አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

‹‹እናንተ ደግሞ ጅል አትሁኑ…ሰሎሜ ሰው ነች…ሰው ስለሆነች ታማለች…የተመመ ሰው ደግሞ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ህክምና ካላገኘ ይሞታል….ይሄ ሀቅ ለሌላ ሰው ከሰራ  ለሰሎሜም ይሰራል፡፡››ሁሴን ነበር የተናገረው፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ሁሉን ነገር አውቃለሁ የምትለው ነገር አለ››አለማየሁ በብስጭት መለሰለት፡፡

‹‹ትክክል ነኛ..ከእናንተ በተሻለ ብዙ ነገር አውቃለሁ…ይልቅስ ሰሎሜ ቀዶ-ጥገናዋን እንድታደርግ እኛ ምን ማድረግ አለብን ?የሚለውን መነጋገር ነው የሚጠቅመን፡፡››

‹‹ትክክል ነህ..የመጣልህ ሀሳብ አለ?››አለማየሁ ነው በጉጉት የጠየቀው፡፡

የቀዶ ጥገና እንዲደረግላት የተወሰነበትንና  እና የገንዘቡን መጠን የሚገልፅ ደብዳቤ ማግኘት አለብን›› ሁሴን ሀሳብ አቀረበ፡፡

‹‹አግኝተንስ ምን እናደርገዋለን?››አላዛር ጠየቀ፡፡

‹‹በሰፈር ጠቅላላ ዞረን እንለምናለን…በትምህርት ቤታችንም እንለምናለን፡፡››

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው..ግን ያንን ሁሉ ብር የምናገኝ ይመስልሀል?››በጥርጣሬ ጠየቁት፡፡

‹‹እስከቻልነው እንሞክራለን…ካልሞላልን ደግሞ ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን..አሁን ደብዳቤውን እንዴት እንደምናገኝ ማሰብ አለብን››

‹‹ለምን ሀኪም ቤት ሄደን ሰሎሜን የሚያክማትን ሀኪም አንጠይቀውም…››አላዛር ነው ሀሳቡን ያቀረበው፡፡

‹‹አይ አንተ ጅል የሆንክ ልጅ..አሁን ሄደን ብንጠይቀው ለ13 አመት ልጇች እንዲህ አይነት መረጃ ሚሰጠን ይመስልሀል?››

‹‹እኔ እንጃ ግራ ስለገባኝ እኮ ነው፡፡››

‹‹ለምን እቴቴን አንጠይቃትም..እሷ ደብዳቤውን ልታስወጣልን ትችላለች››

‹‹አሌክስ ትክክል ነው..ጊዜ ሳናባክን አቴቴን እናናግራት››ሁሴን በአለማየሁ ሀሳብ ወዲያው ተስማማ፡፡

‹‹ግን እኮ እሷ ሆስፒታል ነው ያለችው››

‹‹እኮ እንሂዳ››
ተስማሙና ቀጥታ ሰሎሜ ወደተኛችበት ሆስፒታል ነበር የሄዱት፡፡ሰሎሜ የተኛችበት ክፍል ገብተው ያለችበትን ሁኔታ ካዩ በኃላ‹‹እቴቴ አንዴ ውጭ ልናናግርሽ ፈልገን ነበር፡፡››ሲሉ ጠየቋት፡፡

‹‹ምነው በሰላም?››

‹‹በሰላም ነው..ሰሎሜ ስለተኛች እዚህ ስናወራ እንዳንቀሰቅሳት ነው››አለ ሁሴን፡፡

‹‹እሺ እንዳላችሁ ››በማለት ተስማምታ  ተከትላቸው ወጣች፡፡እዛው ሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ካለ አግዳሚ ወንበር ላይ በመደዳ ተቀመጡ፡፡

ለነገሩ ብዙም ትኩረት ባለመስጠት‹‹እሺ ልጆች ..ለምንድነበር የፈለጋችሁኝ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡

‹‹ሰሎሜ እንዴት ነች?››

ቀዝቀዝ ባለ ስሜት ‹‹ደህና ነች..ምንም አትል››ስትል መለሰችላቸው፡፡

‹‹ማለት ስለቀዶ ጥገናው ነው የምናወራሽ…?እንዴት ነው የሚሆነው…?ያን ያህል ብር ከየት ታመጪያለሽ?››

‹‹ልጇች አትጨነቁ..ከየትም ብዬ ከየትም ይሄንን ብር አግኝቼ ብቸኛ ልጄን ማሳከም አለብኝ….አታስቡ ጓደኛችሁን እንድትድን የተቻለኝን አደርጋለሁ፡፡››ስትል እንባ እየተናነቃት መለሰችላቸው፡፡በእውነት ብሩን ከየት እንደምታመጣው…የትኞቹን ዘመዶቾን እንደምታስቸግር…የትኛውን ንብረቷን ብትሸጥ የተጠየቀችውን ብር ማግኘት እንደምትችል  ምንም አይነት ሀሳብም ሆነ ተስፋ  አልነበራት፡፡ግን ለልጆቹ ይሄንን ምን ብላ በምን አይነት ቋንቋ ልታስረዳቸው ትችላለች፡፡ለዛ ነው በደፈናው ልታፅናናቸው የወሰነችው፡፡

‹‹እቴቴ…ሰሎሜን ለማዳን የተቻለንን ብቻ ሳይሆን ከምንችለው በላይ ነው ማድረግ ያለብን…ሶስታችንም ልክ እንደአንቺ እሷን ለማጣት ዝግጁ አይደለንም…እና የሆነ ነገር ለማድረግ አስበናል፡››ሁሴን ነበር ተናጋሪው፡፡

አቴቴ ግራ በመጋባት‹‹ምን ማለት ነው …?እናንተ ደግሞ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?››

‹‹ከሀኪም ቤቱ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት መወሰኑን እና  ለዛም የሚያስፈልገውን ብር የሚገልጽ ደብዳቤ እንዲሰጡሽ ጠይቂያቸው››

‹‹ማለት ..ደብዳቤው ምን ያደርግልኛል?››

‹‹አይ ላንቺ አይደለም..ለእኛ ያስፈልገናል››

‹‹ለምን .?.ምን ልታደርጉበት?››
ትምህርት ቤታቸውን ሆነ በሰፈራችን እርዳታ እየዞርን እንጠይቃለን..ከየአንዳንዱ ሰው አንድ  ብርም ሆነ አስር ብር እየዞርን እንሰበስባለን…ለዛ ግን ሰው እንዲያምነን እና ስራችን ቀላል እንዲሆንልን መረጃው ያስፈልገናል፡፡››

በወቅቱ የሰሎሜ እናት ስሜቷን መቆጣጠር አልቻለችም ነበር…ሁሉንም አንድ ላይ አቅፋ ጉያዋ ውስጥ በመወሸቅ ስቅስቅ ብላ ነበር ማልቀስ የጀመረች፡፡

አለማየሁ ጉንጮ ላይ ያለውን እንባ በመዳፎቹ እየጠረገላት ‹‹እቴቴ አይዞሽ.. አታልቅሺ …ሰሎሜን እናድናታለን…እሷ የእኛ ንግስት ነች..ንግስታችንን ማጣት አንፈልግም፡፡››ሲል አፅናናት ፡፡

‹‹ያስለቀሰኝ  ሀዘን አይደለም ደስታ ነው፡፡ልጄን ወንድም ወይም እህት ሳልወልድላት ብቸኛ አደረኳት ብዬ ብዙ ጊዜ አዝኜና አልቅሼ ነበር፡፡አሁን ግን እንደተሳሳትኩ በደንብ ነው የገባኝ፡፡ወንድሞች ቢኖሯትም እናንተ ከምትወዷትና ከምትንከባከቧት በላይ ሊንከባከቧት አይችሉም ነበር፡፡
በጣም ነው የማመሰግናችሁ፡፡ እናንተ ስላላችኋት ልጄ በጣም እድለኛ ነች››

‹‹አይ እቴቴ….እሷ ስላለችን እኛ ነን እድለኞች…አሁን መላቀሱ አይጠቅመንም…ሂጂና ዶክተሮቹን ጠይቀሽ ደብዳቤውን አግኚልን፡፡››

‹‹እሺ በቃ ውስጥ ገብታችሁ ጠብቁኝ …መጣሁ››ብላ በነጠላዋ ጫፍ በጉንጮቾ የረገፈ እንባዋን እየጠረገች ወደአስተዳደር ቢሮ ሄደች፡፡

ደብዳቤውን በእጃቸው ካስገቡ በኋላ ሰፈራቸው ወደሚገኝ ባነር መታሚያ ቤት ነበር  የሄድት፡፡ ደብዳቤውን አሳይተውና ሁኔታውን አስረድተው…የሰሎሜ አሳዛኝ ፎቶ የሚታይበትንና ያለችበትን ሁኔታ እጥር ምጥን ባለ ግልፅ ዓረፍተ ነገር አፅፈው ሁለት ሜትር በአንድ ሜትር በሆነ ባነር አሳተሙ፡፡ ..በማግስቱ ወደትምህርት ቤት ይዘው ሄዱ፡፡ቀጥታ ወደ ዳሪክተሩ ቢሮ ሄዱና ሁኔታውን አስረዱት….፡፡.ተማሪዎች በተሰለፉበት ባነሩ ለሁሉም እንዲታይ ተዘርግቶ ሰሎሜ ያለችበትን ሁኔታና የሚያስፈልጋትን ነገር ለሁለቱም ፈረቃ ተማሪዎች ተነገረ…፡፡በእለቱ በኪሳቸው ያላቸው ተማሪዎች ወዲያውኑ ማዋጣት ጀመሩ…ሁለት ሺ ሶስት መቶ ብር አካባቢ ተሰበሰበ፡፡በማግስቱ ሁሉም ተማሪ ለወላጆቹ በማስረዳት የቻለውን ይዞ እንዲመጣና በስም ጠሪዎች አማካይነት በየክፍሉ እንዲሰበስብ ተደረገ፡፡
በአጠቃላይ በሶስት ቀን ውስጥ ከመላው ተማሪና አስተማሪዎች 23 ሺ ብር ተሰበሰበ፡፡ትምህርት ቤቱ የሰሎሜን እናት ጠርቶ ቀጥታ ብሩን አስረከባት፡፡  የትምህርት ቤቱን ቅፅር ግቢ በእልልታ አናጋችው….ሶስቱን የልጇን ጓደኞች እያገላላበጠች ሳመቻቸው፡፡ከልቧ መረቀቻቸው፡፡ከነፍሷ ወደደቻቸው፡፡
እነአለማየሁ ግን እንደእሷ ባገኙት ነገር ፍፅም ደስታ አልተሰማቸውም ነበር፡፡የእነሱ ግምት ቢያንስ 40 እና 50 ሺ ብር እናገኛለን የሚል ነበር፡፡ወዲያው ጊዜ ሳያባክኑ ባነሩን ለሁለት ጉን ለጉን ይዘው አንደኛው በአጀንዳ ላይ እያንዳዱ ሰው የሚሰጠውን ስምና ብር  እየመዘገበ  በሰፈር ውስጥ እያንዳንዱን ቤት እያንኳኩ እና የድርጅቶችንም ቢሮ ዘልቀው እየገቡ  ጭምር መጠየቅ ጀመሩ፡፡
በአራት ቀን ውስጥ ሌላ 20 ሺ ብር አገኙና ለእናትዬው አስረከቧት..፡፡እሷ በፊት ደብተሯ ላይ የነበራትናን ከቢሮዋ ሰራተኞች ተዋጥቶ የተሰጣት አንድ ላይ ሆኖ እነሱ ከሰበሰቡት ጋር  50 ሺ ብር አካባቢ በእጇ ያዘች፡፡
ሶስቱም በአንድ ላይ ተሰብስበው ሄደው ‹‹እቴቴ..አሁን ስንት ብር ሆነልሽ?››ብለው ጠየቋት፡፡
👍599👏1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

…‹‹በቃ ምንም ማድረግ አንችልም ማለት ነው?››አላዛር ነው በተስፋ መቁረጥ የጠየቀው፡፡

‹‹አይ የሆነ ነገርማ ማድረግ አለብን››ሁሴን ተናገረ

‹አዎ….የሆነ ነገርማ ማድረግ አለብን ..የሆነ ሀብታም ፈልገን ለምን ወግትን ብር አንቀበለውም››የአለማየሁ ሀሳብ ነበር፡፡

‹‹ከዛ የተሻለ ሀሳብ አለኝ..አሁን ወደሰፈር እንሂድ››ሁሴን ነበር መላሹ፡፡

‹‹ምን ለማድረግ?››

‹‹ነገ የትምህርት ቤት ተማሪዎችንና ጋዜጠኞችን ይዘን ይሄንን ሆስፒታል እንወረዋለን››

‹‹እንዴት አድርገን...?ተማሪው እሺ ይላል?››

‹‹አዎ ጥሩ ዘዴ ተጠቅመን ከቀሰቀስን ይሳካልናል፡፡
አነአለማየው ቤት ተሰብስበው ለቅስቀሳ የሚጠቀሙበትን ፅሁፍ ሲያረቁ አመሹ፡፡

እህታችን ከሞት እንታደጋት፡፡
ሰሎሜ  ግርማ በጠና ህመም ታማ ሆስፒታል ከተኛች 15 ቀን እንዳለፋት እናውቃለን፡፡ በቀጣዬቹ 15 ቀናት ቀዶ ጥገና ካላደረገች ..ትምህርት ቤቱን ለአንድ ቀን ዘግተ፤ እጃችንን ወደኃላ አጣምረን ፤ለቀብር ቤተክርስቲያን መዋላችን ማይቀር ነው፡፡

እኛ እሷን ለማዳን ቤተሰቦቻችንን ሁሉ አስቸግረን የተቻለንን ብር አሰባስበናል…50 ሺ ብር በእናትዬው እጅ አለ..ሆስፒታሉ ግን 70 ሺ  ካላሳዚያችሁ በስተቀር ቀዶ ጥገናውን ማድረግ አልችልም ብሏል፡፡ይሄ ምን አይነት ሰባዊነት ነው፡፡ነገ በሰሎሜ ቦታ እኛ ብንታመምስ ተመሳሳዩ አይደል የሚገጥመን…?እኛ ተማሪዎች መብታችንን ማስከበር አለብን፡፡ከአስራአምስት ቀን በሃላ ወደቀብር ከመሄድ በነገው ቀን ልክ በእርፍት ሰዓት ተሰብስበው  ሆስፒታሉን በሰላማዊ ሰልፍ መውረር አለብን..ከዛ መንግስትም  ቢሆን ጣልቃ ገብቶ እህታችን እንድትታከም ማድረግ አለበት፡፡በቦታው ላይ የሬዲዬና የቲቪ ጋዜጠኞች ስለሚኖሩ ድምፃችን በደንብ እንደሚስተጋባ አውቃችሁ ለዚህ ተባባሪ እንድትሆኑ እንጠይቃለን፡፡፡
የሚል መልእክት በእጅ ፅሁፍ አረቀቁና…ኮፒ ቤት ሄደው ለምነው በነፃ አፃፉ፡፡በሰፈር ያሉት ኮፒ ቤቶች ሁሉ አንድ 50 ሌላው መቶ  እያለ ከሶስት መቶ በላይ ኮፒአስደረጉና  ጥዋት አንድ ሰዓት ትምህርት ቤት በራፍ ላይ ተገኙ፡፡ …ከዛ እያንዳንዱ ተማሪ ወደትምህርት ቤት ሲገባ አንድ አንድ ወርቀት እየታደለ ነበር የገባው…በእረፍት ሰዓት ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ቅፅር ጊቢ ውስጥ አልቀረም ነበር፡፡አስተማሪዎችም ሆነ ዘበኞቹ ሁኔታውን ሊቆጣጠሩ ቢሞክሩም ሁሉነገር  ከአቅማቸው በላይ ነበር የሆነው….
የትምህርት ቤቱ ዳሪክተር በኃላ እንዳያስጠይቀው ወዲያው ለአካባቢው ፖሊስ በመደወል ሁኔታውን አስረዳ፡፡፡ከአራት መቶ በላይ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ሆስፒታሉን ወረሩት፡፡የተፈጠረውን ነገር ለማጣራትና ከዚህም ከዚያም የተሰበሰቡ ከሺ ባላይ የሚሆኑ  በአካባቢው ሚያልፉ ሰዎች ሰልፉን ተቀላቅለው የበለጠ ደማቅና አስፈሪ አደረጉት፡፡ ….ከተለያየ ጣቢያ የተውጣጡ ጋዜጠኞች ካሜራቸውን ደቅነው በሰልፉ ፊት ለፊት ተኮለኮሉ፡፡አድማ በታኝ ፖሊስና  የእሳት አደጋ መኪና፤አንቡላስ መኪኖች በአካባቢው በቅርብ እርቀት በተጠንቀቅ ቆመው ይታያሉ፡፡ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ታካሚዎች ምን እንደተፈጠረ ግራ በመጋባት ትርምስ ፈጠሩ..ሀኪሞችም ስራቸውን እንዴት እንደሚሰሩ ግራ ተጋቡ…

ከተማሪዎች አንደበት ሚወጣው መፈክር እና  በእጃቸው ፅፈው የያዙት ፅሁፍ ነበር የጉዳዩን ምንነት እንዲያውቁ ያደረገው፡

‹‹ሰሎሜ በገንዘብ እጥረት መሞት የለባትም፡፡››

‹‹ሆስፒታሉ ለሰሎሜ  ህክምና ወጪላይ ቅናሽ ማድረግ አለበት፡፡››

‹‹ሰሎሜ ዛሬውኑ ቀዶ ጥገና እንዲደረግላት እንፈልጋለን፡፡››

ከቆይታ በኃላ ትንንትና ያናገሩት የሆስፒታሉ ኃላፊ በግንባሩ ላይ ላቡ እየጠንጠባጠበ ሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ከሰልፈኛ ተማሪዎች ፊት ለፊት ቆሞ በድምጽ ማጉያ መናገር ጀመረ፡፡

‹‹አንዴ ፀጥታ፡፡በእውነት ጉዳዩ እዚህ መድረስ የለበትም ነበር፡፡የሆስፒታሉ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ከአንድ ሰዓት በኃላ ተሰብስቦ ውሳኔ ያስተላልፋል፡፡እና በእርግጠኝነት የጓደኛችሁ ቀዶ ጥገና  24 ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይሰራላታል፡፡ይሄንን ቃል የገባሁት በህዝብና በሚዲያ ፊት ስለሆነ ምንም ስጋት አይግባችሁ፡፡አሁን ብዙ በሽተኞች እጃችና ላይ አሉ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ደግሞ ስራችንን መስራት ሰለማንችን…ምንም አይነት ግርግር ሳትፈጥሩ ቀጥታ ወደትምህር ቤታችሁ ተመለሱ…እንደምታዩት  ብዙ ፖሊስ በአካባቢው አለ..ችግር እንዳይፈጠር አደራ….ብሎ ላቡን በመሀረብ እየጠረገ ወደውስጥ ተመለሰ፡፡ተማሪዎችም እርስ በርስ እየተነጋገሩ እንዳመጣጣችው ወደትምህር ቤት ተመለሱ፡፡ በእነሱ ምክንያት የተሰበሰበውም የፀጥታ አካልና ተሸከርካሪም እንደፈሩት ምንም ጉዳት ባለመድረሱ ተደስተው እንደአመጣጠቸው ተመለሱ…ከሰዓታት በኃላ ግን ሙሉ ሚዲያው ጠቅላለ ይሄንን ጉዳይ አስፋፍቶና አጋኖ ማቅረብ ጀመረ….አንዳንዱ ሚዲያ የህክምና ባለሞያ ጋብዞ ስለሀገሪቱ የህክምና ዋጋ ውድነት አስተነተነ..ሌላው የህግ ባለሞያ ጋብዞ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሞከረ..  ሌላው ከጤና ጣቢያ ባለስልጣናትን በስልክ በመጠየቅ የመንግስትን አቋም ለማወቅ ሞከረ፡፡
ሁለት ሰዓት ዜና ላይ ግን ሁሉም የሚፈልገው ምስራች አየሩን ተቋጣጠረው፡፡ ለሰሎሜ እናትና ለጓዶቾ የሚያስፈነጥዝ ዜና ነበር፡፡
የሆስፒታሉ ቦርድ ተሰብስቦ በመነጋገር…የተማሪ ሰሎሜን ኬዝ በልዩ ሁኔታ በመመልከት እናቷ ለብቻዋ የምታሳድጋት በመሆኑና ተማሪ ጓደኞቾ እሷን ለማዳን ገንዘብ ከማዋጣት አንስቶ ያደረጉትን ከፍተኛ ትግለ እና አርአያ ያለው ተግባር ከግንዛቤ በማስገባት ሆስፒታሉ ያለምንም ክፍያ ቀዶ ጥገናውን በነፃ ሊያደርግላት ወስኗል፡፡እናትዬው ለቀዶ ጥገናው ልትከፍለው የነበረውን ብር ልጅቷን ከቀዶ ጥገናው በኃለ በማገገም ሂደት ውስጥ  ለሚያስፈልጋት ወጪ እንዲሆናት ፈቅዷል፡፡››የሚል መግለጫ.. ሰጠ፤ እንዳሉትም..በማግስቱ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ ሰሎሜ ወደቀዶ ጥገና ክፍል ገባች፡፡5 ሰዓት ከፈጀ ውስብስብ ቀዶ ጥገና ቆይታ በኃላ በሽታዋ ተወግዶ ወደ ፅኑ ህክምና ክፍል ተዘዋወረች..በዛ መንገድ ከሞት ሾልካ አመለጠች፡፡ሰሎሜ በጓደኞቾ ጥረት እና ተአምራዊ ትጋት ድና ከወር በኃላ ወደትምህርት ቤት ስትመለስ በትህርት ቤት ውስጥ በጣም ዝነኛና ታዋቂ ሆና ነበር፡፡እሷ ብቻ ሳትሆን ጓደኛቾም ጭምር የተከበሩና የተመሰገኑ ሆኑ፡፡ጥምረታቸውም ‹‹ምን አይነት ጓደኛነት ነው?››እየተባለ ሁሉም የሚቀናበትና  እንደምሳሌ የሚቀርብ ሆኖ  በሁሉም ዘንድ እውቅና አገኘ፡፡

ሁለቱም ከትዝታቸው ሲመለሱ አይኖቻቸው እንባ አቅርረው ነበር…..
ኩማንደር አለማየሁ ጉሮሮውን አፀዳዳና ‹‹አሁን ወደሁለተኛው ጉዳይ እንሸጋገር››ሲል አላዛርንም ከገባበት ትካዜ እንዲወጣ አደረገው፡፡

‹‹ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ምንድነው?››ግራ በመጋባትና በፍራቻ ስሜት ጠየቀው፡፡

‹‹ሁለተኛው ጉዳይማ ዋናው ነው…ይሄን ሁሉ ችግር ያመጣውና ልጅቷን በውድቅት ለሊት ብን ብላ ከቤት እንድትወጣ ያደረጋት ችግር››

‹‹ዝም ብለህ እኮ ነው..ጊዜዊ የባልናሚስቶች ጭቅጭቅ ነው…ግድ የለም እኔ አስተካክለዋለው…ሁለተኛ  አይደገምም፡፡››

‹‹እርግጠኛ ነህ?››ኮስተርና ቆፍጠን ብሎ ጠየቀው፡፡
አላዛር ደነገጠ‹‹ማለት?››

‹‹አላዛር …ሁሉን ነገር አውቄዋለው…እኔ የአንተም ሆነ የእሷ የሰሎሜ ጓደኛ ነኝ…እዚህ ጋር ምንም የምንደባበቀው ነገር መኖር የለበትም፡፡››
👍5812