#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
////
አሁን ወደ ቤቴ ልሄድ ወሰንኩና ወደ እሷ ዞርኩ ...እና አሁንም በድጋሜ ከፊል እርቃኗን ስመለከት እርብድብድ አልኩና"አይ በዚህ ሰአት ዘበኞቹ ሰለሚተኙ ግቢውን አይከፍቱልኝ ይሆን እያልኩ እያሰብኩ ነው።››
"ነውእንዴ? ታዲያ እዚህ እደራ!!"ብላ ዘጭ ያለው ሞራሌን መልሳ ሰማይ ሰቀለችው..፡፡እያንቀጠቀጠኝ የነበረው የውስጥ ቅዝቃዜ ከውስጤ እየተወገደ በምትኩ ሙቀት ሲራወጥ ታወቀኝ፡፡
"ይሻላል?"
"አዎ ..ችግር የለውም...፡፡አለችና አንሶላውን እና ብርድ ልብሱን ገልጣ ከውስጥ ገባች...፡፡እኔም በአፌ ምራቅ እየሞላ ጫማዬን ማውለቅ ጀመርኩ፤ ሸሚዜን አወለቅኩ፤ፓክ አውቴንም አልተውኩ አወለቅኩ፤ በመጨረሻ ሱሪዬን አወለቅኩና ልክ እንደእሷ በፓንት ብቻ ወደ አልጋ ላይ እየተስገበገብኩ ወጣሁ።..እያየኋት ብርድልብሱን ወደእኔ ገፋችና በአንሶላና አልጋልብሱ ተጠቅልላ አንደኛውን ጠርዝ ይዛ ተኛች ..
"ብርድልብሱን ልበስ..ደህና እደር"ብላኝ መብራቱን አጠፋችና ለሽ...፡፡
"እንደተባልኩት በብርድ ልብሱ እርቃኔን ጠቅልዬ ለመተኛት ሞከርኩ...፡፡ምን አይነቱ እንከፍ ነኝ እስኪ ደህና እደር እንዳለችኝ ያልሆነ ነገር ከምቀባጥር በክብር ፈጠን ብዬ ይሄን ክፍል ለቅቄ ብወጣስ?...እሷ እያንኮራፍች ነው፤እኔ ግን ..?እኔማ በሁለት እጇቼ እንትኔን አፍኜ ይዤ እየተገለባጥኩ ነው።በግድ ጉብ ልበልባት ይሆን ?አይ ይሄ አይሆንም ጓደኞቼ በፓለቲካ ምክንያት ታስረው ጀግና ሲባሉ እኔ በአስገድዶ ደፈራ ሀያ አመት ....አይ መታገስ መልካም ነው፡፡እኔ ደግሞ በትግስት አልታማም ..በእፅዋት ሳይንስ ከሀረማያ በዲግሪ ተመርቄ አዲስአበባ ላይ በአስተናጋጅነት ተቀጥሬ በመስራት ኑሮዬን እየገፋሁ ያለው ትሁት ትዕግስተኛ። ከዚህ በላይ ትግስት ምን አለ...?በተወለድኩባት አዲስአበባ ከተማ በተማርኩበት ሞያ ስራ ለማግኘት ከአመት በላይ በየመስሪያ ቤቱ ተንከራተትኩ ..ምንም ጠብ ያለልኝ ነገር የለም...አንድ መስሪያ ቤት ጋምቤላ ልላክህ ይላል...ሌላው ጋ ስሄድ የበጋ ስንዴ ፕሮጀክት አርሲ ላይ አለን እዛ እንላክህ ይለኛል።"ምነው ውትድርና የሰለጠንኩ መሠላቸሁ እንዴ? "ብዬ በእነሱ ይሁን በራሴ እያላገጥኩ አላውቅም ሁሉንም እርግፍ አድርጌ ያለሞያዬ ስባክን ይሄው ይሄን የመሠለ ፈተና…..
የባጥ የቆጡን ሳስብ ምንጊዜ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አላውቅም፡፡ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስደኝ፡፡ ….....የበር መንኳኳት ነበር ከእንቅልፍ አለም መዞ ያወጣኝ
‹‹...ማነው? ምንድነው ?››በርግጌ ተነሳው፡፡
"ፅዳት ነው ሰዓት ደርሷል"
"ፅዳት "ዙሪያ ገባውን ቀኘሁ፡፡ነግቷል፡፡ክፍሉ ባዶ ነው.፡፡.ልጅቷ የለችም...፡፡ልብሷቾም ሆነ ዕቃዋቾ የሉም...፡፡ጠረኗ ብቻ ነው ያለው...፡፡ሄዳለች ማለት ነው..፡፡.ምኑ እንክርፍፍ ነገር ነኝ በፈጣሪ...?ምን አለ በጥዋት ተነስቼ ቢያንስ ለመጨረሻ ጊዜ እነዛን አይኗቾን ማለቴ መቀመጫዋን አይቼ በተሰናበትኳት...፡፡በንዴት ከላዬ ላይ ብርድ ልብሱን አሽቀንጥሬ ከላዬ ላይ ወረወርኩ፡፡ ...ከአልጋው ወረድኩ… ጠረጴዛ ላይ ያለውን ልብሴን ሳነሳ የሆኑ ባለመቶ ብር ድፍን ብሮች እና ብጣሽ ወረቀት ድብ ብሎ ወለል ላይ ወደቀ...ብሩን ተውኩና ወረቀቱን አነሳሁት አነበብኩት።
‹‹ደህና ሁን ቆንጇ...ቁርስ በእኔ ነው"ይላል ...
ብሩን አነሳሁና ቆጠርኩት 500 ብር ነው፡፡
‹‹እኔን ብሎ ቆንጆ›› አልኩና በቅጡ እንኳን ልብሴን አስተካክዬ ሳለብስ በንዴት ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ፡፡
ከውስጤ እየተንቀለቀለ ያለው ንዴት በቀላሉ ሊበርድልኝ ስላልቻለ እቤቴ ስደርስ እንኳን የበራፍ አከፋፈቴና አዘጋጌ ኃይል የተቀላቀለበት ነበር ፡፡
‹‹አንተ ቀልማዳ….››
‹‹አቤት አያቴ››
‹‹የትአባህ ነው ያደርከው…?ሰው ያስባል አትልም እንዴ…?ከአሁን አሁን መጣ እያልኩ ቁጭ ብዬ እኮ ነው ያደርኩት››
‹‹ውይ በጣም ይቅርታ ..ጋሼ ስራ አዞኝ እስከ 9 ሰዓት ስሰራ ስለነበር ደከመኝና እዛው ተኛሁ፡፡››
‹‹እና ሮጥ ብለህ አንድ አፍታ መጥተህ ላድር ነው ብትል የትኛውን ድንበር ስታቆርጥ ነው››ጠንከር ባለ የንዴት ቃና ሲቆጡኝ እንባዬ በአይኔ ሞላ ..ተበሳጫቼ አይደለም..፡፡ይሄን ያህል የሚያስብልኝ ሰው ይኖረል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበረ…፡፡
‹ሁለተኛ አይለመደኝም››ቃል ገባሁ፡፡
‹ፍፅምዐእንዳይለመድህ .
ትደግመውናትጣላኛለህ
.በል አሁን እንደደካከመህ ድምፅህ ያስታውቃል ትንሽ ተኛ፡፡››
‹‹እሺ አያቴ›አልኩና አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ፡፡
‹‹ዜና ወርቅ… ›
›.‹‹የዜናወርቅ አዎ እንደዛ ብላ ነበር ስሟን የነገረችኝ…ለዛም ይመስለኛል የዜናወርቅ የሚለው ስም ከእምሮዬ ሞልቶ እየፈሰሰ ያለው….
‹‹ወይ ጉድ ፍቅር ስለሚለው ቃል እራሱ ያሰብኩት ከስንት ጊዜ በኃላ መሆኑ ነው…?አዎ ከስድስት ረጂም አመት በኃላ …፡፡ ፍቅርን እርም ብዬ ነበር…፡፡ልክ እየደጋገሙ እየተንበገበገ ባለ እሳት እጣቱን ከተው እስኪቆስልና ቆዳወ እስኪገሸለጥ ድረስ እያቃጠሉ እንዳስፈራሩት ልጅ አይነት ነበርኩ፡፡.አዎ ፍቅርን የምፈራው ልክ ያ ህፃን ልጅ እድሜ ልኩን እሳትን በሚፈራበት መጠን ነው፡፡እና ጊዜያዊ ስሜቴን ማስወገድ አለብኝ.››.አስቤ አስቤ ሲደክመኝ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
‹‹ወይ ዝም ብዬህ ቻው እንኳን ሳልልህ ሄድኩ አይደል?››
‹‹አዎ…ግራ አጋባሺኝ እኮ››
‹‹አይ አስቸኮይ ነገር ስላጋጠመኝ ነው .ይቅርታ››
‹‹አይ ምንም አይደል…ግን እቤቴን ማን አሳየሽ? ››
‹‹አለቃህ…ማለቴ የሆቴሉ ባለቤት ለመነኩትና ከአንድ ጩጬ ጋ ላከኝ፡፡››
‹‹እሺ የቤቱን በራፍስ ማን ከፈተልሽ...?እኔ ተኝቼ ነበር››
‹እሱን ተወው .በመምጣቴ አልተደሰትክም እንዴ?››
‹‹አረ በጣም ተደስቼያለሁ…ነገሮች ድንገተኛ ስለሆኑብኝ ግራ ተጋብቼ ነው››
‹እንደዛ ከሆነ እቀፈኝ››
‹‹እሺ…ይሄው….ወደራሴ ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት…››
‹‹እዬብዬ.›በተሰባበረ እና በሚያቃትት ድምፅ ጠራችኝ፡፡
‹‹ወዬ ዜናዬ.››
‹በጣም ሞቀኝ…ልብሴን ላውልቅ››
‹አዎ አውልቂ…. እንደውም እኔም ላውልቅ.››አልኩና እኩል እየተረዳዳን ልብሳችንን አወለቅንና እርቃናችንን ተመልሰን እቅፍቅፍ ብለን ተጋደምን….፡፡እርቃናችን ሲፋተግ እሳት ፈጠረ..ነደድኩ… ከንፈሯ ላይ ተጣበቅኩባት…ጭኗን ፈለቀቅኩና ሰርስሬ ከመሀል ገባሁ….ቃተተች…‹‹ወይ የእኔ ጀግና ጎዳኸኝ….ቀስ በል..አመመኝ›››
በእጆቼ አፏን አፈንኳት..እንደዛ ያደረኩት የዜናወርቅን የመቃተት ጩኸት አያቴ እንዳይሰሙንና እንዳይረበሹ ስለፈራሁ ነው፡፡እንኳን እንዲህ የምትቃትት ሴት ይቅርና ጮክ ብሎ የሚያወራ ወንድ ጓደኛ እዚህ ቤት ይዤ መጥቼ አላውቅም፡ተጨነቅኩ፡፡ ስላፈንኳት እሷ ተንፈራገጠች…፡፡ግራ ገባኝ፤ ልልቀቃትና መጮኸን ትቀጥል ወይስ እንዳፈንኳት ልቀጥል …?ብትሞትብኝስ..?፡፡ከመጨነቄ የተነሳ ላቤ መንጠባጠብ ጀመረ …ተስፈንጥሬ ከመኝታዬ ተነሳሁ፤መኝታዬ ባዶ ክፍሉም ኦና ነበር…ዜናወርቅ ሀሳብ ብቻ ነበረች.፡፡ምኞት የፈጠራት ህልም››
‹‹ተመስገን›አልኩ፡፡
‹‹ተመስገን ያልኩት ዜናወርቅ ቤቴ ስላልመጣችና ስላልተዋሰብን ተደስቼ አይደለም..ይልቁንስ የእውነት ሆኖ ጋሽ ሙሉአለም ስላረበሽኳቸውና ስላላስቀየምኳቸው ተደስቼ ነው ተመስጌን ማለቴ..አንዳንዴ ግን ህልም ባይኖር በምኞታችን እና በምናገኘው ነገር መካከል ያለውን ክፍተት በምን እንሞላው ነበር?››
✨ይቀጥላል✨

👍72❤2👏2
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
///
ከሀያ ቀን በኃላ ፤ስለእሷ ማሰብ ካቆምኩ በኃላ ...ኦልሞስት ከረሳኋት በኃላ ድንገት ተከሰተች። እለቱ ቅዳሜ ነው ፤ቅዳሜ ለአብዛኛው ሰራተኛ የደመቀች ቀን ነች። ፈገግታ የሚፈስባት ..ሙዚቃ የሚንቆረቆርባት..የዳንስ ጥበብ የሚጠበብባት ወሲብ የሚወሰብባት በስራ ሳይሆን በመዝናናት ብዛት የሚደከምባት...በወጪ ብዛት ኪስ የሚታጠብባት አዲስ ፍቅረኛ የሚጠባበስባት ክንድ ላይ ያለ ፍቅረኛ ድንገት ሾልኮ የሚሰወርበት… የታሪክ መፃፊያ ቀን ነች።
ከቅዳሜው የተትረፈረፈው ወደ እሁድ ይዘዋወራል።
ያው ከላይ በገለፅኩላችሁ ምክንያት ለእኛ ለአስተናጋጆች ዋና የስራ ቀናችን ነው።እና በዛው ልክ ወከባ አለ፡፡ ከአንዱ ወደሌላው ጠረጴዛ መስፈንጠር ..ከአንዱ ተስተናጋጅ ትዕዛዝ ወደሌላው...ብቻ ከባድ ግን ደግሞ ወሳኝ ቀን ነች።ከባድ ያልኩት የስራውን ጫና ፤ የተስተናጋጆቹ ወከባ፤ የትዕዛዝ መደበላለቅ፤ የሰከራሙ ትንኮሳ፤የሂሳብ መጉደል የመሳሰሉትን ጫና አስቤ ነው። ወሳኝ ያልኩት ሳምንቱን ሙሉ የማናገኘውን ቲፕ እና መሠል ተጨማሪ ገቢ የምናገኝበት ቀን ስለሆነ ነው።ዛሬም እስከ ምሽቱ ሶስት ሰዓት እንደወትሮ የተለመደ ስራዬን እየሠራሁ ሳለ ጋሼ አስጠረኝ።
‹‹አቤት ጋሼ፡፡››
‹‹ወንበርህን ለሌሎቹ አስረክብና ቪ.አይ.ፒ ቁጥር 4 ያሉትን እንግዶች አስተናግድ"
ፈጠን ብዬ ‹‹እሺ ጋሼ "አልኩና በደቂቃ ውስጥ ወንበሬን ለጓደኞቼ አስረክቤ ወደታዘዝኩት ቦታ ሄድኩ ፡፡ በእኛ ሆቴል ስድስት የቪ.አይ.ፒ ቦታዎች አሉ።ልክ እንደትያትር ቤት በሆቴሉ ሰፊ አዳራሽ አራቱ ኮርነሮች ላይ ከፍ ብሎ የተገነብ ሲሆን ወደ እዛ የሚወጣው ከሆቴሉ ሳይገባ በውጭ በኩል ባለ እስቴር ነው።የሁሉም መግቢያ ለየብቻ ሲሆን ቀጥታ በጓሮ በር ገብቶ መልሶ በጎሮ መውጣት ያስችላል..የቤቱ ዙሪያ በጠንካራ ኮንክሪት ግድግዳ የተገነባ ሲሆን አንድ ጎን ማለት ወደሆቴሉ ያለው ጥይት በማይበሳው መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ ነው ..፡፡መስታወቱ እታች ሆቴል ያለውን እንቅስቃሴ ጭፈራውንና እያንዳንድን እድምተኛ ቁልጭ አድርጎ ሲያሳይ ከሆቴል ወደላይ ግን ድፍን ጥቁር መስታወት ግድግዳ ብቻ ነው የሚታየው።ክፍሉ በጣም ዘመናዊ፤ ምቹ ሶፋዋች እና እንደ አማራጭ የባለጌ ወንበሮች ከምቹ ባልኮኒ ጋር ተገጥሞላቸዋል
መብራቶቹም በምርጫ የሚቀያየሩ ተደርገው የተሠሩ ሲሆን ሙዚቃን በተመለከተ ቀጥታ እታች የሚለቀቀው በጥራት የሚመጣበት ወይም ያንን ዘግቶ እዛው የራሳቸውን የተመረጠ ሙዚቃ የሚጠቀሙበት አማራጭ አለው። እዛ ክፍል …ተጠቃሚዎች ወይ በራፍ ላይ ቆሞ ወይ ውስጥ ተቀምጧ የሚያስተናግዳቸው የብቻቸው አስተናጋጅ ይመደብላቸዋል። የተለየ ፕራይቬሲ ከፈለጉ ደግሞ አስተናጋጅ ከክፍሉ ውጭ ይሆንና ልክ መጥሪያውን ተጭነው ከመድገማቸው በፊት ተስፈንጥሮ በመግባት ትዛዛቸውን ተቀብሎ የሚፈልጉትን ያመጣላቸዋል።
ይህን ክፍል የሚጠቀሙት ለደህንነታቸው ወይም ለስማቸው አብዝተው የሚጨነቁ ትላልቅ የቢዝነስ ሰዎች፤ዝነኞችና እና ባለስልጣኖች ናቸው። ቢሆንም ለሁሉም አገልግሎቶች ከመደበኛው ከአራት እጥፍ በላይ ያስከፋላል ።አስተናጋጅም ብዙን ጊዜ ጠቀም ያለ ጉርሻ ያገኛል።እናም ሁሉም እዚህ ቦታ ሲመደብ በደስታና በፈንጠዝያ ነው የሚቀበለው።
ደረስኩ ..በራፋን እንደመቆርቆር አደረኩና ገፋ አድርጌ ስከፍት ደነገጥኩ...፡፡እንደጠበቅኩት ቀለል ያሉ ሰዎች አይደሉም የገጠሙኝ። እርግጥ ሴቲቷ ጀርባዎን ሰጥታኝ የተቀመጠች በመሆኑ ፊቷ አይታየኝም፡፡ግን ዝንጥ ብላለች።ደማቅ ሰማያዊ ረጅም ቀሚስ፤ መካከለኛ ታኮ ካለው ሰማያዊ ጫማ ጋር አስማምታ ለብሳለች። ፀጉሯ የእውነት የእሷ ከሆነ ውብ መሆኑን በቀላሉ መናገር ይቻላል ፤ወገቧ ላይ ተበትኖ ይታያል .፡፡
.ሰውዬው ከእኔ ፊት ለፊት ናቸው ያሉት ፤ትልቅ ሰው ናቸው።ቆፍጣና ፤ኮስታራና አስፈሪ ..ፀጉራቸው ገብስማ ነው..፡፡ሙሉ ዠንጉርጉር የመከላከያ ልብስ ለብሰዋል።ትከሻቸው ላይ አራት ኮከብ ወደጎን ተደርድሯል።መቼስ በዚህ አለባበስ የሆነ ስብሰባ ላይ ወይም ወሳኝ ሀገራዊ ተልዕኮ ላይ አምሽተው ከጊዜ መጣበብ የተነሳ ወደቤታቸው ጎራ ብለው ለመቀየር ሳይችሉ ቀጥታ መተው ነው እንጂ ይሄ የክብር ልብስ ቦታው አይመስለኝም"በውስጤ አጉረመረምኩ ...
እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ወደፊት የተወሰነ እርምጃ ጠጋ አልኩና ‹‹ጌታዬ የጎደለ ነገር አለ?››ብዬ ጠየቅኳቸው፡
"ሚበላ ምን አላችሁ?"ጎርናና እና ሻካራ ድምፅ...እኚ ጄኔራልማ እቤታቸው ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸውን አስቀምጠው ነው ከዚህች ኮረዳ ጋር የሚማግጡት› በሆዴ አማኋቸው፡፡እስቲ አሁን ምን አውቄ ነው ለሰከንድ ያየኋቸውን ሰዎዬ ወደማማትና መፈረጅ የገባሁት ብዬ እራሴን ወቀስኩ።
"ጌታዬ ሜኑ ላምጣ"
"አይ አንድ ክትፎ አምጣልን...ክትፎቸው አሪፍ ነው" አለች ሴቲቱ...አሁንም በደበዘዘው ብርሀን ከእኔ በተቃራኒ የዞረ ፊቷ እየታየኝ አይደለም ።ድምፆ ግን የሚነዝር ኃይል ነበረው። የሚያደነዝዝ...በምን ምክንያት ነዘረኝ...?ስለምንስ ውስጤ ተናጠ... ?
"በቃ ጎረምሳው እንዳለችህ አድርግ"አሉኝ ጄኔራሉ ..ንግግራቸው ብቻውን ምሽግ የሚንድ አይነት ነው፤ተስፈንጥሬ ወጣሁ።በተቻለ ፍጥነት በልዩ ሁኔታ ክትፎውን አሰርቼ ይዤ ተመለስኩ።
"የእጅ ውሀ እዚሁ ልታመጣልን ትችላለህ?"ሴቲቱ ነች ጠያቂዋ፡
"ይቻላል እመቤቴ.. አሁን አመጣለሁ"አልኩና በደቂቃ ውስጥ የእጅ ውሀ ይዤ መጣሁ። ተንደርድሬ ሄጄ በክብር ጎንበስ ብዬ ልክ እማማ ኢትዬጰያን እያስታጠብኩ እንደሆነ ኩራት እየተሠማኝ ጄኔራሉን አስታጠብኩና ወደ ሴቲቱ ዞር ስል ፊት ለፊት አይን ለአይን ግጥም ...ምን ተአምር ነው?...ልደሰት ወይስ ልዘን? ላልቅስ ወይስ ልሳቅ ?
ጎንበስ ብዬ እያስታጠብኳት ቢሆንም ግን በደመነፍስ ነው። ድምፅ አውጥቼ ላወራት አልቻልኩም ? አውቅሻለሁ... ጋብዘሺኛል.. እርቃን ገላሽን በዓይኖቼ አይቻለሁ...በጣቶቼ ዳብሼሻለሁ ልላት ፈፅሞ አልቻልኩም።
‹‹አይ የጎረምሳ ነገር....ውሀውን ደፍተህ ጨረስከው እኮ"አሉኝ ጀኔራሉ እንደመሳቅ ብለው። ለካ እሷ መታጠብን ጨርሳ እጇን ብትሰበስብም እኔ ግን አይኔን አይኖቾ ላይ እንደተከልኩ ፈዝዤ ውሀውን ማንጮርጮሬን ቀጥያለሁ...በጄኔራሉ ንግግር ባነንኩና ተስፈንጥሬ ከስራቸው ወደበሩ መራመድ ጀመርኩ።
"በራፋ አካባቢ ነኝ፤ ስትፈልጉኝ መጥሪያውን ተጫኑ ››አልኩና ክፍሉን ዘግቼላቸው ወጣሁ።የእጅ ማስታጠቢያውን አስቀምጬ በረንዳው ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተሸከረከርኩ መብሰልሰል ጀመርኩ፡፡
"ፍፅም እንደማታውቀኝ እኮ ነው የሆነችው...ምን አይነቷ ባለጌ ነች?" ከንፈሬን በብስጭት ነከስኩ ..‹‹አንድ ለሊትም ቢሆን እኮ እንዲህ በቀላሉ የሚረሳ ነገር አልነበረንም ያሳለፍነው..? ነው ወይስ ውሽማዋን ፈርታ ነው?››
"ብትፈራ ይፈረድባታል .. ጄኔራሉ እኮ እንኳን በጎናቸው የሸጎጡት ሽጉጥ ተጨምሮበት ይቅርና እንዲሁ ያን ግንባራቸውን ቋጠር ፈታ ሲያደርጉት ያርበደብዳሉ...እኔስ ሀይ ሰላም ነሽ የሚል አጭር ሰላምታ እንኳን ለመስጠት ድፍረት ያጣሁት እሳቸውን ከመፍራት አይደል?።ግን ውሽማዎ ናቸው ነው ያልኳችሁ ..?ያንን በምን አወቅኩ ?አልነገሩኝ...ሲሳሳሙ እንኳን አላየሁም"
የመጥሪያው መንጣረር ከሀሳቤ አናጠበኝ። ፈጥኜ ወደውስጥ ገባሁና መሽቆጥቆጤን ሳልቀንስ "አቤት ጌታዬ"አልኩኝ፡፡

👍56👎2❤1👏1