አትሮኖስ
278K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
455 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ምንትዋብ ከተንሴ ማሞ ጋር በተደረገው ውጊያ በእሱ ሆነ በእሷ በኩል ያለቀው ሰው ብዛት በአእምሮዋ እየተመላለሰ እያደር ሰላም ነሳት። ሰላም በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ይበልጥ እንድትገነዘብ አደረጋት። ሰላምን በሃገሯ ውስጥ ለማረጋገጥ
የበለጠ ጠንክራ መስራትና የልጇን መንግሥት ማደላደል እንዳለባት
የበለጠ ተገነዘበች፤ የበለጠ ተጋች።

የልጇን መንግሥት ለማጠናከር ወልደልዑልን፣ ተንሴ ማሞን ባሸነፉ በዓመቱ ራስ ቢትወደድ ብላ ሾመችው። አፄ ፋሲለደስ ያሰሩት የራሶች መኖሪያ ራስ ግንብ ውስጥ እንዲገባ አደረገች።
ያሰበችውን ሁሉ ለማሳካት፣
ዘወትር ጠዋት አስራ ሁለት ሰዐት ላይ ዳዊቷን ደግማ የጸሎት መጽሐፏን አንብባ እንደጨረሰች ወይዛዝርት ልብሷን ያለብሷታል
ያስጌጧታል። ብሎም ቁርስ ታደርጋለች። አፈ ንጉሡ መጥቶ ፍትሕ ፈላጊ እንዳለ ካስታወቃት፣ ሦስት ሰዐት ላይ ዙፋን ችሎት ከኢያሱ ጋር ተሰይማ አቤቱታ ትሰማለች። ፍትሐ ነገሥት
ጠንቅቀው ከሚያውቁ መሃል የተመረጡት ዐራት አዛዦች ፍትሓ
ነገሥት እየጠቀሱ ፍርድ ሲያሰሙና ፍርዳቸውን ሲሰጡ ትሰማለች።መኳንንቱ አንድ በአንድ የሚሰጡትን የብይን ሐሳብ ታዳምጣለች።በመጨረሻም የተለየ የተለየ ፍርድ ካላት ትሰጣለች።

ሽንጎ እንደተነሳ እልፍኟ ትመለሳለች። ከልጇ ጋር ሆና መሣፍንት መኳንንትና ሌሎችም እጅ ይነሳሉ። እነሱን እንዳሰናበተች ዘወትር ለራሷ የምታቀርበው ጥያቄ እንዴት ላስተዳድር?” በመሆኑ ጉባኤ ጠርታ የልጇን መንግሥት ለማጽናት፣ ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና ለሃገሯ
ያሰበችውን ለመሥራት፣ ያንገራገረ መኰንን ካለ ከጥል ይልቅ ዕርቅ
እየመረጠች ለዕርቅ ትደራደራለች።
ጥምረት መፍጠር ካለባት ጋር ጥምረት ትፈጥራለች፣ በጋብቻ
ማስተሳሰር ያለባትን ታስተሳስራለች፤ ማን ከማን ጋር መጋባት እንዳለበት ትወጥናለች። ብሎም የመሣፍንቱንና የመኳንንቱን ቀልብ መሳብ ብቻ ሳይሆን ድጋፋቸውንም አገኘች። ሊቃውንት አድናቂያቸው
ካህናት ደግሞ አክባሪያቸው በመሆኗ ሊፃረሯት ምክንያት አጡ።ደከመኝ፣ ታከተኝ ሳትል ያለ ዕረፍት ራሷን በሥራ ጠመደች።

ሙሉ ለሙሉ ለሃገሯ ሰላምና ደሕንነት ማሰቧ፣ ለልጇ ሕይወት መጨነቋ፣ ከተንሴ ማሞ ጋር የተደረገው ውጊያ ያሳደረባት ድካም፣ ተጽዕኖና ያለ ዕረፍት መሥራቷ፣ ስለ ራሷ የምታስብበት ጊዜ እንዳይኖራት አደረጋት።

በሏ ከሞቱ ሦስት ዓመታቸው ነው
አፍላ እድሜዋ ላይ
በመሞታቸው የልጅነት ጊዜዋ እንደዚሁ መጥፋቱ ክፉኛ አሳሰባት።ሕይወቷ ጨው ጎደለው፤ ድግስ ላይ እንደሚቀርበው አዋዜ፣ ድቁስና
የተሰነገ ቃርያ ማጣፈጫ አጣ። ቋራን ለቃ ቤተመንግሥት የገባች ቀን ሕይወት የፈነጠቀችላትን ብርሃን መልሳ እንደ ክረምት ሰማይ ግራጫ ያለበሰችባት መስሎ ተሰማት።

ሙሉ ፀጋዋንም ሰስታ የያዘችባት መሰላት።

ዳግማዊ ኢያሱ በትምህርቱ ጎበዝ፣ በቅኔ ትምህርቱም ብስል
አእምሮውን እያሳየ ቢመጣም፣ ከቤተመንግሥት ውጭ ወጥቶ መዘዋወርዐእና እንደማንኛውም ልጅ መጫወት በመፈለጉ ወደ ውጭ በወጣ ቁጥር
ምንትዋብ ነፍስና ስጋዋ ይላቀቃሉ። ጠባቂዎች ቢኖሩትም፣ ምንትዋብ
ክፉ ያሰበ ይገድልብኛል ብላ ስለምትሰጋ ከእሷው ጋር ካልሆነ ባይወጣ ትመርጣለች። የኢያሱ የተፋጠነ ዕድገት የደስታ ምንጭ ቢሆንላትም፣ ደጅ ደጁን ማለቱ ግን ተጨማሪ የጭንቀት መነሻ ሆኖባታል።

በዕረፍት ጊዜዋ ከተወሰኑ መኳንንትና የኣፄ በካፋ እህት
የወለተእስራኤል ልጅ ከሆነው ከኢያሱና ከካህናት ጋር ጨዋታ
ባትይዝ ኖሮ ሕይወት የበለጠ እየከበደችባት በመጣች። በተለይም ልዑል ኢያሱ ዘወትር ጠያቂዋ በመሆኑ የቅርብ ወዳጅ እየሆነ መጣ።
ዙርያዋን ከከበባትና ዘወትር ለሥልጣንና ለሹመት ከሚቁነጠነጠውና ከሚወዳደረው፣ ካባውን እያወናጨፈ ከሚከራከረው ባላባት ጎን እሱን ረጋ ብሎ ማየቷ አረጋጋት። ጨዋታው ደስ እያላት መጣ። ለስለስ ማለቱና ቁጥብነቱ ማረካት።

እቴጌ መሆን ታላቅ ነገር ነው። በአደባባይና በሸንጎ የምትታየው
ደርባባዋ፣ ጠንካራዋና ደስተኛዋ ምንትዋብ ግን መኝታ ቤቷ ስትገባ
ብቸኛ ነች። ልጇ ኢያሱ ስላደገ፣ ከእሱ ጋር አንድ መኝታ ቤት
መተኛቱን አቁመዋል ። መኝታ ቤቷ ስትገባ ክፍሉ ባዶ፣ አልጋዋ
ቀዝቃዛ ሆነው ይጠብቋታል። በተለይም ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሐሳቡ፣ ጭንቀቱና መጠበቡ በርትቶባታል።

አንድ ማታ ነው። ሁለተኛ ደርብ ላይ ባለው መኝታ ቤቷ መስኮት
ውጭውን ትመለከታለች አንዳንዴ ከራሷ ጋር ለመሆን ስትፈልግ
እንደምታደርገው። መንፈሷ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ መረጋጋት አቅቶታል። ድፍን ጨለማው ላይ አፍጣ ቆየች። ለወራት ሲያስጨንቃት
የነበረው ሐሳብ ቀስ በቀስ ጭንቅላቷ ውስጥ ተንሸራቶ ገባ። እስተመቸ ብቻየን እቀመጣለሁ? የሚሉት ቃላት ከአፏ አፈትልከው ወጡ።ደነገጠች። የሰማት ሰው እንዳለም ለማወቅ በመስኮቱ ወደ ታች አየች።በአካባቢው ማንም ያለ አይመስልም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስታወጣ ስታወርደው የነበረ ነገር ቢሆንም፣
እንደዚህ ከአፌ ይወጣል ብላ አልገመተችም። ነገሩን ዳግም ላታነሳ ከራሷ ጋር ቃል ተገባብታና አፍና የያዘችው ነገር ከአፏ አምልጠ ሲወጣ ተገረመች። መልሳ ስውር ወደ ሆነውና ምሥጢር ደብቆ ወደ እሚያስቀምጠው የሰውነቷ ክፍል ሰግስጋ ልታስገባው ሞከረች።
አዳምጭኝ እያለ የሚወተውተውን ድምፅ ግን ማስቆም አቃታት።
አወጣች፤ አወረደች። መፍትሔ እንደሌለው ተገነዘበችና በትካዜ ሄዳ አልጋዋ ላይ ጋደም አለች።

ጸሎት ልታደርስ ፈልጋ የጸሎት መጽሐፉን ከዕንጨት የተሠራውና
ከፊት ለፊቱ የመስቀል ቅርጽ ያለው ረጅሙ #አትሮኖሷ ላይ አጋድማ፣ ከአንዱ ጸሎት ወደ ሌላው ብታልፍ መንፈሷ አልረጋጋ አለ። ዛሬስ እዝጊሃር ይቅር ይበለኝ ጠሎቱም እምቢየው ብሎኛል። ገና ግዝየ ነው ዛዲያ ምን ልሥራ? ብላ ጋደም እንዳለች አካሏ በሥራ፣ ስሜቷ በሐሳብ ደክመው ነበርና እንቅልፍ ጣላት።

በጣሙን ያስደነቃትን ሕልም አየች።

እጅም፣ እግርም፣ ፊትም ሆነ ጭንቅላት የሌለው፣ ግን ባያሌው
ደስ የሚል፣ ብርሃን የተሞላው፣ ቀይ አበባ መሳይ ነገር የሚያናግራት ይመስላታል ።
“ምንትዋብ!”
“አቤት! አንተ ማነህ?”
“እኔ ፍቅር ነኝ። ፍቅር ታቂያለሽ?”
“አዎን፣ በልዥነቴ ጥላዬ ሚባል ልዥ ኋላም ባሌን አፈቅር ነበር።”
“ጥላዬ ኻይንሽ ስለራቀ ኸልብሽ ርቋል። ባልሽን ትወጂ ነበር።
ለፍቅር ገና ነበርሽ።”
“ፍቅር ምንድርነው?”
“እኔ አልገለጥም። ሕይወታችሁ ውስጥ ኻሉ ምሥጢሮች አንዱ ነኝ።እናንት ሰዎች እኔን ሙሉ ለሙሉ ማወቅ ስለተሳናችሁ እኔን ሊገልጹ ሚችሉ በቂ ቃላት አላደራጃችሁም። እኔን ትመኛላችሁ፣ ግና ነፍሳችሁ
ምትላችሁን አታዳምጡም። ጠቢቡ እንዳለው የመውደድ ቦታው ነፍስ ነው። ዛዲያ እኔን ለመሸከም ነፍሳችሁን ማዳመጥ ይጠይቃል።”

“እንዴ አሁን እኔ ኸልዤና ካገሬ የበለጠ ማፈቅረው አለ?”

“አየሸ ምንትዋብ እኔ አንድ ነኝ። እናንተ ግና የፍቅር ዓይነት
እያላችሁ አስር ቦታ ትከፋፍሉኛላችሁ። ፍቅር ማለት ሕይወት ማለት ነው፤ ሞትንም ስንኳ በፍቅር ማሸነፍ ይቻላል። ግና ፍቅር ለናንተ ሲያልቅ ያልቃል... ሲያረጅ ያረጃል። ኻንዱ ቀንሳችሁ ለሌላው ታበዛላችሁ። ለምሳሌ አሁን አንቺ ለልዥሽና ላገርሽ ያለሽ ፍቅር ልብሽን በሙሉ ስለገዛ ራስሽን ችላ ብለሻል። ስለዝኸ ሕይወት ሙሉ ትርጉሟን ልትለግስሽ አልቻላት አለ። ጭንቀት ሲፈታተንሽ ውሎ
👍7