#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቢ
‹‹እሺ ሳባ ህይወት እንዴት ነው?››
‹‹አሪፍ ነው…ምንም አይል?››
‹‹ማለቴ የስራ ህይወትሽ እንዴት ነው..ደስተኛ ነሽ?››
‹‹አዎ በስራው ደስተኛ ነኝ….ግን ክፍያው በቂ አይደለም…ማለቴ በቂ ሊሆን ይችላል ለእኔ ግን እየበቃኝ አይደለም፡፡›› ስትል በምሬት መለሰችላት፡፡
‹ይገባኛል…አየሽ አንቺ የተማርሽ ቆንጆና ማራኪ ወጣት ብትሆኚም በዕድሜ ግን ገና ለጋ ወጣት ነሽ…ገና ብዙ ብዙ ዕድል ይጠብቅሻል.. በህይወት የተሰጠሸን እድል ትጠቀሚበታለሽ ወይስ ታባክኚዋለሽ….ዋናው ጥያቄ ይሄ ነው፡፡››
‹‹ማለት አልገባኝም፡፡››አለቻት..እውነትም አለመግባትም ብቻ ሳይሆን ይባስ ብሎም ግራ ገብቷታል፡፡
ስለጀመረችላት ወሬ ይበልጥ ማብራሪያ ትሰጠኛለች ብላ ስትጠብቅ አሷ ‹‹እስኪ ተነሽ አንድ ቦታ ሄደን እንምጣ›› ብላት ቀድማት ከመቀመጫዋ ተነሳች...ሳባም ያለምንም ማቅማማት ተከትላት ተነሳችና ከኋላዋ ተከተለቻት፡፡
በፊት ለፊት በር ትወጣለች ብላ ስትጠብቅ ወደኋላ በር አመራች ..ረጅም ኮሪደር ሰንጥቀው ካቋረጡ በኋላ ወደውጭ ወጡ፡፡ በፅድና በተለያዩ አበቦችና አትክልቶች የተሞላ ውብ ግቢ ነው፡፡በረንዳውን ወርዳ ወደጓሮ ዘልቃ ገባች… ‹‹ይህቺ ሴትዬ ጓሮዋን ልታስጎበኘኝ ነው እንዴ?››እያለች በማልጎምጎም ተከተለቻት፡፡ግን ተሳስታ ነበር…፡፡እስከመጨረሻ ጓሮውን ሰንጥቀው ከጨረሱ በኋላ ሰማይ ጠቀስ በሆነው የብሎኬት አጥር መሀከል የሚያብረቀርቅ ወርቅ ቅብ አይነት ቀለም የተቀባ የላሜራ ግዙፍ በር አለ..በራፉ ጋር አንድ ጥቁር ሱፍ የለበሰ መልኩም ጥቁር የሆነ ወጠምሻ ሰው ቆሟል ፡፡
የኋላ ቤት የኋላ በራፍ በመኖሩ ተገርማ ሳትጨርስ ጭራሽ ጠባቂ ስታይ‹‹ይሄ ምን ጉድ ነው?››ስትል ነበር በውስጧ የጠየቀችው
‹‹….ሴትዬዋ ሀሽሽ አከፋፋይ ትሆን አንዴ?››መልስ ባታገኝም በውስጧ የጠየቀችው ጥያቄ ነበር፡፡ወጠምሻው ጠብ እርግፍ በማለት በትህትና እጅ ነሳና በራፉን ከፈተላቸው፡፡ተያይዘው በራፉን አልፈው ወጡ፡፡የወጡት ግን ወደ አስፓልት አይደለም ወይም ኮረኮንች መንገድ ላይ ወስዶ የሚጥልም አይደለም…ወደ ሌላ ግቢ እንጂ፡፡ ግቢው በግምት አንድ ሺ ካሬ ስፋት ያለው
ሲሆን የሎጅ አይነት አሰራርና አደረጃጀት የተከተለ ነው….ራቅ ራቅ ብለው አንደኛው ከአንደኛው በራፍና መግቢያ ተቃራኒ እንዲሆን ተደርጎ በቁጥር አስር በጎጆ ቅርፅ የተሰሩ ግድግዳቸው ባህላዊ ይዘት ኖሮት በተጠረበ ድንጋይ በጥንቃቄ የተሰሩ ቤቶች ዙሪያቸውን በተክሎች፤በአበባና፤በሀረጎች የተሸፈነና የተከለለ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡
ትብለጥም‹‹ይሄ አንደኛውና ዋነኛው የስራ ቦታችን ነው…ሌሎች ሁለት ቦታዎችም አሉን…ዋናው ግን ይሄ ነው፡፡››በማለት ወደ አንዱ እየመራች ወሰደቻት፡፡
የተዘጋውን በራፍ እጄታውን ጫን አለችና ገፋ አድርጋ ከፈተችው..ሶስት ክፍል አለው፡፡አንዱ ሻወር ቤት…ሁለተኛው ከሻወር ቤቱ የተያያዘ መልበሻ ክፍል፤ሲሆን ሌላው ዋናውና ሰፋ ያለው ክፍል ነው፡፡ ሰፊውና ዋናው ክፍል ውስጥ አንድ ቁም ሳጥን ሁለት ደረቅ ወንበሮች፤ከአንድ አነስተኛ ጠረጴዛ ጋር አንድ መካከለኛ ቁመት ያለው ሰው በምቾት ማስተኛት የሚችል ረዘም ያለ በነጭ ቆዳ የተለበጠ ሶፋ ሲኖር ወለሉ መካከል ላይ ሰፊና ረጅም የማሳጅ ጠረጴዛ አለ፡፡ዙሪያውን ቃኝታ ሳትጨርስ ደረቅ ወንበሩ ላይ ቁጭ ብሎ የነበረ አንድ የተወጣጠረ ጡንቻ ያለው ወጣት ከተቀመጠበት በፍጥነት ተነሳና ወደ እነሱ በመቅረብ ‹‹እንኳን በሰላም መጣችሁ ›› ሲል መጀመሪያ ትብለጥን ከዛ ደግሞ ሳባን ጨበጣቸው…
ሳባ ሲጨብጣት የእጁ ልስላሴና ጥንካሬ ውስጧ ድረስ ተሰማት፡‹‹እንዴት በዚህ መጠን ለስላሳና ጠንካራ ሊሆን ቻለ..?››ስትል ተገረመችበት፡፡‹‹አይ እንደዛማ ሊሆን አይችልም…እኔ ተሳስቼ ነው፡፡›› አለችና ትኩረቷን ለመሰብሰብ ሞከረች፡፡
‹‹ሶፈኒያስ ይባላል እሷዋ ደግሞ ሳባ ትባላለች…ዘመዴ ነች፡፡ሰሞኑን ከተጨናነቀ ስራ ላይ ነበረች፤ከዛ አስነስቼ ነው ያስመጣኋት፤ትንሽ ዘና ማለት ይገባታል
…አንተን ደግሞ እተማመንብሀለሁ….ልከ ለእኔ እንደምታዳርገው ለእሷም እንደዛው፡፡›› የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈችለት፡፡
‹‹እረ ችግር የለውም…ግቢና ልብስሽን ቀይሪ…››ብሎ ፊቱን አዙሮ ወደ ጠረጴዛው ሄደና ለስራ የሚገለገልባቸውን ቅባቶችና የማሳጅ መገልገያ ዕቃዎች ማዘጋጀት ጀመረ፡፡ሳባ የምትለውና የምታደረግው ግራ ገብቷት በተገተረችበት ፈዛ ትብለጥን በትኩረት ትመለከታት ጀመረ፡፡
ገባትና ልትቀመጥ ወደሶፋው መራመድ የጀመረችውን እርምጃ ገትታ እጇን በመያዝ እየጎተተቻት ወደልብስ መቀየሪያው አነስተኛ ክፍል ይዛት ገባች.. የክፍሉ ሁለት የግድግዳው ክፍል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመስታወት የተሸፈነ ነው፡፡በአንደኛው ግድግዳ ተደግፎ የቆመ ለክፍሉ እንዲስማማ ተደርጎ የተሰራ አነስተኛ ቁምሳጥን አለ…አንድ መቀመጫ መግቢያው ላይ አለ‹‹…በይ ልብስሽን አውልቂና ይሄንን ፎጣ አገልድመሽ ነይ…››
‹‹ልብሴን አውልቄ…? ማለት ለምን..?››
‹‹እንዴት ለምን ?ማሳጅ ተሰርተሸ አታውቂም?››
‹‹በፍፁም አላውቅም፡፡››
‹‹እንግዲያው እመኚኝ በጣም ትወጂዋለሽ፡፡›
‹‹እረ ይቅርብኝ..እኔ ወንድ ፊት እርቃኔን ቆሜ አላውቅም..››
‹‹እንዴ ምን ነካሽ የተማርሽና ዘመናዊ ሴት አይደለሽ እንዴ…? እንዳልሽ በወንድ ፊት ልብስሽን አውልቀሽ የማታውቂ ከዛም በላይ የወንድ እጅም ሰውነትሽ ላይ አርፎ የማያውቅ ሊሆን ይችላል…ግን ያ ማለት እስክትሞቺ አንዲህ ሆኖ ይቀጥላል ማለት እንዳልሆነ መቼስ በደንብ ታውቂያለሽ…አንድ ቀን በየተራ አድርገሽ የማታውቂያቸው ነገሮችን ቀስ በቀስ ማድረግሽ የማይቀርና የሚጠበቅ
ነው..አሁን በይ ልብስሽን አውልቂና ነይ…ደግሞ እኮ ብቻሽን አይደለሽም እኔ በክፍሉ ውስጥ ከፊት ለፊትሽ ቁጭ እላለሁ፡፡››
ምንም ማምለጫ መንገድ ልታገኝ አልቻለችም፡‹‹እሺ በቃ››
‹‹አዎ እንደዛ ነው የሚባለው..በይ አውልቂና ነይ .››ብላት ክፍሉን ጥላላት ወጥታ ሄደች…ሳባ የለበሰችውን ቀሚስ አወለቀችና ቀኑን ሙሉ ስትለፋበት የዋለችውን አዲስ የተሰራ ጸጉሯን አንድላይ ጠቅላላ በማያያዝ ፎጣውን አገልድማ ልክ ለዘመናት ሲያልመውና ሲመኘው ወደከረመው መድረክ አድል ቀንቶት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚወጣ አማተር አርቲስት በፍራቻና በሚንቀጠቀጡ እግሮቿ ወደ ውስጥ ገባች…ሁለቱም ቀና ብለው አዯት እና እርስ በርስ ተያዩ
…ፈገግ አለች ትብለጥ
‹‹ምነው?ምን አጠፋሁ?››
‹‹ምንም…ግን በማሳጅ ምንም አይነት ልብስ አይፈቀድም…››
‹‹እንዴ ፓንትም?››
‹‹እሺ ለዛሬ ፓንቱን ይሁን ተይው…ጡት ማስያዣውን ግን አውልቂው…››
‹‹ሴትዬዋ ጉድ ልትሰራኝ ነው እንዴ? ያን ሁሉ እንክብካቤና ጠብ እርግፍማ ለጤና አይደለም›› እያለች ተመልሳ ወደክፍሉ ገባችና ጡት ማስያዣዋን አወለቀችና ተመለሰች…ወደ ጠረጴዛው ቀረበች…
‹‹ዘና በይና ጠረጴዛው ላይ በደረትሽ ተኚ ››አላት…
ከፍራቻዋ ጋር እየታገለች እንዳላት አደረገች..ቅባቱን በእጆቹ አፈሰና ከትከሻዋ አካባቢ እጆቹን አሳረፈ፡፡ ሰውነቷ ሽምቅቅ አለ…ቀስ እያለ መገጣጠሚያዋን እየነካካ እያፍታታት፤ወደታች ወደ ጀርባዋ ወረደ…አንዳንዴ ላላና ለስለስ ብሎ

👍81❤9🔥1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቢ
‹‹በማግስቱ ሰራ መሄድ አልቻለችም…ኸረ እንደውም ከተኛችበት መንቀሳቀስም አልቻለችም፡፡ ሀሳብ እንዲህ ድቅቅ አድርጎ እንደሚያደክም ይሄ በህይወቷ የመጀመሪያው ልምዷ ነው፡፡ ዝልፍልፍ ነበር ያለችው…ስጋትና ጉጉት..ፍራቻና ድፍረት..
‹‹ለአለቃዋ በጣም ስላመመኝ መምጣት አልቻልኩም›› ብላ በሚሴጅ መልዕክት ላከችለት፡፡
‹‹ሳምንቱን ሙሉ ስታወርድና ስታወጣ ስታስብና ስታሰላስል ቆይታ ቅዳሜ ዕለት ወደማታ ለትብለጥ ደወለችላትና እሁድ እንድምትመጣ ነገረቻት፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት መኪና እንደምትልክላት ነገረቻት፡፡
ስትደውልላት ወስና አይደለም….አግኝታት… የበለጠ ማብራሪያ፤የበለጠ ገለፃ እንድታደርግላት ፈልጋ እንጂ...አዎ በሳምንት ውስጥ ከአንድ ሺ በላይ ጥያቄዎች ወደ እዕምሮዋ ተግተልትለው ገብተው መልሰው ወጥተዋል..ታዲያ ቢያንስ መሰረታዊ የሆኑ እንዲመለሱላት የምትፈልገው አስራ ምናምን የሚሆኑ ጥያቄዎች አሉ…የስራውን እድል የምትቀበለውም አሻፈረኝ የምትለውም እነሱ ላይ ተንተርሳ እንደሆነ ከራሷ ጋር ባደረገችው ውይይት ውሳኔ ላይ ደርሳለች፡፡
ለምሳሌ ጥያቄ ቁጥር አንድ የተባለውን ያህል ብር በወር እስከ 100ሺ ብር ታገኛለች?100ሺ ብሩ ይቅር እሺ 50ሺ ብር እንኳን እንደምታገኝ ማረጋገጫዋ ምንድነው…?ይሄ ተስፋ የውሸት ቢሆንስ?
‹በሶስት ወር ስልጠና የተጠበቀውን ያህል ውጤታማ ባትሆንስ…?ተጨማሪ ስልጠና ይሰጣታል ወይስ ትባረራለች?፡፡›
‹‹ከማሳጅ ሙያ ውጭ እንድትሰጥ የሚጠበቅባት አገልግሎት ምንድነው..?
‹‹እንደ ተነገራት ዋናው የደንበኞቿን ፍላጎት ያለምንም መሸራረፍ 100 ፐርሰንትእንድታሟላና ፍፁም ደስተኛ ሆነው እንዲመለሱ ማድረግ ነው…ይሄ የወሲብ ጥያቄንም ያጠቃልላል….?››
‹‹ደንበኞቿ ወንዶች ብቻ ናቸው ወይስ ሴትም ወንድም….? የተመረጡ ሰዎች ናቸው ወይስ ማንም አገልግሎቱን የፈለገና መክፈል የሚችል ሰው ሁሉ መገልገል ይችላል?››
‹‹በስራ ላይ እያለች በደንበኞቿ ጥቃት ቢደርስባት ድርጅቱ እስከምን ድረስ ይከላከልላታል››…ወዘተ
እነዚህን አንድ በአንድ በማንሳት በዝርዝር እንድታስረዳት ካደረገች በኃላ ከዛ በስራው ለመቀጠልና ወደስልጠና ለመግባት ትወስናለች፤ካለበለዚያም እስከአሁን
ላደረገቸላት.እንክብካቤና ቀናነት አመስግናት ወደ ድህነት ስራዋ ትመለሰላች.. አዎ እንደዛ ወስና ነው የደወለችላት፡፡
እሁድ በተመሳሳይ ሰዓት በተመሳሳይ ቁጥር ተመሳሳይ ስልክ ተደወለላት
..ተዘጋጅታ ስትጠብቅ ስለነበረ ቦርሳዋን አነሳችና ወጣች፡፡ ዛሬ እንደባለፈው ሳምንት ፍፁማዊ በሚመስል መሽቀርቀር አይደለም፤ጉጉቷም የተለየና በስጋት የተሞላ ነው፡፡
ካዛንቺስ ደርሰው መኪናውን እንደተለመደው ግቢው ውስጥ አስገብቶ አቆመና ከፍቶ አስወረዳትና እጇን ይዞ ወደሳሎን ወሰዳት….በተመሳሰይ ለሰራተኛዋ አስረከባት..ሰራተኛዋ ቤተኛነትን በሚያሳይ የጋለ ሰላምታ ከተረከበቻት በኋላ ይዛት ወደውስጥ ገባች..ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ ስትጠብቃት የነበረችው ግን ትብለጥ አልነበረችም…ሌላ በእሷ ከእድሜ አራት ወይም አምስት አመት የምትበልጥ ጠይም ረጅም ሞዴል መሳይ ቆንጆ ሴት ነች፡፡ ከመቀመጫዋ ተነሳችና እጇን ለሰላምታ ዘረጋችላት..
‹‹ይህቺም እንደእኔ በስራው ተመልምላ ይሆን የመጣችው..? አንድ ላይ ልታናግረን ይሆናል አንድ ላይ የጠራችን ?››ስትል አሰበችና ቅር አላት…
ያ ሁሉ ጥያቄ ሌላ ሰው ፊት እንዴት አድርጋ ትጠይቃታላች...ሀሳቧን ዘርዝራ ሳትጨርስ…ልጅቷ‹‹ሰገን እባላለሁ..ካልተሳሳትኩ አንቺ ሳባ ነሽ››አለቻት
ለሰላምታ የሰነዘረችውን የሚቀነጠስ የሚመስለውን ጣቷን አየጨበጠች…‹‹አዎ አልተሳሳትሸም››አለቻት
‹‹እትዬ በቃ እናመሰግናለን..የምንፈልገው ነገር ካለ እንጠራሻለን››አለችና ሰራተኛዋን ወደ ውስጥ ሸኘቻትና ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ ሳባንም
ከፊት ለፊቷ እንድትቀመጥ ጋበዘቻት...ሳባ ግራ በመጋባት ከስር እስከ ላይ ብትቃኛትም ምንም መገመት አልቻለችም…ፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ በዛ ያሉ ወረቀቶች ይታያታል፡፡ ፊቷ ያያችው ሰገን እባላለሁ ያለቻት ልጅ መናገር ጀመረች፡፡
‹‹እንግዲህ ስለስራው መጀመር ማለቴ ስለ ስልጠናው ሁኔታ አንዳንድ ቅድመ ዝግጅቶችና የተወሰኑ የሚፈረሙ ውሎች አሉ… ስለዛ እንድንነጋገርና እንደንጨርስ ነው፡፡››
‹‹ግን እኮ››
‹‹ምነው…ችግር አለ?››
‹‹ማለቴ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ደርሼ አይደለም የመጣሁት …አሁንም እትዬ ትብለጥን ጠይቄ መረዳት የሚገባኝ ጥያቄዎች ነበሩኝ..››
‹‹ግን የተነገረኝ እንደተስማማሽ ነበር፡፡ትብለጥ ያለችኝ እንደዛ ነበር››
‹‹አዎ እርግጥ ለእሷ ያልኳት እንደዛ ነው…ማለት በአካል ሳገኛት ላስረዳትና ጥያቄዎቼን ላቀርብላት ነበር የፈለኩት...እና የማላስቸግርሽ ከሆነ ከእሷ ታገናኚኛለሽ?››
‹‹አይ አሁን በቅርብ ስሌለች አልችልም››
‹‹ውይ ያሳዝናል. በቃ ንገሪልኝና በተመቻት ቀን ቀጠሮ ትያዝልኝ እመጣለሁ፡፡››
‹‹ይቻላል….እነግራታለሁ..ግን ከስድሰት ወር በኃላ ነው እሷን የምታገኚያት፡፡››
ልቧ ምንጭቅ ብሎ ወደታች ዝቅ ያለ መሰላት…ወይንም የሆነ ነገር ከቤቱ ኮሪኒስ ላይ ተላቆ ጭንቅላቷ ላይ የወደቀ አይነት ስሜት ነው የተሰማት
‹ስድስት ወር….?››
‹‹አዎ..ዛሬ ወደ አሜሪካ በራለች…አሁን ያለሽ ምርጫ ሁለት ነው፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄዎችሽን ለእኔ አቅርበሽ ስለስራው በመረዳት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተሸ ወደስራ መግባት ወይም ሁለተኛው ምርጫሽ ይቅርብኝ ብለሽ ወደ ተለመደው ኑሮሽ መመለስ…››
‹‹በቃ?››
‹‹አዎ..አየሽ አንቺ የተፈለግሺበት ዋናው ምክንያት የእኔን ቦታ ለመተካት ነው፡፡››
አሁን ተነቃቃች…ቢያንስ ስራውን በጥልቀት የሚያውቀው ሰው ነው ከፊት ለፊቷ ያለው
‹‹ያንቺን…?አንቺ ልታቆሚ ነው፡?፡››
‹‹አይ በፍፁም… እንደነገርኩሽ እሷ አሜሪካ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ስለምትቆይ የእሷን ቦታ ለመተካት ነው….ማለት ድርጅቱን ለማስተዳደር..የእሷ ነገር ሆኖብኝ እንጂ እኔስ አዛው ስራዬን ብሰራ ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹እኔም ስራውን እፈልገዋለሁ እኮ…ግን ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች በውስጤ እየተጉላሉ እየረበሹኝ ስለሆነ ነው፡፡››
‹‹እሺ ትብለጥ…አንቺን በተመለከተ አደራ ስላለቺኝ ስለስራው ከእኔ ታሪክ አንስቼ ላስረዳሽ››
‹‹በፈጠረሽ…ደስ ይለኛል፡፡››
‹‹የዛሬ ስድስት አመት ነው፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2ተኛአመት የማኔጅመንት ተማሪ ነበርኩ፡፡እናቴ በድንገት ታማ ከክፍለ ሀገር አጎቶቼ አመጧትና ሚኒሊክ አስተኞት...ያው አባቴ በልጅነቴ ነበር የሞተብኝ..አጎቶቼ ሲመጡ ለቀናት ቢበዛ ለአንድ ሳምንት ህክምና ብለው ነበር…ግን በሽታዋ እንዲህ በቀላሉ የሚድን አይነት አልነበረም….ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ሁሉም ተራ በተራ ወደ ሀገራቸው
ተመለሱ፤ምክንያቱም ሁሉም የየራሳቸው ልጆችና ቤተሰቦች ያሏቸው ከእጅ ወደአፍ የሆነ ኑሮ የሚኖሩ ድሆች ስለነበሩ ከዛ በላይ ለእናቴ የሚያደርጉላት ምንም ነገር አልነበረም..ሆስፒታል አንድ ወር ከ15 ቀን ተኛች….

👍65❤6👎1🥰1