አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

..ፊሬንዜ ውብ ከተማ ናት፤ የነጻንቴ የነሚኪኤል አንጀሎ ከተማ!

አንዲት ትንሽ ሬስቶራንት ውስጥ እራት ስንበላ ነበር፡፡ ሲልቪ
ምግቧን ረስታ ወደ ኋላዬ በኩል ትኩር ብላ ማየት ጀመረች።
ሳይታወቃት በግራ እጂ ፀጉሯን አስተካከለች ብቻ መስተካከል
አያስፈልገውም ነበር። ገባኝ። የምትጎመጀው ወንድ አይታ መሆን አለበት። ሹካና ቢላዋን ቁጭ አድርጋ ወይን አንስታ ፉት አለችና፣ ብርጭቆውን መልሳ እንደማስቀመጥ፣ በእጆቿ ውስጥ በዝግታ እያሽከረከረችው ወደዚያው ወደ ኋላዬ ማየቷን ቀጠለች። ቀይ ከንፈሮቿ ገርበብ፣ በወይን ረጠብ ብለው ያስጎመጃሉ

እሷ ወደዚያ ስታይ እኔ እሷን ስመለከት፣ ቆንጆ ፊቷ ቀስ ብሎ
ፈገግ አለ፤ ሰማያዊ ኣይኖቿ ስልምልም ማለት ጀመሩ። ምኞቱ
ውስጤ ሲያድግ ተሰማኝ፡፡ አይኖቿ ከአይኖቼ ጋር ተጋጠሙ፣ ፊቷ መቅላት ጀመረ፡ አይኖቿ ተርገበገቡ። ሰውየው ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለግኩ፡ ግን ወደኋላ ከተገላመጥኩ ነገሩ ይበላሻል፣ ስለዚህ ተውኩት

«ፍሬ ይምጣልሽ?» አልኳት
«የለም በቃኝ። አንተ ብላ »
«እኔም በቅቶኛል»
«እንግዲያው እንሂድ?» አለችኝ፣ ወደ ቅድሙ በኩል እያየች
ስንወጣ እሷ ታተኩርበት ወደነበረው በኩል ተመለከትኩ፡፡
በየጠረጴዛው የተበታተኑ አንድ አምስት ወንዶች አሉ፡ የትኛው
ፍላጎቷን እንደ ቀሰቀሰ ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ ግን ፍላጐቷ በሀይል ተቀስቅሷል። አልጋ ውስጥ ስንገባ መብራቱን አጠፋችው፣ እየተንገበገበች አቀፈችኝ፤ በመጨረሻ ላይ በእንግሊዝኛ ቃዥች

«Please, my lord! Please, have mercy!

ሌላ ሰው ሆኜ፣ ግን ማን እንደሆንኩ ሳላውቅ፣ በቅንዝርና
በቅናት እየተቃጠልኩ፣ ጥልቅ የሆነ ስጋዊ ደስታን ተደሰትኩ።
በነጋታው ቀኝ ጡቷን እያመማት ዋለ። ሳይታወቀኝ ጨፍልቄው
ኖሯል በሌላ ቀን፣ «ማን ሆኜ ነበር?» አልኳት። ስንበላ በስተኋላዬ አንድ ሰውዬ እይታ ኖሯል። «ልክ ስመ ጥሩውን ባለቅኔ ሎርድ ሳይረንን ይመስል ነበር አለችኝ እንደዚሀ ስንል፣ እሷ ደስ የሚላትን ወንድ ስታይ፤ እኔ በጭለማ እሱን እየሆንኩ ሳቅፋት እሷ ስትቃዥ፣ እኔ ስነክሳት ስጨፈልቃት፣ እንደዚህ ስንል፣ በሰማያዊ, አይኖቿ ብርሀንና በሰፊ አፏ ሳቅ እያሞቀችኝ፣ በውብ ወጣት ገላዋ እያቃጠለችኝ፡የጣልያንን ከተማዎች እያዞረችኝ «Je men fous» አያለች አያሳቀችኝ፣ እንደዚህ ስንል የበጋው እረፍት ወደ ማለቂያው ተቃረበ፡፡ ከፊሬንዜ ሮማ
ከሮማ ናፖሊ፤ ከናፖሊ ኒስ (ፈረንሳይ) ከኒስ ማርሰይ ተጓዝን።

ከማርሰይ እሷ ቤቶቿን ጥየቃ ፓሪስ ሄደች፡፡ ባቡር ጣቢያው
ሄጄ ስሸኛት ልክ የዛሬ ዘጠኝ ቀን ማክሰኞ ኤክስ እገባለሁ፤ ማታ
ቤቴ እጠብቅሀለሁ» አለችኝ
የሲልቪ ናፍቆት የሚገድለኝ መስሎኝ፤ ዘጠኝ ቀን ሙሉ
እንዴት ሊያልፍልኝ ነው? እያልኩ ስሰጋ ነበር፡፡ ግን ባቡሩ ይዟት
እንደሄደ፣ በሀዘን ፈንታ እፎይታ ተሰማኝ፡፡ ማታ አልጋ ውስጥ
ገብቼ ብቻዬን እንደ ልቤ ስገላበጥ፣ ብቸኝነት ሳይሆን ምቾት ተሰማኝ፡፡ ምቾቴ በደምብ እንዲታወቀኝ ስል በብዙ ተገላበጠኩ።ጧት ስነቃ ሲልቪ የለችም፡ ብቻዬን ነኝ፡፡ በናፍቆት ፈንታ ደስታ ተሰማኝ፡፡ ሲልቪ ሰልችታኝ ኖሯል? ወይስ ከሰው ጋር ለመኖር አልተፈጠርኩም? ሊገባኝ አልቻለም

ኤክስ ሄጄ ሲቴ (ዩኒቨርሲቲ) ውስጥ አንድ የመኝታ ክፍል
ተቀበልኩ፡ ሁለተኛው አመት ወደ መጀመሩ ነበር ጧት ስነሳ በመስኮቱ ደማቅ ሰማያዊ የሆነ ንፁህ ሰማይ ታየኝ።ደስ አለኝ። ሳይታወቀኝ የኤክስ ውብ ሰማይ ናፍቆኝ ኖሯል
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ባህራም ከቅርብ

ኤክስ እንደተመለስኩ መጀመሪያ ያገኘሁት ተካን ነበር፡፡ ያው
እንደ ልማዱ ጥፍሩን እየነከሰ፣ የት ነበርክ? ከማን ጋር ነበርክ? ምን
አደረግክ? ምን አየህ? እያለ በጥያቄ አጣደፈኝ፡፡ ግን ሳየው የጥርሱ መበለዝ የቀነሰ መሰለኝ፡፡ አፉም አልገማኝም፡፡ ጊዜው ከእራት በኋላ ነበር፤ ና ቡና ላጠጣህ ብሎ ወደ ክፍሉ ወሰደኝ፡፡ ቤቱ በጭራሽ
አይገማም!

እንግዲህ፣ የዩኒቨርሲቲው መኝታ ቤቶች ባለ ሶስት ፎቅ
ሲሆኑ፣ እያንዳንዱ ፎቅ ላይ ለሚገኙት ሰላሳ ያህል ክፍሎች የጋራ የሆኑ አንድ የገላ መታጠቢያ ክፍልና፣ አጠገቡ ደግሞ (ልክ ደረጃው መጨረሻ ላይ) አንድ የቡና ማፍያ ምድጃ ያለው ክፍል አላቸው።ተካ ቡናውን ሊጥድ ወደ ማፍያው ክፍል ሲሄድ እኔ የሱን መኝታ ክፍል ተመለከትኩ፡፡ ንፁህ ነው። ፊት መታጠቢያው ዘንድ፡ ግማሹ ያለቀ ኮልጌት የጥርስ ሳሙናና አንድ የጥርስ ብሩሽ አለ። ተካ ጥርሱን ይቦርሻል! ምን ነካው?. ምን ይነካዋል? ያው
የተለመደው መሆን አለበታ! አንድን ጎረምሳ ጥርሱን ሊያስቦርሸው የሚችል ምንድነው? ሴት አይደለችም? ግምቴ ልክ ይሆን? ልክ
መሆን አለበት። አለዚያ ምኑን ደራሲ ሆንኩት?

አንገቴን በበሩ ብቅ አድርጌ አየሁ። ጨለም ያለው ረዥም
መተላለፊያ ኮሪዶር ባዶውን ነው፡፡ ኮሪዶሩ መጨረሻ ላይ ያለው
የቡና ማፍያ ክፍል ተዘግቷል። ተካ ገና ቡናውን በመጣድ ላይ ነው
ማለት ነው። ጊዜ አለኝ፡፡ በሩን ዘጋሁ፡፡ ቶሎ ወደ አልጋው ራመድ
አልኩ፡፡ አንሶላውን ላመሉ ገለጥ ከደረግኩት። ጎምበስ ብዬ ትራሱን
አሸተተኩት፡፡ የሴት ጠረን። ያለጥርጥር። እንዴት ያለች ትሆን?
ቶሎ አልጋውን አስተካከልኩና፣ ቁጭ ብዬ ጋዜጣ እያነበብኩ
ቆየሁት ቡና ከጠጣን በኋላ ሊሎቹን ሀበሾች ፍለጋ ወጣን
ተካ «ተመስገንን ግን አታገኘውም» አለኝ «ወደ ፓሪስ
ተዛውሯል። ለምን እንደተዛወረ ታውቃለህ?»
«ለምንድነው?» አልኩት
«ነጭ ሴት ሰለቸኝ አለ።»
«ምን?
«ጥቁር ሴት ካላገኘሁ ልማር አልችልም አለ፡፡ እዚህ ኤክስ
ውስጥ ሁለት ጥቁር ሴት ብቻ ነው ያለው፡ ሁለቱም አስቀያሚ
ናቸው። ስለዚህ ፓሪስ መሄዴ ነው:: ቢሆን እግዜር ብሎ አንዲት
ሀበሻ ልጅ ታጋጥመኝ ይሆናል፡፡ ባይሆን ደሞ ሌላ ጥቁር ሴት
አላጣም፣ ብሎ ሄዴ»
ተመስገን እውነቱን ነው። ኤክስ ውስጥ ጥቁር ሴት አይገኝም
ሀበሻ ሴት ይናፍቃል። ያገራችን ሴቶች ትዝ ይሉናል፤
አነጋገራቸው፣ አሳሳቃቸው፣ መሽኮርመማቸው ይናፍቀናል፡ ጥቁር ቆዳቸው፣ ነጭ ጥርሳቸው እንቅልፍ ይነሳናል፡ በሀሳባችን
አረ ንሺ» ሲሉ ይሰማናል።

አንዳንድ ጊዜ ተሰብስበን ስለነሱ እናወራለን፡፡ ናፍቆት ሲበዛብን
እየሳቅን እየጮህን እንዘፍናለን
«አንቺ ጥቁር ድንጋይ ፍቅር አይገባሽ በሰው አገር ሆኜ ተቃጠልኩልሽ»
ሉልሰገድማ “ልጆችዬ፣ አብረን አንዲት እምስ የተቀረፀባት ሻማ ለቁልቢው እናብራለትና » አለን እምስ በፖስታ ላክልን፣
መጋረጃ እናስገባልሀለን፣ እንበለው፡፡ እውነቴን'ኮ ነው! ያገሩ ልጆች ነን፡ ይሰማናል። ኧረ እናታችሁን! ይሄ ምኑ ያስቃል?»

እኔና ተካ ሀበሾቹን ሉልሰገድ ቤት እገኘናቸው:: ባህራምና
አንድ ሌላ ኢራናዊ አብረዋቸው አሉ፡፡ ይህ ሌላ ኢራናዊ ጀምሺድ
ይባላል። ረዥም መልከ ቀና ወጣት። ጥቁር ሱፍና ነጭ ሸሚዝ
ከቢራቢሮ ክራቫት ጋር ለብሷል። ግብዣ ለመሄድ የተዘጋጀ
ይመስሳል። ረዘም ያላ ፈት፡ ቀጥ ያለ ረዥም አፍንጫ። ከሀር
መሳይ ውብ ቅንድቦቹ በታች ሰማያዊ ትንንሽ አይኖች ሁልጊዜ
ይጨፍራሉ፡፡ ብርሀን ሳቅ፣ ብልጠት የሚፈራረቅባቸው፣ ህይወት የሞላባቸው አይኖች ናቸው፡፡ በኋላ እንደተረዳሁት፣ ጀምስድ ፈረንሳይ አገር ከመጣ አመት አልፎታል። ታድያ ቢበዛ ስምንት መቶ የፈረንሳይኛ ቃላት ቢያውቅ ነው (የቋንቋ ስጦታ የለውም) ግን እነዚህ ስምንት መቶ ቃላት ለንግግር ኮርተው ይበቁታል። ምክንያቱም ቀጭን ኮሚክ ድምፁና ትንንሽ ብልጮ አይኖቹ፣ ያለ ቃላትም ቢሆን የፈለገውን ይገልፁለታል
👍131
#ምንዱባን


#ክፍል_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ፋንቲን ወደ ትውልድ አገርዋ ስትመለስ ከተማው ይህን መስሎ ነው የቆያት፡፡ ማን እንደሆነች ግን ማንም አላስታወሳትም:: ደግነቱ የመሴይ ማንደላይን ፋብሪካ በር ለእርስዋም ተከፍቶ በፈገግታ ተቀበልዋት:: ሴቶች ከሚቀጠሩበት ክፍል ሥራ አግኝታ ሥራ ጀመረች:: ነገር ግን ሥራው
ለእርስዋ ጨርሶ እንግዳ ነበር፡፡ የማታውቀው ዓይነት ሥራ ስለነበር ግራ ተጋባች፡፡ ስለዚህ የሚከፈላት ገንዘብ ዝቅተኛ ሆነ፡: ግን ትንሽም ቢሆን ለእርስዋ በቂ ነበር፡፡ ሠርታ ለመኖር በመቻልዋ ችግርዋ ተቃለለላት፡፡

ፋንቲን ራስዋን ለማስተዳደር በመቻልዋ በጣም ደስ አላት:: ሰውን ሳያስቸግሩ ራስን ችሎ በሁለት እግር ቆሞ ማደር በጣም ደስ ይላል።የጉልበትዋን ዋጋ አገኘች፡፡ በመጀመሪያ ወር ደመወዝዋ መስታወት ገዛች፡፡
ውብ የሆነ ፀጉርዋን፣ ከወተት የነጡ ጥርሶችዋን፣ የልጅነት መልክዋን ጠዋት ማታ ለማየት በመቻልዋ ደስታዋ እጥፍ ሆነ፡፡ የሰው ልጅ ራሱን ከማየት የበለጠ የሚያስደስተው ነገር የለም:: ከልጅዋ ከኮዜት በስተቀር
ብዙ ነገሮችን ረሳች:: የጠዋት ማታ ሕልምዋ ልጅዋ ነበረች:: ወደፊት ምን ሊሆን እንደሚችል በአሳብ በታያት ጊዜ በደስታ ፈነደቀች:: አንዲት ትንሽ ክፍል ተከራይታ ደሞዟል በቅድሚያ በብድር መልክ ወስዳ ክፍሏን አስጌጠቻት።

«ባል አግብቼ ነበር» ብላ ለመናገር ስለማትችል ስለልጅዋ ሰው ፊት እንዳታነሳ ዘወትር ጥንቃቄ አደረገች::ሰዎች ይህን ካወቁ «ጋለሞታ» እያሉ
ስምዋን ሊያጠፉ እንደሚችሉ ታውቃለች::

ቀደም ሲል እንደተመለከተው ልጅዋን ለወሰዱላት ሰዎች ቃል
የገባችበትን ገንዘብ በወር በወር ሳታጓድል ትልካለች:: ስምዋን ከመፈረም በስተቀር መጻፍ ስለማትችል ለልጅዋ ደብዳቤ ስትጽፍ በሰው ነበር የምታጸፈው::

አዘውትራ ደብዳቤ ትጽፍ እንደነበር ተገንዝበናል:: በመሥሪያ ቤትዋ አካባቢ «ፋንቲን ብዙ ደብዳቤ ትጽፋለች፤ የሚጽፍላትና የምትፅፍለት ሰው አለ ማለት ነው» ተብሎ ብዙ ተወራ:: ስለዚህ ተከታታይዋ በዛ፡፡ ከዚህም
በላይ መልክዋ በተለይ ፀጉርዋና ጥርስዋ በጣም ቆንጆ ስለነበር የሚቀነባትም አልጠፉም::

በአማካይ በወር ሁለት ጊዜ ደብዳቤ እንደምትጽፍና ደብዳቤውንም ለተመሳሳይ ሰው እንደምትልክ የሥራ ባልደረቦችዋ ደረሱበት፡፡ ትክክለኛ
አድራሻውንም አወቁ፡፡ ደብዳቤ የሚጽፍላት ሽማግሌ መጠጥ ቤት ሲለፈልፍ አግኝተውት በሞቅታ ሁሉንም ነገራቸው:: ፋንቲን ልጅ እንዳላት ተሰማ::

«አንዳንድ ሴቶች አሉ፤ የትም ሲዘሉ ልጅ የሚቀፈቅፉ፤ የእዚያ
ዓይነት ሰው ናት ማለት ነው» እያሉ አሟት፡፡

ፋንቲን ፋብሪካው ውስጥ ሥራ ከጀመረች ወደ ዓመት ገደማ
ሆኖአታል፡፡ ኣንድ ቀን ጠዋት እርስዋ ትሠራበት የነበረው ክፍል ተቆጣጣሪ አምሳ ፍራንክ በከንቲባው ስም ትሰጣታለች:: «ምንድነው?» ብላ ስትጠይቃት
ከዚያን እለት ጀምሮ ከሥራ የተሰናበተች መሆኑንና ገንዘቡም ለመሣፈሪያ እንዲረዳት ብሎ ከንቲባው በሀዘኔታ የሰጣት መሆኑን ትገልጽላታለች.
ክንፉ እንደተመታ ዶሮ ክው ብላ ቀረች፡፡ ከተማውን ለቅቃ ልትሄድ
አትችልም:: የቤት ኪራይ እዳ አለባት:: አንዳንድ የቤት እቃ በዱቤ ገዝታለች፡፡ ስለዚህ እዳው መከፈል አለበት:: አምሳ ፍራንክ ደግሞ ለዚህ ሁሉ አይበቃም:: ምን እንዳለች ሳታውቅ እንደመጣላት ተናገረች::
ተቆጣጣሪዋ ወደ ቤትዋ እንድትሄድ ምልክት ሰጠቻት፡፡ አፍራና ተከዛ ከሥራዋ ቦታ ወጥታ ወደ ቤትዋ ሄደች። ጥፋትዋ ምን እንደሆነ በሁሉም ዘንድ ታወቀ፡፡ ለሌሎች ሴቶች አርአያ ልትሆን የምትችል ጋለሞታ! በዚህ
ላይ ቅናትም አለ፡፡

መልስ ለመስጠት ኃይል አጣች፡፡ ከንቲባውን እንድታነጋግር ሰዎች
መከርዋት:: ከንቲባው አምሳ ፍራንክ ሰጥቶ አባርሯታል፡፡ ያውም ደግና አዛኝ ሰው ቢሆን ነው እንጂ በገዛ ፋብሪካው ማን ያዝዘዋል:: ያለ ዳረጎት ዝም ብሎ ሊያባርራትም ይችል ነበር፡፡ «ከዚህ በኋላ ምን ማነጋገር ያስፈልጋል። በማለት ወደ ከንቲባው ሳትሄድ ቀረች::

መሴይ ማንደላይን ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቀው ነገር አልነበረም::
ብዙ ጊዜ አዋቂዎች ሥልጣንን ለሚመለከተው ማስተላለፍ እንደ ግዴታ ይቆጥሩታል:: ይህን የመሰለ የሥልጣን ውክልናን መከታ በማድረግ ነበር
ተቆጣጣሪዋ ራስዋን ከሳሽ፣ ዳኛና ፍርድ አስፈጻሚ በማድረግ በፋንቲን ላይ የፈረደችውና ከሥራ ያባረረቻት::

ፋንቲን በነበረችበት አካባቢ በግርድና ለመሥራት ሰዎች ይቀጥራት እንደሆነ ከቤት ቤት እየዞረች ጠየቀች:: ማንም ሊቀጥራት አልፈለገም፡፡

ከተማውንም ለቅቃ ለመውጣት ኣልቻለችም፡፡ የቤት እቃዋን በዱቤ የገዛችው ውራጅ እቃ ከሚሽጡ ባለሱቅ ስለነበር «እዳሽን ሳትከፍዪ ከአገር ብትጠፊ
ለፖሊስ ነግሬ ካለሽበት አሲዝሻለሁ» እያሉ ይዝቱባታል፡፡ የምትኖርበት ቤት ባለቤት ግን «ወጣት ነሽ፤ ከዚህም በላይ ቆንጆ ስለሆንሽ ያለብሽን የቤት
ኪራይ እዳ መክፈል አያቅትሽም» እያሉ ያበረታትዋታል፡፡ አምሳውን ፍራንክ ከፊሉን ቤት ላከራይዋት ስትሰጥ ከፊሉን ለውራጅ እቃ ሻጭ ከፈለች፡፡የእቃው እዳ ብዙ ስለነበር ለጊዜው በጣም የሚያስፈልጓትን እቃዎች
አስቀርታ ቀሪውን ማለት ሦስት አራተኛ የሚሆነውን ለባለቤቱ መለሰች፡፡ የሚቀርባት እዳ ወደ አንድ መቶ ፍራንክ ገደማ ነበር፡፡

ጎረቤትዋ የሆነ ወታደሮች ልብስ ያሳጥቧት ስለነበር ከዚህ የምታገኘው ገቢ ቆሞ ለመሄድ የሚያስችል ስንቅ መግዣ አደረገችው:: ለልጅዋ
የምትልከው የወር ኪራይ ግን መክፈል አቃታት::

ወደ ትውልድ አገርዋ የተመለሰችለት ያሳደረቻት አሮጊት ተቸግሮ መኖር እንዴት እንደሚቻል የሰጠቻት ትምህርት ለአሁን ኑሮዋ የጨለማ መብራት ሆናት:: ትንሽ ዋሽቶና ትንሽ ገቢ አብቃቅቶ መኖር መቻል የችግር ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን አስረድታት ነበር፡፡ የመጀመሪያው ስውር
ሲሆን ሁለተኛው እንደ ጨለማ ድብቅ ነው» ስትል መክራትም ነበር፡፡

ፋንቲን በጨለማ ያለ መብራት መኖር ለመደችው:: የምትቀምሰውን እራት ለመብላት ከጎረቤት መስኮት በሚመጣ የብርሃን ውጋገን እየተጠቀመች
ትጎርሳለች:: እራት ከሌለም ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ጥቅልል ብላ መደፋት ነው::

ትምህርት የለገሰቻት አሮጊት ሩህሩህ ሴት ነበረች:: ስምዋ ማርጋሬት ይባላል፡፡ ድሃ ብትሆንም ለተቸገረ አዛኝ ፣ ቤተክርስቲያንን መሳም
የምታዘወትር ጽኑ አማኝ፣ ምፅዋት መስጠት የሚያስደስታትና ስምዋን ከመፈረም በስተቀር ማንበብና መጻፍ የማትችል ሴት ነበረች::

የሚገርመው፤ ብዙውን ጊዜ እንዲህ ያለው ደግነት፧ እንዲህ ያለው እምነት የኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ ከሆነ ሰዎች ዘንድ አይጠፋም:: ኣንዴ ሲከፋቸው፣ አንዴም ደስ ሲላቸው ይኖራሉ:: በነገ በጣም ያምናሉ::በመጀመሪያ ፋንቲን በጣም አፍራ ለጥቂት ቀናት ከክፍልዋ ሳትወጣ ከቤትዋ
ውስጥ ቁጭ አለች:: ከቤት ከወጣች ሰዎች ኋላ ኋላዋ እየተከተሉ ጣት በመቀሰር የሚጠነቁሉባት መሰላት:: እውነትም ከቤት በወጣች ቁጥር ሰው ሁሉ ያያታል፤ ሰላምታ ግን አይሰጥዋትም:: መንገደኛ ሁሉ ደግሞ በክፉ ዓይን ሲያያት መጥፎ ስሜት አሳደረባት:: ይህም ስሜት እንደ ጥቅምት
👍18