አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የንጋት ፀሐይ ከወደቀችበት ተነስታ ብርሃኗን ሐመር
ላይ ፈንጥቃለች፡ ካርለት ከወሮ መንደር ሆና ቁልቁል የሐመርን ተፈጥሮ ደኑን የልጃገረድ ጡት መስለው በሰማዩ ደረት የተሰካኩትን የአለሌ  ኤሎ ኤዲ ቢታ… ተራራዎች ስታይ
የምትሆነው ጠፋት ልብ ሰራቂው ተፈጥሮ አነሆለላት እና! ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ወደ ተፈጥሮ ሮጠች ተፈጥሮም ወደ እሷ ገሰገሰች ተቃቀፉ.. አንዱ የሌላውን ሽፋን አወለቀ… አየሩን ሳመችው... መሬቷን አቀፈቻት... ቅጠሉን ሰበሰበችው…ከወፎች ጌር
ሽቅብ ጎነች… ዳመናውን እየበረቃቀሰች በረረች የተፈጥሮ ፍቅር

የሐመር ተፈጥሮአዊ ሕይወት እንደ ቅንቡርስ በውስጧ ገብቶ በሰራ
አካላቷ ተንከላወሰባት ! እንደ እንበሶች ቦረቀች….. ፈነደቀች ከማራኪዋ ተፈጥሮ ጋር እየደጋገመች ተወሳሰበች…..

እንዲህ በደስታ ሰክራ በድካም ጥንዝል ዝርግትግት ብላ
ሳሩ ላይ እንደተንጋለለች የሰው ድምፅ ሰማች፡፡ 'ምን ነበረበት ከእንደዚያ ካለው ዓለም የማይመለሱ ቢሆን!'

ካርለት!

“አቤት" አለች ዞር ብላ እያየች ካርለት፡፡ “ጎይቲ ነይ
እስኪ አጠገቤ ቁጭ በይ"

“ይእ! ምነው እስካሁን ሳትጠይቂኝ ቀረሽ?''

“ምን ብዬ ጎይቲ?

"ይእ! አሁን እውን እሱ የሚረሳ ሆኖ ነው፡ ናፍቆትሽን ውስጥሽ ቀብረሽ ደብቀሽኝ እንጂ…" ያ ሐጫ በረዶ መሳዩን ችምችም
ያለ ጥርሷን እያሳየቻት ጠየቀቻት፡፡

“ደልቲን ነው! ምን ብዬ ልጠይቅሽ? ወሮ እንደማይኖር
አውቃለሁ፤ ዛሬ ግን ሄጀ ላየው እፈልጋለሁ  ናፍቆኛል!"

ጎይቲ ናፍቆኛል የሚለው አባባል የእሷንም እሳት
ጫረባት ወዲያው ገለባው ልቧ ቦግ ብሎ ነደደ፡

“ይእ! ካርለቴ አያ ደልቲ እኔንም ናፍቆኛል ግን የት ሄጄ ላግኘው" ብላ እንባዋ እንደ በጋ ዝናብ የመጣበት ሳይታወቅ ዥጉድጉድ ብሎ ወረደ፡፡ የሳግ ብርቅታ የውስጣዊ ስሜት
ነጎድጓድ… ጎይቲን ደፈቃት፡፡ ካርለት ደነገጠች ደስታዋ በኦንድ ጊዜ ሙሽሽ አለባት፡፡

“ጎይቲ ምን ሆነ? ካርለትን ጩሂ ጩሂ ብረሪ ብረሪ
አሰኛት፡፡ ጎይቲ ግን ካርለት የጠቀቻትን አልሰማችም! በአይነ ህሊናዎ ጀግናዋ እየተንጎማለለ ሲጓዝ አየችው፡፡ ስታየው አቅበጠበጣት ልቧ ዳንኪራ ረገጠባት… ሊርቃት ሆነ፤ መጥራት ፈለገች፡፡
ካልጠራችው እየተንጎማለላ ሄዶ ጫካው ውስጥ ገብቶ ይጠፋባታል፡፡

“አያ ደልቲ!” ተጣራች ጎይቲ ጮክ ብላ እንዲሰማት፡፡

ምን ሆነ ደልቲ" ካርለት ጎይቲን እየነቀነቀች ጠየቀቻት ጎይቲ ግን የጠራችው አንበሳዋ ዞር ብሎ የጠራውን ሰው በአይኖቹ ሲፈልግ የጡቶችዋ ጫፎች እየቆሙ ሰውነቷን እየነዘራት ወደ እሱ
ስትጓዝ ድንገት ጀግናው እየተንጎማለለ ጫካ ገባ፡፡ ሮጠች! እንቅፋቱ
መታት እሾሁ በልቧ ተሰገሰገ… ጫካው ደልቲን ሸፈነው ዋጠው
ለለቀጠው... ስለዚህ ድምጿን ከፍ አድርጋ ተጣራች፡

“አያ ደልቲ ጮኸች ጎይቲ፡፡ ካርለት ግን የምትሆነው
ጠፋት፡-

“ጎይቲ- ደልቲ ምን ሆነ?" ካርለት ሰውነቷ ተንቀጠቀጠባት
አቅም አነሳት• ድካሟ አገረሸ፡፡ ጎይቲ ደግማ ደጋግማ አለቀሰች
እውነተኛውን ደም መሳዩን እንባ!

ደልቲ ምን ሆነ ደ-ል-ቲ ካርለት እንባዋ ግድብን ጥሶ ወጣ› ጎይቲና ካርት ተቃቅፈው ልቅሶአቸውን አስነኩት፡፡

“አያ ደልቲ" እያሉ ጮሁ፤ የገደል ማሚቶው ግን
ድምፃቸውንም ደልቲንም ዋጠው…
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካርለት ለምን አለቀስሽ?" አላት ከሎ ሆራ፡፡ ቲማቲም
የመለለ ፊቷን እያዬ:

እንዲሁ ጎይተን ምን እንደሆነ ደጋግሜ ስለጠይቃት…"አቋረጣት ከሎ፡-

“ጎይቲ ምን አለችሽ ታዲያ?

“ምንም"

“እንግዲያው ለምን አለቀስሽ?''

“እንጃ ክፉ ነገር የደረሰበት መስሎ ተሰማኝ፡፡ ከማጣራቴ በፊት ግን እንደዚህ መሆን አይገባኝም ነበር ይቅርታ! አለች ካርለት፡

ከዚያ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ፡፡

“ከሎ አንተ ግን ለምን አትነግረኝም?"

“ምኑን?

“ስለ ደልቲና ስለ አጋጠመው ሁሉ፡፡"

ካርለት ምን ብዬ ልንገርሽ? ጎይቲ እንደዚያ መሄጃ
መቀመጫ አሳጥታኝ መኪናዋን አስተኛሃት! እያለች ወትውታኝ
ካለረፍት ተጉዘን እዚህ ስንደርስ ደልቲ አልነበረም

“ቡስካ ሄዷል' አሉንና እዚያ ሄደን ስንጠይቅ ዳራ የምትባል የሳላ መንደር ልጃገረድ አብራው እንደተቃበጠችና ደልቲ
መቀመጫውን ሰርቶ እንደሄደ ወይሳ እየነፋ ያም እንደነበርና በእርግጥ አልፎ አልፎ ትክዝ ይል እንደነበር ሰማን፡፡ ከዚያ የላላም
የሻንቆም የቡስካም ሰው ዳግመኛ አለማየቱን ተረዳን፡፡

“ጎይቲ ይህን ጊዜ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች መጮህና ማልቀስ ጀመረች፡፡ ዳራ በበኩሏ ጎይቲ ስታለቅስ እሷም በተራዋ ትንፈቀፈቅ
ጀመር” ብሎ ከሎ ገጠመኛቸውን ሊቀጥል ሲል፦

“ከዚያስ ተገኘ? ካርለት  ረጅሙን ታሪክ መከታተል
አልቻለችም! ሲቃ ያዛት፡፡

“ከዚያማ ጫማ ጣዮች እንዲተነብዩ ተጠየቀና “ክፉ
አልደረሰበትም፧ ራቅ ብሎ ግን ሄዷል' አሉ፡፡ አንጀት አንባቢዎችም ትንሽ ቆይቶ ይመጣል ብለው የታያቸውን ተናገሩ፡፡ጎረምሶች ጫካውን ደአሰሱት መልዕክት በየአቅጣጫው ተላከ ከዚያ  በካሮ  ማህበረሰብ በኩል ያሉት የደንበላ መንደር ሰዎች አየነው ብለው መናገራቸውን ሰማን፡፡

እኔም የአንችን መኪና ይዤ በየመንደሩ ለፍለጋ ዞርሁ
አሁን ደንበላ አይተነዋል እሚለውን ስንሰማ ግን እሱን ልፈልግ ወይንስ አንቺን አዲሳባ ሄጄ ላምጣ በሚለው ከሽማግሌዎች ጋር ስማካር አንች መጣሽ?

ከወጣ  ማለቴ ከሄደ ስንት ጊዜ ሆነው?

"ሃያ ቀን በላይ ሆኖታል፡"
እሽ ለምን ነው አንዳንዴ ከፍቶታል የተባለው?"

“ጎይቲን ያፍቅራታል፡ የአንድ ቤተሰብ አባል በመሆናቸው
እንጂ አብሯት ቢኖር ደስታውን አይችለውም ነበር፡፡ ስለዚህ ከአይኑ
ስትርቅ ላይከፋው ሳይተክዝ አልቀረም። ስለ አንችም ደጋግሞ ያነሳ እንደነበር ሰምቻለሁ የእሷ መባለግ አንሶ ጎይቲንም ይዛት ሄደች!  እያለ እንደሚቆጭ ኮይታውን ከፍሉ እንደጨረሰ አንችን ሲያገባ ያንን
ለስላሳ ገላዋን እገለብጠዋለሁ' እያለም ሲፎክር እንደነበር ሰምቻለሁ" አላት ከሎ ፈገግ ብሎ።

እውነቱን ነው የሐመር ልጃገረድ ነኝ ብዬ ባህሉን
መቀበሌን አሳውቄ! ካለ ሽማግሌ ፈቃድ ያውም ከሐመር ምድር ርቂ መሄዴ በእርግጥ ሊያበሳጨው ይገባል" አለችና በሃሣብ ተውጣ ቆየች፡፡

እንዲህ ካርለትና ከሎ በሃሣብ ተውጠው እንደተቀመጡ ጎይቲ አንተነህ መጣች

“ይእ ምን ሆናችኁል?"
አለቻቸው ሁለቱንም በፍርሃት አየቻቸው ሆዷ ፈራባት “ጎይቲ ምንም አልሆነም፡፡ አንችን
ጠይቄ ልትነግሪኝ ያልቻልሽውን ስለ ደልቲ ከሎን እየጠየቅሁት ነበር"

“እሁሁ… እኔስ ደሞ ምን ሰማችሁ ብዬ የሆንሁትን
አላውቅም" አለችና ሐጫ በረዶ ጥርሶችዋን አሳይታ

“ይእ! የአያ ደልቲን የኦሞ ዳር ጥንቅሽ የቀመስን እኔና
አንች ሌላው ጣምናውን የት ያውቀዋል" ብላ በሣቅ ተፍለቀለቀችና

ነይ በይ አሁን ቡና ጠጭ እህልም ባፍሽ አድርጊ፡፡
የደንበላ ሰዎች “አይተነዋል ብለዋል እንኳን እስካሁን ደና ሆነ እንጂ ከአሁን በኋላስ ከምስጥ ዋሻ ቢገባም አያመልጠን፡፡ ይእ!

አንተስ ና እንጂ  ይኸውልሽ ከመጣን ጀምሮ አበሳውን እያሳየሁት ነው፡፡ ና በል የኔ ጌታ.." አለችውና ከሎን ሶስቱም ተያይዘው በር ወደሌለው የሐመር ጎጆ ሄዱ!
👍291👏1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ብላንክ ፓሎማ' ይሉታል ስፔኖች! ነጭ እርግብ ማለት ነው፡ የዚህ የስፔኑ ተወላጅ እውቁ ሰዓሊ ፓውሉ ፒካሶ ደግሞ ነጭ
እርግብን የሰላም ምልክት አድርጎ ለአለም ህዝብ አበርከቷል፡

ብላንካ ፓሎማ ሮሲ በተባለ ቦታ በዓመት አንዴ የሚከበር ከኢትዮጵያውያን ጥምቀት ጋር የሚመሳሰል በዓል ነው፡፡ ስፔናውያን
እየደነሱና እየጨፈሩ የአለፈውን ዘመን አመስግነው መጭውን
ደግሞ ሰላም የሰፈነበት የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው አምላክን የሚያመሰግኑበትና የሚለምኑበት ክብረ በዓል ነው ብላንካ ፓሎማ።

በዓሉን ለማክበር ከተለያየ ቦታ ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ  እንዲሉ ሴቶቹ ከወገባቸው ጠቡብ ብሎ  ከታች ቦለል በማለት መሬት
የሚነካውን ቀሚሳቸውን ወደ ላይ በጣታቸው ሰብሰብ ያርጉና
አንቧለሌ እየዘሩ ጣቶቻቸውን እንደ ኮብራ አንገት እያሟለሉ ወንዶች ደግሞ የተተፈተፈ የቆዳ ሱሪና ሰደርያ ነጭ ሸሚዝ ሰፊ ባርኔጣ ይለብሱና ብብቱ ውስጥ ዝንብ እንደገባበት ፈረስ ባለ በሌለ ኃይላቸው መሬቱን እየደለቁ እጆቸውን እየሰበቁ እንደ አውራ ዶሮ በሴቷ ክብ ሲዞሩ ጭብጨባው ዝማሬው ፉጨቱና ጨኸቱ
ይቀልጣል፡፡ አሸነፈችው! አሸንፏታል! እየተባለ አቧራው ይጤሳል።

በብላንክ ፓሎማ በዓል
ዘመናዊ ተሽከርካሪ አይኬድም ዘመናዊ ነገር ፈጽሞ እንዲታይም አይፈለግም ወደ በዓሉ ቦታ
የሚጓዘው ሰው በፈረስና በቅሎ  በሚሳቡ ባህላዊ ጋሪዎች የሚበላ የሚጠጣው  ይጫንና ህፃናትና አዋቂን በባህል ልብሳቸው አሸብርቀው አልፎ አልፎ ወንዶቹ በሚገባ በተቀለበ ጠብደል ፈረሰና በቅሎ ሆነው ሶምሶማ እየረገጡ እንደ አባቶቻቸው ወግና ባህል በዓሉ ወደ ሚከበርበት ሮሲ ሲጓዙ በየከተማው ህዝቡ እየወጣ እያጨበጨበና
አብሮ እየጨፈረ ይሽኛቸዋል፡፡

በግብርና ምርቷ በመላው አውሮፖ በይበልጥ የምትታወቀው
ስፔን ህዝቧ በደስታ ፍንድቅድቅ እያለ የአለፈ  ወግና  ልማዱን በዓመት በዓመት እየተከተሉ አምላኩን ሲያመሰግን ሮሲ ሲሰባሰብ ደስታውን ለመክፈል ፈገግተኛና ደስተኛውን የበዓል አክባሪ አይቶ ለመርካት በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ከፈረንሳይ ከፖርቹጋል ከሌሎችም የአውሮፓ አገሮች ወደ ሮሲ ይጎርፋል፡፡

ብላንክ ፓሉማን ለማክበር የሚሰባሰበው ሁሉ ዓላማው በሰላም  መዝናናት ነው፡፡ በቡድን በቡድን ጨዋታና ጭፈራው
ይቀልጣል ፍቅር እየታጨደ ይወቃል ደስታ እንደ ብርቱካን እየተላጠ ይበላል.. በብላንካ ፓሉማ
ኮንችትና ሶራን ወደ ኢትዮጵያ ከመሄዳቸው በፊት እዚህ ባህላዊ በዓል ላይ እንዲካፈል ጋበዘችው፡፡ ሶራ ሆራ ብላንካ ፓሎማን
ለማክበር የተሰባስበው ህዝብ  ለበዓሉ የሚሰጠው ግምት ሲያይ የባህል የማንነት መለያነት ጥቅሙ የመገናኛ ድልድይ መሆኑ
የፍቅር ማጠናከሪያነቱ… ወለል ብhሎ ታየው።
ስዉ ይጨፍራል ይተቃቀፋል በአንድ ጠርሙስ እየተቀባበለ ይጎነጫል እየተሸማ ይበላል... ደስ አለው ሶራን፡፡
እሱንም እየነካኩ  እያጨዋወቱ የስፓኛን ወይን እያቀማመሱ… በህዝቡ መስመር አሰለፉት፡፡ የችሎታውን አጨበጨበ ጨፈረ “ኢትዮጵያዬ' እያለም ጮኸ፡፡ የጥቁሩም የነጩም ፈጣሪ ወደ ሆነው
አምላኩም ምስጋናውን በማህሌተ ዜማው አሰማ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከጎኑ ጽናጽሉን እያንሿሿ ያዜም ቀሳውስት ሲወርቡ የአማራው የጉራጌው የወላይታው. የሲዳማው የኦሮሞው
የኤርቦሬ..ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ባህላዊ ጭፈራ ታየው፡፡ እና ዘለለ!
ብቻውን ሳይሆን ምናቡ ከአመጣቸው ወገኖች ጋር ከዚያ ውብ አፍሪካዊ ጋር ከብላንካ ፓሎማ በዓል አክባሪ ጋር ዘለለ ነጭ
እርግቦች ሰማዩን ሞልተውታል፡

“ብረሩ ሂዱ አፍሪካንም ሙሏት..." ጠራቸው ነጫጭ
እርግቦችን፡፡ እርግቦቹ ይስሙት አይስሙት ግን አያውቅም፡፡

ኮንችት አረንጋዴ ሆኖ ዳር ዳሩ በቀይ ሪባን የተከፈፈ
ቀሚሷን ለብሳ ዞማ ፀጉሯን ጎንጉና አናቷ ላይ በቀይ ሮዝ የፀጉር ማስያዣ አስይዛ የሙቀት ማራገቢያዋን በቄንጥ በመያዝ እንደ አበባ
ፈክታ ወንዶች እንደ ንብ ዙሪያዋን እየበረሩ፤ መሬቱን እየደለቁ ጣታቸውን እየሰበቁ… በዚያ እንደማግኔት በሚስበው ፈገግታቸው እያሽኮረመሟት ሲያይ ኮንችት ልዩ ፍጥረት ሆነችበት፡፡ ጠይሟ
ለግላጋዋ... ኮንችት ደሙን ተክታ በውስጡ ተሰራጨች፡

ብላንካ ፓሎማ… ብላንካ ፓሎማ… ሶራ በሺ የሚቆጠረው ህዝብ ተረሳው፡፡ ሌሎችን ዘነጋቸው. ኮንችት ብቻ ታየችው ኢትዮጵያዊዋ ውብ የጠይም ቆንጆዋ የቁንጅና ልዕልቷ…

“በብላንካ ፓሎማ ስጦታ አበረክትልሀለሁ" ብላዋለች፡፡

“ምን ይሆን ስጦታዋ! ጎመዠ፡፡ እስካሁን ልትሰጠው ስላሰበችው ስጦታዋ አለማሰቡ  አስገረመው፡ አያት ከርቀት
ትደንሳለች፡፡ ቼኮሌቷ ጠይም እንቁዋ! በአይኑ ነካት  በአይኑ ቀመሳት  ጣፈጠችው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እኩለ ለሊት አካባቢ ሰዉ ተዳከመ፡፡ ሁሉም ወደ
የማደሪያው ተበታተነ… ኮንችት ገላዋን ታጥባ ስስ የሌሊት ገዋኗን ለብሳ ስትወጣ ከድንኳኑ ትይዩ ሶራ ያቀጣጠለውን እሳት አየች፡፡
ከሐር የተሰራ ሰፊ  ስጋጃ ተነጥፏል አንድ ጠርሙስ ወይንና   ሁለት ብርጭቆ ይዛለች

እሳቱ አስቸግሮህ ነደደ" አለችው ስጋጃው ላይ
ቁጭ እያለች።

የት ያመልጣል ብሎ ሲያያት የሆነ ነገር ተመለከተ ነጭ ፓንት ተምታታበት፡ አንዳች ሀይል ከውስጡ አንገጫገጨው

"ብላንካ ፓሉማን ወደድከው?"

ቆንጆ በዓል ነው፡ ስሙ ራሱ ነጭ…" እንደገና ወደ እሷ
ተመለከተ ነጩንም ...አየው

ኮንችት ከላይ ገዋኗን ከታች ነጭ ፓንቷን ትልበስ እንጂ
እንደ ሎሚ ሁለት ቦታ ጉች ጉች ያሉት ጡቶችዋ ሰርጓዳ ወገቧ ለስላሳው ጭኗ ካለመከላከያ ይታየዋል፡

ሶራ ጫን ጫን ተነፈሰ ልቡ ፈራ ስሜቱ ተረበሸ ይባስ ብሎ ተንጫጫ።

ኮንችት በሁለቱ
ብርጭቆዎች ለብላንካ ፓሎማ የሚዘጋጀውን ምርጥ ወይን ቀዳችና  የዚህ ዓይነት ወይን ከዚህ
በፊት እርግጠኛ ነኝ የቀመስህ አይመስልኝም፡፡ ውድ ነው! እኔ ግን
የምወደው በውድነቱ ወይንም በቃናው ሳይሆን በመልኩ ነው፡፡
ፀሐይ ላይ ወይን ጠጀ በጨረቃ ብርሃን ደግሞ ወርቃማ ይሇናል ና አዚህ ጋ ቁጭ በልና ተጎንጨው" አለችው፡፡

ሄዶ ከሷ ፈንጠር ብሎ ቁጭ አለ መዓዛዋ ግን
አልራቀውም ለጤናችን ለስጦታዬ" ብላ አየችው፡ ተጎነጫጨለት፡፡

ለስጦታዬ አሰበ ሶራ
እንዳንጋጠጠ ወይኑ መሆኑ
ነው ስጦታዋ .. ውዱ በጨረቃና በፀሐይ ብርሃን እንደ እስስት ቀለሙን የሚቀያይረው

ጣምናውን  ለማወቅ እንደገና ጎንጭ አድርጎ አጣጣመው ወደ አፍንጫው ጠጋ አድርጎ አሽተተው ቀና አድርጎ በጨረቃ ብርሃን ተመለከተው… ወርቃማ ነው!

“ወደድከው አይደል?" የኮንችት አነጋገር እንደ ከላሲካል ሙዚቃ የጆሮውን ታንቡር እየዳሰሰው በሰራ አካላቱ ሰረገ፡፡

“አዎ ጥሩ ነው" ዝም ተባባሉ እሳቱ ይነዳል፡፡ የእሳቱ ብርሃን እነሱ ላይም ተንፀባርቆ ከርቀት ለሚያያቸው እነሱም የሳት
ላንቃ መስለዋል፡፡ ሶራ በጀርባው ስጋጃው ላይ ተኛ እሷ ደግሞ ወደ እሱ ዙራ በጎኗ ተኛች፡፡ የሆነ ነገር እየወዛወዘ እያት እያት አሰኘው ግን ፈራ፡፡

ዛሬስ ገና ስሜቷን እያዳመጠችው ይሆን? ጠየቀ ራሱን ዞር ብሎ ሊያያት አሰበ፡፡ የሆነው ነገር ወዘወዘው እንደገና ቀስ ብሎ ዞር ብሎ አያት  አይኗ ነው የወዘወዘው ፍዝዝ ብሏል አይኗ ከንፈሯ እንደ እንቡጥ ፅጌሬዳ አሞጥሙጧል አይኑን ፈጠጥ አድርጎ አያት፡፡ አየችው እሷም  በፈዘዙ አይኖችዋ፤ የእሳቱ ብርሃን
ግን በመካከላቸው አለ፡፡ ጡቷ ወገቧ ነጩ ፓንት. ታዩት የገዛ ምራቁ ሊያንቀው
ተቃረበ፡፡ ዘወዲያው ልቡ አይኑን ስልብ ስልምልም… አደረገበት፡፡
👍27👎2