አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
489 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስር
:
በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
ታሪካችንን ወደኋላ ስንስበው..-..

አንዳንድ ጊዜ በሆነ አጋጣሚ ፈርሰን ከእንደገና እንሰራለን ..አፍርሰው የሚሰሩን የቅርባችን የሆኑ.. ያመነቸውና በማመናችንም ስነልቦናችንን እምነታችንን፤ ታሪካችንን፤ፍቅራችንን እና ውስጣችንን ሙሉ በሙሉ አሳልፈን የሰጠናቸው ሰዎች ናቸው፡፡እነዛ ሰዎች መልካምና ቅዱስ ከሆኑ ከውስጣችን ያለውን ጥሩነት መዘው በማውጣት ተንከባክበው… አፋፍተው እና አሳድገው ጥሩ ስብዕና… መልካም ልብ እና ብሩህ ማንነት ያለው ሰው አድርገው ይሰሩናል…፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ በአጠገባችን የነበሩ ሰዎች መጥፎና ጨካኝ ከሆኑ ደግሞ ውስጣችን ጫጭቶ ተደብቆ የነበረውን ክፋት መዞ በማውጣት አውሬነታችንን ያሳድጉልናል ክፋታችንን ብስለት እንዲኖረው አድርገው ከእንደገና ሳጥናኤላዊ አድርገው ይሰሩናል፡፡
መልካም ሰው ከሆንን መልካምነታችን ከተከለለበት ሽፋን ገለጥ ገለጥ አድረገው..ከልባሳችን ፈልቅቀው ያወጡን መልካም ሰዎች እንዳሉ ሁሉ.. ክፍ ሆነንና ከመንገድ አፈንግጠን ከሆነ ለመጥፎነታችን፤ ከሀገር ባህል ለማፈንገጣችን፤ የሞራልን ህግ ለመደርመሳችን.፤ለዓለም ስጋት ለመሆናችን ምክንያት የሆኑ በክፉ ስራ ጐልብተው በክፉ ስራ የተመረቁ ሰዎች ከጀርባችን አሉ..፡፡መሰረታችን የገነቡልን እነሱ ናቸው፤ማንነታችንን የሰሩት እነሱ ናቸው፡፡ እሮዛ ክፉ ሰው አፍርሶ ከእንደገና ከሰራቸው እድለቢሶች መካከል አንዷ ነች፡፡
ሮዝ አዲስአበባ ከገባች 1 ወር አልፎታል፡፡ዲላን ለቃ ለሁለተኛ ጊዜ አዲስ አበባ መኖር በመጀመሯ ደስተኛ ነች፡፡ እርግጥ ከኩማንደር ደረሰ ጋር በተስማማችው መሰረት ሙሉውን ብር በቃላቸው መሰረት አልሰጧትም…ግን አልከፋትም፡፡300ሺ ብር አሸክመዋታል፡፡በዛም ደስተኛ ነች፡፡ይሄ ብር በጥሩ ጊዜ ነው የደረሰላት፡፡ ቢያንስ ሳትዋረድ ከመሀሪ እጅ ሾልካ እንድትወጣ አግዞታል፡፡
አሁን የምትወደውን ስራ ጀምራበታለች..22 አካባቢ ውስኪ ቤት ከፍታለች..ይሄ የዘወትር ህልሞ ነበር፡፡ይሄው ባላሰበችው ቀንና አጋጣሚ ተሳካላት፡፡ግን ሙሉ መረጋጋት አይታይባትም፡፡ ትፈራለች ..መሀሪ በህልሞ ሁሉ እየመጣ በሳንጃ ወግቷ ሲያቆስላት፤ በሽጉጥ ተኩሶ ሲገድላት፤ በገመድ ሸምቅቆ ዛፍ ላይ ሲያንጠለጥላት ነው የሚያድረው…፡፡በተለይ ኩማንደር ደረሰ መጥቷ እሷ ጋር አድሮ ስለመሀሪ የባህሪ ለውጥ በዝርዝር ካስረዳት ቡኃላ ስጋቷ ብሷል…፡፡ሰውን ማናገር እንደተወ..የለየለት ጠጪ እንደሆነ ፤እሱንም ችላ እንደለው…ዲላንም ለመልቀቅ ቅያሪ እየጠየቀ መሆኑን ካስረዳት ቡኃላ በቃ እንደጣረ ሞት ሆኖባታል…..፡፡
አሁን ግን ለጊዜው ያስጨነቃት ሌላ ነገር ነው…አንደኛ የልጆ ነገር፤ሁለተኛም የእናቷ ነገር፡፡
ልጆ ሄለን ከመጣች ጀምሮ አንድ ቀን ብቻ ነው በስልክ ያናገረቻት..ልጆ ቁርጥ ያለ ነገር ነግራታለች.-የዘመናት ጥያቄዋን አጠንክራ ‹የአባቴን ማንነት ልትነግሪኝ ካልሆነ በስተቀር ዳግመኛ እኔን ለማግኘት እንዳትደውይ›› ብላ ቁርጥ ያለውን ውሳኔዋን ከነገረቻት 15 ቀን አልፎል፡፡ እሷ ደግሞ እንደዚህ ጥያቄ መስማት ማትፈልገው..እንደዚህ ጥያቄ ሚቀፋትና ሚያስጨንቃት የለም..፡፡ምክንያም ጥያቄዋን መመለስ አትችልም፡፡..አባቷን ልትነግራት ፍጹም አትችልም…አላውቀውም ብትላትም ልታምናት አልቻለችም፡፡
ሌላው ከእናቷ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው፡፡ እናቷ አሁን አዲስአበባ ናቸው ያሉት፤ እናቷ እሷን ጥየቃ አይደለም የመጣችው… ፍጹም፡፡ አመጣጧ ወንድሞ ታሞባት ልትጠይቀው ነው፡፡ መንታዋ፡፡ይሄንን ደውላ የነገረቻት እናቷ ነች‹ ነይና አግኚኝ› ብላታለች፡፡ግን እንዴት አድርጋ ነው ጠላቷ ቤት የምትሄደው? እርግጥ አንድ ቀን እሱ ፊት ለፊት ለመቅረብ ዕቅድ ነበራት ..ያ ቀን ግን አሁን እልነበረም የመጨረሻ ዝግጅቷን ካጠናቀቀች ቡኃላ ነበር እሱ ፊት መቅረብ ምትፈልገው..ልትገድለው በወሰነች ቀን፡፡
አሁን ግራ ገብቷታል፡፡እናቷን ውጭ እንዲገናኙ ብትጠይቃትም በጣም ነው ያንዘራዘራት ስለዚህ ምርጫ ስለሌላት ለመሄድ ወስናለች፡፡ የተንጣለለ የግንብ አጥር ዙሪያውን በአደገኛ ሽቦ የተከበበ ግቢ ደረሰች፡፡መጥሪያውን ተጫነችው፡፡ልክ የሲኦል በራፍ እንደምታንኰኰ እና ሳጥናኤል መንበር ፊት እንደምትቀርብ ሆኖ ነው የተሰማት፡፡በራፉ ተከፈተ ፡፡አንድ ወገቡ ጐብደድ ያለ ዘበኛ ነበር የከፈተላት
‹‹አቤት የእኔ ልጅ..ምን ፈለግሽ?››
‹‹የአቶ ክንፈ ቤት ነው አይደል?››
‹‹ለምን ፈለግሽው ልጄ? ጌታዬ እኮ ሰው ማግኘት ካቆሙ ወራት አለፋቸው ታመው አልጋ ይዘዋል››
‹‹ጥሩ ነው››በሽታ በለገሰው ስቃይ ተደስታ
ሽማግሌው ደነገጡ‹‹ምኑ ነው ልጄ ጥሩ?››
‹‹አይ እኔ ሰው አይደለውም ማለቴ ነው››
‹‹በስመአብ በይ ልጄ..ሰውማ ሰው ነሽ እንጄ …ለዛውም ወርቅና ቆንጂዬ ልጅ››
‹‹ማለቴ እዚህ ልታሰስታምመው የመጣችው እህቱ እናቴ ነች እሷ ደውላኝ ነው፡፡››
‹‹እንዴ አጐትሽ ነዋ…››
‹‹መሰለኝ››
‹‹ወይ ልጄ አፈር በሆንኩ… ግቢ ግቢ››በራፉን ሰፋ አድርገው ከፈቱና እንድትገባ ገለል አሉላት፡፡ገባች፡፡ማራኪ የታዳጊነት ዕድሜዋን ያሳለፈችበትን ጊቤ ስትቃኝ ትዝታዋ ተቀሰቀሰባት፡፡ ..የተከለቻቸው ችግኞች..ያሳደገቻቸው አበቦች… የጥዋት ፀሀይ ትሞቅበት የነበረበት ስፋራ…ትዝታዋን እያጠነጠነች ሳሎን ገባች ማንም አልነበረ..ቁጭ አለች፡፡አብዛኛው ነገሮች እሷ በነበረችበት ጊዜ እነደነበሩ ናቸው..ይሄ ቤት ብዙ ሳቅ የሳቀችበት…ብዙ ደስታ የተደሰተችበት..ብዙ ህልም ያለመችበት ቤት ነው.፡፡በተቃራኒውም ማንነቷን ያጣችበት ፤ህልሟ የጨነገፈበት፤ተስፋዋ የወደመበት፤የህይወት መስመሯ የተሰነካከለበት ቤት ነው፡፡ከልጅነት የዕድሜ ክልል ሳትወጣ የልጅ እናት የሆነችበት ቤት ነው፡፡
‹‹እኔስ ቀረሽ ብዬ ነበር››እናቷ ናቸው ከውስጠኛው ክፍል ወደ እሷ እየመጡ የተናገሩት
‹‹እንዴ እማዬ ሰላም ነሽ?››ከቀመጠችበት ተነሳችና ተሳሳሙ ወደ መቀመጫዋ ተመልሳ ልትቀመጥ ስትል
‹‹እንዴ ነይ እንጂ አጐትሽን አናግሪው››
‹‹አጐትሽን? ››
‹‹ ምነው አዎ አጐትሽን ..ምነው ዛሬም ድረስ የተቀየመሸ መስሎሽ ነው አይደል…?በየቀኑ ያንቺን ስም ሳያነሳ አይውልም…በጊዜው እኔ በስነ ስርዓት ብከታተላት እና ብቆጣጠራት ኖሮ ለእርግዝና አትጋለጥም ነበር የእኔ ጥፋት ነው እያለ ቃላል አይፀፀትም››
‹‹በእውነት ..እንዴት ተፀፅቷል››
‹‹እያሾፍሽ ነው..?በይ ነይ አሁን አናግሪው›› ብላ እናትዬው ቀድማ መራመድ ቀጠለች፡፡ ፈራ ተባ እያለች ተከተለቻት፡፡ ልክ መኝታ ቤቱ በራፍ ጋር ሲደርሱ ድንገት የእናትዬውን ክንድ ጨምድዳ ያዘቻት፡፡ እናትዬው ደንግጣ ‹‹ምነው ፈራሽ እንዴ?››አለቻት
‹‹አይ አልፈራውም ግን ብቻዬን ብገባ ደስ ይለኛል››
እናትዬው እንደማሰብ አለችና‹‹ ጥሩ..እኔ እንደውም ማድቤት ስራ እየሰራው ነበር… መጣው ግቢ››ብላት ጥላት ሄደች፡፡
ሮዝ በራፉን ገፋ አድርጋ ገባች፡፡ሰፊው ባለ 1.80ሜ ሞዝቦልድ አልጋ ላይ ሟምቶ እና ሳስቶ የተዘረጋ አጐቷ ወደ ውስጥ የሰረጐዱ አይኖቹን እያቁለጨለጨ ወደ እሷ ተመለከተ..፡፡በዝግታ ተጠጋችና ስሩ ስትደርስ ቆማ ወደታች አዘቅዝቃ ታስተውለው ጀመረች
.‹‹ሮ..ዝዬ መጣ..ሽ?››አላት በተጐተተ ቃላት
‹‹አንተ እኔስ ገና ሞተህ ሲኦል ከገባህ ቡኃላ ቅጣትህን ምታገኘ ይመስለኝ ነበር..ለካ አንዳንዴ ዘንድሮም እግዚያብሄር ፍርዱ ፈጣን ነው ያ ሁሉ ሰውነትህ እንዲህ ይርገፍ..!ያን የመሰለው መልክህ እንዲህ ይክሰም..አጽምህ ብቻ እኮ ነው ያለው››
ዝም ብሎ እንባዎቹን እያረገፈ ዓይኖቹን እያቁለጨለጨ ምታደርገውን ይከታተላል… የምትለውን ይሰማል
👍31
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_አስራ_አንድ
:
ደራሲ:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
በነ ሄለን ቤት አዲስ ነገር ተከስቷል፡፡አያቷ ወንድማቸው መታመሙን ሰምተው ሊያዩት አዲስአባ ሄደው እንደነበር ይታወቃል..ትናንትና ግን በሰላሙ ጊዜ ያሽከረክረው በነበረው በራሱ መኪና ግን ሌላ ቅጥረኛ ሹፌር እያሽከረከረው ይዘውት መጥተዋል;; መቸስ እንዲ ባለ ደዌ ተነድፎ በዚህ ደረጃ ለታመመ ሰው ጥሩ ህክምና እንዲያገኝ ከዲላ ወደ አዲስአባ ይወሰደል እንጂ በተቃራኒው ከአዲስአባ ወደ ዲላ አይሄድም፡፡ ግን የእሱ የተለየ ስለሆነ ነው… ተስፋ ስለሌለው ነው ተስፋ እንደሌለውና ቀኑን ብቻ አንደሚጠብቅ በአዲስአባበዎቹ ሀኪሞች ስለተረጋገጠ ነው፡፡ሞት ካለ ደግሞ ቀባሪ ያስፍጋል፡፡ቀባሪ በተገቢው ቁጥር ለማግኘት ደግሞ እድር ያስፈልጋል፤ለዚህ ደግሞ የሄለን አያት የመረጡት ዲላን ነው፤ዕድሜያቸውን ሙሉ የኖሩበትን ከተማ፡፡ ሌላው የሚገርመውና በሄለን ያልተጠበቀው ነገር የእሮዝ ተከትሎ መምጣት ነው፡፡፡ትመጣለች ብላ ፈጽሞ አልጠበቀችም ነበር..ግን መጣች..ከመጣች ግን ከግቢው አልወጣችም..አታወራም አትጫወትም..ሁኔታዋን ለሚመለከት በግዳጅ በፖሊስ አስገድደው ያመጧት ይመስላል፡፡
አሁን ከጥዋቱ አራት ሰዓት ቢሆንም እስከ አሁን አላየቻትም ‹‹..ምን አልባት አላስችል ብሏት በጥዋት ተነስታ ወደ ከተማ ወጥታ ይሆናል›› ስትል አሰበች‹‹ያ ጅል ልቡ የተቃጠለ ኩማንደር አግኝቷት ጭንቅላቷን በሽጉጥ እንዳያፈርስላት››ስትል አሰበች፡፡
አያቷን ምሳ በማብሰል ታግዝበት ከነበረበት ማድ ቤት አጐቷ ወደተኛበት መኝታ ቤት አመራች፡፡እንዴት እንዳደረ ልትጠይቀው፡፡ደርሳ ገርበብ ያለውን የመኝታ ቤት በራፍ አልፋ ወደ ውስጥ እንደገባች ባለችበት ገትሮ የሚያቆማት ነገር ገጠማት፡፡
‹‹ልጅሽ ላይ ከዚህ በላይ መጨከን የለብሽም...አባቷ ማን እንደሆነ የማወቅ መብት አላት››የሚል ከደከመ ሰው አንደበት የሚወጣ ተርገብጋቢ ድምጽ በጆሮዋ ተሰነቀረ..ባለችበት በጸጥታ ለመቆም ተገደደች፡፡ሮዝም የሄለንን ንግግሩን መስማት ስታውቅ በተቀመጠችበት በድንጋጤ በድን ሆነች፡፡እሱ ግን ክፍል ውስጥ ማን እንደገባ እና ምን እየተካሄደ እንደሆነ ባለማስተዋል ንግግሩን ቀጠለ‹‹ከዚህ በላይ እልታገስሽም….አንቺ የአባቷን ማንነት ልትነግሪያት ፍላጐቱ ወይም ድፍረቱ ከሌለሽ እኔ አደርገዋው››አላት
ሮዝ አካሎን አንቀሳቀሰች..ባለችበት ጐንበስ አለችና ወደ ጀሮው በመለጠፍ በሹክሸክታ‹‹የዛሬዋ ቀን የመጨረሻህ ነች..ተመልሼ እመጣና እገድልሀለው፡፡ ከወንድምህ ከሳጥናኤል ጋርም አገናኝሀለው››ብላው ከተቀመጠችበት ተነሳችና በድን ሆና የተገተረችውን ልጆን ሄለንን ታካ በማለፍ ክፍሉን ለቃ ወጣች፡፡
ሄለን በዝግታ ወደ አጐቶ መኝታ ተጠጋች ፡፡አልጋው ጠርዙ ላይ ተቀመጠች‹‹አጐቴ ሰላም አደርክ?››
<<ደህና ነኝ ማሬ ..በጣም ደህና ነኝ›› ከህጻንነቷ ጀምሮ ማሬ ነው የሚላት.. በስሟ ጠርቷት አያውቅም፡፡
‹‹አጎቴ አባቴ ማን ነው?››ብላ ድንገተኛ ያላሰበበትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ አንጃ ለምን እናትሽን አትጠይቂያትም.?.እስከአሁን አልነገረችሽም እንዴ?››
‹‹እንዳልነገረችማ አንተም በደንብ ታውቃለህ፡፡ ከደቂቃዎች በፊት እኮ ከእሷ ጋር ስታወራ የነበረውን በራፍ ላይ ተገትሬ ሰማቼያለው››
‹‹አኸ..ሰምተሻል?››
‹‹አዎ ሰምቼያው..አሁን ንገረኝ እና የዕድሜ ልክ ጥቄዬን መልስልኝ››
‹‹እራሷን ጠይቄት ትነግርሻለች››
‹‹በእሷማ ተስፋ ቆርጬያለው…ይሄንን አንድ ጥያቄ ከተወለድኩ ጀምሮ ስጠይቃት ነበር የኖርኩት..ልትነግረኝ ግን ፍቃደኛ አይደለችም..፡፡ችግሯ ምን እንደሆነ ባይገባኝም ልትነግረኝ ፍላጐት የላትም ፡፡አንዳንዴ ሳስበው ከሰይጣን ወይም ከጭራቅ ፀንሳኝ ይሆን እንዴ? ልትነግረኝ ሚያሸማቅቃት ›ስል አስባለው፡፡››
‹‹ምንም ይሁን ምንም ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ ጠይቂያት ትነግርሻለች››
‹‹ካልነገረቺኝስ?››
‹‹ነገ ጥዋት ሁለት ሰአት እኔ ጋር ነይ ስለአባትሽ የማውቀውን ነገር ሁሉ እንግርሻለው፡፡››
‹‹ፕሮሚስ?››
‹‹ፕሮሚስ፡፡››
ጐንበስ ብላ የጐደጐደ ጉንጩን በደስታ ሳመቺው እና‹‹እሺ አጐቴ ቻው እግዜር ይስጥልኝ ..ጥዋት ተመልሼ እንደምመጣ አረጋግጥልሀለው..ምክንያቱም እሷ እንደማትነግረኝ እርግጠኛ ነኝ›› በማለት ከተቀመጠችበት ተነስታ ለመሄድ ፊቷን ስታዞር
‹‹ማሬ ››ሲል ጠራት በተለመደው የደከመ ድምጽ
‹‹አቤት አጐቴ››
‹‹እዛ ሻንጣ ውስጥ አንድ ሰማያዊ የጨርቅ ቦርሳ አለ ታቀብይኝ››
‹‹ችግር የለም አጐቴ ብላ ኮርነር ላይ ወደተቀመጠው ግዙፍ ሻንጣ አመራች እና ካላት ቦርሳ ከውስጥ በርብራ በማውጣት አቀበለችው››
‹‹ያንቺው ነው፡፡ ስጦታ ነው››
‹‹ምንድነው አጐቴ?›››
‹‹ክፍልሽ ገብተሸ እይው››
‹‹እሺ እንዳልክ አጐቴ፡፡ አመሰግናለው፡፡›› ብላ ዳግመኛ ግንባሩን ሳመችውና ወደ ራሷ ክፍል አመራች፡፡በራፉን ከውስጥ ቀረቀረች፡፡ ጫማዋን እያፈናጠረች አውልቃ አልጋዋ ላይ ዘላ ወጣች..እንደጫት ቃሚ እግሮቾን አነባብራ ተቀመጠችና አጐቷ የሰጣትን ቦርሳ በዝግታ ከፈተችው፡፡በውስጡ ያገኘችው ፈጽሞ ያልጠበቀችው ነገር ነው፡፡ከእሽጉ ያልወጣ እጅ ያልነካው መዓት ድፍን ባለ መቶ ብር ኖት…በአድናቆት ሁሉንም ዘረገፈችና ቆጠረችው፡፡ 15 ነው ፡፡ሂሳቡን ስትሰራው 150 ሺ ብር ሆነ ፡፡መልሳ ወደ ቦርሳው ከተተችውና ዚፑን ዘጋችው፡፡ከአልጋዋ ወረደች ፤ጫማዋን አደረገችና ወደ አጐቶ ተመለሰች
‹‹አጐቴ››
‹‹ወዬ ማሬ››
‹‹ተሳስተህ እኮ ሌላ እቃ ነው የሰጠኸኝ..ይሄ ብር ነው››
‹‹አልተአሳሳትኩም››
‹‹እንዴት?››አለች ደንግጣ
‹‹ያንቺው ነው..በዕድሜ ገና ብትሆኜም በአዕምሮ የበሰልሽ መሆንሽን አውቃለው...ስለዚህ ይሄንን ብር እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለብሽ እንደምታውቂ አምናለው፡፡ይሄንን ብር ማንም ሳያውቅ ቀጥታ ለአንቺ የሰጠውሽ በጣም ስለምወድሽ እና ብሩን በፈለግሽው መንገድ ለፈግሽው ጉዳይ እንድትጠቀሚበት ስለምፈልግ ነው፡፡››
‹‹አመሰግናለው፡፡ እኔም እወድሀለው፡፡›› ብላው ለሶስተኛ ጊዜ ሳመችውና እየፈነጠዘችም እየተገረመችም ወደ ክፍሏ ተመልሳ ሄደች፡፡
አዎ ዛሬ ብዙ ስራ ይጠብቃታል፡፡ አጐቷ እንደመከራት እናቷን ለመጨረሻ ጊዜ የአባቷን ማንነት እደትነግራት ትጠይቃታለች፡፡ከነገረቻት መልካም በመሀከላቸው ከሮ የኖረው ጠብም ፈጽሞ ይጠፋል ባይባልም በመጠኑ በረድ ይላል ማለት ነው..፡፡ እንደከዚህ ቀደሙ አሻፈረኝ ብላ አልነግርሽም ካለቻትም ምንም አይደል፡፡ እንደከዚህ ቀደሙ በመረረ ሁኔታ ሀዘን አይሰማትም..ምክንያቱም እስከነገ ጥዋት ብቻ ነው መጠበቅ የሚገባት፡፡ ለእሷ አሳቢ ..ለእሷ ተቆርቋሪ የሆነው አጐቷ እንደሚነግራት እርግጠኛ ነች፡፡እንደዛ ከሆነ… የአባቷን ማንነት ከአጐቷ አንደበት ለመስማት ከተገደደች ግን ሮዝን መቼም ይቅር አትላትም..እንደጠላቻት ትኖራች..ይሄ እምነቷ ነው፡፡በዚህም ሆነ በዛ የአባቷን ማንነት ካወቀች ቡኋላ ግን የብር ችግር ስለሌለባት ህልሞን ታሳካለች..፡፡አባቷ በህይወት ካለ ፈልጋ ታገኘዋለች ..ታወራዋለች..አስራ አንድ አመት ሙሉ ስትናፍቀው እንደኖረች እያለቀሰች ትነግረዋለች..፡፡ሞቶም ከሆነ ቤተሰቦቹን ፍልጋ ትተዋወቃቸዋለች…አዎ ይሄ እቅዷ ነው..ከዛ ቡኃላ ዕድሜዋን ሙል ሲሰማት የኖረው የባዶነት ክፍተት በመጠኑ ይደፈን ይሆናል….።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2