አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
491 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አላገባህም


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

ከእንቅልፉ ባኖ አይኖቹን ሲገልጥ በመስኮቱ ሾልኮ የሚገባው ብርሀና መኝታ ክፍሉን አድምቆታል…ቀኝ እጅን ሊያነቃንቅ ቢሞክር አልቻለም….ጭንቅላቱን ዞር ብሎ ሲመለከት አንድ ጠይም ወጣት ክንዱ ላይ ተንተርሳ  ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝታለች….ትነቃለች ብሎ ሳይጨነቅ ከላዩ ላይ ገፍትሮ ወደጥግ ገፋተራትና ከአልጋው ለመውረድ ወደግራው ሲዞር ሌላ ሴት እርቃኗን ብልቅጥቅት ባላ  ሁኔታ ተኝታ አያት፡፡አቅጣጫውን ቀየረና በግርጌ  በኩል ወረደ ፡፡

ሞባይሉን አንስቶ ሰዓት ሲያይ ሰባት ሰዓት  ሆኗል፡፡ብዙም አልገረመውም ፡፡…እስከዚህን ሰዓት መተኛት የአብዛኛው ቀን የተለመደ ተግባሩ ነው፡፡በተለይ ለሊት የናይት ክለብ ስራ በሚኖረውና እዛ አንግቶ በሚመጣ ቀን ሰባትና ስምንት ሰዓት ድረስ ካልተኛ አእምሮ ንፅህ አይሆነም……ቀጥታ ወደሻወር ቤት ሄደና ፈጣን ሻወር ወሰደ፡፡ከዛ ሲወጣ ነጭ ጋዎኑን ለብሶ ወደኪችን ነው የሄደው፡፡በጣም እርቦታል፡፡ፍሪጁን ከፈተና የሚበላ ነገር መፈለግ ጀመረ፡፡ዳቦና ጁስ ያዘና እዛው ወንበር ስቦ በመቀመጥ መመገብ ጀመረ…ወዲያው አንደኛዋ ሴት እንደእሱ እርቧት ሳይሆን አይቀርም መቀመጫዋ ላይ  ስስ ሻርፕ ነገር አገልድማ በከፊል በመሸፈን እርቃኗን ግዙፍ  ጡቷቾን እያማታች መጣችና የኪችኑ በራፍ ላይ ቆመች፡፡

‹‹እ …..የሚበላ ነገር ትፈልጊያለሽ?››

‹‹በጣም እንጂ የእኔ ፍቅር….››

‹‹ተቀመጪ….››አላትና ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደፍሪጁ በመሄድ እንደእሱ ጁስና ዳቦ አዘጋጅቶ ይዞላት መጣና ፊት ለፊቷ አስቀመጠላት፡፡

እየተስገበገበች መብላት ጀመረች፡፡

‹‹እሱም ከፊት ለፊቷ በመቀመጥ የጀመረውን መመገቡን ቀጠለ‹‹ጓደኛሽስ?››

‹‹ምን አድርገሀት ነው..እራሷን እኮ አታውቅም፡፡››

‹‹ምን አደርጋታለው…አንቺን ያደረኩትን ነዋ፡፡››

አፏ ውስጥ ያለውን ምግብ ማላመጧን ሳታቋርጥ ‹‹ወይ …ጀግና እኮ ነህ››አለችው፡፡

‹‹አመሰግናው››

‹‹እሺ አሁን ፕሮግራማችን ምንድነው?››ስትል በአይኗቾ በመለማመጥ ጠየቀችው፡፡

‹‹ማለት….በቃ እንለያያለና…..እናንተም ወደ ጉዳያችሁ ትሄዳላችሁ..እኔም ወደስራዬ….››

‹‹በቃ…?››አለችው በቅሬታ፡፡

‹‹ምነው? የቀረ ነገር አለ እንዴ?››

‹‹ትንሽ ..››አለችና
ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደእሱ በመቅረብ  እጇቾን በአንገቱ ዙሪያ ጠምዝዛ ጉልበቱ ላይ ተቀመጠችና ከንፈሩን ትስመው ጀመር…. አልተቃወማትም….፡፡
እንደውም ሁለት እጆቹን ሁለት ጡቷቾ ላይ አሳረፈና ያፈተለትላት ጀመር፡…ከዛ ይዟት ቆመ….እሷ አንገቱ ላይ እንደተጠመጠመች መሳሟን ቀጥላለች፡፡

ቀስ ብሎ መሬት አስቀመጣትና የለበሰውን ጋወን አውልቆ እዛው ወለሉ ላይ ተወው…አሁን እርቃኑን ቀረ…..ከዛ የእሷንም መቀመጫዋ ላይ ያገለደመችውን ሻርፕ ቋጠሮ ሲፈታው ልክ እንደእሱ ሁሉ እርቃኗን ቀረች….ከዛ ወደግድግዳው ወሰዳትና ፊቷን አዙሮ ግድግዳውን እንድትደገፍ በማድረግ ከኃላዋ አቀፋት…..‹›የእኔ ፍቅር በጣም ነው የምትችለው እሺ…በጣም›››መቃተት ጀመረች፡፡

በዚህ ጊዜ  ከወደ በራፉ የእግር ኮቴ ተሰማ….ሌለናዋ ጓደኛዋ  ነበረች….ተጣብቀው ሲዋሰቡ ስታያቸው እንደመደንገጥ ብላ ባለችበት እንደመቆም አለችና

‹‹እንዴ አሁንም ትዋሰባላችሁ?አያንገሸግሻችሁም እንዴ?››አለቻቸው፡፡

እነሱ ግን ዞር ብለው ሳያዬት የጀመሩትን ቀጠሉ….እሷም ግራ ተጋባች….‹‹ሄጄ እነሱን ልቀላቀል ወይስ የሚበላ ነገር ልፈልግ?››….ስትል ከራሷ ጋር ሙግት ገጠመች‹‹ይሄ ሰውዬማ የሆነ ማግኔት ነገር አለው››ስትል አሰበች፤መጨረሻ  ስሜቷን እንደምንም ገታ የሆዷን ነገር አስቀደመችና ምግብ ወደመፈለጉ ሄደች፡፡

ለዘሚካኤል ይሄ የተለመደ ህይወቱ ነው፡፡አሁን እነዚህን ልጇች ከሶስት ቀን በኃላ የሆነ ቦታ ቢያገኛቸው….‹.የት ነበር ማውቃቸው ?›እያለ ከራሱ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱ አይቀርም..ስማቸውንማ  አሁንም ቢጠይቁት ወይ ሙሉ በሙሉ አያውቅም ወይም የአንዷ ስም ለሌለኛዋ ቀይሮ መስጠቱ አይቀርም፡፡ሴቷቹም በዛ ድርጊቱ ብዙም ሲከፈቸው አያይም…ምን አልባት እሱ የሚያገኛቸው ሴቷች ከተመሳሳይ ቦታ የሚመጡ ተመሳሳይ አይነት አመለካከት ያላቸው ሆነው ሊሆን ይችላል….በድምፃዊነቱና በፊልም ተዋናይነቱ ባገኘው ጣሪያ የነካ ዝና እና የተትረፈረፈ ሀብት ወደእሱ ገና ሲመጡ ለአንድ ቀንም ቢሆን ከእሱ ጋር ማሳለፍ ልክ ሎተሪ እንደወጣላቸው ስለሚቆጥሩ በማግስቱ ፊቱን ሲያዞርባቸው ብዙም አይከፋቸውም፡፡ወይም መከፋታቸውን በአርቴፊሻል ፈገግታቸው ደብቀው እሱ እንዳያውቅ ያደርጋሉ…ያችን ከእሱ ጋር ያሳለፉትን አንድ ቀን ለአመታት ለሌሎች አቻዎቻቸው የሚናገሩትን የሚጎርሩበት ታሪክ ስለሆነ በፀጋ እንዲቀበሉት ምክንያት ሆኗ ቸው ይሆናል፡፡እና ይሄ ጉዳይ የእሱን ባህሪ ከመስመር እንዲወጣ ገፊ ምክንያት ሆኖል፡፡
//
ከጥርብ ድንጋይ የተሰራ  መስኮት አልባ ጥንታዊ ቤት ነው፡፡ግድግዳው ከሶስት ሜትር በላይ ሲረዝም ጣሪያው ከኮንክሪት የተሰራ ነው፡፡እላይ ጥግ በግድግዳው ማብቂያና በጣሪያው መጀመሪያ መካከል ለአይጥ ማሾለኪያ ተብሎ የታሰራ የሚመስል ሶስት ትናንሽ ቀዳዶች አሉ፡፡ከዛ ውጭ ቤቱ ድፍን ነው፡፡
በዛ ላይ ከዚህ ቤት እንዴት አድርጎ ያመልጣል ብላው እንዳሰቡ አይታወቅም….ከምድር በተቀበረ ብረት ላይ የታሰረ ሰንሰለት እግሩን እና እጁን ተጠፍሯል፡፡ክፍሉ 3 በአራት ስፋት ያለው ቢሆንም እሱ መጠቀም የሚችለው ሁለት በሁለት በሆነች ቦታ ላይ ነው፡፡ በቀን ሁለቴ የብረት በሩ ላይ እንደመስኮት ያለች ትንሽ ማሾለኪያ ትከፈትና በትንሽ ሰሀን ምግብና በኩባያ ውሀ አሾልከው  ወለሉ ላይ አድርገውለት  መልሰው ይዘጉታል፡፡

ከዛ ውጭ በወር አንድ ቀን  እየመጡ የሚያናግሩት መነኩሴ አሉ፡፡ለቅጣው የእሳቸው መምጣት ልክ ገበያ የሄደች እናቱን እንደሚጠብቅ ህጻን ነው በናፍቆት የሚጠብቀው፡፡እሳቸውን ስለሚወዳቸው…ወይንም የሚሰጡትን መንፈሳዊ ትምህርትና ተግሳፅ ስለሚማርከው አይደለም….እሳቸው ሲመጡ ጠባብ መስኮት መሰል ሽንቁር ሳትሆን ዋናው በራፍ ይከፈታል፡፡አንድ ጣባቂ ክላሹን አነጣጥሮ በራፉ ላይ ይቆማል..ሌላው ባለደረባው ፈራ ተባ እያለ ወደውስጥ ይገባና ከብዙ ቁልፎች መካከል አንድን መርጦ ሰንሰለቱን ከብረቱ ጋር ያያዘውን ቁልፍ ይፈታል….ከዛ ‹‹ተነስ ጠያቂህ መጥተዋል››ይለዋል፡፡

እንደምንም ከተቀመጠበት ለመነሳት ይሞክራል….ግን የእግሮቹ ድምስሮች የተሳሰሩ ስለሆነ ቀላል አይሆንለትም…እንደምንም ግድግዳውን ተደግፎ ይቆማል..እለት በእለት ወገቡ ወደውስጥ እተቀለመመ እንደሚሄድ ይሰማዋል…እና ለመንቀሳቀስ እግሮቹን ሲያንቀሳቅስ እላዩ ላይ ተጠምጥመው የተቆለፉበት ሰንሰለት ከብደት ይፈትነዋል..ግን ደግሞ እንደምንም እየተጎተተ ወደበረንዳው ይወጣል…..በረንዳው እንደታሰረበት ክፍል የተፈጥሮ ብርሀን የማያገኝ ቢሆንም ሰው ሰራሽ ብርሀን የሚበራበት ስለሆነ አይኑን ይጨፍናል…አይኑ ብርሀንን ይፈራል…አስር እርምጃ ከተራመደ በኋላ ተከፍቶ ወደሚጠብቀው ከፍል ይገባል…ወደክፍል ከገባ በኋላ አጅበውት ከመጡት ሁለት ወታደሮች አንደኛው ክፍሉን ከውጭ ሆኖ ይቀረቅረዋል፡፡
👍7712👎3👏2🔥1