#ቅድስትና_ትዕግስት
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
ቅድስት ልክ ስምንት ሰዕት ከሩብ ሲል ትዕግስት ቤት ደረሰች፡፡
“ውይ ቅድስትዬ...! ምነው እንዲህ ጠቋቆርሽ...? ፀሐይ እንኳን የለ ዛሬ..! አለች፣ ትዕግስት አራት ጊዜ ጉንጭዋን ስማት ስታበቃ....
“ኧረ ተይኝ ባክሽ....ለእንደኔ ያለ ሰው ከነዚያ ሴቶች ጋር ሦስት ሠዐት ሙሉ ስለ ልብስና ጫማ ማውራት ራሱ፣ ከሰባት ፀሐይ በላይ አያከስልም?” አለች ቅድስት፣ ሶፋው ላይ ዝርፍጥ ብላ እየተቀመጠች...
እናም፣ በተገናኙ ቁጥር የሚያደሩት ተመሳሳይ ወሬያቸው በእንዲህ ሁኔታ ተጀመረ፡፡
“አይ ለእኔ ነው ስለነሱ የምትነግሪኝ ቅድስትዬ? እኔስ ምናቸው
አስመርሮኝ ብረንች መምጣት ተውኩና!”
ደግ አደረግሽ... እኔ የምለው? ማስተርስ ድረስ የተማሩ ሴቶችከልብስና ከወንድ ውጪ ሌላ ነገር ማውራት አለመቻላቸው
አያሳዝንም? በጣም ያሳፍራል እኮ!”
በጣም እንጂ... ዐሥር ሴት ሚኒስትር ቢሾም ታች ያለነው ሴቶች
”ትላንት ስለገዛነው፣ ነገ ስለምንገዛው፣ ልንገዛ ፈልገን ስላጣነው ቶፕ ብቻ ምናወራ ከሆነ፣ ይህች ሀገር እንዴት ብላ ቀና ትላለች...? ሲንፏቀቁ መኖር እኮ ነው!”
“ጎሽ... እኔ እኮ አንቺ ጋር መምጣት የምወደው ለዚህ ነው...
ተንፈስ ስለምታደርጊኝ... ቁምነገር ስለምታዋሪኝ እኮ ነው አንቺ ጋር
መምጣት ደስ የሚለኝ ቲጂዬ!”
“እኔስ ብትይ....! እሺ..... ዛሬስ ምን ተፈጠረ ታዲያ?”
“ምን አዲስ ነገር ይፈጠራል... ያው ሴሞ ሴሞ ነው..ሃሚት ሃሜት... ወሬ... ሰው ቡጨቃ…. እይው የገዛሁትን ልብስ... ይሄ
ሽቶ ደስ አይልም...? እገሊት ጂም ጀመረች.. እንትና ዮጋ ጀመረች
ይሄው ነው ቲጂዬ!”
“አይገርመኝም...ዘለዓለም ያው ናቸው... ዘለዓለም.. ማፈሪያዎች!”
“እህስ!...ዛሬ ደግሞ ያቺ ሶሎሜ መጥታ ጭራሽ ስትጠብስኝ አረፈደች... ደህና ተገላግለናት ነበር፡፡”
“መጣች እንዴ? ዱባይ ቫኬሽን ላይ ነኝ ምናምን ብላ ስታናፋ አልነበረም እንዴ?”
“እንግዲህ ያ የግፍ ዶላር ቶሎ አልቆ ይሆናላ! ወር ሳይሞላት ተመለሰች!”
“አዬ! ለዚህችው ነው ያ ሁሉ ጉራ! ...ግን አንቺን ምን አርጋ አናደደችሽ ቅድስትዬ?”
አረ ተይኝ ገና በሥርዓት እንኳን ሳልቀመጥ እየሮጠች መጥታ ቶፕሽ ያምራል... እኔ የዛሬ ሁለት ዓመት በአራት መቶ ብር ገዝቼው ነበር...በቢጫው አለኝ... አሁን ግን ፋሽን ስላለፈበት ለሠራተኛዬ ስጠኋት' አትለኝም?"
“አታደርገውም!”
"አደረገችው እንጂ ትግስትዬ! አደረገችው!"
እና አንቺስ ዝም አልሻት?”
"ማ? እኔ ቅድስት እንዲህ ባደባባይ ሰድባኝ ዝም የምላት ይመስልሻል?"
“እና... እና ምናልሻት?”
የኔ እናት... ተማስሎብሽ ይሆናል... ይሄ ሌተስት ፋሽን ነው... የጣሊያን እቃ ነው! የገዛሁት ደግሞ አንድ ሺህ ስምንት
መቶ ብር ነው ... አልኳታ!”
'ወይኔ አንቺ... አንጀት አርስ እኮ ነሽ!"
“ታዲያስ...የሆነች ባላገር...ትላንት ብረንች ማለት አቅቷት፣
ብራንች የምትል ሴትዮ፤ አንዴ ዱባይ ሄጄ መጣሁ ብላ ትላጥብኛለች እንዴ?”
ሃሃ... አይ ቅድስት!”
ይልቅ እነሱን ተያቸውና ቲጂዬ የሚበላ ነገር አለሽ? ሁሉም ሰው ዳይት ላይ ነኝ ምናምን ብሎ ደህና ነገር አልበላሁም፡፡”
“ተይ እንጂ...! ዛሬም ዳይት ላይ ናቸው?”
“ታዲያስ! ለተቆራረጠ ሙዝ ሰማንያ ብር ይከፍላሉ... ዳይት ላይ ነኝ... መቀነስ አለብኝ ቅብጥርሶ ይላሉ፡፡ ምናለ ስለአንጎላቸው እንዲህ ቢጨነቁ......!”
“እኮ...! እና ታዲያ ምን ላምጣልሽ?"
“ሥጋ... ቅባት ያለው ነገር ምናምን... አታምጪብኝ! ትንሽ ጨምሬያለሁ ሰሞኑን ደግሞ...”
“ኧረ ተይ! ምንም አልጨመርሽም ቅድስትዬ! እንደውም ሳትከሺ አትቀሪም...”
“አይ ቲጂዬ...ቦዲ ሼፐር አርጌ ነው... ቦርጩን ጥፍንግ አድርጎ ስለያዘልኝ ነው...”
“ፓ! አሪፍ ነገር ነው ባክሽ... የት አገኘሽው? እኔ ፈልጌ ፈልጌ የሚሆነኝ አጣሁ...”
“መድኀኔ ዓለም ሞል ግራውንድ ፍሎር ላይ የሆነ ቤት አለ....
መዓት አላቸው... ዘጠኝ መቶ ብር ነው የገዛሁት... ብዙ አይመችም
ግን ቢያንስ ይሰበስብሻል... አብረን ሄደን ትገዣለሽ ሰሞኑን..."
“እሺ... አስታውሺኝ በቃ... ያስፈልገኛል.... በይ በቃ ሽሮ ላምጣልሽ
እንግዲህ....”
እሺ“ ቲጂዬ...”
ቅድስት የቀረበውን ሽሮ መብላት ጀመረች::
“ውይ ቲጂዬ! ሲጣፍጥ ግን ቅቤ ሞጀርሽበት”
“ሃሃ... ለዚያ እኮ ነው ሚጣፍጠው.."
“ልቀንስ እያልኩሽ ቅቤ ትግችኛለሽ አይደል... አንቺ ምን አለብሽ?”
“ብዪ ባክሽ... ከልኩ አያልፍም..."
“ምን? ቦርጭ?”
“አዎ....”
“ሃሃሃ!”
“ኧረ ቅድስትዬ ሳልነግርሽ... ዮጋ እኮ ጀመርኩ.... ቀጥ አላልኩብሽም ትንሽ?”
“ዮጋ?”
“አዎ... "
“ጎበዝ ነሽ ልጄ... እኔ አንዴ ከሰኒ ጋር ጀምሬ እናቴ... ሁለመናዬ ተላቀቀ፡፡ እሱን ለመጠገን አጥሚት እና መረቅ ስበላልሽ ነው ይሄን ቦርጭ እዚህ ያደረስኩት ቲጂዬ!”
ሃሃሃ... ቀልድሽ እኮ ደስ ሲለኝ ቅድስትዬ!”
አሹፊ አንቺ.... ይልቅ ማን በጣም እንደከሳ ገምቺ...”
እሌሊ..
ማ?
“እሌኒ እሌኒ? መርሻ?”
“እህ!”
“እንዴ? እንዴት አርጋ ከሳች በናትሽ?”
“ሙግግ ብላ መጣች ዛሬ... በሳምንት ሁለት ኪሎ እየቀነስኩ አሁን
ዓሥራ ሁለት ኪሎ ቀንሻለሁ አለችን...”
“ተይ ባክሽ... ያን ሁሉ ሰውነት እንዴት አድርጋ ናደችው በናትሽ?”
“የሆነ ቲቪ ላይ የሚታይ የዳይት ሾው አለ አሉ... እሱን አይቼ ሄጄ ነው አለችኝ...”
“ምን ቲቪ ላይ? እዚህ አገር?”
“አዎ...”
“እና ሄዳ ምን አደረጉላት?”
“ምግብ መጥነው ይሠሩልሻል አሉ... በወር አራት ሺህ ብር እከፍልና ምግቤን ይሠሩልኛል... አሽገው ቤቴ ድረስ አምጥተው ይሰጡኛል አለችኝ...”
“ተይ እንጂ... ምን ቲቪ ነው ልጄ?”
“ፋና መሰለኝ...”
“ለነገሩ እኔ እንዲህ ያለ ነገር ብዙም አይመቸኝ... ግን መቼ መቼ
ነው የሚታየው አለችሽ?”
“እንጃ... እሁድ መሰለኝ... ብቻ ምሳና እራት ዐስራ ሁለት መኮረኒ ተቆጥሮ ነው የሚሰጠኝ ብላ አሳቀችኝ!"
“ሃሃሃ... አትይኝም?”
“ሙች!”
“እና ግን አከሳት?”
በጣም... ምግቡ እህል ቅጠል አይልም፤ ግን ካከሳኝ ምን ቸገረኝ ምናምን አለችኝ...”
“ይገርማል... አምሮባታል በይኛ!”
“ያው መቼስ... ትንሽ ሙግግ ብላለች፣ ረኀብተኛ ነው የምትመስለው፤ ግን ቦርጭዋ ጠፍቶላታል፡፡ ለነገሩ ዛሬ ዕድሜ
ለብራዚል ሂውማን ሄር የማታምር ሴት አለች?”
“ልክ ነሽ እሱስ... ሂውማን ሄር ሴቱን ሁሉ እኩል አደረገው
እኮ.... ምን ዋጋ አለው... ጸጉር ጭንቅላት አይሆን!”
“እኮ!”
የሚገርመኝ ግን ብር ኖሯቸው እንኳን ደህናውን አይገዙም እኮ...
የኔን ዕይው አሁን ከጣልያን ነው ያስመጣሁት... ይኸው ሁለት
ዓመቱ ንቅንቅ አላለም... ከገዛሽ ደህና ነገር ነው... የሚልከሰከስ ሰው አልወድም እኔ...”
“እሺ... ሌላስ ምን አዲስ አለ ታዲያ!”
“ዝናሽም በስንት ጊዜዋ ዛሬ መጥታ ነበር!”
“ተይ እንጂ! እንዴት ናት?”
“አረጀችብኝ.... ጉስቁልቁል ብላለች... ያው እሷን ታውቂያታለሽ.በሜካፕ ኀይል ነው እንጂ እኮ ዕድሜዋ ሄዷል..."
“አዎ እሱስ... ምን ሜካፕ ብትለቀለቅ አንገቷ አሳልፎ ይሰጣት የለ...
ያ.. የአውራ ዶሮ ኩልኩልት የመሰለ አንገት..."
“አንቺ ተይ በስማም... ሃሃሃ!”
“ምን ላርግ ብለሽ ነው....? ደግሞ እኮ ሰው መልክ ባይኖረው ፀባይ
አይኖረውም?

👍1
#የቤተሰባችን_ፎቶ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
አቤት የቤተሰብ ፎቶዋችን ማማሩ የጥርሳችን ንጣቱ የሣቃችን ድምቀቱ!
አባዬ እበርበት ይመስል እኔን ጥብቅ አድርጎ አቅፏል፡፡ እማዬ ይበርባት ይመስል ናሆምን ጥብቅ አድርጋ አቅፋለች፡፡ እኔና ናሆም ያለን ጥርስ ሁሉ እስኪታይ ሥቀን ከእናትና አባታችን ሥር
እንደጉልቻ ቁጭ ቁጭ ብለናል፡፡
የሚያስቀና አራት ጉልቻ፡፡ ዕዩት የእማዬን ሣቅ!
አባዬ ሚስቱን ከሚደብደብበት ቀናት በአንድ ቦክስ ሲነርታት ያወለቀው ጥርሷ የት እንደገባ እንጃ፡፡ የሚታየው እህል ነክተው የማያውቁ የሚመስሉት ነጫጭ ጥርሶቿ ብቻ ነው፡፡ ለወትሮው
ዐይኖችዋን እንደ አጥር የሚከበው ደማቅ ጥቁር ብልዝ፤ ፎቶው ላይ የለም፡፡
አባዬ ፣
“ደሞ ምን ለመሆን ነው ልጅ ከወለዱ እንዲህ ዓይነት ልብስ መልበሱ” እያለ ስለሚቆጣት፣ ብዙ ጊዜ የማትለብሰውን ፡ እጅጌው ጥሩምባ አበባን የሚመስል መዐት አበቦች የፈሰሱበት ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ቀለሙ ዐይን የሚያደነቁር ቀይ ነው:: ከእድሜዋ ፈጥኖ
ለእርጅናና ማዲያት እጅ የሰጠው ፊትዋ በእጅ ሥራ ቆንጅቷል።
እማ ፍክት ብላለች፡፡ አበባ ነገር ሆናለች፡
አባዬን እዩትማ! ከእማዬ ጥርስ ድምቀት ጋር የሚፎካከር የወርቅ ቀለበቱ ብልጭታ፣ እጁ ላይ ትንሽ ፀሐይ ያለ አስመስሎታል። ይሄ አብረቅራቂ የጋብቻ ቀለበቱ ከማያልቀው ጭቅጨቃቸው ባንዱ ቀን፣እንዲያውም ያውልሽ! ካንቺ ጋር ያለኝ ትዳር በዚህ አብቅቷል”
ብሎ የሽንት ቤት ጉድጓድ የወረወረው ነው፡፡ እማዬ በምልጃና በልመና ጎትታ አወጣችው እንጂ!
የለበሰው ደማቅ ሮዝ ሸሚዝ፣ ከጥቁር በሮዝ መስመር መስመር
ከረቫቱ ጋር ፍጹም ተቀናጅቷል፡፡ ይሄን ከረቫት፣ ካንቺ የማያልቅ ጭቅጭቅ ለመገላገል በእዚህ ተንጠልጥዬ በሞትኩ!” እያለ እማዬን
የሚያስፈራራበትና አብዝቶ የሚለብሰው ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማታ ማታ፣ ያውም በተመሳሳይ ሰዐት ፤ ትልቅ
ስልኩን ይዞ እየተንሾካሾከ ወደ ሽንትቤት ሲሮጥ ሲሮጥ ብቻ የማውቀው ሣቁ ያምራል፡፡
ናሆምዬ፣
ቀኝ እጁ ፎቶው ከመነሳቱ ሰከንዶች በፊት የተቀማውን “ሎሊፖፕ”
ሰመያዝ እንደተስተካከለ ተንከርፍፎ ቀርቷል፡፡ የአባዬን ስልክ ነካክቶ
ለእማዬ መስጠት ከጀመረ ወዲህ፣ አባዬ ሊደልለው በየቀኑ የሚገዛለትን ሎሊፖፕ
ነበር የያዘው - እማዬ ፎቶ ውስጥ አይገባም ብላ እስክትነጥቀው
ክንፍ እስከሚያካክሉት ትልልቅ ጆሮዎቹ በተዘረጋው ሰፊ ፈገግታው መሀል በቀርብ የወለቀው ጥርሱ ትቶት የሄደው ክፍተት ይታየኛል፡፡ የእማዬን ወላቃ ጥርስ በጥበቡ የደፈነው ፎቶ አንሺያችን የናሆምን መርጦ መተዉ ገረመኝ፡፡
“ይሄን ሳተላይት ጆሮ የወረስከው ከአባትህ ነው... እሱን ጠይቀው
ትለዋለች እማዬ ፤ ትምህርት ቤት በጆሮዬ ትልቅነት ሳቁብኝ ብሎ እያለቀሰ ሲነግራት፡፡ ያለችውን አምኖ አባዬን ሲጠይቅ፣ የናሆም ጆሮ የዘር ግንድ፣ አዲስ የጭቅጭቅ ማገዶ ይሆናል፡፡ እነሱ
በጩኸት ሲጨቃጨቁ የሳሎኑን ጥግ ይዞ ሲያለቅስ የማየው ልብ ሰባሪ ፊቱ እዚህ የለም፡፡
እኔ፣
አርቴፊሻል ፈገግታዬ ለፊቴ እንግዳ የሆነበት አይመስልም፡፡ ጥርሴ
እንኳን፣ ከዓመት ጀምሮ ከትምህርት ቤታችን ሦስት አጥር ዘልሎ
ካለው መርኬ ጫት ቤት እየሄድኩ፤ ከብዙ ጎረምሶች ጋር ታጅዬ ጫት ሳሻምድና ሺሻ ሳጨስ እንደምውል አያሳብቅም፡፡
አገጬን ሊነካ ምንም ያልቀረው ቢትልስ ሹራቤ ትላንት መርኬ ጓዳ፣ ጥግ ካለው ፍራሽ ላይ፣ የሰሞኑ ጓደኛዬ መሳይ በአንገቱ ላይ የሰራውን የገድል ማስታወሻ ሸፍኖታል፡፡
አቀማመጤ እንደጨዋ ልጃገረድ ሰብሰብ፣ ቆጠብ ! ከረጅም ቀሚሴ ጋር የሚሄድ ነው፡፡ አባዬ፣ ድሮ ሁሉ ነገር እነግረው በነበረ ጊዜ ያቅፈኝ እንደነበረው ስላቀፈኝ፤ ከአስተቃቀፉ ጋር የድሮን
ንጽሕናዬን ለማምጣት ባደረግኩት ከፍተኛ ጥረት ያመጣሁት
አቀማመጥ አይመስልም፡፡
ያቀፈኝ እጁን አያያዜ፣ ጥብቅ ያለና አትልቀቀኝ የሚል ይመስላል፡፡
“አባዬ መልሰኝ... አባዬ ልጠፋ ነው መልሰኝ” የሚል፡፡ ከቤታችን
ሰላም ጋር አብሮ የጠፋው ጨዋነቴን በአባቴ እቅፍ ውስጥ እፈልግ
ይመስል የምለምነው ይመስላል፡፡
...አቤት የቤተሰብ ፎቶዋችን ማማሩ! የጥርሳችን ንጣቱ! የሣቃችን ድምቀቱ!
.
የምፈልገው ቤተሰብ ፎቶዋችን ላይ ያለውን ነው፡፡
የምመኘው ቤተሰብ ፎቶዋችን ላይ ያለውን ነው፡፡
አሁን አሁን የምጸልየው፤ ፎቶው ላይ እንዳለው ያለ ቤተሰብ
እንዲሰጠኝ ብቻ ነው፡፡
💫አለቀ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏

🥰1