አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
488 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እናትነት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

//////

የእኔ ቅንዝርነት የልጅቷ ድህነት፤እናትነት እና ተስፋ ቢስነት

ስሟ ግን ማን ነበር?

ምን አይነት ችግር ላይ እንዳለሁ ልትገምቱ አትችሉም፡፡  ሀገር አማን ነው ብዬ በእንቅልፍ ዓለም ከተዋጥኩ በኋላ በእኩለ ለሊት ላይ ለመንገድ  መብራት ማቆሚያ እደተተከለ  የእንጨት ምሰሶ ቀጥ ይላል፡፡ ቀጥ ማለቱ ብቻ አይደለም እኮ የሚያበሳጨኝ ቀጥ በማለቱ ውስጥ ጥዝጣዜ ነገር አለው፡፡ የመነዝነዝ ዓይነት እና  ለመግለፅ የሚያስቸግር ግራ አጋቢ ህመም ከእቅልፍ እስከማባበነን ድረስ የሚደርስ ኃይል ያለው ህመም ፡፡እስከአሁን ስለምን እንደማወራችሁ አልገባችሁም አይደል?

እንጠራራ እና ከእንቅልፌ ጋር እየታገልኩ ዓይኔን እያሻሸው በዳበሳ ወደ ሽንት ቤት ሄዳለው… ምን አልባት ሽንቴ ወጥሮኝ እንደሆነ ብዬ…ግን ብጨምቀው ባልበው ጠብ አይለኝም ፡፡

በንጭንጭ ወደ አልጋዬ እመለስና እያተገላበጥኩ እንቅልፍ እስኪያሸንፈኝ  እሰቃያለው፡፡ከሰዓታት በኃላ እንደምንም  እንቅልፍ ያሸንፈኛል፡፡ሊነጋጋ ሲል መለልሶ ይቀሰቅሰኛል፡፡የዚህኛውን ጊዜ እንኳን ፊት አልሰጠውም …ከነ ተረቱ ‹ የጥዋት ቁ› ይባል  የለ …ሽንት እንዲወጠር እድርጎት ይሆን ትክክለኛ አምሮት ይሁን መለየት አይቻልም…ሀሰተኛ መሲ ነገር ነው፡፡

ይሄ ነገር  እየተደጋገመ ሲያስቸግረኝ ህልሜን ሁሉ የከተማዋ ቆነጃጅቶች እና በአካልም በምናብም የማውቃቸው ሴቶች ሲሞሉት የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ  ወሰንኩ…፡፡ በእኔ ምክር ሳይሆን በተፈጥሮ ህግ የሚመራውን ቅንዝሬን  የሆነ ዘዴ ፈጥሬ ማቀዝቀዝ አለብኝ..ስለዚህ ግዢ ልወጣ ወሰንኩ፡፡

ሰፈሩን ባልነግራችሁም …ለግዢ ምቹ ናቸው ሲባሉ ከሰማዋቸው የከተማዋ ጉድ ሰፈሮች  መካከል ወደ አንዱ ነው የሄድኩት…ቺቺኒያ አይተንሀል  አላችሁኝ…..?ምን  አልባት እኔን የመሰለ ሰው አይታችሁ ይሆናል እንጂ እኔ ወደ እዛ ሰፈር ዝር አላልኩም…ደግሞስ እናንተ ራሳችሁ እዛ ሰፈር ምን ስትሰሩ ነበር? ለማንኛውም ያልኳችሁ ቦታ ሄድኩ …ቀድሜ አልጋ ተከራየው….
ከዛ ወደ ቡና ቤቶቹ ወይም ወደ ጭፈራ ቤቶቹ አልነበረም ጎራ ያልኩት፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ ጎዳናው ነው የወጣሁት…፡፡ከቤት ውስጥ ግዢ የውጩን ለምን እንደመረጥኩ አልገባኝም…. ብቻ ስሜቴ ወደ እዛ ነው የገፋኝ ፡፡ዞሬ ለመምረጥ… መርጬ ለማነጋገር እና ለመስማማት..ተስማምቶም ይዞ ለመሄድ ..አንድ ሰዓት ገደማ ፈጀብኝ፡፡

ልጅቷ የተከራየሁት ቤርጎ ገብታ አልጋው ጠርዝ ላይ እንደተቀመጠች  ፊቷን ለማንበብ ሞከርኩ..፡፡ፊቷ ሜካፕ የነከካው ቢሆንም በስርዓቱ አልተዳረሰም… የሆነ መዝረክረክ ይታይበታል፡፡ከቀይ ዳማ መልክ ወደ ግራጫ የተቀየረ የፊት ቀለም ይታየኛል..፡፡የዓይኖቾ ቅንድቦች ቀና ማለት ደክሟቸው መሰለኝ ተደፍተዋል፡፡ጉንጮቾ ወደ ውስጥ ስርጉድ ብለው በረሀ ላይ ውሃ እንዲወጣባቸው የተቆፈሩ ጉድጓዶች ነው የሚመስሉት ...፡፡ከንፈሮቾ ቁርፍድፍድ ብለው የመሰነጣጠቅ ምልክት ይታይባቸዋል፡፡ግን በተቀባችው ቀይ ሊፒስቲክ ልትሸፍነው ሞክራለች፡፡ውጭ ከመብራቱ  ፖል አቅራቢያ ከሚገኝ ግንብ አጥር ጋር ተጣብቃ ግማሽ ብርሀን እና ግማሽ ጨለማ ከቧት ሳነጋግራት ይሄ ሁሉ አሁን የዘረዘርኩላችሁን የመልኳ ሁኔታ አልተገለፀልኝ ነበር.፡፡አቋሟን እና የፊቷን ቅርጽ በከፊል ነበር የገመገምኩት….፡፡ገምግሜም አስፓልቱ ላይ ከተኰለኰሉት መሀከል እሷን የመረጥኳት…መርጬም ያነጋገርኳት …አነጋሬም የተሰመመማነው… ተስማምተን ወደ ተከራየውት ቤርጎ ይዤት የገባሁት፡፡

አሁን ..ከገባችና በመጠኑም ፈንጠር ብላ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣ ሳስተውላት ግን አሁን ከላይ እንደዘረዘርኩላችሁ የተለየች ሆና ነው ያገኘኋት፡፡ ገና ያልበሰለች የ16 ዓመት አካባቢ ጨቅላ ወጣት ነች ፡፡ቢሆንም ውስጧ የ60 ዓመት  …የጎበጠች እና የጨረጨሰች አሮጊት በእሷነቷ ውስጥ ተደብቃ ትታያለች፡፡  ወጣትነቷ  በፍጥነት ወደ መጠውለግ ሲንደረደር  ይታያል፡፡

‹‹ተጫወቺ እንጂ …ምነው ከእኔ ጋር ማደሩ ደስ አላለሽም እንዴ? ››አልኳት፡፡

ፊቷን እንዳጨማደደች አላስፈላጊ ጥያቄ እንደጠየቀ ሰው በግርምት እያየችኝ

‹‹መደሰት እና አለመደሰት እዚህ ጋር ምን  አመጣው›ስትል መለሰችልኝ፡፡

‹‹አልገባኝም››

‹‹እንዴት አይገባህም..እኔ ገንዘብህን ነው የምፈልገው፡፡ ከፍለኸኛል….ከከፈልከኝ ደግሞ ደስ አለኝም  አላለኝም  አብሬህ ማደር ግዴታዬ ነው››አለችኝ እና ልብሶቾን ማወላለቅ ጀመረች፡፡
እኔም አወላለቅኩና ተከተልኳት..ተያይዘን  አንድ አንሶላና ፍራሽ ከስር..አንድ አንሶላና ብርድ ልብስ ከላይ አድርገን ከመሀከል ገባን…፡፡

‹‹እዛ ባዶ ቤት ብቻውን በነበረበት ሰዓት ዘራፍ እያለ  እረፍት  ይነሳኝ  የነበረው አጅሬን‹‹ አሁን እስቲ ጉዱህን እየዋለው….ሜዳውም ፈረሱንም ያው አመቻችቼለታለው… ›› አልኩት.፡፡

ግን ለእኔም ሆነ ለአጅሬው እንደአሰብነውና እደጓጓነው የሆነልን አይመስለኝም ….የሆነ ደስ የማይል ስሜት እየተሰማኝ ነው…እሱም አንዴ ቀጥ ከዛ መልሶ  እንደመልፈስፈስ እያለ ፈራ ተባ  ውስጥ ገብቷል፡፡ወደ እሷ ፊቴን አዞርኩና እጄን ትከሻዋ ላይ ጣል አደረግኩ..ስጠጋት ከሰውነቷ የሚረጨው ጠረን ተምዘግዝጎ ወደ አፍንጫዬ ሲገባ ደስ የማይል ስሜት ነው የተሰማኝ..እርግጥ  ከለበሰችው ልብስ አልፎ ሰውነቷ ላይ የቀረ የሽቶ ሽታ አለ ..፡፡ግን  ከሽቶው ተደባልቆ ና ተዋህዶ የሚበተን ሌላ ጠረን  አለ..ምንነቱን ልለየው ያልቻልኩት ትንሽ የሚረብሽ ጠረን….፡፡

እንደዛም ሆኖ በደንብ ተጠጋኋት ..ሰውነቴን ከሰውነቷ አጣበቅኩ…እዳብሳት እና  አሻሻት ጀመርኩ፡፡..ቀስ በቀስ ሰውነቴ እየጋለ እየሞቀ ቢመጣም ከእሷ ወደ እኔ እየተላለፈ ያለ ምንም አይነት ሙቀት ሊሰማኝ አልቻለም…. አሁንም በረዶ እንደሆነችና ሰውነቷ ከፍሪጅ እደወጣ ስጋ እንደደረ ነው፡፡ማሻሸቴ ቀጥሎ ጡቶቾ ጋር ደረሰ ....ጨመቅ ለቀቅ.. ጨመቅ ለቀቅ ሳደርግ አስደንጋጭ ፈሳሽ ከጡቶቾ  ፊን ብሎ ደረቴ ላይ ተረጨ..ደነገጥኩ ፡፡

በደነገጥኩበት ፍጥነት አሷም ይበልጥ በመበሳጨት ጮኸችብኝ፡፡

‹‹በናትህ ዝም ብለህ ማሻሻቱን ጥለህ ..ማድረግ አትችልም ?››

‹‹ምድነው ከጡትሽ የወጣው?››
‹‹ምን እንዲወጣ ትፈልጋለህ… ነዳጅ…››.በማሾፍ መለሰችልኝ፡፡

‹‹እሱማ ወተት ነው…ግን እንዴት...?እንዲህ ይሆናል እንዴ?››

‹‹እመጫት ስለሆንኩ እና ስለማጠባ ነው››ግዴለሽ እና ስሜት አልባ በሆነ ስሜት መለሰችልኝ፡፡

‹‹ማ….? አንቺ?››

‹‹አዎ …የሁለት ወር አራስ ልጅ ቤት ጥዬ ነው የመጣሁት››
በድንጋጤ ከመኝታዬ ተስፈንጥሬ በመነሳት  ቁጭ አልኩ

‹‹ አቤት ጭካኔ ..የሁለት ወር አራስ ቤት አስተኝቶ  ለሽርሙጥና መሰማራት  ሀጥያት ብቻ ስይሆን ወንጀልም ነው..ምን አይነጠቷ አውሬ ነሽ በእግዚያብሄር…!!!!››አልኳት፡፡

ተንፈቅፍቃ የሹፈት ሳቅ ሳቀችብኝ‹‹ሀጥያት አልክ ..?ማነው እኔን  ወንጀለኛ እና ሀጥያተኛ ነሽ ብሎ ሊፈርድብኝ የሞራል ብቃት ያለው..?ያሳደገኝ ማበረሰብ…? ሚያስተዳድረኝ መንግስት …?ቄሱ..?ፓስተሩ…? አንተ ..
37😢3
?ወይስ እግዚያብሄር…?›› ትንፋሽ ወሰደችና ንግግሯን ቀጠለች….‹‹….ልጄ  ወተት ያስፈልጋታል...እኔም መብላት ባልችልም ቀምሼም ቢሆን ማደር አለብኝ...እናቴም አየር ስባ ብቻ አይደለም የምትኖረው….አንገታችን የምናስገባበትን እና ጎናችንን የምናሳርፍበት ደሳሳ ጎጆም  ከመንግስት በችሮታ የተሰጠን ሳይሆን በ6000 ብር የተከራሁት ነው..ነው ወይስ አራስ ልጄን  እና ደህነት እና በሽታ ተባብረው  ያደቀቋትን እናትኔን  ይዤ ጎዳና በመውጣት መንገድ ጠርዝ ጨርቅ አንጥፌ ልለምን?ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው አሉ….ዳሩ ወንድ አይደለህ.. ማስታቀፍ አንጂ መታቀፍ ምን እንደሆነ ጣጣውን እና መዓቱን የት ታውቃለህ?፡፡››

በንግግሯ ደነዘዝኩ ..ጭንቅላቴን ራስምታት ሲወቅረኝ ይታወቀኛል‹‹ይቅርታ ..ስሜታዊ ሆኜ ነው… አሁን ልጅሽን ማን ነው የሚጠብቀልሽ?››ስል ቀዝቀዝ ብዬ ለስለስ ባለ የድምፅ ቃና ጠየቅኳት፡፡

‹‹እናቴ››

‹‹አይቸገሩም?››

‹‹ታስቸግራለች..ግን ብዙ ጊዜ አዳር አልሰራም… ሁለትም ሆነ ሶስት ሰዎችን አግኝቼ ሾርት ከሳራው በኋላ ያገኘኋትን ብር ይዤ ስድስትም ሳባትም ሰዓት ወደቤቴ እገባ ነበር… ዛሬ ግን እንደዛ ስላልቀናኝ ነገ ደግሞ የግድ የቤት ኪራዬን መክፈል ስላለብኝ እና ለዛ የሚሆን በቂ ብር እጄ ላይ ስለሌለ ነው አዳር ለመስራት የወሰንኩት፡፡››

‹‹ሞባይሌን አወጣሁና ሰዓቴን አየው 5፡25 ይላል..ኪሶቼን በረበርኩና ጥዋት ለታክሲ ይሆነኛል ብዬ ሀምሳ ብር ብቻ አስቀረሁና ሌላውን መዳፎ ላይ አስጨበጥኳት.. ከተስማማንበት ሂሳብ ቢያንስ በእጥፍ ይበልጣል….

‹‹በቃ… ለልጅሽ ሂጂላት››

‹‹ለምን?››

‹‹በቃ ሂጂላት››

‹‹ቢያንስ አንዴ ተጠቀምና  ልሂድ››

‹‹አይ አልችልም ስሜቴ ደፈራርሷል››

ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ አለች..ለሽርፍራፊ ሰከንድ ቢሆንም ውስጧ ያለችው አሮጊት ስትከሳ እና ከውጭ የሚታየው ወጣትነቷ ሲፈካ ታዘብኩ‹‹ በጣም ነው ማመሰግነው..በእውነት ከጭንቀት እና ከስጋት ነው የገላገልከኝ….፡፡በድኔ ብቻ ነበር እዚ ያለው…፡፡ ስጋዬም  ነፍሴም ልጄ ጋ ነበር፡፡››እየመረቀችኝ ልብሶቾን ለበሰች… ሞባይሌን ተቀብላ ቁጥሯን መዘገበች ና መለሰችልኝ‹‹ቁጥሬ  ነው ብትደውልልኝ ደስ ይለኛል›› አለችኝ፡፡

‹‹እሺ እደውልልሻለው.. ለማንኛውም አንቺ በርቺ››

‹‹ወድጄ እበረታለው..››አለችኝና ንግግሯን ቀጠለች‹‹በጣም ይገርማል ››አለችኝ፡፡

‹‹ምኑ?››

‹‹ወንዶች ስትባሉ  እንደየመልካችሁ  ባህሪያችሁም ብዛቱ ..ስንቱ አውሬ እና ማሰብ የተሳነው የአእምሮ ድኩማን አለ መሰለህ… እነሱን አስበህ በአዳም ልጆች ተስፋ ልትቆርጥ ስትል ደግሞ እንደ አንተ አይነት በግ  ያጋጥማሀል፡፡››

‹‹በግ?››አልኰኳት … ደንግጬም ተገርሜም፡፡

‹‹ይቅርታ በግ ስልህ ሞኝ ለማለት ፈልጌ አይደለም… ፡፡የዋህ እና መልካም ሰው  ለማለት ነው ..ለማኛውም ብትደውልልኝ ደስ ይለኛል ፡፡ቆንጆ እና የምታምር ልጄንም አሳይሀለው››

‹‹እሺ አይልሻለሁ..››

‹‹እሺ ቻው››ብላኝ  በራፉን ከፋታ በመውጣት መልሳ ዘጋችልኝና ሄደች፡፡እርምጃዋ ቀስ እያለ እየደበዘዘ..እየደበዘዘ ለጆሮ እየሳሳ በስተመጨረሻ ጭልም ብሎ ሲጠፋ ተሰማኝ…፡፡

ግን ነገ ወይ በማግስቱ እደውልላት ይሆን? በውስጤ የተጫረ ጥርጣሬ የወለደው ጥያቄ ነበር፡፡ልደውልላትማ ይገባል….ስለዚህች ልጅ ታሪክ ጠለቅ ብዬ ባውቅ ደስ ይለኛል.. ?እንደዛ አይነት ጉጉት በውስጤ ተፀንሷል፡፡

ተፈፀመ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3229
#ሞት_አያምም!!!

እኖር ብዬ ብታረድም
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
………………………………
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ።
።።።።
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የገደለኝ
መኖር እንጂ የበደለኝ
ሞት አያምም ካቆሰለኝ
ምት አያምም ከገደለኝ!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍126🔥2
#ቀረሽ_እንደዋዛ

እንደ ድመቶቹ
የትም እንደሚያድሩት
እንደ ስልክ እንጨቶች
እንደ ዛፍ ሀረጎች
እንደ ቤት ክዳኖች
ብርድ አቆራመደኝ
ስጠብቅ ስጠብቅ
˝ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ
የልጅነት አይኔ ሟሟ እንደ በረዶ˝
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር
ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር
ብርድ አቆራመደኝ
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ
ጨለማው ሳቀብኝ
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ
መስኮቶች ጨልመው
ቤቶች ተቆልፈው
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ያያሉ
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ፡፡

🔘ገብረ ክርስቶስ ደስታ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍123
አለም ትዞራለች የተባለው ሳይንስ
         አሁን የለው ዋጋ፣
አለም ዛሬ ቆማ ሰው እየዞራት ነው
         እንጀራ ፍለጋ።

🔘ስፍራዬ ጥላዬ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
🔥124
ስትመጪ
ክንዴ በስተራስጌ ክንፍ አቆጠቆጠ
የደጅ አፌ ዳገት፣ ዐይኔ ፊት ቀለጠ

ስትሄጂ
ጸሐዩ ፈረጠ፣ ቁልቁለቱ አበጠ
የቀዬው አብሪ ትል በጽልመት ተዋጠ።

በዳፍንታም አለም፣ ጠባቂ ሲተጋ
እንኳን ቀን ጨልሞ፣ ሌሊቱ ሲነጋ...

መምጣትና መሄድ ቀን ይቀያይራል፥
ምላስሽ ያጎድፋል፣ ምላስሽ ያጠራል
ትንፋሽሽ ያጠፋል፣ ትንፋሽሽ ያበራል።

  🔘ዮሐንስ ሞላ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍7
#ወህኒ

ካቻምና በመስቀል ድፎ ባርኬአለሁ።
ዘንድሮ በጩቤ አጥንት ወግቻለሁ።

          ለምን እንዳትሉ፤
           በቃ ሆነ በሉ፤
           የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

አምና ደግ ነበርኩ ፣ ክፉ ሰው ዘንድሮ
ትናንትና ምሁር ፣ ዛሬ ግን ደንቆሮ ።

            ለምን እንዳትሉ ፤
            በቃ ሆነ በሉ ፤
            የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

መሆን አምሮኝ ያውቃል፤ ፖለቲከኛ ሰው ፣ ኃያል የጦር መሪ ፤
ተመኝቼም ነበር ለመሆን አዝማሪ ፤
ገጣሚ ለመሆን ስንኝ ቋጥሬአለሁ ፤
ደራሲ ለመሆን ተስዬም አውቃለሁ ፤
ሞዴል አርሶአደርም ለመሆን ፈልጌ ፣
አስጠምጄ ነበር ከ 4 ኪሎ ግርጌ ።
ኢንጂነር ዶክተርም ልሆን ነበር እኮ ፤
እንደዚህ ሆንኩ እንጂ ነገር ሌላ ታኮ ።

            ለምን እንዳትሉ፤
            በቃ ሆነ በሉ ፤
            የሰው ልጅ ጠባዩ የሰው ልጅ አመሉ ።

አንድ ሰው አንድ ነው ከንግዲህ አትበሉ ፤
            የሰው ልጅ ወህኒ ነው ፤
እልፍ አዕላፍ ሰዎች ታስረው የተጣሉ ፣
መውጫ አጥተው ነው እንጂ፣አንድ ሰው ውስጥ አሉ።


🔘ይስማዕከ ወርቁ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12
#እውነት_ወደ_ኋላ

ገንዘብ ካለው ጋራ
ፍቅር አይኖርም ወይ ብለሽ ጠይቀሻል!?
እኔ ያንቺን እንጂ
የሌላን አላልኩም እጅግ ተሳስተሻል
አይኖርም አላልኩም...አይጠፋም ይኖራል
ይኖራል
ይኖራል
ግን?...
ከባለሐብት ጋር
ተፋቅራ 'ምናያት የቷም አይነት እንስት...
           'ምን ' ትሁንም 'ምንም '
የሕይወት ታሪኳን ወደኋላ ሄደን ....ጥቂት ብንገመግም
አንድ ቡና ለሁለት ....
አብራ የጠጣችው አንድ አፍቃሪ አታጣም ።

🔘ኤፍሬም ስዩም🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍72
#ያገሬ_መንታ_ገፅ

ውዷ ባለቤቴ፤
እኔም ወግ ይድረሰኝ፤
ወፍራም ሳግ ይውረሰኝ፤
አባት ልሁናቸው ውለጂልኝ መንታ፣
አንድ ሀገር የሚያድን አንዱ የሚፈታ፣
አንዱ ቤት ሚያፈርስ አንዱ 'ሚሆን ዋልታ፡፡
.
.
እንዲያ ነው እንግዲህ፤
በውላ'ጅ አካልሽ፤
መገፋት ቢተርፍሽ፣
ቢጠልዝሽ ደርሶ አካልሽን ቢያጎነው፣
ከቶ አትገረሚ፤
አንዱ ሲንድሽ ነው "ሌላ"ሽ 'ሚጠግነው፡፡

እናልሽ አለሜ፤
እናልሽ ህመሜ፤
እንዲያ ነው ዘመንሽ እንዲያ ነው ዘመኔ፣
አንቺን ሲነኩሽ ግን ታምሜያለሁ እኔ፡፡


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍91
#የኔ_ዓለም!

እንዳንቺ  ሚጣፍጥ - አንጀት የሚያረካ
ጣፋጭ የለም ለካ!
ጥዑም ናቸው ያሉኝ ማርና ቸኮሌት
ካንቺ ሲነፃፀር መረሩኝ እንደ ሬት።

#ማርያምን !

ከድምፀትሽ ልቆ - 'ሚሰማ ሙዚቃ
ከአንባሰል ከባቲ ከብሉዝ ትዝታ
ወድያም ከብሉዙ ደግሞም ከአፍሪቃ
አንድም የለም በቃ !

#ማርያምን!

ካገኘሽ ጠቁሚኝ
ከሄድሽ ብትነግሪኝ.. .
ካንቺ ጋራ ስሆን ሀዘን ጭንቄን ሽሮ
የደስታ ወሰኔን አለቅጥ አንሮ
የሚገርመኝ የለም ከዓለሟ ተፈጥሮ!

ምንድናት ጨረቃ?
ምንድናትስ ፀሀይ ?
ካንቺ አንፃር ስትታይ.. .

ሀዋሳ ላንጋኖ.. . ቢሾፍቱ ሪዞርት
እውን ካንቺ በልጠው እኔን ሊያስደስቱኝ
ኸረ በማዬ ሞት !

#ማርያምን...
የቱ ኮሜዲ ነው የትኛው ቀልደኛ
እኔን የሚያደርገኝ የወሬው ምርኮኛ?
ደግሞ ካንቺ በላይ
እኔን ለማሳሳቅ ማነው የሚደፍረው ?
ባንቺ ጨዋታ ነው
የተደበቀውን.. . ጥርሴን የምገልጠው።

#ማርያምን !
እንደውም ባጭሩ.. .
አሁን ይሄ ግጥም
የቃላት ጥርቅም
እጅግ መሳጭ ሆኖ አንባቢው ቢያደንቅም
ካንቺ ግን አይበልጥም።

ማርያምን...

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍103
#የተጀመረ_አንጀት
በደል ያሰለለው
ጥቃት የበዛበት
         የተገዘገዘ
የተጀመረ አንጀት
        ባልጎለደፈ ቃል
        ባልገረጀፈ ጣት
        በስሱ ካልነኩት
በፍቅር ካልዳሰሱት
       በስስት ካልያዙት
በእውቀት ካላገሙት
      በበደል ፣ በጥቃት
      ዳግም ከደፈቁት
      ደፍቀው ከጓጎጡት
የተብሰከሰከ ፣ የተጀመረ አንጀት
      እንኳንስ ሊቀጥል
ጥቂት ይበቃዋል ቆርጦ ለመለየት ።

🔘ጌትነት እንየው🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍76
#ፍሰሽ

ፍሰሽ በአካላቴ እንደ ወንዙ ፍሳሽ
ወስዶ እንደሚሄደው ልክ እንደ ደራሽ
ውሰጂኝ ውሰጂኝ አስምጪኝ በሞቴ
ይነከር በፍቅርሽ ይራስ ሰውነቴ።

??

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
5👍3
#ይቅር_ታ

በትንሽ ጭንቅላት
በእንጭጭ ልቦና ፥የተጣሉ ለታ፤
ዳግም ለመመለስ
ከሰማይ ከፍ ያለ፥ዳገት ነው ይቅርታ!


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍83
#ላምላክህ_ላምላኬ!

ጀሊሉ ይዳብስህ - ይበርቱ ክንዶችህ
የማርያም ልጅ ደርሶ - ያቁምህ በእግሮችህ!
እግዜር በሽታህን - ይንቀለው ከገላህ
ፈውስ ያውርድልህ - የታመንከው አላህ!
ያደከመህ ይድከም - ይራገፍ በሽታህ
በገጽህ ላይ ይፍሰስ - ይመለስ ፈገግታህ!
ታሞ ተኛ ሲሉኝ - ላፍታ ተንበርክኬ
እንዲህ ነው የጸለይኩ - ላምላክህ ላምላኬ!!

🔘ዘውድአለም ታደሰ 🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
15👍1
#የፍርሃት_ሽንቁር

በስግብግብ ህይወት
            የባርያ ዓለም ግዞት፤
ስንቱን አፍሪቃዊ
             ሀሳቡን ገንዞት፤
ገመናው ተገልጦ
            ጠመንጃ አሳርዞት!
ከኖረ ከኖረ ከኖረ በኋላ
ጨቁኖ ከያዘው የባሪያነት ዱላ፤
ሂድ ወደአለምክበት
ተብሎ በገዢው ከተፈታ ኋላ፤
በእንግዳ ነፃነት
መድረሻው ጠፍቶበት
ይኸው ይኳትናል ነፍሱን እየበላ!

ይሄ አፍሪቃዊ

በዘመን ባርነት
በአስተሳሰብ ውጥረት ተፍቆ ቀለሙ፤
በበርሃ ቀርቶ
በባህር ውስጥ ገብቶ ለሚጠፋ ስሙ፤
በህልም ዓለም ትብታብ
ወድቆና ቆሽሾ ተሰባብሮ ቅስሙ፤
ታሪኩ ቆንጥጦት
ፍርሃት ሸምቅቆት
ተገልጦ አይቆምም ሽንቁር ነው ዓለሙ!

🔘አብርሃም ፍቅሬ🔘
                     
5🔥2
#ሳንመጣ_ለመቅረት

አቤት የኛ ነገር
ዳገት ስንሻማ ከቁልቁለት ገባን
ቀኙን ስንፈልገው ከግራ ተጋባን
ማን መቶ ያግባባን?

በቃል አልባ ቅኝት በተስፋ ቃል ኪዳን
ከደገስነው ድግስ መራራ ሬት ቀዳን
ድግሱም አልቀና
አልጠገብን አልጠጣን ከቀዳነው እሬት
ይኸው ነጋ ጠባ
ማር ማር እንላለን ሳንወጣ ከምሬት
አቤት የኛ ነገር

ስንፈልግ ተጣጣን
ስንሸሽ ተቀጣን
ከመስከረም ጡቶች መከራ እየጠባን
በተራበ አንጀት ስንት በቀል አባን?
በታወረ አይናችን ስን ጊዜ አነባን?
የሆነውን ሁሉ
ያየነውን ሁሉ በማይችለው ቁጥር
አንድ ነን ሁልጊዜ ለዜሮ ስንጥር
መሰንበት ስንሻ ለመኖር ስንቃትት
በወጉ መሞትም ሆኖ አረፈው የክት
አሟሟቴን ይመር
የሚል ተረታችን ያኔ እናዳልተናቀ
ዘመን ቢቀያየር ዛሬ ተናፈቀ
ከዘመኑ በልጦ ቢንቀለቀል ግርሻት
ነገር ላይገናኝ ደጋግሞ በመሻት
ልክ እንደሁልጊዜው
በለመድነው ሙሾ በምናውቀው ተረት
መጣን ብለን እንሂድ ሳንመጣ ለመቅረት

??

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
12🔥1
#እግዜር_ዝቅ_ብሎ

አልመህ ካቀድከው - ከምኞትህ ሁላ
በአይንህ መትረህ - ልብህ ከሚሞላ
ከምድር በረከት - ስጋን ከሚያረካ
ከሰማይ ረድኤት - ነፍስን ከሚያፈካ
:
:
የትኛውን ልስጥህ - ብሎ ቢጠይቀኝ
ካንድ አንቺ በስተቀር - የቱንም አልመኝ

???

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
12👎1
#አጣጥለህ_አትነሳ

አጣጥለህ አትነሳ
ያንዱን ውድቀት፣ አትደገፍ
ጥረህ ፣ግረህ ፣ሰርተህ እለፍ
አሊያ አንደኛ ብትወጣ...
አያጠግብህ የሚበላ፣ አያረካህ የሚጠጣ
አያምርብህ የሚለበስ
በሰው ልፋት፣ አንተ ስትደርስ
ያለ ቦታህ ስትሰየም፣ ያለ ጊዜህ ስትገኝ
ያለእውቀትህ ስትሞገስ፣ ያለ ሞያህ ስትቀኝ
ውጭህ ሙላት፣ ውስጥህ ባዶ
ስኬት አይባልም
የራስን መካብ፣ የሌላውን ንዶ!፡፡

🔘አብርሀም🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍52👏1
#የጠቢብ ቃል!

ባህር ዳር ተኝቼ ሳልሞቅ ጠሀይቷን
አየር ላይ በርሬ ሳልጎበኝ ምድሪቷን

ቁርሴን አዲሳባ ምሳዬን ፓሪስ ላይ
እንዲህ ተዝናንቼ ድሎት ተድላ ሳላይ

በቆንጆዎች ጉያ ስራቸው ሰምጬ
ብኖር ነው ደስታዬ ዓለሜን ቀጭቼ

እያልሁ አስብ ነበር !
አቤት የኔ ነገር ...

ዳምኖ ይሄ ቀኔ ... ሰፍኖበት ፅሞና
ከሎሬቱ ቅኔ.. . አንዷን እመዝና

ምነው እመብርሀን
ኢትዮጵያን ዘነጋሻት?
ቀኝሽን ረሳሻት ... ?
እያልሁ ሳልዘምር ...
ስንኙን ሸምድጄ በቃል ሳልደረድር

በዝናብ ሳልተኛ በሬን ዘጋግቼ
ብልጭልጭ መኪና ሳልሾፍር ገዝቼ

ድንጋይ በድንጋይ ላይ ህንጣ ሳልገነባ
እልፍ ሎሌ ኖሮኝ ታጅቤ ሳልገባ

ይሄ ህይወት ነው ወይ... አሁን የኔ ኑሮ ?
እያልኩ አስብ ነበር ያ...ኔ በፊት ድሮ
ይሄ ታሪኬ ነው ሌላ ነው ዘንድሮ !

ዛሬ ...
ከመጥሀፍ ትንቢት አንዲቷን ቆንጥሬ
ገላልጬ ባየው ...
ይሄ ስንዝር ገላ ድሎት አበጃጅቶት
ወዘና ቢያጠምቀው
ዝናው ባህር አልፎ የአዳም ዘር ቢያውቀው
በስልጣን በውበት ሁሉ ቢያዳንቀው
አሸርጋጅ አጎንባሽ ዙሪያውን ቢያጅበው
ጠቢቡ ሰለሞን አበክሮ እንዳለው
ሁሉም ከንቱ ... ከንቱ ...
የከንቱ ከንቱ ነው !

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍95
የፈጣሪን ክብር
በሴት ልጅ መወድስ
የቀየረ ዘፋኝ …
ሰማይ ቤት ሲደርስ
ተከሶ ወረደ ፣ ወደ ሲዖል እሳት ፤
እርማት !
እርማት !
እግዜ'ር አትሳሳት
ግጥሟን ከደራሲ ፣ ነበር የወሰዳት🙄

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
9