አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ለኀጥአን_የመጣ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#ክፍል_አንድ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው

#መነሻ

ሴራሊዮን በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ በተፈጥሮ ሃብት ማለትም በአልማዝ፣ ወርቅ፣ ቡና፣ ብረት እና ሌሎች ማዕድናት
የታደለች ነገር ግን ድሃ ሃገር ናት።

ሴራሊዮን በ1961 ከእንግሊዝ ነጻነቷን ከተቀናጀች በኋላ ለሶስት አመታት ክቡር
ሚልተን ማርጋይ በጠቅላይ ሚኒስተርነት ስትመሯ ከቆየች በኋላ ክቡር ሚልተን ማርጋይ በ1964 አረፉ፡፡ ከክቡር ሚልተን
ህልፈት በኋላ በሀገሪቱ ሙስና ተንሰራፋ
አስተዳደራዊ ብልሹነቱ ገነነ እና የምርጫ ብጥብጦች በብዛት መታየት ጀመሩ፡፡ ይህም ሀገሪቱ እንድትዳከም እና የትምህርት ስርዓቷ እንዲወድቅ ምክንያት ሆነ። ወጣቶች ተስፋ ቆርጠው ለአማጺ ቡድኑ አማላይ መልዕክት ጆሮቸውን ሰተው ብዙዎች የአብዮት አንድነት ግንባርን ተቀላቀሉ። በእንቅርት ላይ ጆሮ
ደግፍ እንዲሉ በህገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር የወጣው ሲያካ ሴቴቨንስ ሃገሪቱን ወደ አንድ ፓርቲ አገዛዝነት ለወጠ። የሲያካ አስራ ሰባት ዓመታት የፍዳ አመታት ሆኑ፦ እስራት፣ ግድያ እና ስደት: በ1985 ሲያካ ስልጣኑን ለሜጀር ጄኔራል ጆሴፍ ሞሞህ ቢያስረክብም የሃገሪቱ ችግር ከድጡ ወደ ማጡ ሆነ፡፡ በ1991 የአብዮት አንድነት ግንባር
በ ላይቤሪያው ቻርልስ ቴለር ጦር በመታገዝ የጆሴፍ ሞሞህን መንግስት ለመገርሰስ ሲንቀሳቀስ እርስ በርስ ጦርነት ተቀስቀስ።

የእርስ በርስ ጦርነቱ ለአስራ አንድ አመታት ሲቀጥል ሃገሪቱን ሙሉ ሲያካልል ከሃምሳ ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎችን ሞት ምክንያት ሆነ፡፡
=========================

ስለ ጦርነቱ ብዙ ነገር ይባላል ። አንዳንዱ ሩቅ ቦታ፣ ሌላ አገር የተከሰተ ይመስላል። ይህ ግን የቆየው ተፈናቃዩች የእኛ
ከተማ እስኪደርሱ ነው። አሁን ሁላችንም እዚህ ከኛው ሃገር እንደሆነ አውቀናል ተፈናቃዩች ቤተሰቦቻቸው እንዴት
እንደሞቱ ና የቤታቸውን መቃጠል ነገሩን።
አንዳንድ ሰዎች በጣም አዝነው ምግብ ሊሰጡዎቸው ሊያሰጠጎቸውም ወደዱ..
አብዛኞቹ ተፈናቃዩች ግን ፍቃደኛ አልሆኑም። ጦርነቱ ከዚህ ከተማ መድረሱ እንደማይቀር ያውቃሉና።

ልጆቻቸው ቀና ብለው አያዩንም። አቀርቅረው መሬት መሬት ያያሉ፥ የዛፍ መቁረጥ ድምፅ ይሁን የቤት ጣራ በሚጫወቱ ልጆች በድንጋይ ሲመታ በሚሰሙት ድምፅ ህፃናቱ በፍርሃት
ይዘላሉ፤ ይሮጣሉ። ትልልቆች ከጦርነቱ አካባቢ የመጡ ወላጆቻቸው ደግሞ ብዙ ጊዜ ከእኔ ከተማ አዋቂዎች ጋር እያወሩ
ሀሳብ ጭልጥ አድርጎ ይወስዳቸዋል። ከድካም ከመሰላቸት ና ከረሃብ በላይ አዕምሮቸውን የሚረብሽ ነገር እንዳዩ : ሁሉን ዘርግፈው ቢነግሩን ማመን የማንፈልገው አንድ ነገር እንዳዩ
ፊታቸው ላይ ይነበባል። አንዳንዴ አላፊዎቹ የሚነግሩን የተጋነነ
ፀይመስለኝ ነበር።

ስለ ጦርነት የማውቀው መፅሀፍ ላይ ካነበብኩት ወይም ፊልሞች ላይ ከተመልኩት ማለት ራንቦ ፈርስት፣ ብለድ እና የጎረቤት የላይቤሪያን በቢቢሲ ያዳመጥኩት ብቻ ነበር። በዛ
በንቦቀቅላ በአስር አመት እድሜ ስደተኞቹ ደስታቸውን ምን እንደነጠቃቸው የማወቅ የመረዳት አቅሙ አልነበረኝም::

ለመጀመሪያ ጊዜ ጦርነት የገጠመኝ በአስራ ሁለት አመቴ ነበር። ጥር ፡ 1985። ከ ጅንየር ከታላቅ ወንድሜ እና ከጓደኛየ ቶሊ ጋር ወደ ማትሩ ጆንግ የሙዚቃ ውድድር ለመሳትፍ በሄድንበት
ወቅት፡፡ሁለቱም በአንድ አመት ይበልጡ
ኛል ታላቆቼ ናቸው::የቅርብ ጓደኛዬ መሐመድ ከአባቱ ጋር የሳር ቤታቸውን እያደሱ ስለነበር መምጣት አልቻለም:: ገና በስምንት አመቴ ነው አራታችን የራፕ እና የዳንስ ቡድን የመሰረትነው፡፡

ቦምቢ ከተማ ነበር ራፕ ሙዚቃን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዳመጥኩት፡፡ አንድ አራተኛው የከተማው ነዋሪ ለ አሜሪካ
ድርጅት የሚሰሩ የውጭ ሃገር ሰዎች ነበሩ፡፡ አባቴም እዚህ ከተማ ይኖር ነበር፡፡ መዋኛ ገንዳ ላይ ለመዋኝት፧ ቴሌቭዥን
ለማየት እና በእንግዳ መቆያ የሚሰባሰቡትን ነጭ ሰዎችን
ለማየት ቦምቢ እንሄድ ነበር፡፡

አንድ ምሽት እንደ እኛ ጥቁር ወጣቶች በጣም ፍጥነት የሚያወሩበት ሙዚቃ በቴሌብዥን ተመለከትን፡፡ አራታችንም
ተመስጠን ሙዚቃውን አዳመጥን ፧ ሙዚቃዉን ለመረዳት ሞከርን፡፡ በየሳምንቱ መሰል ሙዚቃዎችን ለማጥናት ወደ ከተማ መመላለስ ጀመርን፡፡ ራፕ” እንደሚባል አናውቅም ነበር፤ ጥቁሮች እንግሊዝኛ አቀላጥፈው መናገራቸው እና የሙዚቃ ምት መጠበቃቸው ግን ገረመን፡፡
በኋላ ጅኒየር ከትምህርት ቤት ጓደኞቹ ስለ ውጭ ሃገሩ ሙዚቃ እና ዳንስ ብዙ ተማረ፡፡ ወደ ቤት ሲመጣ የሙዚቃ
ካሴቶችን ይዞ ይመጣና እኔ እና ጓደኞቼን ያለማምደናል፡፡ ሂፕሆፕ ንም አወቅን፡፡ የ ሂፕ ሆፕ ዳንስ እንቅስቃሴን፤ በዋናነት
ደግሞ ግጥሞቹን ማጥናት ያስደስተኝ ነበር፡፡ ግጥሞቹ የቃላት እውቀቴ ያሳደጉታል፡፡

አንድ ቀን እኔ እና ጓደኞቼ ሙዚቃ እያዳመጥን አባቴ መጣ i know you got a soul, ጥሩ ልብ እንዳለሽ አውቃለው የሚለውን የኤሪሪክ ቢ
እና ራኪም ሙዚቃ እያዳመጥን ነበር፡፡ አባቴ ሙዚቃዉን ሲስማ ፈገግ ብሎ ምን
እንደሚል ግን ይገባቹሃል?” ብሎ ጠየቀን፡፡ መልሳችንን ሳይሰማ
ጥሎን ሄደ እና በማንጎ ፣ ዘይቱን እና ብርቱካን ዛፍ መሃል የቅርቅሃ ወንበር ይዞ ተቀመጠ እና ቢቢሲ ራዲዮ ከፈተ፡፡ "ይሄ
ነው እንግሊዝኛ፤ ይሄን ነው ማዳመጥ ያለባችሁ አባቴ ቢቢሲ ማዳመጥ ሲቀጥል ጅኒየር ዳንሱን፤ እንዴት
ከዜማ ጋር መንቀሳቀስ እንዳለብን አሳየን፡፡ አንዳንድ ስንኞችን በቃል መያዝ ጀመርን፡፡ ስንለያይ "ሰላም ሁን ልጄ paece son" እና ሂጃለሁ ፤ወጣሁ (በቃኝ) I" ' m out የሚሉየ
ሃረጎችን ከራፕ ሙዚቃ ወሰደን መጠቀም ጀመርን፡፡ ማታ የወፎች እና የዶሮዎች ዝማሬ ይቀጥላል፡፡

ጥዋት የግጥም ደብተራችን እና ሙዚቃ ካሴቶችን በጀርባ ቦርሳችንን አንግተን ወደ ማታሩ ጆንግ ሄድን፡፡ ሰፊ ጂንስ ሱሪ በውስጥ የዳንስ ቁምጣ እና የስፖርት ቁምጣ፤ እጅጌ ሙሉ ቲ ሽርት በላይ እጅጌ ጉርድ ፤ ቲ ሸርቶች እና ማሊያዎች
እንለብስ ነበር፡፡ ሶስት ጥንድ ካልሶችን ደራርበን ቡፍ ያለ እንዲመስል እናደርግ ነበር።ሲሞቀን ልብሳችንን አውልቀን
,በትክሻ ላይ ጣል አርጎ መሄድ የጊዜው ዘናጭነት ነበር፡፡በሚቀጥለው ቀን እንመለሳለን ብለን ስላሰብን ሳንሰናበት ፤ የት እንደምንሄድ እንኳ ሳንናገር ነበር ከቤት የወጣነው፡፡ ቤታችንን
ለቀን ዳግም ላንመለስ እየሄድን እንደሆነግን አናውቅም ነበር፡፡

ገንዘብ ለመቆጠብ አስራ ስድስት ኪሎ ሜትር በእግር ለመጓዝ ወሰን፡፡ ዉብ የክረምት ወቅት ነበር፡፡ፀሃይዋም አልበረታችም፡፡እያወራን፣እየቀለድን እና እየተሯሯጥን መንገዱ ረጂም መሆኑ
ሳይስማን ተጓዝን፡፡ ወፎችን እና ዝንጀሮዎችን በአለት ደንጋይ
እየወረወርን እንበትን ነበር፡፡ ባገኘናቸው ብዙ ወንዞች ሰንዋኝ አንዱ ላይ ግን የመኪና ድምፅ ሰማን፡፡ ወንዙን በሚያቋርጠው ድልድይ ላይ መኪና ሲያልፍ ከውሃው ውጥተን በነጻ
እንዲወስደን ወደ መኪናዉ ሮጥን፡፡መድረስ ግን አልቻልነም፡፡

ስምንት ስአት አካባቢ ከአያቴ ሰፈር ካባቲ ደረስን፡፡ አያቴ ማሚ ካፓና በሚል ስም ትታወቅ ነበር፡፡ ቆንጆ ነበረች፤ ረጂም
ቁመት ሰልካካ ቆንጆ ፊት ከ ቡናማ አይን ጋር! እጇዋን ከወገቡዎ ወይም ራሷ ላይ አርጋ ትሽቀረቀራለች፡፡ እሷን ሳይ
የእናቴ ቁንጂና ከየት እንደመጣ ይገባኛል። ወንድ አያቴ ታዋቂ
አረብኛ ቋንቋ መምህር እና ባህላዊ ሐኪም ነበር። የአካባቢው ሰው
መምህር ብለው ይጠሩታል

ካባቲ ላይ ከበላን ከጠጣን በኋላ ቀጣዩን ጉዞችንን ጀመርን።አያቴ እንድናድር ፈልጋ