አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ


#ክፍል_ዘጠኝ(🔞)


መቼም ወድጄ አይደለም፤በሌሎቹ ተወዳዳሪዎች ላለመብለጥ በጋዳፊ ዙሪያ የተጻፉ ነገሮችን ማንበቤ የግድ
በቅርቡ አንድ የአውሮፓ ሸሌ የጣልያኑን ሴት ወዳድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ በርልስኮኒ ለማጥማድ ከ10 ሺ ዩሮ በላይ ማውጣት ነበረባት እቅዷ ግን ተሳክቶላታል። ጋዳፊ አብዛኛውን የሊቢያ ነዳጅ የምትሸጠው በሲልቪዮ ቤርልስኮኒ ለምትመራው ጣልያን ነው፤ከመሪዎች በኮሚክነታቸው ተለይተው የሚታወቁት በርሌስኮኒ በአንድ ኦፊሴላዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወቅት ከጋዳፊ ጋ ሲገናኙ ለቆንጆ ሴት
እንደሚደረገው የጋዳፊን እጅ አይበሉባ ዝቅ ብለው በመሳም የአለም መነጋገሪያ ሆነው ነበር፡፡

ጋዳፊና በርልስኮኒ በርካታ የምስራቅ አውሮፓ ቆነጃጅት የሚታደሙበት ድብቅ ፓርቲዎችን በተለያየ ጊዜ
አዘጋጅተው በጋራ አለማቸውን እንደቀጩ በርካታ የምእራቡ አለም ሚዲያዎች በተለያየ ጊዜ ጽፈዋል፡፡እኔ በበኩሌ እንደዚህች ሴት የቤርልስኮኒ የልብ ወዳጅ የሆኑትን የሊቢያውን መሪ ለማጥመድ የገንዘብ ወጪ
ባይጠብቀኝም ከባድ የስነ ልቦናና የንባብ ዝግጅት ማድረጌ ግን የግድ ነበር፡፡ ስለ ጋዳፊ ባነበብኩበት ወቅት
ግን እግረ መንገዴን ያነበብኳቸው ሆኖም እውነት ይሁኑ ሀሰት ያልተረዳኃቸው ንባቦች አጋጥመውኛል፡፡

ለምሳሌ ጋዳፊ ለእያንዳንዱ ሊቢያዊ ቤት ሳይኖረው የኔ ቤተሰብ ቤት አይሰራም ብለው ወላጆቻቸውን
የሚያኖሩት ድንኳን ውስጥ ነው የሚል ነገር አንብቢያለሁ፡፡ በሊቢያ ማንኛውም ዜጋ የመብራትም ሆነ የዉሀ አይከፍልም፡፡ አንድ ሊቢያዊ ማግባት ሲፈልግ ሊቢያ ማዘጋጃ ቤት ሄዶ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
ምክንያቱም የሰርግ ወጪው የሚሸፈንለት በሙአመር ጋዳፊ ስለሆነ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ማዘጋጃ ቤቱ 60
ሺ የሊቢያ ዲናር ትዳር ማሞቅያ አሎዋንስ ይሰጠዋል፡፡ የሊቢያ ባንኮች ለዜጎቻቸው ያለምንም ወለድ ብር ያበድራሉ፡፡ ቤት ልክ እንደ ሰብአዊ መብት ስለሚታይ ማንኛውም ህጻን ሲወለድ ቤት በስሙ ይገነባለታል፡፡ ማንኛውም ሊቢያዊ መኪና ልግዛ ሲል 50 በመቶ መንግስት ይሸፍንለታል፡፡ እያንዳንዱ
ከነዳጅ የሚገባ ገቢ አምስት በመቶ ወደ እያንዳንዱ ሊቢያዊ ዜጋ ባንክ አካውንት ገቢ ይደረጋል፡፡ ስለነዚህ
ጉዳዬች ኡስማንን ጠይቄው በአመዛኙ እውነት እንዳልሆኑ ገልጾልኛል፡፡

#ለጋዳፊ_ሆስተስነት_ምልመላ

እንዳይደርስ የለም ሰአቱ ደረሰ፤ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ 35 የምንሆን ቆነጃጅት ሸራተን ተገኘን፡፡
አብረውን ሶስት ሴት ጋዜጠኞች ነበሩ፡፡ ከኔ ጋር የነበሩት ተመልማዮች አብዛኞቹ ከገጽታቸው የኮሌጅና
የዩኒቨርስቲ ትምህርት የቀሰሙ ይመስላሉ፡፡ሴቶቹ ከዚህ በላይ እንዳይበዙ በልቤ ተመኘሁ፤ጥቂት በኔ ደረጃ ውብ የሆኑ ሴቶችንም በርቀት ተመልከቼያለሁ፡፡ ኩሪፍቱ ገስት ሀውስ ውስጥ ከነበርነው ሴቶች ክልሷ ልጅ ስትቀር ሁሉንም አየኃቸው፡፡ ሶስና በጥግ በኩል ተቀምጣለች፡፡ ሲበዛ ሜካፕ
ተለቅልቃለች፡፡ የምር ቆንጆ ቆንጆ ልጆች ተመልምለው መጥተዋል፡፡ ይህንን ሁሉ ምልመላ ያካሄደው ኡስማን ብቻ ነው ብዬ ለማለት ከበደኝ፡፡

ብዙም ሳንቆይ እንዲት ሴት እየመራች ጋዳፊ ወዳረፉበት ቪላ ወሰደችን፡፡ ሴትዬዋን የሆነ ቦታ አውቃታለሁ

ሆኖም ግን ማስታወስ እቃተኝ፡፡ በኃላ ላይ ሸራተን ሎቢ ውስጥ ጀኔራሉን ስጠብቀው መጥታ ያናገረችኝ
ሊቢያዊት እንደሆነች አስታወስኩ፡፡ ዛሬ የወታደር መለዮ ለብሳለች፡፡ ገዘፍ ያለች ሆና ጠየም ያለች አረብ ናት፤ አብራት የሆነች ጠብደል ጥቁር ሴት አለች፡፡ ይቺ ደግሞ ያው ጋዳፊ እንደ ቻድ ካሉ የአፍሪካ አገራት ያመጧት ድንግል አጃቢያቸው ትሆናለች ብዬ አሰብኩ፡፡እንግሊዝኛዋ ሲበዛ ቀሽም የሚባል
ነው፤በቅርብ ርቀት ጋዳፊ ካረፉበት ቪላ(Deluxe Room/Luxury Vila) የሊቢያ ሰንደቅ አላማ(ባንድራ)
ተሰቅሎ ሳይ ባለሁለት ፎቁ ቪላው ውስጥ ጋዳፊ ያረፉበት መሆኑን ለማረጋገጥ ቻልኩ፡፡

በሆቴሉ ደንብ አንድ ደምበኛ እነዚህን ቅንጡ ባለሁለት ፎቅ ቪላዎች ለቀናት ሲይዝ በቪላው እስከሚቆይበት
ጊዜ ድረስ የሀገሩ ባንዲራ እንደሚውለበለብ እውቃለሁ፡፡ ይህንን ያወቅኩት ከዚህ ቀደም አሁን ጋዳፊ
ካረፉበት ከፍል ሳይሆን ከሱ ጎን ከሚገኝ ሌላኛው ቪላ ከአንድ ኳታራዊ ጋር የማደር እድል ገጥሞኝ ስለነበረ ነው፡፡የቪላውን ውስጣዊ ክፍሎች ውበት ለመግለጽ ቃላት አይበቁኝም፡፡ሳሎን፣ጃኩዚ፣የመዋኛ
ገንዳ፣ባር፣የጥናት ከፍል፣የመኝታ ከፍል መእት ነገር አሉት፡፡ኳታራዊው ባለሀብት በቀን ለቪላው 24000
ዶላር ይከፍል እንደነበር አጫውቶኛል። አሁን ዋጋው ከዛም በላይ ሊሆን ይችላል፡፡እኔን የገረመኝ ግን
ዋጋው አይደለም፡፡ከውጭ እንደ ተራ ነገር የምናየው ቪላ ውስጡ አቅል የሚያስት ዉበት መደበቁ ነው
የቪላውን ውስጣዊ ዉበት ለጓደኛቼ እንዴት ብዬ እንደምናገር ያን ሰሞን ግራ ገብቶኝ ነበር፡፡ በኃላ እንደሰማሁት ሼኩ አገር ውስጥ ሲያድሩ እዚህ ቪላ ውስጥ ነው የሚስተናገዱት፣የሚያድሩት፡፡

ቪላው በራፍ ጋ ስንደርስ የተወሰኑት የጋዳፊ ደናግላን ሴት እጃቢዎቹ ተከፋፍለው ፈተሹን፤ሁሉም
ከወታደራዊው ቆባቸው፣ሚሊተሪ የደንብ ልብሳቸው እና ጉልበታቸው ድረስ የሚደርስ ቡትስ ጫማቸው ጋር ያስፈራሉ፡፡ ድንግል መሆናቸውን ሳስብ ግን ሳቄ መጣ፡፡ወደ ውስጥ ዘለቅን፤ሁለቱ
ፕሮቶኮሎች ተከፋፍለው 17 የምንሆነውን ወደ አንድ ከፍል ወሰዱን፡፡ ወደ መኝታ ከፍል ነበር የሚወስዱን
እጀግ ዉብ ነው፡፡ የጋዳፊ መኝታ ሊሆን እንደሚችል ጠረጠርኩ፤ሁላችንም ደንግጠናል፣በውስጣችን ብዙ ጥያቄዎች ይርመሰመሳሉ፤እንዷ ልጅ በግልጽ በአማርኛ ቅሬታዋን ገለጸች።

ለምንድን ነው ካልጠፉ ክፍል መኝታ ክፍል ያመጡን?ለምን ሌላ ከፍል አልወሰዱንም?ይሄ ነገር ሌላ
አላማ ከለው አሁኑኑ ቢነግሩን ይሻላል?” የልጅቷን ቅሬታ የሰማን ሁሉ ክው ብለን ቀረን፡፡ ቅዳሜ ቅዳሜ ከሚታተም ለጊዜው ስሙን ከማላስታውሰው ጋዜጣ የመጣች ልጅ የልጅቷን ቅሬታ ስትሰማ እስከሪብቶና ወረቀት አምጥታ
መጻፍ ጀመረች፡፡ እነዚህ ሰዎች ጋዳፊን እስቀይመው ለስንት ቀን የለፋሁበትን ነገር እንዳያስቀሩብኝ ስል ፈራሁ በጋዜጠኛዋ ድርጊት ተበሳጨሁ

የተወሰነው ሰፊው አልጋ ላይ ተቀመጥን፡፡ ዝምታ በመሀላችን ሲሰፍን አንዳንድ ሴቶች የጎንዮሽ ወሬ ጀመሩ

ከጎኔ አጭር ሚኒ ለብሳ የተቀመጠችው አስር ጊዜ ሚኒዋን ለማስረዘም ጫፉን ይዛ ትጎትተዋለች
“እንዲህ ከምትጨናነቅ ለምን ድርያ ለብሳ አትመጣም ነበር” አለችኝ በስተቀኜ የተቀመጠች ሌላ ባለፍሪዝ ሴት ድምፄን አፍኜ ሳቅኩኝ፡፡ “እኔ ምልሽ ጋዳፊ የሚመጡ ይመስልሻል? አይገርምሽም! በቲቪ ብቻ ነው አይቻቸው የማውቀው” አለችኝ ባለ ሚኒዋ ልጃገረድ: አይ ከኔ ጋር ግን ጠዋት ጠዋት ሁልጊዜ ማክያቶ አብረን እንጠጣለን” ብዩ ላሾፍባት እሰብኩና ከአፊ መለስኩት። ሁሉም ሴቶች እርስ በእርስ ፍርሃታቸውን በማንሾካሾክ ይገልጻሉ፡፡ ፈረስ የሚያስጋልበው የጋዳፊ መኝታ ቤት ደማቅ የሀሜት ክበብ መሰለ

ድንገት ሁለት ባለወርቃማ ጸጉር የምስራቅ አውሮፓ ገጽታ ያላቸው ሴቶች ወዳለንበት ክፍል ሲገቡ ሁሉም
ሰው አፉን ያዘ ሲበዛ ረዥምና ውብ ናቸው፤እንደ ጋዳፊ ጋርዶች በወታደር መለዮ አይደሉም፤እንግሊዝኛ
ሁለተኛ ቋንቋቸው እንደሆነ ከቅላጼቸው ያስታውቃል፤

"Hello ladies! On behalf of our supreme leader, I welcome you to this special event. Now,
we want to take some photos of you both in groups and individually....! Can you help us
please?”

ሁላችንም ከተቀመጥንበት ብድግ አልን በዲጂታል ካሜራ በርካታ
👍32