አትሮኖስ
281K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_ሁለት


#በሜሪ_ፈለቀ

...ዳግማዊ ስለእኔ ከሰማው ውጪ አብሮኝ በነበረው ቆይታ ሊያውቅ የሚችለው ነገር መኖሩን እንጃ! ነገሩ እኔስ ምን አውቃለሁ? ስለእርሱ አይደለም እኮ አረ ስለራሴ..ስቆላል አይደለም። የሚያውቁኝ የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ሲሉ
እሰማለሁ። ዳሩ እንኳን ሌሎች እራሴም ስለራሴ ነኝ' ያልኩትን ላልሆን እችላለሁ።

#አስቀያሚ_አይደለሁም

እግዜር የስሜት ባለቤት ከሆነ የእርሱን ፈገግታ የመሰለ ውበት አለሽ ባሉኝ ማግስት ምን ያደርጋል የሰከነች
አይደለችም ይሉኛል ፤ ፈገግታሽ የሰማይ መልአክትን መጎናፀፊያ ይመስላል ባሉኝ ማግስት እንደሸርሙጣ ታስካካለች ይሉኛል ፤ የሰውነቴን መዋቅር ከምርጥ ቀራፂ ውብ ቅርፅ ጋር ባነፃፀሩት ማግስት ክብሯን አትጠብቅም ለስሜቷ ትተኛለች ይሉኛል።

#ያላዋቂ_አይደለሁም

ቤተሰቦቼን እና በደቦ ያሳደጉኝን የሰፈሬን ሰዎች ጨምሮ የሚያውቁኝ ሁሉ ከመዋዕለ ህፃናት ጀምሮ እስከ ማስተርስ
በማዕረግ መጨረሴን አድንቀው ሳይጨርሱ ምን ያደርጋልኀቆማ መቅረቷ ነው ይላሉ።ማወቅ የሚሹት ነገር ሲኖር
እንዳልጠየቁኝ፣ የዕለት መፍትሄ ሲሹ እንዳላማከሩኝ፤በኪሎ የሚበልጣትን መፅሐፍ ይዛ የምትዞር ጉረኛ ናት
ይሉኛል፡፡

#ስሜት_አልባ_አይደለሁም

ዛር እንዳለበት ባለውቃቢ አብሮኝ እንዳላበደ፣ የሚያደርገኝ ጠፍቶት በስሜት እንዳልሰከረ የሱ እብደት ጎበዝ
ሲያስብለው የኔ ያለመሽኮርመም ብዙ ወንድ የምታውቅ ባለጌ ያስብለኛል።

#አመለ_ቢስ_አይደለሁም፡፡

ግልፅነቴ ደንቆት አንቺን ያገኘ ወንድ አፈስ ባለኝ ቅፅበት
“ለምን ታዲያ አንተ አታፍሰኝም?” ስለው “ሴት ልጅ እንዲህ እትልም” ይለኛል።

#አላማማኝ_አይደለሁም

ሀይማኖቴ ፍቅር ነው። የሰውን ልጅ ሁሉ መውደድ።ራሴን እወዳለሁ። ለዛ ነው ሌሎችን የሚወድ ልብ ያለኝ፡፡

ለራሱ ፍቅር የሌለው ለሌላ ተርፎት የሚለግሰው መውደድ ብትሉኝ ያንቀኛል። በሰውኛ ልኬት ሰውን የመውደድ ጣሪያ ራስን ከመውደድ ልክ መሆኑን ለማሳየት
ይመስለኛል ክርስቶስ ከህግ ሁሉ የበላይ ህግ የትኛው መሆኑን ሲጠየቅ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ' ያለው::
የፈጣሪ ትርጉሙ ለኔ ፍቅር ነው። የማላየውን ፈጣሪ ማምለክ እና መውደድ በአምሳሉ በፈጠራቸው በሰዎች
ሁሉ ውስጥ አለ ብሎ ማመን እነሱን ማክበርና መውደድ ነው።

ፍቅር ከክፋት በብዙ የራቀ ነውና ለክፋት የሆነ ልብ የለኝም። አንዳንዶቹ ግን እንደነሱ በሀይማኖት ካባ ራሴን
ደብቄ አለማስመሰሌን እኔኑ እያሙ እዛው ካባቸው ውስጥ ይደበቃሉ። በልባቸው ጠብታ ቅንነት ሳይኖር ለፍቅርና
እግዜርን ለመፍራት የሚኖሩ ያስመስሉታል። እኔ ግን ከክፉ ልብ ከመነጨ ምርቃት ይልቅ በአንድ ልኩ ከቅን ልብ የሆነ እርግማን ይሻላል ባይ ነኝ፡፡ ኡኡቴ ብርጉድሽ ቀርቶብኝ ፈስሽን በያዝሽልኝ ትል ነበር እናኒ ( አክስቴ)
#ንፉግ_አይደለሁም

መስጠት ከመትረፍረፍ አንጀት የሚፈልቅ ወይም ከመብዛት ማዕድ የሚዘገን አልያም ከመበልፀግ ማህፀን የሚወለድ እንዳልሆነ አውቃለው።

መስጠት ከመንፈስ እንጂ ከሌጣ እውቀት የተጋባ 'መክሊት' አይመስለኝም ።(መክሊት ያልኩት መስጠት ከምግባር ስለሚልቅብኝ ነው።መስጠት በትርፍ ካርዶች የምትቆምርበት ሲሆን ለሰማዩ ፅድቅም ለምድሩ ብድራትም መብቃቱን እጠራጠራለሁ።በየእለት ልመናዋ 'የምሰጠው አታሳጣኝ' እያለች የምትለምን ልበ መልካም አክስት ናት ያሳደገችኝ።

#የአራዳ_ደንባራ_አይደለሁም

ባህሌን አክባሪ መሆኔን ባወደሱ ቅፅበት እናትና አባቴ ባወጡልኝ ስም (ባንቺ ወግ አየሁ) ሲሳለቁ እሰማቸዋለሁ።በእርግጥ አንዳንዴ ቤተሰቦቼ ከአስር ተከታታይ ወንድ ልጅ በኋላ በየደብሩና በየደጀ ሰላሙ ተደፍተው እና በየአዋቂውና ውቃቢው ቤት አፈንድጀው የወለዱኝን ሴት ልጃቸውን እንኳን ለግለሰብ ለአንድ ሃገር ኸረ ምን ለሃገር ለአህጉር ራሱ የሚበዛ ዓረፍተ ነገር ስም ከነተጎታቹ ማንዘላዘል ውዴታ ነው ጥላቻ? ብዬ አስባለሁ።'ባንቺ ወግአገኘሁ'የእኔ ስም የኔ መጠርያ ሳይሆን የወላጆቼ ታሪክ ነው ያለፈ ታሪካቸውን የውልደቴ ፈንጠዝያቸውን፣ ምን አልባትም የሰፈር ሰው 'ሴት ልጅ ፍለጋ ደርዘን ወንድ ታቅፋ ሽሙጥ የተቀባበላቸውን ስላቅ የመልስ ምት! ምን አለፋችሁ ያደለው 'የህይወቴ እርምጃ ከአፍ እስከገደፉ' እያለ መፅሐፍ ይፅፋል የኔ ቤተሰቦች የህይወት ታሪካቸውን ለዓመታት እንዲነበብ በኔ ስም በደማቁ ፅፈውታል።የሚጠራኝ ሁሉ ያነብላቸዋል።

እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል።ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ።ከሰመሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን ዕድል አይሰጡህም ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረብያ ይስላሉ።ልብህን ከከፈትክላቸው የድርሻቸውን ጠርበዉህ ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።በእርግጥ በአንድ ነገር እስማማለው። እሳት ሳይኖር ጭስ የለም።እሳት ባህሪዬን ከሚያንቀለቅሉት እና ከሚያሰሙኝ ምክንያቶች አንዱ የቢኒያም አይነት ወንዶች ናቸው። የማልቋቋመው 'ወንዳም ውበት' ያላቸው ወንዶች!! ወንዳዊ ውበት የምለው የሰፋ ደረትና ትከሻ ወይም የጎላ አይንና ሰልካካ አፍንጫ አልያም ረጅም ቁመና አይነት የአካል ውቅረቶች አይደሉም።የሆነ እንቅስቃሲያቸው አስተያየታቸው የከንፈር እንቅስቃሲያቸው፣ አስተያየታቸው፣አረማመዳቸው፣የድምፃየው ምት፣አሳሳቃቃቸው፣ ወዘተ ተረፈ....ሽፍደት ያለበት አይነት ጥቂት ወንዶች አሉ። ቢኒ የውሸት ባሌ የዲጉ(ዳግማዊ) ታናሽ ወንድም ከጥቂቶቹ ነው። ገና የወንድሙን ሚስት ሲተዋወቀኝ ነበር።

"ኖ.....ኖ.....ባንቺ አትባልጊ" ያልኩት ለራሴ

በነገራችሁ ላይ ቤተሰቡ በቁልምጫ የመጠራራት ክፉኛ ጥንወት የተጠናወተው ነው። ዳግማዊ-ዲጉ፣ ቅድስት-ኪዱ፣ ቢኒያም-ቢኒ.....እናትየውን ዲጉ 'እናቴ' እያለ ነው የሚጠራቸው፣
ኪዱ 'እታባ' ቢኒ 'እማዬ' ፣ ቹቹ እና የሰፈር ሰው 'አዳዳ'. ...አሁን በናታችሁ ባንቺ ወግ አየሁ ሲቆላጰስ 'ቤች',ይሆናል?....የገረመኝ ሌላ ቁልመጫ የዲጉ ጓደኛ ስም ነው። ስሙ አበጀ ነው።ሲጠሩት 'አጄ' ብለውት እርፍ!!

"የክለብ አመልሽን አልነገርኩትም። ለሶስት ሳምንት ጨዋ መሆን መቼም አያቅትሽም ።" አለችኝ ቹቹ አዳ ከቤተሰቡ ጋር አቀባበል የተደረገልን እለት ማታ ወደ ጆሮዬ ቸጠግታ።

ታውቃለች።የሚያውቁኝ ያውቃሉ። ትንሽዬ ልብ ናት ያለችኝ።ቶሎ የምትግል ቶሎ የምትበርድ። በትንሽዬ ደስታ ምቃ ከደረቴ ልታመልጥ ትፈነጥዛለች። በሚጢጢዬ ሀዘን በረዳ በደረቴ ውስጥ ሟሽሻ ትጠፋለች።ጥሎብኝ በግራ ወይም በቀኝ ጠርዝ የመንጠለጠል ልክፍት ከጥግ እያላተመኝ መካከለኛ አመለካከት ሀጥያት ይመስለኛል። ስለእውነቱ ይሄ የኔ ብቻ ችግር መሆኑን እጠረጥራለሁ።አብዛኞቻችን የተጠረቅንባቸው ጎራዎች ሁለት ፅንፍ ይመስሉኛል። መካከለኛ የሚባል ነገር የማናውቅ እንበዛለን።ወዳጅ ወይም ጠላት፣ህይወት ወይም ሞት፣ መልካም ወይም ክፉ፣ ደጋፊ ወይም ተቃዋሚ....

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሁለቱም ጠርዞች ስላተም፣ ስፈነጥዝም ሳዝንም የሚያበርደኝ ሁካታ ሆኗል።በሁለቱም ዋልታ ስናኝ ከሰው ጋር ማውራት ደስ አይለኝም ። የማደርገው እንደዚህ ነው በፊት በፊት በፀጥታ ረዥም መንገድ በእግሬ መጓዝ በመጠኑ የሚያበርደኝ መድሃኒቴ ነበር።አሁን ግን አብዛኛው እንዲህ ባሉ ቀኖቼ ለዳንኪራ የሚመቸኝን ልብስና ጫማ አደርጋለሁ ፣ ብቻዬን ክለብ እሄዳለው፣ አካሌ ዝሎ እስኪብረከረክ እጨፍራለሁ። ካለማጋነን አይኖችና ቀልቦች የምይዝ ጎበዝ ደናሽ ነኝ። በእንቅስቃሴዬ ስልት በሰውነቴ ላይ የሚደንሱ አይኖች እና ትከሻዬ ላይ ተቆልለው የሚከብዱኝ ቀልቦች ለሁካታው የሰጠሁትን ትኩረት
2👍2😁1