አትሮኖስ
269K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
434 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_11

የካቲት 7 ቀን 1980 ዓ.ም "ዶ/ር አድማሱ በመሃሉ የአባቴን መሞት በመስማቱ ሀዘን ለመድረስ መጣ፡፡ ቤቴን ሰለማያውቀውና ይመጣል ብዬ ጠብቄ ስላልነበር ሳየው ደነገጥሁ፡፡ ነገር ግን እጅግ በሚያስፈልገኝ ሰዓት በመምጣቱ ቢያንስ ጭንቀቴን የማካፍለው ሰው በማግኘቴ ደስ አለኝ፡፡ እንዴት ቤቴን ሊያውቀው እንደቻለ ጠይቄው ከአካባቢያችን ተማሪዎች አድራሻዬን ጠይቆ እንደመጣ ነገረኝ፡፡ እሱ ከመጣ በኋላ የመረጋጋት ስሜት ሰፈነብኝ፡፡ ቤታችን ለእሱ ዓይነት የከተማ ሰው ያውም ለዶ/ር ማደሪያነት የሚመች ስላልነበር በነጋታው እንዲሄድ ብወተውተውም እኔን ሳይዝ እንደማይሄድ ቁርጡን ነገረኝ:: አማራጭ ስላልነበረኝ ለራሴ አውጥቼና አውርጄ አንድ ነገር መወሰን ነበረብኝና ወስንኩ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ የቀረኝ አንድ የቅርብ ወዳጅ እሱ ስለነበር ተከትዬው ከመሄድ የተሻለ አማራጭ ስላልነበር ከእሱ ጋር ለመሄድ ወሰንኩ፡፡ እናቴ ሁለት ነገር _ አጥታለች፡፡ በአንድ በኩል ለአርባ ዓመታት አብሯት የኖረውን የትዳር ጓደኛዋ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በእኔ ላይ በፈጸሙት ሚስጥር የመሰወር ድርጊት የተነሳ የእኔም ፍቅር ቀንሶባታል፡፡ ስለዚህም ይመስላል ተሰናብቼያት ልወጣ ስል የሞትኩ ያህል ለቅሶዋን

የለቀቀችው፡፡ እናትና አባቴ ሁሉንም ነገር ያደረጉት ለእኔ ካላቸው ፍቅር የተነሳ በመሆኑና አሁን ግን በዚህ ሁኔታ አኩርፌያት ከሄድኩ እሷም አንድ ነገር ትሆናለች በማለት የኋላ ኋላም በዚሁ መንስኤ ክፉኛ ልፀፀት እንደምችል ዶ/ር አድማሱ ስላሳመነኝ ላረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ነገር ግን እንደአልተቀየምኳትና አሁንም እንደምወዳት ብነግራትም ከልቧ አላመነችኝም፡፡ አለቃቀሷንም ሳየው በዚህ ሁኔታ ዝም ብያት ብሄድ ተመልሼ እንደማላገኛት ስለተረዳሁ ዶ/ር አድማሱን ሸኝቼ ለተወሰነ ጊዜያት አብሬት ለመቆየት ወሰንኩ፡፡ በእናቴ ገጽታ ላይ የነበረው የመከፋት ስሜት ከፈቷ ላይ እየጠፋና በቦታውም ፈገግታ እየተተካ ሲሄድ በማየቴ በመቅረቴ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆነች በመገንዘቤ በጣም ደስ አለኝ::" የካቲት 8 ቀን 1980 ዓ.ም "አመሻሽ ላይ ያቀጣጠልነው የከሰል ፍም ተንደርኳል፡፡ ፍሙን እየሞቅን ከእናቴ ጋር ግራና ቀኝ ተቀምጠን ስናወራ፤ እጆቼን፣ ፀጉሬንና አንገቴን እየዳበሰች ስለአንድ ነገር ልትነግረኝ እንደፈለገች ሁኔታዋ ያስታውቃል፡፡ እኔም አንድ ልትነግረኝ የፈለገችው ነገር እንዳለ ታውቆኛል፡፡ ቀኝ እጅዋን በሁለት እጆቼ መሐል አድርጌ እያሻሽሁና አንገቴን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጌ የምትለውን ለመስማት ጆሮዬን አሹዬ መጠባበቁን ተያያዝኩት፤ "አልሚና _ እርግጥ አሁን በእኔ መቀየሙን ትተሻል? _ አሁንም እንደድሮ ትወጂኛለሽ?" አለችኝ፤ እውነቱን ለመናገር እናቴን አሁንም ብወዳትም በውስጤ ግን አንዳች የጎደለ ነገር ያለ ዓይነት ነገር _ ስለሚሰማኝ የድሮውን ዓይነት የመውደድ ስሜት አልነበረኝም፡፡ ይህንን መሳዩን ስሜት በውስጤ ደብቄ መዋሸት ደግሞ ሕሊናዬ ሊቀበለው ስላልቻለ፤ "እርግጥ አሁንም ያለሽኝ አንቺ ብቻ ስለሆንሽና ከማንኛዋም እናት ያላነሰ ፍቅር ለግሰሽ እዚህ ስላደረስሺኝ ከማንምና ከምንም በላይ አስበልጬ እወድሻለሁ፡፡ ነገር ግን እናቴን ለማወቅ ምን ያህል ስጓጓ እንደነበር እያወቃችሁ ያን ያህል ዓመታት ሳትነግሩኝ በመቅረታችሁ የተሰማኝን ቅሬታ ከውስጤ ላስወጣው ብሞክርም እምቢ ብሎ ስለአስቸገረኝ አሁንም የመቀየም ስሜት በውስጤ አለ፡፡ ግን ለምን እማዬ? ምናልባት አሰለፉ ኖራ ቢሆን ኖሮ ምንም ላይሰማኝ ይችል ነበር፡፡ እሷ ግን አሁን የለችም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሕይወት ኖራ ቢሆን ኖሮ ይኸን ግዜ ምን ያህል ደስ እንዳለኝ እላይዋ ላይ ተጠምጥሜ እየሳምኳት ልገልፅላት በቻልኩ ነበር፡፡ ሁሌ ስታድጊ እነግርሻለሁ ያለችኝንም ድብቅ ምስጢር እንዳወቅሁት በደስታ እየቦረቅሁና እየተፍለቀለቅሁ ልነግራት በቻልኩ ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ የሙሉ ሰው

ስሜት እንዳይሰማኝ በውስጤ ተደብቆ ሲያስጨንቀኝ የነበረው ተጥሎ የመገኘቴ ስሜት እንዲህ ለዚህ ሁሉ ዓመታት ሲጎዳኝ ባልኖረ ነበር። በተለይም ያቺ ምስኪን አስለፍ ከናፍቆቷና ከፍቅሯ ፅናት የተነሳ ስታገኘኝ ልትውጠኝ እየደረሰች፣ ነገር ግን ልጂ መሆኔን እንኳ ልትነግረኝ ሳትችል መሞቷን ሳስብ ሐዘኔ ከውስጤ አልወጣ ይለኛል፡፡ አትርፍጂብኝ እማዬ እነዚህ ዓይነቶቹ ስሜቶች በውስጤ ተደብቀው እንደድሮዬ እንዳልሆን እየታገሉኝ ሊሆን ይችላል እንጂ፤ አሁንም ቢሆን ከማንም ከምንም በላይ አብልጬ እወድሻለሁ፡፡ አትቀየሚኝ እማዬ! ወድጄ አይደለም" በማለት በውስጤ ያለውን እውነት ምንም ሳልደብቅ ነገርኳትና ደረቷ ላይ ተለጥፌ ልቅሶዬን ተያያዝኩት፡፡ እናቴ ከእኔው ጋር ስታለቅስና ስታባብለኝ ከቆየች በኋላ ልቅሶዬን ትቼ መረጋጋት ስጀምር፤ ፀጉሬን እያሻሸች “አልሚና እኔ መቼም ቢሆን አልቀየምሽም፡፡ ግን አንድ እንድታውቂው የምፈልገው እውነት ስላለ ዝም ብለሽ አዳምጪኝ። እንደምታውቂው እኔና አባትሽ ያው የአንድ ሐገር ልጆች ነን፡፡ በወጣትነት ዘመናችን መንዝ ውስጥ እኔ ሞላሌ፣ እሳቸው ደግሞ ላሎምድር የሚባል ቦታ እንኖር ነበር፡፡ አባትሽ ባጋጣሚ ዘመድ ለመጠየቅ ወደ እኛ ሰፈር መጥተው በነበረበት ጊዜ አይተው ወደዱኝ፡፡ በኋላም ሽማግሌ ልከው እና ቤተሰቦቼን አስፈቅደው በወግ በማዕረግ ተጋባን፡፡ ከዚያ በፊት አይቼው የማላውቀውን ሰው በማግባቴ መጀመሪያ ላይ ውስጤ እጅግ ቢከፋም አባትሽ ግን በጣም ጥሩ ሰው ስለነበሩና እጅግ በጣም ይወዱኝ ም ስለነበር ከመዋል ከማደር እኔም አፈቀርኳቸው፡፡ ለሶስት ዓመታት እዚያው መንዝ ውስጥ እንደኖርን አባትሽ አንድ አሉኝ የሚሏቸው አጎታቸው ከጅጅጋ ሊጠይቁን መጡ፡፡ ጅጅጋ ውስጥ ብዙ መሬት እንዳላቸው፣ ሀገሩም ሊነገድበትና ገንዘብ ሊፈራበት የሚችል በመሆኑና እሳቸውም ከሥጋ ዘመድ ርቆ በብቸኝነት መኖር ስለሰለቻቸው፣ ከእሳቸው ጋር ብንሄድ መሬት እንደሚሰጡንና እዛም የተሻለ ኑሮ መኖር እንደምንችል ለአባትሽ ነግረው አሳመኗቸው፡፡ እኔ ብዙም ደስባይለኝም የተወለድንበትን ቀዬ ትተንና አጎትየውን አምነን ጅጅጋ መጣን፡፡ ሰውዬው ሚስታቸው ሞተውባቸው ብቻቸውን ይኖሩ ስለነበር፤ ያለናቸው ብቸኛ ዘመድ እኛ ብቻ በመሆናችን ከእኛ ቤት አይወጡም ነበር፡፡ አባትሽንም ልጄ ነው ብለው ለየሰዎቹ ሁሉ ስለአስተዋወቋቸው አገሬው በሙሉ የሚያውቃቸው የሳቸው ልጅ አድርጎ ነበር፡፡ ሰውዬው ሲሞቱም ያላቸውን ንብረት ሁሉ ለእኛ አወረሱን፡፡ እንዳሉትም እዚህ የተሻለ ሀብት አግኝተን በፍቅርና በደስታ መኖር ጀመርን፡፡ ቢሆንም አምላክ ይህንን ሁሉ ሰጥቶ ልጅ ግን ነሳን፡፡ አባትሽ

ልጅ ለማግኘት የነበራቸውን ጉጉት አውቅ ስለነበር ሌላ እንዲያገቡ ወይም ወልደው እንዲያመጡ ብጨቀጭቃቸውም፣ እሳቸው ግን እጅግ በጣም ስለሚቆጡ አማራጭ አልነበረምና በዚያ ሁኔታ ኑሮአችንን ቀጠልን፡፡ በመሀሉ አንድ እጅግ በጣም የምንወዳቸው የንስሀ አባታችን ስለታመሙና የሚያስታምማቸውም ሰው ስላልነበር እየተመላለስን እናስታምማቸው ጀመር። ሚስታቸው አንድ ልጅ ከወለዱ በኋላ ባላቸውን ከድተውና ቃል ኪዳናቸውን አፍርሰው ሌላ ባል አገቡ፡፡ የአስር ዓመት ልጃቸውና እሳቸው ብቻቸውን ይኖሩ ስለነበርና በሽታውም እየባሰባቸው በመምጣቱ ከአባትሽ ጋር ተመካክረን ወደ ቤታችን አመጣናቸው። በመሀሉ አንድ ቀን እኔን ጠርተው መሞቻቸው መቃረቡንና ሞትን እንደማይፈሩ፣ ነገር ግን የልጃቸው ነገር ከበሽታው በላይ እያሳሰባቸው መሆኑን ሲነግሩኝ፤ ልጅቷን እኛ እንደምናሳድጋትና ምንም የሚያሳስባቸው ነገር እንደሌለ ይልቅስ ይህንን እያሰቡ በመጨነቅ