#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
...ወደ ደብረዘይት በራሴ መኪና ለመሄድ የወሰንኩት ከነጋ ቡኃላ ነው፡፡አባቴ ሀሳቤን ተቃውሞኝ ነበር…
‹‹ህብረት የመፍጠሪያ እና ወዳጅነትን ለማጎልበት ታስቦ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ለብቻ ተገንጥሎ መሄድ ጥሩ ስሜት አይፈጥርም ››አለኝ.
‹‹እንዴ ምን ችግር አለው..?››
‹‹ችግርማ አለው… አንዳንዴ ማድረግ ስላቻልሽ ብቻ ሁሉን ነገር የግድ ማድረግ አይኖርብሽም…አንቺ በግል መኪናሽ ስትሄጅ ሌሎች የስራ ባለደረቦችሽ ላይ ምን አይነት ስሜት ነው ሊፈጥር የሚችለው….በተለይ እኔ እና አንቺ ለእንዲህ አይነት ጉራ ስንል ያለንን ነገር መጠቀም አያምርብንም››አለኝ
‹‹እንዴት አባ..? ለምን …...?ማን ይከለክለናል..?››ጥያቄዬን ደረደርኩለት
‹‹የእኛ አይደለማ ..ሰርተን የገዛነው መኪና አይደለም..የእናትሽ ላብ ነው››
‹‹እንዴ…. !!!እናቴ ታዲያ የእኔ አይደለች..?››
‹‹…እናትሽ ያንቺ ነች ማለት ንብረቷ ሁሉ ያንቺ ነው ማለት አይደለም…››
‹‹አባ አንተ ደግሞ..ደግነቱ እናቴ እንደአንተ አታስብም…›› ሀሳቡ ውስጤ ገብቶ ቢቧጥጠኝም ምክሩን ሰምቼ ግን መኪናውን ጥዬ ለመሄድ አልፈለኩም…..መኪና መያዜ ከሰውዬው ጋር ላለኝ ወሳኝ ፊልሚያ ያግዘኛል የሚል ግምት አሳድሮብኛል፡፡እና ቀድሜ ደብረዘይት በመድረስ የተቀበልኳቸው እኔ ነኝ፡፡ቡድኑ ያረፈው ቢን ኢንተርናሺናል ሆቴል ነው፡፡ለአለቅዬ ብቻ ሆቴሉ አይመጥነውም ተብሎ አሻም አፍሪካ ሆቴል ነው የተያዘለት…ሰው ሁሉ እንደ አመዳደቡ ሁለት ሁለት እየሆነ በየክፍሉ እየገባ ባለበት ሰዓት እኔ ሆቴሉ በረንዳ ላይ አረፍ ብዬ ማኪያቶ ነገር በመጠጣት ላይ ሳለው አቶ ሰይፉ ወደእኔ መጡ…..
‹‹ፌናን ላስቸግርሽ ነው..?››
‹‹ምነው ምን ቸገሮት..?››
‹‹ባክሽ ሰውዬችን መኪናዬ ተበላሽታብኝ አጉል ቦታ ቆሚያለው ብሎ ደወለልኝ ..…ሚኒባሶ መካኒክ ፍልጋ እስክትሄድ እዛ እንዳይቸገር ባንቺ መኪና ሄደሽ ብታመጪው…..መኪናውን ልጆቹ አሰርተው ያመጡለታል››
‹‹ችግር የለውም እርሶ አዘውኝ እንዴት እምቢ እላለው ››ብዬ ከመቀመጫዬ ተነሳውና መኪናዬን ወደአቆምኩበት ሄድኩ….አጋጣሚው ደስ ብሎኛል…ገቢና ከጎኔ አስቀምጬ እየነቆርኩት ይዤው መጣለው…ሀሳቤ እንደዛ ነበር..
ስደርስ ያላሰብኩት ነገር ነው የገጠመኝ… ከሰው ጋር ነው…ደስ አላለኝም..ለምን ደስ አላለኝም…..?አይ እንዲሁ ይመስለኛል..በቃ አለ አይደለ ብቻውን ነው ብዬ ሰለገመትኩ መደናገር ተፈጥሮብኝም ይሆናል…፡፡
መኪናዬ አቁሜ ወደ እነሱ እየሄድኩ ነው ያሰብኩት…ከእነሚስቱማ አልጭነውም….ይዣቸው ከመሄዴ ለመገላገል የመኪናዋን ብልሽት ቀላል ከሆነ እስኪ ልየው…እድሜ ለአባቴ የመኪና የአካል ክፍል ብትንትን አድርጌ እንዳውቅ አድረርጎኛል…ጫን ያለ ብልሽት ካልሆነ በስተቀር የእኔንም ሆነ የአባዬን መኪና ቱታዬን ለብሼ መሬት ላይ እየተንከባለልኩና በዘይት እየተጨመላለቅኩ የምጠግነው እና ሰርቢስ የማደርገው እራሴው ነኝ….
እሱ ባለበት አቅጣጫ ወደመስኮቱ ተጠጋው..እኔን በማየቱ እጅግ ደንግጦል…እንደህጻን ልጅ ነው የተረብተበተው..እንደዛ ሲርበተበት ደግሞ እኔ ውስጤ እንዲቁነጠነጥና ..መቁነጥነጤን ተከትሎ እንድሾርበት አስገደደኝ..፡፡ያው እንደከዚህ ቀደሙ.. ከዛም ትንሽ ከፍ ባለ ደረጃ ተሸቀርቅሯል…፡፡መቼስ የካምፓኒ ማናጀር ለመሆን ከመዳከር ይልቅ ፕሮፌሽናል ሞዴል ለመሆን ትንሽ ቢጥር አመት ሳይሞላ የሀገሪቱ አይኖች ሁሉ ማረፊያ ይሆን ነበር….፡፡እሷም ቆንጅዬ ነች …አዘናነጧ ግን ጭንቀት የወለደው አይነት ይመስላል…እሱን ላለማሳጣት እየጣረች በሚመስል ሁኔታ....፡፡ግን ምን ማለቴ ነው....?እየተናገርኩ ያለውት እኮ ትርጉም የሚሰጥ አይነት አይደለም..፡፡ጭንቀት ያለበት አዘናነጥ ማለት ምን ማለት ነው…..?እንደውም እኔ ስለእሷ የሰጠውት አስተያየት ይመስለኛል ከጭንቀት የተወለደው…፡፡ለማንኛውም የመኪናውን ኮፈን አስከፍቼ ስመረምረው ብልሽቱ አስቂኝ ነበር…ለማስተካከል ግማሽ ደቂቃ አልፈጀብኝም…እንደዛ በመሆኑ ደግሞ የተሰማኝ ስሜት ልነግራችሁ አልችልም…
…. አሁን ከኃላ እየተከተልኳቸው ነው…..በእስፖኪዬ ወደኃላ እያየኝ መሆኑን በደንብ አውቃለው…ከተማ ውስጥ ገብተን ጌትሼት ጋር ስደርስ ነበር ሚኒባሶ መካኒክ ይዛ ስትመጣ አግኝተን የመለስነው…..
የመጀመሪያው ፕሮግራም ከምሳ ግብዣ ነበር የሚጀምረው...እዛው ብዙሀኑ ያረፈበት ሆቴል እየተጫወትን ከበላን ቡኃላ በወጣው ፕሮግራም መሰረት በከተማዋ መታየት ያለባቸውን ቦታዎች ወደማየት ነው ያመራነው …ስምንት ሰዓት ሲሆን ተንቀሳቀስን፡፡
መቼስ ቢሾፍቱን ስትጎበኝ በዋናነት በሁሉም አዕምሮ ሚመጣው ሀይቆቾ ናቸው..ቢሾፍቱ ፤ሆራ ፤ባቦጋያ ፤ኩሪፍቱ፤ጨለቅለቃ.. መቼስ መታደል ነው…አንድ መለስተኛ ከተማ ይሄ ሁሉ ሀይቆች ባለቤት መሆን በራሱ ትልቅ ድልብ ሀብት ነው፡፡ለከተማዋ ብቻ አይደለም ለሀገሪቱም ጭምር..፡፡በዛ ለይ ከመዲናዋ 50 ኪሎ ሜትር ብቻ እርቃ መገኘቷ….ለአንድ ቀን እንኳን ለስራ ወደሀገሪቱ የመጣ ሰው ጎራ ብሎ አንድ ሁለት ሰዓት ዘና ብሎ ሊመለስባት በሚችልበት ቦታ ላይ መገኘቷ ሌላ እድል ነው…ግን ከተማዋም ሆነች ሀገሪቱ 5 ፐርሰንቱን እንኳን አልተጠቀመችበትም…አለም አቀፍ ቱሪስቶችን በልዩ ሁኔታ እንዲስብ ተደርጎ ፕሮሞሽን አልተሰራለትም… ፡፡ሌሎች ሀገሮች መሰል የተፈጥሮ ፀጋ ባለመታደላቸው አርቴፊሻል ወንዝ እና ሀይቅ በመስራት የቱሪስት ገቢያቸውን በሚያጧጡፈበት በዚህ ቴክኖሎጂ በመጠቀበት ዘመን እኛ ግን ተፈጥሮ በቸርነቷ የለገሰችንን የነፃ ችሮታ እንዲሁ ባልባሌ ሁኔታ ለዘመናት በማባከነ ስንዴ እንለምናለን…ያሳዝናል፤የእኔ ነገር ሳላስበው ወደንጭንጬ ገባው…ለዛውም በዚህ ዘና በማያ ቀኔ… ..ቅድሚያ ሆራ ሀይቅ ነው የሄድነው…ሆራ በከተማዋ ካሉት ሀይቆች በስፋት ትልቁ ነው..ዙሪያውን በተራራ የተከበበ ሲሆን ተራራው ላይ ደግሞ ዘመናዊ የሚባሉ ሎጆችና ሆቴሎች አልፎ አልፎም ቢሆንም ታንፀው ወደአካባቢው ለመዛናናት የሚመጡትን ቱሪስቶች ሆነ ሀገርኛ ቱሪስቶችን ለማስተናገድ እየሞከሩ ነው ፡፡አሪፍ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው ..አብዛኛው በጀልባ ባህሩን ሰንጥቆ በመጓዝ ተዝናንቷል....12 ሰዓት ወደየአረፍንበት ሆቴል ነው የተመለስነው..ለማታ እራት ፕሮግራም ለመዘጋጀት….የእራቱ ፕሮግራም ፕራሚድ ሆቴል ነው የሚከናወነው፡፡አንድ ሰዓት ሁሉም እዛ ተሰባስቦ መገኘት አለበት፡፡
አንድ ሰዓት ከሩብ ሲል ፕራሚድ በሚገኝ የስብሰባ አዳራሽ ሁሉም ስታፎቻችን ቦታቸውን ይዘው ለፕሮግራሙ ዝግጁ ሆነው ነበር…ልክ እንደባለፈው አመት ዘንድሮም የፕሮግራሙ መሪ እኔ ስለሆንኩ ወደ መድረኩ ወጥቼ ሁሉንም አንዴ ቃኘው…የካምፓኒው ከፍተኛ ሀላፊዎች አለቃዬንና ሚስቱን በግራና ቀኝ አጅበው የፊተኛውን ረድፋ ላይ ተደርደረረዋል፡፡
ጉሮሮዬን አፀዳዳውና ማይኩን ፈታትሼ ንግግሬን ጀመርኩ…
‹‹››የተከበሩ የድርጅታችን ስራ አስኪያጅ ፤ እኛን አክብረው በመሀከላችን የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ የተከበሩት የስራ-አስኪያጃችን እጮኛ….የተከበራችሁ የስራ መሪዎችና ድንቅና ምርጥ የካማፓኒያችን ሰራተኞች እንኳን ለዚህ አመት የካማፓኒያችን ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ …አደረሰን፡፡…››
አደራሹ በጭብጨባ ተናጋ…
ፋታ ወስጄ ንግግሬን ቀጠልኩ፡፡
…የዚህ ዓመት በዓላችን ከዚህ በፊቱ የተለየ ይሆናል ፡፡አንደኛ በዓላችን ነው..ሁለተኛ ወጣቱንና እና ካምፓኒያችንንም ሆነ የእያንዳንዱን ሰራተኛ የግል ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋሉ ብለን ሁለችንም ተስፋ

👍1
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
#ፍሰሀ
...ከአዳራሹ ሳይሆን ትንሽ ወደኃላ ተመልሼ ልጀምርላችሁ፡፡ እስከ አሁን አዋዋላችን በጣም ግሩም የተባለ ነበር..ከተለያዩ ሰራተኞችም ጋር በየምክንያቱ የመነጋገር ስሜታቸን ማዳመጥ፤ የመቀላለድ እና እስከዛሬ ከነበረው በተሸለ የመግባባት አጋጣሚውን ስንጠቀምበት ነበር የዋልኩት…ከፌናን ጋር ግን ከሩቁ ከመተያየት በስተቀር ፊት ለፊት የመገናኘቱ አጋጣሚ አልነበረም….ምን አልባት ሰላም ያዋልኩትም እንደዛ ስለሆነ ይሆናል..የማታውን ፕሮግራም ለመጀመር አዳራሽ ከገባን ቡኃላ ከቀኑ ከነበረው አለባበሷ በተቃራኒ በጣም ረጅም ግን ደግሞ በተመሳሳይ ውብ ያደረጋትን ደማቅ ቀይ ቀሚስ ለብሳ ወደመድረኩ ስትወጣ ነበር ያየሆት…
ምትፈልገው የሆነ ዕቃ ኖሮ እሱን ለመውሰድ ወደ መድረክ የወጣች ነበር የመሰለኝ ግን ተሳስቼ ነበር… ፊት ለፊት ቆማ …ልክ ለአመታት የመድረክ ልምድ አንዳለው ፓለቲካኛ በሙሉ በራስ መተማመን ንግግሯን ጀመረች….እኔ እራሱ ምን አይነት እንከፍ ነኝ..እስኪ ቀደም ብዬ ፕሮግራማቸውን ባየው..እርግጠኛ ነኝ ከአስር ደቂቃ ባፊት እንኳን አውቄ ቢሆን እዚህች መድረክ ላይ እንድትወጣ ፈጽሞ አልፈቅድላትም ነበር…. ከመጀመሪያው ንግግሯ ነው የነገር ጦሮን በስውር የወረወረይብኝ..እስኪ እዚህ ሁሉ ሰው መካከል አቶ ፍሰሀና እጮኛቸው ማለት ምን ማለት ነው……..?እጮኛዬ ትሁን አትሁን አልነገርኮት ከየት አባቷ አወቀች…..?አቤት ወስጤ እንደተቃጠለላችሁ ..ሰውነቴ ሁሉ ሲንቀጠቀት ይታወቀኛል…ደግሞ ይህቼ ከጎኔ የተቀመጠችው መፍለቅለቅ ምን የሚሉት ነው…?የማንም ስርዓት አልባ መድረክ ላይ ወጥታ በዘጠና ምናምን ሰዎች ፊት‹‹.. የፍሰሀ እጮኛ… ››ብላ ስለተናገረችላት የእውነት እጮኛዬ የሆነች መሰላት እንዴ..?አናደደቺኝ……..
ከዛ አስተዳዳሪው ወጣ..የካማፓኒውን ሪፖርት እያቀረበ ቢሆንም ምን እንደለ አንዱንም አልሰማው…እያብሰለሰልኩ ያለውት ስለእዛች የተረገመች ልጅ ነው…እንዴት አድርጌ ነው አንገቷን ላስደፋ የምችለው….…እግዜር ይስጠው ሽማግሌው ሪፖርቱን አላንዛዛውም…ጨርሶ አመስግኖ መድረኩን ለዛች እብድ ለቀቀላት….እሷ ማለት ያቺ የተረገመች ወጥታ ስትናገር ብዙም ቁብ አልሰጣዋትም ነበር ..ግን ሽማግሌው ያቀረበውን ሪፖርት እያብራራች እየበታተነች ሳልወድ በግድ እየመረረኝ እንድሰማውና አደረገች…
ከፍተኛ ጥቃት ነው የተፈፀመብኝ ..በእኔ ብቻ አይደለም በካማፓኒውም…..ሰራተኞቹን ጠቃሚ ከሆኑት በላይ ጠቃሚ እንደሆኑ እዲሰማቸው…በትዕቢት ልባቸው እንዲወጣጠርና ነገሮች ለእኔ ከባድ እንዲሆኑብኝ ያሴረችው ሴራ ነው በእያንዳንዱ የዋህ ሰራተኛ አዕምሮ በጥበብ የበተነችው ..አዎ ንግግሯን ሰምተው ያጨበጨብላት ሰራተኞቹ የተናገረችው ሁሉ ለእነሱ አስባ ይመስላቸዋል…የእሷን ሴራ እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው…እንደውም እሷን ማባረሬ በጣም ትክክለኛ ውሳኔ ነው..እና ይቅር ብያት እንድትመለስ የማስበውን ነገር ትቼዋለው..ለዚህችማ አይገባትም…ይህቼ ወጥ ረጋጭ ካቅሟ በላይ የምትንጠራራ… መኪና ተከራይታ ወይም ደግሞ ከሹገር ዳዲዋ ተውሳ እዚህ ይዛ በመምጣት ለመጎረር የምትጥር ከአቅም በላይ ለመኖር ስቃዬን ለምታይ ሴት ማዘን…
ወደመድረክ ስትጋብዘኝ የውስጥ ስሜቴ እየተተረማምሰ ነበር…የተዘጋጀውበትን ንግግር ሁሉ ቃላቶች ብትንትን ብለው ከአዕምሮዬ ተሰደዋል…ብቻ በደመነፍስ ወጣውና ወደጆሮዋ ጠጋ ብዬ‹‹በጣም በጣም ባለጌና መሰሪ ልጅ ነሽ ››አልኳት…ቆሽቴን እንዳሳረረቺኝ ቆሽቷን ላሳርርረው ብዬ..እሷ እቴ ምን በወጣት የመረቅኳት ይመስል ፈገግ ብላና ድምጽን ለሁሉም እንዲሰማ አድርጋ ‹‹አመሰግናለው አቶ ፍሰሀ …በእውነት ለካምፓኒዬ እና ለምወዳቸው የስራ ባለደረቦቼ ከዚህ በላይ መናገር ችዬ ብናገርና ባገለግል ደስ ይለኛል››ብላ ጭራሽ ያረረው ቆሽቴ እንዲከስል አድርገ መድረኩን ለእኔ በመልቀቅ ከኃላዬ ቆመች….
❤️ፌናን
የማታውን ፕሮግራም አትጠይቁኝ…ብዙሀኑ የተደሰቱበት እኔና ሰውዬው በየምክንያቱ በተገናኘን ቁጥር ስንጠዛጠዝና ስንነቋቆር ያሳለፍንበት ገራሚ ምሽት ነበር…በተለይ ፍቀረኛው የእኛኑ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ስትከታተልና ስትጠብቀን ነው ያመሸችው…አራት ሰዓት ሲሆን ይዛው ትሂድ ወይም ይዟት ይሂድ አላውቅም ብቻ ተያይዘው ወጡ….ወደ ማደሪያቸው…
እኔም ከ30 ደቂቃ ቡኃላ ቡድኑን ተለይቼ ወደማደሪያዬ ሄድኩ…..ገብቼ አልጋዬ ላይ እንደተዘርርኩ ነበር እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ ያለው....ትንሽ መጠጥ የቀማመስኩ ጊዜ እንዲሁ ነው የሚያደርገኝ…ክፋቱ እንቅልፌ ቶሎ ያልቅብኛል…ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ ሙለ በሙሉ እንቅልፌን ጨርሼ ፈጠጥኩ…እዛው እየተገላበጥኩ በውስጤ የሚተረማመሰውን ሀሳብ ማመንዠግ ቀጠልኩ… በዚህ ውድቅት ለሊትም ሀሳቤ ስለእሱው ነው….ምን እየሰራው ነው…….?ከልጁ ጋር ምን እንደዚህ አይነት ጫወታው ውስጥ አሰጋባኝ..….? እሱ አልሸነፍ ባይ ስለሆነ ነው..ወይስ እኔ የማሸነፍ ሱስ ስላለብኝ….….?ነው ወይስ ቀጥታ ከአላማዬ ጋር የሚገናኝ ትግል ነው…….?እንዴት እንደዛማ አይሆንም የእኔ ዓላማ በእሱ መሸነፍ ላይ እንደማይመሰረት እርግጠኛ ነኝ..እና ምንድነው ችገሬ…….?ይሄንን ሳስብ የለበስኩትን አንሶላና ብርድልብስ ከላዬ ገፍፌ ከአልጋዬ ወረደኩ….አፍቅሬው ብቻ እንዳይሆን…….?ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ…….?ቆይ እስኪ ፍቅር እንዴት ነበር..….? አውቃለው እንዴ…….?
በሀያ አመቴ አካባቢ አንድ ሁለት የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ጋር ፍቅር ፍቅር መጫወት ጀምሬ ነበር..ግን እኩዬቼ ቢሆንም እኔ በማስበው ልክ ሊያስቡልኝ ስላልቻሉ..እኔ ፍቅርን በምተረጉምበት ልክ ሊተረጉሙልኝ ሳላልቻሉ ከአንዱ ጋር አንድ ወር ከሌለኛው ለሶስት ወራት ብቻ ነበር አብረን መዝለቅ የቻልነው…፡፡ያው ወንዶች ከሴት በእኩል ዕድሜ ሊበስሉ እንደማይችሉ ዘግይቼ ነው የተረዳውት…ማለት ያው የ18 ዓመት ሴት አንድ ቤትን እማወራት ሆና በደንብ ማስተዳደር ትችላለች አንድ የ18 ዓመት ወንድ ግን እራሱንም የማስተዳደር ብቃት ላይ አይደርስም…የድሮ አባቶቻችን እንዲሁ በዘፈቀደ አይደለም ወጣቶችን ሲያጋቡ ቢያንስ ወንዱ ከሴቷ በ5 ዓመት ቢበልጣት ጥሩ እንደሆነ የሚመክሩት እና እንደዛም እንዲሆን በተቻላቸው መጠን የሚጠነቀቁት…
የእሳትነቱን ዘመን ካለፍኩ ቡኃላ ደግሞ ፍቅርን በተመለከተ አንድ ቅድመ ሁኔታ ለራሴ አስቀመጥኩ… የማፈቅረው ሰው እኔ እንደምወደው እሱ ግን እንክትክት እስኪል ድረስ እንደሚያፈቅረኝ እርግጠኛ ስሆን ብቻ ነው እጄን ዘርግቼ ልቀበለው የምችለው፡፡ይሄን ለምን እንዳልኩ ማስረዳት አለብኝ መሰለኝ..ወንድ ልጅ በደንብ እንዳፈቀራት እርግጠኛ ሳትሆን እጇን የሰጠችና ወደጋብቻ የገባች ሴት ብዙ ጊዜ ከሳሪ ነች፡፡ምክንያቱም አብዛኛቹ ወንዶች የፍቅር ጫፍ ላይ የሚደርሱት በመጀመሪያዎቹ የፍቅር ጊዜያቶች ነው…ከዛ ወደግንኙነት ሲገቡ ፤ ከዛም አልፎ ወደ ትዳር ሲሸጋገሩ የማፍቀር መጠናቸው እየወረደ ነው የሚመጣው..ቢያንስ በግንኙነት ፍቅር ላይ የነበረ ስሜቱ ወደ ትዳር ሲገባ መውደድ ላይ አርፎ እንዲረጋጋ ከፍቅር መጀመር አለበት....ለሴት ልጅ ግን ተቃራኒው ነው ፡፡በግንኙነት እና በመላመድ ስሜቷ እያደገና እየጎለበተ ነው የሚመጣው.. ፡፡ በግንኙነት ወቅት መውደድ ከቻለች፤በትዳር ውስጥና በመላመድ ወደላይ ነው የምታሳድገው ወደፍቅር …አብዛኛዋ ሴት እንደዚህ ነች…እና እኔም የምወደውን እና እሱ ደግሞ የሚያፈቅረኝን እንዳገኘው እርግጠኛ እስክሆን ድረስ ለማንም ልቤን ከፍቼ አልሰጥም፡፡ለዚህ ፍሰሀ ለሚባለውም ቢሆን

👍3❤1