አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ሰዓቱ 11.10 ነው።22 አንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብላለች።ብቻዋን ነው ያለችው...ስልኳን አወጣችና ደወለች።
‹‹ሀይ ቃልዬ እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁ ልዩ ደህና ነሽ?››
‹‹አለሁ ...ከስራ አልወጣህም እንዴ?››
‹‹ወጥቼያለሁ ..መገናኛ ነኝ።››
"ለምን መክሰስ አልጋብዝህም 22 ነው ያለሁት"
"ደስ ይለኝ ነበር.. ግን አሁን ጊፍቲ ደውላ  ሰፈር እየጠበቅኩህ ነው ስላለቺኝ ወደእዛው ልሄድ ነው"እንደዛ ያላት አውቆ ነው…ልዩ እንገናኝ ካለችው ጊፍቲንም ይዟት ሊሄድ ስለፈለገ ነው…
"ሰፈር ማለት አንተ ቤት ?"
‹‹አዎ"
‹‹ለምን ይዘሀት አትመጣም..እንደውም አሪፍ ነው?"
አንዳሰበው ስለሆነለት ፈገግ አለ"ልጠይቃትና መልሼ ልደውልልሽ"

"እሺ ቃልዬ...እዛው ቁጭ ብዬ ጠብቃለሁ"አለችውና ስልኩ ተዘጋ። ከጨጓራዋ አካባቢ የተነሳ ቃጠሎ  ጉሮሮዋ ድረስ ሲሰማት ታወቀት፡፡

ቃል የልዩን ስልክ እንደዘጋ ወደ ጊፍቲ ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ ቃለዬ..፡፡››
‹‹አለሁልሽ ጊፍቲ.ላግኝሽ?››
‹‹ደስ ይለኛል..መክሰስ ልትጋብዘኝ ነው ወይስ እራት?››
‹‹አይ መክስ ነው.. ግን ጋባዡ እኔ አይደለሁም.›
‹‹ችግር የለውም እኔ ጋብዝሀለው››
‹‹አይ ጋባዥ አለን›
‹‹ማን?››
ልዩ ደውላልኝ ነበረ ..ልጋብዛችሁ ስላልች ነው የደወልኩልሽ››
ቅሬታዋን መደበቅ አልቻለችም‹‹ቃል ግን እሷ ልጅ…››አንጠልጥላ ተወችው፡፡
‹‹እሷ ልጅ ምን…?››
‹‹እኔ እንጃ ነገረ ስራዋ አያምረኝም…ሌላ አላማ ያላት ይመስለኛል››
እንዳልገባው ሆነ‹ሌላ አላማ ስትይ..?››
‹‹ያው ማለቴ ምትወድህ ይመስለኛል..››
ደስ አለው…..አዎ ቅናት እየጀመራት ነው ሲል አሰበ..‹‹ብትወደኝ ምን ችግር አለው? ጓደኛዬ አይደለች..››
‹‹ቃል ደግሞ… እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም.ምታፈቅርህ ይመስለኛል.ደግሞ ይመስለኛል አይደለም እርግጠኛ ነኝ…››

‹‹አረ ተይ .እኔ ምንም እንደዛ አይነት ስሜት አላየሁባትም.ደግሞ ፍቅረኛዬ እንደሆንሽ ነግሬታለሁ እኮ››
ቢሆንም ተጠንቀቃት.ለማንኛውም የት ነህ ልምጣ.››ያለበትን ቦታ ነገራትና በፈግታ ስልኩን ዘግቶ ለልዩ እንደሚመጡ ለመናገር ደወለላት፡፡

"ይህቺ ጊፋቲ የምትባል ሴት እንዴት ላስወግዳት?"ልዩ እራሷን ጠየቀች... ...ስልኳ ተንጫረረ ..ቃል ነው.. ቀና መልስ እንዲመልስላት በውስጧ እየፀለየች አነሳችው፡፡
"እሺ ቃል?"
"15 20 ደቂቃ እናስጠብቅሻለን።
"ችግር የለውም አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቃችኋለው"አለችና በደስታ ያለችበትን ካፌ ስም ነግራቸው ስልኳን ዘጋችው፡፡

በራሷ ሁኔታ  መገረም ጀመረች"ወይ ጉዴ.. አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቃችኃለው"ስል አሁን መድህኔ ቢሰማ ጭንቅላቱን ይዞ ነው የሚጮኸው...›አለች እንዲህ ልትል የቻለችበት ምክንያት  5 ደቂቃ አረፈድክ ብላ ብዙ ቀን ጮኸበታለች...አስር ደቂቃ አርፍዶ ቀጠሮውን ሰርዛ ጥላው የሄደችበትም ቀናቶች ጥቂት አይደሉም።  

እንዳሉትም ከ20 ደቂቃ በኃላ እጅ ለእጅ ተያይዘው ፊቷ ተከሰቱ፡..መጀመሪያ ልክ እንደረጅም ጊዜ የልብ ጓደኛዋ እሷ ላይ ተጠመጠመችባት ..አገላብጣ ጉንጮቾን ሳመቻት...ጊፍቲ ያልጠበቀችው አይነት አቀባበል ስለሆነ  ግር እንዳላት    ከሁኔታዎ ያስታውቃል...እሷ እራሷ ለምን እንደዛ ኦቨር አክት እንዳደረገች አልገባትም ‹‹...ምን አልባት የይሁዳን መሳም ይሆናል የሳምኳት..››ስትል እራሷን ታዘበች፡፡.ቃልን ከእሷ መለስ ባለ  ሰላምታ  ሰላም አለችውና ሁለቱም ከፊት ለፊቷ ወንበር ስበው ሊቀመጡ ሲሉ‹‹..አይ ቆይ እንውጣ"አለቻቸው፡፡

"ምነው ታሳፍሪኛለሽ ..መክሰስ ትጋብዘናለች ብዬ እኮ ነው ይዤት የመጣሁት..መክሰሱ ቢቀር ቢያንስ ሻይ ጋብዢን እንጂ"ሲል ቀለደ

"አይ የመክሰሱን ሰዓትማ አሳለፍችሁት  አሁን የእራት ሰዓት ነው...እራት የሚገኝበት ቤት እንሂድ.."

‹‹እሱ የተሻለና የተቀደሰ ሀሳብ ነው"አለች ጊፍቲ ...

ተያይዘው ወጡና  መኪናዋ ውስጥ ገቡ… ወደ ዪሆሚያ ክትፎ ቤት ይዛቸው ሄደች ...እዛ ገብተው እስፔሻል ክትፎቸውን አዘው ቀላል ጫወታዎችን እየተጫወቱ ..በልተው ሲያጠናቅቁ አንድ ሰዓት ከሩብ  ሆኖ ነበር። ሂሳብ ልትከፍል ስትጠይቅ ተከፍሏል አሏት...ልቆጣጠረው የማትችለው ንዴት ተናነቃት፡፡..

‹‹ማን ነው የከፈለው ...?››ፊት ለፊቷ ያሉት ቃልና ጊፍቲ ላይ አፈጠጠችባቸው።ሁለቱም ደንግጠው እርስ በርስ ተያዩ   ..."አረ ተረጋጊ እኛ አልከፈልንም"አለት ቃል።
"ማን ነው የከፈለው?"አስተናጋጅን ጠርታ  ጠየቀችው፡፡

"ጋሽ መድህኔ ነው"

ተረጋጋች"እሱ ደግሞ ከእዚህ ቤት አይጠፍም" ስትል በውስጧ አልጎመጎመች፡

"መድህኔ ማን ነው?"ብላ ጠየቀቻት

‹‹ እስቲ አሁን ሆነ ብላ እኔን ለማሳቀቅ ካልሆነ የመድህኔ ማንነት ምን ይረባታል..? በውስጧ ነው ምታወራው…ቀና ብላ ቃልን ስታየው እሱም የመድህኔን ማንነት ለማወቅ የጓጓ መሆኑን በሚያሳብቅ  አስተያየት ነው እያየት ያለው..ለተጠየቀችው ጥያቄ መልስ ከመመለስ ውጭ ሌላ ምርጫ እንደሌላት ግልፅ ሆነላት፡፡ምን ብላ ትመልስ…ግራ ገባት" መድህኔ ጓደኛዬ...ማለቴ ፍቅረኛዬ ነው"አለች፡፡

‹‹የት አለ አስተዋውቂና አረ ጥሪው"ጊፍቲ አሽቃበጠች….፡፡

ልዩ አሁንም የሆነ ነገር ለማድረግ ከአባቱ ፍቃድ እንደሚፈልግ ህፃን በቆረጣ ቃልን አየችው፡፡

ቃልም ልክ ከዚህ በፊት መድሀኒ የተባለወን ስም እንዳልሰማ በማስመሰል "አዎ ጥሪውና እናመስግነው...በዛውም እንተዋወቀዋለን"አላት

"ደወለችለት"

"አንተ የት ነህ?"

"ውስጥ ነኝ ..እጄን እየታጠብኩ"

‹‹ታዲያ ሰላም አትለንም እንዴ?"

‹‹መጣሁ"ከ3 ደቂቃ በኃላ መድህኔ እንደወትሮ ዝንጥ ብሎ በሱፍ እንደታነቀ ፊት ለፊታችን ገጭ አለ...

‹‹ተዋወቁት መድህኔ ማለት እሱ ነው"በየተራ እየጨበጠ ተዋወቃቸው..

"ስለተዋወቅኩህ ደስ ብሎኛል...ልዩ ግን ይሄን የመሰለ ሸበላ ባል እንዳለሽ ለምን እስከዛሬ ደበቅሽኝ?"አለቻት ልዩ ተሸማቀች፡፡ የጊፍቲን ንግግር ለሚሰማ ሰው የሁለቱ ትውውቅና የጓደኝነት ታሪክ አመታትን ያስቆጠረ  ነው ሚመስለው? ልዩ ከውስጧ እየታገለች ዝም አለች

..ቃል ‹‹ቁጭ በላ›› አለው ቦታ እያመቻቸለት

"ቆይ ጓደኞቼን ተሠናብቼ ልምጣ ››አለ

ልዩ ግን መድሀኔ ተመልሶ እንዲመጣና እንዲቀላቀላቸው  ስላልፈለገች..."አይ ለምን እኛም እኮ ልንወጣ ነው"አለችው፡

"እኮ 2 ደቂቃ ብቻ ጠብቁኝና አብረን እንወጣለን ..እንዴ ክትፎ በልቶ ደግሞ አንድ ሁለት ሳይባል ቢገባ ጥሩ አይደለም...እራት እኔ አይደል የጋበዝኮችሁ አንቺና ጓደኞችሽ ደግሞ መጠጥ ትጋብዙኛላችሁ ...››ብሎ መልስ ሳይጠብቅ  ዞሮ ሄደ...ሳታስበው እንደውም ጥሩ ሀሳብ ነው..

ወደእነ ቃል ዞራ "ሰዎች እንግዲህ ቻሉት.. መድህኔ ካለ አለ ነው "አለች

ጊፍቲ"እንዲህ አይነት ድንገተኛ ግብዣ ተገኝቶ ነው...ጭፈራ ቤት ብንሄድ ደግሞ እንዴት ደስ ይለኛል መሰለሽ" ስትል ተቅለብልባ መለሰችላት..ቃል ዞር ብሎ አያትና"በቃ አንቺና ጭፈራ መች ነው የምትለያዩት"አለ፡፡

"ጭፈራ ትወጂያለሽ እንዴ?"ልዩ ነች ጠያቂዋ፡

"አትጠይቂኝ… ጭፈራ ከመውደዴ የተነሳ አንድ አመት ዲጄ ሆኜ ሰርቼያለሁ... "

‹‹አንግዲያው ከመድህኔ ጋር በጠም ትጣጣማለችሁ ማለት ነው›ሥትል ከኃላዋ መድህኔ መጣና በምንድነው የምንጣጣመው? ››ሲል ያልተዘጋጀችበትን ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡…

‹‹ በቅርቡ ልታየው አይደል ››በማለት ድፍን ያለ መልስ መለስችለትና  ተያይዘን ወጡ ...

ይቀጥላል
👍142🥰145🤔3😱2👏1😁1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹ በቅርቡ ልታየው አይደል ››በማለት ድፍን ያለ መልስ መለስችለትና ተያይዘን ወጡ ...

‹‹እሺ ቦታ ትመርጣላችሁ ወይስ እኔ ልምረጥ?››መድህኔ ነው ወደ መኪና ከመግባታቸው በፊት የጠየቀው፡፡

"ቦታውን አንተ ምረጥ ..ግን ጭፈራ ቤት መሆን አለበት"አለችው ልዩ፡

"አሪፍ ነዋ"አለ ፊቱ በርቶ..ከዛ ወደ መኪናው መራመድ ጀመረ...ተከተሉኝ፡፡

እስከ ለሊቱ ሰባት ሰዓት ቀወጡት ..በዋነኝነት ተዋናዬቹ ሶስቱ ነበሩ፡፡ ከመሀከላቸው ቃል መጠጥ አይጠጣም .... ውሀ ይዞ እነሱን መከታተል ነበር ዋና ስራው፡፡ሲጨፍሩ ያየቸዋል... ሲንገዳገዱ ይደግፋቸዋል... ፡፡ እነሱም በእሱ ተማምነን ዘና ብለን እየቀወጡ ነው ምሽቱን በፈንጠዝያ ያሳለፉት።ለነገሩ ልዩም በአብዛኛው ከእሱ ተለጥፋ ነው ያመሸችው፡፡

‹‹ሚስትህ ባሌን እኳ አንሳፋፈችው››አለችው፡፡

‹‹ምነው ቀናሽ እንዴ?››

‹‹ለምን አልቀና እኔ እንደአንተ ደመበራድ አይደለሁም››

እና ምን ይሻላል

‹‹ያው ምን ይሻላል .መጨረሻቸውን ማለት ነው››

እስከወዲያኛው ብትቀማሽስ››

ትሞክረዋ›

<<ምን ታደርጊያለሽ››
እሾክን በሾክ ነዋ…እሷ እኮ ባል አላት›› አለችው…ፉከራዋ አሳቀው፡፡

መድህኔና ጊፍቲ ስለእነሱ ሹክሹክታ ደንታም ሳይሰጣቸው በጭፈራቸው ተመስጠዋል፡፡ ሁለቱም አደገኛ ጨፋሪዎች ናቸው ...ደግሞ በሚገርም ጥምረት ተግባብተው በአየር ላይ የመብረር ያህል አቅላቸውን ስተው ተጣብቀው ሲደንሱ ላያቸወ ከአየን ያውጣችው ያስብላሉ ፡፡ አሁን እዚህ ጭፈራ ቤት ያሉ ሁሉ ልዩና ቃልን ቀዝቃዛ ፍቅረኞች ….ጊፍቲና መድህኔ ደግሞ የበለጡ የሚያምሩና የሚግባብ የጋለ ፍቅር ላይ ያሉ ጥንዶች እንደሆኑ ምሎ ሊናገር ይችላል። ‹‹ግን በትክክልም መሆን ያለበት እንደዚህ ነው።አዎ መድህኔ እኮ በጣም ቆንጆ ፤ዘናጭ፤ ሀብታምና ጥሩ ስነምግባር ያለው ሰው ነው...እና ጊፍቲ መድህኔ ፍቅረኛዋ ቢሆን በጣም ጥሩና የተመቸ ኑሮ ትኖራለች...አዎ እሱን ብታገኝ በጣም እድለኛ ነች።›ስትል አብሰለሰልች፡፡

ግን መድህኔ እንደምትይው ሁሉን የሚያሟላ ተመራጭ ወንድ ከሆነ አንቺስ ለምን እሱን ለቀሽ ቃልን ተመኘሽ?ብሎ የሚጠይቃት ሰው ካለ ምን አይነት መልስ ልትመልስ እንደምትችል አታውቅም..

.ስለቃል የሚሰማት ስሜት ጥልቅና መንፈሳዊ ነው"..ልክ የመድህኔን ኳሊቲ በቀላሉ ዘርዝራ እንደተናገረችው የቃልን እንደዛ ማድረግ አትችልም...እና ደግሞ የቃልን ጉዳይ ባይሆንባት በማንም ሌላ ወንድ መድህኔን መቀየር አትፈልግም ነበር...እና ደግሞ ማንም ሌላ ሴት መድህኔን ልትቀማት ሞክራ ቢሆን ኖሮ አንገቷን ቀንጥሳ ነበር የምትጥላት።ስለ ቃል ሚሰማት ስሜት ይሄን ያህል ውስብስብ ነው

ሰባት ሰዓት ስላለፈ እዛው ሲጨፍሩበት ካመሹበት ሆቴል አንድ ባለ ሁለት አላጋ ክፍል ተያዘና እየተጓተቱ ሄድን ፡፡እውነት ለመናገር ብክት እስኪሉ ሰክረዋል.... መኝታ ቤት እንደገቡ ብርድ ልብስ ገልጦ ከውስጥ የገባ የለም...ልዩና መድህኔ አንድ አልጋ ላይ ቃልና ጊፍቲ አንድ ላይ ተመሳቅለው ተኙ። ልዩ ከጎኖ እጮኛዋን መድህኔ ሰውነቷ ላይ ተለጠፋ የተኛች ቢሆንም ነፍሷ ግን ቃል እቅፍ ውስጥ ነበር ተሸጉጣ ያደረችው።
///
ጥዋት አንድ ሰዓት ተኩል ሲል ከአንቅልፋቸው ተነስተው ሁሉም ለብሰው ያደሩትን የተጨማዳደ ልበሳቸውን በተቻለ መጠን አስተካከሉና ወደሬስቶራንት ጎራ ብለው ፤አፒታይታቸው በፈቀደላቸው መጠን ቁርስ በልተው በማጠናቅ ሆቴሉን ለቀው ለመውጣት ዝግጁ ሆኑ ከዛ ልዩ ጊፍቲን ቢሮዋ ድረሰ ሸኝታት ወደትምህርት ቤት እንድትሄድ በተመሳሳይ ደግሞ መድህኔ ቃልን መስሪያ ቤቱ ድረስ አድርሶት ወደስራው ሊሄድ ድልድል አወጡ፡፡ልዩ እንዲሆን የፈለገችው ተቃራኒውን ነበር...እሷ ቃልን እንድትሸኘው መድህኔ ደግሞ ይህቺን መዥገር ነገር እንዲያደርሳት… በዛውም ሁለቱ ስለማታው የሰመረ የዳንስ ጥምረታቸው እያወሩና ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ እንዲሄዱ ፈልጋ ነበር ….ግን እንዴት ብላ ተቃውሞ ታቅርብ …?ሳትወድ በግድ በድልድሉ ተስማማችና ደስተኛ እንደሆነች ለማስመሰል እየጣረች ጊፍቲን አሳፍራ ወደቢሮዋ ጉዞ ጀመረች…ለረጂም ደቂቃ ምንም አልተነጋገሩም…..ጊፍቲ ነበረች ከዝምታዋ ያነቃቻኝ፡፡
‹‹ምነው እኔን ጥለሽ ጭልጥ አልሽ .?››
ድንገት አፏ ላይ የመጣላትን መልስ መለሰችላት‹‹ስለማታው አስደሳች ምሽት እያሰብኩ ነበር› …እንደዛ ያለችው. እውነት ስላለችው ነገር እያሰበችበት ስለነበር ሳይሆን ሰለማታው ቆይታቸው ምን እንደተሰማት ለመገምገም እንዲረዳት ነው፡፡
‹‹ውይ ብታይ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል...እንዲህ አይነት ፍንጥዝጥዝ ያለ ምሽት ካሳልፍኩ ረጂም ጊዜ ሆኖኝ ነበር.በጣም አመሰግናለሁ›› አለች ጊፍቲ…
ልዩም‹‹አሀ አንዳሰብኩት በጣም ደስተኛ ነበረች ማለት ነው?››ስትል በውስጧ አሰበቸና ይበልጥ ዝርዝሩን ለመረዳት ንግግሯን ቀጠለች ‹‹ደግሞ በጣም ደናሽ ነሽ›ስትል የአድናቆት ቃል ሰነዘረች፡፡
‹‹አዎ ዳንስና ጭፈራ በጣም ወዳለሁ..ግን ባልሽን ጫፍ ላይ አልደርስም…በስመአብ አጥንት ያለው እኮ አይመስልም››
ጊፍቲ በአንድ ቀን ቆይታ ለመድሀኔ ያደረባት አድናቆቶ ካሰበችው በላይ የተጋነነ ሆኖ ነው ያገኘችው…እርግጥ መድሀኔ ሁሉም የሚያወራለት ጨፋሪ እንደሆነ እራሷም ልዩ ታውቃለች…ጊፍቲ በምታወራለት ልክ ግን ሌላ ሰው ሲያደንቀው ሰምታ አታውቅም..እሷ ያው እንደቃል የቀዘቀዘች ባትሆንም ለጭፈራ ያን ያህል ስለሆነች በእሷ ልክ የመድሀኔን ችሎታ ባይታያት አይፈረድባትም፡ስለዚህ ይሄ መደነቋ ሳይበርድ ልትጠቀምበት ይገባል ብላ አሰበች…በጣም ፈጣን የሆነ እቅድ በእምሮዋ ተሰነቀረ፡፡
‹‹ውይ ይቅርታ…አንድ ነገር እያሰብኩ ነበር…ከመድህኔ ጋር ሳምንት ኩሪፍቱ ለመሄድ ቀጠሮ ነበረን፤ በእኛ እስፖንሰርነት ለምን አንቺና ቃል አትቀላቀሉንም››
ከተማ ወጥቶ የመዝናናት ምንም አይነት ዕቅድ የላቸውም ….ግን እሷ ከተስማማች መድህኔን ከከተማ ወጥቶ መዝናናት እንደምትፈልግ መናገር ብቻ ነው የሚጠበቅባት….ምንም አይነት ወሳኝ የስራ ቃጠሮ ይኑረው ወይም ሌላ ፕሮግራም ሁሉንም ጣጥሎ ፍላጎቷን እንደሚያሞላላት እርግጠኛ ነች…ለዛ ነው በልቧ ሙሉነት የግብዣውን ሀሳብ ያቀረበችላት፡፡
‹‹ወይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…?ግን ቃል የሚመቸው አይመስለኝም….መስሪያ ቤቱ ለአምስት ቀን ፊልድ ክፍለሀገር ሊለከው ነው…ነገ ክፍለሀገር ይሄዳል..››አለቻት፡፡
ልዩ በጊፍቲ መልስ ደስ አለት ፡፡ደስ ያለት ለአምስት ቀን ሙሉ ቃልን ላታየው ባለመቻሏ አይደለም…ግን በጉዞችን የቃል አለመኖር ጥሩ ሆኖ ነው ያገኘችሁት… ጊፍቲን ከመድህኔ ጋር ይበልጥ እንዲቀራረብ ለማድረግ አሪፍ እድል ይሆናል ብላ ስላሰበች ነው፡፡
‹‹ታዲያ ለምን አንቺ አትቀላቀይንም ?..በሌላ ዙር ደግሞ ቃልን ጨምረን ተሟልተን እንሄዳለን››
‹‹ተይ ባክሽ..ብቻችሁን ብታሳልፉ ይሻላል?፡፡››መግደርደር መሆኑን በደንብ በሚያሳብቅ ፈራ ተባ ባለ ንግግር መለሰችላት፡
👍845🔥2😱2