አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
471 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


....መጪውን እየፈራሁም ቢሆን እጇ ባዶ ሲሆን ልቀርባት እየጠበቅኩ ነበር። አያትየው ወደ ክሪስ ስለማትመለከትና መንትዮቹ ደግሞ ከመፍራታቸው
የተነሳ እሷ ስትኖር ስለሚንቀጠቀጡ፣ የሰራንላትን ስጦታ መስጠት የኔ ኃላፊነት ነበር. ግን እግሬን እንኳን ማንቀሳቀስ አልቻልኩም: ድንገት ክሪስ በክንዱ ጎሸም አድርጎኝ “ቀጥይ” ሲል አንሾካሾከልኝ፡፡ “በሆነው ደቂቃ ከክፍሉ ትወጣለች”

እግሮቼ ከወለሉ ጋር በሚስማር የተጣበቁ መሰለኝ፡ በሁለቱ እጆቼ ረጅም ቀይ እሽግ ይዣለሁ፡ ከቆምኩበት ቦታ ሲታይ መስዋዕት የማቅረብ ነገር ይመስል
ነበር ምክንያቱም እስከዛሬ ስትሰጠን የነበረው ክፋት ስለነበረና አሁንም የባሰ
ህመም ልትሰጠን እድል እየጠበቀች ያለች ስለሆነች ለሷ ስጦታ መስጠት ቀላል አልነበረ።

በዚያ የገና ጠዋት ካለ አለንጋና ካለ ምንም ቃል ለሁላችንም ህመም መስጠት ተሳክቶላት ነበር በትክክለኛው መንገድ “መልካም ገና አያቴ። ትንሽ ስጦታ ልንሰጥሽ ነበር። እንድታመሰግኝን አይደለም:: ችግር የለውም በየቀኑ ምግብ ስለምታመጪልንና መጠለያ ስለሰጠሸን ለማመስገን ያህል ትንሽ ስጦታ ልንሰጥሽ ነው:” ልላት ነበር፡ ግን አይሆንም እንደዚያ ብላት እያፌዝኩባት
ይመስላት ይሆናል፡ የሚሻለው ዝም ብዬ “መልካም ገና፣ ይህንን ስጦታ እንደምትወጂው ተስፋ አለን ኮሪና ኬሪን ጨምሮ ሁላችንም ነን የሰራንልሽ፡”

ገና ስጦታውን ይዤ ስቀርባት ስታይ እጅግ ተደነቀች።

“በቀስታ አይኖቼ በድፍረት አይኖቿን ለማየት ቀና እያሉ የገና መስዋዕታችንን አቀረብኩ፡ በአይኖቼ ልለምናት አልፈለግኩም ግን እንድትወስደው፣
እንድትወደውና ቀዝቀዝ ብላም ቢሆን “አመሰግናለሁ” እንድትል ፈልጌያለሁ።ዛሬ ማታ ወደ መኝታዋ ስትሄድ ስለኛ እንድታስብ መጥፎ ልጆች እንዳልሆንን
እንድትረዳ ፈልጌያለሁ፡ ለእሷ ስጦታ ለመስራት የለፋነውን እንድታስብና እኛን የምታስደናግድበት መንገድ ትክክል ነው ወይስ ስህተት ብላ ራሷን እንድትጠይቅ ፈልጌያለሁ።

እጅግ በከፋ መንገድ ቀዝቃዛና የንቀት አይኖቿን በቀይ ወዳሰርነው ረጅም ሳጥን ዝቅ አደረገች፡ ላዩ ላይ ካርድ አለ ካርዱ ላይ “ለአያታችን ከክሪስ፣
ካቲ፣ ኮሪና ኬሪ” የሚል ተፅፎበታል: በግራጫ ድንጋይ አይኖቿ ካርዱን ረዘም ላለ ጊዜ ተመለከተች። ከዚያ አትኩሮቷን ቀጥታ ወደ እኔ ተስፋ የተሞሉ፣ የሚለምኑ፣ ክፉ አለመሆናችንን ማረጋገጥ የሚሹ አይኖቼ ላይ
አደረገች ከዚያ ወደ ስጦታው፣ ከዚያ ሆን ብላ ጀርባዋን አዞረችና ቃል ሳትናገር ከበሩ ወጥታ በሩን በሀይል ወርውራ ዘጋችና ቆለፈችው: እኔም የብዙ ረጃጅም ሰአታት ውበት የመስጠት ትጋት ውጤት የሆነውን ስጦታ
በእጆቼ እንደያዝኩ ክፍሉ መካከል ቆሜ ቀረሁ።

ጅሎች! የማንረባ ጅሎች!

አላግባባናትም:: ሁልጊዜም ከሰይጣን የተፈለፈልን አድርጋ ነው የምትቆጥረን!
እሷን በተመለከተ እኛ አልተፈጠርንም ይጎዳል፡ እስከ ውስጥ እግሬ ድረስ ዘልቆ አመመኝ፡ ልቤ ወደ ደረቴ ህመም የሚልክ የተቀደደ ኳስ መሰለኝ፡
ከኋላዬ ክሪስ በፍጥነት ወደ ውስጥና ወደ ውጪ ሲተነፍስና መንትዮቹ ሲነጫነጩ ይሰማኛል።

ይህ ትልቅ የመሆኛ ጊዜዬ ነው፤ እናታችን በትክክልና ውጤታማ በሆነ መንገድ የምትጠቀምበትን ራስን የመቆጣጠር ዘዴ ተግባራዊ የማደርግበት ጊዜ ነው: እንቅስቃሴዬንና ፊቴ ላይ ያለውን ስሜት ከእናቴ ኮረጅኩ።
እጆቼን እሷ እንደምታደርገው አደረግኩ በቀስታና በማታለል አይነት እሷ እንደምታደርገው ፈገግ አልኩ

ከዚያስ? መብሰሌን ለማሳየት ምን አደረግኩ?

ስጦታውን ወለሉ ላይ ጣልኩት! ከዚህ በፊት ጮክ ብዬ ተናግሬያቸው የማላውቃቸውን ቃላት እየተናገርኩ፣ እግሬን አንስቼ ረገጥኩትና መያዣው ሲሰበር እየሰማሁ ጮህኩ! በሁለቱም እግሮቼ ላዩ ላይ ዘለልኩበት ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ያገኘነውና ስጦታውን የሰራንበት የሚያምር ፍሬም እንክትክቱ እስኪወጣ ድረስ ላዩ ላይ ጨፈርኩበት ከድንጋይ የተሰራችን ሴት እንድናግባባ የመከረኝን ክሪስን ጠላሁት እንደዚህ አይነት ቦታ እንድንኖር ስላደረገችን እናቴን ጠላኋት!

እናቷን የተሻለ ልታውቃት ይገባ ነበር እዚህ አምጥታን ውርስ ከምትጠብቅ ሱቅ ውስጥ ጫማ መሸጥ ትችል ነበር። አሁን ካደረገችው የተሻለ ነገር
ማድረግ ትችል ነበር።

በአንድ እብድ አውሬ ጥቃት ስር ደረቁ ፍሬም ብትንትኑ ወጣ ልፋታችንም ሄደ፡

“አቁሚ! ለራሳችን እናስቀምጠዋለን፡” አለ ክሪስ

ሙሉ በሙሉ መበላሸቱን ለመከላከል ፈጥኖ ቢደርስም ስዕሉ ግን ተበላሽቶ
ነበር ለዘለዓለም ሄዶ ነበር አለቀስኩ፡

ስንሰቀሰቅ ክሪስ በክንዶቹ አቅፎኝ በአባትነት ቃና “አይዞሽ ምንም አይደል። ያደረገችው ነገር ችግር የለውም፡ እኛ ትክክል ነን፡ የተሳሳተችው እሷ ናት። እኛ ልንቀርባት ሞክረናል፡ እሷ ናት በፍፁም ያልሞከረችው" አለኝ:

በስጦታዎቻችን መካከል ወለሉ ላይ በፀጥታ ተቀመጥን፡ መንትዮቹ ትልልቅ አይኖቻቸው በጥርጣሬ ተሞልተው ፀጥ ብለዋል፡ በአሻንጉሊቶቻቸው
መጫወት ቢፈልጉም፣ የእኛ መስታወቶች በመሆናቸውና ምንም ብንሆን የእኛን ስሜት የሚያንፀባርቁ በመሆኑ መወሰን አልቻሉም: እነሱን የማየት
ሀዘን እንደገና አሳመመኝ።

እናታችን ፈገግ ብላና የገና ሰላምታዋን አስቀድማ ወደ ክፍላችን ስትመጣ ተጨማሪ ስጦታዎች ይዛ ነበር ከነዚያም መሀል ድሮ የእሷና በጥላቻ
የተሞላች እናቷ የነበረ ትልቅ የአሻንጉሊት ቤት ይገኝበታል። “ይሄ ለኮሪ ለኬሪ የኔ ስጦታ ነው:" አለችና ሁለቱንም አቅፋ ጉንጮቻቸውን ሳመች።ከዚያ እሷ የአምስት አመት ልጅ የነበረች ጊዜ ታደርግ እንደነበረው “የውሸት
ወላጆች፣ የውሽት ቤት” እያደረጉ እንዲጫወቱ ነገረቻቸው።

ብታስተውል አንዳችንም በዚያ የአሻንጉሊት ቤት አልተደሰትንም ነበር።አስተያየት አልሰጠችም: በደስታ እየሳቀች ወለሉ ላይ እንደመንበርከክ ብላ
ተረከዟ ላይ ቁጢጥ አለችና ይህንን የአሻንጉሊት ቤት እንዴት ትወደው እንደነበረ ነገረችን

“ካቲ” አለች እናቴ ክንዷን አንገቴ ላይ አድርጋ፣ “ይህንን ትንሽ ጨርቅ ተመልከቺ ከንፁህ ሀር የተሰራ ነው፡፡ በምግብ ቤት ውስጥ ያለው ደግሞ
ኦሪየንታል ምንጣፍ ነው" አለችኝ የአሻንጉሊቱ ቤት ውስጥ ያሉትን ዋጋ ያላቸው ነገሮች በመጥራት፡

“አሮጌ ሆኖ እንዴት አዲስ ሊመስል ቻለ?” ስል ጠየቅኳት።

በእናታችን ላይ ጥቁር ደመና ሲያጠላና ፊቷን ሲሸፍናት አየሁ። “የእናቴ በነበረበት ወቅት በመስተዋት ሳጥን የተሸፈነ ነበር። እንድትመለከተው እንጂ
እንድትነካው አይፈቀድላትም ነበር። ለእኔ ሲሰጠኝ አባቴ የመስተዋቱን ሳጥን በመዶሻ ሰበረውና እጄን መፅሀፍ ቅዱስ ላይ አስደርጎ ምንም ነገር
እንዳልሰብር ካስማለኝ በኋላ በሁሉም ነገር እንድጫወት ፈቀደልኝ

“ከማልሽ በኋላ የሆነ ነገር ሰበርሽ?” ክሪስ ጠየቃት።

“አዎ ከማልኩ በኋላ አንድ ነገር ሰበርኩ" አንገቷን ስላቀረቀረች ፊቷን ማየት አልቻልንም “በጣም ቆንጆ ወጣት ሆኖ የተሰራ ሌላ አሻንጉሊት ነበር እና ኮቱን ላወልቅለት ስሞክር እጁ ወለቀ ከዚያ አሻንጉሊቱን ስለሰበርኩ
ብቻ ሳይሆን ከልብሱ ስር ያለው ምን እንደሆነ ለማወቅ በመፈለጌ ጭምር ተገረፍኩ።"

እኔና ክሪስ ዝም ብለን ስንቀመጥ ኬሪ ግን ቀልቧ የሚያምር ባለቀለም ልብስ የለበሱት ትንንሽ የሚያስቁ አሻንጉሊቶች ላይ አረፈ፡ እሷ ፍላጎት ስላደረባት

ኮሪም በአሻንጉሊት ቤቱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች መመርመር ጀመረ:

የዚህን ጊዜ ነው እናታችን ትኩረቷን ወደኔ ያደረገችው ካቲ እኔ ስመጣ ምን ሆነሽ ነው ቅር ብሎሽ የነበረው? ስጦታዎችሽን አልወደድሻቸውም? አለች:
👍431
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ

.....የሚያንቀጠቅጥ ሀሳብ መጣብኝı ኬሪ ወይም ኮሪ የሆነ ነገር ሊሰብሩ ቢችሉ ቅጣቱ ምን ሊሆን እንደሚችል!.

እናታችን ቃሏን በመጠበቅ መንትዮቹ ከተኙ በኋላ ወደ ክፍላችን መጣች::በጣም ቆንጆ ከመሆኗ የተነሳ ልቤ በኩራት፣ በአድናቆትና በትንሹ በቅናት
አበጠ የለበሰችው ልብስ ጆሮዎቿ ላይ በረጅሙ ከተንጠለጠሉትና ከሚያበሩት የአልማዝና ኤሜራልድ የጆሮ ጌጦች ጋር አብሮ ያንፀባርቃል። ጠረኗ
በምስራቅ ያለ በጨረቃ ብርሀን የደመቀ ሽቶ ሽቶ የሚሽት የአትክልት ስፍራን አስታወሰኝ፡፡ ክሪስ ፍዝዝ ብሎ እሷ ላይ ማፍጠጡ ምንም አያስገርምም::
በከባዱ ተነፈስኩ፡ አምላኬ እባክህ አንድ ቀን… እንደ እሷ እንድመስልና ወንዶች እጅግ የሚያደንቁት ገባ ያለ ወገብ እንዲኖረኝ አድርግ።

ስትራመድ ግራና ቀኝ ያለው የልብሷ ዘርፍ እንደ ክንፍ ከፍና ዝቅ እያለ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚያ ደብዛዛ ብርሃን ካለው ክፍል ወጣን፡ የእናታችንን ኮቴ
እየተከተልን በሰሜን አቅጣጫ ባሉት ጨለማማ ሰፊ አዳራሾች በኩል መሄድ ጀመርን፡ “ልጅ እያለሁ ትልልቅ ሰዎች ሲደንሱ ለማየት ወላጆቼ ሳያውቁ
የምደበቅበት ቦታ ነበር” ስትል አንሾካሾከች: “ለሁለታችሁ ይጠባችኋል። ግን ተደብቃችሁ ልታዩ የምትችሉበት ቦታ ያ ብቻ ነው: በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን አንድም ድምፅ እንደማታሰሙ እንደገና ቃል እንድትገቡልኝ
እፈልጋለሁ እንቅልፋችሁ ከመጣ ቀስ ብላችሁ ሳትታዩ ወደ ክፍላችሁ ሂዱ እንዴት እዚያ እንደምትደርሱ አስታውሱ:” መንትዮቹ ድንገት ከእንቅልቻቸው ነቅተው ፍርሀት እንዳይስማቸው ከአንድ ሰዓት የበለጠ
እንዳንቆይ አስጠነቀቀችን፡ ምናልባትም እኛን ፍለጋ ሊወጡና አዳራሹ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሊሉ ይችሉ ይሆናል። እንደዚያ ካደረጉ ምን ሊፈጠር
እንደሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው።

በሚስጥር ከስሩ በሮች ያሉት ትልቅ ጠረጴዛ ስር ገባን፡ የማይመችና በጣም ጠባብ ነው፡ ግን ከጀርባው ባለው መስኮት መስል ክፍተት በደንብ መመልከት
እንችላለን፡

እናታችን በፀጥታ ሹልክ አለች።

እኛ ካለንበት በታች ራቅ ብሎ በሚያምር ሁኔታ በሻማ ብርሀን ያጌጠ ክፍል ተመለከትን፡ በህይወቴ እንደዚህ የበዙ ሻማዎች አንድ ላይ ሲበሩ አይቼ
አላውቅም! የሻማዎቹ ሽታ እንዲሁም ብርሃኑ ሴቶቹ ያደረጓቸው ጌጣጌጦች
ላይ ሲያርፍ ያለው ማንፀባረቅ ምትሀታዊና ፊልም ላይ ሲንዴሬላና ልዑሉ የደነሱበትን ቦታ ይመስል ነበር።

በመቶ የሚቆጠሩ እንደ ሀብታም የለበሱ ሰዎች እየሳቁና እያወሩ ነው: ጥግ ላይ ደግሞ ለማመን የሚከብድ የገና ዛፍ ተቀምጧል እጅግ በጣም ትልቅ ሲሆን ባለቀለም ጌጣጌጦች ተደርገውበታል፡ ላዩ ላይ የተደረጉት በመቶዎች
የሚቆጠሩ ወርቃማ መብራቶች አይን ያፈዛሉ በዳንሱ ክፍል ውስጥ ወጣ ገባ እያሉ በትሪዎች ላይ ምግብ ይዘው ትልቅ ጠረጴዛ ላይ ይደረድራሉ፡ ሁሉም
ነገር ውብ፣ የሚያምርና የሚያስደንቅ ነበር ... እናም ከተቆለፈ በር ውጪ ደስተኛ ህይወት መኖሩን ማወቅ ጥሩ ነው።

"ካቲ…” ክሪስ በጆሮዬ እያንሾካሾከ “ከዚያ ጥርት ካለው መጠጥ አንድ ጊዜ ፉት ለማለት ነፍሴን ለሰይጣን እሸጣለሁ” አለ።

የእኔም ሀሳብ ነበር ...

እንደዛሬ ርሀብ፣ ጥማትና መከልከል ተሰምቶኝ አያውቅም: ሆኖም ግን ሁለታችንም ታላቅ ሀብት ሊገዛውና ሊያስገኘው በሚችለው ድምቀት ተገረምን፡ ጥንዶች የሚደንሱበት ወለል በሰም ተወልውሎ እንደ መስተዋት
ያንፀባርቃል፡ ትልልቅ ወርቃማ ፍሬሞች ያሏቸው በክፍሉ ውስጥ ያሉት መስታዎቶች የዳንሰኞቹን ምስል ሲያንፀባርቁ ሲታይ የትኛው እውነተኛ ምስል እንደሆነ እንኳ ለመለየት ያስቸግር ነበር።

እኔና ክሪስ ወጣትና ቆንጆ በሆኑት ጥንዶች ላይ አፍጥጠን ነበር፡ ስለ
ልብሳቸው፣ የፀጉር አሰራራቸውና ስላላቸው ግንኙነት በመገመት አስተያየት እንሰጥ ነበር ከሁሉም በላይ ግን የትኩረት ማዕከል የነበረችውን እናታችንን እያየን ነበር፡ በአብዛኛው ከአንድ ረጅም፣መልከመልካም፣ ጥቁር ፀጉርና ረጅም ፂም ካለው ሰው ጋር እየደነሰች ነበር: የምትበላውንና የምትጠጣውንም
ያመጣላት እሱ ነበር ምግቡን ይዛ ሶፋ ላይ ተቀምጠው መብላት ጀመሩ።በጣም ተጠጋግተው እንደተቀመጡ አሰብኩ። በፍጥነት አይኖቼን ከእነርሱ መልሼ ከትልልቆቹ ጠረጴዛዎች ኀላ ወደ ቆሙት ሶስት ምግብ አብሳዮች
አተኮርኩ አሁንም ምግብ እየሰሩ ነው የምግቦቹ ሽታ ወደኛ ደርሶ የምራቅ እጢዎቻችንን በኃይል እንዲሰሩ አደረጋቸው፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እናታችን ከዚያ ሰው ጋር ትሰወራለች የት ነው የሚሄዱት?ምንድነው የሚሰሩት? እየተሳሳሙ ነው? ፍቅር ይዟታል? ካለንበት ከዚያ ርቀት ላይ ሆነን እንኳ ሰውየው በእናታችን እንደተማረከ መናገር እችላለሁ:
አይኑን ከፊቷ ላይ መንቀል አልቻለም፧ እጆቹም እሷን ከመንካት መከልከል
አልቻለም::

ቀስ ባለ ሙዚቃ ሲደንሱ፣ ጉንጯ ጉንጩን እስኪነካ ድረስ አስጠግቶ ይዟት ነበር ዳንሱን ሲጨርሱ እጁን ትከሻዎቿ ወይም ወገቧ ላይ ያደርጋል። አንድ ጊዜ እንደውም ጡቷን እስከ መንካት ሳይቀር ደፍሯል።

አሁን ይህንን መልከ መልካም ፊቱን በጥፊ ትለዋለች ብዬ አሰብኩ። ምክንያቱም እኔ ብሆን እንደዚያ ነበር የማደርገው: እሷ ግን ዞር አለችና ሳቀች ከዚያ ገፋ አደረገችውና በአደባባይ እንደዚያ እንዳያደርግ ማስጠንቀቂያ
ሊሆን ይችላል የሆነ ነገር አለችው: እሱም ፈገግ ብሎ እጇን ያዘና ወደ ከንፈሩ አስጠጋው ከዚያ አይኖቻቸው ረጅምና ትርጉም ያለው እይታ ተለዋወጡ:
ወይም እንደዚያ እንደሆነ አሰብኩ

“ክሪስ እናታችንን ከዚያ ሰው ጋር አየሀት?”

“አዎ አይቻቸዋለሁ ልክ እንደ አባታችን ረጅም ነው።”

“አሁን ያደረገውን አይተሀል?”
“ልክ እንደሌሎቹ እየበሉና እየጠጡ፣ እየሳቁና እያወሩ እንዲሁም እየደነሱ ነው: አስቢው ካቲ… እናታችን ያንን ሁሉ ገንዘብ ስትወርስ እንደዚህ አይነት
ድግሶች ለገና እና ለልደቶቻችን እንደግሳለን፡ አሁን ያየናቸውን እንግዶች ወደፊት እናገኛቸው ይሆናል። ግላድስተን ላሉት ጓደኞቻችን የግብዣ ወረቀት
እንልክላቸዋለን፡ አቤት! የወረስነውን ሲመለከቱ በጣም ነው የሚገረሙት"አለ፡፡

ወዲያው አያታችን ወደ ዳንስ ክፍሉ ገባች: ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልተመለከተችም ለማንምም ፈገግታ አላሳየችም
ቀሚሷ ግራጫ አልነበረም።
እኛን ለማስደነቅ ያ ብቻውን በቂ ነበር ፀጉሯ በሚገባ ተሰርቷል። አንገቷ፣ጆሮዎቿ ክንዶቿና ጣቶቿ በአልማዝና በሩቢ ጌጣጌጦች አሸብርቀዋል።ያቺ አስደናቂ ንጉሳዊ ግርማ ሞገስ ያላት ሴት በየቀኑ የምትጎበኘን አስፈሪ
አያታችን መሆኗን ማን ያምናል?

ፈቃደኛ ባንሆንም አሁንም አሁንም በሹክሹክታ “እጅግ አስደናቂ ሆናለች '' ብለን አመንን

“አዎ በጣም አስገራሚ”

የዚህን ጊዜ ነው የማናውቀውን ወንድ አያታችንን ያየነው!

ወደ ታች መመልከቴ ትንፋሼን ቀጥ አደረገው ያየሁት ሰው በጣም አባቴን ይመስላል አባታችን እስከሚያረጅ ድረስ በህይወት ቢኖር ኖሮ ይህን ሰው
እንደሚመስል ማየት ይቻላል በሚገፋ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ቶክሲዶ ለብሷል። ሸሚዙ ጥቁር ቁልፍ ያለበት ነጭ ሸሚዝ ነበር፡ የሳሳው ወርቃማ ፀጉሩ ነጭ ወደ መሆን ሄዶ፣ በብርሃን ሲታይ ብርማ መስሎ ያንፀባርቃል።
ቆዳው ደግሞ የተደበቅንበት ቦታ ላይ ሆነን በሩቅ እያየነው ስለሆነ ሊሆን ይችላል፣ አልተጨማደደም: እኔና ክሪስ በመደንገጥና በመገረም አንድ ጊዜ ካየነው ጀምሮ አይኖችንን ወዴትም አላንቀሳቀስንም፡
👍37🥰2👏2