አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
502 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
‹‹እና ምን እያልከኝ ነው››
‹‹እንዴ!! እንዴት እንዲህ ትያለሽ.?መጀመሪያ ከቃል ጋር እራት ቀጠሮ ነበረን..አሁን ለአንቺ ከደወልኩልሽ በኃላ ደውሎ ድንገተኛ ጉዳይ ስላጋጠመው ዛሬ እንደማይችል ነግሮኝ ይቅርታ ጠየቀኝ...የእራት ግብዣው አሌለ ደግሞ ስጦታው አያስፈልግም ››የመዋሸት ብቃቷ  ለእሷው ለራሷ አስደነቃት፡፡

‹‹እና መኪናሽ ወስጥ ሳልገባ ለምን እዛው አልነገርሺኝም፡፡››

‹‹ውዴ አረ ዘና በይ..መምጣትሽ ካልቀረ ሻይ ቡና እንባባል ብዬ እኮ ነው ..ያው የቃል ጓደኛ ነሽ ማለት የእኔም ጓደኛ ነሽ፡፡››

ጊፍቲ በጣም ከመናደዶ የተነሳ መከራከሩንም ስላልቻለች ዝም አለች፡፡ቦሌ ካልዲስ ገቡና የሚፈልጉትን አዘው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጡ፡፡

‹‹ከቃል ጋር የረጂም ጊዜ ጓደኛሞች ናችሁ?››ልዩ ነች የጠየቀችው፡፡
‹‹ከልጅነት ጀምሮ አብረን ነበርን…አንድ ጊቢ ውስጥ ነው ያደግነው፡፡››

ልክ ምንም እንደማያውቅ ሰው ‹‹እና ያው ጓደኛ ብቻ ናችሁ አይደል?.››ብላ የሚያበሰጭ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡

.ለተወሰኑ ደቂቃዎች ፀጥ አለች‹‹እንዴት እንደህ ልትይ ቻልሽ? ቃል ነው እንዲህ ብሎ የነገረሽ?››
‹‹አረ በፍፅም›አለቻት ደንግጣ…የደነገጠችው ሄዳ ቃልን ብትጠይቀውስ.?ብላ በመስጋት ነው…በዚህ ጉዳይ ከቃል ጋር ብትጣላ  ለእሷ ትልቅ ኪሳራና እፍረት ነው፡፡
‹‹ቃል ጓደኛዬም፤ወንደሜም፤ፍቅረኛዬም ሁለነገሬ ነው››በማለት አንጀቷን ለመበጠስ ሞከረች፡፡

‹‹ምን ያህል ነው የምትፈልጊው?››የሚል ፍጥጥ ያለ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡

ጊፍቲ መመለስ ጀመረች‹ቃልን የምፈልገው …እራሴን ከምፈልገው በላይ ነው…ቃል ህልሜ ነው፡፡የልጅነት ህልሜ…ሁለታችንም አንዳችን ከአንዳችን ለረጅም አመት ማለት ከልጅነታችን ጀምሮ ስንደጋገፍና የህይወትን ጨለማ ጎኗንም በመረዳዳት በብርሀኗም አንድ ላይ በመድመቅ ነው እዚህ የደረስነው….፡፡››

ይህቺ ልጅ የዋዛ አይደለችም ››አለች ልዩ..ጥያቄዋን አራዘመች‹‹እና ታገቢዋለሽ ማለት ነዋ?››

‹‹ይሄ ምን ጥርጥር አለው?››

‹‹እሱስ?››

‹‹ነገርኩሽ እኮ…እኛ እስከአሁን የመጣንበትን የሕይወት መንገድ  አብረን ነው የተጓዝነው...ከአሁን በኃላ ያለውን ህይወታችንንም አብረን ከመዝለቅ ውጭ ምንም ምርጫ የለንም፡፡››

‹‹ቃልና አንቺ ግን መች ነው የምትጋቡት?››

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹እኔ እንጃ ማለት.አልተነጋገረችሁበትም..?›
‹‹አይ ተነጋረንበታል…እናማ ሁኔታዎች ሲስተካከሉ እንጋባለን..ደግሞ ምን የሚያጣድፍ ነገር አለ?››

‹‹ቃልን ትወደጂዋለሽ አይደል?.›በሁኔተዋ ተጠራጥራ ጠየቀቻት..

‹‹በጣም እወዳዋለሁ…ባለወደው ከእሱ ጋር ምን አንዘለዘለኝ…. አፈቅረዋለሁ ማለት ታዲያ በኪራይ ቤት እሱን ለማግባት ፍቃደኛ ነኝ እያልኩሽ አይደለም.. በፍፅም እንደዛ አላደርግም….ግን ደግሞ ሌላ ወንድም ማግባት አልፈልግም እስከ ስልሳ አመትም ቢሆን እጠብቀዋለሁ…ምክንያቱም  ቃልን የመሰለ ባል የትም አይገኝም…..አምስት ወንድ እንድ ላይ ተደርበው ቢታሰሩ እሱን አይደርሱበትም፡፡››ብላ አንጀት ሚበጥስ ከረር ያለ መልስ ሰጠቻት፡
‹‹እኮ እኔም  እሱ ነው የገረመኝ….በጎዳና ላይ በተጣለ ዱንኳን ቤትም ቢያገቡት ያዋጣል ብዬ እኮ ነው››ሳታስበው የውስጧን ቀባጠረች፡፡
‹‹ተይ ተይ ህይወት እቃቃ ጫወታ  አይደለችም…ፍቅር እንጀራና ዳቦ መሆን አይችልም…እናንተ የሀብታም ልጆች ፊልምና ህይወት ይምታታባችኋል፡፡አንቺ አሁን ፍቅረኛ አለሽ አይደል?ሰትል እራሷን ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዎ›› አለቻት፡፡
‹‹ማለት?››
‹‹እሺ አለኝ››
‹‹መች ታገቢዋለሽ..››
‹‹በቅርብ…ከሶስት ወር በኃላ፡፡;;
‹‹ቤት አለው…?››
‹‹አዎ አዲስአባባ እና ሰንዳፋ ላይ መኖሪያ ቤት አለው›
‹‹ሁለት ቤት ማለት ነው?››
‹‹አዎ….››
‹‹እሺ መኪናስ?››
‹‹ምን የቤት ነው የንግድ ?ማለት የካማፓኒያችን ከሆነ ቁጥራቸውን አላውቅም››
‹እሺ የቤትስ?››
‹‹ሶስት መኪኖች አሉት››
‹‹አየሽ ለምን እንደምታገቢው?››
ልዩ ተበሳጨች‹‹እና ለብር ብዬ የማገባው ነው ሚመስልሽ..?››
‹‹እና በጣም ስለምታፈቅሪው ነው…አይመስለኝም? ስለእሱ ስታወሪ አይኖችሽ ላይ የሚነድ የፍቅር እሳት አይታየኝም፡››
‹‹እርግጥ ምን ያህል እንደማፈቅረው አላውቅም….ግን ያ ማለት የማገባው ለገንዘብ ነው ማለት አይደለም…እኔ ከቤተሰቤ በውርስ ማገኘው ሀብት ምን አልባት ከእሱ ይበልጥ እንደሆነ እንጂ አያንስም፡፡››
‹‹አይ ይህቺ አለም…አየሽ ዲታውን ከዲታ ከምታጣብቅ ምን አለበት .ያለውን ከሌለው ብታፋቅር….ለፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልም አሪፍ ነበር.››ስትል ቁምነገሩን ከቀልድ ጋር ደባልቃ ተናገረች፡
‹‹ታዲያ ምን ችግር አለው? ባል አንቀያየራ››አለቻት ልዩ
‹‹አይ አንቺ ምን አለብሽ ?ቀልጂ….››
ልዩ ለመቀለድ ብላ አልነበረም የተናገረችው…ሰው አስቦ ይናገራል ፣እሷ ግን ተናግራ ማሰብ ጀመረች..‹ባል እንቀያየር››ደጋግማ ደጋግማ በእምሮዋ አሰላሰለች… ድንቅ ሀሳብ ነው፡፡
በንግግሯ ተስፋ መቁረጥ ፈፅሞ አልፈለገችም..አዎ ስልሳ አመትም ቢሆን ጠብቃው እንድታገባው ፈፅሞ ልትፈቅድላት አልፈለገችም ፡፡ እልክ ውስጥ ገባች፡፡ጊዜ አንፃራዊ ነው..‹‹እሷ ዕድሜ ልክ አብራው ቆይታለች ማለት ከእኔ በላይ ታፈቅረዋለች ወይም ከእኔ በተሻለ እሱ ላይ መብት አላት ማለት አይደለም …ፍፁም፡፡››ስትል የራሷን ድምዳሜ ሰጠች፡፡
ልክ ጊፍቲ  የህይወት ታሪኳን ለሌላ ሰው ስታወራ በጉልህ የምትጠቅሰውና አይኗ እየበራ ምታወራው ስለቃል እንደሆነ ሁሉ የልዩም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው…
‹‹.ምን አልባት በጣም ወደአካላቱ ለጥፎ አቅፎ ከንፈሮቾን ለሺ ምናምን ጊዜ ስሟቸው ሊሆን ይችላል…ጭኖቾንም ፈልቅቆ ለበርካታ ቀናትና አመታት የሚያቃትት አይነት ወሲብ ፈፅመውና እረክተው ሊሆን ይችላል…ይሄም ቢሆን ግን ከእኔ በላይ ቀርባዋለች ብዬ እንዳስብና እንዳምን አያደርገኝም…፡፡አዎ ..እሱን ማግባት ያለብኝ እኔ ነኝ ፡፡ይሄ የህይወቴ ዋናው ግብ ነው፡፡እኔ እሱን ነጥቃታለሁ፡፡ከዚህች  ልጅ ጋ በዘዴና በጥበብ መደራደር አለብኝ›› ስትል  ወሰነች፡፡
‹‹አዎ ባሌን ወስዳ ባሏን ብትሰጠኝ ሁለታችንም በጣም ደስተኞች እንሆናለን፡፡ አዎ ወንዶቹም የሚከፋቸው አይመስለኝም..አዎ ከዛሬ ጀምሮ ይሄንን ትልቅ አላማ አንግቤያለሁ ማለት ነው.ይሄን ሳላሳካ እንቅልፍ በአይኔ አይዞርም››ብላ በውስጧ ፎከረች፡፡
አዎ ቃልን ለማግኘት ስትል መድህኔን ልትሰጣት ወስናለች… ቃል የጊፍቲ ልጅነት ጓደኛዋና ወደፊት ልታገባው ያሰበችው ቃል ኪዳን የገባላት ፍቅረኛዋ እንደሆነ ሁሉ መድህኔም ለእሷ የልጅነት ጓደኛዋ እና እጮኛዋ ነው…..ነገር ግን አሁን እሷም በማታውቀው ምክንያት ቃልን አምርራ ትፈልገዋለች.... ጊፍቲ ደግሞ  መድሀኔን ባትፈልግም ተዋውቀው ሲለማመዱ ግን ልትፈልገው ትችላለች ብላ አሰበች …በእዛ ላይ ጭማሪ ሀብት ትፈልጋለች ብላ አሰበች…ያንን ደግሞ  ቃል ሊሰጣት አይችልም ..ቢያንስ በቅርብ አመት እንደዛ ማድረግ እንደማይችል በማያሻማ ቃል በራሱ አንደበት ነግሯታል.‹‹.ብንቀያየርስ..?ሁሉ ነገር ፐርፌክት ይሆናል፡፡›› ደመደመች፡፡
👍7110🎉4😁3👏2
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ሰዓቱ 11.10 ነው።22 አንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብላለች።ብቻዋን ነው ያለችው...ስልኳን አወጣችና ደወለች።
‹‹ሀይ ቃልዬ እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁ ልዩ ደህና ነሽ?››
‹‹አለሁ ...ከስራ አልወጣህም እንዴ?››
‹‹ወጥቼያለሁ ..መገናኛ ነኝ።››
"ለምን መክሰስ አልጋብዝህም 22 ነው ያለሁት"
"ደስ ይለኝ ነበር.. ግን አሁን ጊፍቲ ደውላ  ሰፈር እየጠበቅኩህ ነው ስላለቺኝ ወደእዛው ልሄድ ነው"እንደዛ ያላት አውቆ ነው…ልዩ እንገናኝ ካለችው ጊፍቲንም ይዟት ሊሄድ ስለፈለገ ነው…
"ሰፈር ማለት አንተ ቤት ?"
‹‹አዎ"
‹‹ለምን ይዘሀት አትመጣም..እንደውም አሪፍ ነው?"
አንዳሰበው ስለሆነለት ፈገግ አለ"ልጠይቃትና መልሼ ልደውልልሽ"

"እሺ ቃልዬ...እዛው ቁጭ ብዬ ጠብቃለሁ"አለችውና ስልኩ ተዘጋ። ከጨጓራዋ አካባቢ የተነሳ ቃጠሎ  ጉሮሮዋ ድረስ ሲሰማት ታወቀት፡፡

ቃል የልዩን ስልክ እንደዘጋ ወደ ጊፍቲ ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ ቃለዬ..፡፡››
‹‹አለሁልሽ ጊፍቲ.ላግኝሽ?››
‹‹ደስ ይለኛል..መክሰስ ልትጋብዘኝ ነው ወይስ እራት?››
‹‹አይ መክስ ነው.. ግን ጋባዡ እኔ አይደለሁም.›
‹‹ችግር የለውም እኔ ጋብዝሀለው››
‹‹አይ ጋባዥ አለን›
‹‹ማን?››
ልዩ ደውላልኝ ነበረ ..ልጋብዛችሁ ስላልች ነው የደወልኩልሽ››
ቅሬታዋን መደበቅ አልቻለችም‹‹ቃል ግን እሷ ልጅ…››አንጠልጥላ ተወችው፡፡
‹‹እሷ ልጅ ምን…?››
‹‹እኔ እንጃ ነገረ ስራዋ አያምረኝም…ሌላ አላማ ያላት ይመስለኛል››
እንዳልገባው ሆነ‹ሌላ አላማ ስትይ..?››
‹‹ያው ማለቴ ምትወድህ ይመስለኛል..››
ደስ አለው…..አዎ ቅናት እየጀመራት ነው ሲል አሰበ..‹‹ብትወደኝ ምን ችግር አለው? ጓደኛዬ አይደለች..››
‹‹ቃል ደግሞ… እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም.ምታፈቅርህ ይመስለኛል.ደግሞ ይመስለኛል አይደለም እርግጠኛ ነኝ…››

‹‹አረ ተይ .እኔ ምንም እንደዛ አይነት ስሜት አላየሁባትም.ደግሞ ፍቅረኛዬ እንደሆንሽ ነግሬታለሁ እኮ››
ቢሆንም ተጠንቀቃት.ለማንኛውም የት ነህ ልምጣ.››ያለበትን ቦታ ነገራትና በፈግታ ስልኩን ዘግቶ ለልዩ እንደሚመጡ ለመናገር ደወለላት፡፡

"ይህቺ ጊፋቲ የምትባል ሴት እንዴት ላስወግዳት?"ልዩ እራሷን ጠየቀች... ...ስልኳ ተንጫረረ ..ቃል ነው.. ቀና መልስ እንዲመልስላት በውስጧ እየፀለየች አነሳችው፡፡
"እሺ ቃል?"
"15 20 ደቂቃ እናስጠብቅሻለን።
"ችግር የለውም አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቃችኋለው"አለችና በደስታ ያለችበትን ካፌ ስም ነግራቸው ስልኳን ዘጋችው፡፡

በራሷ ሁኔታ  መገረም ጀመረች"ወይ ጉዴ.. አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቃችኃለው"ስል አሁን መድህኔ ቢሰማ ጭንቅላቱን ይዞ ነው የሚጮኸው...›አለች እንዲህ ልትል የቻለችበት ምክንያት  5 ደቂቃ አረፈድክ ብላ ብዙ ቀን ጮኸበታለች...አስር ደቂቃ አርፍዶ ቀጠሮውን ሰርዛ ጥላው የሄደችበትም ቀናቶች ጥቂት አይደሉም።  

እንዳሉትም ከ20 ደቂቃ በኃላ እጅ ለእጅ ተያይዘው ፊቷ ተከሰቱ፡..መጀመሪያ ልክ እንደረጅም ጊዜ የልብ ጓደኛዋ እሷ ላይ ተጠመጠመችባት ..አገላብጣ ጉንጮቾን ሳመቻት...ጊፍቲ ያልጠበቀችው አይነት አቀባበል ስለሆነ  ግር እንዳላት    ከሁኔታዎ ያስታውቃል...እሷ እራሷ ለምን እንደዛ ኦቨር አክት እንዳደረገች አልገባትም ‹‹...ምን አልባት የይሁዳን መሳም ይሆናል የሳምኳት..››ስትል እራሷን ታዘበች፡፡.ቃልን ከእሷ መለስ ባለ  ሰላምታ  ሰላም አለችውና ሁለቱም ከፊት ለፊቷ ወንበር ስበው ሊቀመጡ ሲሉ‹‹..አይ ቆይ እንውጣ"አለቻቸው፡፡

"ምነው ታሳፍሪኛለሽ ..መክሰስ ትጋብዘናለች ብዬ እኮ ነው ይዤት የመጣሁት..መክሰሱ ቢቀር ቢያንስ ሻይ ጋብዢን እንጂ"ሲል ቀለደ

"አይ የመክሰሱን ሰዓትማ አሳለፍችሁት  አሁን የእራት ሰዓት ነው...እራት የሚገኝበት ቤት እንሂድ.."

‹‹እሱ የተሻለና የተቀደሰ ሀሳብ ነው"አለች ጊፍቲ ...

ተያይዘው ወጡና  መኪናዋ ውስጥ ገቡ… ወደ ዪሆሚያ ክትፎ ቤት ይዛቸው ሄደች ...እዛ ገብተው እስፔሻል ክትፎቸውን አዘው ቀላል ጫወታዎችን እየተጫወቱ ..በልተው ሲያጠናቅቁ አንድ ሰዓት ከሩብ  ሆኖ ነበር። ሂሳብ ልትከፍል ስትጠይቅ ተከፍሏል አሏት...ልቆጣጠረው የማትችለው ንዴት ተናነቃት፡፡..

‹‹ማን ነው የከፈለው ...?››ፊት ለፊቷ ያሉት ቃልና ጊፍቲ ላይ አፈጠጠችባቸው።ሁለቱም ደንግጠው እርስ በርስ ተያዩ   ..."አረ ተረጋጊ እኛ አልከፈልንም"አለት ቃል።
"ማን ነው የከፈለው?"አስተናጋጅን ጠርታ  ጠየቀችው፡፡

"ጋሽ መድህኔ ነው"

ተረጋጋች"እሱ ደግሞ ከእዚህ ቤት አይጠፍም" ስትል በውስጧ አልጎመጎመች፡

"መድህኔ ማን ነው?"ብላ ጠየቀቻት

‹‹ እስቲ አሁን ሆነ ብላ እኔን ለማሳቀቅ ካልሆነ የመድህኔ ማንነት ምን ይረባታል..? በውስጧ ነው ምታወራው…ቀና ብላ ቃልን ስታየው እሱም የመድህኔን ማንነት ለማወቅ የጓጓ መሆኑን በሚያሳብቅ  አስተያየት ነው እያየት ያለው..ለተጠየቀችው ጥያቄ መልስ ከመመለስ ውጭ ሌላ ምርጫ እንደሌላት ግልፅ ሆነላት፡፡ምን ብላ ትመልስ…ግራ ገባት" መድህኔ ጓደኛዬ...ማለቴ ፍቅረኛዬ ነው"አለች፡፡

‹‹የት አለ አስተዋውቂና አረ ጥሪው"ጊፍቲ አሽቃበጠች….፡፡

ልዩ አሁንም የሆነ ነገር ለማድረግ ከአባቱ ፍቃድ እንደሚፈልግ ህፃን በቆረጣ ቃልን አየችው፡፡

ቃልም ልክ ከዚህ በፊት መድሀኒ የተባለወን ስም እንዳልሰማ በማስመሰል "አዎ ጥሪውና እናመስግነው...በዛውም እንተዋወቀዋለን"አላት

"ደወለችለት"

"አንተ የት ነህ?"

"ውስጥ ነኝ ..እጄን እየታጠብኩ"

‹‹ታዲያ ሰላም አትለንም እንዴ?"

‹‹መጣሁ"ከ3 ደቂቃ በኃላ መድህኔ እንደወትሮ ዝንጥ ብሎ በሱፍ እንደታነቀ ፊት ለፊታችን ገጭ አለ...

‹‹ተዋወቁት መድህኔ ማለት እሱ ነው"በየተራ እየጨበጠ ተዋወቃቸው..

"ስለተዋወቅኩህ ደስ ብሎኛል...ልዩ ግን ይሄን የመሰለ ሸበላ ባል እንዳለሽ ለምን እስከዛሬ ደበቅሽኝ?"አለቻት ልዩ ተሸማቀች፡፡ የጊፍቲን ንግግር ለሚሰማ ሰው የሁለቱ ትውውቅና የጓደኝነት ታሪክ አመታትን ያስቆጠረ  ነው ሚመስለው? ልዩ ከውስጧ እየታገለች ዝም አለች

..ቃል ‹‹ቁጭ በላ›› አለው ቦታ እያመቻቸለት

"ቆይ ጓደኞቼን ተሠናብቼ ልምጣ ››አለ

ልዩ ግን መድሀኔ ተመልሶ እንዲመጣና እንዲቀላቀላቸው  ስላልፈለገች..."አይ ለምን እኛም እኮ ልንወጣ ነው"አለችው፡

"እኮ 2 ደቂቃ ብቻ ጠብቁኝና አብረን እንወጣለን ..እንዴ ክትፎ በልቶ ደግሞ አንድ ሁለት ሳይባል ቢገባ ጥሩ አይደለም...እራት እኔ አይደል የጋበዝኮችሁ አንቺና ጓደኞችሽ ደግሞ መጠጥ ትጋብዙኛላችሁ ...››ብሎ መልስ ሳይጠብቅ  ዞሮ ሄደ...ሳታስበው እንደውም ጥሩ ሀሳብ ነው..

ወደእነ ቃል ዞራ "ሰዎች እንግዲህ ቻሉት.. መድህኔ ካለ አለ ነው "አለች

ጊፍቲ"እንዲህ አይነት ድንገተኛ ግብዣ ተገኝቶ ነው...ጭፈራ ቤት ብንሄድ ደግሞ እንዴት ደስ ይለኛል መሰለሽ" ስትል ተቅለብልባ መለሰችላት..ቃል ዞር ብሎ አያትና"በቃ አንቺና ጭፈራ መች ነው የምትለያዩት"አለ፡፡

"ጭፈራ ትወጂያለሽ እንዴ?"ልዩ ነች ጠያቂዋ፡

"አትጠይቂኝ… ጭፈራ ከመውደዴ የተነሳ አንድ አመት ዲጄ ሆኜ ሰርቼያለሁ... "

‹‹አንግዲያው ከመድህኔ ጋር በጠም ትጣጣማለችሁ ማለት ነው›ሥትል ከኃላዋ መድህኔ መጣና በምንድነው የምንጣጣመው? ››ሲል ያልተዘጋጀችበትን ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቀቻት፡፡…

‹‹ በቅርቡ ልታየው አይደል ››በማለት ድፍን ያለ መልስ መለስችለትና  ተያይዘን ወጡ ...

ይቀጥላል
👍141🥰145🤔3😱2👏1😁1