አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
565 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ዳግመኛ ለማናገር፣ ይቅርታ ለመጠየቅ ፊቷ መቆም ብፈልግም ፈራኋት። ሳያት የሆነ ሰው በደሌን ተነቅሶ፣ ነውሬን የሚለፍፍ ዓይነት ድብርት ይዳበለኛል። በቀን ብዛት ይሄ ስሜት ድል ይነሳል ብልም አልሆነም። ሁሌም ሳያት የሚሰማኝ ስሜት ትኩስ ድብርት ነው። እኔ ከሚሰማኝ ስሜት እሷን ስበድላት የተሰማት እና ከሚሰማት አይበልጥም ብዬ መደበቴን ታገልኩት። አንዳንድ ቀን ያበድኩት እኔ የበደለችኝ እሷ ብትሆን እያልኩ እስክመኝ ድረስ እረፍት አጣሁ። ትግሌ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ከሃኒቾ ጋር የነበረኝን ትዝታ፣ የበደልኳትን በደል፣ ፊት መንሳቷን፣ ለማምለጥ እሷም ትዝታዋም  አይደርሱበትም ብዬ ወዳሰብኩት ቦታ ለሚስቴ አሳማኝ የሚመስል ሰበብ ደርድሬ ቤታችንን አከራይተን ያን ሰፈር ለቀን ሄድን።

በሽሽት የበዳይነት ሕመሜን ድል አደረገው ከሆነ አየዋለሁ!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢3819👍1🔥1
አትሮኖስ pinned «#ማበድ_ይሻላል አእምሮዋን ያማታል፤ ሃና ትባላለች።  በኮሮኮንቹ፣ በአቋራጭ፣ በድልድዩ በኩል አልፋ ቤታችን ትመጣለች፤ ስትመጣ ሰዓት አትመርጥም። የአቅሜን ለማንም ሳልናገር እንድትድን ጥሬያለሁ፤ አልተሳካልኝም እንጂ። መዳኗ በእኔ እንዲሆን አልተመረጠም ወይም ከነጭራሹ እንድትድን አልተፈቀደም። አንዳንድ ቀን መጥታ በሩን በኃይል ስታንኳኳ ልጄ ከእንቅልፉ ይባንናል። በር የሚከፍት ሲጠፋ በጓሮ ያለውን መስኮት…»
#ውርስ_ሕይወት

አባቴ ለብዙ ዓመታት ታስሮ ነበር። አስራ አራት ዓመቴ አካባቢ ተፈታ፤ የተወለድኩት ያን ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፤ አባቴ ሲፈታ እኔም ተፈታሁ። አባቴ አስራ አራት ዓመት ድረስ ሳስብ የነበረውን ቀስ እያደረገ ዳመጠው።

አባቴ የላላ፣ የተቆጠበ ማኅበራዊ ግንኙነት ያለው፣ ረጋ፣ ጀንተል፣ ኮስተር ያለ ግለሰብ ነው። ብዙ ሰዓት ዝም ይላል፤ የስሜት መለዋወጥ አይታይበትም፤ ጺሙ በብዙ ሲያድግ በመቀስ በትንሹ ይከረክመዋል፤ ልብሶቹ፣ የሚጠቀምባቸው እቃዎች ስትር ያሉ ናቸው።

ከእስር እንደተፈታ እኖር ከነበረበት ከእናቴ ቤተሰቦች ቤት ወስዶ ተከራይቶ ከነበረው ሰፊ ግቢ ውስጥ መኖር ጀመርን።

ቤታችን ቅዝቅዝ ያለ ነው። ቅዝቅዝ ያለው ብዙ ወንድም እና እህት ስለሌለን ነው ወይስ እናት ስለሌለኝ ነው፣ አልያም ደግሞ አባቴ ከሰው ጋ በደማቁ ስለማይግባባ፤ ምክንያቱን እርግጠኛ ባልሆንም ውጤቱ ግን ቀዝቃዛ ሰፊ ትልቅ ግቢ ውስጥ ነው የኖርነው።

መቀዝቀዙ የገባኝ፣ በየአገጣሚ የትምርት ቤት ጓደኞቼ ጋ ቤታቸው ስሄድ ይሳሳቃሉ፣ ይጨቃጨቃሉ፣ ይካሰሳሉ፤ በዚህም እቀና ነበር። እጦታችን ያወቅነው ዕለት ጉድለት ይሰማን የለ?!

ስሜ ዋሲሁን ቢሆንም አባቴ ዋሴ ነው የሚለኝ፤ ምንም ነገር ሲያስደርገኝ ሆነ ሳደርግ አምኜበት እንዲሆን አድርጎ ሠርቶኛል። ከፍቶኝ ለምቦጬን ከዘረገፍኩ "ዋሴ ማኩረፍ የአቅመቢስነት ማሳያ ነው፤ መጀመርያ የከፋህን፣ ቅር ያለህን በእርጋታ አስረዳ" እያለ የውይይት ባሕል ልቤ ውስጥ እያኖረ ነው ያሳደገኝ።ያምንብኛል። እንደመታመን አበርቺ እጽ እንደሌለ ያወቅኩት ለራሴ ያለኝ በጎ እና የእችላለሁ ወኔ ከብዙ አቻዎቼ መለየቱን እና ምንጩን ስረዳ እና ሲገባኝ ነው።

በጨዋታ መሀል

“ይሄውልህ ዋሴ ሁልጊዜ እሮሮ የሚዘበዝቡ፣ ሁልጊዜ ሰው ማጣጣል ላይ የተመሰጡ ሰዎች፣ ሁልጊዜም አልተሳካልን ዓይነት ደረት የሚመቱ፤ ለውድቀታቸው ሰው የሚወቅሱ ሰዎች፣ ለመውደቃቸው ኃላፊነት ከማይወስዱ ጋ አትወዳጅ" ይላል።

ይሄ ሰውዬ ጓደኛ የሌለው ለውድቀታቸው ኃላፊነት የሚወስዱ አጥቶ ይሆን እላለሁ አንዳንዴ።

ደግሞ በሌላ ቀን እጅግ ብዙ ቆይቶ

“ዋሴ" ይላል። ልገልጸው የማልችለው አጠራር አለው። ሁሉም ሰው ዋሴ ብሎ ቢጠራኝም በእሱ ዓይነት መንገድ የሚጠራኝ ሰው አልገጠመኝም። የሆነ አለኝታዬ ዋስትናዬ የሚለኝ ነው የሚመስለኝ፤ እወድሃለሁ የሚለኝ በአጠራሩ ውስጥ ባለው ድምጸት በኩል ነው።

"ይሄውልህ ዋሴ ሰው አንተ ላይ ስለሚይዘው . አቋም እንዳትጨነቅ፤ ሰው ለማስደሰት ከዳከርክ የራስህ እውነት ሳይኖርህ ታልፋለህ" ይላል።

አባቴ ጥንቅቅ ያለ ሰውዬ ነው፤ ነፍስ እያወቅኩ ስሄድ ነው ለእሱ ያለኝ ፍቅር እና አክብሮት ያየለው።

ብዙ ዝም ስለሚል ሲያወራ ተስገብግቤ ነው የምሰማው፤ እጦትን የመሰለ ነገሮችን ተፈላጊ አድራጊ ያለ አይመስለኝም እኮ::

"ይሄውልህ ዋሴ"

ወዬ አባቴ

“ስንት ዓመት መቀመቅ ያወረደኝ ሐቀኝነቴ ነው፤ ኃላፊነቴን በአግባቡ ለመወጣት ስዳክር፤ ብልሹ ካልኩት አሠራር ጋ ስታገል፣ መደለያቸውን በጄ ስላላልኩ መቀመቅ ውስጥ ወረወሩኝ።

ብቻዬን ቆምኩ!

በእርግጥ እኔ ቆምኩ ልበል እንጂ ለብዙ ሰው ወድቄያለሁ፤ የወደቀ ከሚለው ጋ ማበር የሚፈልግ ማን አለ? ወደቀ ብለው ተዘባበቱብኝ፤ ስንት ዓመት ለመኖር ነው ግን እንዲህ የከፉት እላለሁ፤ ስለ ተቻለ ብቻ አሳማም ጅብም እንዴት ይኮናል?!

ይኸውልህ ዋሴ

ለእራስህ እውነተኛን መሆን የመሰለ የሕሊና እረፍት የለም፤ ከራስ ጋ ሰላም ከመሆን በላይ ምን ሽልማት አለ? ወድቋል ብለው ሲዘባበቱ እኔ ያልሠራሁት መጥፎ ተግባር ምቹ ትራስ ሆኖኝ ከሰላሜ ጋ ነበርኩ።

አንተ እንዲህ የምትወደኝ እኮ፣ አንተ እንዲህ የጎበዝክልኝ'ኮ ለእውነቴ የተሰጠኝ ሽልማት ነው፤ በዚህ ዕድሜ ጤነኛ የሆንኩት እኮ አምላክ ለመታመኔ የሰጠኝ ስጦታ ነው፤ ሰው ሽልማት ጥሬ ገንዘብ ብቻ ይመስለዋል" ይል'ና በስሱ እንደሁሌው ጥርሱን ገለጥ አድርጎ ፈገግ ይላል፤ አሳሳቁ ሞገስ አለው!!

“እኔን ያሳቀሉኝ እኮ በእስተርጅና የሚመታቸው ልጅ፣ የማይወዳቸው ልጅ ኖሯቸዋል፤ ያመኑት ክዷቸዋል፡፡

“እግዚሃር በሚደግሱት ዝክር የሚሸወድ መስሏቸዋል" እያለ አፉን በትንሹ ከፍቶ ጥርሱን እያሳየኝ ፈገግ ይላል።

አባቴ የሚለኝን ሁሉ እየሆነ ያሳየኝ መምህሬ ነው።

“ይኸውልህ ዋሴ ጥቃቅን ነገር ላይ አታተኩር፤ የምትኖርለት መርሕ ይኑርህ፤ እመቀመቅ ድረስ የምትሄድለት ሕልም እና መርሕ ይኑርህ።"

የሚኖርን እውነት ከመስማት በላይ ምን ሐሴት አለ??

ብቻዬን መቆም አስተምሮኝ፣ ጥቂት ቀን ታሞ ጥቂት ቀን አስታምሜው አለፈ። ብዙ ቆይቼ እስር ቤት ሳለ የጻፋቸውን ሐሳቦችን እና ገጠመኞቹን ሳነብ ከዕድሜዬ በላይ አበሰለኝ።

ሕይወቴ ላይ የብስለቱ ዳና ያረፈብኝ የአባቴ ልጅ እኔ ዋሴ ነኝ!!!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
46👏18
አትሮኖስ pinned «#ውርስ_ሕይወት አባቴ ለብዙ ዓመታት ታስሮ ነበር። አስራ አራት ዓመቴ አካባቢ ተፈታ፤ የተወለድኩት ያን ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፤ አባቴ ሲፈታ እኔም ተፈታሁ። አባቴ አስራ አራት ዓመት ድረስ ሳስብ የነበረውን ቀስ እያደረገ ዳመጠው። አባቴ የላላ፣ የተቆጠበ ማኅበራዊ ግንኙነት ያለው፣ ረጋ፣ ጀንተል፣ ኮስተር ያለ ግለሰብ ነው። ብዙ ሰዓት ዝም ይላል፤ የስሜት መለዋወጥ አይታይበትም፤ ጺሙ በብዙ ሲያድግ በመቀስ…»
#ሊያብብ_ሲል

ሱስ ሳይበላው፣ ሲጋራ መግዣ መለመን ሳይጀምር፤ ጉስቁልና ሳያፈዘው፤ ለልብሱ መቆሸሽ ደንታ ቢስ ከመሆኑ በፊት፤ ሰዎችም ሲጣራ ባልሰማ መሄድ ሳይጀምሩ፤ ቃል አባይ ከመሆኑ በፊት፤ ክብሬ ማለት ሳያቆም፤ ለትንሽ ለትልቁ መላክ ሳይጀምር በፊት… ቆንጆ፣ ተወዳጅ፣ ዘናጭ ነበር። ከጓደኞቹ በላይ ድምቅ ያለ ልጅ ነበር፤ ቆንጆ አማርጦ ይሰክስ ነበር፤ የጸጉሩን ፍሪዝ በመሰታወት አስር ጊዜ እያየ አስር ጊዜ ያስተካክል ነበር።

ሕልመኛ ነበር። እንደ ሁሉም ወጣት ሀብታም መሆን፤ አዋቂ መሆን፤ ቤተሰቦቹን የመርዳት ሕልም ነበረው። የተንሸዋረረ አራድነት አሳስቶት የለኮሳት ሲጋራ፤ ለሳቅ ብሎ የተጎነጫት አረቄ፣ ለሙድ ብሎ የቀነጠሳት የጫት ቅጠል ስትደጋገም አፈዘዘችው፤ ሕልሙን ወጣትነቱን ክብሩን አረገፈችው።

ማንም ብርቱ ነኝ ቢል ታግሎ የማያስመልሳትን ወጣትነቱን ለማያቀው ጣዖት እየሰዋት ነው።

ጥግ ላይ ተቀምጦ ዘመን ሂዶ ዘመን ፤ በመጣ ቁጥር የሚመጡ ለውጦችን ከዳር በትዝብት እየተመለከተ ጊዜው እንዴት ነው የሚሮጠው? የሚል ይመስለኛል።

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
14👍5🔥3
#ባል_ተመኘሁ

አስተዳደጌ ነው የገደለኝ። አስተዳደጌ መጠበቅ እና ማግኘት ነበረበት። አባቴ ሁሌ ቃል ይገባልኛል፣ የሆነ ነገር በጥሩ መልኩ ሳደርግ ይሸልመኛል፣ እናቴ የቤት ሥራ ስሠራ ታመሰግነኛለች፣ ትመርቀኛለች። በምስጋና እና በስጦታ ተንበሽብሼ ነው ያደግኩት፤ ለዛ ነው የጠበቅኩትን ሳጣ የምታመመው ብዬ ሁላ አውቃለሁ፤ ግን በእሱ ብቻም አይደለም!

የማያቸው ሮማንቲክ ፊልሞች እና የማነባቸው መጻሕፍት ናቸው፤ ከፍቅር የሚገኘውን ደስታ እና ሁኔታ ከሚገባው በላይ አጋነው፣ ከቅዱስ የማገኘውን ነገር ሁሉ ያሳነሱብኝ ብዬም አምኜ አውቃለሁ።

ግን እሱ ብቻ አይደለም!

ቅዱስ ራሱ ነው ፍቅረኛሞች እያለን አባቴን መስሎ እና ሆኖ ተንከባክቦ ኑሮ ስንጀምር እርግፍ አድርጎ ትቶኝ የተፈላጊነት ስሜቴን የገደለው።

ኖ በእሱ ብቻም አይደለም!

ገመናዬን፣ ሚስጥሬን፣ ስሜቴን ለሰው ስለማልናገር ነው መፍትሔ ያጣሁት፤ የማይቀለኝ! የሚያብከነክነኝ!

ግን ዋናው ምክንያት ይሄም አይደለም!

ራሴን ከዋናው የሕመሜ ምክንያት፣ የድባቴዬን ምንጭ ለራሴ አልነግር ብዬ ነው።

ቅዱስ አይፈልገኝም። ሲመጣ ባዶ ቤት ቢቆየው ቅር አይለውም። ለስሜቴ ደንታ የለውም። ቆይ ስንት ወራቶች ሞላን ወሲብ እንኳን ከፈጸምን? አልጋ ከለየን ስንት ጊዜ ሆነን? ስንቴ ተዘገጃጅቼ ሊወጣ ሲል፣ ሲገባም ላነሳሳው በሚል አጋጣሚ አስመስዬ ራቁቴን የታየሁት፣ ቀስቃሽ አለባበስ ስንቴ ነው የለበስኩት?

እሱ ግን አያየኝም።

እንዲያዝንልኝ ታመምኩ፤ ኡኡ ነደድኩ፣ ጠዘጠዘኝ፣ ወጋኝ አልኩ፤ ታከሚ ይላል እንጂ አይደነግጥም። ወጣ ብሎ ስልክ ረጅም ሰዓት ያወራል።

መሀላችን ያለው ችግር ቀላል ነው ብዬ አስመሰልኩ... እውነቱ ግን እሱ አይወደኝም።

በመጨረሻ አልፈለግነት ሲጫወትብኝ፣ የድሮ ቦይፍሬንዴ ጋ ሄጄ ተልከሰከስኩ!

እሰይ!! እንኳን ተልከሰከስኩ።

ለሴት ልጅ የአለመፈለግነት ስሜት፣ ለዛውም በእንክብካቤ ላደገች፤ ለዛውም ተለማምጦ፣ ልዕልቴ ናት ብሎ ላገባት፣ ለዛውም መፈለግ እና መውደድ ለምታውቅ ሴት የሚሰማትን የሕመም ስሜት የት ያውቀዋል?!

የምን ጉዝጓዝ፣ ሰበብ፣ ድሪቶ፣ ዝባዝንኬ ነው?!

አለመፈለግ ብቻውን ቀላል ነው?!

ብቻውን ትዳርን መፍታት ብቻ አማራጭ አድርጎ ማሰብ ቀላል ነው?

ብቻውን ወሲብ ማድረግ መፈለግ እና ባል እያለ በፍትወት መቸንከር ቀላል ነው?

ብቻውን ላወራው እየፈለግኩ፣ ስደውልለት ሳያነሳልኝ ሲቀር አያከብረኝም፣ ከምንም አይቆጥረኝም ዓይነት ስሜትስ ቀላል ነው?!

ብቻውን እንዲህ እለዋለሁ ብዬ የሰበሰብኩትን ዓረፍተ ነገር፣ እንዲያዝንልኝ ያጠናሁትን ንግግር፣ እንዲታረቀኝ ያጠራቀምኩትን ቃላት፣ እንዲሳሳልኝ ያከማቸሁትን ሰበብ፣ እንዲረዳኝ የተዘጋጀሁበትን ቃል ፊት ነስቶ ሲያጠፋብኝ ስሜቱ ልብ አይሰብርም??!

ከድሮ ቦይፍሬንዴ ጋር ተንገብግበን፣ ተጠማጥመን ተዋሰብን። ቆንጆ ነኝ ወይ ስለው "ከድሮ በበለጠ” እያለኝ፤ ምኔን ትወድልኛለህ ስለው እያንዳንዱ አካሌን . እየሳመ እያሳየኝ። እየተዟዟርን፣ ቦታ እያማረጥን ተዋሰብን።

ደስስስ አለኝ!!

ለመለምኩ! እየጠወለግኩኝ ነበር።

ያደረግኩት ተግባር ለሌላው፣ ለመንገደኛው፣ ለመርሕ ሰው ሁሉ፣ ለጨዋው ሁሉ፣ ለአማኙ ሁሉ፣ ከዳር ሆኖ ላየኝ ሁሉ፣ ለፈራጅ ሁሉ፣ ለሌባው ሳይቀር ዝሙት ነው!.

ወሲብ ውስጥ ያለውን እፈልግሻለሁ፣ ታምሪያለሽ፣ እወድሻለሁ ሽንገላን መስማት ናፍቆኝ ነበር።

አመሰግንሃለሁ ብዬ አንገቱ ውስጥ ተወሽቄ ሳምኩት። ስለተኛኸኝ አመሰግናለሁ ይባላል? ትዳሬ ላይ ከባለግኩኝ በኋላ ማመስገን ነበረብኝ?

እኔ ግን አመሰገንኩት!

ተሰናብቼው ሳይመሽብኝ ወደ ቤቴ ፈጠን ፈጠን እያልኩ መሄድ ጀመርኩ፤ ቀስ እያልኩ ፍጥነቴን ቀነስኩ፤ እዛ ዱካክ፣ አልፈለግነት የሚበላኝ ቤት መሄድ ፈራሁ። የማይፈልገኝን ባሌን ማየት ሲዖልን የማየት ዓይነት ሆነብኝ፣ የማይናፍቀኝን፣ የማይንከባከበኝ ባሌ ያለበት ቤት መሄድ ጠላሁ፣ ወስልቼበት እንኳን ጸጸት ያልተሰማኝ ባሌ ጋ መሄድ አስጠላኝ።

ለመጀመርያ ጊዜ ልቤን ሰማሁት።

ከእኔ ካልሆነ ሰው ጋር እንድተኛ ያደረገኝ ሰውዬ ጋ ምን አደርጋለሁ??

መሳም እስክናፍቅ ድረስ የገፋኝን፣ መታቀፍን ብርቅ ያደረገብኝን፣ መወደድ እንደሚገባኝ ያሰረሳኝ ሰው ጋ ምን አደርጋለሁ?!

ምን አጠፋሁ? ይቅርታ ለማለት፣ ምን ላድርግልህ እንድለው ትንሽዬ እንኳን ፊት የማይሰጠኝ ሰው ጋ ለመኖር ለምን ወደኋላ ተመለስኩ።

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
36👍4😢1
አትሮኖስ pinned «#ባል_ተመኘሁ አስተዳደጌ ነው የገደለኝ። አስተዳደጌ መጠበቅ እና ማግኘት ነበረበት። አባቴ ሁሌ ቃል ይገባልኛል፣ የሆነ ነገር በጥሩ መልኩ ሳደርግ ይሸልመኛል፣ እናቴ የቤት ሥራ ስሠራ ታመሰግነኛለች፣ ትመርቀኛለች። በምስጋና እና በስጦታ ተንበሽብሼ ነው ያደግኩት፤ ለዛ ነው የጠበቅኩትን ሳጣ የምታመመው ብዬ ሁላ አውቃለሁ፤ ግን በእሱ ብቻም አይደለም! የማያቸው ሮማንቲክ ፊልሞች እና የማነባቸው መጻሕፍት ናቸው፤…»
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ
በሰላም፣በጤና አደረሳችሁ::

መልካም በአል ለመላው የ ክርስትና እምነት ተከታዮች የቻናሉ  ተከታታዮች በሙሉ ::
7👏1
#ምሶሶ_እና_ማገር

ሸክሜን ሳላስተያየው፣ ፍላጎቴን ቸል እያልኩ ከኔ በቀር ማን አለው ለምለው ቤተሰቤ ስል ፍላጎቴን አቀዝቅዤ መናገር የምፈለገውን ሁሉ ሳልናገር እንደ ጓደኞቼ ፋሽን ልከትል ሳልል ኑሮን ለማሸነፍ ስለምባትል ...

የቤታችን ምሶሶ እኔ ነኝ ባይ ነበረኩ!!

ድንገት እናቴ በአስር ቀን ሕመም ተለየችን። ቤታችን በፍጥነት ቀዘቀዘ።

እናታችን የአባቴን ስኳር፣ ደምብዛት እና ኮሌስትሮሉን ያማከለ ምግብ አቀናብራ አቅራቢ ነበረች። ተኝቶ ሳለ ከውጪ ሆነ ከቤት ውስጥ የሚረብሽ የመሰላት ድምጽ ከተተነፈሰ ቀስስ ቀስ ገረመው ተኝቷል ትላለች ድምጿን ለምልክት በቀረበ ማንሻካሾክ። አባታችንም እንዳይረበሽ ድምጽ ቀንስ ለምትለውም ሰው እንዳይቀየም እየተጨነቀች። አባታችን እናታችን ከሌለች ቤት ውስጥ ያገኘውን ሰው 'አልሚ የት ሄዳ ነው? በቃ አንዴ ከወጣች አትመለስም?' እያለ በስሱ ይነጫነጫል። ምቾቱ ሲሰወርበት ማን ዝም ይላል?

የታናሽ ወንድሜ ሱስ ያመጣበትን ግትልትል ብልግና የምትደበቅለት፣ የምትሸሽግለት፣ ብላ እንጂ ገንዘብ የለህ እንደው አንዱ ቦታ ገባ ብለህ የምትጎርስበት፤ እነዛ ጓደኞች እንደሆኑ ሊያጠጡህ ነው የሚፈልጉህ... ደግሞ ሰውነትህ እየቀነሰ ነው... ወይ እንደ ጎረምሳ ጎረስ ጎረስ አድርገህ አትበላ፣ በየትኛው አንጀትህ መጠጡን እንደምትችለው... እያለች ሳትሰለች ግሳጼ እና ምክር እያቀላቀለች ትኩረቷን የማትነግፈው፣  የምትቆረቆርለት፣ ከብልግናው መሀል መልካምነትን አነፍንፋ የምትመሰክርለት እሷ ብቻ ናት።

“ምዕራፌ እኛን እኛን እያልሽ ራስሽን አየበደልሽ እኮ ነው። ጸጉርሽን ተሰሪ እንጂ ደግሞ አማረልኝ እያልሽ ትጎምጂው እና ትጣይኛለሸ! ሴት ልጅ ጸጉሯ ነው ውበቷ..."

ውጪ ስትንገላታ ነው የምትውለው እያለች ታቀብጠኛለች፣ ትመክረኛለች፣ ገመናዬን ትሰማኛለች፣ ትገስጸኛለች፣ ጠዋት ማታ መግባት እና መውጣቴን፣ ሁኔታዬን፣” ገጼን፣ እንቅስሰቃሴን ትከታተላለች።

አደራህን ጌታዬ ከልጆቼ በፊት አድረገኝ፣ የልጅ ሐዘን አታሳየኝ፤ ከጓደኛ በታች አታውላቸው፣ ከክፉ ነገር ጋርዳቸው፤ ለኔ ያደረከውን ለማን አደረክ? ተመስገን፤ ተመስገን አያለች ስታጉተመትም ለሚሰማት ከአምላኳ ጋር የምታወራ አትመስልም፤ ከወዳጇ ጋር እንጂ!! በርግጥ ለታመነ ካምላክ በላይ ወዳጅ ማን አለ!

ምዕራፌ በርቺልን፣ ካላንቺ ማን አለን? አያለች መኖርያ ምክንያት ትለግሰኛለች። ለመመረቅ ሽራፊ. ምክንያት የምትፈልግ ይመስል ላደረኩት ትንሽ ነገር  ስትመርቀኝ ትውላለች።

ለውሻችን ቦቸራ እንኳን በሰዓቱ ምግብ የምትወረውርለት፤ አሞታል እንዴ? ፈዘዘሳ ብላ የምታስተውለው እናቴ ብቻ ናት።

ዘመዶቻችን እንዲመጡ ወትዋች፣ ጠፋችሁ ብላ ወቃሽ፤ ሲመጡ ተንከባካቢ፤ ካልበላችሁ፣ ካልጨመራችሁ፣ ካልቆያችሁ፣ ካላደራችሁ እያለች የምትለማመጥ፤ ሰፈራችን ውስጥ ለቅሶ ሲኖር፣ ሰርግ ሲሰረግ፣ ዝክር ሲዘከር ግንባር ቀደም አጋዥና አድማቂ እናታችን ናት። ለሚውል መዋል፣ ለደግ ደግ መሆን ስለማይከብድ ቤታችን ጉዳይ ሲኖር የሚያግዘን፣ ስንታመም የሚጠይቀን፣ መንገድ ላይ ሰላምተኛችን ብዙ ነው።

ስናጣት ልካችን ተገለጠልን!! እንዴት ይሄን ሁሉ ስትሸከም በዚህ መጠን  አላስተዋልኳትም? ተሸክሞ ሸክምን አለማሳየት ምን ዓይነት ጥበብ ነው?? እናቴን ያሳረፍኳት መስሎኝ ነበር፤ ለካ አሳርፋኝ ነው።

እናቴ ስንት ቀን ፍቅሯ እውነቷን ሲያስደብቃት፤ በድዬ ለእኔ ስታደላ አይቻታለሁ። ልጅ ሳለሁ በንዴት ከገረፈችኝ በኋላ ሲቃ እየተናነቀኝ ጉያዋ ስወሸቅ፣ ተንሰፍስፋ ያባበለችኝ ዕለት ትውስታ ልቤ ውስጥ አለ።

ድከመቴን የማታጎላብኝ፤ መውደዷ · የማይወላውል፣ እንደምወዳት ማስረጃ የማታስስ፤ ተዝረክርኬ ዝንጥ እንዳልኩ የምታሰማኝ፤ ሕመሜ የሚያማት፤ ስኬቴ ከሁሉ በላይ የሚያስፈነድቃት፣ ነገሬን ሁሉ ጉዳዬ ነው የምትል፤ እንደምወደድ እስትንፋሴ ዓለም ላይ ካረፈ ጀምሮ እያሳየች

የመሰከረችልኝ። እምወደድ እንደሆንኩ ልቤ ላይዐያሰረጸችልኝ፤ መወደድን የሚያክል ምንም በረከት እንደሌለ በምርቃት እና በጸሎቷ ያሰማችኝ።

ጥንካሬዋን ፈተና የማይበግረው፣ በደል ሆነ መከፋት የማይሽረሽረው፤ ትሕትና የተላበሰች፣ በየቀኑ ስለ ልጇ ከአምላኳ ጋ የምታወራ  አመስጋኝ፣ ስጉ : ፍጥረት : ናት። እስክንጠግብ የማይርባት፤ አሟት በድካም የምታሳብብ፤ እየረገመችን የምትጸልይልን፣ አንደበቷ ከእውነቷ ጋ የማይገጣጠም ድብቅ ፍጡር ናት። ፍላጎቷን አሽሻ፣ የምትፈልገውን አጣጥላ ለምንወድው ነገር ፍላጎቷን የሰዋች፣ ለልጆቿ ቸር፣ ለራሷ ስስታም ናት።

የልጇን ፊት እንደ ዳዊት ዘወትር የምታነብ፤  ስትናፍቅ፣ ስናረፍድ በስጋት የምትቃዥ እናት፤ የፍጡር ፍቅር ጥግ ናት።

ዋርካችን ሲገነደስ የከለለልን ገበና ገለጠን!

ሞቷ ከእንባ በላይ ነው። አልቅሼ ላውጣው ብል አይወጣም። አንዳንድ ጊዜ አጠገቤ ያለች ይመስለኛል፤ ባትመልስልኝም የልቤን እንዲህ እያልኩ አወራታለሁ።

ለምን የሚወዱሽ ሲያለቅሱ፣ ደረታቸው ሲደቁ፣ ጸጉራቸውን ሲነጩ ዝም ብዬ ፈዝዤ ተመለከትኳቸው?  አቅፈውኝ፣ አዝነውልኝ፣ እያለቀሱ ሲያባብሉኝ ለምን ደነዘዝኩኝ?
ግድ የለም አብሬሽ ሞቼ ነው የሚሆነው። አብሬሽ ሞቼ ባይሆን ድንኳኑ ውስጥ ወዳጅ አዝማድ ተስብስቦ ሲጨዋወት፣ ሲያጽናና እኔ ለምን ብቻዬን ዲዳ ሆንኩኝ?

አብሬሽ ሞቼ ባይሆን

የሚቀርበኝ ጉድሽ ፈላ እያለ ሲመለከተኝ፤ በርቺ አይዞሽ እያለ ማጽናኛ የቃላት ጋጋታ ሲያንጋጋ እንዴት በዚህ ሁሉ መሀል የእንባ ቋቴ አልተረታም? ከሩቅ፣ ከቅርብ ቀዬ ሐዘኔን በአካል ሊጋሩኝ መጥተው አይኔን እያዩ ሲያጨዋውቱኝ፤ ሊያበረቱኝ ሲታገሉ እንዴት ሆድ አይብሰኝም?

አብሬሽ ሞቼ ባይሆን

ቆሌ፣ ቅስሜ፣ ደመነፍሴ፣ ትውስታዬ፣ መጓጓቴ፣ ሕልሜ አብሮ ከአንቺ ጋ ባይቀበር እንዳሁኑ መች እሆን ነበር?

ከዚህ በኋላ አለመኖርሽ አንዴት አያባባኝም?

አንቺ ሞተሽ እኔ አብሬሽ ሞቼ ባይሆን አንድ ዘለላ እንባ እንዴት አልወጣኝም?

ይሁን ሁሉም... አብሬሽ ሞቼ ባይሆን ለምን ምሳዬ አይርበኝም? እንደሁሌው ውሃ ጥሜ ለምን አይታወቀኝም? ቆይ እሺ ለምን አትናፍቂኝም? አብሬሽ ሞቼ ባይሆን፣ ዋርካዬ ሲገነደስ እንዴት ዝም እላለሁ?

ነገሩ ምሰሶው ሲወድቅ ነው ማገር ማንነቱን የሚያውቀው።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
22😢16👍1
#አዎ_እሱ_ጋ_ያመኛል

ትንሽ ስትቀማምስ እና ሞቅ ሲላት “እኔ ጀብራሪት” ስለምትል የሰፈር ጎረምሶች እና ውሪ ሕፃናት ከመንገድ ሲያገኟት ትንሽ

ራቅ ብለጡ ጀብራሪት! ይሏታል

ካልጠጣች ምንም አትልም፤ ሞቅ ካላት ግን ቀኝ እጇን ወደላይ ሰቅላ መዳፏን ጨብጣ “እኔ ጀብራሪት የኩራባቸው ሚስት... የዛ ወንዳወንዱ... የዛ ምሁር!" ትላለች... አንገቷን ወደላይ እያሰገገች፣ አይኗን ፈጠጥ፣ እግሯን ራመድ እንደማድረግ  እያለች፣ ትከሻዋን ወደ ቀኝ እና ግራ እየወዘወዘች ትፎክራለች።

ጀብራሪት የሚሏት ጎረምሳ እና ውሪ ሕፃናት ይዝናናሉ፣ ይፈግጋሉ፤ ሌላው መንገድ ላይ ያላስፎከራት ጀብራሪት ሲላት ስትፎክር ቤቷ ትደርሳለች።

መጠጥ ካልቀማመሰች ትክዝ፣ ቁጥብ፣ ጭምት ማለት መገለጫዋ ነው። ጠይም ገጿ ቀልብ ሰጥቶ ለሚመለከታት እርጅናዋ እና ሐዘኗ ያላደበዘዘው በወጣትነቷ የነበረውን ቁንጅና ከመናገር አይሰንፍም።

አታቲ አክስቴ ናት፤ በልጅነቴ እናቴ ስትሞትብኝ ልታሳድገኝ አምጥታኝ እንደሆነ ተነግሮኛል። እናቴን ሆነ አባቴን አላስታውሳቸውም፤ የማውቀው አታቲዬን እና ጋሽዬን ነው።

የኔ ስም ዕድል ቢሆንም አታቲዬ ዕድሌ ትለኛለች። አንቺ ባትኖሪልኝ የምትለኝ ስለሚመስለኝ ደስ ይለኛል። ጡረታ ከመውጣቷ በፊት ገንዘብ ሚኒስቴር ነበር የምትሠራው፤ የድሮ አስራ ሁለተኛ ክፍል ምሩቅ ናት።

ኩራባቸው የሚባል ባል ነበራት፤ ስድስተኛ ክፍል እያለሁ ሞተብን። ስለ ገዳዮቹ እርግጡን የነገረን የለም። ወደ ቤት ሲመጣ እኛ ቤት መታጠፊያው አስፋልት ጋ ገድለው ጣሉት። ከየትምህር ቤት እየመጣሁ ሳለሁ  ግርግር፣ ጩኸት ተቀበለኝ ለማጣራት ሰው ወደ ተሰበሰበበት ስጠጋ አታትዬ
የወደቀ የኩራባቸው ሬሳ ላይ እየተንከባለለች ትጮኻለች። ሁኔታዋ እስከዛሬ ድረስ መጥፎ ትውስታዬ ውስጥ ተወሽቋል... ከዛ ጊዜ በኋላ ብዙ ደም ሳይ ያዞረኛል፣ እረበሻለሁ። ብዙ ሰው የከበበው፣ ሁካታ ነገር ስመለከት የኔ የሆነ ሰው ጉዳት ደርሶበት፣ ጎድተውት እየተለቀሰ ይመስለኛል። ብርክ ይይዘኛል። ከሰፈሬ፣ ካደግኩባት ከተማ እንኳን ብርቅ ሁካታ፣ የሰው ጋጋታ ክብ ሰርቶ ብመለከት ከመረበሽ ስሜት መላቀቅ አልተቻለኝም።

ማታ ዱዲ ብሎኝ፣ ሱቅ ልኮኝ፣ እራት ስንበላ አጉርሶኝ፣ አደግሽልኝ እያለ በእድገቴ እየፈገገ አምሽተን፤ ጠዋት ጎህ ሲቀድ ተነስተን ቁርሳችንን ተቋድሰን፤ የትምህርት ቤት ክፍያ ሰጥቶኝ፤ ግማሽ · መንገድ ትከሻዬ ላይ መዳፉን አንተርሶ ጥቂት መንገድ የሸኘኝ የእኔ ጋሼ ደም ለብሶና መሬት ላይ ተዘርግቶ የማየው ሰው ነው የሚለውን ነገር በምን መንገድ የልጅ ጭንቅላቴ እንዳመነ ባላውቅም፤ እንጃ ብቻ አፌን ከፍቼ፣ መሬት ላይ ተደፍቼ በደም የጨቀየውን ውሃ ሰማያዊ ሸሚዙን የሙጥኝ ይዤ ተንሰቀሰቅኩ።

ጋሼ ገዘፍ ያለ መካከለኛ ቁመት የነበረው፣ ጺማም ጸጉሩን የሚያጎፍር  አፍሮ ነው። በሽራፊ ሰከንድ ያየው ሰው እርጋታውን፣ የጺሙን ያህል መታየት የሚቻልበት ነበር። ቤታችን ኮርነር ጋ ያለው መጽሐፍ የተደረደረበት መደርደርያ ጋ ያለው ጠረጴዛ እና ወንበር ላይ ተቀምጦ ብዙ ጊዜ ያነባል፣ አንዳንዴ ይጽፋል፡፡

አታቲዬ ጋሺዬ ምንድን ነው የሚያጠናው? ይማራል እንዴ?

ፈገግ ትልና “ጋሼ እኮ ጸሐፊ ነው" ፊት ለፊት ከድርድር መጽሐፉ ጎን የተከማቸውን ጋዜጦች እየጠቆመች “እነዛ ጋዜጦች ላይ ይጽፋል፤ ያኛው ሦስተኛ ድርድር ላይ ለብቻቸው የተቀመጡት መጽሓፍት እኮ የእሱ መጽሓፍት ናቸው" ትለኛለች።

ያ ሁሉ!

“አራት ናቸው እኮ፤ ሦስት ሦስት ቅጂ ተደርጎ ስለተቀመጠ ነው"

ግን እኮ አንዱ ራሱ ወፍራም አይደል እንዴ?

ስስ የተሰሰተ የሚያበረታታ ፈገግታ በጠይም ፊቷ ላይአርብባ

“በእርግጥ አዎ”

“ግን መጻፍ እና ማንበብ ይገናኛል እንዴ?”

“በደንብ እንጂ! ጎበዝ አንባቢ ያልሆነ ጎበዝ ጸሐፊ አይሆንም፡፡ ምናብ ብቻውን ሩቅ አያራምድም፤ ቁንጽል ያደርጋል ይል ነበር የኔ ኩራባቸው”

ዝም ብዬ ያልሽው አልገባኝም፣ አብራሪልኝ ተማጽኖ በሚመስል ሳያት

"ይኼውልሽ ዕድሌ በምትሠሪው ሥራ ታዋቂ፣ ጎበዝ፣ ዝነኛ ለመሆን ሥራው ከሚያስፈልገው ትጋት በላይ ካልኖረሽ በሥራው ላይ ከተሰማሩት የበለጠ ማማ ላይ አትወጪም፤

በእርግጥ ያኔ የነገረችኝ የዛሬን ያህል እውነትነቱ ልቤ ውስጥ አልሰረጸም ነበር፡፡

ተመሳሳይ የቃል እና የሐሳብ ትርጉም በዘመን እና በሁኔታ ጥንካሬው እና ትርጉሙ ይለያይ የለ? አታቲ እና ጋሼ የሚዋደዱ፣ የሚከባበሩ እንደነበር ነፍስ ሳውቅ የበለጠ ተገልጦልኛል። ጋሼ አታቲዬን እንደ ትልቅ ልጁ ነበርየሚንከባከባት፤ እንደ እናት ስትሆን ቆይታ ከውጪ ፌስታል ይዞ ሲመጣ ፈንጠዝ እንደማለት ዓይነት ከተቀመጠችበት አልያ ከቆመችበት ተስፈንጥራ ፌስታሉን ትቀበለዋለች፤ እንደዛ ስትሆን ታላቅ እህቴ ነው የምትመስለኝ፡፡

ከውጪ ሲገባ ወይ ከውጪ ስትገባ ሁሌ ግንባሯን ይስማታል። አንዳንዴ ለእኔ ያኔ የማይገባኝን የጻፈውን በወፍራም ጎርናና ድምጹ በጣም ረጋ ብሎ ቴፑን ለስላሳ ሙዚቃ ከፍቶበት ያነብላታል፤ እኔ እንደማጠና መጽሐፌ ላይተደፍቼ ጆሮዬን ደቅኜ እሰማለሁ።

አታቲ ስትሰማው ትቆይ እና “ፓ አንተ እኮ ምድር ባትመጣ ታጎድላለህ!” ትለዋለች።

አንዳንዴ ደግሞ ሲያነብላት ታጨበጭባለች ወይም ታቅፈዋለች፤ አንብቦላት ያልተደመመችበትን ቀን አላስታውስም።

እጅግ አልፎ አልፎ ጽሁፉን ካነበበላት በኋላ ይሟገታሉ፤ በእርጋታ ይሰማት... ይሰማት እና ያብራራል፤ ትሰማዋለች። ሙግታቸው የጎበዝ አስተማሪ እና የጎበዝ ተማሪ ወይም ደግሞ "ሆነ የሚዋደዱ የታናሽ እና የታላቅ ዓይነት ነው። ያኔ
የሙግታቸው እና የውይይታቸው ኮንተንት  አይገባኝም ነበር፣ ሁኔታቸው ብቻ እንጂ። ከእነሱ ጋ መኖር ያስለመደኝ ነገር  ቢኖር ረጅም ሰዓት መስማት እና ያልገባኝን ነገር ለመረዳት ስል በትህትና መጠየቅን ነው።

አታቲዬ ጋሼ ከሞተብን በኋላ በቀስታ አረቄ ውስጥ መሸገች።

ትንሽ ቀማምሳ እቤት ትመጣና

“ዕድሌ” ትለኛለች ወይ አታቲዬ

“በጣም ጎበዝ፣ በጣም ተንከባካቢ፣ በጣም ጀግና እና ታታሪ እንዳታገቢ እሺ... ድንገት ካጣሺው ትዝታው እና እጦቱ አያራምድሽም”

እሺ አታቲዬ

“ዕድሌ…”

አቤት አታቲዬ

“ስታገቢ ተራ፣ ከሰው የተለየ . ጉብዝና ያላየው፣ የትም የሚገኝ፣ የትም ያለ፣ ከብዙ ሰው የማይለይ፣ መርሕ እና ግብ ያልታጨቀበት አግቢ እሺ፤ ብታጪው እንኳን ማንነትሽ አይናድም... እሺ ዕድሌ”

እሺ...እሺ...አታትዬ

አንድ ዕለት ፀሐይ አዘቅዝቃ ሳለች ንጋት ለምሽት እጅ ለመስጠት በእርጋታ ስትጣደፍ ቤታችን ደረስኩ ቤታችን በትንሹ ገርበብ እንዳለ ነበር፤ የሚያስገባኝን ያህል በቀስታ ገፍቼ ስገባ አታቲ ሽሮ ከለር ዕድሜ ጠገብ አጀንዳ እያነበበች በለሆሳስ ስታለቅስ ደረስኩባት፤ ቀስ ብላ ፊቷን በሌለሁበት አቅጣጫ አዙራ በሻርፕ እንባዋን እንደዳበሰች እንቅስቃሴዋ ነገሮኛል... እንዳላየሁ ሆኜ የኔ አታቲ ደህና ነሽ ስላት?

“ደህና ነኝ ዕድሌ” አለችኝ ምንም ስሜቷን የሚያውክ ሐዘን ውስጥ እንዳልነበረች ለማስመስል እየሞከረች።

ማበስ የማንችለውን እንባ፣ ምንጩን የማናደርቀውን ሐዘንን እንዳላዩ ከማየት በቀር የምንጋፈጥበት ምን አቅም አለን!? በድምጻችን ውስጥ እኔ አለሁልህ/ሽ ከማለት በቀር ምን እናደርጋለን? በሌላ ቀን ቤት በሌለችበት ዕለት ጠብቄ ስታነበው የነበረውን አጀንዳ በሦስተኛ ረድፍ አካፋይከተደረደረው መጽሐፍ ጀርባ ካለው ሁለተኛ ረድፍ ውስጥ ፈልጌ አገኘሁት፤ በሚያምር የጋሼ እጅ ጽሑፍ የተጻፈ ነበር፡፡

አጀንዳውን እንደዘበት ስከፍተው እንዲህ የሚል አገኘሁ...
22👍7
“ምድር ከሰጠችኝ ገጸ በረከት እሷ ዋነኛዋ ነች። ምድር ላይ መቆየት ካማረኝ የሚያምረኝ በእሷ ምክንያት ነው። የሕይወት ተጋድሎዬን ያህል ነው ትርጉም የምትሰጠኝ፤ በዚህ በዝባዥ ስርዓት፣ በእዚህ አምባገነን ስርዓት፤ ሕዝብ ከቁጥር በቀር ትርጉም በማይሰጠው ይህን በዝባዥ አገዛዝ እታገለው ዘንድ እሷ የምትሰጠኝ ተስፋ እና ፍቅር ግዙፍ ነው።

'Socialism እና Karl Marx' እንደማይነጣጠሉ ሁሉ የኖረኝ ክብር እና ዝና ከእሷ ከሚስቴ ጋር ሊነጣጠል እና ካለ እሷ የሚቻል አልነበረም። አይኔን አይታ የምትታዘዘኝ እና የምታዝንልኝ የእኩለ ሌሊት ብርሃኔ እሷ ናት።

እሷ ጠይም የደስታ መግቢያ በሬ ናት። እሷ ሳትኖረኝ ምንስ ቢኖረኝ ምን ያደርግልኛል? ስንት ቀን እሱን ያየ፤ ከእሱ ጋ የቆመ እንደሎጥ ሚስት የጨው ሐውልት ይሆናል ተብሎ ታውጆ እንኳን ምን ቢመጣ ካላንተ ስሆን ከሚሰማኝ አይበልጥም ብላ አብራኝ ነበረች፤ ስንቴስ መቀመቅ ሲያወርዱኝ ከእሷ በቀር ማን አብሮኝ ቆመ?

እሷ የነፍስ ምግብ ጸዳሌ ናት። ምንም ብሆን፤ ምንም ባጣ የማይደንቀኝ ልበ ደንዳና እንደሆንኩ ያለፍኩበት ጨለማ ይመሰክራል፤ እሷ ብቻ ከእኔ ጋ ትሁንልኝ እንጂ።

እሷ ከቀደመችብኝ ያን ዕለት ነው ኩራባቸው መንፈሱ የሚታወከው፤ እሷ ካለችማ ኩራባቸው ልቡ ላይ ሐሴት እንደተመላለሰ የተሰፈረለትን ዘመን ይጨርሳል ..

እሷ የልቤ ብርሃን ናት። ግፍን እቋቋም ዘንድ የተቸረችኝ ጫንቃዬ ናት፤ በንፅሕና ከእውነት ጋ እንድቆም፤ አቋሜ እንዳይሸረሸር፤  መንገዴን፣ አቋሜን  በፍቅር  ከመንገዴ እንዳልሰናከል በትልቁ አቅም ሆናኛለች።

በጠላት፣ በአሰናካይ፣ በቀለብተኛ ተከብቤ : ሳለሁ እንዳላፈገፍግ የምታበረታኝ የደስታዬ ፍላጽ መዓዙን የዓላማዬ ያህል ነው የምወዳት... ይላል። .

ሌላ ገጽ ገለጥኩ

'I will not quit until I make my dreams come true. tius. ኣ"ደምን እንደምን ድምጽ ለመሆን መጥቼ ዝም እላለሁ?

በዜጎች መሀል ግጭትን የሚቸረችር አገዛዝ፤ የማንነታችንን ግንብ የሚሸረሸር ትርክት  የሚያንሸረሽሩ ቀለብተኞች ባሉበት፤ ግፍ ባራኪ፣ ሞራል አልባ አሸከር፣ ፈሪ፣ መርሕ አልባ አለቅላቂ ልሒቃን በተሰባሰቡበት ምድር ተገኝቼ  እስክሞት ዝም አልልም። ደግሞስ ላለመሞት አልመጣሁ፣ ይግደሉኝ እንጂ መቼም እንደማልደለል እኔም፣ መዓዙም፣ እነሱም ያውቃሉ።

እኔ ኩራባቸው ዓለሙ አገር እንድታብብ ከማለም በቀር፤ መነሻ አልባ ትርክት ከማጋለጥ በቀር አንድም ስውር ሕልም እና ግብ ኖሮኝ እንደማያውቅ የልቤን እውነት የምታውቀው መዓዚ እና ሕያው አምላኬ ምስክር ነው እንጂማ ስንቴ በስልጣን ሊደልሉኝ ታከውኝ የለ! እንጂማ በጉቦ ሊጥሉኝስ አላሴሩም? እኔ ኩራባቸው ሳንቲም ግድ የሚሰጠኝ መስሏቸው… ሃሃሃሃሃ የሚታገሉትን ኩራባቸውን አያውቁትም ::

ሌላ ገጽ ገለጥኩ

“አንቺ ግዙፍ ሕልሜን የምታክይ፤ አይበገሬው ልቤን የበገርሽ፣ ኮስታራ ግንባሬን ገንብረሽ ለፈገግታ የራቀውን ፊቴን የምታፈኪ ሚስቴ ሆይ የሕይወት ዘመን ንዑዴ ነሽ። በትንሽ ቀልድ፣ በትንሽ ጨዋታ የምትደሰችልኝ፤ በወደኩበት
በታመምኩበት በታሰርኩበት ሰው ሁሉ ፈርቶ ከእኔ ሲርቅ፣ ከእኔ ጋ ላለመተያየት ሲደበቀኝ በኩራት ፈቅደሽ መርጠሽ ከእኔ ጋ የሆንሽ የእኔ መዓዚ ሕልሜን ልቤ ውስጥ ካስቀመጠው በረከቴ እኩል ባንቺም ተባርኬያለሁ። ባንቺ ምክንያት የምድር ቆይታዬ ከሕልሜ ያላስበለጥኩት የእኔን ያህል መርሄን ስለምትወጅልኝ መስሎኝ...

ጽሑፎቹ እንኳን ለጉዳዩ ባለቤት ለማንም መንገደኛ ትርጉም ይሰጣሉ፤ አጀንዳውን ከተቀመጠበት አኖርኩት፡፡

ጋሼ ታዋቂ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ፣ መንግሥት እንቅስቃሴውን የሚያጠናው፣ መንግሥትም ሆነ መንግሥት የሚቃወሙ አካላት በዛቻ እና በንዋይ ሊደልሉት እንደሚሞክሩ በርካታ ጸሐፊያን በማስረጃ ከትበው አንብቤያለሁ፡፡ እንዲህ እየወደዳት፣ እንዲህ እየተመካባት፣ እንዲህ እየተንሰፈሰፈላት ሲቀጭባት፣ ሜዳ ላይ ሲሞትባት የገዳዩን ማንነት ከመላምት በቀር ገላጭ ሲጠፋ አረቄ ውስጥ ባትደበቅ ከማዘን ውጪ ማጠንከሪያ አቅም እና ሞራል ከየት በኩል ይወለዳል?

ብዙ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ሰዎች ስለ ኩራባቸው ዓለሙ ቃለ መጠይቅ እንድትሰጥ ይለምኗታል። አንድም ቀን ግን እሽ ብላ አታውቅም። አንድ ዕለት ስለ ሌላ የባጥ የቆጡን እያወራሁ ሳለ ...

እኔ የምልሽ አታቲ ለምንድን ነው ግን ስለ ጋሼ ምስክርነት፣ እውነት እና የሕይወት ዘመን እንቅስቃሴው የማትናገሪው? ካንቺ በቀርስ ስለሱ ሊያወራ የሚችል ማን ይኖራል? አልኳት...

አታቲ አይኗን ቦዘዝ አድርጋ ጠረጴዛው ላይ ከተቀመጠው ትልቅ ጉርድ ፎቶ ላይ በትካዜ ተክላ

“ይሄውልሽ ዕድሌ ኩራባቸው ምስክርነት አያስፈልገውም። የራሱን ሐውልት ገንብቶ ነው ያለፈው፤ ስለ እሱ ከሥራዎቹ በላይ መናገር የሚቻለው አንድም የለም። ሥራዎቹን መመርመር እና ሥራዎቹን መሞገት ይችላሉ፤ ሕልሙን ጽፎ
አቋሙን ተንትኖ ታግሎ የተሰዋ ሕያው ነው፡፡ ከጻፈው ውጭ የምናገረው፣ ማለት ፈልጎ ያላለው አንድም እውነት የለውም። ከእኔ ጋ ያሳለፍነውን በየሜዳው፣ በየስፍራው ለማንም አላወራም፤ ይነፍስበታል፣ ይቀልብኛል፤ ቀስ እያልኩ እየተረኩ እያዋዛው፣ እያስታወስኩ ራሴ ጋ የማስቀምጠው የሕይወት ዶሴዬ ነው..."

አታቲ ትንሽ ስትቀማምስ ጀግና እንዳላገባ የምትመክረኝ ምክሯ አልሠራም። ከቢልልኝ ጋ ተፋቀርን፤ ቢልልኝ እውነት፣ ከስሜትም፣  ከፍቅርም ይበልጣል የሚል የዘመኑ የማይናወጥ ጀግና ነው።

አታቲ ሞቅ ባላት ቁጥር “ጀግና እንዳትወጂ” ብትለኝም ልቤ ግን ጀግና፣ ባለ ራዕይ፣ ትጉህ እያየ ስላደገ ጀግና ከማፍቀር የታደገው የለም።

ቢልልኝ ኩራባቸው ዓለሙ አሳዳጊ አባቴ እንደሆነ ሲያውቅ የተሰማው ሐሴት ልዩ ነበር። የሰው ማንነት፣ እውነት የተወሸቀው እያየ ባደገው የተበጃጀ ፍጡር ነው ስለሚል የደስታው ምክንያት አልጠፋኝም።

ቢልልኝን አንድ አርብ ዕለት አመሻሽ ላይ ከአታቲ ጋር አስተዋወቅኳቸው። በጋራ እየተጫወትን ሳለ ጨዋታችን ሀገር፤ ትግል፤ እውነት፤ ታሪክ ሆነ። አታቲ የቢልልኝ ሐተታ ምቾት የሰጣት አልመሰለኝም። ስትሰማው ቆየች እና ተቆርቆሪነትህ እና አቋምህ ዋጋ እንደሚያስከፍል ታውቃለህ አይደል? አለችው በፍጹም እናትነት በስስት እያየችው።

ቢልልኝ ትንሽ ዝም ካለ በኋላ እኔ እንደምጠራት “አታቲ" አላት ፊቷ ሐዘን እንደተላበሰ በቀጥልልኝ ዓይነት አየችው
"ክብር አይደለምን ለሚያማኑበት ጉዳይ ዋጋ መክፈል?” ኣላት። ትክዝ ብላ እኔንም እሱንም አፈራርቃ ካየችን በኋላ አቅም አልባነት ፊት እያሳየችን መርዶ እንደሰማ ሰው በእንባ ታጅባ “አዬ መረገሜ” አለች፡፡

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
38
#እንባ_አዳሽ_ነፍሶች

አብረውኝ ከሚሰሩት ለየት ይልብኛል፤ ግሬይ፣ አመድማ፣ ሽሮ ከለር ልብሶች ያዘወትራል። አይዘንጥም፣ ጸጉሩን ስለማይንከባከብ የብርድልብስ ብናኝ በተለይ ጠዋት ላይ ከጸጉሩ አይጠፋም። ጺሙን በቶሎ አያነሳውም፣ ከሰው ጋ አይተራረብም፣ ሰው ሲተረብም አይስቅም። ፖለቲካ ይከታተላል፣ አንባቢ ነው፤ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅን ይወደዋል፤ ጆን ሎክን ይተነትናል፤ አረቄ ነፍሱ ነው።

አንዳንድ ጠዋት የተመሳቀለ ፊት ይዞ ይመጣል። ፊቱ አልኮል ያመሳቀለው ይመስለኛል። ስለ ራሱ አያብራራም፣ ሰው እሱ ላይ ሰለሚይዘው አቋም አይጨንቀውም።

የሚረዳው የለም ብዬ ዋስ ጠበቃ ለመሆን እጋጋጣለሁ፣ ግን ነገሮችን ስለሚመረምር ለራሱ አያንስም።

ሲያወራ፣ ሲሰማ፣ ሐሳብ ሲሰጥ ጥድፍ ጥድፍ አይልም። የዋዛ አንቅስቃሴዎቹ ላይ እንኳን እመለከታለሁ። አስተውሎትን

ሰኞ ዕለት ያሳደገው፣ ያስተማረው አንድ ወንድሙ በመኪና አደጋ ሞተበት። የቢሮ ሰዎች ተሰባስበን ቀብር ላይ ተገኘን። ብሩክ ፍልስፍናው፣ መጀናተሉ ቀሰስ ማለቱ ከእሱ በኖ ጠፋ። መሬት እየተንከባለለ ሲያለቅስ ሳየው አንጀቴ ተንሰፈሰፈ። እንባዬ አካላቴን ሳላወናጭፍ፣ ድምጽ ሳላወጣ ወለል እያለ ወረደ። ብሩክ አቅም አልባነት ሲያጥመለምለው፣ ለብዙ ሰው አለኝታ የነበረውም ወንድሙ ተጀቡኖ ወደ ጉድጎድ ሲወረወር ከንቱነት በላኝ።

በነጋታው ጠዋት ከእነ ዱካኬ ከእንቅልፌ ነቃሁ። ተጣጥቤ፣ ቁርሴን በልቼ ከሥራ መልስ ብሩክ ጋ ለመሄድ ጥቁር ሻርፔን ቦርሳዬ ውስጥ ከትቼ ወደ ቢሮዬ ሄድኩ።

አይኔን አላመንኩትም፤ ብሩክ ወንበሩ ላይ ፋይል ከምሮ አንገቱን ደፍቶ ይሠራል። ሳየው ደነገጥኩ፤ በደመ ነፍሴ ብሩኬ ስለው ኮስተር እንዳለ በማያቀርብ አስተያየት እያየኝ "ሰላም ሊዲያ” አለኝ።

ሁላችንንም ፊት ነሳን። በሌሊት ሥራ ይገባል፣ አምሽቶ ይወጣል፣ ምሳ ብቻውን ይበላል። አይኑ አባብጦ እንባ ያሸበረው ፊት አይበታለሁ፤ ማንም እንዳያጽናናው መንገዱን ዘጋጋው። አለቃችን እንኳን በረታህ ብሎ ሲጀምር አዎ ይልና ከአጠገቡ እብስ ይላል፣ ወይ ደግሞ ወሬ ይቀይራል።

ወንድሙ ካለፈ በአስራ አራተኛው ቀን ላይ ብሩኬ ደህና ነህ? ግን ምነው እራቅከኝ? አልኩት።

"ትንሽ ቀን ነው የምፈልገው ደህና እሆናለሁ፤ ሁሉም ደህና ይሆናል" ብሎኝ ጭጭ አለ።

በቅጡ አንዳላጽናናህ እኮ መንገዱን ዘጋኸው፤ : ሰው በሚያስፈልግህ ጊዜ ነው ከሰው የራቅከው አልኩት። አየኝ፣ አጎነበሰ ቀስ ብሎ ቀና ብሎ እያየኝ ከትንሽ ዝምታ በኋላ...

“ይሄውልሽ ሊዱ ማጽናኛችን የጎደፈ ነው፤ አንዳንዱ ቤትሽ የሚመጣው ለወጉ ነው፤ አይኑ ላይ ምንም እንባ ሳይታይ ወንድሜ፣ ወንድሜ እያለ ድንኳን ውስጥ ይገባል። አጠገብሽ ይመጣና ምን አገኘው? ገጪው ተያዘን ወንድሜ፣ ሰላምተኛዬ፣ ጥሩ ሰው፣ መከታዬ ይላል። ሐኪም ቤት አልወሰዳችሁትም? ጥያቄ በጥያቄ። የሚያስቆጭ፣ ሐዘን የሚፈጥር ጥያቄ፣ የሚያጎላ ጥያቄ። እንዳልታዘበው፣ እንዳልቀየመው ሐዘንህን መጥቻለሁ ፊቶች፣ ፊታቸውን ለማሳየት የሚጋጋጡ ሰዎችን ጋቢ ለብሶ መታዘብ ሕመም ነው።

በጣም ከባድ ነው ሊዱ፤ ሁሉም የሚጽናናበት መንገድ ሊሆን ይችላል እኔ ግን አልቻልኩም፤ የአጽናኞቼን መንገድ የዘጋጋሁት ሆን ብዬ ነው። ለማጽናናት ስለጉዳዩ ማተት የግድ አይደለም እኮ፤ አብሮ መሆን በቂ ነው፤ ማቀፍ በቂ ነው። ጊዜ ኃያል ነው፤ የማያዶለዱመው ሕመም የለም።

ወንድሜ ጋሽዬ ለእኔ ብዙ ነበር። እሱ ነው ያሳደገኝ፤ የምምለው እንኳን በእሱ አይደል? ለቁም ነገር እንድደርሰ ያልሆነልኝ አልነበረም፤ ኃላፊነቱ ነበርኩ፤ የበኩር ልጄ ነው የሚለኝን ወንድሜን ነው ያጣሁት።

ጉዳዬ ከእግዜር ጋ ነው።

እሱ ነው የተመሳቀለውን እጦቴን በመልክ በመልኩ በእግዜርኛ የሚያበጃጅልኝ፤ እንጂማ በፍጡር ሊያውም ማብሸቅ በሚመስል ማጽናኛ አልድንም። ለዚህ ነው ከቀብር ጀምሮ ቤተክርስትያን የማድረው። ከአማኝ ጥቅማጥቅማችን አንደኛው ከአቅማችን በላይ የሆነ ሁነት ሲጋረጥብን እግዜርላይ ሙጥኝ ማለት አይደል? ከትናንት ዛሬ በደንብ እየበረታሁ ነው፤ የታመንኩት አምላክ እያጽናናኝ እያጸናኝም ነው።"

የብሩኬ አወራር፣ ሁኔታው፣ ሕመሙ አንጀቴን አላወሰው። አይኔ ላይ ያቀረረው እንባ አለመውረድ አልቻለም። አንድ ነገር ብቻ አልኩት

እግዜር ያበርታህ ወዳጄ።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏1615😢3
#አርፋጅ

አንድ ሰፈር ነው ያደግነው፡፡ አንድ ዩኒቨርስቲ ተማርን። ብሩክ ፈታ ያለ ነው፣ ጨዋታ ያደምቃል፣ ጨዋታም ያውቃል። እሱ ካለ የሳቅ ድምጽ አይጠፋም። ስድስተኛ ክፍል አልፈልግህም ተብሎ የተላከለትን ደብዳቤ አባቱ አግቶበት
የመታውን ጠረባ፣ ለፍቺም ደርሰህልኛላ እያለ የሚጦልበውን ጡለባዎችን እየቀመመ ሲያጫውት አፉን ከፍቶ የማይስቅ አልነበረም።

ታላቅ ወንድሙ ላይ የሚሠራውን ተንኮል፣ የግድያ ሙከራ የሚመስሉ ድብደባዎችን ኮስተር ብሎ በፌዛም ፊቱ እያወጋ ያዝናናን ነበር። ግሬድ ሲሰቅልም፣ ሲሾቅም ማላገጡ የሚጠበቅ ነው። በዙሪያው የማንጠፋው ፍሬንዶቹ ላይ እንዳይደብረን አድርጎ ለጨዋታ ፐርፐዝ ብቻ ይቀልድብናል።

ብሩክ እንደ ጃካራንዳ ዛፍ በዙሪያው ሚያጅበው አይጠፋም፣ ሰው ይወደዋል። ከሰው ጋ እይጋጭም፣ መከባበር የማይደራደርበት ዋነኛ ፖሊሲው እንደሆነ በደንብ የሚቀርበው ሁሉ ያውቃል፣ የጠበቀ ወዳጅነት ያለን ደግሞ በይበልጥ እናውቃለን።

ብሩክ ለእኔ ወንድሜ ነው የማልለው ባልጀራነትን ማሳነስ ስለሚመስለኝ ነው። ብዙ ሳቅ እና ጭንቀቶችን ተጋርተናል። በድዬ ሳለሁ ለእኔ አግዞልኛል፣ እስከ ድክመቱ ተቀብየዋለሁ፤ ጓደኛዬ ነው፣ ምንም ሳይኖረን ጊዜ ብቻ እያለን ነው ነፍሳችን የተናበበው፤ የጓደኝነት ትርጉም መተንተን ሳንጀምር ነው የተወዳጀነው።

እኔ ታላቅ ወንድሜ የጀመረውን ቢዚነስ ተቀላቅዬ በሂደት ብዙ ሳንቲም ማግበስበስ ጀመርኩ። ብዙ ሀብት ባገኘሁ ቁጥር መፍጨርጨሬ ጠነከረ፣ ነገሮችን በውሎዬ ስለምመዝን እነጫነጫለሁ፣ ብሩክ ነገሮችን ከእሱ አንጻር ስለሚያይ መነጫነጬ አይገባውም።

ብሩክ ቀልደኝነቱ መፍዘዝ ጀመረና መገለጫው ያልሆነ ጨለምተኝነት ወረሰው። ምሬቱን ቀልቤን ሰብስቤ አሰላስዬ አላውቅም፣ መንገዱን ለመደልደል አልጣርኩም። ከእጮኛው ጋ የሚያጋጥመውን ግጭት በምሬት ሲነግረኝ ቀልቤን ሰብስቤ ከጊዜያዊ ስሜት የገዘፈ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም።

የድሃ ልጅ መሆኑ፣ አይዞህ የሚለው አለመኖሩን ሲጠቅስ አብሬው ከማሸብሸብ የዘለለ ጊዜ ሰጥቸው ምን ላግዘው? ከእኔ ምን ይጠበቃል? ብዬ ለአፍታ አሰላስዬ አላውቅም።

እድገት ላይ በመመሰጤ ያሉኝን በረከቶች ለማስተዋል አልተቻለኝም ነበር። ያሉንን እየጣልን የምናመጣው አዲስ ስኬት እንደምን የምንፈልገውን ደስታ ሊያመጣልን ይቻለው ይሆን??

ለሥራ ኔትወርክ የማይሰራበት ቦታ ከርሜ ስመጣ እንድንጠጣ፣ እንድንስቅ ደወልኩለት ግን ስልኩ ዝግ ነው። ደጋግሜ ደወልኩ፤ አሁንም ስልኩ ዝግ ነው። ስልክ ማጥፋት፣ ስልክ አለማንሳት፣ ለብቻው መሆን አዲስ ያመጣው ፋሽኑ መሆን ጀምሯል። ቤቱ ልሄድ ተነሳሁ።

ፀሐዩ ሀሩር ነው፤ ዘንድሮ ፀሐዩን ለማምለጥ እንደዝናብ መጠለል እና መሮጥ መጀመራችን አይቀርም። የድሮ ሰፈሬ ደረስኩ፣ የነ ብሩኬ ደጅ ላይ ድንኳን ተደኩኗል፤ ብሩኬ አያቱ ጠንካራ ሕመም እያንገላታቸው እንደሆነ ነገሮኝ ነበር።

አያቱ በሕይወቱ ደማቅ ስፍራ አላቸው፤ ይወዳቸዋል፡፡ እንደ ወንድሙ ነበር የሚያዋራቸው፣ እንደ ጓደኛቸው ነበር የሚያጫውቱት። ከልጅነት ጀምሮ የምናቀውን ሰው ማጣት ሕመሙ ብርቱ ነው። ድብርት እና ምሬት ሳይጣባው አያቱ ሳይተኙ ለመድረስ ነበር የሚሮጠው።

እርምጃዬን ቀስ እያደረኩ ወደ ድንኳኑ ስሄድ የሰፈራችን ለቀስተኞች አይን እኔ ላይ አረፈ፣ አጎነበስኩ። ቀስ ብዬ የድንኳኑ መግቢያ በር ላይ ያገኘሁት ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ፣ በቀስታ ቀና ብዬ ብሩኬን በአይኔ ሳስሰው ወንበርተደርድሮ በተቀመጠ ፍራሽ ላይ የደከሙ አያቱን አየኋቸው፤ ፍጥጥ ብዬ እንዳየኋቸው አስታውሳለሁ።

ከአጠገባቸው እናቱን አየኋት፣ በጥሩ መንፈስ አላየችኝም፤ አይኔ ወደ ተሰቀለው ፎቶ ተምዘገዘገ። ከዛ ሰዓት በኋላ የሆነውን ብዙ አላስታውስም። ለቀበሌ መታወቂያ ብሎ አብረን ሄደን የተነሳነው የብሩኬ ፎቶ ተሰቅሏል። በጣም እንደጮህኩ አስታውሳለሁ፤ እናቱን ሂሩቴን እየወደቅኩ፣ እየተነሳሁ የሆነውን ለመጠየቅ ፍራሹ ጋ ለመሄድ መሞከሬንም አልረሳሁትም። የሆነውን ሁሉ ፡ አለማወቄ ተገለጸላቸው፡፡ ረጭ ያለው ለቅሶ ቤት ታወከ፤ ሁኔታዬ ያሳዘናቸው ሰዎች አብረውኝ ያለቀሱ ይመስለኛል።

አያቱን አንቄ ጋሽ በላይ ጓደኛዎት የት ሄደ፣ ብሩኬ የት ሄደ? አልኳቸው። በዛለ እጃቸው አቅፈውኝ በትኩስ እንባ ታጅበው እጁን በእጁ በላ አሉኝ። እግሬ አልጸና ያለ ይመስለኛል፤ ብዙ ሰዎች ያዙኝ፤ ክንዴን ክንዴን ብዬ ጮህኩኝ፤ ሰው ለካ እንዲህ ደካማ ነው፤ የቻልኩት መጮህ እና የሆነውን መካድ ነበር።

በቀን ብዛት ተበረታታሁ ያወራነውን ሳሰላስለው ኋላ መቅረት ሲንጠው እንደነበር ገባኝ። ጨለምተኝነቱ ለመኖር ያለውን ፍላጎት ቀድሞ እንደገደለበት ገባኝ። ለካስ ማስተዋል አቅቶኝ ነው እንጂ ሁሉም ነገሩ ይገባ ነበር። አብረን ብንሆንም ለካ ተለያይተን ነበር፤ ለካ እሱ ነበር ጓደኛዬ እንጂ እኔ ጓደኛው አልነበርኩም። አናቱ ላይ በፍጥነት የወረረውን ሽበት ከ"stress"፤ ከመብሰልሰል የተፈጠረ መሆኑን አልጠረጠርኩም ነበር።

ተሳክቶለታል የምባለው እኔ ነገሮች ሲጠሙብኝ፣ አንዳንድ ነገሮች ሲከፉብኝ ይቺ ዓለም እንደምትሰለቸኝ አውርቼው አላውቅም።

ራሴን ልገድለው እንደነበር ነግሬው አላውቅም። ሽራፊ ፈገግታ በሀሩር ፀሐይ ጤዛ እንደመፈለግ ሆኖብኝ ሳለ፣ የሞከርኩት ሙከራዎች ሲከሽፉ፣ ከሰው ሁሉ አነስኩኝ ስሜቴ ሲበላኝ፣ ብቻ መሆን ሲጨፍርብኝ፣ አለመፈለግ ስሜት ሲወዘውዘኝ፣ ያለኝን ነገር ሁሉ ያፈሰስኩበት ተስፋዬ ሲጠፋ፣ ሕልሜ ሰፍቶኝ ስንከላወስ፣ የምሸሸግበት ጥግ ሳጣ፣ በማምነው ሰው ስካድ፣ ዕድለቢስነት እንዳልጠራጠር አድርጎ ሲመሰክርብኝ ራሴን ልገለው ዳድቶኝ ነበር። መዳዳቴን እንዴት ድል እነደነሳሁት ሳልነግረው!

አምላኬ ጋር ሙጥኝ እያልኩ፤

አንዳንዴ በረከቶቼን ፈልፍዬ ለራሴ እየተረኩ፣

አንዳንደ ጭላንጭል ብርሃኔ ላይ ተመስጬ፣

ብሞት የምሰብራቸውን ሰዎች አዝኜላቸው።

አንዳንዴ ክችች ያልኩበትን ጉዳይ እያላላሁ፣ አንዳንዴ ግትርነቱን እየገሰጽኩ፣ አንዳንዴ ሆስፒታል ያሉ አካላቸው የማይታዘዝላቸው ነፍሶችን እየረዳሁ፣ አንዳንዴ እስረኞችን እየጠየቅኩ ነው ራሴ ላይ የራራሁት ሳልለው
ይሄ ትግሌ ለብሩኬ ትርጉም ሊሰጠው እንደሚችል ማሰብ አልተቻለኝም ነበር። የምንወዳቸውን ሰዎች ምን ያህል እንደምንወዳቸው ካለ እጦት እንዴት መረዳት ያቅተናል? ለራስ ሰው አለመድረስን ያህል አርፋጅነት የለም።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
32👍11😢9
ስላንቺ ሳወራ ዋልኩኝ
       አልወዳትም እያልኩኝ፡፡
              ሰልችቶኛል
        መናፈቅ በቅቶኛል፡፡
        እያልኩኝ... ለፈፍኩኝ
ፈሪ ሰው መሆኔ ያዝተኛል ስንቱን?

የወንድ ልጅ ዛቻ ፍጥረቱ ደመና
            የሰነፍ ሽመና

       በቅቶኛል እያልኩኝ
         በቅኔ ነገርኩኝ
        በዜማ ነገርኩኝ።
        ነገርኩኝ በተረት
       የሚሰማኝ የለም።
አደመብኝና ካንቺ ጋራ ፍጥረት፡፡

          ጭራሽ መቀለጃ
          "በቃኝ" መጫወቻ
           ምጸት ነው አቻዬ
  ከመለየት በላይ ያስቃል ዛቻዬ፡፡

                 አንቺዬ...

         "በቃኝ" መጫወቻ
          ምጸት ነው አቻዬ
   ከመለየት በላይ ያስቃል ዛቻዬ፡፡

                  አንቺዬ...
                   በገላ
                  በመላ

ይሄ ንክር ልቤን ስንቱን ያስተማርሽው
ዝም ብሎ መሄድን ምነው ያልነገርሽው?        እሸፍናለሁ ስል ተጋልጥኩኝ ጭራሽ
           አስሬ ስጠራሽ
  መዘበቻ ሆነኩኝ በፉከራ መዘዝ
በገዛ ቃሌ እንኳ አልቻልኩኝም ማዘዝ?

               ታዲያ... ታዲያ
       ይሄን ሁሉ ነገር በሩቁ እያየሽ
               ተለየን ትያለሽ?

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍109
ይ ረ ሳ ል አ ይ ደ ል ?

አ ን ዱ ፣ ዳ ር ፣ እ ን ደ ጣ ሉ ት ፣ ማ ስ ቲ ካ ፥
የ ሆ ነ ፣ ረ ፋ ድ ፣  እ ን ደ ረ ገ ፈ ፣ ዘ ለ ላ ፣ጸ ጉ ር
በ ል ጅ ነ ት ፣  እ ን ደ ወ ለ ቀ ፣  ወ ተ ት  ፣ ጥ ር ስ

ወ ይ፣ ት ና ን ት ፣  በ ቅ ሎ፣  ዛ ሬ  ፣ እ ን ደ ሟ ሸ ሸ  ፣ ቡ ግ ር . . .

. . . ል ብ  ያ ና ወ ጠ ፥ እ ዉ ር  ያ ረ ገ 
መ ዉ ደ ድ ፣  ሁ ሉ  ፣ በ እ ድ ሜ ፣ በ ጊ ዜ
  ይ ረ ግ ፋ ል ።

እ ን ዳ ል ነ በ ር ፥ እ ን ደ ም ን ም ፣  ይ ዘ ነ ጋ ል ።

🔘ሳሙኤል ደረጄ🔘
👍12😢43
#እግዜር_አደራውን_ሲበላ

ግርግር ከማይወዱ ጓደኞቼ ዛብሎን አንደኛው "ነው። እይታዎቹ በወፍ በረር የተኮረጁ አይደሉም፤ ስለማያውቀው ነገር ከተወራ ይሰማል ረጋ ብሎ ስለሚያወራ፣ ስለሚያውቀው ነገር ብቻ ስለሚያወራ እያዳመጠ ስለሚያወራ፣ መናገር .. ሲጀምር የማይሰማው የለም።

ጨዋታው ብዙ ሰው ላይ ያለው እመነኝ፣ ቅዱስ ነኝ ዓይነት ስብከት የለበትም።

ክላስ አለው!!

አጠገቡ ያለ ሰው ስለማያውቀው ነገር ሲቀባጥር፣ ዛብሎን ደግሞ ስለጉዳዩ በደንብ እውቀት ካለው ለስለስ አድርጎ ቀባጣሪው የቀባጣሪነት ስሜትን ሳያሳድርበት ደርበብ ባለ መልኩ ሐሳቡ ላይ ብቻ አተኩሮ ሙግት ውስጥ ሳይገባ ስለሚያውቀው ነገር ይናገራል። እንደዚህ ዓይነት ግለሰብ ሰውዬው የበታችነት ሳይሰማው፣ አላዋቂነት ሳይታገለው የያዘውን መረጃ አልያም አቋም እንዲመረምር ያስችላል።

ዛብሎን ጺሜ አደገ፣ ጸጉሬ ተንጨባረረ ብሎ ጸጉር ቤት እንደማይሄድ የጸጉሩ መንጨባረር እና የጺሙ መንዥርገግ ምስክር ናቸው። ዘናጭ አይደለም ግን ንፁሕ ነው። ከሁሉ የሚገርመኝ ካላሳቀው አይስቅም። በጋራ ተሰብስበን ሁላችንም እየሳቅን በእርጋታ ሳቃችን እስክንጨርስ ጠብቆ በትንሽ ፈገገግታ አልገባኝም ብሎ ስለሳቅንበት ነገር ማብራሪያ ይጠይቃል፤ ተጨብጭቦለታል ብለን ለምናጨበጭብ ሰዎች አጀብ ነው ይሄ፡፡

ካፌ ውስጥ እንደተቀመጥን ዛብሎን አስተናጋጇን በምልክት ጠራትና መጥታ

'ምን ልታዘዝ'

"ተቆራጭ አምጭልኝ" አስናጋጇ ስትሄድ ጠብቄ

የገና ጾም አትጾምም እንዴ?

“አልጾምም!“

ለምን?

“እናቴ ስትሞት ነው ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር ያለኝ ቁርኝት የተፋታሁ፤ ተስፋ ቆረጥኩ፣ የምለፋበት ምክንያት አጣሁኝ። ድሮ ቤተክርስትያን ስሄድ ነጭ ሐበሻ ቀሚስ የለበሱ፣ ሹርባ የተሠሩ እናቶች ሳይ፣ ሥራ ስይዝ ለእናቴ እንዲህ እገዛለሁ እለው ነበር እግዚአብሔርን። ቆርበው ከቤተክርስትያን በር ላይ መኪና የሚጠብቃቸው እናቶችን ሳይ እኔ ለእናቴ እንዲህ እንደምንሆን ለእግዚአብሔር ፈገግ እያልኩ አጫውተው ነበር። ስማር እንቅልፌ እየመጣ እግሬን ውሃ ውስጥ ዘፍዝፌ የማጠናው ከእግዜር ጋር የተጨዋወትነውን ምኞቴን ለማሳካት ነበር። እሱ እኮ እሹ ታገኛላችሁ፣ አንኳኩ ይከፈትላችኋል ነው የሚለው እያልኩ።

ሱሰኛ ያልነበርኩት እናቴ ልጄ እኮ እንደዚህ ዓይነት ነገር አይወድም፤ የእኔ ልጅ እኮ ብላ እንድትጎርር ነበር። ሕልሜን ከእናቴ ጋ ብቻ ማቆራኘት አልነበረብኝም። ግን እኮ ወድጄ አይደለም፤ ቤተሰቦቿ አረገዝሽ ብለው ሲያባርሯት፣ አባትየው ሲክዳት፣ ምድረ በዳ ላይ ተነጥሎ እንደቀረ ሰው እኔን አገሯ፣ ዓለሟ አድርጋ የተዋደቀችልኝ ናት"

ፊቱ ቅዝቅዝ አለ... ትኩስ እንባ አይኑ ላይ ቅርርር ሲል አየሁ። ከዚህ በፊት አስተውየዋለሁ፤ ስለ አምላክ ሲወራ አስተያየት አይጎጥም። በቤተክርስቲያን ስናልፍ በእጃችን እያማተብን ከጉልበታችን ሸብረክ ስንል እሱ ግን ልክ መንገድ ላይ የምናውቀውን ሰው አግኝተን ሰላም ስንል ስለማያውቀው ብቻ እልፍ ብሎ እንደሚሄደው ልክ እንደሱ አልፎ ይሄዳል።

ውለታ የዋለለትን ሰው የእግዜር ስምን እያጠቀሰ ሲመርቀው አሜን አይልም። ተመጽዋች ምጽዋት ሲጠይቀን ከሌለን እኛ እግዜር ይስጥልን እንላለን ወደ እሱ ዞሮ ሲለምነው የለኝም ይላል።

እግዚአብሄሩን አኩርፎት እንደሆነ ካስተዋልኩ ቆየሁ። በዙሪያው የሚያፈቅረው የለም፤ አለማፍቀሩ ከፍቅር ሾልከው የሚመጡ ስጋት፣ ተስፋ እና ስስት የሚባሉትን ከውስጡ አሽሽቶለታል። አንድ ቀንም ለእግዜር ስሞታም፣ ውዳሴም ሲያቀርብ አይቼው አላውቅም። ዝም ብዬ ሳየው በለሆሳስ ብቻውን ከእግዚአብሄሩ ጋር የሚዋቀስ ነው የሚመስለኝ።

ሳየው በዝምታ እግዜሩን ለምን አደራኽን በላህ የሚለው ነው የሚመስለኝ!!!

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
19🤔7
አትሮኖስ pinned «#እግዜር_አደራውን_ሲበላ ግርግር ከማይወዱ ጓደኞቼ ዛብሎን አንደኛው "ነው። እይታዎቹ በወፍ በረር የተኮረጁ አይደሉም፤ ስለማያውቀው ነገር ከተወራ ይሰማል ረጋ ብሎ ስለሚያወራ፣ ስለሚያውቀው ነገር ብቻ ስለሚያወራ እያዳመጠ ስለሚያወራ፣ መናገር .. ሲጀምር የማይሰማው የለም። ጨዋታው ብዙ ሰው ላይ ያለው እመነኝ፣ ቅዱስ ነኝ ዓይነት ስብከት የለበትም። ክላስ አለው!! አጠገቡ ያለ ሰው ስለማያውቀው ነገር…»
#ኀሰሳችን_ከሽፎ_እንጂ

ጥዑም ጊዜ ላይ ነበርን። ወይን እየተጎነጨን፣ እየተሳሳምን፣ ድንገት ሳላቅድ፣ ሳልቀምር፣ ሳላስብበት ከአንደበቴ የውስጤ እውነት አመለጠኝ፡፡

ትክ ብዬ ሳያት ፈገግ ብላ “እችን የመሰለች ልጅ ጠበስክኣ?" አለችኝ ወደ ራሷ እያመለከተች፤ በትንሹ ፈገግ አልኩ። ፈገግታዬን እንደ መስማማት ቆጥራ በሚያምር ፈገግታዋ እያየችኝ "እናትህማ መርቀውሃል" ስትለኝ ይሄኔ ነበር የልቤ እውነት ያመለጠኝ።

ታውቂያለሽ ግን አንቺ ሕልሜ እንዳልሆንሽ፤ የመጣሽበት መንገድ፣ ዕቅድሽ፣ መርሕሽ ከእኔ ጋ መች ይሄዳል? አልኳት።

ሽማግሌ ከላክሁኝ በኋላ፣ በጋራ ስለምንወልዳቸው ልጆቻች ስናወራ ከርመን እንዴት እንዲህ ይባላል? ሁሉ እውነት እንዴት ይወራል? የልብ እውነት ሁሉ ይዘረዘራል?! ትበሳጫለች ብዬ ነበር ግን ደግሞ የጠበኩትን የፊት መለዋወጥ አላየሁም። ረጋ እንዳለች፣ ፊቷ ሳይለዋወጥ ትክ ብላ አየችኝ፤ ቅፍፍፍ የሚል  ስሜት ዋጠኝ፤ ምን አለ አስማተኛ በሆንኩ እና እንዳልሰማች ማድረግ አልያም እንዳልተናገርኩ መሆን ብችል።

ቃላቱን እርግጥ አድርጋ

“ትክክል!! ጊዜው አሳዝኖን ነው አብረን የሆነው፤ አብረን ሆነን በስሱ ሌላ የፍለጋ ሙከራ ስላልተሳካልን ነው የምንጋባው። አንዲት ቀን 'Messenger ህን ከፍቼ አይቻለሁ፡፡ የምታወራቸውን እንስቶች ቀልብ ለመግዛት የምትሄድባቸውን መንገዶች፣ መሻፈዶች፣ ላጤ ነኝ ጨዋታዎች፣ ብልግናዎች ተመልክቻለሁ፤ ሁሉም ከእኔ ጋ አንድ ዓይነት ነበሩ። የማደርገውን ነበር የምታደርገው፤ ከፍቶኝ ነበር እንዳላኮርፍ፣ እንዳልጨቀጭቅህ፣ እንዳልጣላህ ካንተ አለመሻሌ አሸማቀቀኝ። የብዙ ሰዎች ትዳር እንዲህ እንደሆነ አይቻለሁ፤ ከገቡ በኋላ በልጆቻቸው ይጽናናሉ፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሚስትና እና ባላቸውን እየከሰሱ ኑሮን ይገፉታል።

ለዛ ነው እንከን የለሽ ትዳር የሚያስሱት ቆመው የሚቀሩት! በቆዩ ቁጥር መለኪያቸውን እየቀየሩ ካጣጣሉት፣ ከተጠየፉት የኑሮ ቀንበር ላይ ራሳቸውን ያገኙታል። ለዛ ነው እንደሚታረድ በግ ሁሉን እያወቅኩ ሽማግሌ ስትልክ፣ ቀለበት ስታጠልቅልኝ፣ የልቤን እውነት አፍኜ የምከተልህ።"

ሲዘበራረቅብኝ ይታወቅኛል። ግራ ገባኝ፤ የሕይወት አጋርን በዚህ ደረጃ አለማወቅ ምን ይባላል? እችን ልጅ ነገሮች በዚህ ደረጃ ይገባታል ብዬ አላሰብኩም። ሴት ልጅ ትታልልህልሀለች እንጂ አታታልላትም እኔ እንዲህ እንደሚሰማኝ እንጂ እሷ እንደዚህ እንደሚሰማት አላውቅም ነበር።

ለምን ታድያ አብረን እንሆናለን ሁለታችንም እንዲህ
ከተሰማን?

"እንሂድ"

ምን አልባት ጊዜያችን፤

ምን አልባት ዕድሜያችን አሳዝኖን?

ምን አልባትም በዙሪያችን ያለ ውትወታ?

ምን አልባት ዘራችንን ለመተካት ካለን ፍላጎት?

ምን አልባት መላመዳችን እንዳንለያይ አግቶን ይሆን?

ምን አልባት አንዳችን ለአንዳችን ካለን ውስጣዊ ስሜት ይሆን?

ምን አልባት በዙሪያችን ካሉት ሰዎች የበለጠ ስለምንዋደድ??

ምን አልባት በስሱ ሌላ ለማግኘት ያሰስነው ኀሰሳ ስላልተሳካ??

ሰው የልቡን ሁሉ አለማውጣቱ ይሆን ቁርኝታችንን
ያላሳደፈው? ባለጋራችንን አለማወቅ ጠቀሜታ ይኖረው ይሆን? አንዳንድ ዕውቀት ምቾት አይሰጥም። ዕውቀት ትካዜን ታበዛለች እንዲል መጽሐፉ፤ አንዳንድ ውይይቶች ሽንቁር ያበጃሉ። የጀመርኩትን ወይኔን በአንድ ትንፋሽ ወደ ጉሮሮዬ አንቆረቆርኩት።

እንደዚህ ዓይነት ሎጂክ ተዘባዝቦ ግንኙነት፣ ትዳር መመሥረት ይቻል ይሆን? እንዳለችው ፍርሀት ነው? እጦት ነው? መላመድ ነው? ምንድን ይሆን በትክክል ያጋመደን?

ምን አስቸኮለን? ምን አሸበረን? ይሄን እውነታ ከተዘራዘሩ በኋላ እንዴት ጎጆ ይቀለሳል? ልጅ ሳይመጣ፣ ንብረት ሳናፈራ፣ ኑሮ ሳይንጠን የግንኙነታችንን መዓዘን መገምገም እንዳለብን ነው የገባኝ። አሁን የምጎዳት ነገ ከምሰብራት አይበልጥም፤ ዛሬ የሚሰማኝ ሕመም ነገ ከሚጋረጥብኝ መከራ አይበልጥም።

ማሬዋ ሰው ውድ ፍጡር ነው። ችኮላችን ብልጣብልጥነታችን፣ በራሳችን ማስተዋል መንጠልጠላችን የእኛ የራሳችን የሆኑት ሰዎች ጋ አንድንሸዋወድ ያደርገናል። ጊዜ እንውሰድ፣ ተነጣጥለን ዙሪያችንን፣ መንገዳችንን እንመርምር፤ ብልግናችንን ይቅር እንበለው። የቆምንባቸውን ስፍራዎች እንቃኛቸው፣ ከፈጸምናቸው ጥፋቶች ጋ እንፋጠጥ፣ እናርማቸው፣ እናበጃጃቸው። ብቸኝነት አባብቶን፣ አቻ ግፊት ወትውቶን፣ መላመድ አሳስሮን፣ የቤተሰብ ግፊት ገፈታትሮን ኑሮ አይመሰረትም። የሁሉም ጓዳ እንዲህ ነው ተብሎ አዲስ ጎጆ አይበጅም፤ ሁሉም ሄዷል ተብሎ እንኳን በስሕተት መንገድ በትክክለኛ መንገድ መሄድ ተገቢ አይደለም።

ከመጣንበት መንገድ የምንሄድበት ሩቅ ነው። ራሳችንን ከእርስ በእርሳችን ነጣጥለን እናጢነው። የአሰተውሎት መንገድ ደግሞ አሜን ካልነው ባሻገር ያለውን እውነታ መጋፈጥን ይጨምራል።

ያኔ የውስጣችን እውነት ፍንትው ብሎ ይታየናል፤ ለውሳኔም ይረዳናል። ስሕተታችንን ለማረም ከፍርሀት ጋ መጋፈጥ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

ከዚህ ሁሉ መንገድ በኋላ መመለስ እንዳስፈራት ታስታውቃለች። እኔም የወጠንኩትን፣ የለመድኩትን፣ የወሰንኩትን ዳግም ለመመርመር እና ለመከለስ ሳስብ ደስስ የማይል የሚቀረዝዝ ስሜት ሲወረኝ እየተሰማኝ ነው።

🔘አድኀኖም ምትኩ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
21👍2
Forwarded from 🔥አረፍ አሪፍ folder disk channel🔥
🚨እድሜዎ ስንት ነው ?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from 1137439312:AAGumjHJ7pzA6vrrfVMlKoqTUsCs59GySrg
ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲህያዉንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 10-15 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ይቀላቀሉ