አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሁቱትሲ


#ክፍል_ሰባት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#ልጆቹን_ስሰናበት

ዳማሲን ከመሄዱ የቄሱ ግቢ የፊት በር ተንኳኳ፡፡ ያንኳኳው የቪያኒ የሁለተኛ ደረጃ መምህር የሆነው ንዚማ ሲሆን አመጣጡም ቄስ ሙሪንዚን ፈልጎ ነው፡፡ የሹክሹክታ ንግግር ከተደረገ በኋላ በሩ ተዘጋ፡፡ ወጥቼ ንዚማን በቄሱ ዛፍ ጥላ ስር ተቀምጦ አገኘሁት፡፡ በዚያ ደብዘዝ ባለው ብርሃንም ቢሆን በፊቱ ላይ የሚነበበውን ህመም ማየት አይከብድም፡፡
እንደፈራ ልጅ አድርጎታል - ‹‹ምን ያደርጉናል? የሚገድሉን ይመስልሻል?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡
በሩ ጋ መምጣቱን እንደሰማሁ በራስ ወዳድነት ስሜት ተውጬ የማበረታቻ ቃላት ይሰነዝርልኝና ጥንካሬ ይለግሰኝ ዘንድ ተመኝቻለሁ፤ ግን እርሱ ነው ሁለቱንም ላያገኛቸው ይሻቸው የያዘው፡፡
መምህር ንዚማ ሚስትና ልጆቹ ራቅ ባለ መንደር አማቱን ሊጠይቁ ሄደዋል፡፡ ደኅና ስለመሆናቸው ምንም የሚያውቅበት መንገድ ስላጣና ጥርጣሬ ስለገባው ተሰቃየ፡፡ ‹‹የማልተዋቸው ህልሞች አሉኝ›› አለ፡፡ ‹‹ሚስቴና ልጆቼ ሲታረዱና እፊቴ ሲቆራረጡ ይታየኛል፡፡ ይህን ለማስቆም እንደምታዪኝ ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ በአሁኑ ሰዓት እኮ ተገድለው መንገድ ላይ ተጥለው ነው የሚሆነው፡፡›› በቻልኩት መጠን ላጽናናው ሞከርኩ፤ ግን ምን ልለው እችላለሁ? እኔ ራሴ እርግጠኛ ባልሆንኩበት ሁኔታ ነገሮች ጥሩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ስንት ጊዜ ልናገር?
በጣም አቃሰተና ‹‹የት አባቴ ልግባ? ውጪ ያለው ሁሉም ሰው ገጀራ ይዟል፤ ጠመንጃ የያዙም አይቻለሁ፡፡››
‹‹ግድያው እስኪያቆም ድረስ እዚህ ቆያ፤ ከዚያም ከቤተሰብህ ትገናኛለህ›› አልኩት መንፈሱን ለማረጋጋት፡፡
ራሱን ነቅንቆ ቆመና ‹‹ልጄ፣ እዚህ አልቆይም፤ ሌላ የምሄድበት ቦታም የለኝ፡፡››
‹‹እጸልይልሃለሁ፡፡››
‹‹አመሰግናለሁ ኢማኪዩሌ፡፡››
ተሰናብቶኝ ቄስ ሙሪንዚ ይጠብቁት ወደነበረበት ወደ ቤቱ ፊት ለፊት ሄደ፡፡ ቄሱ ንዚማን እንደማይሸሽጉት ነግረውት ሳይሆን አይቀርም በሩን በእጃቸው ሲያመላክቱት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ወጣ፡፡ በኋላ እንደሰማሁት ይህ ምስኪን ሰው ተቆራርጦ የተገደለው ከቄሱ ቤት ጥቂት መቶ ሜትሮች ርቆ ባለ መንገድ ላይ ነው፡፡ ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ ብቻዬን በተቀመጥኩባት በአንዲት ትንሽ መኝታ ክፍል ቄስ ሙሪንዚ ሌሎች አምስት ቱትሲ ሴቶችን በጸጥታ አስገቡ፡፡ ሁሉም የአካባቢያችን ሰዎች እንደሆኑ ባውቅም አንዳቸውንም በደንብ አላወቅኋቸውም፡፡ ሴቶቹን ወደ ክፍሏ ሲያመጧቸው ቄሱ ተደናግጠዋል፡፡ ‹‹ፍጠኑ፣ ፍጠኑ!›› የሚንሾካሾኩት በጣም በፍጥነት ስለሆነ ልንሰማቸው አልቻልንም፡፡ ‹‹እዚህ ጠብቁኝ፤ ታዲያ ደሞ ዝም በሉ እሺ›› አሉን በሩን ዘግተው ሲወጡ፡፡ አብረን የነበርነው ስድስት ቱትሲ ሴቶች ከሞላ ጎደል እርስ በርስ የማንተዋወቅ ቢሆንም ሁለት ነገሮች ግን ያመሳስሉናል - እየታደንን መሆናችንና የምንደበቅበት ምንም ስፍራ የሌለን መሆኑ፡፡ ለመናገርም ሆነ ለመተዋወቅ በጣም ፈርተን እርስ በርሳችን እየተያየን ቆመናል፡፡ ውጪ ምን እየተከሰተ እንዳለ አናውቅም፣ ከቄሱ ድንጋጤ እንደተረዳነው ግን ነገሮች ተበለሻሽተዋል፡፡
ከቤቱ ውጪ ድንገት ጩኸቶች ይሰሙ ጀመር - በእጆቻችን ላይ ያሉትን ጸጉሮች እንዲቆሙ ያደረጉ እጅግ የሚያስጨንቁ የሲቃ ጩኸቶች፡፡ ከዚያ በኋላ አሰቃቂዎቹ ንዴት የሚንጸባረቅባቸው ድምጾች መጡ፣ ‹‹ግደሏቸው! ግደሏቸው! ሁሉንም ግደሏቸው!››
ብዙ መጯጯህና የድረሱልኝ ጥሪ ይሰማል፤ ‹‹ግደለው! ግደሉት! ግደላት!›› የሚልም ድምፅ ይከተላል፡፡
ፈራን፡፡ ከሴቶቹ አብዛኞቹ መሬት ላይ ተኙ፣ አልጋም ስር ተደበቁ፡፡ በጣም ከመንዘፈዘፌ የተነሣ መሬቱም ጭምር የሚንቀጠቀጥ መሰለኝ፡፡ ዓይኖቼ ቤቱን መደበቂያ ፍለጋ ሲያስሱ በኮርኒሱ ላይ ባለች አንዲት ቀዳዳ ላይ አተኮሩ፡፡
‹‹እዚያ ላይ መደበቅ እንችላለን›› አልኩ ወንበር ወደ ቀዳዳዋ ስር እየሳብኩና በእጆቼ ወደላይ እየተንጠራራሁ፡፡ አንዷን ሴትዮ ወደ ላይ ስቤ አወጣኋት፡፡ ሁለታችን ደግሞ አንድ ላይ ሌሎቹን በቀዳዳዋ ሽቅብ ሳብናቸው፡፡ ከዚያም ቄሱን እስኪመለሱ እንጠብቃቸው ያዝን፡፡ በዚያች በተጨናነቀችና በምታፍን ቦታ ልብሶቻችን በላብ እስኪጠመቁና አየር እስኪያጥረን ድረስ ጭብጥ ብለን ተቀመጥን፡፡ ቄስ ሙሪንዚ ከሁለት ሰዓታት በኋላ ተመልሰው በቤቱ መካከል ቆመው ራሳቸውን በግራ-ግባት ያኩ ገቡ፡፡
‹‹የት ይሆኑ? አይ አምላኬ እዚህ ነበር የተውኳቸው!››
በጣም ባልፈራ ኖሮ ሳቄን እለቀው ነበር፡፡ በቀዳዳዋ ራሴን አውጥቼ ‹‹እዚህ ነን!›› ስል አንሾካሾክሁ፡፡
ቄሱ ራሳቸውን ነቅንቀው ሊያናግሩን መፈለጋቸውን ገልጸውልን ወዲያውኑ እንድንወርድ አዘዙን፡፡ ፊታቸው አሁንም በጣም እንደተቸገሩ ያስታውቃል፡፡ ‹‹ሁላችሁም እንደፈራችሁ አውቃለሁ፤ በእርግጥ ልትፈሩም ይገባችኋል›› አሉን፡፡ ‹‹ውጪ ላይ ነገሩ ሁሉ ከቁጥጥር ውጪ ሆኗል፡፡ ገዳዮቹ በሁሉም ሰው ቤት እየዞሩ ነው፡፡ ዛሬ እኔ ቤት አልመጡም፤ በማናቸውም ሰዓት ግን ሊመጡ ይችላሉ፡፡ እውነቱን ንገረን ካላችሁኝ ምን እንደማደርጋችሁ አላውቅም… እስኪ ላስብበት፡፡››
ፍራቻችንን አይተው ወዲያውኑ መፍትሔ አመጡ፡፡ ‹‹አይዟችሁ አላስወጣችሁም›› ሲሉ አረጋገጡልን፡፡ እስኪ በጥሞና አዳምጡኝ፡፡ ነገ ሲነጋጋና ማንም ከመኝታው ሳይነሳ ግድያው እስኪያቆም ድረስ ወደምትቆዩበት አንድ ሌላ ክፍል እወስዳችኋለሁ፡፡ በቤቱ ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዳስወጣኋችሁ እነግራቸዋለሁ፡፡ የእናንተን እዚህ መኖር የማውቀው ብቸኛ ሰው እኔ ብቻ እሆናለሁ፡፡ ተራ ሐሜት እንኳን ሁላችንንም ሊያስገድለን ይችላል፡፡ እነዚህን የግድያ ዘመቻዎች ካሁን በፊት አይቻቸዋለሁ - አንዴ የደም ጥማቱ ከጀመረ ማንንም አታምኑም፣ የራሳችሁንም ልጆች ሳይቀር፡፡ አንድ ሰው ካገኛችሁ አለቀላችሁ! ስለዚህ በእግዚአብሔር ደማችሁ በቤቴም ሆነ በጄ እንዲፈስ አልፈልግም፡፡››
ከዚያ ቄሱ ወደኔ ዞረው እንደ ቢላዋ የቆረጡኝን ቃላት ነገሩኝ - ‹‹ወንድምሽና ጓደኛው እዚህ መቆየት አይችሉም፡፡ አሁኑኑ ሄደው ሕይወታቸውን ያትርፉ፡፡ ወንዶችን ማስጠለል ለኔ በጣም አደገኛ ነው፡፡ እንደምታዪው እናንተ ሴቶቹም በዝታችሁብኛል፡፡››
በሙሉ ዓይናቸው ሊያዩኝ አልቻሉም - ቪያኒንና ኦገስቲንን በዚያ ሰዓት ማባረሩ በእርግጠኝነት ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ወደ ሞታቸው መላክ ማለት እንደሆነ ሁለታችንም እናውቃለን፡፡
‹‹እንዴ! ቄስ ሙሪንዚ ኧረ እባክዎት! እንዴት -››
ጸጥ በይ በሚል ዓይነት ምልክት ጣታቸውን ከንፈራቸው ላይ አድርገው ንግግራችንን ቋጩት፡፡ ‹‹መሄድ አለባቸው፣ ኢማኪዩሌ፡፡ ልወስዳችሁ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ስመጣ ወደ በሩ ወስደሽ ታስወጫቸዋለሽ፡፡ ታዲያ ማንም እንዳያይሽ ተጠንቀቂ፡፡››
ቄሱ ቤቱን ለቀው ሲሄዱ በሹክሹክታ ረገምኳቸው፡፡ ለኛ ከለላ በመስጠት እንደ ቅዱስ እየሰሩ እንዴት እንደገና ተገልብጠው ወንድሜንና ኦገስቲንን ወደ ገዳዮቹ እጆች ያስገቧቸዋል?
እያዳኑን የነበሩትን ሰው ልቆጣቸው አልፈለግሁም፣ ቢሆንም ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም - የባሰውንም ጠረጠርኩ፡፡ በሌሎች የግድያ ዘመቻዎች አንዳንድ የሁቱ ወንዶች ወንድ ቱትሲዎችን ትተው ሴት ቱትሲዎችን
👍1