አትሮኖስ
282K subscribers
113 photos
3 videos
41 files
491 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
''ቱ በል ልምታልህ'' አለችው
ሲያለቅስ አቀፈችው።

''ቱ" አለ
በእጇ መታችለት በጥፊ መሬቱን
ማልቀሱ አበቃ አቆመ ምሬቱን!

አደገ
ትልቅ ሆነ

ህይወትን ቢቀየም
ለብቻው አዘነ በዕንባ ላይወጣለት


ዛሬ ሰው የለውም
ጊዜን ማን ይምታለት ?


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍32🥰7
#የምትመስለው

የኔ ልዕልት ...

ጸዳል ክብሯ ከሴት መሐል አቻ የሌለው
በማለዳ ደምቃ የፈካች
ውብ ጸሐይ ነው የምትመስለው

ብዬሸ ነበር ያኔ ድሮ ልጅ እያለው

ግና ዛሬ አደግሁና
ሁሉን በጥልቅ ሳስተውለው
ይቅር በይኝ ማሪኝ ውዴ አጥፍቻለው

ለካ ጸሐይ ራሷ ናት
ቁር'ጥ አንቺን የምትመስለው !
👍16🥰7👏2
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_10

ለመቀንጠስ እጁን ሲያሾል ነበር ያቆምኩት:: ንባቤም ቀጠልኩ። የኔቶ ቀባጣሪም መቀባጠሯን ቀጠለች፣ "ጊዜ በጊዜ እየተተካ በሄደ ቁጥር እኔም ንዴቴ ቀስ በቀስ እየበረደ መጣ። እርግጥ በደሱ ሊረሳ የሚችል አልነበረም። ማንኛውም የሰው ፍጡር የህይወቴ ጎዳና ይህ ይሆናል፣ ሀይወቴንም በዚህ መንገድ፣ እንዲህ አድርጊ! እመራዋለሁ ብሎ የወጠነው ሁሉ ተመሰቃቅሎ ከፊት ለፊቱ የሚያየውና ሊጓዝበት ያሰበው ለስለሳና ደልዳላ መንገድ በእሾህና በጋሬጣ ታጥሮ መውጪያውና መግቢያው ወደማይለይ አባጣና ጎርባጣ መንገድ በቅጽበት ሲለወጥበትና ተስፋ ለተስፋቢስነት ቦታ ሲለቅ ሲያይ መበሳጨት እንዴት ይበዛበታል:: የኔ ሁኔታ ከዚህ የተለየ አልነበረም:: ከአማረ ጋር ሆኜ በደስታና በፍቅር አሳልፈዋለሁ ያልኩት ህይወት የማይጨበጥ ህልም ሆኖ ሲቀር የምመካበትና አንድ አለኝ የምለው ሰው ሲከዳኝና በአንድ ጊዜ ተስፋዬ ተሟጦ የወደፊት ህይወቴ ምን ሊሆን እንደሚችል ልገምት በማልችልበት ሁኔታ ላይ ሆኜ እያለሁ ደስታ ይኖረኛል ብሎ መገመት የዋህነት ነው:: ይሁን እንጂ ዶ/ር አድማሱ በጭንቅት ቀን ከእግዜር የተላከ መልአክ ተመስሎ ባጠገቤ በመገኘቱ ብዙውን ነገር ቀስ በቀስ ባልረሳው እንኳን ለመርሳት እንድሞክር ረድቶኛል:: አብዛኛውን ከትምህርት ውጪ ያለውን ጊዜዬን የማሳልፈው ከእሱ ጋር ነበር፡፡ ብዙውን ጊዜ በትምህርቴ እንድጠነክርና ሁሉንም ነገር እንደ ተራ ነገር እንድረሳው ይመክረኛል፡፡ እኔም አብዛኛውን ጊዜ የግቢውን ወሬ ሳልፈራና ለማንም ቁብ ሳልሰጥ እሱ ቤት እያመሸሁ ጥናቴን ተያያዝኩት፡፡ የሚቸግረኝን እየረዳኝ ከጎኔ ሳይለይ የሚያፅናናኝም እሱ ብቻ ነበር፡፡ ከእሱ ጋር ያለኝ ግንኙነት እየጠነከረ የመሄዱን ያህል የትምህርት ቤት ጎደኞቼ ደግሞ ይበልጥ በጥላቻ ይመለከቱኝ ጀመር። አብዛኛው ተማሪ ከዶ/ር አድማሱ ጋር የነበረኝን ግንኙነት አማረን በጥቅም _ ለውጬ የፈጠርኩት ግንኙነት አድርጎ የተሳሳተ ግንዛቤ ፈጥሮ ስለነበር ቢጠሉኝም በእነሱ አልፈረድኩም:: በተለይ ጓደኞቹ እኔን ጠይቀው በመረዳት ፈንታ እኔን አኩርፈው ወሬውን በመሰላቸው መንገድ ያናፍሱት ስለነበር ተማሪዎቹ የሰሙትን የተሳሳተ ወሬ ሰምተው ቢጠሉኝ አያስገርምም፡፡ ከሃዲዋ እኔ ላልሆን ከሀዲው አማረ መሆኑንና ከዶክተር አድማሱም ጋር ያለኝ ግንኝነት የወንድምና የእህትነት ዓይነት እንደሆነ ለጓደኞቼ ብናገርም የሚያምኑኝ አልነበሩም። ስለዚህም እኔ ይህንኑ ተንትኜ ለማስረዳት እቅሙም ሆነ ችሎታው ስላልነበረኝ እንደመፍትሄ የወሰድኩት ለማንም ሳልጨነቅ ይበልጥ ከተማሪዎች በመራቅ አብዛኛውን ጊዜዬን ከዶክተር አድማሱ ጋር ማሳለፍ ብቻ ነበር።

ጥር 30 ቀን 1978 ዓ.ም

ተሾመ ለእኔ ያለው የፍቅር ስሜት የእብደት እንጂ የጤንነት ነው ማለት ያዳግታል፡፡ አማረ ግቢ ውስጥ በነበረበት ወቅት ምን ያህል እንደምንዋደድና በዚህም የተነሳ ከእሱ ጋር መደባደቡን እያወቀ፣ ከዚህም አልፎ ተርፎ እኔ ለእሱ ፍቅር እንደሌለኝ ደግሜና ደጋግሜ ብነግረውም በፍጹም ሊተወኝ አልቻለም፡፡ እንዲያውም ቀስ በቀስ በሰላማዊ መንገድ እንደማያገኘኝ ስለተረዳ ማስፈራራትና መማታቱን ቀጠለ፡፡ ሌላ የማገባ ከሆነ እኔን፣ የማገባውን ሰውና የራሱን ህይወት ጭምር እንደሚያጠፋ መዛት የዘወትር ተግባሩ ሆነ፡፡ ይሁን እንጂ በወቅቱ ይህንን ለአማረ መናገር ማለት ተጋደሉ ማለት ስለመሰለኝ ለመናገር አልፈለኩም ነበር። አማረ ግቢውን ከለቀቀ በኋላም ተሾመ ይህንኑ ድርጊቱን አጠናክሮ በመቀጠሉ ለመክሰስ እንደወሰንኩ ለኤልሳ ነገርኳት፡፡ ኤልሳ ግን ከከሰስኩት ከዩንቨርስቲ _ ስለሚያባርሩት እሷ እንዲያርፍ እንደምትነግረውና ነገር ግን ምክሯን ሰምቶ ካላረፈ ለወላጆቹ ደውላ እንደምትነግር ቃል ስለገባችልኝ ክሱን ተውኩት፡፡ የነገርኳትን ነግሬዋለሁ ካለች በኋላ ለተወሰነ ጊዜ መተናኮሉን ቢያቆምም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ዶ/ር አድማሱ ቤት አዘውትሬ መሄዴን በማወቁ ተመልሶ አገረሸበት፡፡ ኤልሳ ይህንኑ ጉዳይ ለወላጆቹ ነግሬአለሁ ትበል እንጂ እሱ ግን በፍፁም ሊታገስ አልቻለም፡፡ በተለይ ሁሌ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ማታ ማታ እየጠበቀ የሚያስፈራራኝና የሚመታኝ ባጋጣሚ ከኤልሳ ተለይቼ በምሄድበት ጊዜ ስለነበር ሆን ብላ ከእሱ ጋር እየተነጋገረች ምክንያት ፈጥራ ከእኔ የምትለይ እየመሰለኝ መጣ፡፡ በወንድምነት ይሁን ወይም በጾታዊ ፍቅር መሆኑ በግልጽ ባይገባኝም፤ ኤልሳ እንደምትወደው ግን አውቃለሁ፡፡ እሱ ግን ለእሷ አንዳችም ፍቅር የለውም.፡፡ እኔ እንዲያውም አንዳንዴ ብገላገል በማለት እስኪ እንደምትወጂው ልንገረው ካልኳት፤ ይህንን ከነገርኩት እንደምንጣላ ከመናገር ውጪ እሱን የእሷ ለማድረግ የምታደርገው ጥረት ግን የለም፡፡ ተሾመ ከእኔ ጋር የሚፈጠረውን አምባጓሮ እያየች ምንም የቅናት ስሜት ስለማላይባት ሆን ብላ እኔና እሱን ለማፋቀር የምታደርገው ምክንያት እንጂ ከእሱ ጋር ፍቅር የላትም ብዬ እንድጠረጥር አደረገኝ፡፡ በመጨረሻም ማስቸገሩ ሲበዛብኝ ሁኔታውን ለዶ/ር አድማሱ ነገርኩት፤ ልከሰው ስላሰብኩም ምን እንደሚመክረኝ ጠየቅሁት፡፡ እሱ ግን መፍትሄ እንድሚፈልግልኝ ቃል ገብቶ እንዳልከሰው ከለከለኝ፡፡ ዛሬ የመጀመሪያውን ሴሚስተር _ ፈተና ጨርስን ውጤት ተለጥፎ በነበረበት ምሽት ወደ ራት ስሄድ ተሾመን እንደተለመደው ከራት ስመለስ ብቻውን አገኘሁት፡፡ ገና እንደደረሰ በጥፊ ካጮለኝ በኋላ፤

"አንቺንም፣ ያን ዶክተርሽንም ካልደፋኂችሁ እኔ ተሾመ አይደለሁም፡ ብሎ ዝቶብኝ ሄደ። አጥፊው በላይ ፊቱ ላይ የነበረውን ንዴቱን ሳይ ክፉኛ ደነገጥኩ፣ ተናደድኩም፡፡ ወዲያው ዶ/ር አድማሱ ጋ ሄድኩና፤ "አንተ ነህ እንዲህ እምትጫወትብኝ፣ ልክሰስ ስልህ እኔ አስታግሰዋለሁ እያልክ ልታስገድለኝ ነው፡፡ ከአሁን ወዲያ የፈለከውን ብትል አላምንህም፣ ቢፈልጉ እንኳን ከዩንቨርስቲ ማባረር _ ቀርቶ እንጦሮጦስም ይክተቱት እንጂ እኔ እንደሆነ ነገ መክሰሴ አይቀርም" እያልኩ ጮህኩበት፡፡ እሱ ግን በተራጋጋ መንፈስ በጥፊ የቀላውን ፊቴን በእጁ እያሻሸ፤ “በቃ ተይ አትናደጂ፣ ከአሁን በኋላ መክሰስ ትችያለሽ፣ እኔ አያገባኝም፡፡ እኔ ይሰማኛል በማለት አንድ ሁለት ጊዜ መካክሬው ነበር፡፡ እሱ ግን ብመክረውም ተመልሶ እዛው ስለሆነ ከአሁን በኋላ አያገባኝም፤ ነገውኑ ክሰሺው" አለኝ፡፡ ጠዋት እሱን ለመክሰስ ወስኜ ከቤት ብወጣም፣ ኤልሳ ቁርስ እየበላን ሳለ ተሾመ በዶ/ር አድማሱ ሁለት ኮርሶች ኤፍ (F) ማግኘቱንና ከዩንቨርስቲ መባረሩን ነገረችኝ፡፡ ይህንን ስሰማ በጣም ደነገጥኩ፡፡ እንደተለያየን በጥድፊያ ወደ ዶ/ር አድማሱ ቢሮ አመራሁ፡፡ እንደገባሁም በሩን ከኋላዬ ዘግቼ! "ዶ/ር፣ ለእኔ ብለህ ነው እንዴ ለተሾመ ኤፍ (F) ሰጥተህ ከትምህርት ቤት እንዲባረር ያደረከው" ብዬ አፈጠጥኩበት?' እሱ ግን ምንም እንደማያውቅ በሚመስል ሁኔታ፤ "ተሾመ ኤፍ አምጥቶ ተባረረ ነው የምትዪኝ? እኔ የሰማሁት አሁን ገና ከአንቺ አፍ ነው፡፡ ለመሆኑ በምን ትምህርት ነው ኤፍ ያመጣው?" ብሎ እኔኑ መልሶ ጠየቀኝ፡ "አንተ በምትሰጣቸው ሁለት ትምህርቶች ነው ወድቆ የተባረረው። ይህንን አታውቅም ማለት ነው?' አልኩት በንዴት፡፡ "ማወቅ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ልጁ ሰነፍ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ እሱ ትምህርቱን ትቶ አንቺን አፈቀርኩ እያለ ሲሟዘዝ ስለሚውል ቢወድቅ የሚደንቅ አይደለም፡፡ እርግጥ በእኔ ትምህርት ኤፍ ያገኙ ተማሪዎች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ እኔ ሁሌ ፈተና ሳርም እንዳላዳላ (Bias እንዳልሆን) በማለት ስም ስለማላይ ኤፍ ያገኘው እሱ ይሁን ሌላ ሰው የማውቀው
👍404
ነገር የለም፡፡ ያም ሆነ ይህ አንቺ ምን አስጨነቀሽ? እንዲያውም አንቺ ከስሰሺው ለእሱ መባረር ምክንያት ከመሆን ድነሻል" ብሎ በተረጋጋ መንፈስ አባብሎ ሸኘኝ።

ከተሾመ መባረር በኋላ የግቢው ሰው በእኔ ላይ ያለው ጥላቻ እየተባባሰ መጣ። እርግጥ ተሸመ ከእኔ ጋር ባለው ጠብ የተነሳ ሆን ተብሎ በዶ/ር አድማሱ እንደተባረረ ለአካዳሚክ ኮሚሽን ከሶ በተደረገው ምርመራ ይህንን የሚደግፍ ወይም የሚያረጋግጥ ምንም ማስረጃ ስላልተገኘ ክሱ ውድቅ ተደርጎበታል፡፡ ይሁን እንጂ እኔን ራሴን ጨምሮ አብዛኛው ተማሪ ዶ/ር አድማሱ ሆን ብሎ ያደረገው ነው በማለት በመጠርጠራቸው በዚህ የተነሳ ቢጠሉኝ አያስደንቅም፡፡ ያም ሆነ ይህ እያዘንኩም ቢሆን ተሾመ ግቢውን ለቆ በመሄዱ ሰላም አገኘሁ፡፡ ነገር ግን ኤልሳ በዚሁ የተነሳ ውስጥ ውስጡን ተቀይማኝ ስለነበር ጓደኝነታችን ቢቀጥልም እንደድሮው ግን ሊሆን አልቻለም፡፡ ሰኔ 4 ቀን 1978 ዓ.ም "እግዚአብሄር ሳይደግስ አይጣላም እንደሚባለው ሁሉ፣ በዚህ ግቢ ውስጥ የተለያየ ችግርና መከራ ቢፈራረቅብኝም በዶ/ር አድማሱ እርዳታ የመመረቂያ ፕሮጀክቴን በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቲ ለማቅረብ ዝግጅቲን ጨረስኩ:: የምመረቀው በእርሻ ምህንድስና ሲሆን የመመረቂያ ፕሮጄክቴ ጥቃቅን የመስኖ ቴክኖሎጂ (Micro-Irrigation) በሚባለው ላይ ነበር። እነዚህ በቀላሉ በሰው ጉልበት ወይም በእንስሳት ኃይል ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ የህ ፓምፖች ሲሆኑ ወንዞችን፣ በጉድጓድ ወይም በኩሬዎች የተከማቸ ውሀን በመጠቀም ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የሚጠቅም የመስኖ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ እንደ ዛምቢያና ናይጄሪያ በመሳሰሉ አገሮች በስፋት የሚጠቀሙበት ሲሆን “አርፈሽ ተኚ” እያሉ ይጠሩታል:: ይህ ስያሜ የተሰጠው ወንዱ ቀን ቀን በዚህ ፓምፕ ውሀ ለማውጣት በእግሩ ወይም በእጁ ፓምፑን ሲያሽከረክር ውሎ ደክሞት ወደ ቤት ስለሚገባና ለወሲብ የሚሆን አቅም ስለሌለው ሚስቱ እንዳትረብሸው የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማሳየት የሚጠቀሙበት ብሂል ነው:: ለፕሮጄክት የተጠቀምኩበት ቴክኖሎጂ በአገራችን እምብዛም የተለመደ ስላልነበር ተግባር ላይ ቢውል ጠቀሚታው የጎላ ነው በሚል የመረጥኩት ሲሆን፤ በአነስተኛ ወጪ ከአካባቢ ቁሳቁስ ሊሰራ የሚችልና ማንኛውም ሰው በቀላሉ ተረድቶ ሊተገብረው የሚችል ተስማሚ ቴክኖሎጂ ነው:: ፕሮጄክቱን በዓለማያ አካባቢ ካሉ አርሶ አደሮች ጋር በጋራ ያከናወንነው ሲሆን ገበሬዎቹ ይህንን ፓምፕ በአካባቢያቸው ከሚገኝ ቁሳቁስ _ ሰርተው ውሀ ለማውጣትና ሰብላቸውን ለማጠጣት ተጠቅመውበታል፡፡ በዚህም ከፍተኛ ምርት ሊያገኙ ችለዋል፡፡ የመመረቂያዬ ቀን ተቃርቦ ፕሮጄክቴን የማቀርብበት ቀን ሲደርስ የተደባለቀ ስሜት ፈጠረብኝ፡፡ በአንድ በኩል ይኸን ለእኔ ገነትም ገሀነምም የነበረውን ዩንቨርስቲ ለቅቄ የምወጣበት ቀን በመድረሱ ሁሉንም ነገር በቶሎ

አጠናቆ መውጣት ደስታን ሲፈጥርብኝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ፍቅርን ከነፈጉኝ ተማሪዎች ፊት ቆሜ ፕሮጄክቴን ማቅረብ ፍርሀት ነዛብኝ: ዶ/ር አድማሱ ቀደም ሲል ፕሮጀክቴ አድናቆት ማግኘቱን፣ አብሬ ከምሰራው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የአምስት ሺ ብር ሽልማት ያስገኘልኝና በዩንቨርስቲውም ተደናቂነትን ያተረፈ መሆኑን ያውቅ ስለነበር፤ ያለፈውን ነገር ሁሉ ትቼ ዛሬ ፕሮጄክቴን በተዋጣለት መልኩ በማቅረብ ላይ እንዳተኩር ደጋግሞ መክሮኛል:: ለእኔም ከሐሳብ የመውጪያ ብቸኛው መንገድ ይኸው በመሆኑና ብዙ ደክሜበት ስለነበር የተዋጣለት እንደሚሆን እርግጠኛ ነበርኩ:: ቀኑ ደርሶ ፕሮጄክቴን ለማቅረብ ስወጣ ጉልበቴ አካላቴን መሸከም አቅቶት ተብረከረከ፡፡ እንደምንም ወጥቼ የመጀመሪያውን ቃል ለመናገር አፌን ከከፈትኩ በኋላ ግን ፍርሀቴ ጠፍቶ ሁለመናዬ ፕሮጄክቴ ውስጥ ገባ:: የፈራሁት የተማሪዎች ዓይን ብዙም ተፅዕኖ ሳያሳድርብኝ ሁሉም ነገር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡ ጥሩና ስኬታማ ነገር በማቅረቤ ተማሪው እጅግ ከመደነቁ የተነሳ ባልጠበቁት ሁኔታ ወደ መቀመጪያ ቦታዬ እስከምደርስ ድረስ ቆመው አጨበጨቡልኝ፡፡ የጠበቅሁትን ሳይሆን ያልጠበቅሁትን በማየቴ እጅግ ተደሰትኩ፡፡ እነዚያ ይጠሉኛል ብዬ የምገምታቸው ተማሪዎች ሁሉ ቆሞው ሲያጨበጭቡልኝ ሥራዬ በእርግጠኝነት የተዋጣለት መሆኑ ተሰምቶኛል፡፡ ከእኔ በፊትም ሆነ በኋላ እንደ እኔ የተጨበጨበለት ተማሪም አልነበረም:: ወደ ወንበሬ እንደተመለስኩ መጀመሪያ መመልከት የፈለኩት ዶክተር አድማሱን ነበር፡፡ እንደእኔ የደከመበት ፕሮጄክት ስለነበር ምን እንደተሰማው ለማወቅ መጓጓቴ አግባብነት ነበረው:: መድረኩ ላይ ቁጭ ብሉ ተማሪዎቹ ሁሉ የእኔንና የእሱን ሁኔታ እንደሚከታተሉ ቢያውቅም፣ ለዚህ ምንም ቁብ ሳይሰጠው ከሌሎች አስተማሪዎች በተለየ ሁኔታ እያጨበጨበ ፊቱ በፈገግታ ተሞልቶ በአድናቆት ራሱን ሲነቀንቅ በማየቴ ዓይኔ በእምባ ተሞላ፡፡ ስሜቴን መቆጣጠር ተስኖኝ የደስታ እምባ በጉንጮቼ ላይ ወረደ:: እርግጥ ደስታና ሐዘን የተፈራረቀበት የዩንቨርስቲ ህይወቴ ባልጠበቁት አኳኋን እንዲህ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ በደስታ ብዛት ባነባ የሚገርም አልነበረም። እነሆ እኔና ዶ/ር አድማሱ የለፋንበትና የደከምንበት ፕሮጄክት በውጤታማነት ተጠናቀቀ፡፡ ሁሉም ነገር በዚህ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የረዳኝን አምላኬንም እዚያው እተቀመጥኩበት ዓይኔን ጨፍኜ ምስጋና አቀረብኩለት፡፡ ለእኔ የዚህ ፕሮጄክት መሳካት ለትልቅ ግምት የሚሰጠው ነበር፡፡ ምክንያቱም በሁሉም ውጤቶቼ ከተማሪው በሙሉ የተሻለ ከፍተኛ ውጤት ያመጣሁ በመሆኔና ፕሮጄክቴም በጠበቅሁት ሁኔታ ከተጠናቀቀ የሽልማቱ ወርቅ የእኔው እንደሚሆን የማረጋግጥበት ወቅት በመሆኑ ነው:: ይህንንም ዛሬ ማረጋገጥ ስለቻልኩ በደስታ ባለቅስ የሚበዛብኝ አልነበረም:: ተማሪው ይህንኑ

ስለሚያውቁ፣ እኔን ቢጠሉኝም ሥራዬን ግን በመውደዳቸው አልባቸው አጨብጭበውልኛል:: ተማሪዎቹ ሁሉ ይጠሉኛል ብዬ የማስብ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ግን "ማን ያውቃል ብዙ የሚወዱኝ ሊኖሩ ይችላሉ ብዬም ማሰብ ጀመርኩ:: ሰኔ 25 ቀን 1978 ዓ.ም ዛሬ የመመረቂያችን ቀን በመሆኑ ግቢው ጥቁር ገዋን በለበሱ ተማሪዎች፣ የአበሻ ቀሚስና ሱፍ ልብስ በለበሱና ልጆቻችውን ለማስመረቅ ተጋጊጠው በመጡ ወላጆች አሸብርቋል። ይህ ቀን ለእኔ እንደአለፈው ሕይውቴ ሁሉ ሁለት ገፅታ አለው፡፡ በአንድ በኩል የተማሪዎች ቁንጮ መሆኔ የሚበሰርበት የብስራት ቀን ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ውጣ ውረድ የበዛበት የታሪኬ ምዕራፍ የሚዘጋበት ዕለት ነበር:: አባቴ በወቅቱ በመታመሙ ምክንያት ባይመጣም እናቴ ግን መጥታ ነበር፡፡ የምፀልየው ግን እናቴ የሳንቲሙን አንድ ገፅታ ብቻ ሰምታና አይታ እንድትመለስ ነበር፡፡ ይህም ደክማና ለፍታ ያሳደገቻት ልጅ የተማሪዎች ቁንጮ ሆና ስትመረቅ ማየት ነው:: ይህንንም ሳስብ ልቤ በደስታ ይሞላል:: እንደጠበቅሁትም ሆነ፡፡ የሽልማቱን ወርቅ አጥልቄ እንዳየች እናቴ ማልቀስ ብቻ ሳይሆን በእምባ ታጥባ ነበር፡፡ ተቃቅፈን ተላቀስን፡፡ ዶ/ር አድማሱም ዛሬ ደስታውን መቆጣጠር _ አልቻለም:: _ ከአዳራሹ ስንወጣ የተማሪዎቹ ዓይን ሳይፈራ አቅፎ ሳመኝና፤ “አንቺ ገና ብዙ ትላልቅ ነገር ሊሰራ የሚችል ጭንቀላት ያለሽ ነሽ፡፡ አደራ በማይረባ ነገር እንዳታበላሺው" አለኝ፡፡ ለራሴም ከአሁን በኋላ ይህንን ጭንቅላት ላላበላሸውና ትላልቅ ረቂቅ ነገሮችን የሚያብሰለስል እንጂ ግለሰቦችንና የእነሱን ዝባዝንኬ ታሪክ በማውጣትና በማውረድ እንዲላሽቅ እንደማላደርገው ቃል ገባሁ፡፡ ከምረቃው አዳራሽ እንደወጣን ፎቶግራፍ ለመንሳት ወደ አትክልቱ ቦታ አመራን፡፡ አማረን ለማስታወስ
👍252
በማለት በእነዚያ በአጭሩ በተከመከሙና በመንገዱ ግራና ቀኝ በተተከሉ ፅዶች በተዋበው "የፍቅር ጎዳና" ላይ እስከሚበቃኝ ድረስ ከእናቴ፣ ከዶ/ር አድማሱና ከብዙ አድናቂ ተማሪዎች ጋር ፎቶ ተነሳሁ፡፡ እያንዳንዷ ከሰዎች ጋር ተቃቅፌ የምነሳት ፎቶ፣ ከአማረ ጋር ከላይብረሪ ወጥተን በዚህ መንገድ ላይ ተቃቅፈን የሄድንበት ጊዜ የሚያስታውሰኝ በመሆኑ ከደስታዬ ባሻግር አንዳች ነገር እንደቀረብኝ ዓይነት ስሜት ተሰማኝ፡፡ አፍ አውጥቼ ባልናገርም፤

"ምናለ ዛሬ አጠገቤ በነበርና ደስታዬ እጥፍ ድርብ በሆነ˚ አልኩ፡፡ ምረቃው ካበቃ በኋላ ግቢውን ለቅቄ የምሄድበት ቀን ቁርጥ እየሆነ ሲመጣ ደግሞ ፍርሀት ወረረኝ:: ግን ለምን? ከዚህ በኋላ እዚህ ምን ቀረኝ? ለምንስ ፈራሁ? ራሴን ጠየቅሁ:: አዎ! እርግጥ ነው የእኔ ለእዚህ መብቃት ምሥጋናው መድረስ ያለበት ለዶ/ር አድማሱ ነው:: ይህንን ሁሉ መከራ አልፌ ለዚህ እንድደርስ ያበቃኝ እሱ ነው:: የቀረኝ አንድ ጓደኛም እሱ ብቻ ነበር:: ዛሬ ደግሞ በተራው እሱንም ላጣው ነው። ከእሱ መለየቴን ሳስብ ልቤ በፍርሀት ራደ:: ለዚህ ሁሉ ውለታው ምን ሊከፈለው ይቻላል? ይህን ምንም ስጦታ ሊተካው የማይችለውን ውለታውን እኔ ከፍዬ ልወጣው ስለማልችል አምላኬ ሁሉንም ጥሩ ጥሩ ነገር እንዲያደርግለት ተመኘሁ:: እናቴን ግቢውን እያዞርኩ ሳስጎበኛት በመዋሌ በጣም ደክሟት ስለነበር በጊዜ መተኛት በመፈለጓ አልጋዬን ለቅቄላት እኔ ግን ከጎደኞቼ ጋር እንደማድር ነግሬያት ተሰናብቼያት ወጣሁ፡፡ ይህንን ሁሉ ጊዜ አጠገቤ ሆኖ ሲያፅናናኝና ሲረዳኝ የነበረውን ዶክተር አድማሱን ቀኑን ሙሉ ስላላገኘሁትና የዋለልኝን ውለታ ሁሉ ልመልሰው የማልችል ቢሆን እንኳ ቢያንስ አቅሜ የቻለውን ስጦታ መስጠት አለብኝ ብዬ በመወሰኔ ስጦታዬን ይዤ ወደ ቤቲ አመራሁ:: ወደ ቤቱ እንደምመጣ ያወቀ ይመስል ቤቱን አሰማምሮ ጠበቀኝ:: ጠረጴዛው በምግብና በተለያዩ መጠጦች በመሞላቱ ሌላ እንግዳ ይኖራል ብዬ ገመትኩ፡፡ እንደገባሁ እቅፎና ጉንጬን ስሞ ወንበር ስቦ አስቀመጠኝ:: ብቻችንን እንድንሆን ፈልጌ ብሄድም የዶክተር አድማሱ ዝግጅት ሲታይ ግን እንግዳ እንዳለበት ያመላክታል፡፡ ከዚህ ቀደም ሰው ሲጋብዝ አይቼው ስለማላውቅ፤ “እንግዶች ጋብዘሃል እንዴ?'' አልኩት፡፡ “አዎን ትልቅ እንግዳ፣ ከእንግዶች ሁሉ የላቀና የማከብረው'' አለኝ:: "ማንን?" አልኩት ግራ ተጋብቼ፡፡ "አንቺን” አለኝ ጉንጬን እየሳመ፡፡ ፍላጎቴ ይህ ስለነበር ደስ አለኝ፡፡ ጠረጴዛው ላይ _ ለስላሳና አልኮል መጠጦች እንዲሁም የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ተደርድረዋል:: በሕይወቴ ከአማረ ጋር ከጠጣሁት ቢራ ውጪ ሌላ አልኮል መጠጥ ጠጥቼ አላውቅም፡፡ ዶ/ር አድማሱ አልፎ አልፎ ወደ ቤቱ ስሄድ ቢጋብዘኝም፤ ያቺ የመጀመሪያዋ መጠጥ ያስከተለችውን መዘዝ ስለማውቅ፣ መልሴ ሁሌ "አልወድም ነበር፡፡ ታዲያ ዛሬ የተለያዩ የአልኮል መጠጦችንም ደርድሮ ሲጠብቀኝ ገረመኝ፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ ደስ

ስላለኝና ቀኑንም ለየት ላደርገው ስለፈለግሁ እንካንስ መጠጥ የሚያስደስት ከሆነና ካልገደለኝ መርዝም ቢቀርብልኝ እንደምጠጣው እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ የማላውቀውን የመጠጥ ዓይነት ሲያስመርጠኝም አልጠጣም የሚል ቃል ትንፍሽ አላልኩም:: “የቱ ይሻልሻል? ውስኪ፣ ቢራ ወይስ ወይን?” አስመረጠኝ፡፡ “አንተ የምትጠጣውን፣ ደስ ያለህን ቅዳልኝ' አልኩት፡፡ "እንግዲያውስ ውስኪ ይሻልሻል፡፡ ዛሬ የደስታ ቀን ስለሆነ በመጠኑ ብትጠጪ አይጎዳሽም ብሎ ቀዳልኝ፡፡ በሆዴም ቢጎዳስ፣ ለአንድ የደስታ ቀን ያልሆነ ጨጎራ ወይም ጉበት ይበጣጠስ አልኩ፡፡ (የሚጎዳውን ባላውቅም መቼም ከእነዚህ አንዱን ይሆናል ብዬ ጠርጥሬ)። ራት ከበላን በኋላ በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ ትንሽ ፓኮ አምጥቶ ስጠኝ፡፡ ክፈቺው ብሎ ስከፍተው ውስጡ የወርቅ ሀብልና ፖስት ካርድ ነበረበት:: ሀብሉን አንስቶ አንገቴ ላይ አጠለቀልኝና ፖስት ካርዱን "አንብቢው" አለኝ። “የእኔ በመሆንሽ ኮራሁብሽ፣ እንኳን ደስ አለን፡፡ ለእኔ የመጀመሪያዬና የመጨረሻዬ እንደምትሆኚ ቃል እገባለሁ" ይላል፡፡ ደነገጥኩ፡፡ የደነገጥኩት ስጦታ ልሰጠው መጥቼ ስለቀደመኝ ሳይሆን እኔ እሱ ለሚመኘው ጉዳይ መብቃቴ ላይ እርግጠኛ ስላልነበርኩ ነው፡፡ ከስጦታው በኋላ መጠጡን እየቀማመስን መዝናናቱን ተያያዝነው:: በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበረ ሙዚቃ ተከፍቷል። ከቴፑ የሚወጣው ድምፅ እንኳንስ ህያው ሰብዓዊ ፍጥረትን ቀርቶ ዛፍንም ቢሆን ማንቀሳቀሱ አይቀርም ያሰኛል:: ዶክተር አድማሱ መለያየታችን ተሰምቶታል፡፡ ከወትሮው ለየት ባለና በሚያሳዝን ሁኔታ ስለመለያየታችን አስከፊነት እየደጋገመ ያወራኛል:: በመሀሉ ፈራ ተባ እያለ “እንደንስ አለኝ" “አልችልም" አልኩት “ምን መቻል ያስፈልጋል፣ ነይ እኔ አሳይሻለሁ" ብሎ እንድንደንስ እጁን ሰጠኝ፡፡ በቀዝቃዛ ሙዚቃ ታጅበን ቯልስ መደነስ ጀመርን:: ከአንገቱ ስር ውሽቅ ብዬና ደረቱ ላይ ተለጥፌ ስደንስ ሰውነታችን ብቻ ሳይሆን ልባችንም ሲደንስ ምቱ ይሰማ ጀመር:: የሰውነታችን ሙቀት ከእኔ ወደ እሱ ከእሱ ወደእኔ ሲመጣ በግልፅ ታወቀኝ::

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍30
''ምነው?'' አላት ዝም አለች
ለቅሶ ከየት ይምጣ ዕንባ ጨርሳለች

    ''ንገሪኝ'' ብሎ ዓይኗን ሲያየው
        ቆይቷል ሰው ካወያየው።

          አቀፋት ዝም እንዳለች
          ለዘላለም ቀዝቅዛለች

             "ደና ነሽ" አላት
          እንደምንም እየጣረ

      አንድ ቃል አወጣች
                ''ደና ምን ነበረ?''

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
🥰14👍112
ከቃላት ስብስብ ከመፃፍት ማህደር
ከሊቅ ፀሐፍቶች ከአዋቂዎች መንደር
የቅን ልብ መግለጫ አንቺን የሚመስልሽ ፈልጌ አስፈልጌ ቃል አጣሁ ሚገልፅሽ!።

አለኝ ብዙ መውደድ አለኝ እልፍ ፍቅር መግለፅ ስላልቻልኩኝ ፍፁም እንዳይልሽ ቅር
ብቻ እንድታውቂው እኔ ደስ እንዲለኝ
አንድ ነገር ልበል በልብሽ ፃፊልኝ፣

እ-ወ-ድ-ሻ-ለ-ው!!
9👍7
#ወፍ_በሆንኩኝ

ምንአለ ለዛሬ በሆንኩኝ እና ወፋ፤
በክንፌ በርሬ ግቢአችሁ ለማረፍ፤ ስትገቢ-ስትወጭ አንችን እያየሁኝ፤ ለሰከንድኦች እንኳን ምነዉ ወፍ በሆንኩኝ፤

ፍቅርሽን ሰርቄ ይዠው በበረርኩኝ፤
👍7
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_10


የዶክተር አድማሱ ሁኔታ ዛሬ ለየት ያለ ቢሆንም እነን ግን አላስፈራኝም:: ብዙ ጊዜ ወደ ቤቱ ስመጣ በራስ የመተማመን ስሜት ይሰማኛል:: የማልፈልገውን ነገር ከፍቃዴ ውጪ እንደማያደርግ እርግጠኛ ነኝ:: ይህ ጠባዩ ነው እሱን አእማረ የተሻለ የሚያደርገው:: ከውስኪው እየተጎነጨሁ በሄድኩ ቁጥር የደስታ ስሜት እየተሰማኝ መጣ:: ለምደንሰው ዳንስም መጠንቀቅ ትቼአለሁ:: ሰውነቱ ላይ ተለጥፌ ስደንስ፣ እሱም አንገቴን ሲስመኝ ሰውነቴ ልክ ኮረንቲ እንደያዘው ነዘረኝ፡ “አልሚና እውነት እኔና አንቺ አሁን ልንለያይ ነው?" ይለኛል በየጨዋታው መሀል፡፡ ዝም ስለው ትንሽ ቆየት ይልና እርግጠኛ በሚመስል አኳኋን፤ “በፍፁም አንለያይም" ይላል:: እኔ ግን ዳግም እንደማንገናኝና ዛረ የመጨረሻችን እንደሚሆን እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ “አልሚ ዛሬ መቼም መሸ እንደማትይኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ለመሆኑ እናትሽን የት አስተኛሻቸው?" አለኝ በዳንሳችን መሃል። እኔ አልጋ ላይ ተኝታለች፡፡ እኔ ግን አንተን ሳልሰናበት መሄድ ስለሌለብኝና ላደረክልኝ ውለታ ተመጣጣኝ የሆነ ነገር ማድረግ ባልችልም ቢያንስ ያለችኝን ትንሽ ስጦታ ልሰጥህ ነው የመጣሁት” አልኩት፡፡ “የስጦታ ትንሽ የለውም፡፡ ደግሞስ ምን ውለታ ውዬልሽ ነው? እኔ ያደረኩት ነገር ቢኖር በተሳሳተ መንገድ ተጉዘሽ ተስጥኦሽን አላግባብ እንዳታጠፊው መንገዱን ማሳየት ብቻ ነው'' አለኝ፡፡ እኔም የእሱ ውለታ እንዲህ እንደቀላል ነገር የሚታይ እንዳልሆነና የሰውን ልጅ የሕይወት ጎዳና ከማስተካከል የበለጠ ክቡር ውለታ እንደሌለ ነገርኩት። ጭምቅ አድርጎ አቅፎ ዓይን ዓይኔን ወደ ታች እያየና ግንባሬን እየሳመ ምን እንደሚያደርግ ግራ እንደተጋባ ሰው ተመለከተኝ:: በመሀሉ እንደባነነ ሰው፤ “አልሚ ግን ስጦታው ምንድነው?''አለኝ፡፡ “ልሰጥህ የምችለው ትንሽ ነገር፤ ግን ክቡር የሆነውን ራሴን ነው ብዬ ልብሴን ማወላለቅ ጀመርኩ፡፡ ዶክተር አድማሱ የሀፍርት ሸማውን ስቀድለት ፊቱ በሙሉ በፈገግታ ብርሀን ተሞላ፡፡ እቅፍ አድርጎ እየሳመ ወደ መኝታ ቤት ተሸክሞ ወሰደኝ:: የተዘጋጀሁበት ጉዳይ ስለነበር በመደሰቱ ደስ አለኝ፡፡ ቢያንስ ዛሬ በእኔ ይደሰት:: የባከነ ገላን ለአንድ ቀን ብዙ ውለታ

ለዋለና አለኝታ ለነበረ ጓደኛ አሳልፎ መስጠት ትልቅ ስጦታ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል አይደለም፣ ያውም ደስታው ለጋራ ለሆነ ነገር! ዶ/ር አድማሱ አልጋ ላይ አስተኝቶኝ ልብሱን አወላልቆ ራቁትን ላየው አፍረት ተሰማኝ፡፡ ለምን እንደሆን ባይገባኝም ፍቅረኛዬ ሳይሆን አስተማሪዬ መሆኑ ጎልቶ ስለታየኝ በእፍረት መልክ አንሶላውን ገልጩ ውስጥ ገባሁ፡፡ መብራቱንም ለማጥፋት እጄን ስዘረጋ፣ እጀን ወደ ቦታው እየመለስና አንሶላውን እየገፈፈ፤ "አልሚና ዛሬማ ይህንን የናፈቅሁትን ገላ እንዳላይ ሊሸፈንብኝና መብራት ሊጠፋብኝ አይገባም፡፡ ሲሆን ሲሆን ጠግቤ በደንብ እንዳየው ተራ መብራት ብቻ ሳይሆን ፓውዛ ሊበራበት በተገባ ነበር" እያለ ከላይ ጀምሮ ገላዬን እየሳመ ቀስ በቀስ ወደ ሆዴ መውረድ ጀመረ፡፡ እንደፈራሁት ሳይሆን ሰውነቴ ሰውነቱን ለመቀበል ተዘጋጀ፡፡ ዶክተር አድማሱ ግን እዚህ ላይም እንደሌላው ጊዜ ረጋ ያለ ስለነበርና ሳይቻኮል መሳምና መደባበሱን ብቻ ስለተያያዘው እዚሁ ላይ እንዳይቆም መፍራቴ አልቀረም፡፡ እኔ ሁሉም ነገር በቶሎ እንዲሆን ከመጠን በላይ የቸኮልኩ ቢሆንም እሱ ግን ስሞና ዳሶ ሊጠግበኝ አልቻለም፡፡ በስስት መልክ የማይስመው የሰውነቴ ክፍል አልነበረም፡፡ ይህ ደግሞ እኔን ይበልጥ አጣደፈኝ፡፡ እንደፈራሁት አልሆነም ስሞኝ እንደጠገበ ስጦታዬን ተቀበለኝ፡፡ ግን ነገሩ ሁሉ እንደቸኮልኩለት አልሆነም፡፡ ደስታው የእሱ እንጂ የጋራችን ሊሆን አልቻለም፡፡ ለእኔ እዳ የመክፈል ያህል ሲሆንብኝ ለእሱ ግን ሴት ገላ ውስጥ ሳይሆን ገነት የገባ ያህል ተሰምቶት ነበር:: በጣም የገረመኝ ነገር ቢኖር በየመሀሉ የማስበው ከፍቃዴ ውጪ ከአማረ ጋር ያሳለፍኩትን ያን በእጅጉ የተሻለውን ሌሊት ነበር፡፡ እሱ እንደዚያ እየጮኸ ደስታውን ሲገልፅ ሳይና ደስታውን ልጋራው አለመቻሌን ስገነዘብ፤ ያውቅብኛል ብዬ ስለፈራሁ የውሸት ድምፅ እያወጣሁና ውስጤ አድማሱን ሳይሆን አማረን እንዳቀፍኩ ያህል እንዲሰማው ዓይኔን ጨፍኜ ለማሳመን ሞከርኩ። ባይሳካልኝም በተወሰነ መልኩ ደስታውን የጋራ ለማድረግ ጣርኩ፡፡ ሁሉም ነገር ካለቀ በኋላ ግን ለምን እንዲህ ሊሆን ቻለ? ስል ራሴን ጠየቅሁ :: ለምን ገላዬን ብቻ ሰጠሁት? ለምን ሁለመናዬን ልሰጠው አልቻልኩም? ምነው ደስታን እየሰጠሁት ደስታን መቀበል ተሳነኝ? እሱም አድማሱም እንደአማረ ለወንድ ልጅ የተሰጠውን ጾታዊ ፀጋ የተላበስ ሆኖ ሳለ ለእኔ ግን ለምን ከእሱ አንሶ ታየኝ? የሚሉት ጥያቄዎች ተመላለሱብኝ እንጂ ትዝታው ከእኔ ጋር ሊቀር አልቻለም፡፡"

ሠራተኛዬ ጋሼ ብላ ስትጠራኝ ከገባሁበት የሐሳብ ባህር ተስፈንጥሬ ወጣሁ። የሚገርመው ነገር መንቃቴን እንጂ ሠራተኛዬ እንደቀሰቀሰችኝ አላወቅሁም ነበር፡፡ ከፊት ለፊቴ ቀጥ ብላ ቆማ በመገረም ዓይን ትኩር ብላ ትመለከተኛለች፡፡ “ምነው?'' አልኳት በንዴት፡፡ “ምነው ደህና አይደሉም እንዴ? እረባክዎትን ሀኪም ቤት ይሂዱ:: ደግሞም ከሥራ ከቀሩ ይኸው ዛሬ ሁለተኛ ቀኖት ነው፡፡ የሆኑ ሰውዬ ከመሥሪያ ቤትም ደውለው ደህንነቶን ጠይቀውኝ ነበር፡፡ እኔም የምመልሰው ሳጣ ዘመድ ጥየቃ ወደ ገጠር ሄደዋል አልኳቸው፡፡ እሳቸው ግን! "የምን ገጠር ነው የምታወሪው? የሱ ዘመዶች በሙሉ አዲስ አበባ አይደሉ እንዴ ያሉት?'' ብለው ጮሁብኝ፣ "አይ እንግዲያው በደንብ ሳልሰማ ቀርቼ ይሆናል፣ ምናልባት ጓደኛዪ ጋ ብለውኝ ይሆናል" ብዬ እየፈራሁ መለስኩላቸው፣ "ከደወሉ ወንድወሰን ደውልልኝ ብሎሃል ብዬ እንድነግሮትም ነግረውኛል" እያለች የባጥ የቆጡን መቀባጠሩን ተያያዘችው:: መቼም እሷና ሬዲዮ አንዴ ወሬ ከጀመሩ ካልዘጓቸው በስተቀር አያቆሙም፡፡ ነገር ግን ምን ታድርግ ሁኔታዬ እንኳን ለእሷ ለእኔም ግራ የሚያጋባ ሆኗል፡፡ ግራ መጋባቷን ሳይ አዘንኩላት:: አልፎ አልፎ አብረን በምናሳልፋቸው ሌሊቶች የምትፍለቀለቅባቸውና የምትደሰትባቸው ወቅቶች ነበሩ:: አሁን ግን ፍቅረኛዋ እሷን ዘንግቶ ሌሊቱን በፍቅር ሳይሆን በማያቋርጥ ንባብና ትካዜ ሲያሳልፈው ስታይ እንዴት ግራ አትጋባ፣ እንዴትስ ጤነኛ ነው ብላ ታስብ፡፡ እርግጥ ነው ጤነኛ አልነበርኩም፡፡ ራሴን የሚያዞር ማለቂያ የሌለው ታሪክ ከእንቅልፍ ማጣት ጋር ተደምሮ ጩህ ጩህ ሊያሰኘኝ እየቃጣው ነው:: በዚህ ላይ ደግሞ የማነበው የሚያጓጓና የሚያስደስት ታሪክ ሳይሆን የሀዘንና የመርዶ ዜና ነበር፡፡ እርግጥ ከዚህ በላይ ምን መርዶ ይኖራል? “እጅግ ለምትወደው" ፍቅረኛዋ ለአንድ ቀን ሳትወድ በግድ በሰጠችው ገላ የምትፀፀት ሴት፣ ዛሬ ደግሞ በፍላጎቷ ለማትወደው ሰው የምወደውንና የማፈቅረውን ገላ በስጦታ ገፀ በረከት ካቀረበች በኋላ "ደስታ አጣሁበት" እያለች ስትደሰኩርና እኔን ብቻ ገላዋ እንደናፈቀ አድርጋ ስታወራ ከመስማት የበለጠ ምን የሚያናድድ መርዶ አለ:: ግን ዜናው የመርዶ መሆኑን ባውቅም ልተወው
👍313👏2
አቅም አልነበረኝምና ሳልወድ በግድ ንባቤን ለመቀጠል ወሰንኩ:: መጨረሻውን ማወቅ ስለነበረብኝ ዲያሪውን መሬት ላይ ወድቆ አገኘሁት:: የተኛሁት ልብሴንም ሆነ ጫማዬን ሳላወልቅ ነበር። ያነበብኩትን የመጨረሻ ታሪክል ላስታውሰው ባልፈልግም ራስ ምታት ጥሎብኝ እንደሄደ ግን አልረሳሁትም:: የከሀዲዋ ፍቅረኛዬ የክህደት ታሪክ አሁን የተፈፀመ ያህል ሊያሳብደኝ ደርሷል:: ንባቤን ትቼ ወደ ሥራ መሄድ እንዳለብኝ ቢሰማኝም ጨክኜ መሄድ ግን አልቻልኩም :: ሥራ ልግባ ብልም ቀኑን በሙሉ ይህንኑ ሳብሰለስል እንጂ ሥራ ስርቼ እንደማልመጣ እርግጠኛ ነበርኩ።

ሰኔ 26 ቀን 1978 ዓ.ም

የትምህርት ቤቱን ግቢ ለቅቂ የምወጣበት ቀን በመድረሱ የተደበላለቀ ስሜት ወረረኝ። በአንድ በኩል በደስታ ያልተጠናቀቀው ታሪኬ የሚጠናቀቅበት ቀን በመሆኑና እነዚያን ባየኋቸው ቁጥር አማረን የሚያስታውሱኝን የፍቅር መንገዶችና ለምለም ሳሮች ዳግም ላላያቸው የምሰናበትበት ቀን በመሆኑ ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳን እያፈቀረኝ ላፈቅረው ባልችልም የምወደውን ዶ/ር አድማሱን ጥዬው ስለምሄድና ወደ ብቸኝነት ባህር ተመልሼ እንደምገባ ሳስታውስ ደግሞ ሀዘን ይሰፍንብኛል፡፡ ግን ምን ላድርግ? ልወደው ሞከርኩ፣ ያለኝንም ልሰጠው ፈቀድኩ፣ ግን አልሆነም :: እኔ ለእሱ፣ እሱ ለእኔ የተፈጠርን አልነበርንም:: ስለዚህ ዳግም ዓይኑን ሳላይ ግቢውን ለቅቄ ለመውጣት ተጣደፍኩ፡፡ ይሁን እንጂ ነገሮች ሁሉ እንዳሰብኳቸው በቶሎ የሚቋጩ አልነበሩም:: ዩንቨርስቲው ያመጣሁትን ውጤት መሰረት በማድረግ እዚያው ቀርቼ ለድህረ ምረቃ (ማስትሬት) እንድማርና በትርፍ ጊዜዬ በረዳት ሌክቸረርነት እንድሰራ ጠየቀኝ:: እኔ ግን ይህንን ለመቀበል ዝግጁ ባልሆንም ዶ/ር አድማሱ ግን በዚህ ዕድል መጠቀም እንዳለብኝ ይገፋፋኝ ጀመር:: እየደጋገመም ሁሌ የሚለውን፣ችግሮችን በመጋፈጥ እንጂ በመሸሽ ማምለጥ እንደማይቻል ይነግረኛል:: የሚሸሽን ማባረር ይቀላል፤ ነገር ግን ደፍሮና ዓይኑን አፍጦ የመጣን ችግር ወይም ተመሳሳይ መሰናክል ጀግና ካልሆኑ በስተቀር መጋፈጥ ያስፈራል:: ችግርም ፈሪን ይደፍራል፤ የሚጋፈጠውን ግን ይሸሻል፡፡ ስለዚህ ገና ለገና ያለፈውን አስቸጋሪ ጊዜ እያስታወስኩ ከፊቴ የመጣውን ብሩህ ዕድል እንዳላበላሽው እየደጋገመ ይመክረኛል፡፡ ለሚመጣው ችግር ከጎኔ እንደማይለይ እየገለፀ እዚሁ እንድቀር ይጎተጉተኝ ጀመር፡፡ ምንም እንኳን እዚህ መቆየት እንደማልፈልግ ብነግረውም ሁለት ዓመታትን ታግሼ የማስትሬት ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ ግቢውን ለቅቄ ልሄድ እንደምችል እየነገረ ሊያግባባኝ ሞከረ።

ከብዙ ማሰብ፣ ማውጣትና ማውረድ በኋላ ግን ከዚህ ወጥቼ የማሳልፈውን ባዶ ህይወት በማሰብ፣ እንዲሁም በዶ/ር አድማሱና በጓደኞች ውትወታና ግፊት የተነሳ ሐሳቤን ለውጬ ትምህርቴን ለመቀጠል ወሰንኩ:: እርግጥ ነው ራሴን በትምህርት መጥመዱ ከጭንቀት ለመውጣት የተሻለ መንገድ መሆኑን ባውቅም መራቅ የፈለኩት ግን ግቢውን ነበር። በመጨረሻ ግን ዶ/ር አድማሱ ካለ ብቸኛ እንደማልሆን ገባኝ፡፡ ከትምህርትና ከሥራR ጋር ተያይዞም አንዳንድ የማሟላቸው ቅድመ ሁኔታዎች በመኖራቸው ከእናተ ጋር ወደ ቤቴ መመለስ አልቻልኩም። ያለኝ አማራጭ እናቴን ከእኛ አካባቢ ከመጣች ልጅ ጋር አያይዞ መላክ ስለነበር ከዶ/ር አድማሱ ገንዘብ ወሰድኩና እንደምመጣ ነግሬ ተሰናበትኳት፡፡ ሳልወድ በግድ በዚያ በማልወደው ግቢ ውስጥ ዳግመኛ መኖርና መማር ጀመርኩ፡፡ ከትምህርቴም ጎን ለጎን የረዳት ሌክቸረርነት ሥራዬንም ተያያዝኩት:: ሁለቱን ግራና ቀኝ ማካሄድ ከባድ ቢሆንም እንደፈለኩት ሙሉ ጊዜዬንና ትኩረቴን የሚወስድ ስለነበር ለጭንቀት የማጠፋውን ጊዜ አስወግዶልኛል፣ በዚህም ደስተኛ ሆንኩ:: በረዳት ሌክቸረርነት የምሰራው ተማሪዎችን በሙከራ ሥራዎች ላይ ማገዝ ስለነበር የሚከብድ ሥራም አልነበረም። ከዚህ በላይ ደግሞ ብቸኝነቴን ለማባረር ስል ከዶ/ር አድማሱ ጋር የነበረኝን ግንኙነት ይበልጥ አጠናከርኩት፡፡ ከትምህርትና ከሥራ መልስ በኋላ አዳሬ በተሰጠኝ ቤት ውስጥ ሳይሆን ከዶ/ር አድማሱ ጋር ሆነ:: ሊያገባኝ እንደሚፈልግ እየደጋገመ ቢነግረኝም መጀመሪያ ትምህርቴን መጨረስ እንዳለብኝ ስለነገርኩትና እሱም ስለአመነበት ሊያስገድደኝ አልፈለገም፡፡ ለስሙ ነው እንጂ አዳሬ ከእሱው ቤት በመሆኑ አኳኋናችን ሁሉ ትዳር እንደመያዝ ያህል ነው:: እወቁልኝ ባይባልም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ የሚያየን ልክ እንደባልና ሚስት ነበር: በምረቃው ዕለት የተጀመረው የፍቅር ጨዋታም የዘወትር ተግባር እየሆነ መጥቷል፡፡ አንዳንዴ ይህንን ሁኔታ ሳስብ ሳትወድ በግድ ወደአላሰበችው ወጥመድ ውስጥ የገባች ፍጡር የሆንኩ ያህል ይሰማኛል:: በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ ይበልጥ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ራሴን አሳልፌ ልሰጠው ዝግጁ ብሆንም የሚወደኝን ዶ/ር አድማሱን ግን መውደድ አለመቻሌ ነው:: አንዳንዴም ፍቅር የሚይዘው አንዴ ብቻ ሊሆን ይችላል ብዬ ስለማስብ ከእንግዲህ ወዲህ ወንድ አልወድ ይሆን? እያልኩ እሰጋለሁ፡፡ መሥጋቴ ግን ተገቢ ይመስለኛል፣ በፍቅርና ከፍቅር ውጪ ያለውን ሕይወቴን ሳወዳደር ፍቅር የሕይወት ቅመም ነው የሚባለው እውነት

መሆኑን አረጋግጫለሁና:: ታዲያ ወጥ ያለ ቅመም እንደማይጣፍጥ ሁሉ ሕይወት ያለ ፍቅር ባዶ ናትና መፍራቴ የሚደንቅ አልነበረም:: ዶ/ር አድማሱ ለእኔ ያለው ፍቅር ወደር የለውም። ከሥራ እንደወጣ የሚመጣው በቀጥታ ወደ ቤት ነው:: ጥናት እያስጠናኝ እንኳን በየመሀሉ ጉንጩን እየሳመ እየደጋገመ እወድሻለሁ ይለኛል:: ደግነቱ ፍቅሩ የእኔን ጥናት የሚረብሽ አልነበረም:: ዘወትር እንደሚወደኝና ትምህርቴን ስጨርስ ተጋብተን ልጅ ወልደን በደስታ እንደምንኖር! እኔም ትምህርቴን ሳጠናቅቅ እሱ ሥራ ለውጦ አዲስ አበባ እንደሚገባ፣ እዚያም እኔና እሱ የተሻለ ኑሮ እንደምንኖርና ከዚህ ከማልወደው ግቢም በዚህ መልኩ እንደምገላገል ይነግረኛል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ የራሱን ቤት የሠራ በመሆኑ እዚያ እንደገባም መኪና እንደሚገዛና አንደላቆ እንደሚያኖረኝ እየደጋገመ ይነግረኛል፡፡ እኔ ግን ለዚህ ሁሉ መልስ አልነበረኝም:: ለእኔ ደስታ ማለት መኪና፣ ቤት፣ ወይም ሌላ ሊሆን አይችልም፣ የእኔ ደስታ ከአማረ ጋር አክትሟል።" ዲያሪውን እያነበብኩ አንዳንዴ ሳቄ ይመጣል፡፡ ሌላ ግዜ ደግሞ በውኔ ሳይሆን በህልሜ ያማየው ይመስለኛል:: አልማዝ በዲያሪዋ ላይ መዋሸትዋን ቀጥላለች፣ እኔን የጨነቀኝ ግን ሌላ ሳይሆን ይህቺ ሰው በህይወት ትኖር ይሆን? ወይስ እንደዋሸች ሞታ ይሆን? የሚለው ነው:: ብዙ ውሸቶችን ባነበብኩ ቁጥር በዲያሪው ውስጥ መሞቷን ባነብ እንኳ ሌላ ውሸት ነው ብዬ አስብ እንደሆን እንጂ፣ በእውነትም ሞታለች ብዬ ለመቀበል ሳያስቸግረኝ አይቀርም። አባቴ የሚዋሽ ሰው አይወድም ነበር፡፡ ምንም ያህል መጥፎ ሥራ ብሰራ ያን ድርጊት መፈፀሜን ካመንኩ ንክች አያደርገኝም፡፡ አንዴ ትዝ ይለኛል አንድ አዲስ ቤት እየሰራ ስለነበር እኔም ከአናጢውና ከግንበኛው ጋር አብሬ ስሰራ እውል ነበር፡፡ የሚያወሩት ወሬ ከሴት ጋር ስላሳለፉት የፍቅር ጨዋወታ ስለነበር ወሬያቸውን መስማት ያስደስተኝ ነበር፡፡ አንድ ቀን ታዲያ እዚሁ አዲስ ቤት ውስጥ ከጓደኞቼ ጋር ሆኜ በሳንቲም "ዘውድ “ጎፈር" እያልን ድብድብ ስንጫወት አባቴ ይመጣል:: ወደ ቤት ስንገባ አይቶን ስለነበር ቢጣራና በሩን ለመክፈት ቢሞክርም መልስ ስላጣ በመስኮት ብቅ ብሎ፤ “እናንተ! ብላችሁ ብላችሁ ቁማር ትጫወቱ ጀመር?" ብሎ ሲጮህብን፣ ያታለልኩት መስሎኝ፤ “አይ አባዬ ቁማር እየተጫወትን አይደለም፣
👍213
ለስፖርት ገንዘብ እያዋጣን ነው" ስላልኩት በሩን አስከፈተኝና፣

“የምትጠፈጥፈውን እያየሁት ትዋሽኛለህ" ብሎ ቀበቶውን ፈትቶ የገረፈኝ አይረሳኝም:: ከዚያ በኋላ ውሸት የሚባል ነገርን ሞክሬው አላውቅም:: ስለዚህም ራሴ ከመዋሸት መቆጠብ ብቻ ሳይሆን ሌላውም ሲዋሽ ካየሁ ለእሱ የነበረኝ ክብርና ፍቅር ይቀንሳል፡፡ ታዲያ እነሆ እንደዚያ የማፈቅራት! የምወዳትና የማከብራት አልማዝ ከምጠብቀውና ከማስበው ውጪ ዲያሪዋን በቅጥፈት ሞልታው ሳይ ለእሷ ያለኝ ፍቅርና ክብር ቢቀንስም መጨረሻውን ሳላውቅ ማቆም ስለማልችል ሳልወድ በግድ እየቀፈፈኝም ቢሆን ማንበቤን ቀጠልኩ፡፡ TC 28 43 1980 99 "የሁለተኛ ዓመት የድህረ ምረቃ ትምህርቴን ለማጠናቀቅ ፕሮጄክቴን እየሠራሁ ሳለ በመሀሉ አባቴ በጠና በመታመሙ የተነሳ ቶሎ እንድደርስ ተጠርቼ ወደ ሀገር ቤት ሄድኩ፡፡ እጅግ ከመክሳቱ የተነሳ ተኝቶ እያለ አልጋው ላይ ሰው የተኛበት አይመስልም ነበር፡፡ ሰውነቱ ገርጥቶ በጠና መታመሙ በግልፅ ይታይ ነበር። “ጎሽ ልጄ መጣሽ፣ ሳላገኝሽ ልሞት ነው ብዬ ፈርቼ ነበር!” ብሎ ተጨማሪ ቃላት ለመናገር አፉን ለመክፈት ቢሞክርም፣ ከንፈሩን የሚያላቅቅበት ሀይል እንኳ ስላልነበረው አፉን እንደከፈተው ቀረ፡፡ ጉንጮቹም ከመክሳታቸው የተነሳ አፉ ውስጥ የተጣበቁ መስለዋል፡፡ እንደዚያም ሆኖ እኔን ለመሳም ቀና ብሎ ቁጭ ለማለት ሲሞክር ፍጥነቱን ላየ የታመመ አይመስልም ነበር፡፡ እናቴ ራሷ እንዲህ ፈጠን ብሎ ሲነሳ በማየቷ ተገርማለች፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ጉንጬን ስሞ ሁለተኛውን ሳይደግም ወገቡን ይዞ እያቃስተ ጋደም አለ፡፡ እኔም ጎንበስ ብዬ የጀመረውን እንዲጨርሰው ያልተሳመውን ጉንጩን ሰጠሁት፡፡ አባቴ በጠና የታመመው ከህክምና እጦት ነው ብዬ በመገመቴ አሁን ደርሼለታለሁና አድነዋለው ብዬ ገመትኩ፡፡ ከብቶቻችን ሁሉ በድርቅ ምክንያት በማለቃቸውና አባቴም እንደ ድሮው እያረሰና እህል እያመረተ ማስገባቱን ትቶ ሌሎች በውል ካረሱለት ላይ በክፍያ ድርሻ ይኖራል፡፡ ባጠቃላይ በቤተሰቦቼ ላይ ድህነት ጎጆ ቀይሶባቸዋል:: ለመታከሚያ የሚሆን ገንዘብ ስላልነበረው ከጠበል ውጪ ያደረገው ህክምና አልነበረም:: ይሁን እንጂ የእኔን መድረስ እንደጥሩ አጋጣሚ ቆጥሬ አድነዋለሁ ብዬ ተፅናናሁ፡፡ እሱን አሳክሜ ማዳን የመጀመሪያ ተግባሬ ለማድረግ ወሰንኩ፡፡ አባቴ መልካም ሰው በመሆኑ ለዚህ ጊዜ የሚሆኑ የቅርብ ወዳጆች ነበሩት፡፡ በመሆኑም ከቤት በተገኘው ገንዘብ ላይ እኔና እናቴ በብድር ያገኘውን ጨመርንበትና ውዬ ሳላድር ወደ አዲስ

አበባ ይዤው በረርኩ፡፡ ይሁን እንጂ ሳይታከም ብዙ ጊዜ በመቆየቱና ጉበቱም በጣም በመጎዳቱ ሙሉ በሙሉ መዳን እንደማይችል በተከታታይ በተደረገለት ሳምንት የፈጀ ምርመራ ተረጋገጠ። አዲስ አበባ መቆየት ምንም ሊጠቅመው የሚችል ነገር ስላልሆነ ገንዘቤን አላግባብ ከማባክን ይልቅ የታዘዘውን መድኃኒት ገዝቼለት ወደ ቤት ይዤው እንድሄድና በሽታው እንክብካቤ የሚፈልግ በመሆኑ ጥሩጥሩ ምግብ እየመገብን እንድንከባከበው ሀኪon ነገረኝ:: አማራጭ ስላልነበረኝ እያለቀስኩ ወደ ሀገር ቤት ይዤው ተመለስኩ:: ያንን ሁሉ ውለታ ውሎ እዚህ ያደረሰኝ አባቴ አሁን ጥሩ ደረጃ በደረስኩበት ሰዓት ቢሞት እጅግ በጣም ማዘኔ ስለማይቀር በተቻለኝ መጠን እሱን ተንከባክቤ ለማዳን ጣርኩ። ይሁን እንጂ ከቀን ወደ ቀን ህመሙ ይበልጥ እየጠናበት መጣ:: እኔ ግን ይሻለዋል ብዬ ስለማስብ ተስፋ አልቆረጥኩም ነበር። አንድ ቀን ማታ አባቴ ጠራኝና ሊነግረኝ የሚፈልገው አንድ ጉዳይ ስላለ እንዳዳምጠው፤ ነገር ግን እንደማልቀየመው ቃል እንድገባለት ጠየቀኝ። እኔም ይህንን ሲለኝ ከዚህ በፊት ወላጆቼ አነማን እንደሆኑ በጠየቅኋቸው ጊዜ እንዳይቀየሙኝ በቅድሚያ ቃል ያስገባኋቸው ትዝ አለኝ፡፡ ዛሬ ደግሞ አባቴ በተራው እኔንም ተመሳሳይ ጥያቄ ሲጠይቀኝ ደነገጥኩ፡፡ የያኔው የእኔ ጥያቄ የእነሱን የወላጅነት ቅስም ሰብሮ አልፎል፡፡ ዛሬ ደግሞ ይኸኛው ጥያቄ ምን ሊያስከትል እንደሚችል መገመት ማን ይችላል? ግን በዚህ የመጨረሻ ሰዓት ላይ ምንም ቢናገር ልቀየመው እንደማልችል እርግጠኛ ስለነበርኩ፣ እጅግ በጣም እንደምወደውና የፈለገውን የሚያስቀይም ነገር ቢነግረኝ እንኳን እንደማልቀየመው ቃል ገባሁለት:: አባቴ በዚህ ተበረታትቶ ንግግሩን በዝግታ ጀመረ። “ይኸውልሽ ልጄ፤ ያቺን አሰለፉን ማለትም ያቺን ሠራተኛ የነበረችውን ታስታውሻታለሽ?" ብሎ ሲጀምር እንባው ቀደመውና መናገር ስላቃተው ዝም አለ፡፡ እንባው ግን መፍሰሱን ቀጠለ፡፡ እኔም የእሱን እንባ በማየቴ እምባዬ መፍሰስ ጀመረ። እሷ ከሞተች ጀምሮ አባቴ በሀዘን ተጎሳቅሏል፡፡ እኔም ብሆን እጅግ በጣም እወዳት ስለነበር ለክረምት እረፍት መጥቼ ሳለ መርዶዋን ሲነግሩኝ ክፉኛ እዝኛአለሁ:: እሷም ብትሆን ከእነሱ ባልተናነሰ ሁኔታ ተንከባክባ ያሳደገቺኝ በመሆኗና የእኔ ነገሮች ሁሉ ከምንም ነገር በላይ የሚበልጡባት ስለነበረች ሀዘኔ ከባድ ነበር:: በተመቻት ጊዜ ሁሉ ከአካባቢው ሳንርቅ ሽርሽር ይዛኝ ትወጣና ልክ እንደ ልጅ ሆና ከእኔ ጋር አንዴ ሌባና ፖሊስ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ድምቡሼ ገላ እንጫወታለን:: የተሸነፈ አዝሎ ማዞር ስላለበት አውቃ እየተሸነፈች አዝላ ታዞረኛለች:: ታዲያ ምን ግዜም ቢሆን ትዝ የሚለኝ ከቤት ወጣ እንዳልን ጉንጮቼን በተደጋጋሚ ምጥጥ አድርጋ ትስማቸውና ዓይኖቼን ትኩር ብላ ታያቸዋለች፡፡ _ ሌላው

እስከአሁን ትዝ የሚለኝ ደግሞ አንገቴን እየሳመች የምታሸተው ጠባይዋ ነው:: አብዛኛውን ጊዜ ከእሷ ጋር እንደልባችን የምንጫወተው አልፎ አልፎ እናቴና አባቴ ወጣ ካሉ ብቻ ነበር። አግቢ ይዛኝ ስትወጣ ካዩ ደስ አይላቸውም:: በተለይ አባቱ፣ “አንቺ ሴትዮ ልጂቷን ውጪ አታውጪ ስትባዪ አትሰሚም፤ ልታባልጊያት ነው፣ በኋላ ግን አንድ ነገር ብሰማ የመጨረሻሽ ይሆናል በማለት ብዙ ጊዜ ይቆጣት ነበር፡፡ አንዳንዴም በዚሁ የተነሳ ጥፊ ትቀምሳለች:: ይሁን እንጂ እነሱ ወጣ ካሉ የመጣው ቢመጣ ከእኔ ጋር መላፋቷና መጫወቷ አይቀርም ነበር:: ምንግዜም ገላዬን ስታጥበኝ በጣም ደስ ይላታል፡፡ ያለመጥገብ ሰውነቴን እየደጋገመች ትስመዋለች:: ነገሩ ባይገባኝም አገላብጣ ስማኝ እንኳ አትረካም ነበር፡፡ ደግነቱ ሴት ነች እንጂ ወንድ ብትሆንማ ኖሮ አሁን የምረዳው በሌላ መልኩ መሆኑ የማይቀር ነበር:: ታዲያ ትዝ የሚለኝና ሁሌም የምጠይቃት፤ እኔና እሷ እደጅ ስንወጣ ለምን እማማና አባባ እንደሚቆጡ ነበር፡፡ "ቆይ ስታድጊ እነግርሻለሁ" ትለኝ ነበር፡፡ እሷ ያንን እነግርሻለሁ እያለች ያዳፈነችውን ጉዳይ ሳትነግረኝ ብትሞትም እኔ ግን ያወቅሁት እጅግ ኖሬ ኖሬ ነበር፡፡ እደጅ ከወጣሁ ሰዎች የእነሱ ልጅ እንዳልሆንኩ ሊነግሯት ይችላሉ ብሎ አባቴ ስለሚፈራ፣ እኔ እደጅ ስወጣ ደስ አይለውም ነበር:: ትምህርት ቤት እንኳ ወይ እናቴ አሊያም አባቴ ያደርሱኛል እንጂ ከእሷም ሆነ ከሰፈር ልጆች ጋር እንድሄድ አይፈቀድልኝም ነበር:: ትምህርት ቤቴም ራቅ ያለ ስለነበር የምሄደውና የምመጣው በበቅሎ ነበር። አንዳንዴ ለምን እዚህ ቅርብ ካለው ትምህርት ቤት አልገባም ብዬ ስጠይቅ፤ “የዚህ ሰፈር ልጆች ባለጌ ስለሆኑ ያባልጉሻል የሚል ነበር" ከዚህ በላይ ደግሞ በዚሁ ምክንያት የተነሳ ከሰፈር ልጆች ጓደኛ እንዲኖረኝ አይፈቀድልኝም ነበር። ይሁን እንጂ እንደፍርሀታቸው እና ስጋታቸው ብዛት ታሪኩ ተደብቆ መቅረት አልቻለም፡፡ እርግጥ በስተርጅና ያገኙኝ ልጃቸው ስለሆንኩ እውነተኛ ወላጆቼ አለመሆናቸውን ማወቄ ምን ያህል ሊጎዳቸው እንደሚችል በደንብ ይገባኛል:: ሌላው ቀርቶ ተለይቼያቸው ዩንቨርስቲ
👍282👏1😁1
ከገባሁ በኋላ በየክረምቱ ስመጣ ይበልጥ አርጅተውና ተጎሳቅለው ነበር የማገኛቸው። የእኔ ከእነሱ መራቅ የእነሱን ደስታ ያጠፋዋል:: እንዳሉትም _ ኩራዛቸው ባልጠፋም ብርሀኔ ግን ደብዝዞባቸዋል:: ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ወላጆቼ አለመሆናቸውን በማወቄ የተነሳ የምከዳቸው መስሎ ስለሚሰማቸው የብቸኝነትና የፍርሀት ስሜት አጥልቶባቸዋል፡፡ እኔ ግን እስከመቼም ቢሆን አሉኝ የምላቸው ብቸኛ አለኝታዎቼ በመሆናቸው ለእነሱ ያለኝ ፍቅር ቅንጣት

ያሀል አልቀነሰም:: ሁሌም የማስብላቸውና ኑሯቸው በደንብ ተለውጦና አልፎላቸው ላላይ እንዳይሞቱብኝ ዘወትር እፀልይ ነበር። ግን አልሆነም፤ አባቴ የሠራተኛዋን ስም ሲጠራ እሱም ሊከተላት እንደሆነ ስለገባኝ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም:: ውለታውን ሳልመልስ ለሞትብኝ መሆኑን ሳስብ እንባዬ እንደ ጎርፍ መውረድ ጀመረ:: ሕይወቱን የማቆየት ስልጣን ያለው ይመስል እግሩን እያሻሸሁ እንዳይሞትብኝ ተማጸንኩት:: ሞትን አሱ ይቆጣጠረው ይመስል ዛሬ እሱን ለመርዳት አቅም ባለኝ ጊዜ ውለታውን መልሼ ጤነኛና ደስተኛ ሆኖ ሳላየው እንዳይሞትብኝ ወተወትኩ። አባቴ ግን ነፍሱ ሳትወጣ ሊነግረኝ የሚፈልገው ነገር መኖሩን እየነገረኝ ዝም እንድል ለመነኝ:: እኔም ጥሩ ነገር ይሆናል ብዬ ገምቼ ስለነበር እንባዬን እንደምንም ቋጥሬ እጅግ መራራ ቃላቱን አዳመጥኩት፡፡ መቼም ቢሆን ልገልጸው ከምችለው በላይ አዘንኩ፡፡ ማንን እንደማምን ግራ ገባኝ፡፡ ያም ሆነ ይህ ያላሰብኩት ነገር ሆነ፡፡ ከዚያን በኋላ እንባዬን ቋጥሬ ማቆም ስለተሳነኝ እንባዬ በጉንጮቼ ላይ ጎረፈ፡፡ የገባሁለትን ቃል መጠበቅ አልቻልኩም፡፡ ይህንን አስምሎ ከሚነግረኝ ሳይነግረኝ ቢሞት እጅግ የተሻለ ነበር:: አሁን መንገሩ ምን እንደሚፈይድ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ በዚህም የተነሳ አባቴን ከልቤ ተቀየምኩት፣ ጠላሁትም፡፡ ከዚያ በኋላ አምላክን የለመንኩት አባቴ እንዳይሞት ሳይሆን ቶሎ እንዲገላገል ነበር፡፡ ፈጣሪ ልመናዬን ከመቅጽበት የሰማ ይመስል ከአባቴ ፊት ርቄ ለማልቀስ እግሬ ገና ከቤት ወጣ ከማለቱ አባቴ ላይመለስ አሸለበ:: ይህንንም ያወቅሁት እናቴ ስትጮህ እንጂ ዞር ብዬ ለማየት እንኳ የሚራራ ልብ አልነበረኝም:: ነገር ግን እናቴ ብቻዋን ስታለቅስ ጨክኜ መሄድ ባለመቻሌ ተመልሼ ማልቀስ ጀመርኩ:: ለቅሶዬ ግን ድርብ ነበር፡፡ ይኸውም እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ከሠራተኛው እንደወለደኝ ሊነግረኝ ላልደፈረው ወላጅ አባቴና ስታድጊ እነግርሻለሁ እንዳለች ሁሉንም በውስጧ አፍና ሳትነግረኝ ለሞተችው ወላጅ እናቴ ለአሰለፉ ነበር። ከአባቴ ቀብር በኋላ እናቴንም በአባቴ ዓይን እያየኋት እሷንም እንደሱ በጥላቻ ዓይን እመስከታት ጀመር፡፡ እርግጥ እሷም ብትሆን ሚስጥሩን ልትነግረኝ ትችል ነበር። ነገር ግን ትንሽ ቆየት ብዬ ሳስብ ለእሷም አዘንኩላት:: ባሏ በእሷ ላይ፤ ያውም ከሠራተኛዋ፣ ልጅ ወለደባት፡፡ በዚህም ተቀይማ ተለይታው መኖር ባለመቻሏ ሁኔታውን ችላና ተቀብላ ኖረች፡፡ እውነቱን ደብቀው እና መኖሪያ ለውጠው የጋራ ወላጆች ለመምሰል ሞከሩ፡፡ ጉዳዩ እየቆየ ሲሄድም የራሳቸው ውሸት እነሱንም ማወክ በመጀመሩ የአብራካችን ክፋይ ናት እኛም እውነተኛ እናትና አባቷ ነን ብለው እስከማመን ደረሱ:: እናቴ በአባቴ የበላይነትና በአምነሽ ተቀበይ ሐሳብ

ተዋጠች፡፡ በእዚህ ላይ የእኔ ፍቅር ተጨምሮበት በዚህ ጉዳይ ማንም ጣልቃ እንዳይገባ ማድረግ ነበረባቸው:: አሳዳጊ እናቴም ዲቃላዋን ልጅ ልጄ ናት ብላ አምና ተቀብላ ልክ እንደልጇ አሳደገችኝ፡፡ ወላጅ እናቴ አሰለፈችም ብትሆን ልትነግረኝ የፈለገችውን የእሷን ወላጅነት ለመንገር የሕሊና አቅምና ድፍረት ስላልነበራት ጉዳዩን ሳትነግረኝ የእነሱን ውሸት እውነት ነው ብላ መቀበል ስለነበረባት እውነቱን በውስጧ አምቃና ቀብራ ለዘላለም አለፈች፡፡ ለካስ ድህነት ገንዘብን ብቻ ሳይሆን ከማኅጸን የተገኘ ልጅንም ያሳጣ ነበር። ያም ሆነ ይህ ለአሳዳጊ እናቴ የነበረኝን የድሮ የልጅነት ፍቅሬን እንዲመልስልኝ አምላኬን ደጋግሜ ለመንኩት፡፡ ግን ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጌ ልተወው ስል የወላጅ እናቴ ነገርና እሷን ለማወቅ ምን ያህል እጓጓ እንደነበር እያወቁ ሳይነግሩኝ መቅረታቸውን ሳስብ ደግሞ፤ ንዴትና ጥላቻ ያገረሽብኛል:: በተዘበራረቀ ዓለም ውስጥ ገብቼ ዙሪያዬ በሙሉ ገደል ሆነብኝ :: ከአሁን ወዲያስ ልማርበትና አስተማሪ የሚነግረኝን ልረዳበት የምችል ንፁህ ትርፍ አእምሮ ይኖረኝ ይሆን? ብዬ ተጠራጠርኩ፡፡ የትምህርት ግዜዬን እያባከንኩት ቢሆንም በሁኔታው ላይ ግን ለመወሰን ሳልችል ቀረሁ፡፡ ልማር ወይስ ልተወውና ሥራ ልፈልግ? ብማርስ ከእንግዲህ ምን ለማግኘት ነው? ያገኘሁትንስ ባገኝ ከእንግዲህ ደስታ ይኖረኛል? ወዘተ... የሚሉ ጥያቄዎችና ተስፋ የመቁረጥ ስሜቶች ያንዣብቡብኝ ጀመር።

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍405
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_11

የካቲት 7 ቀን 1980 ዓ.ም "ዶ/ር አድማሱ በመሃሉ የአባቴን መሞት በመስማቱ ሀዘን ለመድረስ መጣ፡፡ ቤቴን ሰለማያውቀውና ይመጣል ብዬ ጠብቄ ስላልነበር ሳየው ደነገጥሁ፡፡ ነገር ግን እጅግ በሚያስፈልገኝ ሰዓት በመምጣቱ ቢያንስ ጭንቀቴን የማካፍለው ሰው በማግኘቴ ደስ አለኝ፡፡ እንዴት ቤቴን ሊያውቀው እንደቻለ ጠይቄው ከአካባቢያችን ተማሪዎች አድራሻዬን ጠይቆ እንደመጣ ነገረኝ፡፡ እሱ ከመጣ በኋላ የመረጋጋት ስሜት ሰፈነብኝ፡፡ ቤታችን ለእሱ ዓይነት የከተማ ሰው ያውም ለዶ/ር ማደሪያነት የሚመች ስላልነበር በነጋታው እንዲሄድ ብወተውተውም እኔን ሳይዝ እንደማይሄድ ቁርጡን ነገረኝ:: አማራጭ ስላልነበረኝ ለራሴ አውጥቼና አውርጄ አንድ ነገር መወሰን ነበረብኝና ወስንኩ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ የቀረኝ አንድ የቅርብ ወዳጅ እሱ ስለነበር ተከትዬው ከመሄድ የተሻለ አማራጭ ስላልነበር ከእሱ ጋር ለመሄድ ወሰንኩ፡፡ እናቴ ሁለት ነገር _ አጥታለች፡፡ በአንድ በኩል ለአርባ ዓመታት አብሯት የኖረውን የትዳር ጓደኛዋ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በእኔ ላይ በፈጸሙት ሚስጥር የመሰወር ድርጊት የተነሳ የእኔም ፍቅር ቀንሶባታል፡፡ ስለዚህም ይመስላል ተሰናብቼያት ልወጣ ስል የሞትኩ ያህል ለቅሶዋን

የለቀቀችው፡፡ እናትና አባቴ ሁሉንም ነገር ያደረጉት ለእኔ ካላቸው ፍቅር የተነሳ በመሆኑና አሁን ግን በዚህ ሁኔታ አኩርፌያት ከሄድኩ እሷም አንድ ነገር ትሆናለች በማለት የኋላ ኋላም በዚሁ መንስኤ ክፉኛ ልፀፀት እንደምችል ዶ/ር አድማሱ ስላሳመነኝ ላረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ነገር ግን እንደአልተቀየምኳትና አሁንም እንደምወዳት ብነግራትም ከልቧ አላመነችኝም፡፡ አለቃቀሷንም ሳየው በዚህ ሁኔታ ዝም ብያት ብሄድ ተመልሼ እንደማላገኛት ስለተረዳሁ ዶ/ር አድማሱን ሸኝቼ ለተወሰነ ጊዜያት አብሬት ለመቆየት ወሰንኩ፡፡ በእናቴ ገጽታ ላይ የነበረው የመከፋት ስሜት ከፈቷ ላይ እየጠፋና በቦታውም ፈገግታ እየተተካ ሲሄድ በማየቴ በመቅረቴ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆነች በመገንዘቤ በጣም ደስ አለኝ::" የካቲት 8 ቀን 1980 ዓ.ም "አመሻሽ ላይ ያቀጣጠልነው የከሰል ፍም ተንደርኳል፡፡ ፍሙን እየሞቅን ከእናቴ ጋር ግራና ቀኝ ተቀምጠን ስናወራ፤ እጆቼን፣ ፀጉሬንና አንገቴን እየዳበሰች ስለአንድ ነገር ልትነግረኝ እንደፈለገች ሁኔታዋ ያስታውቃል፡፡ እኔም አንድ ልትነግረኝ የፈለገችው ነገር እንዳለ ታውቆኛል፡፡ ቀኝ እጅዋን በሁለት እጆቼ መሐል አድርጌ እያሻሽሁና አንገቴን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጌ የምትለውን ለመስማት ጆሮዬን አሹዬ መጠባበቁን ተያያዝኩት፤ "አልሚና _ እርግጥ አሁን በእኔ መቀየሙን ትተሻል? _ አሁንም እንደድሮ ትወጂኛለሽ?" አለችኝ፤ እውነቱን ለመናገር እናቴን አሁንም ብወዳትም በውስጤ ግን አንዳች የጎደለ ነገር ያለ ዓይነት ነገር _ ስለሚሰማኝ የድሮውን ዓይነት የመውደድ ስሜት አልነበረኝም፡፡ ይህንን መሳዩን ስሜት በውስጤ ደብቄ መዋሸት ደግሞ ሕሊናዬ ሊቀበለው ስላልቻለ፤ "እርግጥ አሁንም ያለሽኝ አንቺ ብቻ ስለሆንሽና ከማንኛዋም እናት ያላነሰ ፍቅር ለግሰሽ እዚህ ስላደረስሺኝ ከማንምና ከምንም በላይ አስበልጬ እወድሻለሁ፡፡ ነገር ግን እናቴን ለማወቅ ምን ያህል ስጓጓ እንደነበር እያወቃችሁ ያን ያህል ዓመታት ሳትነግሩኝ በመቅረታችሁ የተሰማኝን ቅሬታ ከውስጤ ላስወጣው ብሞክርም እምቢ ብሎ ስለአስቸገረኝ አሁንም የመቀየም ስሜት በውስጤ አለ፡፡ ግን ለምን እማዬ? ምናልባት አሰለፉ ኖራ ቢሆን ኖሮ ምንም ላይሰማኝ ይችል ነበር፡፡ እሷ ግን አሁን የለችም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሕይወት ኖራ ቢሆን ኖሮ ይኸን ግዜ ምን ያህል ደስ እንዳለኝ እላይዋ ላይ ተጠምጥሜ እየሳምኳት ልገልፅላት በቻልኩ ነበር፡፡ ሁሌ ስታድጊ እነግርሻለሁ ያለችኝንም ድብቅ ምስጢር እንዳወቅሁት በደስታ እየቦረቅሁና እየተፍለቀለቅሁ ልነግራት በቻልኩ ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ የሙሉ ሰው

ስሜት እንዳይሰማኝ በውስጤ ተደብቆ ሲያስጨንቀኝ የነበረው ተጥሎ የመገኘቴ ስሜት እንዲህ ለዚህ ሁሉ ዓመታት ሲጎዳኝ ባልኖረ ነበር። በተለይም ያቺ ምስኪን አስለፍ ከናፍቆቷና ከፍቅሯ ፅናት የተነሳ ስታገኘኝ ልትውጠኝ እየደረሰች፣ ነገር ግን ልጂ መሆኔን እንኳ ልትነግረኝ ሳትችል መሞቷን ሳስብ ሐዘኔ ከውስጤ አልወጣ ይለኛል፡፡ አትርፍጂብኝ እማዬ እነዚህ ዓይነቶቹ ስሜቶች በውስጤ ተደብቀው እንደድሮዬ እንዳልሆን እየታገሉኝ ሊሆን ይችላል እንጂ፤ አሁንም ቢሆን ከማንም ከምንም በላይ አብልጬ እወድሻለሁ፡፡ አትቀየሚኝ እማዬ! ወድጄ አይደለም" በማለት በውስጤ ያለውን እውነት ምንም ሳልደብቅ ነገርኳትና ደረቷ ላይ ተለጥፌ ልቅሶዬን ተያያዝኩት፡፡ እናቴ ከእኔው ጋር ስታለቅስና ስታባብለኝ ከቆየች በኋላ ልቅሶዬን ትቼ መረጋጋት ስጀምር፤ ፀጉሬን እያሻሸች “አልሚና እኔ መቼም ቢሆን አልቀየምሽም፡፡ ግን አንድ እንድታውቂው የምፈልገው እውነት ስላለ ዝም ብለሽ አዳምጪኝ። እንደምታውቂው እኔና አባትሽ ያው የአንድ ሐገር ልጆች ነን፡፡ በወጣትነት ዘመናችን መንዝ ውስጥ እኔ ሞላሌ፣ እሳቸው ደግሞ ላሎምድር የሚባል ቦታ እንኖር ነበር፡፡ አባትሽ ባጋጣሚ ዘመድ ለመጠየቅ ወደ እኛ ሰፈር መጥተው በነበረበት ጊዜ አይተው ወደዱኝ፡፡ በኋላም ሽማግሌ ልከው እና ቤተሰቦቼን አስፈቅደው በወግ በማዕረግ ተጋባን፡፡ ከዚያ በፊት አይቼው የማላውቀውን ሰው በማግባቴ መጀመሪያ ላይ ውስጤ እጅግ ቢከፋም አባትሽ ግን በጣም ጥሩ ሰው ስለነበሩና እጅግ በጣም ይወዱኝ ም ስለነበር ከመዋል ከማደር እኔም አፈቀርኳቸው፡፡ ለሶስት ዓመታት እዚያው መንዝ ውስጥ እንደኖርን አባትሽ አንድ አሉኝ የሚሏቸው አጎታቸው ከጅጅጋ ሊጠይቁን መጡ፡፡ ጅጅጋ ውስጥ ብዙ መሬት እንዳላቸው፣ ሀገሩም ሊነገድበትና ገንዘብ ሊፈራበት የሚችል በመሆኑና እሳቸውም ከሥጋ ዘመድ ርቆ በብቸኝነት መኖር ስለሰለቻቸው፣ ከእሳቸው ጋር ብንሄድ መሬት እንደሚሰጡንና እዛም የተሻለ ኑሮ መኖር እንደምንችል ለአባትሽ ነግረው አሳመኗቸው፡፡ እኔ ብዙም ደስባይለኝም የተወለድንበትን ቀዬ ትተንና አጎትየውን አምነን ጅጅጋ መጣን፡፡ ሰውዬው ሚስታቸው ሞተውባቸው ብቻቸውን ይኖሩ ስለነበር፤ ያለናቸው ብቸኛ ዘመድ እኛ ብቻ በመሆናችን ከእኛ ቤት አይወጡም ነበር፡፡ አባትሽንም ልጄ ነው ብለው ለየሰዎቹ ሁሉ ስለአስተዋወቋቸው አገሬው በሙሉ የሚያውቃቸው የሳቸው ልጅ አድርጎ ነበር፡፡ ሰውዬው ሲሞቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ለእኛ አወረሱን፡፡ እንዳሉትም እዚህ የተሻለ ሀብት አግኝተን በፍቅርና በደስታ መኖር ጀመርን፡፡ ቢሆንም አምላክ ይህንን ሁሉ ሰጥቶ ልጅ ግን ነሳን፡፡ አባትሽ

ልጅ ለማግኘት የነበራቸውን ጉጉት አውቅ ስለነበር ሌላ እንዲያገቡ ወይም ወልደው እንዲያመጡ ብጨቀጭቃቸውም፣ እሳቸው ግን እጅግ በጣም ስለሚቆጡ አማራጭ አልነበረምና በዚያ ሁኔታ ኑሮአችንን ቀጠልን፡፡ በመሀሉ አንድ እጅግ በጣም የምንወዳቸው የንስሀ አባታችን ስለታመሙና የሚያስታምማቸውም ሰው ስላልነበር እየተመላለስን እናስታምማቸው ጀመር። ሚስታቸው አንድ ልጅ ከወለዱ በኋላ ባላቸውን ከድተውና ቃል ኪዳናቸውን አፍርሰው ሌላ ባል አገቡ፡፡ የአስር ዓመት ልጃቸውና እሳቸው ብቻቸውን ይኖሩ ስለነበርና በሽታውም እየባሰባቸው በመምጣቱ ከአባትሽ ጋር ተመካክረን ወደ ቤታችን አመጣናቸው። በመሀሉ አንድ ቀን እኔን ጠርተው መሞቻቸው መቃረቡንና ሞትን እንደማይፈሩ፣ ነገር ግን የልጃቸው ነገር ከበሽታው በላይ እያሳሰባቸው መሆኑን ሲነግሩኝ፤ ልጅቷን እኛ እንደምናሳድጋትና ምንም የሚያሳስባቸው ነገር እንደሌለ ይልቅስ ይህንን እያሰቡ በመጨነቅ
👍342
በሽታቸውን እንዳያባብሱ መጠንቀቅ እንዳለባቸው ነገርኳቸው፡፡ የሚገርመው ግን ይህንን ተናግሬ ከመጨረሴ የልጃቸውን ነገር እንደገና አደራ ብለውና በምድር የሰጡኝን በሰማይ እንደሚቀበሉኝ ተናግረው ሞቱ፡፡ እኛም በነፍስ አባታችን ሞት ብናዝንም ልጅ በማግኘታችን ግን ደስ አለን፡፡ ልክ እንደአንቺ በፍቅር ማሳደጉን ተያያዝነው፡፡ በመሀሉ ዕድሜዋ አስራ ስድስት ዓመት አካባቢ እንደደረሰ እናቴ ስለሞተችብኝ ወደ መንዝ ለመሄድ ተነሳን፡፡ ይሁን እንጂ ጊዜው የእርሻ ወቅት ስለነበር አባትሽ ቀርተው እኔ ብቻ ብሄድ የተሻለ መሆኑን ስላሳመንኳቸው ብቻዬን ሄድኩ፡፡ ሁለት ወር ያህል ቆይቼ ስመለስ ግን የልጃችን የአሰለፉ ጠባይ እንደድሮ ሊሆን አልቻለም፡፡ በተለይ አባትሽን ባየች ቁጥር እንደድሮዋ መጫወቷ ቀርቶ መበርገግና መተከዝ አበዛች፡፡ አልፎ አልፎ አንድ ጉዳይ ልትነግረኝ የፈለገች ትመስልና መልሳ ትተወዋለች፡፡ ምን እንደሆነች ብጠይቃትም መልሷ "ምንም" ብቻ ነበር። ግን ነገሩ ሁሉ ተደብቆ ሊቀር አልቻለም፡፡ የማይደበቀው ነገር እያደር እየፈጠጠ መጣ፡፡ ቀስ በቀስ እርጉዝ መሆኗ ታወቀ፡፡ እኔም በጣም ደነገጥኩ፡፡ ልጂቱ ከቤት ወጥታ ስለማታውቅ ከአባትሽ ውጪ ከማንም ልታረግዝ እንደማትችል እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ የጠባይዋም መለዋወጥ ምክንያቱ ሌላ ሳይሆን ይኸው እንደነበር ስለገባኝ፤ ጠርቼ ማን አስረገዘሽ ሳይሆን፣ "እኔ የሄድኩ ጊዜ ነው አባትሽ የደፈሩሽ?" ብዬ ስጠይቃት መናገር አቅቷት ልቅሶዋን ተያያዘችው፡፡ ከዚያ በላይ መጠየቅ አላስፈለገኝም፡፡ አባትሽ የራሳቸው ልጅ እንዲኖራቸው በጣም እንደሚፈልጉ አውቃለሁ፡፡ ይህንን ደግሞ እኔ ላደርገው አልቻልኩም፡፡ ድርጊቱ እጅግ በጣም የሚዘገንን ቢሆንም የሳቸው የዘወትር ምኞት ግን ተሳክቶ እውን ሆኗል፡፡ እኔ መሀል ላይ ሆኜ ደስታቸውን ላጠፋው ስላልፈለግሁ አመቺ ግዜ ጠብቄ ጥያቸው ወደ መንዝ

ተመለስኩ፡፡ እዛም ለስድስት ወር ያህል ከቆየሁ በኋላ አባትሽ እዚያው አካባቢ ሲያፈላልጉኝ ከርመው ወደ መንዝ መሄዴን ስላወቁ እዚያ ድረስ ሄደው ይቅርታ እንዳደርግላቸውና ወደ ቤቴ እንድመለስ ነጋ ጠባ ይወተውቱኝ ገቡ። በኋላ ግን ማምረሬን ሲያዩ ሽማግሌዎች ይዘው እግሬ ላይ ተደፍተው ይቅር እንድላቸውና ሁለተኛ እንደዚያ ዓይነት ድርጊት እንደማይፈፅሙ የእመብርሀንን ስም እየጠሩ መማል ጀመሩ፡፡ ከእግሬ ላይ ተነሱ ብልም እግሬን ጥርቅም አድርገው ይዘው ይቅርታ ካላደረኩላቸው እንደማይነሱ በመናገራቸው ያንን ሁሉ ሽማግሌም ላለማሳፈር ስል ወደ ቤቴ ተመለስኩ። በእኔ ግምት አባትሽ እኔ ጥያቼው ከሄድኩ ሌላ ልጅ ጨምረው በደስታ ይኖራሉ ብዬ አሰብኩ እንጂ፣ ከዚያ በኋላ ለእኔ ያንን ያህል ፍቅር ይኖራቸዋል ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ ነገር ግን ወደ ቤት እስክንመለስ ድረስ እቅፍ አድርገው ዓይን ዓይኔን በጉጉት እየተመለከቱና ይቅርታ እንዳደርግላቸው በተደጋጋሚ እየወተወቱ ወደ ቤታችን ጉዞ ጀመርን፡፡ ነገር ግን የድሮ መሬትና ቤታችንን ሸጠው እዚህ ጭናክሰን ውስጥ ሌላ ቤትና ቦታ ገዝተው ጠበቁኝ፡፡ ከጎረቤቶቼ በመለየቴ ባዝንም "እንዴት አድርጌ የጎረቤቶቼን ዓይን አያለሁ?" እያልኩ እጨነቅ ስለነበር አድራሻ መለወጣችንና ጉዳችን ወደ ማይታወቅበት መንደር መሄዳችን ግን በጣም ደስ አለኝ፡፡ አሰለፉ የእኔን መምጣት እንደሰማች አንቺን አልጋ ላይ አስተኝታ በጓሮ በር ወጥታ ጠፋች፡፡ ወደ ቤት ስንገባ የአንቺ ለቅሶ ቤቱን አድምቆት ነበር፡፡ ስመኘው የነበረውን የልጅ ለቅሶ ባላሰብኩት መንገድ ስሰማ አንዳች ነገር ሰውነቴን ወረረው፡፡ ጠጋ ብዬ አልጋውን ስመለከት፤ ዞማ ፀጉር ያላት ቀይ ቆንጆ ድንቡሽቡሽ ያለች፣ ወገቧ ላይ ብቻ እራፊ ጨርቅ የታሰረ ሕጻን ራቁቷን ሆና ወፍራም እግሮቿን ወደ ላይ እያንፈራገጠች የምታለቅስ ልጅ አየሁ፡፡ የወለድኩ ያህል ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ከአልጋ ላይ አንስቼ ሳቅፍሽም ደረቴ ላይ ልጥፍ ብለሽ ወዲያው ማንቀላፋት በመጀመርሽ ገና እናትሽን መለየት እንዳልጀመርሽ ስላወቅሁ ደስ አለኝ፡፡ ደረቅ ጡቴንና የላም ወተት እያጠባሁ አሳደግሁሽ፡፡ መጀመሪያ ላይ አንቺን በማግኘቴና አሰለፉ በመሄዷ ደስ ይበለኝ እንጂ ቀስ በቀስ ግን የንስሐ አባቴ የሙት መንፈስ በተደጋጋሚ በህልሜ እየመጣ "ልጄን የት አደረግሻት?'' እያለ ይጠይቀኝ ስለነበር ነፍሴ መጨነቅ ጀመረች። ነገር ግን የትም ባፈላለግ ላገኛት አልቻልኩም፡፡ ይህ ከሆነ ከአራት ዓመት በኋላ የእንቁጣጣሽ በዓልን ምክንያት በማድረግ እኔና አባትሽ ልብስና የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦችን ለመግዛት ወደ ጅጅጋ ሄድን፡፡ ከመኪና ወርደን ወደ ገበያ እየሄድን ሳለ መንገድ ዳር ቁጭ ብላ የምትለምን ወጣት ባጋጣሚ አየሁና ገንዘብ ልሰጣት ጠጋ ስል ባየሁት ነገር

ደንግጬ እቆምኩበት ደርቄ ቀረሁ፡፡ የምትለምነው ሴት እናትሽ አሰለፉ መሆኗን ሳይ ከመደንገጤ የተነሳ እጄ እየተንቀጠቀጠ የያዝኩት ሳንቲም እርስ በእርሱ እየተጋጨ ድምፅ ማሰማት ጀመረ፡፡ ግን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ስለገባኝ ሳንቱሙን የዘረጋችው ጨርቋ ላይ ጥዬ በጥድፊያ ወደ አባትሽ ተራመድኩ፡፡ እሷ ግን አቀርቅራ ስለነበር አጎንባሳ ከመመረቅ ውጪ ማን እንደሆንኩ እንኳ ቀና ብላ አላየችም ነበር። ስለአየሁት ነገር ለአባትሽ መናገር በመፍራቴ ምንም ቃል ሳልተነፍስ ወደ ገበያ ገባን፡፡ የምንፈልገውን ገዛዝተን ከጨረስን በኋላ ሁሌ ስንሄድ ወደምናርፍባቸው የድሮ ጎረቤታችን የነበሩና እንደዘመድ ወደምንተያየው ባልና ሚስት ቤት አመራን፡፡ አካሄዳችን ደርሶ ለመመለስ ቢሆንም ባልና ሚስቱ ስንጫወት አድረን በነጋታው እንድንሄድ ስለለመኑንና እኔም ስለአሰለፉ ጉዳይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ የማሰቢያ ጊዜ ባገኝ በማለት አባትሽን ለሁለት አሳምነን ለማደር ወሰንን፡፡ ስናወራና ስንጫወት ካመሸን በኋላ አባትሽ ገና ጋደም እንዳሉ እንቅልፍ ወሰዳቸው፡፡ እኔ ግን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሳወጣና ሳወርድ እንቅልፍ በዓይኔ አልዞር አለ፡፡ ዝም ብዬ ብሄድ የንስሀ አባታችንን አደራ በማፍረስ የምፈፅመውን ኃጢያት ሳስብ ያስፈራኝ ጀመር፡፡ በሌላ በኩል እሷን ይዞ ለመሄድ በትዳሬ ላይ ሊመጣ የሚችለውን አደጋና በተለይ ደግሞ አንቺን የማጣበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ሳስብ ይበልጥ ያስጨንቀኝ ጀመር፡፡ ይህንን ሳወጣና ሳወርድ እንቅልፍ ሸለብ አደረገኝ፡፡ ይሁን እንጂ በመሀሉ የንሰሀ አባታችን በሕልሜ መጡብኝ፡፡ "ልጄን አደራ ብሰጥሽ ለማኝ አደረግሺያት?" እያሉ ሲያናገሩኝ፤ ከእሳቸው ጋር _ የመጣ ሰው ይመስለኛል፣ ጦር እየሰበቀ ሊወጋኝ ወደ እኔ ሲመጣ ጮሄ ከአልጋ ላይ ባንኜ ተነሳሁ፡፡ አባትሽ በሁኔታው ደንግጠውና እንደእኔው ባነው ተነስተው "ምን ነካሽ?" ብለው ጠየቁኝ፡፡ ምንም ሳልደብቅ ያየሁትን ነገር ሁሉ ነገርኳቸው፡፡ እሳቸው ግን አንድ ነገር ለማድረግ በማሰብ ላይ እንደነበሩ ቢያስታወቅባቸውም "እንዲህ ብናደርግ ይሻላል" የሚል የመፍትሄ ሀሳብ ለመስጠት ግን አልደፈሩም፡፡ እኔ ግን ጥያት ለመሄድ ሳላልፈለግሁ በነጋታው ጠዋት ሽንት ቤት የምሄድ መስዬ ትላንት ስትለምን ወደ ነበረችበት ቦታ ሄጄ መጠባበቁን ተያያዝኩት፡፡ እንደገመትኩትም ወደ እዛው ቦታ መጥታ ቁጭ ስትል በስሟ ጠራኋት፡፡ ቀና ብላ አየችኝና እኔ መሆኔን እንዳወቀች እላዬ ላይ ተጠመጠመችብኝ፡፡ "ይቅርታ አድርጊልኝ እማዬ፣ የእኔ ጥፋት አይደለም፣ ምናባቴ ላርግ? ብታገልም ከአቅሜ በላይ ሆኖብኝ ነው" እያለች እየዬዋን ለቀቀችው፡፡ እሷ አቀርቅራ እያለቀሰች እኔም እሷን እሷን እያየሁና እያነባሁ ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ የሆነውና የተደረገው ሁሉ የእሷ ጥፋት እንዳልሆነ እንደማውቅና ይቅርታ እንዳደረግሁላት ነግሬ
👍291👏1
ካረጋጋኋት በኋላ ከእኛ ጋር

እንድትሄድ ጠየቅኋት፡፡ በመጀመሪያ ላይ እምቢ ብትልም በኋላ ግን የአባቷ አደራ እንዳለብኝና ጥዬያት እንደማልሄድ እቅጩን ስለገርኳት ለመሄድ 情們叫:: እቤት እንደገባን ግን መረበሼ አልቀረም፡፡ በአንድ በኩል እኔ ለአንቺ ያለኝን እናትነቴን እንዳትቀማኝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አባትሽ በድጋሚ ስህተት እንዳይፈጽሙና ትዳሬ እንዳይፈርስ መጨነቅ ጀመርኩ፡፡ ለዚህ የነበረኝ አማራጭ አንድ ብቻ ስለነበር አሰለፉንና አባትሽን እሁድ ዕለት ወደ ቤተክርስትያን ይዤያቸው ሄድኩ፡፡ እሷ መቼም ቢሆን ከእኛ ፍቃድ ውጪ እናትነቷን ላንቺ እንዳትናገር፣ አባትሽም ዳግመኛ ተመሳሳይ ስሀተት እንደማይፈፅሙ፣ ሁለቱም የቤተክርስትያን AC ይዘው Παουλ እንዲያረጋግጡልኝ አደረግሁ፡፡ እንግዲህ አልሚና እውነቱ ይኸ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በዚህ ሁኔታ የተፈፀመው ላንቺና ለትዳሬ ካለኝ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ነው፡፡ አሁንም እጅግ የምወድሽ ልጄ ነሽ፡፡ ምንግዜም ቢሆን እናትሽ ነኝ፡፡ እኔ የአንቺ እናት መሆኔን ከማጣ ሞቴን እመርጣለሁ" አለቺኝ፡፡ ይህንን ታሪክ ስሰማና እናቴ ለእኔ ያላት ጥልቅ ፍቅር ምን ያህል እንደነበር ስገነዘብ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ፡፡ እምባዬንም _ መቆጣጠር ተሰኖኝ አቅፌያት ተንሰቀሰቅሁ፡፡ ለእናቴ ያለኝን የኖረ ፍቅር አምላኬ ምንም ሳያስቀር _ እንዲመልስልኝም ደረቷ ላይ ተለጥፌ ለመንኩት፡፡ እዚያ በቆየሁባቸው ቀናትም እናቴን እንዳልተቀየምኳትና አሁንም እንደጥንቱ እንደምወዳት ለማሳየት ጣርኩ፡፡ በዚህም ተረጋጋች ፡፡ በየወሩ እየመጣሁ እንደምጠይቃት ቃል ገብቼና ጥቂት ገንዘብ ሰጥቻት ወደ ዓለማያ ተጓዝኩ፡፡ የካቲት 15 ቀን 1980 ዓ.ም "ዘግይቼ በመድረሴ የፕሮጄክት ሥራዎቼን በመርሀ ግብሩ መሰረት ማካሄድ አልቻልኩም፡፡ ምንም እንኳ ብዙ ጊዜ ያባከንኩ ቢሆንም ዶ/ር አድማሱ እየረዳኝ ራሴን ከተማሪዎች ጋር ለማቀራረብ ቻልኩ፡፡ ይሁን እንጂ ከሌሎች ጋር እኩል ለመራመድ ብዙ ማንበብና እንቅልፍ ማጣት ነበረብኝ፡፡ በዚህ ላይ የተዘበራረቀው ህይወቴ በትምህርቴ መሃል ጣልቃ እየገባ ሥራ ያስፈታኝ ነበር፡፡ አብዛኛው የግቢው ሰው ውጣ ውረድ የተሞላበትን የሕይወቴ ታሪክ ባያውቅም በአባቴ ሞት የተነሳ ያጋጠመኝን ጉዳት እያየ እንድፅናና የማይመክረኝ አልነበረም፡፡ ሁሉም በሞት ያጣውንና የሚወደውን ዘመዱን እየጠቀሰ፣ ሐዘኑ የሚከብድ ቢሆንም ሐዘን ሲበዛ በሽታ እንጂ ምንም እንደማያስገኝ፤ ከሞትም የሚቀር ማንም እንደሌለ እየገለፀ ያፅናናኝ ነበር።"

መጋቢት 1 ቀን 1980 ዓም "እንዲህ በተዘበራረቀ መልኩ ሕይወትን እየመራሁት ሳለ በመሀሉ አንድ ያልጠበቅሁት ክስተት ተፈጠረ። ሰብዙ ጊዜ ድምፅዋን ሰምቼው የማላውቀው ጓደኛዬ ኤልሳቤጥ ደብዳቤ ላከችልኝ። ኤልሳቤጥ ካምፓስ ውስጥ አለች የምላት ከአማረ ቀጥሎ የምወዳት ብቸኛ ጓደኛዬ ነበረች:: ፍቅር ስጀምር የሚሰማኝን እንግዳ ነገር የምነግራት፣ ሁሌ የማይለየኝ ችግርና ሀዘን ሲደርስብኝ የማዋያት ጓደኛዬ እሷ ብቻ ነች፡፡ ከተመረቅን በኋላ የተሰጠኝን የማስትሬት ትምህርት ዕድል ትቼ ግቢውን ለቅቄ መውጣት እንደምፈልግ ስነግራት ከዶ/ር አድማሱ ጋር ሐሳቤን እንድለውጥና መማር እንዳለብኝ ደጋግመው ይመክሩኝ ስለነበር ለውሳኔዬ መለወጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራት፡፡ እሷም አማረን እንደእኔ ስለምትወደው እንደከዳኝ ብነግራትም አላምን ስላለችኝ የፃፈውን የክህደት ደብዳቤ አውጥቼ ባሳያት እንኳን ልትቀበለኝ አልፈቀደችም ነበር፡፡ እሷም እንደአብዛኛዎቹ ተማሪዎች በመጀመሪያ ዶ/ር አድማሱን ወድጄ አማረን ለመተው ምክንያት የምፈጥር አድርጋ ታስብ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ በእኔ ላይ የተከሰተውን የህይወት መመሰቃቀል ስታይና ስሜቴን ስትረዳ ታፅናናኝ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዶ/ር አድማሱን አስመልክቶ በሚነሳ ጉዳይ ላይ _ ሁሌም _ ውሳኔውን ለእኔ ትተወዋለች፡፡ እርግጥ እኔ ለዶ/ር አድማሱ ያለኝን ስሜት እየተረዳች በመምጣትዋ ስሜቴን መጉዳት ስለአልፈለገች ይሆናል እንጂ ለአማረ ካላት ፍቅር የተነሳ ከዶ/ር አድማሱ ጋር ትዳር ብመሰርት ቅር እንደሚላት አስባለሁ፡፡ ኤልሳ ከተመረቀች በኋላ የተመደበችው ግብርና ሚኒስቴር ውስጥ በአፈር ኤክስፐርትነት ነበር፡፡ እንደተመደበች ስለሁኔታው ደብዳቤ የፃፈችልኝ ቢሆንም ከዚያ በኋላ ግን የምትፅፍልኝ በጣም እየዘገየችና አልፎ አልፎ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ደብዳቤ መፃፍ አቁማ ስለነበር እኔም በተደጋጋሚ ደብዳቤ እየፃፍኩላት መልስ በማጣቴ መፃፌን አቆምኩ፡፡ ዛሬ ደብዳቤዋ ሲደርሰኝ ግን እጅግ በጣም ደስ አለኝ፡፡ እንዲህ ሐዘን በተጫጫነኝ ሰዓት ደብዳቤዋን በማግኘቴ አጠገቤ ቁጭ ብላ የምታፅናናኝ መሰለኝ፡፡ ደብዳቤዋ እንዲህ ይላል፡፡ "ይድረስ ለውድ ጓደኛዬ ለአልማዝ ታፈሰ ከተለያየንበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ እንደምን ሰንብተሻል፣ እኔ ከአንቺ ሐሳብና ናፍቆት በስተቀር እግዚአብሄር ይመስገን በጣሙን ደህና ነኝ፡፡ አልሚና ባለፈው ሳምንት እናንተ ጋ የመመረቂያ ጽሑፉን የሚሰራ አስፋው የሚባል የድህረ ምረቃ ተማሪ ለዚሁ የሚረዳውን መረጃ እኛ ዘንድ ለማሰባሰብ መጥቶ ከእኔ ጋር ተገናኝተን ስለአንቺ ጠይቄው አባትሽ እንደሞቱብሽ ሲነግረኝ እጅግ በጣም አዘንኩ፡፡ ይህ ደግሞ ለአንቺ ምን ያህል

ከባድና አሳዛኝ ማለት እንደሆነ ለምናውቀው ጥቂት ሰዎች ሐዘንሽ ምን ያህል መራራ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ይሁን እንጂ የሰው ልጅ ታሪክ ሁሌም ቢሆን በውልደት ተጀምሮ የሚጠናቀቀው በሞት ስለሆነና ሞት ደግሞ ቶሎ ሊመጣ ወይም ሊዘገይ ይችል እንደሆን እንጂ እንደማይቀር ሲታሰብ ሐዘንን መቻልና ማቅለል የግድ ይላል፡፡ እርግጥ ሐዘንሽን አቅልሎ እንድትረሺው አንቺን ለመምከር መሞከር ምን ያህል እንደሚከብድ ብገነዘብም ሐዘንን ማጥበቁ ለአንቺም ቢሆን ጥሩ ሊሆን እንደማይችል ተገንዝበሽ ሁሉንም ለመርሳት ሞክሪ፡፡ አልሚና በሥራ ተወጥሬ እንጂ አጠገብሽ ሆኜ ማፅናናት እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ እርግጥ መምጣቴ አይቀርም፤ ግን እስክመጣም ቢሆን አንቺን ሳላፅናና የሚያልፍ አንድ ሌሊትም ቢሆን እንቅልፍ ስለሚነሳኝና አስቀድሜ መጻፍ ስላለብኝ ነው የፃፍኩት፡፡ ስለዚህ ሐዘን አታብዢ፣ እግዚአብሄር የፈቀደውን ሊወስድ ያልፈቀደውን ሊያቆይ ሥልጣኑ የሱ ስለሆነ የሚያደርገውን ነገር ሁሉ በፀጋ ተቀብለሽ አሳልፊው፡፡ በተረፈ አንድ በጣም የሚገርም ነገር አጋጥሞኛል፡፡ ምንም እንኳን ሐዘን ላይ ብትሆኚ ይህንን ሣልነግርሽ ማለፍ የለብኝም፡፡ እንደምታውቂው እኔ የተለያዩ መጽሔቶችን አገላብጣለሁ፡፡ ከእጄ መጽሔት ሲጠፋም ቅር ይለኛል፡፡ ታዲያ አንድ ቀን አንድ መጽሔት ገዝቼ ሳገላብጥ አማረ የጻፈውን አንድ ጽሑፍና ፎቶግራፉን ሳይ ደነገጥኩ፡፡ ዓይኔ ያየውንም ማመን እስከሚያቅተው ድረስ መጽሔቱ ላይ ተተክዬ ቀረሁ፡፡ መጽሄቱ ላይ ያለው ፎቶግራፍ የእሱ ሆኖ ሳለ ስሙ ግን የእሱ አልነበረም፡፡ እንደሚመስለኝ የብእር ስሙ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የእኔንና የአንቺን እንቆቅልሽ ሳላስበው ልፈታው በመቻሌ ገረመኝ፡፡ ጽሁፉ ሴቶችን የሚያጥላላ በመሆኑ እሱን የማግኘት ስሜቴን ገፋፋው፡፡ ጋዜጠኞቹን ጠይቄ አድራሻውን በመከራ አገኘሁት፡፡ የሚገርመው ግን እኔ ላናግረው የምፈልገውን ያህል እሱ ግን ገና ሲያየኝ አስጠላሁት፡፡ ይህም የበለጠ ግራ ስላጋባኝ እሱን የማነጋገር ጉጉቴን ጨመረው፡፡ ለምን የራሱ በደል በእኔ ፊት ላይ ታየው? በማለት መንስኤውን ለማወቅ ጓጓሁ፡፡ ሊያናግረኝ ባይፈልግም በተደጋጋሚ ወደ ቢሮው እየሄድኩ ላናግረው እንደምፈልግ አለበለዚያ ግን መምጣቴን እንደማላቋርጥ ስነግረው ሊያናግረኝ ፍቃደኛ ሆነ፡፡ የሚሰራው አንድ የውጪ ድርጅት ውስጥ የእርሻ
👍222
ባለሙያ ሆኖ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ንግግሩን የጀመረው፤ "እናንተ ሰዎች አሁን ደግሞ ከእኔ ምን ቀራችሁ? ሕይወቴን ለምን ሰላም ትነሷታላችሁ?" በሚል ንግግር ነበር፡፡ አባባሉ ቀደም ሲል የነበረኝን

ጥርጣሬ ስላጎላው የማወቅ ስሜቴ ከፍ አለ። ምን ማለቱ እንደሆነም ጠየቅሁት፡ ነገር ግን መግለፅ የፈለገው እያፈቀረ እንደተከዳ አድርጎ ነበር። እኔ ደግሞ የማውቀው የእሱን ከዳተኝነት ስለነበር ብዙ ስድብ አዥጎደጎድኩበት፡፡ እንደውሸታምም ቆጠርኩት፡፡ ነገር ግን በእሱ አባባል ከዳተኛው እሱ ሳይሆን አንቺ እንደሆንሽና ከፈለግሁ መረጃው ቤት ውስጥ ስላለው ሊያሳየኝ እንደሚችል ነገረኝ። እኔም እንዳምነው ከፈለገ እንዲያሳየኝ ስለገፋፋሁት በነጋታው ልንገኛኝ ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡ የሚያሳየኝ ነገር ይኖረዋል ብዬ ስላልገመትኩ በነጋታው ይመጣል ብዬ አልጠበቅሁም ነበር። እሱ ግን መጣ። መረጃውን ሊያሳየኝም ወደ ቤቱ ይዞኝ ሄደ፡፡ አኗኗሩን ሳይ ደነገጥሁ፡፡ ቤት አልሰራም፣ አንዲት ትንሽ ቤት ተከራይቶ ነው የሚኖረው፡፡ ቤቷ ሁለት ክፍል ስትሆን ሣሎኑ በጣም ጠባብ ሆኖ እዚያች ውስጥ ያሉት ከገጠር ተሰርቶ የመጣ አንድ ጠረጴዛ እና አራት ወንበሮች፣ ከብረትና ከገመድ ተሰርቶ ስፖንጅ የተነጠፈበት ሶፋ ተብዬ ነገር እና አንድ ትንሽ የስልክ ማስቀመጫ ጠረጴዛ ብቻ ናቸው፡፡ ልጆች ይኖሩታል ብዬ ስለገመትኩ የሄድኩት ኩኪስ ገዝቼ ነበር ፡፡ የሚገርመው እሱ ግን ያው ወንደላጤ ሆኖ ነበር የጠበቀኝ፡፡ ኩኪሱን ሲያይ ልጆች ይኖሩታል ብዬ ገምቼ እንደመጣሁ ስለገባው፤ "ወንደላጤ ስለሆንኩ የሚያስፈራ ነገር የለምና ተዝናኚ" ብሎኝ መረጃውን ሊያመጣ ወደ መኝታ ቤት ገባ፡፡ ይልቅ መኝታ ቤቴ ነው ብሎ ባሳየኝ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋና ትልቅ የመጽሐፍ መደርደሪያ አለው፡፡ የሚገርመው ግን ያ ትልቅ የመጽሐፍ መደርደሪያ በሙሉ በመጽሐፍ የተሞላ ሲሆን ከትራስጌው አጠገብ ካለው ኮመዲኖ ላይ የአንቺ ፎቶ ተቀምጧል፡፡ ምንም እንኳ ቤቱ ትንሽ ብትሆንም የራሱ ከሆነችም አንድ ነገር ነው ብዬ፤ "ቤቱን ሰርተህ ነው ወይስ ተከራይተህ " ብዬ ጠየቅሁት፡፡ “አንድ ታዋቂ የሀገራችን ደራሲ እንዳሉት እኔ ቤት ሠርቼ ገንዘብ ሲተርፈኝ መጻሕፍት የምገዛ ሳልሆን መጻሕፍት ገዝቼ ሲተርፈኝ ቤት የምስራ ነኝ፡፡ ግን ምን ያደርጋል ከመጻሕፍት መግዢያ ተርፎ ቤት የምሰራበት ገንዘብ ባለማግኘቴ ቤት አልሰራሁም፣ የምኖረው ተከራይቼ ነው አለኝ፡ በነገራችን ላይ መጻሕፍት ለእኔ የዕውቀት ማእድ ብቻ ሣይሆኑ መደበቂያዬም ናቸው" አለኝ፡፡ አይገርምም? መጀመሪያ ከማን ነው የሚደበቀው በማለት ግራ ተጋብቼ ነበር፡፡ በኋላ ግን መረጃ ያለውን ሲያሳየኝ ግልፅ ሆነልኝ፡፡ የገረመኝ ግን ይኸ ብቻ አልነበረም፡፡ ያልጠበቅሁትን ያንቺን

ደብዳቤ አውጥቶ ሲያሳየኝና ሳነበው እጅግ በጣም አዘንኩለት፡፡ ሳላውቅ ስለሰደብኩትም ይቅርታ ጠየቅሁት፡፡ ድሮም እንደጠረጠርኩት የከዳሺው አንቺ መሆንሽን አረጋገጥሁ፡፡ እርግጥ ትዳር ማለት የግል ህይወት፣ ባልም የግል ምርጫ ነው፡፡ እኔም ብሆን ማንም ሰው ከፍላጎቴ ውጪ ተገፋፍቶ የማይፈልገውንና የማይወደውን ሰው ማግባት አለበት ብዬ አላምንም:: ውሳኔሽ የሆነው ይሁን ለምን እኔን መዋሸት እንደፈለግሽ ግን አልገባኝም: እስከማውቀው ድረስ ከእኔ ወዲያ ምስጢርሽን የምታካፍያት የሴት ጓደኛ አልነበረሽምና ለምን ልትዋሺኝ እንደፈለግሽ ግን አልገባኝም፡፡ እኔ አንቺ የምትፈልጊውንና የምትመኚውን እንድታገኚ እተባበር እንደሆን እንጂ ከፍላጎትሽ ውጪ እንድታደርጊ የምገፋፋ አይደለሁም። አስቢው እስኪ፣ ባልበደለው በደል እሱን በደለኛ አድርጌ ልጠላው ወይም ልሰድበው አይገባኝም ነበር፡፡ አልሚና እኔም ደብዳቤ መፃፍ ያቋረጥኩት በሌላ ምክንያት ወይም አንቺን በመርሳት ሳይሆን በዚሁ ተቀይሜ ነው፡፡ ለጻፍሽልኝም ደብዳቤዎች መልስ ያልሰጠሁሽ በዚህ የተነሳ ነው፡፡ ዛሬ ግን እንዲህ ከፍተኛ ሐዘን ሲደርስብሽ ዝም ማለት ስላላስቻለኝ ይህንን ደብዳቤ ጽፌልሻለሁ፡፡ እርግጥ እኛን አፍረሽ እንጅ ዶ/ር አድማሱን እንደምትወጂው እኔም እጠረጥር ነበር፡፡ ለአማረ ያለሽንም ፍቅር ከመጀመሪያ ጀምሮ የምትነግሪኝ ለእኔ ስለነበርና ሁኔታውም በአንዴ ተገልብጦ ሌላ ሰው በመውደድሽ ይህንን መናገር ሊከብድ ስለሚችል ብትዋሺኝም የሚገርም አይደለም፡፡ አልፎ አልፎ እንደሚታየው ሰው የሚያገባው እሱ ተመኝቶ የመረጠውን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር መርጦ የሰጠውን ነውና ለአንቺም እግዚአብሄር የመረጠልሽ እሱን በመሆኑ ብትነግሪኝም አልቀየምሽም ነበር፡፡ በተረፈ እግዚአብሄር ያጥናሽ እያልኩ አሁንም ቢሆን አንቺን የምትተካና እንዳንቺ የምወደዳት ጓደኛ የለኝም፡፡ እወድሻለሁ ያንቺው ኤልሳቤጥ ታምሩ "

ይህንን ደብዳቤ ሳይ ተስፋ መቁረጥ አንዣበበብኝ፡፡

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍355
ዝናብ ካለፈ በኋላ
ዣንጥላ 🌂 ለሁሉም ሰው
ሸክም ይሆናል!

ጥቅም ሲቆም ታማኝነት
የሚያበቃው በዚ መንገድ ነው።

እያንዳንዱ ፈገግታ እውነተኛ አይደለም
🥰16👍63
በልብ እያነቡ. . . . . .

ደህና ነኝ ማለት ወንጀል ቢሆን እንደው

ቀድሜ እኔ ነበርኩ ዘብጥያ የምወርደው፣
👍22😢2😱1
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_12

ይህንን ደብዳቤ ሳይ ተስፋ መቁረጥ አንዣበበብኝ፡፡ የምጓዝበት መንገድ ሁሉ በመከራ ጋሬጣ የተሞላ እንደሆነ ያለጥርጥር ተገነዘብኩ፡፡ አለኝ የምለውን ወዳጄን ሁሉ በየተራ እያጣሁ የመጣሁ፣ ከምረቃዬ ዕለት ውጪ አንድም ቀን የደስታ ቀን የምለው የሌለኝ፣ ነገር ግን ሐዘንና መከራ ብቻ ለእኔ _ ተመርጦ _ የተሰጠኝና የማይለየኝም እስኪመስል ድረስ ቢከታተለኝና ተስፋ መቁረጥ ቢያንዣብብብኝ የሚገርም አልነበረም፡፡ ምርጥ ምርጡን ለልጆች" እንደሚሉ ሁሉ መከራና ሐዘኑ ለአልማዝ የተባለ ይመስል የሕይወቴ ታሪክ ሁሉ የመከራና የሥቃይ ታሪክ ሆነ:: በድህነት የተነሳ

የሕይወቴን ጉዞ ያለወላጅ እናት ጀመርኩት፡፡ ቀስ በቀስ የምወዳቸውና አሎኝ የምላቸው ሁሉ ከዱኝ፡፡ እናቴንም እናትነቷን እንኳ ሳላውቅ እንደናፈቅኂት በሞት ተለየችኝ:: ወላጅ አባቴ በጭካኔ ተሞልቶ የሀዘን ማቅ አልብሶኝ አለፈ፡፡ ዛሬ ደግሞ የምወዳት ጓደኛዬ ያንን ሁሉ ዓመት አብረን አሳልፈንና ጠባዬን ጠንቅቃ እያወቀች ምንም ሳታቅማማ ከዳተኛ አድርጋ ስትመለከተኝ ከእንግዲህ ምን ቀረኝ ልል እችላለሁ:: ከዚህ ሁሉ በላይ በጣም የሚገርመው ደግሞ አለኝ ብዬ አምኜው ሳፈቅረው የከዳኝ አማረ በበደሉ ተፀዕቶ ይቅርታ በመጠየቅ ፋንታ ዛሬ እኔ እንደበደልኩት እሱ ግን ንፁህ ፍቅረኛ እንደነበር ሲናገርና በቅጥፈት በተሞላ ንግግሩ ጓደኛዬን ከእኔ ሲያርቃት ላይ ይበልጥ አዘንኩ:: ራሱ በደለኛ ሆኖ እያለ እኔን በደለኛ ለማድረግ መሞከሩ ለምን ይሆን? ብዬም ራሴን ጠየቅሁ:: ነው ወይስ እርግጥ እኔ ራሴ በደለኛ ሆኜ ይሆን? አሊያም የጻፈውን ደብዳቤ መልእክት አዛብቼ ተረድቼው ይሆን? ብዬም ተጠራጠርኩ:: ጥርጣሬዬ ስላየለብኝ የጻፈልኝን የክህደት ደብዳቤ መፈለግ ጀመርኩ፡፡ ደብዳቤዎቹን አንድ በአንድ እያየሁ ቀናቱን ተከትዬ ወደ ኋላ ስሄድ ያንን የመርዶ ደብዳቤ አገኘሁት:: እግረ መንገዴን ያገኘሁትን ደብዳቤ ሁሉ እያነበብኩ ስለነበር አማረ በተለያየ ወቅት የጻፋቸውን ደብዳቤዎች ላይ ራሴን መጠራጠሩ ተጠናከረ:: ይኸ ሁሉ ፍቅር የት ሄደ? ሁሉም ደብዳቤዎች እኔን ምን ያህል ይወደኝና ያፈቅረኝ እንደነበር የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ግን ይህ ሁሉ ፍቅር ከምኔው በንኖ ጠፍቶ እንዴት በአንድ ጊዜ ሲጠላኝ ይችላል? ብዬም ራሴን ራሴ ስጠይቅ እኔው ጥፋተኛ እንዳልሆን ፈረሁ። ደብዳቤውን ደጋግሜ አነበብኩት አገላብጬም አየሁት፡፡ ነገር ግን መንፈሱ ያው ጥንት እንደተረዳሁት ነው፤ አልተሳሳትኩም፡፡ ሌላ ሳይሆን ያው የማውቀው የክህደት ደብዳቤ ነበር:: ከዳተኛው እኔ ሳልሆን እሱው ነበር። ለእኔ የተሻለ ህይወት እንደሚመኝልኝ እሱ ግን ቢጤውን መውደዱንና ዳግም እንዳልጽፍና እንዳልረብሸው ተማፅኖ በዘጋው ደብዳቤ ፍቅራችንን በክህደት የደመደመው እኔ ሳልሆን እሱ ነው ብዬ በእርግጠኝነት ለራሴ ተናገርኩ፡፡ ነገር ግን ደብዳቤዎቹን በየተራ እያገላበጥኩ በሄድኩ ቁጥር ላምነው የማልችለው ነገር አጋጠመኝ:: በሆነው ነገርም ራሴን መቆጣጠር ተሳነኝ:: ከዚህ ደብዳቤ ጀርባ እንቆቅልሽ አለ፡፡ የእንቆቅልሹን ስም ባውቀውም ወርቁን ግን ላገኘው አልቻልኩም፡፡ እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ? ለምን? ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች እዚህ ሆኜ ልፈታቸው የምችል ስላልነበሩ ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረብኝ። በነጠላ ወረቀት ፊትና ጀርባ የተጻፈችው ደብዳቤ እንዳትጠፋብኝ በማለት በጥንቃቄ በዲያሪው የመጨረሻ ሽፋን ላይ ለጠፍኳት፡፡ ከመቅፅበት ስልኩን አንስቼ ለኤልሳ ደወልኩና ልፈታው የምፈልገው እንቆቅልሽ ስላለ ከአሥራ አምስት ቀን በኋላ እሷ ጋ መምጣት እንደምፈልግ፣

ሆቴል ይዛ እንድትጠብቀኝና ስመጣም ሁሉንም ነገር እንደማጫውታት ነገርካት:: በውስጤም የተደበላለቀ ስሜት ወረረኝ፡፡ በአንድ በኩል ይህ ሁሉ ነገር ውሸት ከሆነ እንደገና ከአማረ ጋር ሊኖረኝ የሚችለውን ፍቅር ሳስብ ደስታ ይሰማኛል፡፡ በተለይ አለማግባቱንና ፎቶዬ አሁንም ራስጌው አጠገብ መኖሩን መስማቴ እጅግ በጣም አስደስቶኛል:: በሌላ በኩል ደግሞ እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ የሚለው ሐሳብ ይበልጥ ያስጨንቀኝ ጀመር፡፡ ወደ ቤት መመለስ በፍፁም አስጠላኝ፡ ግቢው የሐዘን፣ የመከራና የክህደት ግቢ ስለሆነ ለቅቄ መውጣት አለብኝ ብዬ ወሰንኩ! በምድር ላይ ያለ ሌላ ፍጡር ሊለውጠው የማይችል ውሳኔ! " ይላል ዲያሪው:: ዲያሪውን ጣለው፣ ቅደደው የሚለኝ ስሜቴ እየታገለኝ ሳነብ እንዳልነበር ሁሉ አሁን ደግሞ አንብብ፣ አንብብ የሚል ስሜት ገፋፋኝ :: የአልማዝ እንቆቅልሽ የእኔም እንቆቅልሽ በመሆኑ እንቆቅልሹን ፈትቼ ሰምና ወርቁን ማወቅ ፈለግሁ:: ማንበብ ከጀመርኩ ለመጀመሪያ ጊዜም አልማዝ አልከዳቺኝም እንዴ? የሚል ጥርጣሬ በልቤ ውስጥ ፈነጠቀ። መቼም ምንም ያህል ውሸታም ቢኮን፣ አንድ ሰው ተስፋ ቆርጦ መኖር ባስጠላው ወቅት ሲሞት ብቻ በሚነበብ ዲያሪ ውስጥ እንዲህ ሽምigi አድርጎ ይዋሻል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ነው:: ምናልባት እኔስ የእሷ የክህደት ደብዳቤ አልደረሰኝ እንደሆንስ? የደብዳቤውን መንፈስ በትክክል ያልተረዳሁት ከሆነስ? ድንገት ወደ ሌላ የሐሳብ ውዥንብር ውጣ ውረድ በመግባት ይህ ሁሉ ድርጊት ህልም ወይም ቅዠት ቢሆንስ? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ:: ሕሊናዬ ፋታ አጣ፡፡ የእሷን ደብዳቤ ካስቀመጥኩበት ኮመዲኖ ውስጥ አውጥቼ አነበብኩት፡፡ አንዳችም የእንቆቅልሽ ነገር አልታየኝም:: ደብዳቤው አሁንም ቢሆን የክህደት ደብዳቤ ነው:: ክህደት የተፈጸመው በአልማዝ እንጂ በእኔ አይደለም:: እኔማ ከእሷ ሌላ አማራጭ አጥቼ ይኸው እስከአሁን ድረስ ሌላ ሴት አልታይህ ብላኝ ሕይወቴን በብቸኝነት እመራለሁ:: ሁሉንም ደብዳቤዎች አውጥቼ ደግሜ ደጋግሜ በየተራ አነበብኳቸው፡፡ ለእኔ ግን ሁሉም ግልፅ ናቸው፡፡ ከኋላቸው የተደበቀ ምንም እንቆቅልሽ አልነበረም:: ደብዳቤዎቹን አስቀምጬ ዲያሪውን አነሳሁ፡፡ ግን ማንበቤን ከመጀመሬ በፊት የውጪው በር ተንኳኳ፡፡ ያ ፖሊስ መቼም ሆን ብሎ ጠብቆ በዚህ ሰዓት መጥቶብኝ ይሆን እንዴ በማለት ተጨነቅሁ፡፡ ልክፍት፤ አልክፈት በማለት በዚያች አጭር ጊዜ ውስጥ ከራሴ ጋር ታገልሁ፡፡ አማራጭ ስላልነበረኝ ከፈትኩት፡፡ ነገር ግን በሩን ስከፍት የቆመችው አለሚቱ ነበረች፡፡ የሚበላ ይዛ መጥታ ነበር፡፡ ገና እንደገባች ያንን የስለቸኚን ጥያቄ እየደጋገመች "አልተሻሎትም _ እንዴ ጋሼ?" እያለች ብትጠይቀኝም መልሴ “ደህና ነኝ ብቻ በመሆኑ እያጉረመረመች ምግቡን በጥድፊያ ጠረጴዛ ላይ

አስቀመጠችው ፧ የመወርወር ያህል ነበር። ክፉኛ ተናዳለች፣ እንደ ድሮ “ጋሼ አፈር ስበላ ብሉ" ከማለት ይልቅ ከኩርፊያዋ ብዛት የተነሳ ከንፈሯ ተንጠልጥሎ መሬት የሚነካ መሰለ፡፡ ኮስተር ማለቷ ነው መሰለኝ፤ ግንባሯን የተጨረማመተ ጣሳ አስመሰለችው፡፡ ይሁን እንጂ በፉንጋ ፊቷ ምክንያት መልክ ባይኖራትም የተትረፈረፈ የደስ ደስ ስላላት የምታስጠላ አልነበረችም:: በዚህ ላይ ብስል ወይን መሳይ መልካ ወንድን ለወሲብ ለመጋበዝ በቂ የመሳብ ኃይል አለው፡፡ "ይሰማሉ ጋሼ ጤነኛ ካልሆኑ ሆስፒታል ቢሄዱ ጥሩ ነው:: እኔም ከሆንኩ ያስጠላሆት ደሞዜን ሰጥተው ቢያሰናብቱኝ ይሻላል እንጂ እንዲህ እየሆኑ እዚህ መኖር አልፈልግም:: ደግሞ ይህ ሁሉ ኩርፊያስ በምን ምክንያት እንደሆነ አልገባኝም፡፡ ማንበብ ከሆነ ድሮም ቢሆን ያነባሉ፡፡ እኔን ግን እንደዚህ አያስጠላዎትም ነበር:: ዛሬ ግን እኔን ማናገርም ሆነ ማየት አስጠልቶዎታል ስለዚህ ያሰናብቱኝ" አለችኝ በቁጣ:: በአባባሏ ተገረምኩ እንጂ አልፈረድኩባትም:: በገባች ቁጥር ቶሎ ውጪ እያልኩ ነበር የማጣድፋት:: ይህንንም
👍246
የማደርገው ወድጄ ሳይሆን ዲያሪውን ማቋረጥ ባለመፈለጌ ነው:: እርግጥ ባለውለታዬ ነች፡፡ ምንም ጎራዳ ብትሆን ለእኔ ውብ እና የክፉ ቀኔም ነች:: በተለይም ገበናዬን ሽፍናና ሁሉንም ነገር ችላ የምታስተናግደኝ እሷው ነች፡፡ ስለዚህም ላጣት አልሻም:: ከወንበሬ ተነስቼ ወደ እሷ አመራሁና ከንፈሯን እየሳምኩ፤ "አትቀየሚኝ የእኔ ቆንጆ፣ ወድጄ አይደለም፣ ከመሥሪያ ቤት የሰጡኝ ሥራ የግዴታ ማለቅ ስላለበት ነው፡፡ ይህንን ስጨርስ ደግሞ እንደ ዱሯችን እንሆናለንና ለትንሽ ቀን ብትታገሺኝ" አልኳት:: ፊቷ ወዲያውኑ በፈገግታ ተሞላ፡፡ ይህንንና ያንን ይመስላል እያልኩ የተለያዩ ስያሜዎች የሰጠሁት ምናምን ፊቷ በአንድ ጊዜ ውብ ሆነ:: “በሉ እሺ ምሳዎትን ብሉ" ብላ ተመልሳ ወጣች:: ምስኪን! አልኩ በሆዴ፡፡ ከመቅጽበት በአንድ መሳም ከብስጭትና ንዴት ተላቃ ወደ ደስታ ስትለወጥ በማየቴ በእጅጉ ገረመኝ:: ምናለ ስው ሁሉ እንደእሷ ገርና ቅን ቢሆን አልኩ፡፡ ምግቤን እንደጨረስኩ ተቻኩዬ ዲያሪውን አነሳሁ፡፡ ግን ማንበብ ከመጀመሬ በፊት ስልኩ አቃጨለ:: ላንሳው አላንሳው እያልኩ ከራሴ ጋር ታገልኩ:: አማራጭ ስላልነበረኝ፤ "ሀሎ አልኩ" ስልኩን አንስቼ። የሰማሁት ድምፅ ግን አስደንጋጭ ነበር።

"እንደምን ዋልክ እቶ አማረ፣ ሃምሳ አለቃ ነኝ። ምነው እንደወጣህ ቀረህ? እኔማ ቤት ትኖራለህ ብዬ አልጠረጠርኩም ነበር። አገር ለቀህ የጠፋU መስሎኝ ነበር:: አሁን ባስቸኳይ ዲያሪውን ይዘህ ቢሮ እንድትመጣ" አለኝ:: በድንጋጤ ክው አልኩ:: ተረጋግቼ ሳልርበተበት አንዲት ቃል እንኳን መተንፈስ የምችል አልነበርኩም። ይኼ ሰውዬ ሁለት ቀን ሙሉ ሳይፈልገኝ ቆይቶ እንዴት ዛሬ ሊፈልገኝ እንደቻለ ግራ ገባኝ:: አሁን ደግሞ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከሄድኩ የታሪኩን መጨረሻ ሳላውቅ ልታሰር ነው በማለት ሐሳብ ገባኝ:: ብዙ አውጥቼ እና አውርጄ የታየኝ አንድ አማራጭ ብቻ ነበር። ይኸውም አልቤርጎም ቢሆን ተከራይቼና ተደብቄ የጀመርኩትን ታሪክ አንብበ መጨረስ፡፡ ከዚያ በኋላ ስለመሄድም ሆነ አለመሄድ ጉዳይ ከታሪኩ መጨረሻ ተነስቼ የማደርገውን መወሰን እችላለሁ ብዬ ወሰንኩ:: ወዲያው በሚንቀጠቀጥ ድምፅ፤ “ጌታዬ እባክዎን አንድ ቀን ብቻ ይስጡኝ፡፡ ታሪኩን ለመጨረስ የቀረኝ ትንሽ ገፅ ነው፡፡ ነገ ይዤው እመጣለሁ" ብዬ መማፀን ጀመርኩ:: ሃምሳ አለቃው ይሆናል ብዬ ባልገመትኩት ሁኔታ ምንም ሳያንገራግር፣ “ጥሩ እሺ፣ ነገ እጠብቆታለሁ'' ብሎ ስልኩን ዘጋው:: ለራሴ 'ቆይ ያገኘኛል!" አልኩ:: "አራጁን እንደሚከተል በሬ ባላጠፋሁት ጥፋት እጄን ስጥቼ ሊያስረኝ ይፈልጋል? ጅል!" አልኩ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሳስበው የሚያስፈራኝና የበደልኩት በደል ወይም የሠራሁት ወንጀል ስለሌለ ምን ያሸሸኛል? ለምንስ በቀጥታ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄጄ እውነቱን አላውቅም? እላለሁ:: ለምን እንደምፈራ ግን ማወቅ ቸገረኝ፡፡ እኔ ተበደልኩ እንጂ አልበደልኩም፡፡ ደግሞስ ማሰር ከፈለገ እና በቂ ሕጋዊ ምክንያትና መነሻ ካለው ማን ከለከለው? ቤቴ ውስጥ እንዳለሁ በማወቁ ነው እዚህ የደወለው፡፡ እያልኩ ሐሳቦችን በመቀያየር ማውጣትና ማውረዱን ተያያዝኩት:: በመጨረሻ ግን ጊዜ ሳላጠፋ ማንበብ እንዳለብኝ ስለወሰንኩ ዲያሪውን አነሳሁ፡፡ ዲያሪው መጋቢት 13 ቀን 1980 ዓም ብሎ ጀመረ፡፡ ጉዳችንን እየዘከዘከም የእንቆቅልሹን መጨረሻ ሊያሳየኝ ትረካውን ቀጠለ፡፡ ይሁን እንጂ እንቆቅልሹ ይበልጥ ተወሳሰበ፡፡ ቢሆንም በተሰጠኝ አንድ ቀን ውስጥ መጨረስ ስላለብኝ በጥድፊያ ማንበቤን ተያያዝኩት፡፡ “የፕሮጄክቴ ማቅረቢያ ወቅት እየተቃረበ ቢመጣም እኔ ግን ሥራውን እርግፍ አድርጌ ተውኩት:: ዶ/ር አድማሱ የጠባዬ መለወጥና አልፎ ተርፎም ሥራውን ማቆሜ ይበልጥ ያስጨንቀው ጀመር:: “ምን ሆነሻል?" የሚለው

ጥያቄው ሁልጊዜ “ምንም" በሚል አጭር መልስ ብቻ ቢዘጋም በየቀኑ ግን መጠየቁን አላቆመም:: የእኔ ዝግጅት ግን ለመመረቅ ሳይሆን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግቢውን ለቅቂ ለመውጣት ብቻ ነበር:: የሚያስጨንቀኝ ግን ለዶ/ር አድማሱ ምን ምክንያት ጠቅሼ ከእጁ መውጣት እንደምችል ብቻ ነበር። በመጨረሻ ግን ቢቀበለውም ባይቀበለውም ምክንያቶቼን ደርድሬ ለመለያየት ወሰንኩ:: ይህንኑ እንዴት እንደምነግረው ሳወጣና ሳወርድ እሱ ራሱ መንገዱን እንዲህ በማለት ከፈተው:: “ስሚ እንጂ አልማዝ ምን እየሆንሽ ነው? የፈተና ቀናት እየተቃረቡ መሆናቸውን ታውቂያለሽ፡፡ አንድ ዓመት ሙሉ የደከምሽበትን ውጤት በምታዪበት ሰዓት ላይ ትምህርትን ከነጭራሹ የሚያስቆም ምን ምክንያት ተገኘ? አሳማኝ ምክንያትም ካለሽ ንገሪኝና ልስማው:: እኔስ ብሆን ቀን ስደክም ውዬ ማታ ደግሞ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳልል አንቺን የረዳሁበት ያ ሁሉ ድካሜ መክኖ ሲቀር አያሳዝንሽም:: እርግጥ መማሩንም ካልፈለግሽና ትምህርትሽን የምታቆሚበት አሳማኝ ምክንያት ካለሽ ብታቆሚም ቅር አይለኝም፡፡ ከዚህ ቀደም ቃል በተግባባነው መሰረት ተጋብተንና ልጅ ወልደን መኖር እንችላለን፡፡ እኔም ካለፍላጎትሽ ተማሪ እያልኩ አላስጨንቅሽም:: ግቢውም ካስጠላሽ ዛሬ ነገ ሳንል ለቀን መውጣት እንችላለን:: ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ እንድንነጋገርበት እፈልጋለሁ'' አለኝ:: የዶ/ር አድማሱን አርቆ ማሰብ ሳይ አሳዘነኝ። እሱ ሁሌም የሚያስበው ትምህርቴን ጨርሼ _ ከእኔ ጋር ስለሚመሰርተው ትዳርና ስለሚወልደው ልጅ፣ እንዲሁም አብረን ስለምናሳልፈው የደስታ ሕይወት ነው:: እኔ ደግሞ ከሌላ አንጻር የማስበውና የማሰላስለው የምወደውን አማረን ይቅርታ ጠይቄ ስለማሳልፈው ሌላኛው የደስታ ሕይወት ነው፡፡ ይህ ድብቅ ፍላጎቴ እውን ቢሆን ደግሞ በእሱ ላይ የሚከሰተው ነገር ያው እኔ ያለፍኩበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት እንደሆነ ስለገባኝ ማዘኔ አልቀረም፡፡ ግን አባቶቻችን “ከራስ በላይ ንፋስ" እንደሚሉት ሁሉ፣ ለእሱ ደስታ ስል የራሴን ደስታ መስዕዋት ማድረግን ደግሞ ሞክሬው ስለነበር እንደማይቻል አይቼዋለሁና ወደ እዚያ መመለስ የማይታሰብ ሆነብኝ፡፡ እሱ የሚመኘውና አብረን የምናሳልፈው የደስታ ሕይወት ደግሞ በእሱ ምናብ ውስጥ ያለ አሊያም ለእሱ ብቻ የሆነ ደስታ እንጂ እኔ የምጋራው አይደለም፡፡ ይህንን ሀቅ ለእሱ ነግሬ መለየት ደግሞ የእሱን መከፋት እያየሁ ጨክኜ መሄድ ማለት ነው፡፡ የእሱን መከፋትና ማዘን ፊት ለፊት ቆሞ ማየት ደግሞ ለምንጊዜም ቢሆን ከህሊናዬ ላይጠፋ ይችላል ብዬ ስለገመትኩ የውስጤን በውስጤ ይዤ ተራ ምክንያቶችን መደርደር ጀመርኩ::

“ዶ/ር ከእንግዲህ ወዲህ ስለትምህርቴ ባታነሳብኝ ደስ ይለኛል:: እኔ እዚህ ግቢ ከገባሁበት ዕለት ጀምሮ ካሳለፍኩት የደስታ ቀናት ይልቅ የሐllኒ አእምሮዬን ሰብስቤ ቀናት የበዙ ናቸው:: በተለይም አባቴ ከሞተ በኋላ መማር አልቻልኩም:: ሥራ ይዤ አባቴን ማሳከም ሲገባኝ እማራለሁ ብዬ አጣሁት:: አሁንም ይህንን ስህተት መድገም አልፈልግም። እናቴ አልፎ አልፎ እንደሚያማት ጎረቤቶቿ በስልክ ነግረውኛል፡፡ አሁን ደግሞ እሷን ማጣት አልሻም፡፡ ስለዚህም አውጥቼ እና አውርጄ መሄድ እንዳለብኝ ወስኛለሁ:: ትምህርቱ ለጊዜው ይበቃኛል። አዲስ አበባ ሥራ ፈልጌ መግባትና እናቴን ማስታመም አለብኝ:: አዲስ አበባ ያለችው ጓደኛዬ ኤልሳ ይህንኑ ሐሳብ ነግሬያት ሥራ አግኝታልኛለች፡፡ ስለዚህ አዲስ አበባ ለመሄድ ወስኛለሁ:: ከአንተም ጋር ጋብቻችንን ከእዚያ በኋላ ማድረግ እንችላለን አልኩት፡፡ ዶ/ር አድማሱ ግን የእኔን ተልካሻ ምክንያት ተቀብሎ በቀላሉ ሊለቀኝ አልፈለገም:: ይልቁንም መሄድ የሚለውን ነገር እንድተወው፣ ለእናቴም ማሳከሚያ ገንዘብ ሊሰጠኝ እንደሚችል፣
👍204