አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
461 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////

ሚካኤልና ፀአዳ አንድ ሬስቷራንት ቁጭ ብለው ተፋጠዋል፡፡ከሁለቱም ፊት ለፊት ተከፍቶ የተቀመጠ ቢራ አለ..አንዳቸውም ግን አንስተው አልተጎነጩለትም፡፡

‹‹ለምን ጊዜችንን ትጨርሳለህ…የሆንከውን ካልነገርከኝ እንደማለቅህ ታውቃለህ››

‹‹ፀዲ..ለምን ችክ ትያለሽ..?ምንም አልሆንኩ የስራ ጉዳይ ነው አልኩሽ እኮ››

‹‹እኮ ግድግዳ በመዶሻ የሚያስነድል ምን አይነት የስራ ጉዳይ ነው?፡፡ሚኪ እኔ እኮ ለአመታት ነው የማውቀው..አንተን የስራ ጉዳይ በዚህ ልክ ሊያበሳጭህ…ኦረዲ አብደሀል እኮ››

‹‹ተይ ፀዲ አታጋኚ››

‹‹አጋነንኩ እንዴ…?የማትነግረኝ ከሆነ …››አለችና እጇን ወደ ሱሪ ኪሷ ሰዳ ስልኳን አወጣች፡፡
‹‹ምን ልታደርጊ ነው?››ግራ በመጋባት ጠየቃት፡

‹‹ብቻዬን አልቻልኩህም..ለአዲስ ደውልላትና ትምጣ..ከዛ ለሁለት እንሞክርሀለን››

‹‹በፈጠረሽ……የእሷን ጭቅጭቅና ለቅሶ የምሸከምበት ትእግስቱ የለኝም››

‹‹እና ንገረኛ››

‹‹እሺ ነግርሻለው››
ስልኩን ጠረጴዛ ላይ ከቢራ ጠርሙሱ ጎን አስቀመጠችና ሙሉ ትኩረቷን ወደእሱ አደረገች፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቁዘማ በኋላ እንደምንም አፉን ከፈተ‹‹የአባቴ ጉዳይ ነው››

‹‹እሱንማ አውቄለው…ከዛ ውጭ አንተን በዚህ ልክ ሊረብሽ የሚችል ሌላ ጉዳይ የለም…በዝርዝር ንገረኝ፡፡

‹‹አባቴ እናቴንም ሆነ እህቴን እንዳልገደላቸው ነገረኝ…እኔም አምኜዋለው››

ፀአዳ ክፉኛ ደነገጠች‹‹እና ማን ነው የገደላቸው..?ማለቴ እንዴት ሞቱ?››ተንተባተበች፡፡

‹‹እሱን አላውቅም…አባቴ ግን ከመሞቴ በፊት እናትህንና እህትህን እኔ እንዳልገደልኳቸው በትክክለኛ ማስረጃ አረጋግጥልኝ፡፡ከመሞቴ በፊት ልጆቼ እኔ ንፅህ ሰው መሆኔን ማወቃቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለው››አለኝ በማለት ሙሉውን ታሪክ በዝርዝር ነገራት፡፡

‹‹እና አሁን ምን ልታደርግ ነው…?እንዴት አድርህ ማረጋገጥ ትችላለህ?››

‹‹ግድግዳውን የናድኩት ለዛ ነበር..አባቴ እዛ ግድግዳ ውስጥ የደበቃቸው የተወሰኑ ማስረጃዎች ነበሩ..አለና ስልኩን ከፍቶ  በሚሞሪ ያሰቀመጣቸውን ቪዲዬዎች አስደመጣት፡፡ሽምቅቅ አለች፡፡

‹‹በጣም ያሳፍራል አይደል?››አላት፡፡

‹‹በእውነት ምን እንደምልህ አላውቅም››ስትል መለሰችለት፡፡

‹‹አየሽ ክህደት ምን እንደሆነ ምን አይነት ህመም እንደሚያስከትል ከእኔ በተሻለ አንቺ ታውቂያሽ..አባቴ እነዚህን ሁሉ መረጃዎች ካወቀ በኋላ ሚስቱ እሱን ሳይሆን ሌላ ሰው እንደምታፈቅር ከተረዳ በኋላ…በጣም የሚወዳት ቀምጥል ልጁ የእሱ ሳትሆን የሌላ ሰው ልጅ እንደሆነች ካወቀ በኃላ  ….የሁለት መንታ ወንድ ልጆቹ እናት እሱን ጥላ ወደልጅነት ፍቅረኛዋ ልትሄድ ዝግጅት ላይ እንዳለች በግልፅ ካወቀ በኋላ  ምንድነው ማድረግ ያለበት?ይሄንን ሁሉ በደል እንዴት መቋቋም ይችላል…?እና  እሱ ቢቀውስና የእብድ ስራ ቢሰራ ይፈረድበታል?››

‹‹በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው…ግን እኮ አላደረኩትም ብለውሀል….›››

‹‹እሱማ  አዎ እወነቱን እንደሆነ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ….ግን እንዳውቀው ካስቀመጠልኝ መረጃ አንድም እሱ እንዳለደረገው የሚገልጽ ፍንጭ ማግኘት አልቻልኩም..እና መተንፈስ እስኪያቅተኝ ድረስ በጣም ግራ ተጋብቻለው፡፡

‹‹ምን እንደገረመኝ ታውቃለህ?››አለች፡፡

ትኩረቱን በሙሉ ወደእሷ ሰበሰበና‹‹ምን? ››ሲል ጠየቃት፡፡
አባትህ በግድያው ተጠርጥረው ፍርድ ቤት በሚመላሰሱበት ጊዜ ይሄንን አሁን ለአንተ የሰጡህን መረጃዎች ለምን ለፍርድ ቤቱ አላቀረቧቸውም….ቢያንስ እኮ የተፈረደባቸው የሞት ቅጣት ወደእድሜ ልክ ይቀየርላቸው ነበር፡፡››

‹‹አዎ..ትክክል ነሽ…መረጃዎቹን እንዳገኘው እኔም ወደ አእምሮዬ የመጣው የመጀመሪያ ጥያቄ እሱ ነበር..እና ትናንትና ወደወህኒ ቤት ሄጄ አግኝቼው ነበር….ለምን ለፍርድ ቤት እንደመረጃ አድርገህ አላቀረብከውም ስለው…ለእናንተ ስል?››ሲል መለሰልኝ፡፡

‹‹አልገባኝም… እንዴት ለእኛ ስትል ?››ብየየ መልሼ ጠየቅኩት፡፡
‹‹እንዳልከው ይሄንን ለፍርድ ቤት እንደወንጀል ማቅለያ አድርጌ ባቀርብ ኖሮ ይሄኔ እናትም አባትም ነበር የምታጡት፡፡በወቅቱ የእኛ ቤተሰብ ጉዳይ በየጋዜጣውና መፅኄቱ እንዴት እንደሚፃፍ ታውቃለህ..ይሄ ነገር ወጥቶ ቢሆን ኖሮ ስለእናትህ ምን እንደሚፃፍ አስበው…የተፃፈ ነገር ደግሞ ታሪክ ሆኖ ይቀመጣል…የልጅ ልጇቼ ጭምር ስለወንድ እና ሴት አያታቸው ታሪክ ሲያነብ ምን አይነት የልብ መሰበር ያጋጥማቸዋል…የእኛን ማህበረሰብ ለነገሮች ያለውን ብያኔ የምታውቀው ነው..በእኔ ጉዳይ ምን ያህል ፈተና እና መገለል እንደሚገጥማችሁ አውቃለው…ይሄ የእሷ ታሪክ ቢጨመርበት ኖሮ መግቢያ መውጫ ነው የሚያሳጦችሁ››በማለት መለሰልኝ፡፡

‹‹አይገርምም !!ወላጅ መሆን እኮ እዳ ነው..አንዳንዴ የነፍስ ክፍያ ለመክፈል እንኳን የማታመነታበት ምስጢራዊ ፀጋ ነው፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ››

‹‹አሁን አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያለን››

በንቃት‹‹ምን ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ሰውዬውን ፈልገን ማነጋገር››

‹‹የትኛውን ሰውዬ?››

ፈራ ተባ እያለች ‹‹የእናትህን ጓደኛ…..››ስትል መለሰችት፡፡

የሚካኤል ደም ስር በንዴት ውጥርጥር አለ‹‹እሱ እኮ ጠላታችን ነው..እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የከተተን እሱ ነው…ፊት ለፊት አግኝቼ እንድገድለው ነው የምትፈልጊው፡፡››

‹‹የሆነ ፍንጭ ለማግኘት የግድ እሱን ማግኘት አለብን…የግድ አንተ ልታናግረው አይገባም…ቆይ እስኪ››  አለችና ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠችውን ስልክ አንስታ ከፈተች ..ምን ልታደርግ ነው ብሎ ሲጠብቅ‹‹ስሙ ማን ነበር››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹የማ?››

‹‹የሰውዬው ነዋ››

‹‹ለሚ በቀለ ››

ስሙን ሰርች ላይ ከታ መፈለግ ጀመረች፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ዳይሬክተር ዳይሬክቶሪት ደ/ር ለሚ  በቀለ የሚል ዜና አየች፡፡

‹‹እንዴ ሰውዬው ባለስልጣን ነው እንዴ?››

ምንም አልመለሰላትም..ዜናውን ከፍታ ለማንበብ ሞከራች…ከአምስት አመት በፊት የተፃፈ ዜና ነው፡እሱን ተወችና ….ሌላ ፈለገች ..ሶስት አራቱን ከከፈተች በኃላ በአራተኛው ትኩረት ሚስብ ዜና አገኘች‹‹የግብርና ሚንስቴሬ ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት የሆኑት ዶ/ር ለሚ  በቀለ በጤና እክል ምክንያት መልቀቂያ በማስገባት ስልጣናቸውን ለቀዋል ››ይላል፡፡ከአራት አመት በፊት የተለቀቀ ዜና ነው፡፡

ወደፌስብክ ገባችና በስሙ ፈለገች.. ዲአክቲቬት ከሆነ አመታት አልፈዋል፡፡

‹‹ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ አይመስለኝም….ቆይ ለእኔ ተውልኝ››

‹‹ምን ልታደርጊ አሰብሽ….?››

‹‹ያለን ምርጫ አንድ ብቻ ነው፣ቢያንስ አሁን አንድ ነገር አውቀናል..ከአራት አመት በፊት ግብርና ሚኒስቴር ይሰራ ነበር…ስለዚህ አዛ ሄድና አሁን ሚገኝበትን አድራሻ ጠይቃቸዋለው…ቢያንስ ስልኩን ይሰጡኛል፡፡››

‹‹እስቲ እናያለን››ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡

‹‹አይዞህ ምንም አትጨነቅ..ይሄንን ነገር እንፈታዋለን….የፈለገ መስዋእትነት ያስከፍል የአባትህን ምኞት እናሳካለን….ይሄ ጉዳይ ዘሚካኤልንም ወደቤተሰቦቹ እንዲመለስ ለማድረግ ያግዘን ይሆናል፡፡››

‹‹እኔ እንጇ..ዘሚካኤል እናቱን እንደፈጣሪው ነው የሚወዳት..ለእሱ እሷ እንከን አልባ መልአክ የሆነች ሴት ነች…ይሄንን ሲሰማ ዳግመኛ ይበልጥ  እንዳይሰበር ነው የምፈራው፡፡

‹‹አይዞህ ….ከመሰበር በኃላ ያለ መጠገን ነው እኛን ሞርዶ ሙሉ ሰው የሚያደርገን፡፡ደግሞ እናትህ ጥፋት ያጠፋችው  በሚስትነቷ ነው እንጂ በእናትነቷ  እስከወዲያኛው ምሉ እንደሆነች ነው፡፡››
👍6610🥰1
#አላገባህም


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////

አዲስ አለም በራሷ መኪና ግን ሹፌር እየነዳላት  ከአዳማ ወደአዲስ አበባ እየተጓዘች ነው፡፡

የተቀመጠችው ከኋላ ወንበር ላይ ሲሆን ከግራዋ የራሷ ልጅ ቅዱስ ሲኖር ከግራዋ ደግሞ የፀአዳ ልጅ ምሰር ትገኛለች፡፡

አዲስአለም ወደአዲስ አበባ የምትሄደው እናቷን ለመጠየቅ ነው፡፡ይሄ ቤተሰቦቾ አዳማ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ  በወር ወይም በሁለት ወር አንዴ የምታርገው ነገር ስለሆነ ማንም ለምን እንዴት ብሎ የሚጠይቃት የለም፡፡ምስርን በምን ሰበብ አስፈቅዳ ከእሷ ጋር ይዛት እንደምትመጣ ግን ግራ ገብቷት ነበር፡፡ማታ ነበር ፀአዳ ጋር የደወለች፡፡

‹‹እሺ ጓደኛዬ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ ምነው ቀን ተገናኝተን ነበር እኮ..በዚህ መሀከል ምን ትሆናለች ብለሽ አሰብሽ?››.

‹‹አንቺ ደግሞ ከአፍሽ ቀና ነገር ቢወጣ ምን አለበት?››

‹‹በይ አሁን ምን ፈልገሽ ነው ወደገደለው ግቢ….››

‹‹በእናትሽ ነገ እነማዬ ጋር አብረን እንሂድ››

‹‹ነገ ››

‹‹አዎ ነገ››

‹‹ያምሻል እንዴ…?ስንት ስራ እንዳለብኝ  ስነግርሽ ውዬ እንዴት የማልችለውን ነገር ትጠይቂኛለሽ?››

‹‹ውይ ለካ ስራ አለብሽ..ብቻዬን መሄድ እኮ ደብሮኝ ነው››

ብቻሽን መሄድ ከደበረሽ  ታዛዥ እና ጣፋጭ የሆነ ምርጥ ባል አለሽ እሱን አስከትለሽ ሂጂ››

‹‹አንቺ እየሰማሽ እኮ ነው››

‹‹ላውድ ላይ አድርሽ ነው እንዴት የምታወሪኝ… አንቺ እኮ ቅሌታም ነሽ….ለነገሩ ሚኪን በተመለከተ መጥፎ ነገር እንደማልናገር እርግጠኛ ስለሆንኩ እንደፈልገሽ››

‹‹መጥፎ ነገር እንደማትናገሪ እኔም ምስክር ነኝ … ውሸት ግን ትናገሪያለሽ..ምን አልባት እንዳልሺው ጣፋጭ ሊሆን ይችላል ታዛዣ ግን አይደለም..ልክ እንደአንቺው ስራ አለኝ አልችልም የሚል መልስ ነው የሰጠኝ››

‹‹በቃ ከልጅሽ ጋር ሒጂ››

‹‹ወይ እንደውም ተውት ከልጆቼ ጋ ሄዳለው…ምስርን ቆንጆ አድርገሽ አሳምሪያትና ወደስራ ስትሄጂ ይዘሻት ውጭ.. በዛው መጥቼ ወስዳታለው››

‹‹ምን እያልሽ ነው?››ፀአዳ እንደመበሳጨት አለች፡፡

‹‹የራስሽው ምክር እኮ ነው፡፡ልጆቹን ይዤ ሄድና ዘና እንላለን…እናንተም ካለልጆቻችሁ ይድላችሁ…እሁድ ማታ ተመልሰን እንመጣለን፡፡››

‹‹አንቺ እኮ የሆነ መዠገር ነገር ነሽ…እኔ ለራሴ ስንት ስራ አለብኝ..?ገና አሁን እሷን ሰውነቷን ሳጥብ..ፀጉሯን ሰሰራ….››

አላስጨረሰቻትም፡፡‹‹በቃ…ጥዋት ሁለት ተኩል አካባቢ ስራ ቦታሽ እመጣና ወስዳታለው..ደህና እደሪ..እወድሻለው፡፡››ብላት ስልኳን ዘጋችው፡፡እንዳለችውም ጥዋት ስትሄድ ፀአዳ ከነንጭንጯ ልጇን ምስርን አስባና አሳምራ ነበር የጠበቀቻት፡፡

‹‹ውይ ጎደኛዬ ንዴት እንደሸወድኩሽ ስታውቂ እንዴት ትናደጂ ይሆን?›› ብላ አሰበችና ብቻዋን ፈገግ አለች፡፡

ሹፌሩ ጎሮ አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቾ ቤት ካደረሳት በኃላ  ሚካኤል እንዲገዛለት ያዘዘው ዕቃዎች ስለሉ ወደመርካቶ ለመሄድ ተዘጋጀ….

‹‹በቃ ነገ አስር ሰዓት አካባቢ እዚህ ድረስ ››አለችው አዲስ፡፡

‹‹እዚህ የምትንቀሳቀሺበት አይቸግርሽም?››

‹‹ችግር የለውም..የትም የመውጣት እቅድ የለኝም…ምን አልባት የምወጣም ከሆነ ራይድ እጠቀማለው››አለችና ሸኘችው፡፡

ከዛ ልጆቹን ወደቤት አስገብታ እናቷን በቅጡ እንኳን ሰላም ሳትል ነው ወደጓሮ ሄዳ ስልክ የደወለችው፡፡ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ‹‹እንዴት ነህ ዘሚካኤል?››

‹‹ሰላም ነኝ..ግን አልተሳካልኝም ብለሽ እንዳታበሳጪኝ››

‹‹አረ ተሳክቶልኛል…መጥተናል እማዬ ቤት ነው ያለነው፡፡››

‹‹በጣም ጎበዝ…..በቃ ጎሮ አካባቢ ነው ያልሺኝ፡፡››

‹‹አዎ… ትክክለኛ አድራሻውን በሚሴጅ ልክልሀለው››

‹‹በቃ..በአንድ ሰዓት ውስጥ እመጣለው››

‹‹ጥሩ ነው..እኛም ገና አሁን መድረሳችን ስለሆነ እስከዛ ከእማዬ ጋ እንጫወታለን…በል ቻው››

‹‹አዲስ በጣም አመሰግናለው…ቻው››

ስልኩ ተዘጋ ፣፣እሷ ግን ፈዛ ቀረች…ከዘሚካኤል ጋር በዚህ መጠን መቀራረብ መቻሏ የተአምር ያህል ነው….ለዘመናት ስታልመውና ስትመኘው የነበረ ነገር ነው፡፡ግን በዚህ መንገድ ይሆናል ብላ ፈፅሞ ሀሳብ አልነበራትም..እሱ የእሷን የልብ ጓደኛ አፍቅሮ እሷ ደግሞ እሱን ከሚያፈቅራት ልጅ ጋር ለማቀራረብ ስትጥር….በራሷ ድርጊት ፈገግ አለች፡፡

‹‹ምን አለበት…. ለሚያፈቅሩት ሰው የሚያፈቅረውን ነገር እዲያገኝ መርዳት ትንሽ ህመም ቢኖረውም ግን ደግሞ ደስ የሚል ስሜት አለው፡፡››አለችና ለስሜቷ ድጋፍ ለመስጠት ሞከረች…የባሏ ሚካኤል ምስል በድንገት መጥቶ አየሩን ሞላው‹‹ፍቅሬ ምን እያሰብሽ ነው…?የገዛ ወንድሜን!!!››ብሎ በሀዘን በተሰበረ ስሜት ሲወቅሳት አየች፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ይሄ እኮ ያለፈ ታሪክ ነው….ታውቃለህ እሱን ለማግኘት ስትጥር ነበር ከአንተ ጋር የተቀራረብኩት…ከዛ እሱም ሀገር ጥሎ ጠፋ አንተም ለእኔ ምርጥና ተወዳጅ ሆንክልኝ..እናም  በሙሉ ልቤም ወድጄ አገባሁህ››

‹‹ግን ስታገቢኝ…ወደሽ ነው..ወይስ አፍቅረሺኝ?››

‹‹አይ አንተ ደግሞ ምን ቃላት ትመነዝራለህ….ለማንኛውም..የእሱ ያለፈ የአፍላ የወጣትነት ስሜት ነው..አሁን እየቀረብኩትና እየረዳሁት ያለሁት ያንተ ወንድም ስለሆነ ብቻ ነው››

‹‹እንዴ…!!ምንድነው  ጓሮ ተደብቀሽ ብቻሽን ምታወሪው?››የእናትዬው የመገረም ንግግር ነበር ከገባችበት ቅዠት መሰል ሀሳብ አባኖ ያወጣት፡፡

‹‹አይ እማዬ ..ምንም አይደል ..የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር››

‹‹የሆነ ነገር..ምነው ከሚካኤል ጋር ተጣላችሁ እንዴ?››

‹‹ወይ እማዬ ምንድነው የምታወሪው..?ከሚካኤል ጋር ለምንድነው የምጣለው?››

‹‹ባልና ሚስት ለምንድነው የሚጣሉት?››

‹‹እኔ እንጃ..እኔና ሚኪ ስንጣለ አይተሸን ታውቂያለሽ?››

‹‹እሱ መልካምና ታጋሽ ባል ስለሆነ ነዋ…እንጂማ እንደአንቺ መመነጫጨቅ ቢሆን… ››እናትዬው ነግግሯን ሳታገባድድ አንጠልጥላ ተወችው፡፡

‹‹እማዬ ደግሞ… የእኔ እናት ነሽ  የእሱ?››

‹‹የሁለታችሁም…ባሌ ነው ብለሽ አምጥተሸ ካስተዋወቅሺኝ ቀን ጀምሮ እኮ ልክ እንደአንቺ እሱም ልጄ ሆኗል…በዛ ላይ አሁን ወርቅ የሆነ የልጅ ልጅ ሰጥቶኛል…በይ አሁን ነይ ግቢ ቁርስ ቀርቧል…››አሏትና ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ፡፡ 

ዘሚካኤል እንዳለውም ከአንድ ሰዓት በኃላ በራፍ ላይ ደርሶ ደወለላቸው፡፡ተዘጋጅታ ስትጠብቀው ስለነበረ ወዲያውኑ ነው ልጆቹን ይዛ የወጣችው፡፡ከግዙፉ ሀመር መኪናው ወርዶ በራፍን ከፍቶ ቆሞ እየጠበቃቸው ነበር…የስድስት አመቷ ምስር እንዳየችው ደነገጠች…..መጀመሪያ የት እንደምታውቀው ነበር ግራ የገባት..ከዛ የምትወደው ዘፋኝና ተዋናይ መሆኑን ስታውቅ ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት እየተንደረደረች ወደ እሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ከቆመበት እጆቹን ዘርግቶ ወደእሷ ተንቀሳቀሰ…እቅፉ ውስጥ ወደቀች.. ጭምቅ አድርጎ አቀፋትና በአየር ላይ አንጠለጠላት..የምስርን ድርጊት ያየው ቅዱስ እጆቹን ከእናቱ እጅ አስለቅቆ ኩስ ኩስ እያለ ምስር እንዳደረገችው ወደዘሚካኤል ሮጠ….አዲስአለም በልጆቹ ያልተጠበቀ ድርጊት  በድንጋጤ አፏን ከፈተች ….ሚካኤል ቅዱስ ስሩ ሲደርስ ምስርን ወደአንዱ እጁ አዘዋወራትና ጎንበስ ብሎ ቅዱስን አቅፎ ወደላይ አነሳውና ጉንጮቹን እያገላበጠ ሳመው…..በዚህ ጊዜ አዲስ አለም ከመደነቅ ሳትወጣ ስራቸው ደርሳ ነበር፡፡

‹‹ቆይ ከእነዚህ ልጆች ጋር ከዚህ በፊት ትተዋወቁ ነበር እንዴ?››

ጉንጮቾን እያገላበጠ ሰማት..ትንፋሹ ልክ ሰው ፊት ላይ እደሚበትን አደንዛዥ ዕፅ ኃይል አለው…
👍6612