አትሮኖስ
269K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
434 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_12

ይህንን ደብዳቤ ሳይ ተስፋ መቁረጥ አንዣበበብኝ፡፡ የምጓዝበት መንገድ ሁሉ በመከራ ጋሬጣ የተሞላ እንደሆነ ያለጥርጥር ተገነዘብኩ፡፡ አለኝ የምለውን ወዳጄን ሁሉ በየተራ እያጣሁ የመጣሁ፣ ከምረቃዬ ዕለት ውጪ አንድም ቀን የደስታ ቀን የምለው የሌለኝ፣ ነገር ግን ሐዘንና መከራ ብቻ ለእኔ _ ተመርጦ _ የተሰጠኝና የማይለየኝም እስኪመስል ድረስ ቢከታተለኝና ተስፋ መቁረጥ ቢያንዣብብብኝ የሚገርም አልነበረም፡፡ ምርጥ ምርጡን ለልጆች" እንደሚሉ ሁሉ መከራና ሐዘኑ ለአልማዝ የተባለ ይመስል የሕይወቴ ታሪክ ሁሉ የመከራና የሥቃይ ታሪክ ሆነ:: በድህነት የተነሳ

የሕይወቴን ጉዞ ያለወላጅ እናት ጀመርኩት፡፡ ቀስ በቀስ የምወዳቸውና አሎኝ የምላቸው ሁሉ ከዱኝ፡፡ እናቴንም እናትነቷን እንኳ ሳላውቅ እንደናፈቅኂት በሞት ተለየችኝ:: ወላጅ አባቴ በጭካኔ ተሞልቶ የሀዘን ማቅ አልብሶኝ አለፈ፡፡ ዛሬ ደግሞ የምወዳት ጓደኛዬ ያንን ሁሉ ዓመት አብረን አሳልፈንና ጠባዬን ጠንቅቃ እያወቀች ምንም ሳታቅማማ ከዳተኛ አድርጋ ስትመለከተኝ ከእንግዲህ ምን ቀረኝ ልል እችላለሁ:: ከዚህ ሁሉ በላይ በጣም የሚገርመው ደግሞ አለኝ ብዬ አምኜው ሳፈቅረው የከዳኝ አማረ በበደሉ ተፀዕቶ ይቅርታ በመጠየቅ ፋንታ ዛሬ እኔ እንደበደልኩት እሱ ግን ንፁህ ፍቅረኛ እንደነበር ሲናገርና በቅጥፈት በተሞላ ንግግሩ ጓደኛዬን ከእኔ ሲያርቃት ላይ ይበልጥ አዘንኩ:: ራሱ በደለኛ ሆኖ እያለ እኔን በደለኛ ለማድረግ መሞከሩ ለምን ይሆን? ብዬም ራሴን ጠየቅሁ:: ነው ወይስ እርግጥ እኔ ራሴ በደለኛ ሆኜ ይሆን? አሊያም የጻፈውን ደብዳቤ መልእክት አዛብቼ ተረድቼው ይሆን? ብዬም ተጠራጠርኩ:: ጥርጣሬዬ ስላየለብኝ የጻፈልኝን የክህደት ደብዳቤ መፈለግ ጀመርኩ፡፡ ደብዳቤዎቹን አንድ በአንድ እያየሁ ቀናቱን ተከትዬ ወደ ኋላ ስሄድ ያንን የመርዶ ደብዳቤ አገኘሁት:: እግረ መንገዴን ያገኘሁትን ደብዳቤ ሁሉ እያነበብኩ ስለነበር አማረ በተለያየ ወቅት የጻፋቸውን ደብዳቤዎች ላይ ራሴን መጠራጠሩ ተጠናከረ:: ይኸ ሁሉ ፍቅር የት ሄደ? ሁሉም ደብዳቤዎች እኔን ምን ያህል ይወደኝና ያፈቅረኝ እንደነበር የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ግን ይህ ሁሉ ፍቅር ከምኔው በንኖ ጠፍቶ እንዴት በአንድ ጊዜ ሲጠላኝ ይችላል? ብዬም ራሴን ራሴ ስጠይቅ እኔው ጥፋተኛ እንዳልሆን ፈረሁ። ደብዳቤውን ደጋግሜ አነበብኩት አገላብጬም አየሁት፡፡ ነገር ግን መንፈሱ ያው ጥንት እንደተረዳሁት ነው፤ አልተሳሳትኩም፡፡ ሌላ ሳይሆን ያው የማውቀው የክህደት ደብዳቤ ነበር:: ከዳተኛው እኔ ሳልሆን እሱው ነበር። ለእኔ የተሻለ ህይወት እንደሚመኝልኝ እሱ ግን ቢጤውን መውደዱንና ዳግም እንዳልጽፍና እንዳልረብሸው ተማፅኖ በዘጋው ደብዳቤ ፍቅራችንን በክህደት የደመደመው እኔ ሳልሆን እሱ ነው ብዬ በእርግጠኝነት ለራሴ ተናገርኩ፡፡ ነገር ግን ደብዳቤዎቹን በየተራ እያገላበጥኩ በሄድኩ ቁጥር ላምነው የማልችለው ነገር አጋጠመኝ:: በሆነው ነገርም ራሴን መቆጣጠር ተሳነኝ:: ከዚህ ደብዳቤ ጀርባ እንቆቅልሽ አለ፡፡ የእንቆቅልሹን ስም ባውቀውም ወርቁን ግን ላገኘው አልቻልኩም፡፡ እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ? ለምን? ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች እዚህ ሆኜ ልፈታቸው የምችል ስላልነበሩ ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረብኝ። በነጠላ ወረቀት ፊትና ጀርባ የተጻፈችው ደብዳቤ እንዳትጠፋብኝ በማለት በጥንቃቄ በዲያሪው የመጨረሻ ሽፋን ላይ ለጠፍኳት፡፡ ከመቅፅበት ስልኩን አንስቼ ለኤልሳ ደወልኩና ልፈታው የምፈልገው እንቆቅልሽ ስላለ ከአሥራ አምስት ቀን በኋላ እሷ ጋ መምጣት እንደምፈልግ፣

ሆቴል ይዛ እንድትጠብቀኝና ስመጣም ሁሉንም ነገር እንደማጫውታት ነገርካት:: በውስጤም የተደበላለቀ ስሜት ወረረኝ፡፡ በአንድ በኩል ይህ ሁሉ ነገር ውሸት ከሆነ እንደገና ከአማረ ጋር ሊኖረኝ የሚችለውን ፍቅር ሳስብ ደስታ ይሰማኛል፡፡ በተለይ አለማግባቱንና ፎቶዬ አሁንም ራስጌው አጠገብ መኖሩን መስማቴ እጅግ በጣም አስደስቶኛል:: በሌላ በኩል ደግሞ እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ የሚለው ሐሳብ ይበልጥ ያስጨንቀኝ ጀመር፡፡ ወደ ቤት መመለስ በፍፁም አስጠላኝ፡ ግቢው የሐዘን፣ የመከራና የክህደት ግቢ ስለሆነ ለቅቄ መውጣት አለብኝ ብዬ ወሰንኩ! በምድር ላይ ያለ ሌላ ፍጡር ሊለውጠው የማይችል ውሳኔ! " ይላል ዲያሪው:: ዲያሪውን ጣለው፣ ቅደደው የሚለኝ ስሜቴ እየታገለኝ ሳነብ እንዳልነበር ሁሉ አሁን ደግሞ አንብብ፣ አንብብ የሚል ስሜት ገፋፋኝ :: የአልማዝ እንቆቅልሽ የእኔም እንቆቅልሽ በመሆኑ እንቆቅልሹን ፈትቼ ሰምና ወርቁን ማወቅ ፈለግሁ:: ማንበብ ከጀመርኩ ለመጀመሪያ ጊዜም አልማዝ አልከዳቺኝም እንዴ? የሚል ጥርጣሬ በልቤ ውስጥ ፈነጠቀ። መቼም ምንም ያህል ውሸታም ቢኮን፣ አንድ ሰው ተስፋ ቆርጦ መኖር ባስጠላው ወቅት ሲሞት ብቻ በሚነበብ ዲያሪ ውስጥ እንዲህ ሽምigi አድርጎ ይዋሻል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ነው:: ምናልባት እኔስ የእሷ የክህደት ደብዳቤ አልደረሰኝ እንደሆንስ? የደብዳቤውን መንፈስ በትክክል ያልተረዳሁት ከሆነስ? ድንገት ወደ ሌላ የሐሳብ ውዥንብር ውጣ ውረድ በመግባት ይህ ሁሉ ድርጊት ህልም ወይም ቅዠት ቢሆንስ? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ:: ሕሊናዬ ፋታ አጣ፡፡ የእሷን ደብዳቤ ካስቀመጥኩበት ኮመዲኖ ውስጥ አውጥቼ አነበብኩት፡፡ አንዳችም የእንቆቅልሽ ነገር አልታየኝም:: ደብዳቤው አሁንም ቢሆን የክህደት ደብዳቤ ነው:: ክህደት የተፈጸመው በአልማዝ እንጂ በእኔ አይደለም:: እኔማ ከእሷ ሌላ አማራጭ አጥቼ ይኸው እስከአሁን ድረስ ሌላ ሴት አልታይህ ብላኝ ሕይወቴን በብቸኝነት እመራለሁ:: ሁሉንም ደብዳቤዎች አውጥቼ ደግሜ ደጋግሜ በየተራ አነበብኳቸው፡፡ ለእኔ ግን ሁሉም ግልፅ ናቸው፡፡ ከኋላቸው የተደበቀ ምንም እንቆቅልሽ አልነበረም:: ደብዳቤዎቹን አስቀምጬ ዲያሪውን አነሳሁ፡፡ ግን ማንበቤን ከመጀመሬ በፊት የውጪው በር ተንኳኳ፡፡ ያ ፖሊስ መቼም ሆን ብሎ ጠብቆ በዚህ ሰዓት መጥቶብኝ ይሆን እንዴ በማለት ተጨነቅሁ፡፡ ልክፍት፤ አልክፈት በማለት በዚያች አጭር ጊዜ ውስጥ ከራሴ ጋር ታገልሁ፡፡ አማራጭ ስላልነበረኝ ከፈትኩት፡፡ ነገር ግን በሩን ስከፍት የቆመችው አለሚቱ ነበረች፡፡ የሚበላ ይዛ መጥታ ነበር፡፡ ገና እንደገባች ያንን የስለቸኚን ጥያቄ እየደጋገመች "አልተሻሎትም _ እንዴ ጋሼ?" እያለች ብትጠይቀኝም መልሴ “ደህና ነኝ ብቻ በመሆኑ እያጉረመረመች ምግቡን በጥድፊያ ጠረጴዛ ላይ

አስቀመጠችው ፧ የመወርወር ያህል ነበር። ክፉኛ ተናዳለች፣ እንደ ድሮ “ጋሼ አፈር ስበላ ብሉ" ከማለት ይልቅ ከኩርፊያዋ ብዛት የተነሳ ከንፈሯ ተንጠልጥሎ መሬት የሚነካ መሰለ፡፡ ኮስተር ማለቷ ነው መሰለኝ፤ ግንባሯን የተጨረማመተ ጣሳ አስመሰለችው፡፡ ይሁን እንጂ በፉንጋ ፊቷ ምክንያት መልክ ባይኖራትም የተትረፈረፈ የደስ ደስ ስላላት የምታስጠላ አልነበረችም:: በዚህ ላይ ብስል ወይን መሳይ መልካ ወንድን ለወሲብ ለመጋበዝ በቂ የመሳብ ኃይል አለው፡፡ "ይሰማሉ ጋሼ ጤነኛ ካልሆኑ ሆስፒታል ቢሄዱ ጥሩ ነው:: እኔም ከሆንኩ ያስጠላሆት ደሞዜን ሰጥተው ቢያሰናብቱኝ ይሻላል እንጂ እንዲህ እየሆኑ እዚህ መኖር አልፈልግም:: ደግሞ ይህ ሁሉ ኩርፊያስ በምን ምክንያት እንደሆነ አልገባኝም፡፡ ማንበብ ከሆነ ድሮም ቢሆን ያነባሉ፡፡ እኔን ግን እንደዚህ አያስጠላዎትም ነበር:: ዛሬ ግን እኔን ማናገርም ሆነ ማየት አስጠልቶዎታል ስለዚህ ያሰናብቱኝ" አለችኝ በቁጣ:: በአባባሏ ተገረምኩ እንጂ አልፈረድኩባትም:: በገባች ቁጥር ቶሎ ውጪ እያልኩ ነበር የማጣድፋት:: ይህንንም