይቅርታ
“ችግር የለውም ኡስማንዬ፤እንቅልፍ ላይ አይደለሁም፣አንድ የአልጀዚራ ዶክመንተሪ እያየሁ ነበር "አሪፍ
ዛሬ ምሳ ሰአት ላይ መገናኘት አለብን”
ድምጹ ውስጥ ትዕዘዝ የሚመስል ጥንካሬ አየሁበት፡፡ አንዳች ጥርጣሬ ወረረኝ፡፡
“ምነው ኡስማን!በሰላም ነው?”
በሰላም ነው ሮዝ!የስራ ጉዳይ ነው፣ያው በስልክ የሚወራ ስላልሆነ ነው
ሆቴል ሰባት ሰዓት የተለመደችው ቦታ ላይ፤ ግብዣው በኔ ነው
ሳቅኩኝ፡፡
የሳኩት ግብዣ ሆኖ ስለማያውቅ ነው፡፡ ኡስማን ወፎቹን በፍጹም አስከፍሎ አያውቅም፡፡ ሲበዛ ይንከባከበናል፡፡ ስነ ስርዓት ያለው ሰው ነው፡፡
የሳኩበትን ምከንያት ነገርኩት፡፡ ከስልኩ ማዶ ኡስማን ፈግ ሲል ታየኝ፡፡
ኡስማን በዚህ ፈገግታው ብቻ ኪሱ ያስገባው ረብጣ ዶላር ባንክ ይቁጠረው፡፡ እርጋታውና ፈገግታው
ከንግግር በላይ ሰው ያሳምናል፡፡ የኡስማንን ፈገግታ አይቶ እምቢ ማለት possible አይደለም፡፡ ከንፈሩ
ሲላቀቅ የሆነ ማጂክ ይረጫል፡፡ እሺ የሚያስብል ማጂከ፡፡ ኡስማን አይደለም በአካል በስልክ ውስጥ የማይታይ ፈገግታ ታድሏል፡፡ ሰዎች እምስ እየቸረቸረ ነው የሚኖረው” እያሉ ያሙታል፡፡እኔ ግን እላለሁ ኡስማን ፈገግታውን እየቸረቸረ ነው የሚኖረው፡፡
ከኡስማን ጋር ካለኝ የስራ ግንኙነት ሁለት ነገሮችን ተረድቼያለሁ፡፡በራስ መተማመን እና ፈገግታን፡፡ ሁለቱ ነገሮች ካሉ ቃላት ጉንጭ ከማልፋት ሌላ ዋጋ የላቸውም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ብዙ በመናገር የሰውን
ሀሳብ ማስለወጥ የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡ እንደ ኡስማን ያሉት ግን በራስ መተማመንና ፈገግታን
በመርጨት ብቻ ራሳቸውን ያስተዳድራሉ፡፡ኡስማን“…ሰው አንተ የምትናገረውን አይደለም የሚሰማህ…መስማት የሚፈልገውን ነው የሚሰማህ…ስለዚህ ብዙ መናገር ድካም ነው” የሚላት ነገር እውነት ሳትሆን አትቀርም፡፡
ብዙ ወንዶች “እንቺ ትንሽ ከሌሎች የተለየሸ ነሽ” ይሉኛል፡፡ ከሌሎች ሸሌዎች ማለታቸው ነው፡፡ ለምን እንደዚያ እንደሚሉኝ አውቀዋለሁ፡፡ ኮንፊደንሴ ስለሚገዛቸው ነው፡፡ እነሱ ብዙ ሲያወሩ እኔ ብዙ ሳዳምጣቸው በመጨረሻ በራሳቸው ጊዜ እነሱ ራሳቸውን ከኔ አንሰው ያገኙታል፡፡ ወይም እንደዚያ
እንዲሰማቸው ይገደዳሉ፡፡ብዙ የማዳመጥ፣ ፈገግታን ያለመቆጠብ እና የመረጋጋት ክህሎትን በከፊል
ያዳበርኩት ከኡስማን ይመስለኛል፡፡ ከአለቃዬ ከኪንግ ኡስግን።
ከልምድ እንደማውቀው ብዙዉን ጊዜ ኡስማን ደውሎ "በአካል ተገናኝተን ማውራት ይኖርብናል!” ካለ
ጉዳዩ ከባድና በጥብቅ ምስጢር የተያዘ ነው ማለት ነው፡፡የዛሬው ምስጢራዊ ጕዳይ ምን ሊሆን ይችላል? ብዬ አሰብኩ፡፡ በርካታ ሀሳቦች በአእምሮዬ ጓዳ ተመላለሱ፤ኡስማን ቆቅ ነው፤ለመረጋጋት የሚያስችል ፍንጭ እንኳን አይተውም፡፡አንድ የማይገረሰስ ቋሚ መርህ አለው፤”ሁሉን ምስጢር እስክናገር ምንም አልናገርም!"የሚል፡፡ ደግሞ “ግማሽ ሚስጢር ከሙሉ ሚስጢር ይበልጥ አደገኛ ነው” ይላል፡፡ ምን ማለቱ እንደሆነ

👍9❤1