አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
495 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እንደነገርኩሽ_ነው 
         
        አፍሽም ለብቻው - ስሙን እያወጣ ፣
        ጆሮሽም ለብቻው - ስሙን እያወጣ ፣
        ወየው ! ወየው ! እንጂ … ወዬ ! የሚል ታጣ

እግዜሩም! እንደ ሰው!
         ባለመስጠት ሞላ ፣ ከመስጠት ጎደለ ፤
         ብጠራው? ብጠራው? 'አቤት' አልል አለ ።
ማለትሽን ሰምቼ
… እኔ ምልሽ...
ምስኪን እግዜርሽን!
         ካመልሽ አዛምደሽ ፣ ከምትጠረጥሪው ፣
         እስቲ ቅፅሉን ተይና  በዋና ስም ጥሪው ።

ሰሚን ሲደልሉ !
ጠሪን ሲበድሉ !
ለግዜሩም! 'ቅፅል-ስም' አወጡለት አሉ ።

እናልሽ  . . .
በልጥፍጥፍ መአት ዋናው ገጽ ፈረሰ ፤
ስም አውጪው ቢበዛ አቤት ባይ አነሰ ።

ደግሞ . . .
አመሌን ! አመልሽን ! ለማያውቁ ሁሉ ፣
"ጠርቼው አልመጣም" ትይኛለሽ አሉ ።

         እሷ የስም ሀብታም !
         ትጠራው አታጣ ! ትሸኘው አታጣ !
እኔ ባለ አንድ ስም ― ምን ሰምቼ ልምጣ ?

         እሷ የስም ሀብታም !
         ስትገዛ በደርዘን ! ስትሸጥ በደርዘን !
ይኸው ከስረን ቀረን ― አንድ አንድ ስም ይዘን።

         ሰሚን ሲያጣጥሉ ― ጠሪን ሲያቃልሉ ፤
         ስም አምራቾች ሞሉት ― ጉራንጉሩን ሁሉ ።

      ]  የላክሽው ፎቶ አንሺ  [
በጥላሽ ከልሎ ፣ ባንቺ ብርሃን ኩሎ ፤
ፎቶ ነስቶኝ ሄደ ― ፎቶ አነሳሁ ብሎ ።

        ፓ!  ፓ¡  ፓ!  ካሜራ ¿  ...  ኧረረ ! !  ካሜራ ¡ ¡
                     በሌሉበት ሁሉ ማንሳት የማይራራ ¡
                     ሊያውም በክት ልብስ ጥለት አዛንቄ …
                     ሊያውም በጀግና ልብስ በኒሻን ደምቄ …

             ... … እያገላበጠ … …

     'ተዟዟርር' እያለ ― ሲያነሳኝ ሰንብቶ ፣
              በትኖልኝ ሄደ ― ልብስ የሌለው ፎቶ ።
                      ካሜራሽ ስልጡኑ ¡ ካንቺ እኩል ያወቀ ¡
                                  ፎቶ ያጥባል ! አሉኝ … ልብስ እያወለቀ ።

እንደነገርኩሽ ነው

              የማንም ያልሆነን ― ያንተ ነው ተብዬ ፣
              በምስልሽ ፈንታ ― ፍሬምሽን ሰቅዬ …
                       … ግራ የገባው ዓይኔ …
               በከልካይ መነፅር ከቧልት ይፋጠጣል!
                       … ካሽሙር ይፋጠጣል …
                   የጀግና ፎቶዬ ከሱቅሽ ይሸጣል ።
.
                 አንቺ የመልክ ሀብታም ፤ ቀለም የተረፈሽ ፣
                 አንቺ የመልክ ሀብታም ፤ መስመር የተረፈሽ ፣
                 የተኩላዎች ክፋት ― በበጎች ስም ፅፈሽ ፤
                 መጥቀሻል ይሉኛል ― በምኞት መሠላል ።
       … ግድየለም ምጠቂ …
                 ቅዠት ሲደጋገም ― ከህልም ይመሳሰላል ።

እንደነገርኩሽ ነው
      ቧልተኛው ዶክተርሽ በስላቁ ፈዞ ፣
             'አከምኩህ' ይለኛል ¡¿
      የራሱን መዳኒት ለመምተኛው አዞ ።

የመምተኛሽ ደግሞ …
       ካኪምሽም ብሶ ሁለቴ ገደለኝ ፤
               ተመረመርኩልህ ይቺን ዋጣት አለኝ።
                       በታመመ ልኩ ― ጤና ሲሰፍርልኝ …
                                በሽተኛ ልጅሽ ― ተመረመረልኝ ።
.
መድሃኒት ከሰረ
      ጤና ተቃወሰ በሽታ ተስፋፋ
              ግብረ ገብ ጎደለ ስነ ምግባር ጠፋ
                             ወዘተ . . . ወዘተ . . .
                  ጉባኤ ሰብስበው ሰበብ ሲያዳምቁ
                              እኔን የገደለኝ ከበሽታው ይልቅ
                                        በሽተኛው በውል አለመታወቁ ።

ያንቺማ ዓይነቱ
ማድማቱን ደብቆ ፣ መድማቱን ለብቻ እያስመረመረ ፤
             ፈውስ በስም ብቻ ተድበስብሶ ቀረ ።

በኔ"ና አንቺ ዓለም … ከማዘን ! ― ማሳዘን !
       ከመሳት ! ማሳሳት ! ― ከደም ማነስ ! ደም ማሳነስ !
               ከመርሳት ! ማስረሳት ! በእጥፍ ይቀድማል ፤
                       ከበሽታው ይልቅ … በሽተኛው ያማል ።
.
ኧረ ያንቺስ ሞያ
       ትንሽ እየሰፋ ― ብዙ መቅደድ ያውቃል ፤
       ክርሽ ስራ ፈትቶ ― መርፌሽ ብቻ ያልቃል ።
ኧረ ያንቺስ አራጅ ቅርጫሽን ሳንበላው …
" ያልቅብሻል " አሉ! ሞረድ እና ቢላው ።
.
... እንደነገርኩሽ ነው

                        ጎዳናው ሳይጠበን አመል እያጋፋን !
                        እንኳን አካሄዱ ― አቋቋሙ ጠፋን ።

🔘በረከት በላይነህ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍5511👏6🥰1