#አዎ !
ለጊዜውም ቢሆን፤ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ ፤ ወደፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፤ ሚስቱን ያስረግዛል
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ለጊዜውም ቢሆን፤ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ ፤ ወደፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፤ ሚስቱን ያስረግዛል
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
YouTube
አትሮኖስ_ Tube
Share your videos with friends, family, and the world
👍10🔥4
#አዎ_ትመጣለች
ትመጣለች እያልሁ
ቀኔን እንደ ምግብ ስበላው አኝኬ
አዝኖልኝ ነው
መሰል አትመጣም የሚል ቃል ይልካል አምላኬ
ሰይጣን ደግሞ በጎን ቄጠማ ነስንሶ
ትመጣለች ጠብቅ
ብሎ ይነግረኛል ቃሉን አለስልሶ
አውቃለሁ እውነት ነው
ፈጣሪ ያለው ቃል አይስትም ሚዛኑን
ሰይጣን ስግብግብ ነው
ቀን እየነጠቀ ያስረዝማል ቀኑን
ቢሆንም
ቢሆንም
እውነት እንደ ኮሶ እያንገሸገሸኝ አልጠጣም ደፍሬ
ተስፋን በገሃዱ እጋታለሁ እንጂ ከውሸት ቆንጥሬ
አዎ ትመጣለች
እውነቱን እያወቅሁ አላምንም እውነቱን
ቀን የተቀማ ሰው
ሃሰትን ተግቶ ተስፋን እየጠጣ ያረዝማል ህይወቱን
ሰይጣን ትመጣለች አይደል?
🔘✍️በላይ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ትመጣለች እያልሁ
ቀኔን እንደ ምግብ ስበላው አኝኬ
አዝኖልኝ ነው
መሰል አትመጣም የሚል ቃል ይልካል አምላኬ
ሰይጣን ደግሞ በጎን ቄጠማ ነስንሶ
ትመጣለች ጠብቅ
ብሎ ይነግረኛል ቃሉን አለስልሶ
አውቃለሁ እውነት ነው
ፈጣሪ ያለው ቃል አይስትም ሚዛኑን
ሰይጣን ስግብግብ ነው
ቀን እየነጠቀ ያስረዝማል ቀኑን
ቢሆንም
ቢሆንም
እውነት እንደ ኮሶ እያንገሸገሸኝ አልጠጣም ደፍሬ
ተስፋን በገሃዱ እጋታለሁ እንጂ ከውሸት ቆንጥሬ
አዎ ትመጣለች
እውነቱን እያወቅሁ አላምንም እውነቱን
ቀን የተቀማ ሰው
ሃሰትን ተግቶ ተስፋን እየጠጣ ያረዝማል ህይወቱን
ሰይጣን ትመጣለች አይደል?
🔘✍️በላይ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍11❤5😢1
#አዎ_እሱ_ጋ_ያመኛል
ትንሽ ስትቀማምስ እና ሞቅ ሲላት “እኔ ጀብራሪት” ስለምትል የሰፈር ጎረምሶች እና ውሪ ሕፃናት ከመንገድ ሲያገኟት ትንሽ
ራቅ ብለጡ ጀብራሪት! ይሏታል
ካልጠጣች ምንም አትልም፤ ሞቅ ካላት ግን ቀኝ እጇን ወደላይ ሰቅላ መዳፏን ጨብጣ “እኔ ጀብራሪት የኩራባቸው ሚስት... የዛ ወንዳወንዱ... የዛ ምሁር!" ትላለች... አንገቷን ወደላይ እያሰገገች፣ አይኗን ፈጠጥ፣ እግሯን ራመድ እንደማድረግ እያለች፣ ትከሻዋን ወደ ቀኝ እና ግራ እየወዘወዘች ትፎክራለች።
ጀብራሪት የሚሏት ጎረምሳ እና ውሪ ሕፃናት ይዝናናሉ፣ ይፈግጋሉ፤ ሌላው መንገድ ላይ ያላስፎከራት ጀብራሪት ሲላት ስትፎክር ቤቷ ትደርሳለች።
መጠጥ ካልቀማመሰች ትክዝ፣ ቁጥብ፣ ጭምት ማለት መገለጫዋ ነው። ጠይም ገጿ ቀልብ ሰጥቶ ለሚመለከታት እርጅናዋ እና ሐዘኗ ያላደበዘዘው በወጣትነቷ የነበረውን ቁንጅና ከመናገር አይሰንፍም።
አታቲ አክስቴ ናት፤ በልጅነቴ እናቴ ስትሞትብኝ ልታሳድገኝ አምጥታኝ እንደሆነ ተነግሮኛል። እናቴን ሆነ አባቴን አላስታውሳቸውም፤ የማውቀው አታቲዬን እና ጋሽዬን ነው።
የኔ ስም ዕድል ቢሆንም አታቲዬ ዕድሌ ትለኛለች። አንቺ ባትኖሪልኝ የምትለኝ ስለሚመስለኝ ደስ ይለኛል። ጡረታ ከመውጣቷ በፊት ገንዘብ ሚኒስቴር ነበር የምትሠራው፤ የድሮ አስራ ሁለተኛ ክፍል ምሩቅ ናት።
ኩራባቸው የሚባል ባል ነበራት፤ ስድስተኛ ክፍል እያለሁ ሞተብን። ስለ ገዳዮቹ እርግጡን የነገረን የለም። ወደ ቤት ሲመጣ እኛ ቤት መታጠፊያው አስፋልት ጋ ገድለው ጣሉት። ከየትምህር ቤት እየመጣሁ ሳለሁ ግርግር፣ ጩኸት ተቀበለኝ ለማጣራት ሰው ወደ ተሰበሰበበት ስጠጋ አታትዬ
የወደቀ የኩራባቸው ሬሳ ላይ እየተንከባለለች ትጮኻለች። ሁኔታዋ እስከዛሬ ድረስ መጥፎ ትውስታዬ ውስጥ ተወሽቋል... ከዛ ጊዜ በኋላ ብዙ ደም ሳይ ያዞረኛል፣ እረበሻለሁ። ብዙ ሰው የከበበው፣ ሁካታ ነገር ስመለከት የኔ የሆነ ሰው ጉዳት ደርሶበት፣ ጎድተውት እየተለቀሰ ይመስለኛል። ብርክ ይይዘኛል። ከሰፈሬ፣ ካደግኩባት ከተማ እንኳን ብርቅ ሁካታ፣ የሰው ጋጋታ ክብ ሰርቶ ብመለከት ከመረበሽ ስሜት መላቀቅ አልተቻለኝም።
ማታ ዱዲ ብሎኝ፣ ሱቅ ልኮኝ፣ እራት ስንበላ አጉርሶኝ፣ አደግሽልኝ እያለ በእድገቴ እየፈገገ አምሽተን፤ ጠዋት ጎህ ሲቀድ ተነስተን ቁርሳችንን ተቋድሰን፤ የትምህርት ቤት ክፍያ ሰጥቶኝ፤ ግማሽ · መንገድ ትከሻዬ ላይ መዳፉን አንተርሶ ጥቂት መንገድ የሸኘኝ የእኔ ጋሼ ደም ለብሶና መሬት ላይ ተዘርግቶ የማየው ሰው ነው የሚለውን ነገር በምን መንገድ የልጅ ጭንቅላቴ እንዳመነ ባላውቅም፤ እንጃ ብቻ አፌን ከፍቼ፣ መሬት ላይ ተደፍቼ በደም የጨቀየውን ውሃ ሰማያዊ ሸሚዙን የሙጥኝ ይዤ ተንሰቀሰቅኩ።
ጋሼ ገዘፍ ያለ መካከለኛ ቁመት የነበረው፣ ጺማም ጸጉሩን የሚያጎፍር አፍሮ ነው። በሽራፊ ሰከንድ ያየው ሰው እርጋታውን፣ የጺሙን ያህል መታየት የሚቻልበት ነበር። ቤታችን ኮርነር ጋ ያለው መጽሐፍ የተደረደረበት መደርደርያ ጋ ያለው ጠረጴዛ እና ወንበር ላይ ተቀምጦ ብዙ ጊዜ ያነባል፣ አንዳንዴ ይጽፋል፡፡
አታቲዬ ጋሺዬ ምንድን ነው የሚያጠናው? ይማራል እንዴ?
ፈገግ ትልና “ጋሼ እኮ ጸሐፊ ነው" ፊት ለፊት ከድርድር መጽሐፉ ጎን የተከማቸውን ጋዜጦች እየጠቆመች “እነዛ ጋዜጦች ላይ ይጽፋል፤ ያኛው ሦስተኛ ድርድር ላይ ለብቻቸው የተቀመጡት መጽሓፍት እኮ የእሱ መጽሓፍት ናቸው" ትለኛለች።
ያ ሁሉ!
“አራት ናቸው እኮ፤ ሦስት ሦስት ቅጂ ተደርጎ ስለተቀመጠ ነው"
ግን እኮ አንዱ ራሱ ወፍራም አይደል እንዴ?
ስስ የተሰሰተ የሚያበረታታ ፈገግታ በጠይም ፊቷ ላይአርብባ
“በእርግጥ አዎ”
“ግን መጻፍ እና ማንበብ ይገናኛል እንዴ?”
“በደንብ እንጂ! ጎበዝ አንባቢ ያልሆነ ጎበዝ ጸሐፊ አይሆንም፡፡ ምናብ ብቻውን ሩቅ አያራምድም፤ ቁንጽል ያደርጋል ይል ነበር የኔ ኩራባቸው”
ዝም ብዬ ያልሽው አልገባኝም፣ አብራሪልኝ ተማጽኖ በሚመስል ሳያት
"ይኼውልሽ ዕድሌ በምትሠሪው ሥራ ታዋቂ፣ ጎበዝ፣ ዝነኛ ለመሆን ሥራው ከሚያስፈልገው ትጋት በላይ ካልኖረሽ በሥራው ላይ ከተሰማሩት የበለጠ ማማ ላይ አትወጪም፤
በእርግጥ ያኔ የነገረችኝ የዛሬን ያህል እውነትነቱ ልቤ ውስጥ አልሰረጸም ነበር፡፡
ተመሳሳይ የቃል እና የሐሳብ ትርጉም በዘመን እና በሁኔታ ጥንካሬው እና ትርጉሙ ይለያይ የለ? አታቲ እና ጋሼ የሚዋደዱ፣ የሚከባበሩ እንደነበር ነፍስ ሳውቅ የበለጠ ተገልጦልኛል። ጋሼ አታቲዬን እንደ ትልቅ ልጁ ነበርየሚንከባከባት፤ እንደ እናት ስትሆን ቆይታ ከውጪ ፌስታል ይዞ ሲመጣ ፈንጠዝ እንደማለት ዓይነት ከተቀመጠችበት አልያ ከቆመችበት ተስፈንጥራ ፌስታሉን ትቀበለዋለች፤ እንደዛ ስትሆን ታላቅ እህቴ ነው የምትመስለኝ፡፡
ከውጪ ሲገባ ወይ ከውጪ ስትገባ ሁሌ ግንባሯን ይስማታል። አንዳንዴ ለእኔ ያኔ የማይገባኝን የጻፈውን በወፍራም ጎርናና ድምጹ በጣም ረጋ ብሎ ቴፑን ለስላሳ ሙዚቃ ከፍቶበት ያነብላታል፤ እኔ እንደማጠና መጽሐፌ ላይተደፍቼ ጆሮዬን ደቅኜ እሰማለሁ።
አታቲ ስትሰማው ትቆይ እና “ፓ አንተ እኮ ምድር ባትመጣ ታጎድላለህ!” ትለዋለች።
አንዳንዴ ደግሞ ሲያነብላት ታጨበጭባለች ወይም ታቅፈዋለች፤ አንብቦላት ያልተደመመችበትን ቀን አላስታውስም።
እጅግ አልፎ አልፎ ጽሁፉን ካነበበላት በኋላ ይሟገታሉ፤ በእርጋታ ይሰማት... ይሰማት እና ያብራራል፤ ትሰማዋለች። ሙግታቸው የጎበዝ አስተማሪ እና የጎበዝ ተማሪ ወይም ደግሞ "ሆነ የሚዋደዱ የታናሽ እና የታላቅ ዓይነት ነው። ያኔ
የሙግታቸው እና የውይይታቸው ኮንተንት አይገባኝም ነበር፣ ሁኔታቸው ብቻ እንጂ። ከእነሱ ጋ መኖር ያስለመደኝ ነገር ቢኖር ረጅም ሰዓት መስማት እና ያልገባኝን ነገር ለመረዳት ስል በትህትና መጠየቅን ነው።
አታቲዬ ጋሼ ከሞተብን በኋላ በቀስታ አረቄ ውስጥ መሸገች።
ትንሽ ቀማምሳ እቤት ትመጣና
“ዕድሌ” ትለኛለች ወይ አታቲዬ
“በጣም ጎበዝ፣ በጣም ተንከባካቢ፣ በጣም ጀግና እና ታታሪ እንዳታገቢ እሺ... ድንገት ካጣሺው ትዝታው እና እጦቱ አያራምድሽም”
እሺ አታቲዬ
“ዕድሌ…”
አቤት አታቲዬ
“ስታገቢ ተራ፣ ከሰው የተለየ . ጉብዝና ያላየው፣ የትም የሚገኝ፣ የትም ያለ፣ ከብዙ ሰው የማይለይ፣ መርሕ እና ግብ ያልታጨቀበት አግቢ እሺ፤ ብታጪው እንኳን ማንነትሽ አይናድም... እሺ ዕድሌ”
እሺ...እሺ...አታትዬ
አንድ ዕለት ፀሐይ አዘቅዝቃ ሳለች ንጋት ለምሽት እጅ ለመስጠት በእርጋታ ስትጣደፍ ቤታችን ደረስኩ ቤታችን በትንሹ ገርበብ እንዳለ ነበር፤ የሚያስገባኝን ያህል በቀስታ ገፍቼ ስገባ አታቲ ሽሮ ከለር ዕድሜ ጠገብ አጀንዳ እያነበበች በለሆሳስ ስታለቅስ ደረስኩባት፤ ቀስ ብላ ፊቷን በሌለሁበት አቅጣጫ አዙራ በሻርፕ እንባዋን እንደዳበሰች እንቅስቃሴዋ ነገሮኛል... እንዳላየሁ ሆኜ የኔ አታቲ ደህና ነሽ ስላት?
“ደህና ነኝ ዕድሌ” አለችኝ ምንም ስሜቷን የሚያውክ ሐዘን ውስጥ እንዳልነበረች ለማስመስል እየሞከረች።
ማበስ የማንችለውን እንባ፣ ምንጩን የማናደርቀውን ሐዘንን እንዳላዩ ከማየት በቀር የምንጋፈጥበት ምን አቅም አለን!? በድምጻችን ውስጥ እኔ አለሁልህ/ሽ ከማለት በቀር ምን እናደርጋለን? በሌላ ቀን ቤት በሌለችበት ዕለት ጠብቄ ስታነበው የነበረውን አጀንዳ በሦስተኛ ረድፍ አካፋይከተደረደረው መጽሐፍ ጀርባ ካለው ሁለተኛ ረድፍ ውስጥ ፈልጌ አገኘሁት፤ በሚያምር የጋሼ እጅ ጽሑፍ የተጻፈ ነበር፡፡
አጀንዳውን እንደዘበት ስከፍተው እንዲህ የሚል አገኘሁ...

❤26👍7